ከአህያ ጋር ብጣሪ በልታ ከፈረስ ጋር ገብስ ትበላለች
“ከአድባይነት እርግማን ይሰውረን!”
ታክሎ ተሾመ
የኃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ እንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል። አንድ ነጋዴ ሩቅ ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል። ከቤቱ ከተረፈው ረመጥ – መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል። “ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት” አለ። በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ አለቀሰ። ደረቱን መታ። ፀጉሩንም ነጨ። ገላውን እንደገና የማቃጠል፤ የሐዘን ሥነ-ስርዓት እንዲካሄድም አደረገ።