ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሚያዚያ 30, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
የዕለቱ ዜና
ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡ … የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዚህ ሣምንት እያወጣቸው ባሉ ተከታታይ የፕሬስ መግለጫዎች በዓለም ዙሪያ […]![]()
US State Dpt urges Ethiopia and Vietnam to release detained journalists 02-29-15
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ ለተቃውሞ የወጡ ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበው እንዲታሰሩ በተደረገ ማግስት፣ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በምሽት በማፈን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች …
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ ባሃድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በጊምቢቾ ከተማ የፊዚክስ መምህር የነበረው ጌታቸው አብራሃም ፣ በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል። የመድረክ አባል የነበረው መምህር ጌታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። የተቃዋሚ አባል በመሆኑ ብቻ የ3 ወር ደሞዙን እንዳያገኝ የተከለከለው መምህር፣ አቤቱታውን …
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢችል ቀሬ እና ብርሃኑ ታየ የተባሉ ወጣቶች መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። ወጣቶቹ በምን ምክንያት ታፍነው እንደተወሰዱም ሆነ ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ለወጣቶቹ መሰደድ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ አልጄዚራ በድረ-ገጹ ባወጣው ፅሁፍ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለኢትዮጵያውያኑ መሰደድ በዋነኛነት የሚነሱ ምክንያቶችን ዘርዝሯል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገሮች መካከልም ስሟ የሚጠራ ቢሆንም ዜጎቿ ግን መሰደድን አላቆሙም በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ በሚመርጡት ህገወጥ ስደት ብዙዎች እየሞቱ ይገኛሉ በከተሞች አካባቢ አጥጋቢ የስራ እድል አለመኖሩ, በአብዛኛው የሚሰሩ ስራዎች የዜጎችን […]![]()
የመታሰራችንዜና ከተሰማ ጀምሮ ብቻችንን አልታሰርንም፡፡ ብዙዎች አኛን ከከለለን አጥር ውጪ አብራችሁን ታስራችኋል፡፡ ስለዚህ የእስርቤት ጌጥ የሆኑት የመረሳትና ተስፋ የማጣት ስጋቶች እንዳይጎበኙን ያደረገንና በብርታት ያቆመን የእናንተው በእሳት የተፈተነ አብሮነት ነውና ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኋል፡፡#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw
የአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወቁ፡፡ እስማኤል፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ቤቱ በመምጣት ‹‹ቃል ሰጥተህ ትመለሰላህ›› በማለት ከቤቱ ወደ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በኋላ ‹‹ቃሉን ሰጥቶም ቢሆን መለቀቅም እንደማይችል አስታውቀውት ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ […]![]()
የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን […]![]()
ጋሻው መርሻ . ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ […]![]()
በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት […]![]()
‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው …![]()
አብዛኞቻችን ፈሳሽ ነገሮች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ሻይ እና የመሳሰሉትን መጠጣት ለሰዉነታችን የሚያስፈልገዉን ዉሃ እንደሚተካ እናስባለን፡፡ እዉነታው ግን እነዚህ ፈሳሾች ስኳር እና ጨው በውስጣቸው ስለሚይዙ በሰውነታችን ተመጠው በዉሃ እርዳታ ከእንሽርሽሪት ይወገዳሉ፡፡ በየቀኑ 8 ያህል ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው የአፍና ጉሮሮ ድርቀት እንዳይከሰት ከማድረጋቸው በላይ የተለያዩ በሽታዎችና ህመሞችን…
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት …
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ …
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማምረቻ ወይንም በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ መንግስት በያዘው የአምስት ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት መከናወን ካለባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሚንቶ በስተቀር አለመሳካቱን አንድ ሰነድ አመልክቷል፡፡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ እንዳመለከተው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የአምስት ኣመት እድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀቶችና ከነባር ፋብሪካዎች …
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ …
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ …
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

Minilik Salsawi የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው ስንታየሁ ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዶዋል።
ስንታየሁ ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ ትግል እራሱን ሰጥቶ ይታገል የነበረ ጠንካራና ለትግሉም በምንም የማይደለል ታማኝ ወጣት ታጋይ ነው።

Rest in Peace brothers
ባለሥልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት የታሠሩ አባላቶቻቸዉን ለማስለቀቅና በፓርቲዉ ላይ ተከፈተ ያሉትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስወገድ ፓርቲዉ በፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል።
ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሙሉ ክፍያ ፈጽመዋል
የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅፈር ይፋ ከተደረጉት አራት ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው 40/60 ከተመዘገቡ 165 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሰባት ሺሕ ያህሉ ውላቸውን ሲያቋርጡ፣ 8,329 ተመዝጋቢዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ክፍያ ፈጽመው ቤታቸውን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው…
“እያንዳንዳችን ወደልቦናችን መመለስ አለብን“ የክርስትና ተወካይ
“ቀዳዳውን አብረን እንድፈን“ የእስልምና ተወካይ
“በሰሃራ በረሃ አካላታቸው ለተበለተ ወገኖቻችን ዝም ማለት የለብንም“ የኤርትራ ተወካይ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 27, 2015)፡- ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት (16፡00) ጀምሮ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከ2000 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሰርገልስ አደባባይ በመሰብሰብ በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመባቸውን ወገኖቻቸውን በማሰብ ኀዘናቸውን እና ተቃውሟቸውን በጋራ ገለጡ።
አጥናፍ ብርሃኔ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ
– ሳጅን ምንላድርግልህ
-ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም )
– ኢንስፔክተር አሰፋ
– ም/ሳጅን መኮንን
– ኢንስፔክተር ገብሩ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 17 እስከ ሃምሌ 11 /2006 አም
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ በተለይ ቢሮ ቁጥር 5.፣ 32
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– ታደሰ የተባለው መርማሪ ፓሊስ ያለምንም ምክንያት ምርመራ ክፍል ውስጥ እያነቀኝ በተደጋጋሚ “እውነቱን የማትናገር ከሆነ ሽባ ነው የምናደርግህ ፣ እኛ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም” በማለት በጥፊ ሲደበድበኝ ነበር
– ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለ መርማሪ “ጦማር ምን ማለት አንደሆነ ተናገር” ሲለኝ ጦማር ማለት መጻፍ ነው ብለውም ፡።፡።”ምህጻረ ቃል ነው እያንዳንዷ ምጻረ ቃል ምን ማለት አንደሆነች ካልተናገርክ አንላቀቅም” በማለት ከግርግዳ ጋር እያጋጨ ደብድቦኛል፣ ከግርግዳ ማጋጨት ብቻም ሳይሆን ረጅም ሰአት ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል አንቅስቃሴ እየሰራሁ የተመረመርኩ ሲሆን ምራቁን እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ ሲሰድበኝ ነበር፡፡
– ግንቦት ወር ላይ ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለው መርማሪ “ ኢህአዴግን ለምንድነው ተችታችሁ የምትጽፉት ?” “ከአገር ውጪ የምትሄዱት የመንግሰትን ስም ለማጥፋት ነው አንጂ የአባይ ግድብ ቦንድ ለመግዛት አይደለም” በማለት እጄን ወደላይ አድርጌ አንድመረመር አንዲሁም ጆሮዬን እየጎተተ በጥፌ ሲደበድበኝ ውሏል፡፡ ከዚህ ቤት ደንቁረህ ነው የምትወጣው በማለትም ያስፈራራኝ ነበር፡፡ እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ እየተሰደብኩ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል፡፡
– በሰኔ ወር ኢንስፔክተር አሰፋ የሚባለው መርማሪ ሌሊት 6 ሰአት አካባቢ ጠርቶኝ አላማችሁን ካልተናገርክ ጭለማ ቤት ነው የምትገባው በማለት ከማስፈራራቱም በላይ ሌሎች እስረኞች ሲደበደቡ እና ሲጮሁ ሲያለቅሱ በማሰማት እነደነሱ አንዳትሆን በማለት ዛቻ ተፈጽሞብኛል።
– ሰኔ ወር ላይ ኢንስፔክተር ገብሩ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ በመግባት ወረቀት ጽፈሃል የሚል በውል በማላውቀው ምክንያት ከሌሎች እስረኞች ለይቶ በተኛሁበት በተደጋጋሚ ከባድ የእርግጫ ደብደባ ፈጽሞብኛል። ሲደበድበኝም ህዝብ ልታጫርስ ነው እያለ ነበር፣ አስካሁንም የዛን ቀኑን ድብደባ ምክንያት ነው ያሉትን ነገር አላውቀውም፡፡
– በማእከላዊ ቆይታዬ 4በ4 በሆነች ክፍል ውስጥ በቀን ሁለቴ ብቻ ለ15 ደቂቃ ወደውጪ በመውጣት ከአስር ሰው ጋር ተቆልፎብኝ ታሬያለሁ ፡፡ የመጸዳዳት እድልም ቀኑን ሙሉ አልነበረኝም ፡፡ በየቀኑ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ መስራት የምርመራው አካል ነበር፡፡
– በሃምሌ ወር ከምሽቱ 2.30 አካባቢ ሳጅን ምንላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን መኮንን እና ሌላ የማላውቀው መርማሪ በመሆን ጭንቅላቴን በሃይል ከግንብ ጋር በማጋጨት እና የኮምፒውተር ኬብል በማሳየት አንደምገረፍ በመንገር ሳጅን ምንላድርግልህ የተባለው መርማሪ ፓሊስ የጻፈው የእምነት ቃል ላይ በግዳጅ አንድፈርም ተገድጃለሁ፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
አቢይ አፈወርቅ
በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ያስቆጣቸው የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን እሁድ ኤፕሪል 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ የሻማ ማብራት ስርአት አካሂደዋል። በዚህ በኒው ሳውዝ ዌልስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አስተናባሪነት በተዘጋጀው ሥነሥርዓት ላይ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር።
በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው […]
ኤዶም ካሳዬ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ደስታ በዋናነት
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – በተያዝኩባቸው ቀናት በሙሉ በተለይ ሚያዝያ 18 ,20, 21, 22, 23
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ቢሮ ላይ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
-መርማሪዬ ደስታ በተደጋጋሚ በጥፊ ይመታኝ ነበረ ሲሆነ ከዚህ ቤት የፈለግነውን ልናደርግሽ እንችላለን በአካል አትወጪም እያለ አስፈራርቶኛል
-የዞን 9 አባል አይደለሁም በማለቴ ፌቴን አዙሬ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ የሰራሁ ሲሆን በተጨማሪም አላማቸውን ተናገሪ ሲለኝ የተለየ አላማ እንዳላቸው አላውቅም በማለቴ ሳታውቂ አንዴት አብረሻቸው ትውያለሽ ሸርሙጣ ብሎ በተደጋጋሚ ሰድቦኛል፡። ሌሎቹ መርማሪዎች አብረው ተቀምጠው በስድቦቹ ይስቁ ነበር
-ሌላኛው ተከሳሽ አጥናፍ መደብደቡን ፍርድ ቤት በመናገሩ አንቺ ትሞክሪውና ዋጋሽን ታገኛለሽ እኛ ፍርድ ቤት አያዘንም የግለሰብ መብትም አያሳስበንም ብሎኛል
-ጥጋቡ የሚባለው መርማሪ ምርመራ መሃል ደንገት በሩን ከፍቶ ገብቶ በጥፊ መቶኝ ይወጣ ነበር ( ስለምናወራው ጉዳይም ሆነ ስለምርመራው ሳይሰማ) እምቢ ካለችህ ልብሷን አስወለወቀህ ግረፋት ብሎ እኔን የተለመደውን ስድብ ሰድቦኝ ሄዷል
-በምርመራ ወቅት የዞን አባል ነኝ ብለሽ እመኚ ተብዬ ልብሴን አውልቄ ሙሉ እርቃኔን አንድመረመር ተገድጃለሁ ፡። በጥፊ እመታ የነበረ ሲሆን በዚህ ቀን ምርመራው ምሽት ላይ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰአት ቆይቷል
-በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር ፡፡ በጥፊው ተደጋጋሚነት የተነሳ ታምሜ ክሊኒክ ተመላልሻለሁ::
-በጋዜጠኝነት ሞያየ የተሳተፍኩበትን ስልጠናዎች ስናገር አንቺ ለምን ተመረጥሽ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ለምን አይሄዱም አንቺ ለፈረንጅ ስለምትሰልዬ ነው ብሎኛል፡፡ በተጨማሪም ዞን9 ላይ የሚወጡት ጽሁፎች አንድ ገጠር ያለ ሰው ቢያነበው ለአመጽ የሚያነሳሳው ልማቱን የሚያጣጥል ነው ብሎ በተደጋጋሚ በጥፊና በካልቾ ተመትቻለሁ፡፡
-በተጨማሪም በተፈቺ እስረኛ ወደውጪ መልእክት ልከሻል በሚል ሰበብ ሌሊት ተጠርጬ በዱላ ሲዛትብኝ አርፍዷል
-በእስሩ ወቅት ከማህሌት ፋንታሁን ጋር ለብቻችን ከሰው አንዳንገናኝ ተደርገን ቆይተናል፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
ላለፉት አራት ዓመታት ለንባብ ሲበቃ የቆየው የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት ደህንነቶች ቢሮው ድረስ በመሄድ ዛቻና ማስፈራራት ስላደረሱበትና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ መገደዱን እንደነገራቸው ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ የደህንነት ኃይሎች በየጊዜው ወደ ቢሮው እየሄዱ “ክስና እስር ይጠብቅሃል” እያሉ ያስፈራሩት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሬሱን የሚወነጅል […]![]()
በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡ የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት […]![]()
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው # ስንታየሁ_ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታቀቀ ቦታ ተወስዶዋል። ስንታየሁ_ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል […]![]()
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) መርማሪ የህይስ መርማሪ ጽጌ መርማሪ ታደሰ ( ስሙን እርግጠኛ ያልሆንኩት)
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት ማእከላዊ ምርመራ በቆየሁበት ጊዜ ሁሉ
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
-በውል በማላስታውሳቸው ቀናት እስከእኩለ ሌሊት ድረስ የቆየ ምርመራ ተደርጎብኛል
-ለ75 ቀናት በተለምዶው ሳይቤሪያ የሚባለው ቦታ በቀን 15 ደቂቃ ብቻ የጸሃይ ብርሃን ለማየት ተፈቅዶልኝ ከዚያ ውጪ ያለውን ጊዜ 24 ሰአት አንድ በር ተዘግቶብኝ ቆይቻለሁ፡፡
-አራት በአራት በሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ ቁጥራቸው አስር ከሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ጤናዬን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ
-በእስር በቆየሁባቸው ቀናት በቀዝቃዛው ሳይቤርያ ውስጥ በማሳለፌ በከፍተኛ ቅዝቃዜው የተነሳ ለጤና ጉዳት እና ለበሽታ ተዳርጌያለሁ
-ከፍተኛ እና ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ያደረኩ ሲሆን በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ እመታ ነበር
-በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት ደረሰብኝ ሲሆን በስተመጨረሻም ያላልኩትን አለ ተብዬ ፣ የማላምንበት እና ያልፈጸምኩትን ጥፋተኛ ነኝ ብለህ ፈርም በመባሌ ለመፈረም ተገድጃለሁ
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ ሳጅን ምን ላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን አብተው
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 22 ( ከምሽቱ 2 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 23 ከጠዋቱ 4 ሰአት፣ ግንቦት 6( ከምሽቱ 3 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 24 ከጠዋቱ 4 ሰአት እና ከሚያዝያ 22 እስከ ግንቦት 6/2006 ድረስ ባሉት ቀናት ከእሁድ በስተቀር
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 30፣ 32 በ1981 አም በተሰራው ህንጻ ላይ 2ተኛ ፎቅ በስተግራ ጥግ በኩል ያለ ቢሮ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– በምርመራ ወቅት ዛቻ እና ማስፈራሪያ የደረሰብኝ ሲሆን በተጠራሁባቸው ቢሮ ውስጥ ሁሉ በጥፌ ተደብድቤያለሁ ፡፡ በጥፌ መመታት የተለመደ ነበር ፡። በተደጋጋሚ ክፍተኛ ስፓርት የሰራሁ ሲሆን በቀን 10 ደቂቃ ብቻ የፀሃይ ብርሃን እያየሁ በጠባብ ክፍል ውስጥ ያለምንም ተፈጥሮ ብርሃንና መጸዳጃ ለ 76 ቀናት ቆይቻለሁ፡፡
– ጫማዬን አውልቄ በባዶ እግሬ አንድቆም ከተደረኩ በኋላ እግሮቼ ጣቶች ላይ መርማሪዎቹ በጫማቸው በሃይል በመርገጥ እግሬ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰውብኛል፡፡ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስም እጄ እንደታሰረ አናቴ ላይ አድርጌ እንድመረመር ተገድጄ ነበር፡፡
– የምሽት ምርመራዎች ወቅት በአብዛኛው ጊዜ እጄን ወደላይ አድርጌ እንድመረመር እገደድ ነበር ፡። ምርመራው ቀኑን ሙሉ የሚቆይ ሲሆን ምሽት እስከ ሌሊቱ ስድስተ ሰአት ድረስ ስፓርት በመስራት እና ፌቴን በማዞር እንድመረመር እገደድ ነበር፡፡
– ሰብአዊነቴን የሚነኩ ስድቦች ልክስክስ ፣ ውሻ መሳሰሉትን ስድብ በምርመራ ወቅት እሰደብ የነበረ ሲሆን አካለ ጎዶሎ ሆነህ ነው ከዚህ ቤት የምትወጣው ፣ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም አንተን አንደፈለግን እነድናደርግ አሰራራችን ይፈቅድልናል የሚሉ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያዎች ነበሩብኝ ፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
“የታረዱትንና በጥይት የተደበደቡት ኢትዮጵያዊያን ሰማእታት ናቸው ‘ነፍስ ይማር’ ወይንም RIP ሊባልለት የሚገባው በቁሙ ለሞተው አይሲስ ነው።” ዲያቆን መምህር አድማሱ ዘባን
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 25, 2015)፦ ራሱን የእስላም መንግስት በማለት የሚጠራው እና ዘግናኝ ግድያዎችን በንጹሃን ዜጎች ላይ በመፈጸም ላይ በሚገኘው ቡድን እጅ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያኖችና በሳውዝ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖች ላይ የሚፍጸመውን ሰብአዊነት የጎደለው አስከፊ ድርጊት በመቃዎም በቫንኩቨር (ካናዳ) ታላቅ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄደ።
በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት ተቃወሙ
ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 24, 2015) የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሕብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።
* ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በህክምና ስህተት ለ9 ዓመታት ለከፋ አደጋ መዳረጉ ተረጋግጧል ! * የሳውዲ ጤና ጥበቃ ልዩ አጣሪ ኮሚቴ የሰጠው ውሳኔ ግን አሳዝኖናል * የብላቴናው ቀሪ ህይዎቱም ውስብስብ ሆኗል * አሰልችውን የዘጠኝ አመታት ፍትህ ፍለጋ ግን አልሰመረም * ” ከሬሳ የማይተናነስ በድን አድርገው አኮላሽተው ውስጅ ይሉኛል ፣ እንዴት ይህን ውሳኔ ልቀበል ? ፍትህ እሻለሁ! እርዱኝ! […]![]()