ሥልጣን የማይጠግቡ አየፍሪቃ መሪዎች
አንዳንድ የአፍሪቃ መሪዎች ከ20 እና 30 ዓመታት በላይ በሥልጣን መቆየታቸው አልበቃ ብሏቸው የየሀገራቸውን ሕገ-መንግሥት ለመቀየር ሲጥሩ፤ በዚህ ሰበብም ገሚሱ ዳግም ላይነሳ ተንኮታክቶ ሲወድቅ ታይቷል።
አንዳንድ የአፍሪቃ መሪዎች ከ20 እና 30 ዓመታት በላይ በሥልጣን መቆየታቸው አልበቃ ብሏቸው የየሀገራቸውን ሕገ-መንግሥት ለመቀየር ሲጥሩ፤ በዚህ ሰበብም ገሚሱ ዳግም ላይነሳ ተንኮታክቶ ሲወድቅ ታይቷል።
በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩት አቶ ተማም አባቡልጉ አባዲኮን ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ በሚል ለ፩ አመት ከሰባት ወር የጥብቅና ፍቃዳቸውን ታግዳል። አቶ ተማም አባቡልጉ በግፍ ለታሰሩት ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጥብቅና በመቆም የወያኔን መሰሪ አሰራር ለአለም በማጋለጥ የሚታወቁ ሲሆን የካንጋሮ ፍርድ ቤት ፍርደ ገምድልነት ቁልጭ ብሎ እንዲታይ ያደረጉ የሀገር አብት ጠበቃ ናቸው። ይህ ያልተመቸው […]![]()
በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ውስጥ የከረረ ተቃውሞ በፖሊስ አባላቱ በመነሳቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መታሰራቸው ተሰማ፡፡ ቅዳሜ ዕለት ሰኔ 27 2007 ዓ.ም ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የከረረ ተቃውሞ የተነሳ ሲሆን ተቃውሞውን ተከትሎ የበርካታ ፖሊስ አባላት እስር እና ከአካባቢው መሰወር ተከስቷል፡፡ በስብሰባው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያትና ሰበብ የፖሊስ ፅ/ቤቱ ዋና […]![]()
በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በይግባኝ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ በማረሚያ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትናንት የአመክሮ ጊዜዋ ተጠናቆ ከእስር ተለቀቀች። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ግለሰቧ በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሶስት የሽብ በይግባኝ ባደረገችው ክርክር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኝነት ሙዋየዋን በመጠቀም የሽብር ቡድንን ደግፋለች በሚል ወንጀል ብቻ ጥፋተኛ ናት በማለት የ14 ዓመቱን […]![]()
የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ተጠናቆ ሙሉ ውጤቱ ይፋ ከሆነ እነሆ ሳምንታት አለፉ። የምርጫው ሂደት ያስነሳው የፖለቲካ ትኩሳትና አቧራ በርዶ ፤ የምርጫው ተዋናዮች ግርግርና አስረሽ ምቺው ሰክኖ ምርጫ 2010 ከሰበር ዜናነት ወደ ታሪክ ማህደርነት የሚተላለፍበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የዚህን ምርጫ ታሪካዊ አንድምታና በታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚኖረው ስፍራ በታሪክና ሶሻል ሳይንስ ተመራማሪዎች ወደፊት የሚለካ ሲሆን ይህ ጽሁፍ የዚህን ምርጫ ሁለት ለየት ያሉ ባህርያት ላይ ትኩረት በመስጠት ለመቃኝትና ለመዳሰስ ይሞክራል። በመጀመሪያ ይህን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ የሚያደርገው ለምርጫ የወጣው ህዝብ ብዛት (turn out) ሲሆን ከተመዘገበው 36.8 ሚሊየን ህዝብ 34.8 ሚሊየን ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በምርጫው ተሳትፏል። በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁ ቀጥተኛና ነጻ የሆነ ህዝባዊ ተሳትፎ የታየበት የፖለቲካ ክስተት ያደርገዋል። ይህን መሰል ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የታየበት ምርጫ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በብዙ አገሮች ከሚታዩት የህዝብ የምርጫ ተሳትፎዎች ጋር ሲንጻጸር ከፍተኛ አሃዝ ከተመዘገበባቸው አንዱ የሚያደርገው ሲሆን ይህም የምርጫውን የዲምክራሲያዊ መሰረት ያሰፋ፤ ፉክክራዊ ባህርይውን ያጎለበትና ለተአማኒነቱንም ዋስትና እንዲኖረው ካደረጉት ምክንያቶች እንደ አንዱ ሆኖ ሊጠቅስ የሚያስችል ነው። ከሁሉ በላይ ግን ለምርጫ ከወጣው የህዝብ ቁጥር አሃዝ ጀርባ ያለው ዋናው ቁምነገርና ይህንን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በይዘት የተለየ የሚያደርገው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት መብቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋትና በጥልቀት እየተረዳ መምጣቱ የተንጸባረቀበት፤ ለዲሞክራሲ ስርአት ያለው ፍላጎትና ቁርጠኝነት እየሰፋና እየጎለበት መምጣቱን በግብር ያረጋገጠበት ምርጫ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫን የማይገሰስና የማይቀለበስ ቋሚ ባህሉ […]
(አዲስ ከድሬዳዋ) መንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግና በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ኢንቨስትመንቶችን በማስተናገድ ኢኮኖሚው እያደገ ነው፡፡ ዋነኛው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የስራ እድል ፈጣሪ መንግስት በሆነበት ሁኔታ በመንግስት ሜጋ እና ትናንሽ ፕሮጄክቶች አማካኝነት ወደገበያው እየተለቀቀ ያለው ገንዘብና ከገበያው የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን ልዩነቱ ሰፊ በመሆኑ የግሽበት ተጋላጭነታችን ከፍተኛ ነው፡፡ ባንድ ወቅት ከ40 ፐርሰንት በላይ ደርሶ የነበረው የሀገራችን የዋጋ ግሽበት አሁን ወደ ባለአንድ አሀዝ ግሽበት(ከ10 ፐርሰንት በታች) መውረዱ እንደትልቅ ስኬት እየተነገረ ነው፡፡ ለመሆኑ ቀድሞ ነገር ኢንፍሌሽኑ እንዴት ጀመረ፣ አሁንስ እንዴት ሊቀንስ ቻለ ኢንፍሌሽኑ የጀመረው በተደጋጋሚ እንደሚነገረው መንግስት በሚያስተገብራቸው በርካታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደገበያው እየለቀቀ ስለሆነ ነው፡፡ በኢኮኖሚስቶች የሚመከረውና መንግስት ኢንፍሌሽኑን ለማረጋጋት መውሰድ ያለበት እርምጃ በዋናነት ወደገበያው እየለቀቀው ያለውን ገንዘብ መቀነስ ነው፡፡ መንግስት ግን ይህ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን ያቀዘቅዝብኛል በሚል ተመራጭ እርምጃ አድርጎ አልወሰደውም፡፡ አንድ አመት በከፊል ሞክሮት የነበረ ቢሆንም ቀጣይነት ግን አልነበረውም፡፡ መንግስት ይልቁንም በገበያው ላይ ያሉ ተጫዋቾች ላይ ቁጥጥሩን በማጥበቅ፣ ቁጠባን በማበረታታትና የግብር መሰብሰብ አቅሙን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ነው ችግሩን ለመፍታት የሞከረው፡፡ በእርግኑን ይህንን አማራጭ በመከተሉ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ሳይቀዛቀዝ ኢንፍሌሽኑን በእጅጉ መቀነስ ችሏል፡፡ ሆኖም ለዚህ የተወሰኑ ዜጎች ያለአግባብ ዋጋ እንዲከፍሉም ተደርጓል፡፡ ሁለቱን ልጥቀስ የመንግስት ሰራተኞች፡- በ1994 ዓ.ም. የነበረው 400 ብር የመግዛት አቅም በ2004 ከነበረው 1000 ብር ጋር ተመጣጣኝ በሆነበት ሁኔታ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በእነኚህ አስር አመታት 250 ፐርሰንት ሊያድግ ይገባ ነበር፤ […]
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ የጦር አዛዦች በተገኙበት የወታደራዊ ጥቅል አቋማቸውን አቅርበዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ፣ ጄ/ል ሳሞራ ” ጦራችን ከጊዜው ጋር እየዘመነ አይደለም፣ የታንኮቻችን አቅም ያረጀ ነው፣ ተዋጊ አውሮፕላኖቻችን ከገበያ የወጡ ናቸው፣ መቀየሪያ እቃዎቻቸው ( ስፔር …
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞችም እየታፈሱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ የተቃዋሚ ሃይሎች ሰርገው ሳይገቡ ገብተዋል የሚል መረጃ ለደህንነት ክፍሉ እንደደረሰ የኢሳት ምንጮች ገልጸው፣ አሁኑ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል ሲሉ ግምታቸውን …
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም በ2007 ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም ከሀገር ከመኮብለላቸው በፊት ቀደም ብለው ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ወደ አሜሪካ …
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሽን ጨምሮ 10 ተከሳሾች ሐምሌ 1/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ብይኑን ሳይሰጥ ቀርቷል። ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ …
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ የዋጋ መረጃው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም የሸቀጦች ዋጋ ካለፈው ጋር ሲነጻጸር መጨመሩን ይፋ አደረገ፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሰረት በግንቦት ወር 9 ነጥብ 4 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የዋጋ ግሽበትን …
‹‹ሁላችንም በአንድ ነገር ላይ ዕምነት ነበረን – ከዚህ በኋላ ያለው የእስራቸው ጊዜ ጊዜ አጭር ሊሆን እንደሚችል፡፡ ማን ያውቃል …›› ሰኔ 05 ቀን 2005 ዓ.ም (ከ25 ቀናት በፊት) እነተስፍሽን በቂሊንጦ በጠየኳቸው ቀን ይህንን አውግተን ነበር፡፡ ዛሬ እውነት ሆነ! ደስስስስ! ——————-የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ሃይለጊዮርጊስ ከእስር ተፈቱ። ‹‹…ተስፍሽ፣ በፍቄና አጥናፍ መጡ፡፡ […]![]()
በኢትዮጵያ ከ1ዓመት በላይ ታስረው ከቆዩ ጋዜጠኞችና የዞን ዘጠኝ ጦማር ጸሀፊዎች መካከል፤ ሶስቱ መፈታታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከምንጮቹ አረጋግጧል፤ የፋና ሬድዮ የተፈቱት ጋዜጠኞችና የጦማር ጸሃፊዎች 5 ናቸው ሲል ዘግቧል። በሽብር ወንጀል ተከሰው ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በእስር ያሳለፉት ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስና …
በኢትዮጵያ ታስረው ከቆዩ የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ሶስቱ ዛሬ ተፈቱ – VOA Read more »
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ዝርዝር ዘገባው እየተጠናቀረ ነው፤ እንደተጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃ እናወጣለን፡፡
በኤርትራ መንግሥት ተንኳሽነት ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስጠነቀቁ።
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ የተካተቱ ተከሳሾች ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዛሬ ተከሳሾች በነጻ ይሰናበቱ ወይስ ይከላከሉ በሚለው ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበር ቢሆንም ብይኑ ሳይሰጥ ተቀጥሯል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና […]![]()

–ለካፒታል ፕሮጀክቶች 65 በመቶ ተመደበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ2008 ዓ.ም. 31.8 ቢሊዮን ብር በጀት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡ ይህ በጀት ከ2007 ዓ.ም. በጀት ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ከተያዘው በጀት 65 በመቶ ለካፒታል ፕሮጀክቶች፣ 35 በመቶ ለመደበኛ ወጪዎች ተመድቧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካፀደቀው በጀት ውስጥ በማዕከል ደረጃ ለሚካሄዱ የካፒታል ፕሮጀክቶች 16.9 ቢሊዮን ብር፣ ለመደበኛ ወጪዎች 5.2 ቢሊዮን ብር፣ ለመጠባበቂያ 1.99 ቢሊዮን ብር መድቧል፡፡ በክፍላተ ከተሞች ለሚካሄዱ የካፒታል ፕሮጀክቶች 2.2 ቢሊዮን ብር፣ ለመደበኛ ወጪዎች 5.5 ቢሊዮን ብር ተመድቧል፡፡
ይህ ትልቅ በጀት የሚሸፈነው ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ነው፡፡ ከአገር ውስጥ ታክስ ገቢ 22.97 ቢሊዮን ብር፣ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 2.9 ቢሊዮን ብር፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች 2.98 ቢሊዮን ብር፣ ከመንገድ ፈንድ 50.4 ሚሊዮን ብር ለማግኘት መታቀዱን የበጀቱ ረቂቅ ያመለክታል፡፡ በፌዴራል መንግሥት አማካይነት ከውጭ አገሮች በተለይ በብድር መልክ 2.6 ቢሊዮን ብር፣ ከዕርዳታ ደግሞ 238 ሚሊዮን ብር ይገኛል ተብሎ ታቅዷል፡፡ በወጪ ደረጃም 12.7 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ የተመደበ ሲሆን፣ 19.09 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ ተበጅቷል፡፡ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የቀረበው በጀት አዋጅ እንደሚያስረዳው፣ ከተያዘው በጀት ትልቁ ተጠቃሚ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንና የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ናቸው፡፡
መንገዶች ባለሥልጣን 156.9 ሚሊዮን ብር ለመደበኛ የተያዘለት ሲሆን፣ 5.9 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ተመድቦለታል፡፡ ለውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 1.2 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት ሲያዝለት፣ 4.4 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ተመድቦለታል፡፡
የከተማው ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት (2007 ዓ.ም.) 27.9 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ በተጠናቀቀው በዚህ በጀት ዓመት በማዕከል ደረጃ ለሚገነቡ የካፒታል ፕሮጀክቶች 16.6 ቢሊዮን ብር፣ ለመደበኛ ወጪዎች 4.1 ቢሊዮን ብር፣ ለመጠባበቂያ ደግሞ 1.4 ቢሊዮን ብር መመደቡ ይታወሳል፡፡ በክፍላተ ከተሞች ለሚካሄዱ የካፒታል ፕሮጀክቶች 1.6 ቢሊዮን ብር፣ ለመደበኛ ወጪዎች 4 ቢሊዮን ብር መመደቡ አይዘነጋም፡፡
ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት የ2007 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባለፉት 11 ወራት 25.674 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የተሰበሰበው 19.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም የዕቅዱን 75 በመቶ ብቻ ያሳካ ነው፡፡
ከዚህ በጀትም ለመደበኛና ለካፒታል ወጪዎች 15.6 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አምስት ቢሊዮን ብር (32.11 በመቶ) ለመደበኛ፣ 10.6 ቢሊዮን ብር (68 በመቶ) ለካፒታል ወጪዎች ማስፈጸሚያ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
‹‹በአጠቃላይ የገቢ አፈጻጸማችን ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዕድገት ያሳየ ቢሆንም፣ ከዕቅዳችን አኳያ ሲታይ ዝቅተኛ ነው፡፡ በቀጣይነት የገቢ መሠረቱን የማስፋት፣ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን የማጠናከርና ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ መሰብሰብ የሁሉንም አካላት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፤›› በማለት የከንቲባ ድሪባ ሪፖርት በቀጣዩ ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ማሳየት አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥቷል፡፡

በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅና በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን እንዲያፀድቅ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማሻሻያዎቹን ቢቀበላቸውም፣ ተፈጻሚ
የሚሆኑበት ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ከመፈረማቸውና በነጋሪት ጋዜጣ ከመታወጃቸው በፊት ሊሆን አይገባም የሚል ክርክር ተነሳ፡፡
ምክር ቤቱ ሰኔ 29 ቀን ባደረገው ጉባዔ ካፀደቋቸው ረቂቅ አዋጆች መካከል፣ የመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅና የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎች ይገኙበታል፡፡ ከሁለቱ አዋጆች መካከል የግል ድርጅቶች ጡረታ አዋጅ ማሻሻያ ቀደም ሲል አማራጭ አድርጎ ያቀረበውን የፕሮቪደንት ፈንድ ሥርዓት የሚያነሳ አንቀጽ በማካተቱ፣ በርካታ ድርጅቶች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ውጪ ይህ አዋጅ በመንግሥት ድርጅቶች የተጠራቀሙ በፕሮቪደንት ፈንድ የሚተዳደር ገንዘብ ወደ ግል ጡረታ እንዲዘዋወር የሚል አንቀጽ በማስገባቱ፣ ከፍተኛ ሥጋትን በግል ሠራተኞች ላይ ፈጥሮ ነበር፡፡
ይህንን ሥጋት የቀረፈ ማሻሻያ ፓርላማው አንቀጹን በመሠረዝ ያደረገ ቢሆንም፣ በፕሮቪደንት ፈንድ የታቀፉ ድርጅቶች አሁንም በምርጫው ይቀጥሉ የሚለውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ሁለቱ አዋጆች ላይ ማሻሻያ ያቀረቡት የመንግሥት ድርጅቶች ጡረታ ኤጀንሲና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ኤጀንሲ አዋጆቹ የሚፀኑበትን ጊዜ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡ በኋላ በሚል አስቀምጠው የነበረ ቢሆንም፣ የፓርላማው የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሁለቱም አዋጆች ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የፀኑ ይሆናል በሚል አሻሽለውታል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የፓርላማ አባል፣ ‹‹አዋጆች ተፈጻሚ መሆን የሚጀምሩት በሕገ መንግሥቱ መሠረት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርመውበት በነጋሪት ጋዜጣ ታውጆ ነው፡፡ ይህ ማሻሻያ አዋጅ የተለየ አሠራር ያመጣው ለምንድነው?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ማሻሻያ አዋጁ እንዲፀድቅ ለፓርላማው የውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡት የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ፣ ከበጀት ዓመቱ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እንዲሆን ጠቁመው፣ የበለጠ ግን በምክር ቤቱ የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት እንዲሰጡበት ጠይቀዋል፡፡
በዚሁ መሠረት የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት እንዲሰጡ አፈ ጉባዔው በጋበዙት መሠረት፣ የምክር ቤቱ የመከላከያና የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ የተነሳውን የሕገ መንግሥት ጥያቄ በመደገፍ መስተካከል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የመሸርሸር ጉዳይ እንዳይሆን ፍርኃት አለኝ፡፡ በሕገ መንግሥቱ ለፕሬዚዳንቱ ከተሰጡ ሥልጣኖች ውስጥ አንዱ ይኼ ነው፤›› በማለት ሐሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
በማከልም ሕግ ሲወጣ በተቻለ መጠን ምንም ዓይነት ውዥንብር መፍጠር እንደሌለበት የተናገሩት አቶ ተስፋዬ፣ ‹‹አዋጁ ተፈጻሚ መሆን ያለበት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ቢሆን ዓላማው ገንዘብ የመሰብሰብ ያስመስለዋል፡፡ ስለዚህ አሠራራችንን ባንጥስ የሚል አስተያየት አለኝ፤›› ብለዋል፡፡ ሌላኛው የሕግ ባለሙያ የፓርላማው፣ የሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ ‹‹የሕግ ክርክር ለማንሳት አይደለም፡፡ በዚህ ምክር ቤት ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት አዋጆች የሚፀኑበትን ቀን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ሳያስቀምጥም ዝም ሊል ይችላል፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል ብሎ ሊወስንም ይችላል፤›› በማለት ተቃርነዋል፡፡
ሕገ መንግሥቱ የሚለው ፕሬዚዳንቱ በ15 ቀናት ውስጥ ይፈርማሉ እንጂ፣ ከአሥራ አምስተኛው ቀን በኋላ እንደማይል የተናገሩት አቶ አስመላሽ፣ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል መባሉ ፕሬዚዳንቱን ከመፈረም እንደማያግዳቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ የፕሮሲጀር ጉዳይ ስለሆነ ምክር ቤቱ በቀረበው መልኩ ቢቀበለው ችግር የለውም፡፡ ከሕገ መንግሥቱም ሆነ ከሌሎች ሕጎች ጋር አይጋጭም፤›› ብለዋል፡፡ በዚሁ የአቶ አስመላሽ ማብራሪያ መሠረት የመንግሥት ጡረታ አዋጅ ላይ የተደነገገው ማሻሻያ ላይ ተቃውሞ አቅርበው የነበሩትን አቶ ተስፋዬ ዳባን ጨምሮ፣ በሰጡት ድምፅ ያለ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
ቀጥሎ የቀረበው የግል ድርጅቶች ማሻሻያ የውሳኔ ሐሳብም በተመሳሳይ አዋጁ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እንዲፀና የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህ የውሳኔ ሐሳብ በቀረበበት ወቅት በድጋሚ ዕድል ያገኙት አቶ ተስፋዬ ዳባ፣ ‹‹አቶ አስመላሽ ያነሱትን መከራከሪያ አከብራለሁ፤›› ብለዋል፡፡ አክለውም እርሳቸው የተለከቱት ከመብት አንፃር መሆኑን፣ አቶ አስመላሽ ደግሞ ከሥነ ሥርዓት (Procedure) አንፃር መሆኑን በዚህም መሠረት፣ ‹‹ሁለታችንም ኤ ነው ያገኘነው›› በማለት ምክር ቤቱን ፈገግ አሰኝተዋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ግን አዋጆች ተፈጻሚ መሆን ያለባቸው በነጋሪት ጋዜጣ ከታተሙ በኋላ መሆን እንዳለበት ይከራከራሉ፡፡ ፓርላማው ራሱ ያወጣው የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ 3/1995 አንቀጽ 2(2) ማናቸውም የፌዴራል መንግሥት ሕግ የሚወጣው በፌዴራሉ ነጋሪት ጋዜጣ ይሆናል እንደሚል፣ በነጋሪት ጋዜጣ የወጣን ሕግ ማንኛውም ኅብረተሰብ የማወቅና የመቀበል ኃላፊነት እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡
በዚሁ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 2(3) ላይ፣ ‹‹ማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚና ተርጓሚ እንዲሁም ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚወጣ ሕግን የመቀበል ግዴታ ይኖርበታል፤›› እንደሚል የሚጠቅሱት የሕግ ባለሙያዎች፣ ፓርላማው ያፀደቀውን ሕግ ኅብረተሰቡ አውቆታል ተብሎ የሚገመተው በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣ በኋላ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም በነጋሪት ጋዜጣ ያልወጣን ሕግ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ብሎ አንቀጽ ማስገባት፣ አዋጁ ተፈጻሚ በሚሆንባቸው ዜጎች ወይም ድርጅቶች ላይ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል ሲሉ ይከራከራሉ፡፡
በተለይ የፀደቁት አዋጆች ጡረታ ሰብስበው በማያስገቡ ቀጣሪዎች ላይ ወለድና ቅጣት የሚጥሉ በመሆናቸው፣ አዋጁ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ መፅደቁን የማያውቁ ድርጅቶች ወይም ቀጣሪዎች ላይ የሕግ ተጠያቂነትን መጣል አግባብ አይሆንም ብለዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ዳባ በፓርላማው ስላነሱት ክርክር ተጨማሪ አስተያየት ይኖራቸው እንደሆነ ለማጣራት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 57 ፕሬዚዳንቱ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ባይፈርም፣ ሕጉን በሥራ ላይ ከማዋል የሚያግድ እንደማይሆን ይደነግጋል፡፡

–ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 12 ቢሊዮን ብር ማትረፉ ተሰምቷል
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 16 የግል ባንኮች በ2007 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ እንደሚያገኙ ሲጠበቅ፣ አንዳንድ ባንኮችም የትርፍ ምጣኔያቸውን ከእጥፍ በላይ ማሳደጋቸው ታወቀ፡፡
የ2007 ዓ.ም. የባንኮቹ የመጀመሪያ ደረጃ ጥቅል መረጃ እንደሚያሳየው ሁሉም ባንኮች በአትራፊነታቸው ዘልቀዋል፡፡ ከአምናው የበለጠ ትርፍ ማግኘትም ችለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ሁሉም ባንኮች ከታክስ በፊት አትርፈውት የነበረው ግርድፍ ትርፍ ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ሁሉም የግል ባንኮች በ2007 በበጀት የሒሳብ ሪፖርት ተቀናናሽ ሒሳብ ቢኖርባቸውም፣ ጥቅል ትርፋቸው ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ይሆናል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ከፍተኛ ትርፍ በማግኘት ዘንድሮም ከግል ባንኮች ከፍተኛውን ትርፍ ያስመዘገበው ዳሸን ባንክ ሲሆን፣ ከታክስ በፊት ከ950 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉ ተጠቁሟል፡፡ በ2006 ዓ.ም. ባንኩ ከታክስ በፊት 928 ሚሊዮን ብር ማትረፉ አይዘነጋም፡፡
አዋሽ ባንክም ወደ 890 ሚሊዮን ብር ገደማ ማትረፉ እየተነገረ ነው፡፡ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ከግል ባንኮች በትርፍ መጠኑ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የመጣው የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በማትረፍ ደረጃውን ይዞ መቀጠሉ ታውቋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በትርፍ ምጣኔው ከፍተኛ ዕድገት ካሳዩ ባንኮች መካከል እናት ባንክ አንዱ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል፡፡ ይህ ትርፍ ባለፈው በጀት ዓመት ካገኘው ትርፍ ጋር በንፅፅር ሲቀመጥ ከእጥፍ በላይ ማደጉን ያሳያል፡፡ ባንኩ በ2006 በጀት ዓመት አስመዝግቦት የነበረው ትርፍ 31 ሚሊዮን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡
እንደ እናት ባንክ ሁሉ ከአምናው የትርፍ ምጣኔ ጋር ሲነፃፀር ከ50 በመቶ በላይ ብልጫ ያለው ትርፍ ያስመዘገበው አንበሳ ባንክ ነው፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ የአንበሳ ባንክ በ2007 ዓ.ም. ያልተጣራ ትርፍ 275 ሚሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ይህ ትርፍ አምና አስመዝግቦት ከነበረው 127 ሚሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር ከ145 ሚሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አንበሳ ባንክ በትርፍ ዕድገቱ ብቻ ሳይሆን 580 ሚሊዮን ብር የነበረውን የተቀማጭ ገንዘብ አቅሙን ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር በማድረስ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉ ይጠቀሳል፡፡
ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ በ2006 ዓ.ም. 131 ሚሊዮን ብር የነበረውን ትርፍ ወደ 140 ሚሊዮን ብር ማድረስ ችሏል፡፡ ንብ ባንክ ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ እንዳተረፈ ሲነገር፣ አምና 350 ሚሊዮን ብር ያተረፈው አቢሲኒያ ባንክ ደግሞ ከ365 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉ ተጠቁሟል፡፡ ደቡብ ግሎባል ባንክም ከአምናው በተሻለ ከታክስ በፊት 31 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ችሏል፡፡ ይህ ትርፍ ከሁሉም ባንኮች ያነሰ ነው፡፡ ባንኩ አምና ያገኘው ትርፍ 19 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡
ሌሎቹም ባንኮች የትርፍ ምጣኔያቸው ዕድገት የተለያየ ቢሆንም፣ የትርፍ ዕድገት በማሳየታቸው በአጠቃላይ የግል ባንኮችን የትርፍ መጠን አምና ከነበረበት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያሳድገዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2007 በጀት ዓመት 12 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ማትረፉ ተሰምቷል፡፡ ንግድ ባንክ ባለፈው ዓመት 9.7 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ማትረፉ ይታወሳል፡፡ የዘንድሮው ግን ትልቅ ትርፍ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በአምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የተሳተፉት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) የምርጫው ውጤት ሕዝቡን ወዳልተፈለገ
አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው አስታወቁ፡፡ ሰላማዊውን የፖለቲካ ትግል ውስብስብ እንዳደረገውም ገልጸዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ይህንን ያስታወቁት ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. በራስ ሆቴል በጋራ በሰጡት መግለጫ ወቅት ሲሆን፣ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ፣ የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደና የኢራፓ ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ናቸው፡፡
ሥርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍሬያማ ከመሆን ይልቅ እየቀጨጨና እየኮሰመነ በመሄድ ላይ ለመሆኑ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ዋና መገለጫ የሆነው የምርጫ ሒደት ችግር ቁልጭ አድርጐ እያሳየን ሲሉም ደምድመዋል፡፡
የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እውን እንዳይሆን ገዥው ፓርቲ እንቅፋት ሆኗል የሚለው የፓርቲዎቹ መግለጫ፣ ‹‹ገዥው ፓርቲ ከዚህ ግትር አቋሙ ፈቀቅ የማይል ከሆነ የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም ሆነ አጠቃላይ የአገሪቱ ሰላም አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል ብለን እናምናለን፡፡ ገዥው ፓርቲ የምርጫ ዴሞክራሲያዊነትና ፍትሐዊነት መርሆዎችን ካላከበረ ሕዝቡን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይመራዋል ብለን እንሰጋለን፤›› ሲልም ያክላል፡፡ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ የከሰመው የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በአገሪቱ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ጥያቄ ያስቀመጠ መሆኑንም ፓርቲዎቹ አመልክተዋል፡፡
‹‹በ2007 ዓ.ም. የተከናወነው አምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ባለመሆኑ ምክንያት፣ በአገራችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሏል፡፡ ይህም በመሆኑ በአገራችን ያለው አንፃራዊ ሰላም አስተማማኝ አይሆንም የሚል ሥጋት አድሮብናል፤›› በማለትም የፓርቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡
‹‹በአገራችን ዴሞክራሲ እንዲጠናከርና እንዲያብብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁ ተቋማት በምርጫው ሒደት ላይ የፈጠሯቸው ተግዳሮቶች በሰላማዊ ትግሉ ላይ ትልቅ ጋሬጣ በመሆናቸው፣ የወደፊቱን ሰላማዊ ትግል እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ አድርጐታል፤›› በማለት በመግለጫው አትቷል፡፡
የፓርቲዎቹን አጠቃላይ የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ ሲናገሩ፣ ‹‹ከሦስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለቱ የጋራ ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ እኛ ግን አይደለንም፡፡ ልንሆንም አንችልም፡፡ ሙሉ በሙሉ በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ አብረን እንሠራለን ማለት አይደለም፤›› በማለት ለጊዜው በጋራ የሚሠሩት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
በጋራ ለመሥራት ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በጋራ መጥራትና የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፎችን ማዘጋጀት ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹ሙሉ በሙሉ በአንድ ላይ ለመሄድ የምናርቃቸውና የምንመለከታቸው ጉዳዮች ይኖራሉ፤›› በማለትም ፓርቲዎቹ በጋራ የሚሠሩባቸውን ተጨማሪ ጉዳዮች ለመለየት በድርድር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፣ ‹‹በተለይ ተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም የምናራምድ ፓርቲዎች በተጠናከረ ስልትና ስትራቴጂ ሐሳቦቻችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እያደረግን ለመሥራት እንድንችል የሚያስችለንን ስልት ነድፈን እንሄዳለን ብለን እናምናለን፤›› በማለት ሦስቱ ፓርቲዎች የሚያግባቧቸውን ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ እንዳለዩ ገልጸዋል፡፡
ኅብረት፣ ግንባር ወይም ውህደት ፈጥሮ ለመሥራት በርካታ ሒደቶችን የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን በሌሎች የፖለቲካ ተንታኞችም እየታገዝን በጉዳዩ ላይ ወደፊት እንወስናለን፤›› በማለት ሐሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡
በምርጫ 97 ጠንካራ ተወዳዳሪ የነበረው ቅንጅት እንዲዳከም ትልቅ በር የከፈተው የመኢአድና የኢዴፓ ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከቅንጅት ራሱን ያገለለው ኢዴፓ ከምርጫ 97 በኋላ ከተለያዩ ኅብረቶች፣ መድረኮችና ጥምረቶች ራሱን በማግለል የቅንጅት አባል ከነበሩ ፓርቲዎች ጋር አንድ ላይ ለመሥራት የሚያስችል መሠረት እንደሌለ፣ በጫና አባል መሆኑ ስህተት እንደነበር በራሱ ላይ ግለ ሒስ ማቅረቡም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
የፖለቲካ ተንታኞች ከዚህ አንፃር ኢዴፓ መሥራች አባላቱ ተገንጥለው የወጡበት መአሕድ ራሱን በሒደት ወደ መኢአድ ከመቀየሩ አንፃርና ኢራፓ ከ1997 በኋላ በ2001 ዓ.ም. የተፈጠረ አዲስ ፓርቲ ከመሆኑ አኳያ፣ ከእነዚህ ፓርቲዎች ጋር የጀመረው ግንኙነት ያልተጠበቀ መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡
–ውሳኔውን አንብቦ ለመጨረስ ሦስት ቀናት ፈጅቷል
ራሳቸውን የሙስሊሙ ኅብረተሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ በማለት ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ዓላማዎችን ለማራመድ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመጣል፣ ኢስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት፣ በህቡዕ
በመደራጀትና የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል ተብለው የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው 18 ግለሰቦች ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ ተባሉ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የሽብር ድርጊት ክስ የመሠረተባቸው ሁለት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና 29 ግለሰቦችን የነበረ ቢሆንም፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ያላቸው 18 ተከሳሾችን ብቻ ነው፡፡ የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ መሐሙድን ጨምሮ 11 ግለሰቦችና ድርጅቶቹ ከክሱ በነፃ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱ ለሦስት ዓመታት ያህል ሲያከራክርና ሲመረምር የከረመውን የፍርድ ሒደት አጠናቆ የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጠው በአቶ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼክ መከተ ሙሔ፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሐመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ሙራድ ሽኩር፣ አቡበከር ዓለሙ፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሼክ ባህሩ ዑመር፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼክ ሰዒድ ዓሊ፣ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፣ ሙባረክ አደምና ካሊድ ኢብራሂም ላይ ነው፡፡
ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በሁሉም ተከሳሾች ላይ አራት ክሶችን ያቀረበ ቢሆንም፣ ሦስተኛና አራተኛ ክሶች የሚያተኩሩት መንግሥታዊ ባልሆኑት ድርጅቶች ላይ በመሆናቸው ድርጅቶቹ ነፃ በመሆናቸው ክሶቹም ቀሪ ሆነዋል፡፡ በአንደኛና በሁለተኛ ክሶች ላይ ተከሳሾቹ ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱኛል ያላቸውን የሰዎችና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል፡፡ ከመቶ በላይ ምስክሮችንም አሰምቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሰዎችና የሰነዶች ማስረጃዎች ጨምሮ፣ የተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ የዓቃቤ ሕግን ክስና የምስክሮች ቃል ማፍረስ አለማፍረሱን መርምሮ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹም ከ400 በላይ መከላከያ ምስክሮችን አስመዝግበው 157ቱን በማሰማት ቀሪዎቹን ትተዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግና ተከሳሾቹ በምስክሮቻቸው ያስረዱትን የምስክርነት ቃል ከክሱና ተገቢ ሕግ ጋር በመመርመር፣ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሰብሳቢ ዳኛ በሆኑበት ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት፣ አምስት ጭብጦችን ይዞ የክስ መዝገቡን መመርመሩን ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ የያዛቸው ጭብጦች፣ ‹‹መንግሥት በሙስሊሙ ጉዳይ ጣልቃ ገብቷል ወይስ አልገባም? መንግሥት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ከፋፍሏል ወይስ አልከፋፈለም? የመጅሊሱ ምርጫ በቀበሌ እንዲሆን መደረጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? ተከሳሾችን ለመያዝ የተደረገው የብርበራ ሒደት የኢትዮጵያን ሕግና ሕገ መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችን የተከተለ ነው ወይስ አይደለም? እና ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ ተከላክለዋል ወይስ አልተከላከሉም?›› የሚሉ ናቸው፡፡
ፍርድ ቤቱ የሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ከመቶ ገጾች በላይ በመሆኑ ማንበብ የተጀመረው ሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ቢሆንም የተጠናቀቀው ከሦስት ቀናት በኋላ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ነው፡፡ ሰኔ 26 ቀን 2007 (ዕለተ ዓርብ) ችሎት አልነበረም፡፡ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ያቀረቡት በርካታ ገጾች ያሉት የሰነድ መከላከያ መስረጃ ማቅረባቸውን ገልጾ፣ ከክሱ ጋር የሚዛመዱትንና ፍሬ ነገር ያለባቸውን ሰነዶች መውሰዱን ገልጾ ባጭሩ አሰማ፡፡
ተከሳሾቹ ከመቀመጫቸው ተነስተው ‹‹ጥያቄ አለን›› በማለት ሲያመለክቱ፣ ‹‹ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እየተነበበ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤›› ቢልም መናገራቸውን ቀጠሉ፡፡ እስካሁን መታፈናቸውን (የጥፋተኝነት ውሳኔው እስከተሰጠበት ቀን) ተናግረው ያቀረቡት 20,000 ገጽ ማስረጃ ሆኖ ሳለ አራት ገጽ እንኳን የማይሞላ ማስረጃ ተደርጎ መወሰዱን እንደሚቃወሙ ገለጹ፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን እንዳልሠራው በመናገር ይኽንን ሊያስብላቸው የቻለው በውሳኔው ውስጥ የተፈቱ ሰዎች ስም ዝርዝር ሲጠቀስ በመስማታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ሠርቶት ቢሆን ኖሮ የተፈቱ ሰዎች ሊካተቱ እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በተነበበላቸው ውሳኔ ውስጥ በርካታ ስህተቶች እንዳሉም አክለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት በተለይ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመሰብሰብ እየከፋፍሉትና የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛትና ሙስሊሙን ሊከፋፈሉ እንደሆነ በመግለጽ የሃይማኖት ተከታዮችን ማነሳሳታቸውን የዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡ ገልጿል፡፡ የወሃቢያ አስተምህሮ መጥቶ ሃይማኖታቸውን ሊያስቀይራቸው መሆኑን የፌዴራል ጉዳዮች ለሙስሊሞች መንገሩን፣ የአወሊያ ተማሪዎች በመጅሊሱ መባረራቸውን፣ የወሃቢያ አስተምህሮ ሕገ መንግሥቱን ለማፈራረስ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን፣ ሙስሊሞች በጨለማ ውስጥ መታሰራቸውን፣ መንግሥት ከአወሊያ ላይ እጁን ያላነሳና መጅሊሱ ያወጣው መተዳደሪያ ደንብ ሙስሊሙን የሚያከብር እንዳልሆነ በመናገር መንግሥት አስቸኳይ መልስ ካልሰጠ፣ በሌላው ዓለም የሚታየው አክራሪነት በኢትዮጵያም የማይታይበት ምንም ምክንያት እንደሌለ፣ ምርጫ ከመስጊድ ውጪ መደረግ እንደሌለበት በመንገርና በመቀስቀስ አመፅ ማነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ ካቀረበው የሰነድና የሰው ምስክሮች መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ አብራርቷል፡፡
ተከሳሾቹ በተለያዩ ቦታዎች ባደረጉዋቸው ንግግሮች የፖለቲካ አጀንዳ እንደሌላቸው፣ ኢስላማዊ መንግሥት የመመሥረት ዓላማ እንደሌላቸውና ሞኝ አለመሆናቸውን፣ የሚፈልጉት ጥያቄያቸው እንዲመለስላቸው ማለትም የመጅሊስ ምርጫ በመስጊድ እንዲሆንና ታዛቢ እንደማያስፈልግ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን የሚወክለው መፍትሔ አፈላላጊው ኮሚቴ ብቻ ምርጫውን የማድረግ ኃላፊነት እንዲወስድ፣ ወዘተ እንዳሉ የገለጹ ቢሆንም፣ ሃይማኖቱን ሽፋን በማድረግ ሙስሊም ኅብረተሰቡን ለአመፅ ማነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ በሰነድና በምስክሮች ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ተከሳሾቹ ሰላማዊ መሆናቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠላቸውን የሃይማኖት እኩልነትና መንግሥት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ለማረጋገጥ ስለእምነታቸው ከመጠየቃቸው ባለፈ፣ ምንም ወንጀል አለመፈጸማቸውን የሚያስረዱላቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማቅረባቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ሁሉም ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ አቶ አቡበከር በስተቀር ዓቃቤ ሕግ ፈጽመዋል ያለውን የወንጀል ድርጊት ፖሊስ በወንጀል ሕግ 27 መሠረት በግዳጅ ቃላቸውን እንዲሰጡ ያደረጋቸው መሆኑን መናገራቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ ነገር ግን ዓቃቤ ሕግ በምስክሮቹና በሰነድ ማስረጃዎቹ ተከሳሾቹ በፖሊስ ጣቢያ አምነው የተናገሩትን በማረጋገጡ፣ ተከሳሾቹ ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የዓቃቤ ሕግን ክስ ከማረጋገጥ ባለፈ ከተጠያቂነት የሚያድናቸው አለመሆኑን ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የተመሠረተባቸውን ክስ ማስተባበል አለመቻላቸውን አንድ በአንድ ሲገልጽ፣ መጀመርያ አቶ አቡበከር ከመቀመጫቸው በመነሳት ‹‹አሏህ አክበር፣ ነፃነቴን ያረጋገጥኩበት ፍርድ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ፤›› ሲሉ፣ ሁሉም እጅ ለእጅ ታይዘው ‹‹አሏህ አክበር›› በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ አስፈላጊውን ዕርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ መደብዳባቸውንና ከፍተኛ በደል እንደደረሰባቸው በመከላከያ ምስክሮች ቢያስረዱም፣ በተለይ እርስ በርስ (እስረኞቹ) ከመመሰካከራቸው አንፃር ምስክርነቱ ተዓማኒ ሊባል እንደማይችል ፍርድ ቤቱ በመግለጽ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የኢትዮጵያን ሕግ፣ ሕገ መንግሥትና ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚጥስ ድርጊት የፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ ሁሉንም ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያቸውን፣ ዓቃቤ ሕግ ደግሞ የቅጣት ማክበጃውን እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያስገቡ በማዘዝ ፍርድ ለመስጠት ለሐምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡
–የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የተቀጡት በሌሉበት ነው
መንግሥታዊ ሰነዶችን በሐሰት በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ፣ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ማጭበርበራቸው የተረጋገጠባቸው የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅና ሁለት ግለሰቦች፣
ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ከአምስት እስከ 12 ዓመታት ከስድስት ወራት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው፣ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት አበጀ፣ ይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ የተባለ ድርጅት ተወካይ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ይትባረክ አፈወርቅ ናቸው፡፡
የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በ2005 ዓ.ም. የተለያዩ ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነዶችን አዘጋጅተዋል፡፡ ያዘጋጁትን ሐሰተኛ ሰነድ ይፍመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ለተባለው ድርጅት በመስጠት ወንጀሉን መፈጸማቸውን ያስረዳል፡፡
በሥራ አስኪያጁ የተዘጋጀውን ሐሰተኛ ሰነድ የድርጅቱ ተወካይ አቶ ብርሃኑ በመቀበልና ሐሰተኛ የሽያጭ ዋስትና በማስያዝ፣ ከአንድ የማደያ ድርጅት ውል ተዋውለው 900,000 ብር የሚያወጣ የሞተር ዘይት፣ ቅባቶችና የነዳጅ ኩፖን ወስደው በወንጀሉ መሳተፋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
የይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ሥራ አስኪያጅ ናቸው የተባሉት አቶ ይትባረክ፣ ከአቶ ብርሃኑ ጋር በመተባበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ላደረጉት የእንጨት ምሰሶዎች አቅርቦት ውል፣ ሐሰተኛ ሰነዱን በዋስትና በማቅረብ 4,908,623 ብር ቅድመ ክፍያ ከኢትዮ ቴሌኮም በቼክ መውሰዳቸውን ይገልጻል፡፡ ገንዘቡንም ወደ ድርጅታቸው አካውንት በማስገባትና አውጥተውም ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውም በክሱ ተጠቁሟል፡፡
የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ሦስቱም ተከሳሾች ድርጊቱን መፈጸማቸውን በምስክሮችና በሰነድ በማረጋገጡ፣ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በሌሉበት በስምንት ዓመታት ጽኑ እስራት፣ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬ በ12 ዓመት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራትና አቶ ይትባረክ አፈወርቅ በአምስት ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ሰጥቷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው ። ወ/ ሮ ሚልድሬድ ማሼጎ እና የአብራካቸው ክፋይ የሆነችው ፓትሪሲያ ስማቸው የአለማችን የድንቆች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው። በደቡብ አፍሪካ ካስቲል ነዋሪ የሆኑት የ38 አመቷ እናት ወ/ሮ ማሼንጎና የ19 አመቷ ወጣት ልጃቸው ፓትሪሲያ በአንድ ወር ውስጥ፣ በአንድ ሣምንት ውስጥ እንዲሁም ከተመሳሳይ ሰው በመውለድ ወ/ሮ ማሼንጎ ልጅና የልጅ ልጅ አገኙ ፣ ወጣት ፓትሪሲያ ልጅና […]![]()
ቴዲ አፍሮ ከጎሳዬ ጋር ተጣምረው ያቀርቡታል የተባለው ኮንሰርት በቪዛ ምክንያት ፕሮግራሙ መፋለሱ የሚታወስ ሲሆን ቴዲ ግን ዛሬ የበረራ ጉዞ ነበረው።ጉዳዩ ከሙዚቃ ስራ ጋር የተያያዘ አልነበረም።ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በአሁኑ ሰአት ለጤንነት ቼክሃፕ ኬንያ ናይሮቢ ትገኛለች።ቀደም ብላ የሄደችው ሚስቱን እንዴት ነሽ? ለማለትና ከጎኗ ለመሆን ፈልጎ ለጉዞ የሚያስፈልጉትን የነፍስ ወከፍ እቃዎች በሻንጣ በመሸከፍ በዛሬው አለት ከቀኑ 11 ሰአት […]![]()
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
DRC in Ethiopa, Embassy employees not paid 15 years – 07-07-15
ለኢህአፓ ሲምፖዝየም የቀረበ ወዴት እየሄድን ነው? § ዛሬ፣ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ፣/ መኖሯን የማይሹ፣/ ከቻሉም የየራሳቸውን የጎጥ መንግስታት ለማቋቋም የሚፈልጉ ኃይሎች አጋጣሚው እስከሚፈጠርላቸው እየጠበቁ ነው። § ዛሬ ኢህአዴግ በሚከተለው ፖሊሲ ኢትዮጵያ ለክፋ አደጋ እየተጋለጠች ነው። § ዛሬ፣ በዘር የተደራጁ ኃይሎች አመቺ አጋጣሚ እየጠበቁ ናቸው። § ዛሬ እነ አይሲስና መሰል ኃይሎች ምን እንዳዘጋጁልን አናውቅም። አርፈው እንደማይተኙ ግን […]
Hailemariam Desalegn repremanded Eritrea – 07-07-15
ህወሃት የሚመራዉ የመከላከያ ሰራዊት የዘመቻ መምሪያና ክትትል ቢሮ እንዲሁም የመከላከያ ደህንነት የበላይ ሃላፊዎች በአርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ለመከላከያ ሚኒስቴር በማመልከት በአስቸኳይ የመከላከያ ሐይል ተጨምሮ ስፍራዉን የመልሶ ማጥቃት የጦር ክልል ካላደረግነዉ በስተቀር የተዋጊዎቻችዉ የጦር ስልት ከባድና የሚያሰጋ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የከፈተዉን ጦርነት መልሶ ያጠቃል የተባለ ሐይል ከጎንደርና ከወሎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሰሞኑ በተደረገ ጦርነት ብቻ የ 44 ተኛ […]![]()
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ ለፓርላማ አባሎች እንደተናገሩት የኤርትራ መንግስት አካባቢውን የማተራማስ አጀንዳውን ካላቆመ ፣ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ሻእቢያ ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማተራመስ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል። የኢትዮጵያን ህዝብ አስታውቀን እርምጃ እንወስዳለን ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ እስካሁንም ለደረሰብን ጥቃት ተመጣጣኝ እርምጃ ስንወስድ ቆይተናል ሲሉ አክለዋል። የአቶ …
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ ዋና ከተማ ጋሮው በከባድ መኪና ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩትን ሰማንያ ሁለት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና የተሽከርካሪውን ሹፌር አብሮ መያዙን የፑትላንድ ፀጥታ ሹም ኃላፊ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአስር ሽህ በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች በመሳፈር ባሕር አቋርጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ …
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለማቀፍ ታላላቅ የመገኛኛ ብዙሃን አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር እና የመድረክ የፖለቲካ ማህበር አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና ´´አሜሪካ አምባገነኖችን የምትደግፍም …
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
በኤርትራ ላይ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛቱ፡፡
የአስተዳደር ሓላፊዎቹ÷ የተዛቡ መረጃዎችንና ያልተጨበጡ ወሬዎችን እየነዙ በተለይ በሒሳብ አሠራር፤ በቆጠራ አካሔድ፤ በኦዲት ክንውን፤ በንብረት አያያዝ እና በግዢ ሥርዐት ዙሪያ ሰበካው በተለያዩ ጊዜያት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና መመሪያዎች እንዳይተገበሩ አድርገዋል፡፡ በፓትርያርኩ እና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጣቸው ተስፋ ከተግባር የራቀባቸው የሰበካ ጉባኤው አባላት፣ ከሚመለከታቸው የፍትሕ እና የጸጥታ አካላት ጋር እየመከሩበት ነው፡፡ ‹‹ምእመኑን ጃኬት ለባሽ አይመራንም …![]()
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 3 ቀናት ወደ አረብ አገር እንወስዳችሁዋለን በሚል የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ ለማጓጓዝ መሞከሩን ወጣቶች ተናግረዋል። ወጣቶች እንዳሉት ወደ አረብ አገራት ትሄዳላችሁ ተብለው ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም እያጓጓዙ ሲሆን፣ አንዳንዶች መንገድ ላይ ጠፍተዋል። ካለፈው አመት ጀምሮ ወታደሮችን ለማሰልጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ …
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 18 የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በሙሉ ጥፋተኞች ሲባሉ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት ለሃምሌ 27 ቀጠሮ ሰጠ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በ አቶ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ …
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ካውንስል፣ ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በአስቸኳይ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል እንድትለቃቸው ጠይቋል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው የተመድ የሰብአዊ መብት ካውንስል በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በጭካኔ የተሞላ አካላዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙባቸው የሚያትቱ ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዳሉት ለኢህአዴግ መንግስት በላከው 8 ገጽ ደብዳቤ ላይ ማስፈሩን …
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ዘይሴ በሚባል ቀበሌ፣ ከ4 ቀናት በፊት አንድ ግለሰብ ከመሬት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የመሬት አስተዳደር ሃላፊውን ጨምሮ ሌሎች 3 የወረዳ ሹሞችን ገድሏል። ግለሰቡ በ2007 ምርጫ የተቃዋሚ አባሎችን ደግፈሃል በሚል የያዘውን መሬት እንዲለቅ የመሬት አስተዳዳር ሃላፊው በጠየቁት ጊዜ፣ ” ከአባቴ ያገኘሁትን የውርስ መሬት …
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጣሊያን ውስጥ የሚገኘውና ሃኪንግ ቲም ” hacking team” በመባል የሚታወቀው ለደህንነትና ለስለላ የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር ሶፍት ዌሮችን የሚሸጠው ድርጅት፣ የራሱ መረጃዎች በሌሎች ሃይሎች የተዘረፈ ሲሆን፣ እስካሁን ይፋ በሆኑት መረጃዎችን ቢንያም ተወልደ የተባለ ኢትዮጵያዊ በብሄራዊ ስለላ ድርጅት ስም 1 ሚሊዮን ዶላር በአንድ ጊዜ መክፈሉን የወጣው ሰነድ ያመለክታል። ገንዘቡ …
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ግን ማስተባበያውን አጣጥለውታል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ የወርቅ ልማት ኩባንያ ከሆነው ሚድሮክ ጐልድ በሕግ የተወሰነውን ገቢ ባለመሰብሰቡ፣ አገሪቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ አጥታለች ማለቱ ይታወሳል። ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ …
Aba Begu
ኢሳት ዜና (ሰኔ 28 2007 አም) የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታ ሲከታተል የቆየው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የካሳ ክፍያ በመፈጸም አቶ አንዳርጋቸውን በአስችኳይ እንዲፈታ ማሳሰቡን አለማቀፍ ሚዲያዎች ዘገቡ። ባለስምንት ገጽ ውሳኔውን በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በኩል ለኢትዮጵያ ያቀረበው ድርጅቱ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእስር ቤት ቆየታቸው ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰባዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው መግለጹን ዘ-ፋይናንሺያል ኤክስፕረስ …
Ethiopian opposition parties opposed Obama’s visit to Ethiopia. 04-06-15
…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው ። ጊዜው ተቀይሯል.. ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም ።ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ …Filed under: political opinion![]()