VOA የአማርኛ ዜናዎች – ሰኞ Sep 12, 2011
News, Sports, African Topics and Health
News, Sports, African Topics and Health
News, Radio Magazine or Mestawot
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የምሥራቅ አፍሪካን ድርቅና የረሃብ ሁኔታ በቅርብ ይከታተላል፡፡
የአፍሪካ ቀንድን በመታው ድርቅ ዙሪያ በተከታታይ በሚቀርቡት ዘገባዎች ከምንቃኛቸው አካባቢዎች ሪፖርተራችን ሄኖክ ሰማእግዜር ተዘዋውሮ የተመለከታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የቦረና ወረዳዎች ይገኙባቸዋል፡፡ ደቡብ ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት ገፅታዎች ያሏት መሆኑንና የክረምቱ ዝናብ በወቅቱ በጀመረባቸው ከአዋሣ ከተማ በፊትና አልፎም ስፋት ባላቸው አካባቢዎች አዝመራው ከወትሮው …
ትዮጵያና ናይጀርያ ለሊብያ አማጽያን እውቅና ሰጡ
የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት የታወቁ የፖለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችን ይዞ ማሠሩን አስታውቋል።
ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች የታሠሩት ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ መሆኑን የቡድኑ የኢትዮጵያ ተመራማሪ ክሌር ቤስተን ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት ታዋቂ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ይዞ አሥሯል፡፡ የአንደኛው ክስ ‘በሽብር ፈጠራ ነው’ ተብሏል፡፡ ይህንን የመንግሥት እርምጃ በፖለቲካ ምክንያት የተነሣሣ ነው ሲሉ ተቃዋሚ መሪዎች አውግዘውታል፡፡
ነባር የተቃዋሚ መሪ ናቸው የሚባሉት በቀለ ገርባ የተያዙት ‘በኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ፈጠራ ቡድንነት ተፈርጆ ከታገደው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው’ በሚል መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥታ ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት በቀለ ገርባ …
የዛሬው «ኢትዮጵያ በጋዜጦች» ፕሮግራማችን -ኢትዮጵያ 300,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንደምታስገባ ገለጸች -የህንድ ኩባንያዎች መዋዕለ-ነዋይ በምስራቅ አፍሪቃ -ሚሱቡሺ በደቡብ ኢትዮጵያ የጸሃይ ኤነርጂ ለማስገባት ተዋዋለ -ኢትዮጵያ ሜሪሎዎችንና ቱካናዎችን ለማስታረቅ እርምጃ ወሰደች የሚሉትን ርዕሶች ይዞ ቀርቧል።
ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ደኤታ ምትኩ ካሣ በድርቁ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥርም የፊታችን ጥቅምትና ኅዳር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ምትኩ ካሣ በኢትዮጵያ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የአደጋ መከላከል፣ ዝግጁነትና የምግብ …
በኢትዮጵያ አሁንም ሆነ ባለፉት ሃያ ዓመታት ድርቅ እንጂ ረሃብ የለም ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በጎዴ አከባቢ የገቡ ሶማልያውያን ስደተኞች ቁጥር ከ 17,000 በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ። እስካሁን ባለው ጊዜ በቂ እርዳታ እንዳልተሰጣቸውና ይህም በአከባቢው ህበረተሰብ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገልጿል። በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ የፓብሊክ ኢንፎርሜሽን ረዳት አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሄር …
በሶማልያ ክልል የገቡት ሶማልያውያን ስደተኞች ቁጥር ከተባለው 17,500 በላይ ስይሆን አልቀረም ተባለ Read more »
የቢቢሲው ኒውስ ናይት ፕሮግራምና የምርመራ ጋዜጠኝነት ቢሮ በመተባበር ሀገሪቱ ውስጥ “በድብቅ ሠራነው” ባሉት ጥናታዊ ፊልም “የኢትዮጵያ መንግሥት በቢሊዮኖች ዶላር የሚያገኘውን የልማት እርዳታ ለፖለቲካ ጭቆና በመሣሪያነት እንደሚጠቀምበት አረጋግጠናል” ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ወያኔ የቀረቡበትን ክሦች “የሃሰት ውንጀላዎች ናቸው” ሲል ውድቅ አድርጓል። ሰሎሞን …
ቢቢሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በድብቅ የተሠራው ፊልም ለዕይታ በቅቷል፡፡
ሰሞኑን ወደአርሲ ያመራ ሰው ከመንገዶች ግራና ቀኝ የሚመለከተው የድርቅና የረሃብ ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡ ዘግይቶም ቢሆን ዝናቡ የጀመረ፣ ‘ጠብ..ቁኝ’ ያለ ይመስላል፡፡ … ገበሬው ማረስ በሚገባው ሰዓት አላረሰም፡፡ ለምግብ ወደገበታ፣ ለሽያጭም ወደገበያ የሚወጣ እህል የለም፡፡ አገሩ ግን አረንጓዴ … ጎተራው ግን ባዶ …
ድርቅ በተከሰተባቸው የምዕራብ አርሲ አካባቢዎችና በሌሎችም መሰል ወረዳዎች ያሉ አርሶ አደሮች ዘንድሮ እንዳላመረቱ ይናገራሉ። ለጊዜው ተስፋቸውን የጣሉትም በእርዳታ እህል ላይ ነው።
በዶሎ ኦዶ ኮቤ የስደተኞች መጠለያ ረሃብ እየገደለው ያለው ሰው ቁጥር አሁንም ከፍተኛ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ ስደተኞቹ የኢትዮጵያን ድንበር እያቋረጡ መግባት የጀመሩት ከስድስት ሣምንታት ወዲህ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነርና የኢትዮጵያ መንግሥት ቃኚዎች ጥምር ቡድን አረጋግጧል፡፡ …
ከሶማሊያ ድንበር ተሻግረው ከ17 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደኢትዮጵያ ጎዴ አካባቢ ገቡ፡፡
አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል አንድ ከፍተኛ የረድ ኤት ባለስልጣን።
ውሸት መናገር፥ አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲባል ይሁነኝ ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ወይም ሃሰተኝነት በማኅበራዊ ህይወት ውስጥ ከሚያስከትላቸው ችግሮችና ዋሾነት፥ በግለሰብ ደረጃ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን የሚያሳጣ ስብዕና ከማላበሱ ባሻገር፥ ውሸት በበሽታነት የሚፈረጅበት ሁኔታ ይኖር ይሆን? አንዳንዴ ለምንና እንዴት ሊሆን እንደቻለ እንኳን ምክኒያቱ …
«ባህላችን የሁለንተናዊ ማንነታችን መሠረት ነውና እሱን ይዘን እንከኖቹን ነቅሰን ማሻሻልና ማጎትበት እንችላለን።» «የለም የፖለቲካ ባህላችን ዛሬ ላሉን ችግሮች የአንዳንዱ መነሻ ነውና ከሥር መሠረቱ መቀየር አለበት።»
የኢትዮጵያ የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም በአርአያነት ተጠቀሰ
በኤርትራ ላይ የሚጣለው ማዕቀብ ህዝቡን የማይጎዳ እንደሚሆን ሱዛን ራይስ ጠቅሰዋል
በሚንቀሳቀስባቸዉ የተለያዩ የአርሲ ወረዳዎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ቢጨምርም፣ አስፈላጊዉ ድጋፍ ግን እየተደረገ መሆኑን በምግብ እደላ ስራ የተሰማራው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታ ድረጅት አስታውቋል። አቅርቦቱን ከካቶሊክ የእርዳታ ድርጅት በመቀበል ስርጭቱን የሚያካሄደዉ የመቂ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የልማት ክፍል መሆኑም …
በሚንቀሳቀስባቸዉ የተለያዩ የአርሲ ወረዳዎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ቢጨምርም፣ አስፈላጊዉ ድጋፍ ግን እየተደረገ መሆኑን በም
በምእራብ አርሲ ሻላ ወረዳ አጄ ከተማ ለአካባቢው ነዋሪዎች የእህል እርዳታ ታደለ፡፡
እርዳታውን የሚሰበስበውም የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት መሆኑን ገልጿል። የእርዳታው እንቅስቃሴ መሠረት ያደረገውም መንግሥታ ያወጣውን ሠነድ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡ ከሐምሌ ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የአደጋ መከላከል፣ ዝግጁነትና ዋስትና ዘርፍ …
በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ባለፈው አመት ሃምሌ ወር ከነበረው 50ከመቶ የሚጠጋ ጭማሪ ማሳየቱን የመንግስቱ ማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገችው አራት ልጆች ብቻዋን የምታስተዳድር የአሰላ ከተማ ነዋሪ ዛሬ ማርፈጃውን ገበያ ወርዳ ነበር። “ከበርበሬ አቅም በፊት 30 እና 40 ብር የነበረው …
“የመጣሁት ከሳለሪ ነው። እንደ ፍየል የሆነ ቅጠል እበላ ነበረ። ዝናም በመጥፋቱ ምክኒያት አሁን ያም ቅጠልም ጠፋ።” ከሳለሪ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ የአራት ቀን የእግር ጉዞ አድርገው ዶሎ የደረሱ አንዲት የ80 አመት
“ድርቁ ያስከተለው የምግብ እጥረት የዝናብ መጥፋት፥ ማዳበሪያ የመግዛት አቅም ማጣትና የጉልበት ማነስ ናቸው። አልፎ አልፎ ይዘንባል። ደግሞም ጨርሶ ይጠፋል። መዝነብ በሚገባው ወቅት አይዘንብም። ቢዘንብም ያለ ወቅቱና
የሶማልያው ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን ዐል ሸባብ ባለፈው ቅዳሜ ከሞቕድሹ እንደወጣ ይታወሳል። የሶማልያው ፕረዚዳንት ሼኽ ሸሪፍ አሕመድ አማጽያኑ መሸነፋቸውን ገልጸዋል። ዐል-ሻባባ ግን ወታደራዊ ማፈግፈግ ነው ያደረግኩት ይላል። ስለ ጉዳዩ እንዲያብራሩልን የጋበዝናቸው የአፍሪቃ ጥናትና ምርምር ምሁር ዶክተር አለም ሃይሉ በበኩላቸው ዐል-ሻባብ ከሞቕድሾ …
የሶማልያ የሽግግር ፕረዚዳንት ሼኽ ሸሪፍ አሕመድ ግን ተሸንፎ ነው የወጣው ይላሉ
መሬት ከሰዎች አሠፋፈር፤ ከሰብዓዊ፣ የዜግነትና የንብረት መብቶች፣ ከተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና ልማት ጋር በጥብቅ የተቆራኘና የተሣሰረ በመሆኑ በየደረጃው የሚሰጠው ትርጉም የዚያኑ ያህል ጠበቅ ያለ ነው፡፡ የመሬት ይዞታን ሥሪት ከሚደነግገው መንግሥት በስንዝር መሬት ሙግት ሙሉ ዕድሜአቸውን እስከሚፈጁ ግለሰቦች አንገብጋቢና ትርጉም ያለው የሃብት …
ይህ World Heritage Committee የሚባለው የዩኔስኮ አካል ባሕላዊና አካላዊም እሴትና ትርጉም ያላቸውን አካባቢዎች እየመዘገበ የሚይዝ ተቋም ሲሆን ግዙፉ ግቤ ሦስት ግድብ እየተገነባ ያለበት ኦሞ ወንዝ የሚገባበትን በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ ያለውን ቱርካና ሐይቅም በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ የተቋሙ ቃል አቀባይ ነፃ …
በዓለም የዲሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባትና ለማጠናከር የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። National Endowment for Democracy በምህፃረ ቃሉ፥ NEDከዩናይትድ ስቴት
በረሃብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት እና እናቶች በየሠፈሩ ይታያሉ። በቂ እርዳታ አላገኘንም የሚሉም አሉ። የመለስካቸው አምሃ ሪፖርት ይቀጥላል፡፡ ዶሎ ኦዶ ከተማ በደቡባዊ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አገሪቱን ከሶማሊያ ጋር ከሚያገናኙ ትናንሽ ከተሞች አንዷ ናት። በዶሎ ኦዶ ከተማና በሶማሊያ ድንበር መካከል ያለው ልዩነት 2 …
የዛሬው «ኢትዮጵያ በጋዜጦች» ዝግጅታችን የሚከተሉትን ርዕሶች ይዟል -ኢትዮጵያ አርብቶ-አደሮችን በዘለቄታ ለማስፈር አቀደች -ኢትዮጵያ ለካሩቱሪ ኩባንያ የተመደበውን መሬት ቀነሰች -ኢትዮጵያ በስድስት አመታት ውስጥ ጋዝ ልታመርት እንደምትችል አስታወቀች
እንደ አል-ሸባብ ያሉ አሸባሪ ድርጅቶች ከረድዔት ድርጅቶች ምንም አይነት ክፍያም ሆነ እርዳታ እንዳያገኙ የሚከለክሉ የጸረ-ሽብር አሰራሮችን ዩናይትድ ስቴይትስ አላልታለች።
በመጠለያዎቹ ያሉት ትንንሽ ልጆች በምግብ እጥረት እንደማቀቁ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የበቆሎ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተጠቃሚዎችና የችርቻሮ ነጋዴዎች መማረራቸውን ይናገራሉ። ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ገበያ ወጥቶ ሸማቾችንና ነጋዴዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት።
የአፍሪካ ኅብረት የዚህ ዓመቱን የመሪዎች ጠቅላላጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ጠርቶ በነበረ ጊዜ የኤርትራ መንግሥት መጠነ ሰፊ ጥቃት ለማድረስ አቅዶ እንደነበረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ጥቃቱ በታቀደው መሠረት ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ በሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱ አይቀር እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የሰየመው የሶማሊያና …
«ኢትዮጵያ በጋዜጦች» የተሰኘው ፕሮግራማችን ሶስት ርዕሶችን ይዞ ቀርቧል። – ኤርትራ አዲስ አበባን ባግዳድ የማድረግ እቅድ እንደነበራት ተገለጸ -የአፍሪቃ ቀንድ ረሀብ የምዕተ-አመቱ ቅሌት ሊሆን ይችላል ተባለ -የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጊቤ ሶስት ግድብ ግንባታ እንዲቆም ጠየቅ የሚሉት ናቸው
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዝግጅቶቹን እንዲቀይር ከኢትዮጵያ መንግስት የሚደርስበት ምንም አይነት ጫና እንደሌለ አስታወቀ። የሚመራው በነጻነት እንዲያገለግል በአዋጅ በተቋቋመበት ህግና በቻርተሩ ሃላፊነት መሆኑን ቪኦኤ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ላይ ያቀረበውን ክስና፣ የቪኦኤ ምላሽ፣ ከሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ጋር …
ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ፊት ቀርባ ጉዳይዋን ለማብራራት ባለፈው ሰኔ ወር በጠየቀችው መሰረት ትላንት ማክሰኞ የኢትዮጵያ፣ የሶማልያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ ተወካዮች በተገኙበትጉድይዋን ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ምክር ቤት ለማቅረብ ችላለች።ኤርትራ ብቻዋን ነበር ጉዳይዋን ለማቅረብ የፈለገቸው። ይሁና እንደ …
ኤርትራ ስለ ሶማልያ በሚደረጉ ስብሰባዎች እንዳትገኝ መታገድዋን አቶ የማነ ገብረአብ ገለጹ Read more »
ሳምንታዊው “ኢትዮጵያ በጋዜጦች” ዝግጅታችን -African Institute of Mathematical Science በኢትዮጵያ እንደሚመሰረት ተገለጸ -የአውቶብስ አገልግሎት በሀዋሳ ከተማ -በኢትዮጵያና በኬንያ የተቅማጥ በሽታ ገባ -በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ በሰሜን ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያደረሰው ጉዳት የሚሉትን ርዕሶች ይዞ ቀርቧል።
በአፍሪካ ቀንድ ከአሥር ሚሊየን በላይ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ 4 ነጥብ 5 ሰው ለረሃብ ያጋለጠ ባለፉት ስድሣ ዓመታት ያልታየ የከበደ ድርቅ መከሠቱ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቃራኒው ምዕራብ ኢትዮጵያን የከበዱ የጎርፍ ሁኔታዎች እንደሚያሰጉት ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲን የጠቀሱ የሚድያ ዘገባዎች እንደሚሉት በሃገሪቱ …
እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም …
ባለሥልጣናቱ ትናንት በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሰሉ ባለፉት ስድሣ ዓመታት ባልታየው በዚህ ድርቅ ሣቢያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከ 11 ሚሊየን በላይ ሰው አፋጣኝ የሕይወት አድን እርዳታ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት …