Share:

ለኢትዮጵያ የዛሬ አርባ አመት ነው አዲስ ህይወትና ምዕራፍ የተከሰተው፡፡ ሆኖም 1966 ዓ.ም የነገሮች ሁሉ መነሻ አልነበረም፡፡ በዛች ወቅትና አመት በተከሰተው ሁኔታ ብቻ አይደለም ወጣቱ ህይወቱን ለመስጠት የተሰናዳው፡፡ ነገር ግን የአብዮት መፈንዳት የእያንዳንዳችን የውስጥ ስሜት ስለነካ ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የማደርገው ራሴን ነው፡፡ ማህበረሰብ እንዲለወጥ የአንድ ጊዜ የጋራ እርምጃ ሳይሆን የተጠራቀመ ነገር ያስፈልገዋል፡፡ በወቅቱ ወደ 11ኛ ክፍል አልፌ ነበር፡፡ እኔ እኖር የነበረው ከአዲስ አበባ ውጭ ፍቼ ከተማ ነው፡፡ ይህም ለገጠሩ ህዝብ ቅርብ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ ቤተሰቦቼ የሀይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡ አባቴ ቄስ ነው፡፡ የአባቴ ወንድሞች፣ የአባቴ አባት፣ የእናቴ ወንድሞች፣ የእናቴ አባት…ብዙዎቹ ቄስና የሀይማኖት ሰዎችና ቤተሰብ ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው በነበረው ስርዓት የቤተ ክርስትያን ሰዎችና የመንግስት አስተዳደር ቅርብ ነበር፡፡ በመሆኑም እኔም ለሀይማኖት ቅርበት ነበረኝ፡፡ ቅረበቴ ግን ለእኔ የሰጠኝ ከስርዓቱ ጋር መሳሳብና መዋደድ አልነበረም፡፡ እኔ የቄስ ልጅ እንደመሆኔ የሀብታም ልጅ አልነበርኩም፡፡ (መቼም ዛሬ ካልሆነ ቄስ ሀብታም ሆኖ አያውቅም፡፡)
ለቤተ-ክርስቲያን ቅርብ ስትሆኑ ለጪሰኛውና ለመሬት ቅርብ ትሆናላችሁ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ‹‹እኩል ከእርስት›› የሚባል ነገር ስለነበራት ነው፡፡ እኔ ቤት ባይሆንም የአባቴ ቤተሰቦች ቤት ይህን ስርዓት በግልጽ ማየት ችያለሁ፡፡ ገና 6ኛ እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ጭሰኞች ከገጠር እህል ሲያመጡ፣ ግብር ሲበላ፣ ድግስ ሲደገስ፣ ሲስተናገድ (እንዴት ህዝብ በየ ደረጃው ይስተናገድ እንደነበር) በቅርብ ማየት ችያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ገና 6 እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ይመስለኛል ፍቅር እስከ መቃብር የታተመው፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን አነበብኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ላይ የፊውዳልና የጭሰኛውን ግንኙነት ሳነብም በስርዓቱ የተማረርኩት እኔ ብቻ አለመሆኔን አመንኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ለልቤ ጥያቄ መልስ ሰጠኝ፡፡ ከእኔው ውጭ ሌሎች ሰዎች እንደሚከፋቸው ማየት ችያለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን የጭሰኞችን ግንኙነት አይቻለሁ፡፡ አንድ ሰው ሁለት አጥር ይኖረዋል፡፡ ጭሰኞች የውስጠኛውን አጥር ከመግባታቸው በፊት ማደግደግና፣ አጋሰሶቻቸውን ማራገፍ አለባቸው፣ እህሉን ተሸክመው ለመግባት፡፡
6ኛ ክፍል ሆኜ ትምህርት ቤት ስሄድ ትንሽ ልጅ የሚመራቸው አንድ መንገድ ዳር ላይ የሚለምኑ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ እናም በዛች ትንሽ ጭንቅላቴ ብዙ አስብ ነበር፡፡ ጭሰኞቹ ሲያረጁ እንደዚህ ሰውዬ እንደሚሆኑ አስብ ነበር፡፡ ምክንያቱም ያፈሩትን እየሰጡ ነው፤ ሲያረጁ ደግሞ ከመሬታቸው ይነሳሉ፡፡ እናም ግን ለምን? ግን ለምን? ግን ለምን? የሚል ጥያቄ በብዛት በአዕምሮዬ ይመላለስ ነበር፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን እንዳገኝና እንዳነብ ያደረገኝ ወንድሜ ስለ ችግሮቹ እንድጽፍ ያደርገኝ ነበር፡፡ የተሰማኝን መጻፍ ጀመርኩ፡፡
እስከ 9ኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ ሶስትና አራት ባለ 50 ገጽ ደብተር ጻፍኩ፡፡ በ1966 የጻፍኳቸውን ደብተሮች ብቻ ይዤ አዲስ አበባ በመምጣት ንግድ ስራ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ በ1967 ዘመቻ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ዘመቻ እንደሄድኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት የማኦን ስለ ጭሰኞች የሚያወራ ‹‹The peasant uprising›› የሚለውን መጽሃፍ ነበር፡፡ ውስጤ ያለውን የሚነካ ነገር ተፈጠረ፡፡ ይህ ነገር (አብዮት) ያስፈልገናል ብዬ አመንኩ፡፡ የቄስ ልጅ፣ አክራሪ ኦርቶዶክስ ነበርኩ፡፡ ሆኖም በዘመቻው ወቅት በመጾምና ባለመጾም ተፈትኛለሁ፡፡ ወጣት ስትሆኑ ደግሞ አዲስ ነገር መቀበልና መሆን አለባችሁ፡፡ በሶሻሊዝም መጾም የለም፣ እንዲያውም በሶሻሊዝም ስም ማረድ (መባረክ) አለብን ሁሉ ይባል ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ለ6 ወር ያህል ተፈትኛለሁ፡፡ በኋላ ተሸነፍኩና ተቀላቀልኩ፡፡ ስለ ኮምኒዝም የሰማሁት 7ኛ ክፍል ሆኜ ነው፡፡ ስለቻይና ሶቬት አብዮት ነው፡፡ ኮሚኒስት ከሆንን መኪና የለም፣ ቤት የለም፣ ሱፐር ማርኬት ሄዶ መግዛት የለም፣ በካርድ ብቻ መግዛት ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ለእኔ በውስጤ የነበር ነው፡፡ የማኦ መጽኃፍና ሌሎች መጽሃፎች ሲጨመሩ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ እንደሚያስፈልጋት አመንኩ፡፡ ይህ መነሻ ሆኖ ዘመቻ ጣቢያ እያለሁ ዴሞክራሲያን ሳነባት ደግሞ ይበልጡን አመንኩበት፡፡ እንዲያውም ዴሞክራሲያን የሚጽፉት ሰዎች መላዕክት ይመስሉኝ ነበር፡፡ እስከዚያ ድረስ የሚመስጥ ጽሁፍ ነበር፡፡ ያ መመሰጥ ውስጤ ከነበረው መመሳሰል ጋር በመመሳሰሉ ነው ኢህአፓ ውስጥ ያስገባኝ፡፡ ማንም ቀስቅሶኝ አይደለም፡፡ እኩል ተቀስቅሰን እኩል መሄድ አልቻልንም፡፡ እኩል እንደ እኔ ቢቀሰቀሱም ከዘመቻ ተመልሰው ትምህርታቸውን የቀጠሉና ሌላ አቅጣጫን የመረጡ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ውስጤ ያለውን ነገር ስለነካ ነው ገብቼ የቀረሁት፡፡ ባላምንበት ኖሮ ከተቀሰቀስኩ በኋላ ቤት ስመለስ በተውኩት ነበር፡፡
1966 አብዮት በእኔ ምሳሉ ሳየው ድንገተኛ አልነበረም፡፡ የካቲት ወር በአንድ ሰልፍ ዩኒፎርም ለብሰን መንገድ ላይ ስንወጣ ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ!››፣ ‹‹እንኳን ጀግና ሆናችሁ!›› እንባል ነበር፡፡ ነባራዊ ሁኔታው፣ የኑሮ ውድነት (ከዛሬው ጋር የሚወዳደር አልነበረም) አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አባቴ በርካታ ቤተሰብን በ80 ብር ማስተዳደር ይችል ነበር፡፡ የዛን ጊዜና የአሁኑን ማመሳሰል አይቻልም፡፡ የተወደደው ቅቤ ሳንቲም ጨምሮ 3 ብር፣ ዘይት ሁለት ብር፣ ጤፍ 50 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ የ1966ቱ የኑሮ ውድነት ከዛ በፊት ከነበረው ርካሽ ኑሮ ጋር የሚነጻጸር ነው፡፡ ከድሮው ጋር ሲነጻጸር የኑሮ ውድነቱ እሳት እንደነደደ ይቆጠራል፡፡ ያ የምርት ግንኙነት፣ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ችግር ጋር ሲደማመር እንጅ ወታደሩና ተማሪው ስለተሰለፈ ብቻ የመጣ አይደለም፡፡ ያን ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ (አብዮት) ለመቀየር፣ የታክሲ ሾፌሮች፣ የወታደሩ የደሞዝ ጭማሬ፣ የሴክተር ሪቪው ተጨምሮበት 1966ን የኢትዮጵያ አንድ ምዕራፍ አደረገው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ባለመሆኑና ብዙ ስላልተሰራ ነው አብዮቱ የፈነዳው፡፡ አሁን እኮ እየተመለስን ያለነው ወደ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ቢሆን ያለምንም ውጣ ውረድ የተሳካ ስርዓት በገነባን ነበር፡፡ የከፈልነው መስዕዋትነት የማይገባ ነበር፡፡
በዘመቻው ወቅት ከአዲስ አበባ ወጥተን ገጠር በመግባታችን ለማንበብም ሆነ ለህዝብ ቅርብ መሆን ችለናል፡፡ ውስጣችን የነበረውን እምነት የቀየረው ይህ ነው፡፡ ወጣቱም አንዴ ከተነሳ መመለስ ያቃተው ለዚህ ነው፡፡ ኢህአፓ ውስጥ ስገባ ያጋጠመኝ ነገር ደግሞ በፊት ከማስበው የተለየና እምነቴን ያሳደገልኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደ ሰው አይደሉም የሚለውን እምነቴን አጠናክሮልኛል፡፡ በወጣት ማህበራት እንገናኝ ነበር፡፡ የፓርቲው ሳይሆን ኢህአወሊ (የወጣት ማህበሩ) አባል ነበር፡፡ ኢህአወሊ ራሱን የቻለ ፓርቲ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከወጣት ሊጉ ከገባሁ በኋላ ሀይለኛ ስብዕና አግኝቻሁ፡፡ ከዛ በፊት የነበረኝ አላማ ዩኒቨርሲቲ መግባት የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ፕሮፌሰር ሆኜ የምሁር ህይወት መኖር ነበር፡፡ ያ ሁሉ ህልሜ ቀርቶ ከዘመቻ ስንመለስ ‹‹ከትግል በኋላ ትምህርት›› የሚለው የወጣት ሊጉን መፈክር ይዘን ትግል ገባን፡፡ ትግሉ እየከረረ መጣ፡፡ ደም በደም ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ደም በሚኒስትሮቹ ጀመረ፡፡ በእነሱ የተጀመረው ግድያ ወደ ሌላ ግድያ ተቀየረ፡፡
ኢህአፓ ውስጥ ከገባን በኋላ የሰዎቹ መልካምነት፣ እድገት በህብረት ሄጄ የዩኒቨርሲቲ ካየሁ በኋላ ባገኘኋቸው ተማሪዎች ስብዕና በማየቴ ከውስጤ ነው ያመንኩት፡፡ ምክንያቱም ኢህአፓ የውስጣችን ስሜት ነው የነካው፡፡ ፓርቲ ውስጥ ያየሁት ደግሞ ይበልጡን ልቤን የሚሞላ ነበር፡፡፡ ለራሳችን መኖርና ስብዕናችንን መጠበቅ እንዳለብን፣ ነገር ግን ቅድሚያ ለህዝብ እድንኖር በተግባር አስተምረውናል፡፡ ኢህአወሊ እያለሁ አንድ ሰልፍ ነበር፡፡ ለማምለጥ ስንሮጥ አንድ ሰፈር ውስጥ የተደረመሰ ሽንት ቤትና ውጭ ደግሞ የሚመጥ የቆመ መኪና ላይ ደረስን፡፡ በዚህም ምክንያት አስም ተቀሰቀሰብኝ፡፡ ትንሽ እንደሄድን መራመድ አቃተኝና ተቀመጥኩ፡፡ ሌላው እየሮጠ አንድ በእድሜ የሚበልጠኝ ሰው ቆሞ ይጠብቀኛል፡፡ ‹‹ለምንድን ነው የቆምከው? አምልጥ!›› ስለው ‹‹ለምን ጥየሽ እሮጣለሁ? ይልቁን ጥቂት እርጅኝና ጥግ አስይዤሽ እሄዳለሁ›› አለኝ፡፡ ጥይት እየተተኮሰ እኔን ይጠብቃል፡፡ ይህ ድርጅቱ ለእኔ እንደሚቆም ማወቅ ስላስቻለኝ ብርታት ሰጥቶኛል፡፡ አስሙ እየባሰብኝ ሲሄድ ባልጠበኩት ሁኔታ የአስም መድሃኒት ተላከልኝ፡፡ ይህኛውም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡
ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መኖር ከባድ ሆነ፡፡ ወደ አሲምባ ለመሄድም አይቻልም ነበር፡፡ ናዝሬት ላይ አንድ ቤዝ ሊቋቋም ነበር፡፡ ያኔ ከእኛ ሰፈር ሶስት ወጣቶች ወደ ቤዙ ሊሄዱ ነበር፡፡ ግን መድረስ ባለመቻላቸው ተመልሰው መጡ፡፡ ከተመለሱ በኋላ ታሰሩ፡፡ ልጆቹ በመታሰራቸው ለእኔ ሂስ መጣልኝ፡፡ ቁጭ ብየ አነበብኩት፡፡ ሂሱም ልጆቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሚተዋወቁት ሰዎች መካከል ሊሆን እንደሚችልና፤ መረጃ ከእኔ በኩል አፈትልኮ እንደሆነ የሚያሳይ ጠንከር ያለ ሂስ ነው፡፡ እኔ የት እንደሄዱ ስላላወቅሁ በጣም አዘንኩ፡፡ መልስ መጻፍ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ እኔም ለእንዲህ አይነት ድርጅት ከሆነ አባል የሆንኩት መሳሳቴንና ከድርጅቱ እንደምወጣ ጻፍኩ፡፡ በሳምንቱ ግን የሚገርም መልስ ጻፉልኝ፡፡ መልሱ ለእኔ ለትንሹዋ ልጅ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ‹‹ተንበርክከን ይቅርታ እንጠይቃለን›› የሚል ከጸኃፊው ማብራሪያ ጋር ተዳምሮ ይቅርታ ተጻፈልኝ፡፡ ‹‹እንደ አንቺ ያለ ጠንካራ አባል ስላለን እንኮራለን›› አሉኝ፡፡ ይህም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡ ይህን የጻፉልኝ ለአባላት ትልቅ ክብር እንዳላቸው መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ሂስና ግለሂስን የተማርኩት ያኔ ነው፡፡
ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ሞቱ፣ የተረፍነው ዳንን፣ ከእስር ተፈታን፣ መኖር የግድ ነውና መኖር ጀመርን፡፡ ያ ውስጤ የነበረን አላማ የነካውን ኢህአፓና ኢህአወሊ ውለታ ተሸክሜ መኖር አቃተኝ፡፡ በእርግጥ 20ና 30 አመት አልፎታል፡፡ ያ ትውልድ የሞተው፣ እኔ ያን ሁሉ የሆንኩት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ባይሆንም በርካቶች ግን መኖር እንዳንወድ አድርገው ይወቅሱናል፡፡ በእርግጥ ስለማያውቁን ነው የሚል ጥያቄ ይመላለስብኝ ነበር፡፡ አንድ ወቅት ይህን መልስ እንዳገኝ አደረገኝ፡፡ አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት በምሰራበት ወቅት አንድ ቡድን ይዤ ለልምድ ልውውጥ ወደ ኬንያ ሄድኩ፡፡ በእረፍት ሰዓት ሰብሰብ ብለን ስናወራ ስለ ‹‹ያ ትውልድ›› መወራት ጀመረ፡፡ አጥፍተውት አለፉ እያሉ ይወቅሱታል፡፡ የአንድን ነገር ውጤቱን ብቻ አይቶ መገምገምና መውቀስ ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ትወቅሷቸዋላችሁ?›› ስለቻው፤ ‹‹አታውቂያቸውም!›› አሉኝ፡፡ ‹‹እኔን አታውቁኝም? እንዴት ነው እኔ የማላውቃቸው? ያ ትውልድ ማለት እኔ ነኝ!›› አልኳቸው፡፡ ‹‹አንቺ ምንድን ነሽ?›› አሉኝ፡፡ ‹‹ኢህአፓ ነበርኩ!››፡፡ አላመኑም፡፡ ‹‹እኔ አላማ የለኝም? ጭራቅ ነኝ? እኔ ክፉ ነኝ? እኔ ኢትዮጵያን አልወድም?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው፡፡ ‹‹አትቀልጅ! ያ ትውልድማ እንዲህ ሊሆን አይችልም›› አሉኝ፡፡ በእርግጥ በደርግ ጊዜ ሲማሩ ኢህአፓን እንደ ጭራቅ አድርገው ይስሉላቸው ስለነበር ነው፡፡ ‹‹እንግዲያውስ የጠፋው ጠፍቷል ነገር ግን አውቀን አላጠፋነውም አልኳቸው፡፡›› አንድ ነገር መለካት ያለበት በውጤቱ ብቻ አይደለም፡፡ የእኛ አጀንዳ ኢትዮጵያን ማጥፋት አልነበረም፡፡
ልጆቹን ‹‹ስለዛ ትውልድ፣ ስለ ኢህአፓ ማወቅ ትፈልጋላችሁ ልጻፍ?›› አልኳቸው፡፡
‹‹አዎ ጻፊ!››
‹‹ምን አይነት ልጻፍ?››
‹‹ትንሽ እንጨት እንጨት እንዳይል እንጅ ጻፊ!››
‹‹ምንድን ነው እንጨት እንጨት እንዳይል ማለት?
‹‹ትንሽ ፍቅር ቢጤ ጣል አድርጊበት?
‹‹እንዴ! እኛም እኮ ፍቅር እናውቅ ነበር ከየት አምጥቼ ነው ጣል የማደርገው?››
ከዛም ‹‹ምርኮኛ››ን መጻፍ ጀመርኩ፡፡ ከ30 አመት በኋላ ይህን መጽኃፍ የጻፍኩት የዛ ዘመን ፖለቲካ ስላሳመነኝ ነው፡፡ ከአንድ ነገር ጋር ለመዝለቅ ውስጣችን መነካት አለበት፡፡ ሌላ አጀንዳ ካለን፣ ሌላ የምናስበው ነገር ካለን፣ ያንን አጀንዳ ብለን የምንገባ ከሆነ በጊዜ መውጣት ነው የሚያዋጣው፡፡ እኔ የምችለውን ያህል ሄጃለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ተሂዶ ተሂዶ መዝለል የማይቻል ጎርጅ ላይ ሲደረስ የግዱን ይቆማል፡፡ ከዛ በኋላ ያ ትውልድ ለምንድን ነው ያልቀጠለው የሚለው ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የደረሰውን ስነ ልቦናዊ ችግር ሲታሰብ ከባድ ቢሆንም ከዛም በኋላ ግላዊ ህይወት ባሻገር ለአገር መስራት አይቻልም ነበር ወይ? የሚለው የእኔም ጥያቄ ነው፡፡ የትውልዱ አለመቀጠል ግን በርካታ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡
የ1966 አብዮት ሲፈነዳ ከላይ የጠቀስኳቸው እርሾዎች ሆነው አብላልተውታል፡፡ ተማሪውም ጥያቄ የጀመረው ቀደም ብሎ ስለነበረ ነው፡፡ የዓለም የፖለቲካ ሁኔታም ስላገዘው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ የ1966ን አብዮት አዲስ ምዕራፍ ቢያስከፍተውም ያ ምዕራፍ ግን መዝለቅ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም አንዳንዴ ያልታሰበ ውጤትና ስኬት ሰውን ወደ ሰማይ እንዲመጥቅ ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት መነሻን አለማሰብ ነገር ተከስቷል፡፡ ብዙ ፖለቲካ ብስለት ሳይኖር ብዙ ነገሮች ተከሰቱ፡፡ ስለዚህ የ1966 አብዮት ለውጥ አምጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም የመከነ ለውጥ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ለብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ የተሻገረ የአገር ፍቅር ሰጥቶን አልፏል፡፡ ስብዕናችንን እንድንሞርድና እንድንሻሻል አድርጎናል፡፡ እኔ ስለ እራሴ ብቻ ነው መናገር የምፈልገው፡፡ ቢያንስ እኔ አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ እንዳላጭበረብር ያደረገኝ ግን እኔ ልዩ ሰው ሆኜ ሳይሆን ያኔ የተፈተሸው ማንነቴ ይመስለኛል፡፡ እኔ ለራሴ ጥቅም ብዬ በማንም ላይ ተራምጄ አላውቅም፡፡ ዛሬ 55 አመት ያለፈኝ ትልቅ ሰው ነኝ፡፡ ግን አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ ይህን ያላደረኩት ግን የሚፈትነኝ ነገር ጠፍቶ አይደለም፡፡ ህይወትን ለማሸነፍ ይህኛውን መንገድን (ማጭበርበሩን) ብመርጥ እንደሚያዋጣኝ አጥቸው አይደለም፡፡ ግን በዛን ወቅት የተሞረደው ስብዕናዬ ዛሬም ድረስ አብሮኝ ስላለ ነው፡፡ ብዙዎቹ ይህ ስብዕና አላቸው፡፡ እናም 1966 ብዙ ሰው ፈጥሯል፣ ብዙ ሰው ገድሏል፡፡ የገደለው ግን ያመዝናል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት ሁኔታ የደረሰችው፡፡ የትም አልደረስንም፤ መዋሻሸት አያስፈልግም፡፡ ዛሬም የትም አይደለንም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ውስጥ ገብተን ካየነው ዛሬም የምንበላው የለንም፣ ዛሬም ድሃ ነን፣ እኔ በዙሪያዬ ብዙ በልተው የማያድሩ ሰዎች አሉኝ፡፡ በዙሪያየ የሚኖረው ህብረተሰብ በታክሲ መሄድ የማይችልና ድሃ ነው፡፡ ጤፍ መግዛት የማይችል ማህበረሰብ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምክንያት ከ1966 በኋላ በተከሰተው ችግር ነው፡፡ እሴቶቻችንን አጥተናል፡፡ እምነታችንን አጥተናል፡፡ ድሮኮ የእኛ ቤተሰቦች የሆነ ቦታ መሄድ ፈልገው የተሸከሙትን ነገር ቁጥቋጦ ውስጥ ደብቀው ተመልሰው ያገኙት ነበር፡፡ ይህን መጣል ነበረብን? በምን ተክተነው? መጣል አልነበረብንም፡፡ ነገር ግን እምነትን ጣልን፣ መታመንን ጣልን፡፡ አገር ባላደገበት ግን ለራሳችን ለማደግ ብንፍጨረጨርም ከመውደቅ አንድንም፡፡ አንድን ነገር ይዞ ለመዝለቅና ለመነሳሳት ከውስጥ እርሾ ታስፈልጋለች፡፡ 1966ንም የወለደው ያ እርሾ ነበር፡፡ ነገር ግን መነሻው ጥሩ አልነበረምና የተጋገረው ዳቦ ሊጥ ሆነብን፡፡ እናም እዚህ ደረስን፡፡

(ከአዘጋጁ:- ይህን ጽሑፍ ያሰናዳነው ቆንጅት ብርሃኑ ባለፈው ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝተው ለወጣት የፓርቲው አባላት የትግል ልምዳቸውን ባካፈሉበት ወቅት ከተናገሩት ውስጥ ነው፡፡)

Share:

በሴቶች የነጻነት ቀን በሴት አባላቶቻችን ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ እናወግዛለን !
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

*********************

‹‹ማርች-8›› የሴቶችን ነጻነትና እኩልት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

እንደሚታወቀው ታላቁ ሩጫ በተለያየ ጊዜ በሚካሄድበት ወቅት ተሳታፊዎች በሐገራቸው የሰፈነውን ጭቆና በመቃወም ሀሳብን የመግለጽ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን የሚያሰሙበት በመሆኑ ‹‹የብሶት መግለጫ›› መድረክ እስከመባል ደርሷል፡፡ ልክ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በእሁዱ የጎዳና ሩጫም በርካታ የሩጫው ተሳታፊዎች ይህን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የመጣውን ጭቆና በመቃወም ድምጻቸውን ሊያሰሙበት ችለዋል፡፡
በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ለህዝብ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆሙ በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተደረገውም ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡

ምንም እንኳ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ ህገ ወጥ እርምጃ አዲስ ባይሆንም በሴቶች ነጻነት ቀን በአባላቶቻችን ላይ የተወሰደው ህገ ወጥ እርምጃ አገዛዙ በህገ መንግስቱም ሆነ በሌሎች ህጎች ለሴቶች መብት መከበር የደነገጋቸው አንቀጾች ከወረቀት ያለፉ እንዳልሆኑ በተጨባጭ ያሳየ ምሳሌ ነው፡፡ ከምንም በላይ አባላቶቻችን የታሰሩበት ምክንያት ‹‹የጣይቱ ልጅ ነን፣ የምኒልክ ልጅ ነን›› ማለታቸው እንደሆነ በመርማሪ ፖሊስ የተገለጸላቸው መሆኑ ነው፡፡

ይህም ህወሓት/ኢህአዴግ ምን ያህል ከታሪክ ጋር የተጣላ መሆኑን ከማሳየቱም በተጨማሪ አባላቶቻችን ለማሰር አሳፋሪ የሆኑ ምክንያቶች እየፈለገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህኛውን እርምጃ የተለየ የሚያደርገው ሰማያዊ ፓርቲ በመላው አገሪቱ መዋቅሩን እያደራጀና ህዝብን ከጎኑ እያሰለፈ ባለበት ወቅት መሆኑ፤ የህዝብ ድጋፍ የሌለው ገዥው ፓርቲ በሰበብ አስባቡ ሰማያዊ ፓርቲን ከወዲሁ ለማዳከም የወሰደው ነው፡፡

በተለይ የምርጫ ወቅት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ይህን ህገ ወጥ እርምጃ መውሰዱ አሁንም ቢሆን የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ እንደሄደ ያሳያል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መቼም ቢሆን ይህንና መሰል የአገዛዙን አፈናዎች አጥብቆ የሚያወግዛቸውና የሚታገላቸው መሆኑን እየገለጸ በሴቶች የነጻነት ቀን ያላአግባብ የታሰሩ አባላቶቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል፡፡ ኢትዮጵያውያንና መላው የዓለም ማህበረሰብ ይህን ህገ ወጥ እርምጃ ተመልክቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Share:

ዛሬ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችና አባሎች ለመጋቢት 5 ተቀጠሩ
እሁድ ለት በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ላይ ለነፃነት እንሩጥ በሚል መርህ በሩጫው ላይ በመሳተፍ በርካታ ፖለቲካዊና መሀበራዊ ጥያቄዎችን ያነሱ የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊዎችና አባላት እንዲሁም ሰፍራው ንበረቶ ነን ቻቸውን ይዘው የነበሩ ሁለት የፓረቲው ከፍተኛ አመራሮች እና አንድ አባል ታፍሰው ወደ ሾላ የካ ፖሊሰ መምሪያ መወሰዳቸው ይታወቃል ፡፡

በዛሬው እለትም ፍርድቤት ቀርበው የተከሰሱበትን ምክንያት መርማሪ ፖሊሱ /ኮማንደር የማታ/አብራርቷል፡፡ የተከሰሱበት ምክንያት እሁድ በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ላይ ተመሳስሎ በመግባት የጣይቱ ልጆች ነን ፣ የምኒልክ ልጆች ነን ፣ ኑሮ መረረን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ በሚል ሁከትን ለማነሳሳት ቀስቅሳችኋል የሚልኘ ሲሆን መርማሪው መረጃ አሰባስቤ ስላልጨረስኩና መረጃዎቼን ያጠፋሉ ሰዎችንም እንዳይመሰክሩ ያስፈራሩብኛል በተጨማሪም ብዙዎቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ስለሆነ መረጃ እስካሰባስብ የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮችም እድል እየጠየቁ ለማስረዳት ጥረት ያደረጉ ሲሆን የተከሰሱበት ምክንያት ሀሳባቸውን በአጋጣሚው በነፃነት በመግለፃቸውና በተባለው መልኩ ሳይሆን አስበው እና ሩጫውንም እንደማንኛውም ሴት ኢትዮጵያዊ ቲሸርት ገዝተውና ተመዝግበው ሲሆን አሉ የተባለውን እንዳሉ አስረግጠው ነገር ግን ሁከት አለማስነሳታቸውንም እንዲሁም ሩጫው ሲጠናቀቅ አፍሰው እስርቤት እንደወሰዷቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አብረው የታሰሩት ወንዶችም በወቅቱ በቦታው የጓደኞቻቸውን እቃዎች ተሸክመው ሩጫውን እስኪፈፅሙ እየጠበቁ በነበረበት ሰዓት ሴቶቹን እየለቀሙ ሲወስዱ ለምንድነው የምትወስዷቸው በማለታቸው ብቻ አብረው እንደታሰሩ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አክለውም እኛ ህጋዊ ሰውነት ያለን የፓርቲ አመራሮችና አባላት ነን ስራችንም በዚሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ሳለና በተፈለግን ጊዜ የምንገኝበት ግልፅ አድራሻ በምርመራ ወቅት ተመዝግቦ እያለ ዋስትና አይሰጣቸው የተባለው ተቀባይነት የለውም እንዲሁም መረጃ ላሰባስብ የሚለውም ምክንያት ሁሉም ንብረቶቻችን በወቅቱ ተወስደው በፖሊሶች እጅ የሚገኝ ስለሆነ ተገቢ አይደለም በሚል ፍርድ ቤቱን ሞግተዋል፡፡
ክሱን የሚመራው ኮማንደር ይህን በማስተባበል የዋስትና መብታችን ይከበር ማለታቸውን “ፍርድ ቤቱ እንደሚያውቀው በሀገሪቱ ያለው ነገር የታወቀ ነው የአሸባሪዎች ስጋት አለ እና ከዛ ጋር የሚተባበሩ ተልዕኮ ያላቸው ስለሆኑ ለማጣራት ጊዜ ያስፈልገኛል” በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲነሳ ጠይቋል፡፡
በመጨረሻ ዳኛው ኮማንደሩ ይህን ለማጣራት የጠየቀው ጊዜ የተንዛዛ ስለሆነ በአምስት ቀን ውስጥ አጣርቶ ለአርድ መጋቢት 5 እነዲቀረቡ አዞአል ለታሰሪዎቹም ፓርቲው አሰፈለጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በሀገር ወሰጥ ሆነ ከሀገር ውጭ ሆናችሁ ደጋፍ ላደረጋችሁልን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

Share:

today’s 5000 meter running event ended dramatically.
In a major show of force, dozens of Addis Ababa police officers in riot gear arrested the Blue Party Women Groups who were shouting that political prisoners must be released. These young women were demanding for the release of journalists and political prisoners.

The women were shouting “Release Reeyot Alemu!!” .. “Release the Journalists!!”… “Release all political prisoners!!”

The police arrested dozens of these women who all are members of the Blue Party. Some of these are members of the Executive Committee of the Blue Party. They have been interrogated and assaulted for they supported the peaceful struggle of the women form the Blue Party in the rally!

Here are names of the ladies and executives of the party still arrested:-

Woyinshet Molla
Woyni Niguse
Nigest Wondifraw
Meron Alemayehu
Emebet Girma
Metasebiya Tekle

Getaneh Balcha (Head of Organizational affairs)
Brhanu Tekleyared (Head of Public Relations)
Abel Ephrem (member of Public Relations committee)

The other two women who were leading the protest namely Eyerus Tesfaw and Elsabeth Wessna are still not found and no one knows where they are taken.

Share:

ስለ ወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደትና ትብብር በስፋት አትታለች

አድዋን ዘክራለች!

ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ በታሰበው መሬት ህጋዊና ፖለቲካዊ ትንታኔዎች ተሰጥቶባታል

ኢትዮጵያ ለምን ወደ ኋላ እንደቀረች ተተንትኖባታል

ስለ አገራችን የምርጫ ፖለቲካና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮችም አካትታለች
Neger Ethiopia Issue 2 In PDF

Share:

በመስክ ጉብኝት፣ አደረጃጀቶቻቸውን በማጠናከር ላይ የነበሩት ከአዲስ አበባ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ከአንድ ቀን እስር በኋላ ዛሬ ጠዋት ቢፈቱም የወላይታ ዞን የፓርቲው ተወካዮች ግን አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የተፈቱት የፓርቲው አመራሮችም ቢሆን ቀጣይ መዳረሻቸው ወደሆነችው አርባ ምንጭ እንዳይንቀሳቀሱ ከመከልከላቸውም በተጨማሪ የስራ ሰነዶቻቸውን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶቻቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር በመሆናቸው ከመንቀሳቀስ እንዳገዳቸው በእስር ላይ የነበሩትና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከወላይታ ሶዶ ወደ አርባ ምንጭ በማቅናት ላይ እያለ የከተማው ፖሊስ ‹‹በመሳሪያ ዝውውርና በሽብርተኝነት ጠርጥረናችኋል›› በሚል ከህዝብ ማመላለሻ መኪና አስወርዶ እንዳሰራቸው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩ በኋላ እንግልት የደረሰባቸው ሲሆን ‹‹ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት የፖሊስ አዛዦች ስራ ላይ ነን በሚል ባዶ ሜዳ ላይ ዝናብ ሲያስመቱን አምሽተዋል›› ብለዋል፡፡ በትናንትናው እለት ምግብና ጠያቂ መከልከላቸውን ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወቃል፡፡
አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ለእስሩ እንደምክንያት ካነሳቸው ነገሮች መካከል ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ አገር ተቃውሞ የማይታሰብ ነው›› የሚል እንደሚገኝበት ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ ለከተማው ፖሊስ ጣቢያ ማንነታችን ገልጸን ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት በአግባቡ ሊያነጋግሩን ባለመቻላቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ የወላይታ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ለሊሼ ኦንን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ማግኘት ብንችልም ጋዜጠኞች መሆናችንን ሲያውቁ ስብሰባ ውስጥ መሆናቸውን በመግለጽ መረጃ እንደማይሰጡን ገልጸውልናል፡፡ ይሁንና ለኢንስፔክተሩ በምንደውልበት ወቅት ኃላፊው ስብሰባ ላይ አለመሆናቸውንና በአቅራቢያቸው እንደሚገኙ የልዑካን ቡድኑ ገልጸውልናል፡፡

Share:

ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር እንዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር ገምግሞ መፍትሄ መስጠትም አንዱ ሌላው የጉዞ አላማው ነው፡፡
የመስክ ጉበኝቱ በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡

ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ሰማያዊ ከድሬዳዋ ከተማ ህዝብ ጋር ተወያየ

*‹‹ወደ ድሬዳዋ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፤

ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡

በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተመለከተ ‹‹በኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ፓርቲያችን በግለሰብ ነጻነትና መብት ያምናል፡፡ ምክንያቱም የግለሰብ መብት ከተከበረ የቡድን መብትም አብሮ እንደሚከበር እናውቃለን፡፡ እስኪ ለአብነት የግለሰብ መብት ተከብሮ የቡድን መብት የማይከበርበት ሁኔታ ካለ እናንሳ…የለም፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በግለሰብ መብት መከበር ከሆነ የቡድን የሚባሉ መብቶችም አብረው መከበራቸው እሙን ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹ሞደሬት ሊብራሊዝም› አይዶሎጅን እንደሚያራምድ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የመሬትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ መነሻነት የተቃኙ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ አብሮ በመስራትና በትብብር ያምናል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ምርጫ ሲደርስ እንደሚደረገው በሩጫ ወደ ውህደት ለመግባት አንፈልግም፡፡ ካለፉት የሌሎች ተሞክሮዎች ብዙ ተምረናል፡፡›› ብለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ድሬዳዋ በነበረው ቆይታ በዚያው የከፈተውን ቢሮና የአካባቢውን መዋቅር የማስተዋወቅና የማጠናከር ስራም ሰርቷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share:

እሁድ የካቲት 16 ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ በሳምራት ሆቴል ከራስ ሆቴል ፊት ለፊት – ከዚራ
ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በፓርቲው ዓላማና ፕሮግራሞች ላይ ህዝባዊ ውይይት ያካሄዳል

አዘጋጅ የድሬደዋ ዞን ሰማያዊ ፓርቲ ማስተባበሪያ መዋቅር!

Share:

በክፍል.1 ላይ ቃል በገባሁት መሰረት ዛሬ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት ስር ሆኜ «ስለነዚያ» ወጣቶችና በዙሪያቸው ስለነበሩ የአርበኝነት ተጋድሎው አጋሮች በጥቂቱ አወሳልሃለሁ፡፡ አዎ፣ ዛሬ ስለ የካቲት 12 ቀን፣ በዋነኛነትም ስለ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስግዶም እንዲሁም ሌሎች ከጉዳዩ ጋር የተገናኙ የታሪኩ ዋና ዋና ተዋናዮችና ነጥቦችን እያነሳን እንጥላለን፡፡

የካቲት 12/1929 ዓ.ም የአዲስ አበባ ህዝብ የግፍ እልቂት በተነሳ ቁጥር ሞገስ አስግዶም እና ጓደኛው አብርሃ ደቦጭ አብረው ይነሳሉ፡፡ ሁለቱም ወጣቶች የኤርትራ ተወላጆች ናቸው፡፡ ሁለቱም ከኤርትራ ወደ አዲስ አበባ በጣሊያኖች አማካኝነት እንዲመጡ ከተደረጉ በሗላ ሞገስ በዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት፣ እንዲሁም አብርሃ በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገብተው መማር ቀጠሉ፡፡ እዚህ ላይ መረሳት የሌለበት ነጥብ ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ የመምጣታቸው ምስጢር ለፋሽስት ጣሊያን አስተርጓሚና ሰላይ ሆነው እንዲያገለግሉ ታስቦ እንደነበር ነው (ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛ፣ እንግሊዝኛና በመጠኑ ጀርመንኛ እንዲሁም የሀገሬውን ቋንቋ ይናገሩ እንደነበር ተጠቅሷል)፡፡

በሌላ ወገን ደግሞ የወጣቶቹን ወደ አዲስ አበባ መምጣት በወቅቱ በፋሽስት አስተዳደር ስር በነበረችው ኤርትራ ያለውን ጭቆና ገፊ ምክንያታቸው እንደነበር የሚጠቅሱ አሉ፡፡ በተለይም ወጣት ሞገስ ኢትዮጵያን አብዝቶ ይወድና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ነበር፡፡ ስለሆነም ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት የዘወትር ፍላጎቱ ሆኖ ቆይቷል፤ «ሞገስ ጣሊያንን ሳያስፈቅድ የቅኝ ግዛት ድንበር አቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ ገባ» እንዲል፡፡ ኸረ እንዲህም ተመስክሮለታል፤ «His heart and mind was for Ethiopia.»፤ ከዚህ ነጥብ መረዳት እንደሚቻለው ኢትዮጵያ በህልሙም በእውኑም ሞገስ ውስጥ ነበረች፡፡

ሞገስና አብርሃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ሞገስ በመሬት ይዞታ መስሪያ ቤት ጸሐፊ ሆኖ ሲቀጠር አብርሃ በበኩሉ በጣሊያን ሌጋሲዮን ተቀጥሮ መስራት ቀጠሉ፡፡ በጊዜው በጣሊያን ፖለቲካ ውስጥ ከሞገስ ይልቅ አብርሃ ብዙ ስራዎች ሲሰራ ነበር፤ ሞገስ ባብዛኛው የአብርሃ ረዳት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የካቲት 12/ 1929 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ (ያኔ ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት) በግራዚያኒ ላይ አብርሃና ሞገስ ቦምብ ጥለው አቆሰሉት ከመባሉ በፊት በጣሊያን ላይ አኩርፈው ተቀምጠዋል ከተባሉ መኳንንት ጋር ወጣቶቹ ምስጢራዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በነገራችን ላይ የካቲት 12 ግራዚያኒንና ሌሎች የፋሽስት ወታደራዊ ባለስልጣናትን ለመግደል በተሸረበው ሴራ ዋና ተዋናዮቹ ሞገስና አብርሃ ብቻ አልነበሩም፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በእለቱ ለተፈጸመው ጸረ ፋሽስት ድርጊት ከጽንስሱ ጀምሮ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስማቸው ይነሳል፡፡ እነዚህም ቀደም ብለን የጠቀስናቸው ሞገስና አብርሃ፣ በመምህርነት ሞያ ይሰራ የነበረው ስብሃት ጥሩነህ፣ ስምዖን አደፍርስ፣ ቤጅሮንድ ለጥይበሉ ገብሬና ባሻህውረድ ሃብተወልድ ነገሩን አውጥተው አውርደው ጥቃቱ እንዲፈጸም ታትረዋል፡፡ (ስምዖን አደፍርስ እነ አብርሃን ከጥቃቱ በሗላ በታክሲ በመሸኘት እንዲሸሹ ያስቻላቸው እሱ መሆኑን ስላሴ ካቴደራል በሚገኘው የመቃብር ስፍራው ላይ የሰፈረው ጽሑፍ ይናገራል፡፡)
የሚገርመውና የሚደንቀው ግን ስደት ላይ የነበሩት ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በሴራው ላይ እጃቸው ነበረበት መባሉ ነው፡፡

ስደተኛው ንጉስ በየካቲት 12ቱ ሴራ እቅድ እጃቸው እንደነበረበት የሚጠቅሱት ወገኖች የሚያነሱት ነጥብ ንጉሱ ከቤጅሮንድ ለጥይበሉ እና ባሻህውረድ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ማድረጋቸውን ነው፡፡ ዝርዝር እቅዱንና አፈጻጸሙን ሁሉ ያውቁ ነበር ባይባልም እነ ቤጅሮንድ ለጥይበሉ ከእነ አብርሃ ጎን እንዲቆሙ ግን ድጋፋቸውን አሳይተው እንደነበር ታውቋል፡፡

ማይጨው ላይ ዘምተው ድል መሆናቸው የማይቀር መሆኑን የተገነዘቡት ንጉሰ ነገስቱ ሸሽተው ወደ አውሮፓ ቢሰደዱም ትግላቸው ግን አልተገታም ነበር፤ በተለይ በዲፕሎማሲው መስክ፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ንጉሱ እንግሊዝ ሎንደን ሆነው አርበኞችን በመደገፍና ምስጢራዊ ግንኙነት በማድረግ ወራሪው ፋሽስት የኢትዮጵያ ቆይታው በአጭር እንዲቀጭ ሚናቸው የላቀ ነበር፡፡
አሁንም የሰማዕታት ሐውልቱ ስር ነን፡፡ ድጋሜ ላስታውስህ፤…ሞገስና አብርሃ ቦምብ በጣሉበት አዲስ አበባ ብቻ 30,000 ህዝብ የፈጀ ጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል፡፡ ቀጥሎም አብርሃና ሞገስ ሸሽተው በሄዱበት ደብረሊባኖስ ገዳም በተመሳሳይ ግንቦት 12 ቀን ብዙ ህዝብ ተጨፍጭፏል፡፡ በሗላም ሰሜን ሸዋ ወደነበሩት የተባበሩት አርበኞች ግንባር ይዞታ በሄዱ ጊዜ አንዳንዶቹ በሰላም ሲቀበሏቸው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምን እንደሚሰራ በቂ መረጃ እንደነበራቸው የሚታወቀው እነ ሻለቃ መስፍን ስለሺ እና ባላምባራስ አበበ አረጋይ ግን ወጣቶቹን እንዲታሰሩ አደረጓቸው፡፡
እነሞገስ ከእስር እንደተፈቱ ሀገር ጥለን ወደ ጠረፍ እንሄዳለን ብለው ምክንያት ከመስጠታቸው በቀር በትክክል ወደየት እንደሄዱ አይታወቅም የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከእስር እንደተለቀቁ ወደ ዳር ሀገር በመሸሽ ላይ እያሉ ቋራ ላይ እንደተገደሉ ይናገራሉ፡፡

የግራዚያኒ የጭፍጨፋ ትዕዛዝ መነሻ «እነ አብርሃ ቦምብ ወርውረውብኝ ሲሄዱ ህዝብ ወንጀለኞችን በዝምታ ከመመልከቱም በላይ ትብብሩን አሳይቷል» የሚል ነበር፡፡ በጊዜው ግራዚያኒ ወጣቶቹ የሚገኙበትን ለጠቆመ እስከ 10,000 ማሪያ ትሬዛ ብር ለመስጠትም ቃል ገብቶ ነበር ይባላል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ሰላማዊውን ህዝብ በጥይት፣ በአዷማ፣ በገጀራ፣ በአካፋ፣ በመጥረቢያ… በአውሬያዊ ጭካኔ ከማንኮት አልተመለሰም፡፡
ወራሪው ጣሊያን የፈጀውን ህዝብ ስንመለከት አስከፊነቱ በቁጥር ብቻ የሚገለጽ አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያ ባለ በሌለ አቅሟ ውጭ ሀገር ድረስ ልካ ያስተማረቻቸው ውድ ልጆቿ በፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ጠፍተዋል፡፡ እንዲያውም በወቅቱ አንድ የተማረ ትውልድ «ሙሉ ለሙሉ» ወድሟል ይባላል፡፡ ይህም ሀገሪቱን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላት መገመት ትችላለህ፡፡

የፋሽስት ግፍ ሌላም ታሪክ እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡ አዎ፣ ከዚህ የጭፍጨፋ ታሪክ አንድ አመት ቀደም ብሎም ጣሊያን አቡነ ጴጥሮስን በግፍ መግደሉ ይታወሳል፡፡ በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤት አጠገብ በጥይት ተደብድበው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን ህዝብ ለአርበኝነት ያነሳሱና ለፋሽስት መገዛትን ያወግዙ የነበሩ ጀግና አባት ነበሩ፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ምክንያትም አቡኑ ለይስሙላ በተሰየመ የፋሽስቶች ችሎት ቀርበው የመሐል ዳኛ በነበረው ጣሊያናዊ ዳኛ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

«ካህናቱም ሆነ የቤተ ክህነት ባለስልጣኖች፣ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም ጭምር የጣሊያንን መንግስት አሸናፊነት አምነውና አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመጹ? ለምንስ ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?»
አቡነ ጴጥሮስ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ «አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ሃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለሀገሬና ስለቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፤ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ተከታዮቼን ግን አትንኩ» በማለት ተናገሩ፡፡ (በነገራችን ላይ ግብፃዊው አቡነ ቄርሎስ በየካቲት 12ቱ ጥቃት ወቅት ከግራዚያኒ ጎን ነበሩ፤ በዚህም በቦምብ ፍንዳታው ቆስለው እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡)

አቡነ ጴጥሮስ እንዳሉትም ሆነ፤ ፋሽስት ቀድሞውኑ አቡኑን ለመግደል ወስኖ ስለነበር የአዲስ አበባ ህዝብ መቀጣጫ እንዲሆነው ግድያው ሲፈጸምባቸው እንዲመለከት በማድረግ አረመኒያዊ እርምጃውን ወሰደባቸው፡፡ አቡኑም ከመሞታቸው በፊት የኢትዮጵያ ህዝብና መሬት ለፋሽስት ጣሊያን እንዳይገዙ አወገዙ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ የፍቼ ቀዬ ያፈራቸው ድንቅ አርበኛና የቤተ ክርስቲያን አባት ነበሩ፡፡
ከዚህ ጋር በተገናኘ ሌላ ነገር እናስታውስ፤ ስመጥሯ ሴት አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ በጣሊያን ሰዎች ተይዘው ወደ አዚናር ተወስደው ታስረው ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለበትን የነጻነት ትግል እና መስዋዕትነት ለመመስከር የቆመው ሐውልት ስር ሆኜ ታሪካቸውን ሳወሳ ለአሁኑ ማንነቴ የዋሉልኝን ውለታ እውቅና በመስጠት ነው፡፡ አቤት፣ ነጻነት ዋጋዋ ብዛቱ! አቤት፣ ኢትዮጵያዊነት እና የአልገዛም ባይነት ስሜት የተቆራኙበት ሲባጎ ጥንካሬ! በል ለእነዚህ ሰማዕታት የከበረ ምስጋና እናቅርብ….የወደቁላትን ሀገር መልካሙን ብቻ ልናደርግላትና ነጻነቷን ልንጠብቅ ቃል እንግባላቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ የተሰዋችሁ ሁሉ ክብር ለእናንተ ይሁን!

(የቀዳማዊ ሃይለስላሴን ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ፣ የፋንታሁን እንግዳ ታሪካዊ መዝገበ ሰብ፣ የኢያን ቻምቤል «Ethiopia 1937: The Plot to Kill Graziani» እና የአምስቱ የመከራ አመታት አጭር ታሪክ የተሰኙ መጽሐፍትን መረጃ ተውሸባቸዋለሁ፤)

Share:

ክፍል.1
በላይ ማናዬ

ስድስት ኪሎ አደባባይ የካቲት-12 ሰማዕታት ሐውልት ሥር ሆኜ ያን ዘመንና የወቅቱን አሰቃቂ ድርጊት ባሰብኩ ጊዜ ስቅጠት ተሰማኝ፡፡ የቆመው ሐውልት ማንን ለመዘከር እንደተጀነነ ባወኩ ጊዜ ደግሞ አንገቴን ቀና አድርጌ እኔም እንደ ሐውልቱ መጀነን ከጀለኝ፡፡ እናማ ሐውልቱ ሥር ሆኜ….ስሜቴ ዝብርቅርቅ ነው፤ ቋንቋዬ ብዙ ነው፤ መንፈሴ ጠንካራ ሐዘኔ መራራ ነው፤ ምናቤ የኋሊት ጎታች ምኞቴ ወደ ፊት ሸምጣጭ ነው፤ ሐውልቱ ለኔ የውስጠቱን ይገልጥልኛል፤ ታሪኩን ይነግረኛል….የተጋድሎ ታሪክ ይተርክልኛል፡፡

እንዲህ እያለ….
የካቲት 12 ከመባቱ በፊት የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ሌሎች መምጣት ያለባቸውና መገኘት የሚችሉ ሁሉ በዚህ በስድስት ኪሎ እንዲሰባሰቡ ጥሪ ቀረበ፡፡ እምቢልታ ተነፋ፤ ስማ በለው ተለፈፈ፤ ነጋሪት ተጎሰመ፤ ጥሩምባ ከወዲህም ከወዲያም አምባረቀ፡፡ ጥሪውን የሰማው ወገን ሁሉ በዕለቱ ለት ከተተ፡፡ የጥሪው መነሻ ፋሽስት ጣሊያን ሀገራችንን ከሞላ ጎደል ድል አድርጋ አዲስ አበባ ላይ ከከተመች ወዲህ መሪ ነኝ ባዩ ማርሻል ሮዶልፍ ግራዚያኒ «ሰርግና ምላሽ» የሚያደርግ መሆኑ ነበር፡፡ በዕለቱ የሮማ መንግስት ልዕልና እና የልጇ ልደት የሚዘከርበትም ጭምር ነበር፡፡

እናም ህዝብ አዳሜ ስድስት ኪሎን በዕለተ ሚካኤል አጥለቀለቀው፡፡ ህጻኑ፣ አዛውንቱ፣ ወጣቱ፣ ቆነጃጅቱ፣ ባንድ ቦታ ታደመ፡፡ ግራዚያኒ በጠባቂዎቹ ታጅቦ ግብር ለማብላት የንግስናው መንበር ላይ ተቀመጠ፤ ሰገነቱ ላይ ተንቆራጠጠ፡፡ ነጭና ሐበሻ ድምበር ለይቶም ቢሆን ተቀራርቦ የበረታው ቆሞ፣ የደከመው ተቀምጦ ሁኔታውን ያጤን ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ፈረሰኞችም አለፍ አለፍ ብለው ይታያሉ፤ ባንዳዎችም ሲያሸረግዱ የጉድ ነበር፡፡

ሰርግና ምላሹ ተጀምሮ ጥቂት ነገሮች በሰላም ከሄዱ በኋላ አካባቢው ተረበሸ፤ ከዚያ በሗላማ….
* * *
ሐውልቱ ሥር ሆኜ ታሪኩን አጣጣምኩት፤ ወደ ህይወት መለስኩት፤ ጊዜውን ጎትቼ አሁን ላይ አጫወትኩት፡፡ እናም እነዚያ ወጣቶች በሐገር ፍቅር ሲነዱ አየኋቸው፤ የወገን ጥቃት ሲያንገበግባቸው ተመለከትኩ፤ አውጥተው አውርደው መክረው ዘክረው ስለወሰኑት ውሳኔ አሰላሰልኩ፡፡ ውሳኔያቸውን የሚተገብሩበት ሰዓት ሲደርስ ተሰማኝ፤ ኢትዮጵያዊነት ወኔያቸው ወደ ፊት ሲገፋቸው፤ እምቢ ለሀገሬ ብለው ሲሸልሉ በውስጣቸው ሰመጥኩ፡፡
ባቀዱት መሰረት ወደ ተሰበሰበው ህዝብ ዘልቀው ገቡ፤ የያዙትን ነገር ደብቀው ወደ ግራዚያኒ እና ጠባቂዎቻቸው በቻሉት መጠን ተጠጉ፤ የወራሪዎች ትዕቢትና ንቀት ካሰቡት በላይ የሆነ መሰላቸው፡፡ የተሰበሰበው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለበትን ስሜት አጤኑ፤ ከፋቸው! አዎ፣ ሀበሻ የበላይነት ተወስዶበታል፤ ችግረኛ ተምበርካኪ ሆኖ ታያቸው፡፡ በዱር በገደሉ ከወራሪው ጋር የሚፋለሙትን አርበኞችም አሰቧቸው፤ ልባቸው ደነደነ፡፡ በገጠር የሚፋለሙትን አርበኞች ማገዝ፣ መተባበር አለባቸው፡፡ ስለዚህም ያቀዱትን ሁሉ ዛሬ የካቲት 12 ቀን በግራዚያኒ ላይ መፈጸም አለባቸው፡፡

ሰዓቷ ደረሰች፤ የያዙትን የእጅ ቦምብ ፈቱት….ወደ ኢላማቸውም ሰነዘሩት! ግ…ር!….ሽብ..ር…..ሽብርብር! ምስቅልቅል! የድርጊቱ ፈጻሚዎች ወዲያውኑ አካባቢውን ከግርግሩ መሐል ገብተው በመሹለክለክ ተሰናበቱ፡፡ ግራዚያኒ በጥቃቱ ቆስሎ ተንገዳገደ፤ ጠባቂዎች ተረባበሹ፣ ቆሰሉ፣ ሞቱ…የአለቃቸው መጎዳትም ጎዳቸው፡፡
ግራዚያኒ ትዕዛዝ አስተላለፈ፤ «ይሄን ሐበሻ በሉት፤ እረዱት!!»
ወዲያው የፋሽስት ሰይፍ ተመዘዘ፡፡ የሚካኤል ሰይፍ ግን ተጠቂዎችን ለማዳን ሰገባውን ሾልኮ አልወጣም ነበር፤ የካቲት 12…ዕለተ ምካኤል በአዲስ አበባ መርገምት ወረደ፡፡ ውጥንቅጡ የወጣ ነገር….. የህጻናት ዋይታ…የእናት እሪታ…..የባንዳ ሽለላ…..የፋሽስት ጥይት ጨኸት….የአዛውንቶች እግዚኦ…..የእግሬ አውጭኝ ሩጫ…..የታጣቂ ጡጫ….የፈረሶች ርግጫ….የቀሳውስት ከንቱ ምልጃ…..የቆነጃጅት መቅበዝበዝ…..የጎልማሶችና ጎበዛዝት መደንዘዝ…ኦህ! ያማል!
የደም ጎርፍ….የተቀላ አንገት….የተቦደሰ ታፋ…..የተጎለጎለ አንጀት….የተቆረጠ እጅ…..የታረደ ጉሮሮ….የተገመሰ ጭንቅላት…..የተቆራረጠ ጣት…..የሚያቃስቱ ነፍሳት…..የተጋደመ ሬሳ….የተነባበረ የሰው ልጅ ክምር…..የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትንቅንቅ…..የውስጥ አርበኞች ሽምቅ…..በደም ስካር….በግዳይ ሽለላ….ተጨማሪ ነፍሳትን ለመንጠቅ መታተር….ሐበሻን የመጨረስ ሩጫ…..እድሜ፣ ዖታ፣ እቴ…አባቴ ሳይሉ በያዙት መሳሪያ ማንከት….መሰየፍ….መቀልጠም….መረሸን…..አቤት ጭካኔ!! አቤት የግራዚያኒ ጭካኔ! አቤት አረመኔነት!

የሺዎች ጩኸት፣ የሺዎች ዋይታ፣ የሺዎች መሰዋት፣ የሺዎች እልቂት….መች በዚህ አበቃ፡፡ ግራዚያኒ ህክምናውን ተከታተለ፤ ሐበሻ ግን ጥራሞቱ እየተደመጠ፣ ማቃሰቱ እየታዬ፣ እስትንፋሱ እየተፈተሸ እንዲጨረስ ተደረገ፡፡ ግራዚያኒ እልቂቱን ባዬ ጊዜ ደስ አለው፤ እርካታ ሊያገኝ ግን አልቻለም፡፡ ስለዚህም ጭፍጨፋው ለሶስት ቀናት እንዲቀጥል አዘዘ፤ ገዳማት እንዲወድሙ መመሪያ ሰጠ፡፡
አዲስ አበባ በደም ጨቀየች፡፡ ስድስት ኪሎ በደም ጎርፍ ተጥለቀለቀች፡፡ ኢትዮጵያ ወገቧን በገመድ አስራ አዘነች፤ እምምም ብላ ወደ ፈጣሪ ተመለከተች፤ አንገቷን ከመድፋት ይልቅ ቀና ብላ ፈጣሪ ያለበትን ሰማየ ሰማያት አየች፡፡ ፋሽስትም አንገት ከመድፋት ይልቅ ቀና ማለትን የሐበሻ ይትብሓል ባዬ ጊዜ ፍርሃት ናጠው፤ የሀበሾች ንግርት ‘ስታጠቃኝ ጠንክሬ እዋጋሃለሁ’ የሚል ሆነበት፡፡ አርበኞችን ባሰበ ጊዜ የእንሺርት ውሃው ፈሰሰ፡፡

እነዚያን ጥቃት ፈጻሚ ወጣቶች ክፉኛ ኮነናቸው፤ የሮማን ሃያልነት መቀበል አንሻም ብለው «ኢትዮጵያ!!» ያሉትን ጀግኖች በአዕምሮው አመላልሶ አያቸው፡፡ የምር ቆራጦች ናቸው! የምር አርበኞች ናቸው! የምር ኢትዮጵያዊያን ናቸው! የምር አድዋ ላይ የግራዚያኒን አባቶች ያንበረከኩት ልጆች ናቸው!

ግራዚያኒ ስለነዚህ ወጣቶች በቀል በአዲስ አበባ ያደረገውን ተዘዋውሮ ተመለከተ፤ በእብሪት የተሞላው ልቡ ቅንጣት ታህል ሀዘን አልተሰማውም፤ እንዲያውም «በግዳዩ» ላይ በንቀት ምራቁን ጢቅ አደረገ፡፡ በሰማዕታት በድን ላይ በመኮፈስ ተራመደ፡፡

ግራዚያኒ የመግደል ሙከራ የተደረገበትን ስድስት ኪሎ ተመለከተ፡፡ የሬሳ መዓት አንዱ በአንዱ ላይ ተነባብሯል፤ እናት ልጇን እንደያዘች ባፍጢሟ ተደፍታለች፤ ጎልማሶች እጆቻቸውን ለጡጫ እንደጨበጡ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተጋድመዋል፡፡ ግራዚያኒ እነዚህን መሰል ሬሳዎች ሲያይ እንደገና ደም ደም ይሸተዋል፡፡ ትንሽ አለፍ ሲል ደግሞ ሽለላ ላይ የነበሩ አዛውንቶች አፋቸውን ከፍተው ወድቀዋል፤ «አድዋ!!» ሲሉ እንደነበር እያሰበ በንዴት ይተክናል፡፡

ግራዚያኒ የባንዳ ሬሳ ሲመለከት ብቻ ሳቁ ይመጣበታል፤ እንዴት እርስ በእርሳቸው እንዳገዳደላቸው እያሰበ ይረካል፤ ባንዳዎች ሀገራቸውንና ወገናቸውን ከድተው ለሱ በማደራቸው ይንቃቸዋል፤ ፍርፋሪ ለመለቃቀም ሲሉ ከጎኑ ስለሆኑ ከሰውነት ተራ ያስወጣቸዋል፤ ጀግንነታቸው የፈሪ ጀግንነት እንደሆነ አድርጎ ያስባቸዋል፤ በህይወት ባሉ ባንዳዎች ዘንድም ትዝብት ያሳድርባቸዋል፡፡

ዋ አረመኔው ግራዚያኒ!…..ስንቱን ጦስ ይዘህ መጥተህ ነበር! በሶስት ቀናት ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ 30,000 ንጹሐን ተጨፈጨፉ፤ በታሪካዊው ደብረ ሊባኖስ ገዳም ያሉ መነኮሳት ተረሸኑ፤ ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ መኖሪያ ቤቶች ፈርሰዋል፡፡ ዋ አረመኔው ግራዚያኒ!
* * *
ሐውልቱ ስር ሆኜ ያስታወስኩት ይህን ብቻ አልነበረም፤ ስለ የካቲት 12 ቀን፣ ስለነዚያ ወጣቶች እና ስለ ሌሎች የታሪኩ ተዋናዮችም ሳውጠነጥን ነበር፡፡ እነዚያ ወጣቶች ያልኩህ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስግዶምን ነው፡፡ በቀጣይ ስለነዚህ ወጣቶችና በዙሪያቸው ስለነበሩ የአርበኝነት ተጋድሎው አጋሮች እናወሳለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን የሐውልቱን ምስክርነት የሰማዕታቱን ሞገስ ስድስት ኪሎ ተገኝተህ ጎብኝ፡፡ እነዚያ ወጣቶች ጋር በቀጣይ እንገናኝ፡፡

የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ እለትን በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በመገኘት በተዘጋጀው ሻማ ማብራትና የፓናል ውይይት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል!!!

እሮብ ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ

በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት /ከካሳንቺዝ ወደ አዋሬ መንገድ የአዋሬ አጥቢያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያ አካባቢ!

img {float:left;}
p.main {text-align:justify;}
p.main {vertical-align:text-top;}

የሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ከህዝብ ጀርባ የሚያካሂደውን የኢትዮጵያ – ሱዳን ድንበር ማካለልን በመቃወም በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል በእለቱም የፓርቲው አስተባባሪ ለህብረተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና አምባገንን ስርዓት ውስጥ ሆናችሁ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን በሚል ንግግር ፕሮግራሙን ከፍተው የሰልፉን አላማ አብራርተው የፓርቲውን ሊቀመንበር ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበርም ለተሰላፊዎቹ ባስተላላፉት መልእክት ለወጣቶች የሀገራቸውን ክብር እንዲያስጠብቁ እራሳቸውንም ከፍርሀት እና ከስጋት በማላቀቅ ለራሳቸውም ለሀገራቸውም አለኝታ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ስርዓቱ ላይ ያሉት አስተዳደሮች ስልጣን ወቅታዊ መሆኑን አውቀው በኢትዮጵያ ድንበር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ደባ እንዲያስቆሙ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዲድኑ፤ ለልጆቻቸውም ውርደትን ሳይሆን ክብርን እንዲያወርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓርቲውም የጠራውን ሰልፍ እና ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት በተሳካ ሁኔታ አስተላልፎ ፕሮግራሙን አጠናቋል፡፡ ፓርቲውም በአካባቢው የሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎችን እንዲሁ የጎንደር እና የአካባቢው ህዝብን ለዚህ ሰልፍ መሳካት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ “ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘች የህዝብ ልሳን የሆነች ጋዜጣ ለማሳተም ዝግጂት እያደረገ የነበረ ሲሆን ዝግጂቱን አጠናቆ ወደ ማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ ግን ከፍተኛ የሆነ ስልታዊ ማደናቀፍ እየደረሰበት በመሆኑና ለጊዜው ማሳተም ባለመቻሉ እነሆ በድረ-ገፃችን ለንባብ በቅታለች! እርሰዎም ይታደሟት! ለጓደኛ ወዳጇችዎም ያጋሯት! መልካም ንባብ!
በ PDF ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ

በጎንደር ከተማ በነገው ዕለት የሚካሄደውን የሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ ቅስቀሳ ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን ሥራውን ለማሰናከል በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ክትትል እና ወከባ እየተደረገበት ነው፡፡
እንደሚታወቀው የፓርቲው አመራሮች እና አባላት እራሳቸውን በተለያየ ቡድን በማደራጀት የመጡበትን ተልዕኮ ለማሳካት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሠረት በቅስቀሳው ላይ ያለው ቡድን በከተማው ልዩ ልዩ ስፍራዎች ስራውን እያከናወነ ሲገኝ ነገር ግን የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ቅስቀሳውን ለማደናቀፍ የተለያዩ ሙከራ በማድረግ ላይ ቢሆኑም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ቡድኑ በከፍተኛ ቆራጥነት አፈናውን ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
በሌላ በኩል የነገውን ሠልፍ የተሳካ ለማድረግ ደግሞ ሌላው ቡድን ሌሎች የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ሲሆን ባረፉበት ሆቴል ሀኖ ስራውን በመስራት ላይ የሚገኘውን ቡድን የደሕንነት እና የፖሊስ ሃይሎች ሆቴሉን በመክበብ ጫና ለማሳደር ዛቻ እና ማስፈራሪያ እያደረሱበት ነው፡፡

በጎንደር ከተማ ለሰአታት በወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አመሻሹ 12 ሰዓት ላይ የተለቀቁ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ሁሉም ባረፉባቸው ሆቴሎች እንደሚገኙ ከአካባባው የተላከው መረጃ አረጋግጣል፡፡ ሆኖም የከተማው ከንቲባ ቢሮ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይችሉና በሚመጣው እሁድም ምንም አይነት ሰልፍ ማድረግ እንደማይችሉ በቅድመ ሁኔታ እንደለቀቃቸው የገለጸ ሲሆን፤ አመራሮቹ ግን በሀገሪቷ ህግ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማንኛውንም ቅስቀሳ ማድረግ ስለማይቻል ከነገ ጠዋት ጀምሮ ግን በዛሬው እለት ተቋርጦ የነበረውን ቅስቀሳ እንሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ ፖሊስም እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ምንም እንኳ ታጋቾቹን የለቀቀ ቢሆንም የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን ላፕቶፖች እና ካሜራዎች እንዳልመለሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በጎንደር ከተማ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሕወሓት ኢህአዴግ በህገ ወጥ መንገድ ሉዓላዊ መሬታችንን ለሱዳን መንግስት አሳልፎ አሳልፎ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ህገወጥና ሀገር ቆርሶ የመስጠት ወንጀል በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ጥር 25 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱን የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሀኑ ተክለ ያሬድ ገለፁ፡፡የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አያይዘው እን

ሻ/ል አየለ ማሞ አረፉ! ትላንት ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሻ/ል አየለ ማሞ በተለያዩ የፖሊስና የወታደራዊ ማዕረጎች ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ መስራችና የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ነበሩ፡፡ የቀብር ስነሥርዓታቸው ዛሬ ጥር 11 ከረፋዱ በ4፡00 በጀሞ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለትግል ጓዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ

ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከረፋዱ አራት ሰአት ጀምሮ እስከ አምስት ሳአት ተኩል ድረስ በድሬደዋ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የህዝብ ግንኙነት በሆኑት በአቶ እምላዕሉ ፍስሐ እና በሰማያዊ ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጊዜአዊ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል የፓርቲውን የእስካሁን ድረስ እንቅስቃሴና ያጋጠሙ ችግሮችን ተወያይተዋል፡፡ በቀጣይነትም ከጥንካሬአችን እና ከድክመታችን ተምረን ምን መሰራት እንዳለበት የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበው ጊዜአዊው ጽህፈት ቤቱ የከተማውን ህብረተሰብ ማዕከል ባደረገ መልኩ በንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ተስማምተዋል፡፡
በእለቱ አባላትን ስለማብዛትና የአባላቱ አቅም በፈቀደ መልኩ መዋጮን በማሰባሰብ የተደራጀና የተጠናከረ ስራ እንዴት መስራት እንደሚቻል በመወያየት ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን በተለይ ጊዜያዊው ኮሚቴው የግድ ከዋናው ጽህፈት ቤት የሚመጣለትን የተዋረድ ትእዛዝ ሳይጠብቅ የከተማዋን ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየት የተሸለ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበትን ሰላማዊ የትግል አቅጣጫ መቀየስ ይጠበቅበታል፡፡ በቅርቡም በከተማዋ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የጊዜአዊው ኮሚቴ አባላት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ያስታወቁ ሲሆን ይህንኑ ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ በእለቱ ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የተወከሉ ሰዎች እንደሚገኙ ታውቆአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን ጉዳይ ላለፉት ወራት ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የቆየ ሲሆን በጉዳዩም ላይ አቋሙን በመግለጫ መልክ ማውጣቱ ይታወሳል አክሎም ፊታችን ጥር 25 ቀን ለቦታው ቅርበት ካላቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ጎንደር ከተማም ተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ አንቅስቃሴዎች በተጨማሪም ድንበራችንን ጉዳይ በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ይፈጠር ዘንድ ትምህርታዊ ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በዘርፉ ለረጅም አመታት በመስራት የሚታወቁት የረጅም ጊዜ የጆግራፊ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ድንበሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ እርስዎም በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል!

ቀን፡- ቅዳሜ ጥር 17 ቀን
ሰዓት፡- ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡- በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት
(የጽ/ቤታችን መገኛ ከካሳንችዝ ቶታል ወደ አዋሬ በሚወስደው መንገድ ላይ “የአዋሬ አጥቢያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን” ጋር ሲደርሱ ወደ ቀኝ በሚያስገባው መታጠፊያ 50 ሜትር ላይ ነው)

Thank you one and all who came out to the town hall meetings in the U.S. and Europe over the past several weeks and supported Semayawi Party!

In a report last week, Ethiomedia.com described Semayawi Party (SP) as the “newest opposition sensation” which “raises new hopes” for nonviolent change in Ethiopia. Yilikal Getnet, Semayawi Party’s young and dynamic chairman, presented Ethiopians in various U.S. and European cities his party’s vision of the Beloved New Ethiopia founded on hope, peace and unity.
Beginning with the first North American town hall meeting in Arlington, VA on December 15, 2013, Yilikal told his audiences that he did not come to the U.S. to solicit financial support or to beg for money. His primary mission was to introduce his party to Ethiopians living abroad, share with them his Party’s vision, positions and programs, review some of its humble accomplishment in the short time the Party has been in existence and most importantly to answer any and all questions about the Party. He did an outstanding job as the spokesman-in-chief of his Party. He answered all questions put to him without evasion or obfuscation. He addressed policy issues with thoughtfulness and insight. His presentations were complete with anecdotal and statistical facts. He awed his audiences with his razor sharp logic and spellbinding eloquence and wit. I am proud that I was able to stand beside Semayawi Party and Yilikal during this tour and show my unreserved support.
I thank all of those Ethiopians in the Washington, D.C. area, Atlanta, Houston, Dallas, San Jose, Los Angeles, Las Vegas and Seattle for their moral support and financial help to Semayawi Party. Thank you all; I am so proud of you!
On behalf of Semayawi Party Support Group North America, I thank all of those Ethiopians who showed up at the town hall meetings, listened attentively, asked challenging questions and gave generously. Most importantly, on behalf of Semayawi Party I thank all party members and active supporters who braved the rain, snow, sleet and gloom of night to attend the meetings and show their unwavering support. Your support has made all the difference.
When I asked Yilikal of his general impressions of his first ever U.S. tour, he was effusive in his gratitude and praise. He was awed by the passionate patriotism of the Ethiopians he met; he was deeply moved by their heartfelt concerns for the future of the country; and he is inspired by their advice and counsel to help Ethiopia’s youth. He is grateful not only for the extraordinary support Semayawi Party received in the U.S. in such a short time but also the respect, love and understanding he was shown by all.
Scenes from the tour
The Semayawi Party tour was at once an educational, inspirational, confirmational, exceptional and even emotional experience for all of us. For me, the tour represented memorable “moments of truth”. I had written and talked about Ethiopia’s youth and their historic destiny for so long that it was a dream come true to stand on the side of a political party (and in my view a youth movement) that is formed by youth, for the youth and of the youth. After all, 70 percent of Ethiopia’s population is today under the age of 35.
It was a special honor and privilege for me as a member of Ethiopia’s Hippo Generation (older generation) to work so closely with members of the Ethiopia’s Cheetah Generation (younger generation). These young people were amazing. I marveled at the agility of their minds, dazzled by their insights and foresightedness, overwhelmed by their decisiveness in taking action, fascinated by their proficiency in the deployment of technology, awe-struck by their technical organizational skills and thrilled by their harmonious working relationships. I confess I thoroughly enjoyed my role as a full-fledged honorary Cheetah (though I regard myself to be a “Chee-Hippo”, a member of the intermediate generation whose job is to build bridges to connect the Cheetah and Hippo Generations) giving advice and counsel, consulting, answering questions and showing up wherever I was needed as a witness for Semayawi Party.
The one word that best describes our collective experiences in the Semayawi Party tour is “humbling”. We were overwhelmed by the passionate convictions of fellow Ethiopians who are determined to help birth the Beloved New Ethiopia that treats all of its citizens equally and respects the rights and dignity of each citizen. We were inspired by those who rejected all attempts to divide and dehumanize Ethiopians along ethnic, religious, regional and linguistic lines. We were grateful to those who schooled us on the mistakes of the past and showed us ways of avoiding known pitfalls. We were emboldened by those who assured us that we should never fear failure itself but the fear of failure which is paralyzing and incapacitating. We were comforted by those who promised and pledged to support us for as long as its takes so long as we continue the peaceful struggle for change. We were delighted by the curiosity of those genuinely interested in finding out about Semayawi Party.
We also experienced a few somber notes. We were saddened by the cynicism of some who had given up hope. “All of those who have come before you have failed. You probably will too”, they declared. We understood their disappointments. We were amused by the arrogance of others who thought the young people just did not know what they were doing and tried to lecture us on what should and should not be done. We did not mind. We are always ready to learn. We were engaged by the doubting Thomases. “We have seen them come and go? You don’t sound much different from the others. What makes you so special, so different?”, they would ask pointedly with slight derision. Doubt is the foundation of faith and we did all we could to convince them that the New Beloved Ethiopia will be built by Ethiopia’s young people, with the support of the older generation of course. We listened patiently and respectfully to those who bellyached, grumbled, moaned and groaned. They had legitimate reasons to do so.
We also learned a great deal about ourselves and what we must do. We had to defend and explain our mode of struggle. “How could you expect to win against a powerful regime with a proven history of barbaric brutality, with all the weapons of war and police and security forces?” Our response was the same as Gandhi’s “Strength does not come from physical capacity”, nor does it come from guns, tanks and war planes. “It comes from an indomitable will.” We have the indomitable will to press on with our nonviolent struggle. An indomitable will powered by love is invincible.
We preached that change must first take place in the hearts and minds of individual men and women before it can happen in society at large. We must therefore struggle with the demons of hate and revenge that have taken residence in our hearts before we can struggle with those who seek to demonize us. We are tolerant and respectful of those who disagree with our ideas, methods and means. In matters of principle, we shall always stand our ground. We believe in nonviolent social and political change. On this principle, we can agree to disagree with anyone without being disagreeable. We believe we should be judged on our own merits, and not on the achievements or mistakes of others. We are keenly aware that we must practice what we preach. That means we must maintain the highest standards of accountability, transparency and civility. We know our supporters expect us to be different, show more integrity and forthrightness and be open minded. We shall aim to practice these virtues in our daily lives.
The struggle ahead: Ethiopian David against the TPLF/EPDRF Goliath
The struggle for nonviolent change in Ethiopia will be a difficult one requiring great sacrifices. We are not unmindful that the regime will do everything in its power to weaken and destroy Semayawi Party. We take it for granted that the regime in power in Ethiopia today will arrest, jail, torture, conduct kangaroo trials and kill Semayawi Party members. To predict regime persecution of Semayawi Party persecution is like predicting the sun will rise tomorrow. We know the regime’s standard operating procedure for the last 23 years. Semayawi Party leaders and members are not afraid. They are not afraid of goons with guns. There is a new breed of young Ethiopian leaders on the rise and unafraid of thugs clad in the stolen mantle of state power. Eskinder Nega, Reeyot Alemu, Woubshet Taye, Andualem Aragie, Olbana Lelisa, Bekele Gerba, Abubekar Ahmed and so many others languish in the infamous Meles Zenawi Prison in Kality because they refused to be intimidated and bullied by the regime in power.
Those of us committed to nonviolent change in Ethiopia struggle to win the hearts and minds of all Ethiopians. We measure our victory by the number of people we are able to convince to choose the path of peaceful change. Those in power measure their victories and how powerful they are by the number of Ethiopian corpses they can scatter on the battlefield. I believe the outcome of this struggle was foretold and foreordained long ago. There was once a mighty man called Goliath. Clad in armor of iron and brass, Goliath would strut over the hill day after day and terrorize the people. Feared by all, no one would dare challenge Goliath. Then came a meek young shepherd named David who feared no one but God. David decided to fight Goliath not for the rewards of gold, silver or riches but to restore the pride, dignity and faith of his people. David was offered a sword, spear, armor and an iron helmet. He chose to fight Goliath with a sling and five smooth stones. Goliath huffed and puffed and taunted little David to come out and fight him. David met Goliath and Goliath was no more.
Semayawi Party is Ethiopia’s David standing up to a fearsome and loathsome Goliath known as the TPLF/EPDRF. Semayawi Party stands up against the mighty TPLF/EPDRF Goliath armed to the teeth with guns, bombs, tanks, artillery and warplanes. Semayawi Party stands against a Goliath with a legion of repressive police and security cadres unrivalled in Africa today. Semayawi Party stands against a Goliath backed by billions of dollars of international aid money, loans and stolen cash from the people. Semayawi Party stands against a Goliath in whose blood courses the poison of hate and division, in whose mind circulates falsehoods and deceit, in whose spirit dwells despair and misery and in whose heart darkness itself lives and breathes.
Semayawi Party is poised to fight the TPLF/EPDRF Goliath armed only with a sling and five smooth pebbles called Love, Truth, Hope, Peace and Unity. In the end Semayawi Party will win against the TPLF/EPDRF Goliath; and Goliath will be saved, saved indeed, because Semayawi Party’s pebbles do not kill; they only heal. It is an honor for me to be the water carrier for Ethiopia’s David standing up to the TPLF/EPDRF Goliath.
Let’s give Semayawi Party a chance, a fighting chance
It was a distinct honor and privilege for me to be the “keynote speaker” at the various Semayawi Party town hall events. I did not consider myself a “keynote speaker”. I showed up as a volunteer “witness”. I became a witness to ask, and hopefully to convince, Ethiopians in the U.S. to give Semayawi Party a chance, a fighting chance, a sporting chance as it struggles to stand up to the TPLF/EPDRF Goliath.
I wholeheartedly support Semayawi Party because I believe Ethiopia’s young people are the only ones with the vision, energy, intelligence and passion to change the destiny of their country and build the New Beloved Ethiopia. Today, 70 percent of Ethiopia’s estimated 94 million people consists of young people under the age of 35. The vast majority of the victims of human rights violations in Ethiopia today are young people. The targets of political persecution and harassment, arbitrary arrests and detentions, torture, abuse and maltreatment in the prisons are largely young people. Young Ethiopians are disproportionately impacted by pandemic unemployment and lack of educational and economic opportunities. The yearning of Ethiopia’s youth for freedom and change is self-evident. Change, peaceful change, will come to Ethiopia but it will be like the arrival of train that is late. The only question is whether the country’s youth will seek change through increased militancy or by other peaceful means.”
For the past eight years, I have tried to make a small contribution to the human rights struggle in Ethiopia. It is a responsibility I took much later in life. I have no greater honor than to hear Ethiopian Cheetahs and Hippos telling me that they have learned something from my weekly commentaries or speeches. What more can a teacher ask?
In the past I have asked, urged and pleaded with my readers to support the cause of human rights and the dignity of the individual. Now, I ask, actually I plead, with my readers to support Ethiopia’s young people and Semayawi Party which I believe represents the interests of the young people more than any other party in existence today.
I do not want my readers to support Semayawi Party not because I support them, but because they deserve support on their own merits. When I decided to support Semayawi Party, I asked a few questions: 1) Do I truly believe in nonviolent social and political change? 2) If I truly believe in nonviolent change, who do I believe is best positioned in Ethiopia today to effect such a change? 3) If the young people can effect such a change, what can I do to help them?
We can all help Semayawi Party in the Ethiopian Diaspora in a variety of ways. Those with means can help financially to the extent of their abilities. Semayawi Party needs a lot of financial help to do its organizational work and to sustain its outreach efforts. There are other equally important ways we can provide support to Semayawi Party. Learning about Semayawi Party and educating others is valuable support. Providing Semayawi technical support in all areas including policy analysis and development is vital, and Ethiopian scholars and academics could play a critical role in this regard. Spreading Semayawi’s message of hope, unity and peace is more important support than any other form of support. Defending Semayawi against false accusations and fear and smear campaigns is invaluable support. Giving moral support and inspiring Semayawi Party leaders and members to greater heights is priceless. Cheerleading for Semayawi is support that every patriotic Ethiopian could perform every day.
On a personal note…
It was an amazing experience for me to work with the young people in the Semayawi Party support groups. For so many years I have sought to teach, preach and reach out to Ethiopia’s young people in my weekly commentaries and occasional speeches. I am delighted to serve in the capacity of advisor to the young professionals, business entrepreneurs and university students doing the heavy lifting for Semayawi Party stateside. The proliferation of support groups for Semayawi Party throughout the world rekindles my belief that Ethiopian Cheetahs united can never be defeated.
I want to share a few personal observations about Semayawi Party chairman Yilikal Getnet. Over the past eight years, I have met many Ethiopian political, business and community leaders in one context or another. Many of these leaders have impressive qualities. I consider character the most important quality in any political leader.
Yilikal is a young engineer who has given up on his professional ambitions and subordinated his family’s interest to work for nonviolent change in Ethiopia. It takes great character and personal integrity to make such a choice. I observed different aspects of Yilikal’s character during the tour. He proved himself to be a man of principle. He was challenged that his nonviolent way idealistic and doomed to fail. He argued convincingly that violence is the weapon of the weak. No one can change hearts and minds by force and violence. He was challenged to tow the politically correct line that Ethiopia must remain a collection of klililistans (kilils) and the only rights that matter are the rights of “nations and nationalities”. He convincingly defended the principle that when individual rights are respected and preserved, group rights are necessarily protected and preserved. He was challenged that the brutal regime could persecute him, jail, torture and kill him and others in the party leadership . He was unafraid because he and other Semayawi Party leaders formed their party ready to do the right thing and make any sacrifices for their country and fellow Ethiopians.
When Yilikal was lectured and hectored that Semayawi Party was creating divisiveness by separating the young and old, he categorically denied such allegations. As a matter of principle, he made it clear that there has to be a generational division of labor. The older generation of Ethiopians could play a decisive role as advisors and supporters while the younger generation did the heavy lifting and suffered the street beating and jailing. However, only the Cheetahs have the will power, stamina, fortitude, energy and creativity to bring about lasting change. I said, “Amen!” Yilikal was chastised for not “uniting” his party with others to oppose the ruling regime. He said his party works and coordinates with other parties but there are fundamental differences in policies, strategies and tactics that make “unity” challenging. He wondered why the rest of us in the Diaspora who urge opposition unity inside the country are unable to teach by example by uniting and working together against the regime on the outside.
There is one quality that I appreciated most in Yilikal, his humility. Yilikal is a young man of small physical stature. He has on more than one occasion commented on the fact that he is somewhat vertically challenged. In reality he is truly a humble giant. He showed genuine respect and appreciation to all those he met. He listened attentively and patiently to them. He showed restraint and good judgment even when asked deliberately provocative questions. He never lost his cool and told it like it is when it comes to the truth. He never presented himself as a “party leader” or someone special. He was easily approachable and showed candor in his public and private dealings.
I appreciated Yilikal’s sense of humor. As we toured the various sites, I tried to convince him that there were indeed Cheetahs and Hippos populating the town hall meetings. Looking from the stage into the audience he could only see younger Cheetahs sitting next to older Cheetahs. He wanted me to point which ones were the Cheetahs and Hippos. I could not. There were only older Cheetahs sitting next to younger Cheetahs. I learned an important lesson. Being a Cheetah or a Hippo is as much a state of mind as a state of being. Thank you younger and older Cheetahs for coming out and supporting Semayawi Party Cheetahs!
Give Semayawi Party a chance!
Semayawi Support-North America
P.O. Box 75860
Washington DC, 20013
Website: http://www.semayawiusa.org/
Email: [email protected]
To donate: http://www.semayawiusa.org/donate/
Donation can be made by check/money order, PayPal or direct deposit to Semayawi Support-North America account.
Thank you…

SHARE:

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲውን በአውሮፓ እና በአሜሪካ የማስተዋወቅ ስራቸውን ቀጥለው በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ ጀኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ መንግስት ላይ በሚያደርጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ከሰልፉም መጠናቀቅ በኋላ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት( IOM ) ከአለምአቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) እና ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ( UN Human Rights Commission) ሀላፊዎች ጋር በሳውዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይላይ ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡ በነገው እለትም በጂኔቫ የመሸኛ የእራት ፕሮግራም የተዘጋጀላቸው ሲሆን ቅዳሜም ወደ ሆላንድ አምስተርዳም በመብረር እዛ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡

SHARE:

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል?
እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

SHARE:

ማምሻውን በደረሰን መረጃ
ሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን በድል እና ስቃይ ለመቃወም አዲስ አበባ በተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሶች አሰቃቂ ድብደባና እሰር መፈፀማቸው ቀደም ተብሎ መገለፁ የሚታወቅ ነው፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ወደ 100 የሚጠጉ እስረኞች የተለቀቁ ሲሆን ፤ከነዚህም መካከል ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት ለማወቅ የተቻለ ሲሆን የተቀሩት ማለትም፡-
1ኛ. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀ/መ
2ኛ. አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ም/ት ሊቀ/መ
3ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ የፓርቲው የፋይናስ ጉዳይ አላፊ
4ኛ. አቶ ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ አላፊ
5ኛ. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አላፊ
6ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ አላፊ
7ኛ. አቶ አብታሙ ደመቀ የብሔራዊ ም/ቤት አባል
8ኛ. አቶ ዮናስ ከድር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
9ኛ. ዮሴፍ ተሻገር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
10ኛ. ወጣት አቤል ኤፍሬም አባል
11ኛ. ሰለሞን ወዳጄ አባል
12ኛ. ፋሲካ ቦንገር አባል
13ኛ. መርከብ ሀይሌ አባል
14ኛ እመቤት ግርማ አባል
15ኛ. አስራት አብርሃም ደራሲና ጻአፊ (በግል)
16ኛ. ዳዊት ፀጋዬ ደራሲና ጻአፊ (በግል)
17ኛ. እየሩስ ተስፋ አባል
18ኛ. ንግስት ወንድኢፍራው አባል
ከላይ በስም ዝርዝ የተገለፁ እስካሁን መስቀል ፍላወርና ፒያሳ ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ ደብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል፡፡ እንዲ አይነቱን ድርጊት ፓርቲው ያስቆጣው መሆኑን እየገለፀ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡

SHARE:

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም

SHARE:

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ!

ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆምና የዜጐችን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ዜጐቻችን በአፋጣኝ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያመቻች እና በተጨማሪም በዜጐቻችን ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ኃላፊነቱን የሚወስዱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤ ለተጐዱ ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊው ካሳ እንዲደረግላቸው ፓርቲያችን አበክሮ እያሳሰበ፤ የብሄራዊ ክብርና የወገኖች ስቃይ የሚያሳስባቸው አካላት በሙሉ በዚህ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፈፃፀም፡-
1. በዜጐቻችን ላይ የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ያደረሰው የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ኢምባሲ በሚገኝበት ቦታ አርብ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ፣
2. ከአርብ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀዘን ልብስ (ጥቁር ልብስ) በመልበስ በግፍ ለሞቱና ለተንገላቱ ወገኖቻችን ሀዘናችንን መግለፅ፣
3. የእምነት ተቋማት አርብ በመስጊድ በጁምአ ሥነ ሥርዓት ላይ እና ቅዳሜና እሁድ በአብያተ ክርስቲያናት የፀሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ ወገኖቻችንን በፀሎት እንዲታሰቡ፣
4. ቅዳሜ በሚደረገው የኢትዮጵያና የናይጄሪያ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተጫዋቾቻችን ጥቁር ሪቫን በክንዶቻቸው ላይ አጥልቀው እንዲጫወቱ፣ እንዲሁም መላው ደጋፊ ጥቁር ጨርቆችን በመያዝ ወይም ልብስ በመልበስ ሀዘኑንና ቁጭቱን እንዲገልፅ፣

በፓርቲው የተወሰነ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓለም አቅፍ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠራነው የተቃውሞ ሰልፍና እንቅስቃሴዎች ላይ በመገኘት ከግፉአን ወገኖቻችን ጐን መቆሙን እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያበቃ በፅናት እንታገላለን!!!

SHARE:

በአዲስ አበባ ስኬታማ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን በማድረግ ጉዞውን የጀመረው ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ያሉ መዋቅሮቹነ በመገምገምና አደረጃጀታቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት ባለፈው እሁድ በ24/2/06 በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ወረዳዎችን በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት የገመገመ ሲሆን በእለቱም የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ በቦታው በመገኘት ስለ ፓረቲው አጠቃላይ ሁኔታና ጉዞ ገለፃ በማድረግ ስኬታማ ውይይት ከአባላት ጋር አካሂደዋል፡፡
በተመሳሳይም ከዛሬ ማክሰኞ 26/2/2006 አ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በአርባ ምንጭ በወላይታ በአዋሳና ሆሳእና ከተሞች ላይ ከአባላት ጋር ውይይት የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ከተሞች ላይ ውይይቱ የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል፡፡

SHARE:

ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ከ2 ቀን ቆይታ በኋላ ተለቀቁ
አባላቱ በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰአት በአራዳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስም ለፍርድ ቤቱ በፌደራል ፖሊስ ካምፕ አካባቢ የፓርቲ አርማ ይዞ ማለፍና ባልተፈቀደ ቦታና ሰአት ቅስቀሳ ማድረግ የሚል አስቂኝና የፈጠራ ክስ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን ቅዳሜና እሁድ ወጣቶቹ ያለአግባብ እንደተንገላቱ ለፖሊስ በመግለፅ በአስቸኳይ በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ በማዘዙ ሁሉም አባላት ሊፈቱ ችለዋል፡፡

SHARE:

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
ቅዳሜ እለት በጃንሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ታስረው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ችሎት አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊሰ ጣቢያ ተወስደው 2 ቀን እንዲያድሩ ከተደረጉ በኋላ ዛሬ ጠዋት ወደ ጃንሜዳ ፖሊስ ጣበያ ተመልሰው የተወሰዱ ሲሆን አሁንም በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ በወረዳ 9 የ2 ቀን ቆይታቸውም የፖሊስ አባላት በግዴታ የወንዶቹን ፀጉር የቆረጧቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡አባላቱ ዛሬ በ8 ሰአት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተነገራቸው ሲሆን በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የፓርቲው አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እየጠየቋቸው ይገኛሉ፡፡

SHARE:

ሰማያዊ ፓርቲ ለጽ/ቤት መጠቀሚያ ተከራይቶ ነበረውን ቢሮ በግድ ካልወጣችሁ ሲሉ ከነበሩት የጉለሌ ክ/ከተማና ወረዳ 03 ካድሬዎች መካከል በተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማፈላለግ መሀከል የገባው የመነን አካባቢ ፖሊስ በውይይት ለመፍታት ሁለቱም አካላት ከቤቱ እንዲወጡና ፖሊስ ቤቱን እንዲጠብቅ፤ በቀጣዩ ቀን ለመነጋገር ስምምነት ተይዞ የፓርቲው አባላት ወደቤታቸው ለመሄድ ከጽ/ቤቱ ለቀው ቢሄዱም ከመንገድ ላይ
1.ወ/ት ሀና ዋለልኝ (የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ)
2.አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
3.ወ/ት እየሩስ ተስፋው
4.አቶ ዮናታን ተስፋዬ
5.አቶ አቤል ኤፍሬም
6.አቶ አህመድ መሀመድ
7አቶ እያስፔድ ተስፋዬ
የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስና የደህንነት አካላት ወደ ጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው አሁን በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት እንደሚታወሰው የጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ የፓርቲውን አባላት እያሰረ ይደበድብ እንደነበረ ፤ አሁንም ከአንድ ሰአት በላይ አባሎቹን ምን እያደረጋቸው እንደሆነ ማወቅ አለመቻሉ እየተደበደቡ ይሁን? የሚለውን ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አጭሯል፡፡

SHARE:

አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረዉን ቤት ‘ለወሔነት’ ባርና ሬስቶራንት ለፔንሲዮን አገልግሎት እንዲሚጠቀምበት ቢሆንም የፔንሲዮኑ ባለቤት የሆኑት አቶ በላቸዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ 3 አስተዳደር በግዴታ እንዲከራዩ የእያስገደዷቸዉ ሲሆን አቶ በላቸዉና የቤቱ ባለቤቶች እኛ ተገደን ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱን ለፓርቲ ጽ/ቤት እንዳይከራይ እየተከራከሩ ያሉት በአቶ ያለዉ እዉነቱ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሚመሩ የመስተዳድሩ አካላት መሆናቸዉ በይበልጥ ለፓርቲዉ ጽ/ቤትነት ለመጠቀም እንዳንችል መንግስት እጁ እንዳለበት መገንዘብ ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

SHARE:

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡

SHARE:

ሰማያዊ ፓርቲ ቀድሞ ከነበረበት ጽ/ቤት ወደ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ ፅ/ቤት ተከራይቶ ከቤቱ ባለቤቶች ጋር ለ2 ዓመት የሚቆይ ውል የተዋዋለ ሲሆን በውሉ እንደተገለፀውም ከዛሬ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ የሰማያዊ ፓርቲ በመሆኑ ቤቱን ለመረከብ በሄዱበት ወቀት ቤቱን እኛም ተከራይተንዋል በሚሉ ግለሰቦች ቤቱን በፖሊስ ሀይል ታግዘው ይዘውታል፡፡ የፓርቲው አመራሮችም ቤቱን በህጋዊ መንገድ እንደተከራዩትና ከዛሬ ጀምሮ የቤቱ ባለመብቶች እንደሆኑ ለፖሊስ ያስረዱ ሲሆን ይህ ዜና እስከደረሰን እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስም አብዛኛው የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ ጣቢያ እንደሆኑና በስልክም ማነጋገር አስቸጋሪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይነት የሚኖረውን ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን፡፡
(ፎቶ፡- ፓርቲው ከአከራዮቹ ጋር የገባው ውል)

SHARE:

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መንግስት በሚያስተዳድረው ሐገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን፣ ተቋማትን፣ የሀገር ሉዓላዊነትን፣ ታሪክን፣ ባህልን፣ የእምነት ነፃነትንና ደህንነትን ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት ወድሟል፡፡
እጅግ የሚያሣዝነው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡ ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡ በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲያችንን ከልብ አሳስቦታል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት፡-
1. አንጋጫ ኪ/ምህረት 2. ዳገት ሚካኤል 3. የደርበን ሚካኤል
4. ዋሻ መድሀኒዓለም 5. መንክር ማሪያም 6. ቀዝቀዝ ገብርኤል
7. ደማም እየሱስ 8. ምስለ ዋሻ ጊዮርጊስ
አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ የወደሙ ሲሆን የተወሰኑት በአካባቢው ሕብረተሰብ ጥረት በከፊል ተቃጥለው የተወሰነ ንብረት ሊተርፍ ችሏል፡፡ ፓርቲያችን በህግ ተመዝግቦ ህጋዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተወዳደሮ የመንግስት ሥልጣን ከመያዝ በተጨማሪ በተለያየ ጊዜ በሐገርና በህዝብ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን መከታተልና በሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረት ማደረግ ስለሆነ በመንግስት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የቃጠሎው ምክንያት ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀመው አካል በህግ ተጠያቂ እንዲሆንና ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለፅ እያሳሰብን እንዲህ ዓይነቱ በሕዝብ አመኔታ የሚጣልባቸው ተቋማትን የማውደም ተግባር ወደፊትም እንዳይደገም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
መስከረም 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

SHARE:

መስከረም 21/2006 ዓ.ም. የዋለው የአራዳ ምድብ ችሎት በአንድ መቶ ብር (100.00 ብር) ዋስትና የለቀቃቸው የሰማያዊ ፓርቲ የብ/ም/ቤት አባል የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ስሜነህ ጸሀይ የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ውጭ ወደአልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውንና ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱም ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፖሊስ እንዳካሄደባቸው የፓርቲው አመራሮች መረዳት ችለዋል፡፡

SHARE:

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መስከረም12 ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፓርቲው የሰልፉን ቦታ እንዲቀይር የጠየቀ ቢሆንም ፓርቲው ሰልፉን በመስቀል አደባባይ እንደሚያካሂድ በአፅንኦት በመግለፅ ዛሬ ደብዳቤውን ለአስተዳደሩ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊና ምክትል ኃላፊ በተገኙበት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር አቶ ማርቆስ ብዙነህ አስፈርመው አስረክበዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ በፓርቲው በኩል የሰልፉ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ::

SHARE:

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች ህገ ወጥ እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መስከረም 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል እንዲያውቀዉ አድርጓል፡፡ ይህንን ተከትሎ የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የሰለፉን ዓላማ፣ የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመርና የሰልፉ መዳረሻ ከግንባታ ስራና ከፀጥታ ጥበቃ ጋር ያለውን ችግር አስመልክቶ ማብራሪያ እንደሚያስፈልግ በጠየቀዉ መሠረት፡-
1ኛ. የሰልፉ ዓላማ፤
በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር፣ዜጐች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11፡3 በግልፅ የተደነገገው መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው ድንጋጌ እንዲከበር፣ መንግሥት የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ ሠልፍ መንግሥትን ለመጠየቅ መሆኑን፤
2ኛ. የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመር
መነሻው ከፓርቲው ጽ/ቤት ግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል በኩል በአሮጌው ቄራ በአምባሳደር ቴአትር አልፎ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ በዚህ መንገድ ላይ ምንም ዓይነት የግንባታ ሥራ የሌለበትና ሠልፉ የሚደረገውም እሁድ ከጥዋቱ 3፡ዐዐ-7፡00 ሰዓት ባለው የእረፍት ቀን በመሆኑ በዕለቱ ምንም ዓይነት የመንግሥት ሥራና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበትና መድረሻ ቦታችንም መስቀል አደባባይ ከቅርብ ቀናት በፊት በኃይማኖት ተቋማት አስተባባሪነት ሠልፍ የተደረገበት መሆኑና ወደፊትም መስከረም 12 ቀን ከሚደረገው ሠልፍ አንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሁሉም ማዕዘናት በሚመጡ ምዕመናን የመስቀል በዓል የሚከበርበት ቦታ መሆኑን ጳጉሜ 04 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፍነው ደብዳቤ አብራርተናል፡፡
የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1987 አንቀፅ 6 ቁጥር 2 “የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጁ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ስፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሔድ አይችልም ማለት አይችልም” በሚለው መሰረት የእዉቅና ጥያቄ የቀረበለት አካል በፅሁፍ በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡
ፓርቲያችን በሕግ የሚጠበቅበትን ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉን በመቆጣጠርና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያውክን ሁኔታ በማስወገድ የሰላማዊ ሰልፈኞች መብቶችን ለመጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በአዋጁ ቁጥር 3/1987 የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውኑ እናሳስባለን፡፡
መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

SHARE:

ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
(ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)
ሰማያዊ ፓርቲ ለነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጠርቶት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂ ኋይሎች ሕገ-አራዊት እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ፓርቲያችን ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጳጉሜ 2 ቀን 2005ዓ.ም ሠልፉ በድጋሚ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ሠልፉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን በፓርቲ በኩል ልዩ ልዩ ተግባራት ከመከናወናቸው ጎን ለጎን አስፈላጊው የጸጥታ ጥበቃና የአስተዳደር ድጋፍ እንዲሰጠን በህጉ መሰረትም ሠልፉ እውቅና እንዲያገኝ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሰወቂያ ክፍል ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ደብዳቤ ለማስገባት በአካል ተገኝተን ጠይቀናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ክፍል ደብዳቢያችንን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
በፓርቲው በኩል በሁኔታው ተስፋ ባለመቁረጥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል የማሳወቂያ ደብዳቤውን ከላይ በተጠቀሰው ቀን የላክን ሲሆን ውጤቱ ግን አሁንም በፖስታ ቤት በኩል የተላከውን ደብዳቤ በእንቢተኝነት አለመቀበል ሆኗል፡፡
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአስተዳደሩ ፅ/ቤት በመገኘት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር እረጅም ሰዓት የወሰደ ከቢሮ ቢሮ መንከራተት የተሞላበት ደጅ ጥናት ካደረጉ በኋላ በመጨረሻም በከንጺባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ጋር ለመነጋገር ተችሏል፡፡
በዚህም ውይይት የጳጉሜ አምስቱ ቀናት በከተማው አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ እድል ለመፍጠርና እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ በየዓመቱ አስቀድሞ በከተማው ማዕዘናት ያሉ ቦታዎች ለዚህ አገልግሎት ስለሚያዙ በነዚህ ቀናት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የማይችሉ መሆኑን አበክረው ገልጸውልናል፡፡ ፓርቲው በከንቲባ ጽ/ቤቱ የቀረበውን ምክንያት ከመረመረ በኋላ የበዓሉ ዋዜማና የዘመን መለወጫ በዓል ካካፋ በኋላ ባሉት ቀናት ሰልፉን ለማድረግ በመወሰን ለጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓም ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ የዚህን ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ክፍል በማቅረብ የሰልፉ ማሳወቂያ ደብዳቤ ቀሪ ላይ በማስፈረም ገቢ አድርጓል፡፡
በመሆኑም ከለይ በተጠቀሰው ምክንያት ሠልፉ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006ዓ.ም መተላለፉን እየገለጽን ከዚህ በፊት የጠራናቸው የተቃውሞ ሰልፎች የተሳኩ እንዲሆኑ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማሕበራትና በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላደረጋችሁት ድጋፍ ፓርቲያችን ምስጋናውን እያቀረበ፤ አሁንም ቀጣዩ ሠልፍ በታሰበለት ዓላማ መሠረት የተሳካ እንዲሆን የተለመደ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ምንግዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!!
ነሐሴ 30 ቀን 2005ዓ.ም
አዲስ አበባ