የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይቭ ዘገባ
የአንድነት ፓርቲ ዛሬ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤዉን ያደርጋል። ምርጫ ቢቦርድ ከሕግ ዉጭ አንድነት ፓርቲ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክት አልሰጥም በሚል፣ አንድነትን ከምርጫዉ ለማስወጣት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአንድነት ፓርቲ ግን ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን መሰናክል ለማለፍና ለምርጫ ቦርድ ቀዳዳዎችን ሁሉ ለመዝጋት በሚል ነው ስብሰባው የተጠራው። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ እንዲገኝ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም ሌሎች ግለሰቦች ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቷልና በሁለት ስብሰባዎች መገኝት አንችልም በሚል ታዛቢ እንደማይልኩ በደብዳቤ ገልጸዋል። ሆኖም የአንድነት ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ኖረም አልኖረም ጠቅላላ ጉባኤዉን እንደሚያደርግ በመግለጽ ለምርጫ ቦርድ ምላሽ ሰጥቷል።
11:00 AM አዲስ አበባ ሰዓት
ዲፕሎማቶች አንድነት በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ተገኝተዋል። “የአንድነት አባል በአንድ ፌሽካ በአንድ ቀን መገኘት ይችላሉ!” የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ

10፡30 AM አዲስ አበባ ሰዓት
ተወካዮች ቦታቸውን ይዘዋል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ መቀመጫቸዉን ይዘዋል። ከክፍለ ሃገር የመጡ በርካታ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የተወሰኑቱ በዚህ መልክ ነበር በአንድነት ጽ/ቤት ውጁስጥ ያደሩት።
