አስራት አብርሃም ተለቀቀ

ትናንት ቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ተሰጥቶለት የነበረውን የፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃምን የዋስ መብት አላከብርም በማለት ያሰረው የከተማይቱ ፖሊስ ከቅርብ ሰዓታት በፊት አስራትን በዋስ መልቀቁን ለሰላማዊው ታጋይ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡
አስራ ለእስራት የተዳረገው የመድረክ ሰላማዊ ሰልፍን ለመቀስቀስ በቡራዩ የከተማ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በመታሰራቸው ለጥየቃ ባመራበት እንደነበርና ፖሊስም አላሰርኩም በማለቱ አቶ አስራት አብርሃምን ፖሊስ ሰወረ በማለት መዘገቡም አይዘነጋም፡፡ በነካ እጃችሁ በግንቦት 20 ምክንያት ለምን ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች እና ጦማሪዎችን ልቀቁዋቸው ብዕር እንጂ መሳሪያ አልጨበጡም፤ መሳሪያ ያነገበ እንዴት ብዕር ይፈራል? ያውም ዲሞክራሲ አመጣሁላችሁ ብሎ 23ኛ ዓመቱን ለማክበር ሽር ጉድ የሚል አካል፤ ማሰር፤ ማንገላታት መፍትሄ አይሆንም ይልቅ ብሄራዊ ዕርቅ በማድረግ ሰልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚተላልፈበትን መንገድ እንምከር10325409_641028839315387_2062526112924134023_n