በደህንነት ቢሮ ለሊቱን ያጋመሰ ግምገማ መካሄዱ ተሰማ::
አለመተማመኑ እና ክፍተቱ እየሰፋ መምጣቱን በገሃድ ያሳየ ግምገማ መሆኑ ታውቋል:: Minilik Salsawi
የሕወሓት የደህንነት አባላት በተለየ ሁኔታ አዳማጭ የሆኑበት ትላንትና የተጀመረው በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰማሩ የፌዴራሉ ደህንነት አባላት ግምገማ እጅግ በተካረረ እሰጥ አገባ ለሊቱ አጋማሽ ድረስ ቢደረግም በማጉረምረም እና ባለመስማማት መበተኑ ታውቋል::በአንድ ብሄር የበላይነት የተከሄደው እና በተያያዘ የአንድን ብሄር በተለየ ሁኔታ ያልነካው ይህ ግምገማ በገዛ አገራችን እንደ እንጀራ ልጅ እና እንደ ባይታዋራ ነገሩን ሁሉ በሌሎች ላይ ለምን ይላከካል የሚል ጥያቄ አስነስቷል::

መገምገም ካለበት ትእዛዝ ከሚሰጡ የበላይ ሃላፊዎች ጀምሮ ነው እንጂ ሁሉም እኩል የሰራውን ስራ የትግራይ ተወላጆችን ለይቶ አስቀምጦ አዳምጭ አድርጎ እኛን ለይታችሁ የምትገመግሙበት ምክንያቱ ምንድነው? ሁላችንም አንድ የጋራ ስራ እስከሰራን ድረስ በጋራ ልንገመገም ይገባል ግደሉ ስንባል ገለናል ዝረፉ ስንባል ዘርፈናል ተካፈሉ ስንባል ተካፍለናል::ይህንንም ስራ የትግራይ ተወላጆች አብረውን ፈጽመዋል::ብሄር የለየ እና ያማከለ ግምገማ የዜግነት መብታችንን ይጋፋል እንዴት እንዲህ እንቀጥላለን::ሁሉም በጋራ ሊገመገም ይገባል::አንዱን የቤት ልጅ ሌላውን የጎዳና ዱርዬ አድርጎ መገምገሙ ለምን አስፈለገ የሚሉ አስተያየቶች የተደመጡ ሲሆን:ሃላፊዎቻችን በቡድን በቡድን አደራጅተው በግል ትእዛዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ስራዎችን መስራታችን እየታወቀ ከነሱ በወረደ ትእዛዝ ለሰራነው ስራ ልንጠየቅም ሆን ልንገመገም አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል::በየክልሉ እየተገደሉ የሚጣሉ ግለሰቦችንም ኖን የሚዘረፉ ንብረቶችን የሚጠየቁ ገንዘቦችን አስመልክቶ ሃላፊዎቻችን ወርደው ሊገመገሙ ሲገባ እንዲሁም በማናለብኝነት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች የሕወሓት የደህንነት አባላት መጠየቅ ሲገባቸው እነሱን ከዚህ ሁሉ ድርጊቶች አግለሎ እኛን መኮነኑ የማያዋጣ የግምገማ ሂደት ስለሆነ ሊታረም ይገባል ሲሉ ተገምጋሚዎቹ በአንድ ድምጽ ተናግረዋል::

በግምገማው ላይ ከተነሱት ጉዳዮች ሌላው ትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶችን በአዲስ አበባ ዙሪያ ማእረግ እና ሃላፊነት በመስጠት በፖሊስ ሰራዊት እና በመከላከያ ቢሮ ውስጥ ሲመደቡ የሌላው ብሄር ተወላጆች ወደ በረሃ በመወርወር በተዘዋዋሪ እየበደሉ እነ በክትትል እያሰቃዩ እስከ ሞት የደረሱ እንዳሉ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ጉዳይ ሊታይ ይገባዋል::መልቀቂያ የጠየቁ የደህንነት አባላት የሚጠብቃቸው እስር መሆኑን እያየን ነው:: የተሰደዱ አባላት በርካቶች ናቸው::የመንግስትን ይሁን የፓርቲ መረጃ የሚሸጡት የሕወሓት አባላት የሆኑ ደህንነቶች መሆናቸው ይታወቃል:; እነሱን አትንኩብን ማለት ነገ ለሚፈጠረው ችግር ተተያቂው ማነው? በሚል ጉዳይ ዙሪይ ጥያቄዎች ቢነሱም በማያረኩ ምላሾች ጉዳዮቹ ሳይገመገሙ አልፈዋል::ለሊት አጋማሽ ድረስ የዘለቀው ግምገማ ቀጣይ ሁኔታዎች ተጠንተው ድጋሚ ሌላ ግምገማ ይጠራል በሚል የበላይ ሃላፊዎች የተረጋጋ አንደበት ስብሰባው መዘጋቱን ምንጮቹ የገለጹ ሲሆን በደህንነት ክፍሉ ውስጥ አለመተማመኑ እና ክፍተት እየሰፋ መምጣቱን የስርአቱን መበስበስ ያመለክታል::

Image

(አዲስ ከድሬዳዋ) በሶሻል ሚዲያ(በተለይ በፌስቡክ) ብዙ ጊዜ አስተማሪና ምክንያታዊ የሆኑ ፅሑፎችን በመፃፍ የሚታወቀው ዶክተር ብርሀነ መስቀል አበበ ሰኚ ሰሞኑን ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛም የፌደራል መንግስት፣ እንዲሁም የድሬዳዋ እና የአዲስአበባ አስተዳደሮች የስራ ቋንቋ እንዲሆን የሚጠይቁ ፅሑፎችን በተከታታይ እያወጣ ሰፊ ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡ ሀሳቡንም በግሌ እደግፈዋለሁ፡፡ነገር ግን በምን መልኩ ነው የስራ ቋንቋ የሚሆነው , እንዲሁም በአተገባበር ሒደት ምን ሊያጋጥም ይችላል የሚለው ግን የታሰበበት አይመስልም፡፡ ኦሮምኛን የስራቋንቋ ይሁን ስንል የሀገሪቱ የቋንቋ አጠቃቀም ፖሊሲ ምን ይመስላል የሚለውን በጨረፍታ ማየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የላትም፡፡ በሀገሪቱ የሚነገሩ ቋንቋዎች ሁሉም እኩል ናቸው፡፡ በርካታ ወይም አነስተኛ ተናጋሪ ስላለው አንድ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዳይማር፣ አገልግሎት እንዳገኝ፣ እንዳይዳኝ፣ . . . . አይከለከልም፡፡ሆኖም ከኢኮኖሚ አቅም እና የተማረ የሰው ሀይል ውስንነት ጋር ተያዞ በመማሪያነት እያገለገሉ ያሉ ቋንቋዎች ከ30 አይበልጡም(በርግጥ ይህ ከ90 ፐርሰንት በላይ ኢትዮጵያውያንን ይሸፍናል)፡ ስለዚህ ሁሉም ቋንቋ እኩል ከሆኑ አንድን ቋንቋ የፌደራል የስራ ቋንቋ አድርገህ ሁሉም ክልሎች በትምህርት ቤቶቻቸው እንዲስተምሩት፣ በጋራ መግባቢያነት እንዲጠቀሙት፣ . . ለመወሰን የተለየ መነሻ ያስፈልጋል፡፡በዚህ ረገድ አማርኛ በ ታሪክ አጋጣሚ በብዙ ቦታዎች በሁለተኛ ቋንቋነት፣ በጋራ መግባቢያነት ( lingua franca) ና በመንግስት ቋንቋነት ሲያገለግል ስለቆዬ በሚል መነሻ የፌደራሉ መንግስት የስራቋንቋ እንዲሆን በህገ መንግስቱ ተወስኗል፡፡ ኦሮምኛስ ኦሮምኛ በሀገሪቱ በርካታ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ነው፣ ሆኖም ቋንቋው ከኦሮሚያ ውጪ በሁለተኛ ቋንቋነት እምብዛም አገልግሎት አይሰጥም፣ ልክ እንደ ትግርኛና […]

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የአረና ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል የመሰኖ ውሃ እንዳያጠጡ በመከልከላቸው፣ ሰብሎቻቸው እየደረቁ ነው። 12 አርሶ አደሮችን በመወከል ለኢሳት የተናገረው አቶ ህድሮም ሃይለስላሴ የተቃዋሚ አባላት ብቻ በመሆናችን አትክልቶቻችንን የመስኖ ውሃ እንዳያጠጡ፣ ከእነሱ መካከል ሁለቱ ብቻ …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞ የሸእቢያ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦህዴድ 25ኛ አመት የእዮቤልዩ በአሉን ድል ባለ ድግስ ለማክበር በማሰቡ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶችን ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ የድርጅቱ ካድሬዎች ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። የክልሉ ፕሬዚዳንት የካቲት 29 ቀን 2007  ዓም ባለሃብቶች በአሉን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ስብሰባ ጠርተዋል። ድርጅቱ …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የሚገኘው ደን ካለፉት 3  ቀናት ጀምሮ በእሳት እየወደመ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጸጥታ ሃይሎች እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ ናቸው። ይህን መረጃ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምን ያክል ስፋት ያለው ደን እንደወደመ ለማወቅ አልተቻለም። በባሌ ዞን በወረዳ ሼዳ ቀበሌ አካባቢም …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ  ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት  ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ  በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ  ድልድይ በመስራት በሚታወቀው  ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው …

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ  ሰራዊት  ከፍተኛ  መኮንኖች  እና  መንግስት  ከፍተኛ  አመራሮች  በተገኙበት  በተደረገው  የምስጋና  ሲመፖዝየም  በከተማዋ  ከሚገኙ  ክፍለ  ከተማዎች  የተመረጡ  የገዢው  ፓርቲ  አባላትና  አቀንቃኞች እንዲሁም ከየመምርያው  የተወከሉ አባላት በተገኙበት መከላከያ ሰራዊቱ ለሃገሪቱ ዘብ የቆመ፣ በልማቱ ተሳታፊና ሁለንተናዊነቱን በማንሳት መወድሰ- መከላከያ ሰራዊት ሲደረግ ውሎአል። በዚህ የሰራዊቱን አመራሮች የማድነቅ ስነስርዓት ላይ ንግግራቸው …

የቻይና ኤኮኖሚ ባለፉት ሁለት አሠርተ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ እድገት በማስመዝገብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለተኛዋ ናት። ይኸው 12,2% የነበረው የእድገት መጠን ግን በሚቀጥሉት ጊዚያት በጉልህ ሊቀንስ እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ጠበብት ገምተዋል። ይህም በቻይና ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በዓለም ኤኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ጠበብት ጠቁመዋል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ከስምምነት እንዲደርሱ በአደራዳሪና ሸምጋዮች የተሰጣቸዉ የጊዜ ገደብ ዛሬ እኩለ ለሌሊት ከመሆኑ አስቀድሞ ያከትማል። ሆኖም እስካሁን ከአዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች ተደራዳሪዎቹ የተጠበቀዉ ስስምነት ላይ መድረሳቸዉን አያመለክቱም።

ከጠፋ አንድ ዓመት ሊሞላዉ ጥቂት ቀናት የቀረዉ የማሌዢያ አዉሮፕላን ጉዳይ ዛሬም እንዳነጋገረ ነዉ። በበረራ ታሪክ ለደረሰ አደጋ ከፍተኛ ወጪና ኃይል አሰባስቦ ከተከናወነ ፍለጋ በኋላ ያለ ዉጤት የተጠናቀቀበት የበረራ ቁጥር MH 370። አዉሮፕላኑ የጠፋበት ቀን ሲታሰብ ፈላጊዎቹ ለተሳፋሪዎቹ ቤተሰቦች የሚሰጡትን የመጨረሻ ቃል እየፈለጉ ነዉ።

የግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በካርቱም፣ ሱዳን በዐባይ ወንዝ ውሃ ክፍፍል እና ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለሶስት ቀናት ያደረጉትን ዉይይት ዛሬ አጠናቀዋል። የውይይቱ ውጤት ገና በይፋ አልወጣም።

በጴጥሮስ አሸናፊ እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ…

The post የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት…

The post አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የኤርምያስ ለገሠን ‹ግልጽ ደብዳቤ› አነበብኩት፡፡ አንብቤው በሁለት ምክንያት ሳልጽፍለት ዘገየሁ፡፡ በአንድ በኩል ስለ ኤርምያስ ከነበረኝ የዋሕ ግምት የተነሣ ኤርምያስን ያህል ሰው ይህን ያህል አይሳሳትምና በቀጣዮቹ ቀናት በስሜ የወጣ ጽሑፍ ነው…

The post ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ለአቶ ኤርሚያስ ለገሰ የሰጠው ምላሽ: ኤርምያስ ኤርምያስ ሆይ! appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ተጻፈ በ  

መንግሥት በሲኖትራክ ሳቢያ የሚከሰተውን አደጋ የሚያጠና ግብረ ኃይል ማቋቋሙ…

Moresh Wegene

The post እታች ያሉት ሕፃናት እላይ ያለችውን ሕፃን ያውቋት ይሆን ? እላይ ያለችዋ ሕፃን እታች ያሉትን እፃናት ታውቃቸው ይሆን ? እስኪ አዕምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ይፍረድ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሐዲስ ዓለማየሁ የባሕል ማዕከል 3ኛ ጉባኤ ላይ የቀረበ
‹‹አበሻ ባል ሚስቱ ስታረግዝ እርሱ ዕንቅልፍ አይወስደውም›› ይባላል፡፡ ስለምን ቢሉ የልጅ ስም ፍለጋ፡፡ ስም ደግሞ በአበሻ ምድር እንዲሁ አይወጣም፡፡ ቢቻል ከአያት፣ ካልተቻለም ከአባት ጋር የሚገጥም፣ ዘመኑንና ሁኔታውን የሚያሳይ፣ ተስፋንና  ምኞትን የሚያመለክት፣ አንዳንዴም ድጋፍንና ተቃውሞን የሚገልጥ መሆን አለበት፡፡ ‹ጅል እንደ ሠራው በርና መቃን የማይገጥም ስም ይዘህ. ይባላልኮ፡፡ በተለይ በሰሜኑ ማኅረሰብ ስም መጠሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እንደ መዝገብ ታሪክን፣ እንደ ሚዲያ ሐሳብን፣ እንደ መጽሐፍ ፍልስፍናን፣ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት እምነትን፣ እንደ ሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞን የሚያሳይ  የመገናኛ መሣሪያ ጭምር ነው፡፡

በደርግ ዘመን ተቆራጭና መዋጮ በዝቶ ሠራተኛውን መከራ ሲያሳየው፣ በባሕርዳር ጥጥ ፋብሪካ የነበረ በዛብህ የተባለ ወዛደር ለሁለት ልጆቹ ‹ተቆራጩ› እና ‹መዋጮው› የሚል ስም አወጣላቸው፡፡ የልጅ እናቱ በየአሥራ አምስት ቀኑ የልጆቿን ተቆራጭ ልትወስድ ስትመጣ ደመወዝ ከፋዩ ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹ተቆራጩ በዛብህ› ‹መዋጮው በዛብህ› እያለ የሕዝቡን ተቃውሞ ሲገልጥ ኖሯል፡፡ በአብዮቱ ዘመን የተወለዱ ብዙ ልጆች ‹አብዮት› የሚለውን ስም በመያዝ ታሪክ መዝግበው አልፈዋል፡፡ ኀዘንን ለመርሳት ያስችላል የተባለውን ልጅ  ማስረሻ፣ ከመከራ በኋላ የተወለደውን አልፈነው፣ አልወልድም ካሉ በኋላ የተወለደውን እምቢ በል፣ ከሌላ ተረገዘ ተብሎ ሲታማ አባቱን መስሎ የተወለደውን ምስክር እያሉ መጥራት ከስም በላይ ጉዳይ ያለበት ነው፡፡ ከዐሠርት ዓመታት በፊትም ልጃቸው ‹ይገደብ ዓባይ› ብለው ትንቢት የተናገሩ ወላጆችም ነበሩ፡፡
እንኳን የልጅ ስም የውሻ ስም ከአንድ ጋዜጣ በላይ የሆነ ማኅበራዊ ጉዳይን ሲገልጥ ኖሯል፡፡
ሁለት ውሾች አሉኝ የማሳድጋቸው
አንዱ ሰምቶ መቻል ሌላው መተው ናቸው
የሚለው ሐሳብኮ ባለስሞቹ ውሾች ሊሸከሙት የሚከብዳቸው ነው፡፡ 
በጎንደር ከተማ በ1970ዎቹ መጀመሪያ የነበሩ አቶ ጨከነ የተባሉ አባት ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ልጆቻቸው መንግሥቱና መልአኩ የሚል ስም አወጡ፡፡ ልጆቹም ‹መንግሥቱ ጨከነ› ‹መልአኩ ጨከነ› ተባሉ፡፡ ‹የእግዜር ታናሽ ወንድም› የተባለለት መልአኩ ተፈራ ሰምቶ ሊገላቸው ቢነሣ አገር ጥለው ጠፉ፡፡ ጠፍተውም ዝም አላሉም፡፡ የመከራው ዘመን ሲረዝም በፈጣሪም ተስፋ ቆረጡ መሰል ሦስተኛ ልጃቸውን ‹አምላኩ ጨከነ› ብለው ስም አወጡለት፡፡ 
እኒህ ዛሬ የምንዘክራቸው ሐዲስ ዓለማየሁ እንደሚተርኩልን በአንድ ወቅት እዚህ ምሥራቅ ጎጃም ሲመጡ ‹ኦክስጅን› የሚባል ስም ይሰማሉ፡፡ ገርሟቸው አባትዬውን ሲጠይቁት ትርጉሙን አያውቀውም፡፡ ‹ታድያ እንዴት አወጣህለት› ሲሉት ‹‹በአንድ ወቅት ደጃዝማች ግርማቸው ተክለ ሐዋርያት እዚያ አካባቢ መጥተው ይህንን ቃል ሲሉት ሰማኋቸው፡፡ መቼም ከእርሳቸው አፍ ክፉ አይወጣም ብዬ ኦክስጅን አልኩት› ብሎ መለሰላቸው፡፡ 
እኛ አገር ስም ብዙ ነገር ነው፡፡
እንዲያውም ሰሞኑን አዲስ አበባ አንድ ስም ሰማሁ፡፡ ቆጥቡ፣ አስቀምጡ በሚባልበት ዘመን የተወለደች ስለሆነች መሰለኝ፤ ‹ባንኬ› ብለው ነው የሰየሟት፡፡ እነ ገንዘቤ፣ ንብረቴ፣ ሀብቴ አንድ ደረጃ አድገው ‹ባንኬ› ሆኑ ማለት ነው፡፡ ምነው ብዬ ብጠይቅ ሰውዬው ለ20/80ም ይሆን 40/60 የሚቆጥቡት ብር አጠራቸው፡፡ ደግሞ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው ይህን ያህል ብር ቆጠብን ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ስማቸው መልአኩ ነበርና ልጃቸው ‹ባንኬ መልአኩ› ብለው የኔስ ባንክ መልአኩ ነው ብለው ተጽናኑ አሉ፡፡ ደቡብ ወርጄ ደግሞ ‹መቶ ሃያ› የሚባል ስም ሰምቼ ነበር፡፡ መቼም በ120ው የጌታ ቤተሰብ ሰይመውት ነው ስል ለካስ ነገሩ ሌላ ነው፡፡ ‹‹በቴሌቭዥን 120 ፕሮግራም ሲጀመር ስለተወለደ ነው›› አሉኝ፡፡ 

ከታምሩ መቅድሙ እንዳይበዛ ብለን አሁን ተአምሩን መንገር እንጀምራለን፡፡
የሐዲስም አባት እንዲሁ የሆኑ መሰለኝ፡፡ ወላጆቻቸው ‹ዓለም አየሁ› ብለው ስም ሲያወጡላቸው አንዳች ተስፋ ነገር መሰነቃቸውን ያሳብቅባቸዋል፡፡ ለነገሩ ያ ዘመን  የተስፋ ዘመን ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በቴዎድሮስ የጀመረችውን ዝመና በምኒሊክ በኩል እውን እያደረገች የነበረችበት ዘመን፡፡ መኪና፣ ስልክ፣ ፖስታ፣ ዘመናዊ ትምህርት ቤት፣ የቧንቧ ውኃ፣ አዲስ ሆነው እየመጡ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ሥልጣኔ እየገሠገሠች የነበረችበት ዘመን፡፡ ይኼን ዘመን ለታሪክ ካስቀሩልን መዛግብት መካከል የዚያ ዘመን ስሞች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እንደ ሐዲስ ዓለማየሁ አያት ያሉ ተስፋ ሰናቂዎች ‹ዓለም አየሁ› ብለው በልጆቻቸው ስም ዘክረውታል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ልጅ እምቢ ብሏቸው፣ እንደ ሐናና ኢያቄም፣ ወይም እንደ እግዚእ ኀረያ እና ጸጋ ዘአብ ሲናቁና ሲተቹ ኖረው የጀግና ልጅ አባት የሚሆኑ ጀግና ሲያገኙ ጊዜ ‹ዓለም አየሁ› ብለዋቸው ይሆናል፡፡ በኛ ትውፊታዊ ትርጉም ‹ዓለም› ብዙ ነገር ነዋ፡፡ ዓለም – ተድላ ነው፣ ተስፋ ነው፣ ኑሮ ነው፣ ሀብት ነው፣ ትዳር ነው፡፡
‹ዓለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ
እህህ እቴ ሸንኮሬ›› እንዲል፡፡ 
ዓለምን መቅጨት፣ ዓለምን ማየት፣ ከዚህ ግጥም ጋር ለምስክርነት ተቆጥረዋል፡፡ ‹ዓለሜ› ሲል ደግሞ ሁለመናዬ የሚለውን ይተረጉም ዘንድ አለው፡፡ ‹‹የዓለም የሲሳይ ቤት ይሁን› ሲባልም ትርጉሙ ሁለመና ነው፡፡ የማይተነተን፡፡ በርግጥ የዛሬ ተጋቢዎች ‹‹እኔ በመሠረትኩት ትዳር፣ እኔ በሠራሁት ቤት – ዓለምና ሲሳይ ምን አገባቸውና የእነርሱ ቤት ይሆናል› ብለው ይሞግታሉ አሉ፡፡
ታድያ ተስፋ ተስፋን ወለደና አቶ ዓለም አየሁም ልጃቸውን ‹ሐዲስ› ብለው ጠሩት፡፡ አዲስ ዘመን፣ አዲስ ዓለም፣ አዲስ አበባ የሚባሉ ተስፋን የሰነቁ ስሞች በወጡበት ዘመን፡፡ የመታደስ፣ የመነሣት፣ የመሠልጠን፣ እንደ አዲስ የመጀመር ምኞት ሥግው በሆነበት ኢትዮጵያዊ ጊዜ ነበርና፣ እርሳቸውም ‹ሐዲስ ዓለም አየሁ› ብለው ትንቢት መሰል ስም ሰጡ መሰለኝ፡፡ 
ታድያ ለእኔ ፍቅር እስከ መቃብርን የደረሱት ልጅዬው ሐዲስ ሳይሆኑ አባትዬው አቶ ዓለም አየሁ ይመስሉኛል፡፡ ቢያንስ እርሳቸው ረቂቁን አውጥተው፣ ትልሙን ተልመው፣ ቅመሙን ቀምመው ለሐዲስ ሳይሰጡ አልቀሩም፡፡ እንገር ሲያጠጧቸው፣ ቅቤ ሲያውጧቸው፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርና ሌሎቹም የሐዲስ ዓለም አየሁ ድርሰቶች – አዲስ ዓለም አየሁ ናቸው፡፡ 
በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ ፊውዳሊዝም እየበሰበሰ፣ ሊሸከሙት ከሚቻለው በላይ እየሆነ ይታያል- በዚያ ውስጥ ጉዱ ካሣ – አዲስ ዓለም አየሁ ይላል፡፡ በድንጋይ ካብ እየመሰለ ሲፈርስ ይታየዋል፡፡ እንደ ሰብለና በዛብህ ያሉ አዳዲስ ትውልዶች፣ ቀደምቱ በቀረጸላቸው ፊደል ብቻ የማይጽፉ፣ ነባሩ በቀደደላቸው ቦይ ብቻ የማይፈሱ፣ የሚያፈተልኩ አዲስ ዓለመኞች ይታያሉ፡፡ ከፊውዳሉ ማኅጸን ውስጥ እንደ ጉዱ ካሣ ያሉ ፈንቅሎች፣ አይፈሬዎችና ለውጥ ፈላጊዎች እንደሚመነጩ – ሐዲስ ዓለም – አይተዋል፡፡ አንድ ሥርዓት እየበሰበሰ፣ ከሕዝቡ የልቡና ሸክም በላይ ሲሆን ያወጣቸው ሕጎችና አሠራሮች እንኳን ሊታደጉት እንደማይችሉ- በፊታውራሪ መሸሻ የደብረ ማርቆስ ክስና ፍርድ – አዲስ ዓለም አሳይተዋል፡፡ 
በነ አበጀ በለው ዐመጽ በኩል አይቀሬ የነበረውን የገበሬዎች እምቢ ባይነት አባታቸው ቀድመው ቢያዩት መስሎኝ – ልጃቸውን – ገና ምኑም ሳይወጠወጥ ስማቸው – ‹ሐዲስ ዓለም አየሁ› ያሏቸው፡፡ 
ደግሞም ‹ሐዲስ› ነገር ሁሉ ደግ አይደለምና የዚህች ሀገር ‹ክፉው› ሐዲስም ታይቷቸው ነበር አባትዬው፡፡ እንደነ አባ ሞገሴ ያሉ በሞራል የወረዱ፣ ተልዕኳቸውንም የሳቱ፣ ሥልጣን የያዘውን ብቻ ማወደስ ሥራቸው የሆነ መንፈሳዊ መሪዎች፣ በነ አቡነ ጴጥሮስ ቦታ እንደሚተኩ ታይቷቸዋል ልበል፡፡ በ65 – 66 ብቅ ያለው የእንቡጦቹ የአብዮት ሙሽሮች የወጣቶቹ የለውጥ ጉዞ፣ ከስኬት ሳይደርስ መንገድ እንደሚቀር ቢታያቸው አይደል እንዴ – ሰብለ ወንጌልንና በዛብህን ጎሐ ጽዮን ላይ ያስቀሯቸው፡፡ እንደነ በዓሉ ግርማ፣ እንደነ አቤ ጎበኛ፣ እንደነ ግርማቸው ተክለ ሐዋርያት ያሉ ጉዱ ካሣዎች፣ እዚህች ሀገር ፍጻሜያቸው ለውጥ አምጥተው፣ በትውልዱ ዘንድ ከፍ ብለው መታየት ሳይሆን፣ ከለውጥ አምጭው ትውልድ ጋር አብሮ መሞትና መቀበር መሆኑን ቀድመው በትንቢት መነጽር ቢያዩም አይደል እንዴ ጉዱ ካሣን ከነ ሰብለና በዛብህ ጋር ጎሐ ጽዮን የቀበሩት፡፡ 
በዛብህ አዲስ አበባ ሩፋኤል ነበር የመጣው፡፡ ሰብለንም ሊያመጣት ያሰበው አዲስ አበባ ሩፋኤል ነበር፡፡ ሩፋኤል ደግሞ ፈታሔ ማኅፀን ነው፡፡ የጦቢትን ዓይንም የገለጠ እርሱ ነው፡፡ ‹‹በዓለ መድኃኒትም›› ይባላል፡፡ በዛብህ ግን ማኅፀን ፈቺውንና በዓለ መድኃኒቱን አየው እንጂ አላገኘውም፣ ተሳለመው እንጂ አልተሾመበትም፡፡ ይህቺ ሀገር አንዱ የሚያስፈልጋትኮ የኪነ ጥበብ፣ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲ፣ የዕውቀት፣ የጥበብ፣ የፖለቲካ፣ የለውጥ፣ የሰብአዊነትና የእምነት ጀግኖች ትወልድ ዘንድ ፈታሔ ማኅፀን ነው፡፡ የሚያዋልድ፣ ከምጥ የሚያሳርፍ፡፡ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አካባቢያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ዕውቀታዊ፣ ተቋማዊ ሕመሞቿ እንዲድኑ በዓለ መድኃኒት ያስፈልጋታል፡፡ የትውልዱም ዓይን ከጫትና ከሐሺሽ፣ ከፊልምና ዳንስ፣ ከውጭ ሀገርና ከስደት፣ ላቅ ያለ ነገር እንዲያይ እንደ ጦቢት ዓይን ገላጭ ያሻታል፡፡ በዛብሃዊው ሰብላዊውና  ጉዱ ካሣዊው ትውልድ ግን ገና አላገኘውም፡፡ ጎሐ ጽዮን ላይ ቀረ፡፡ ይህን ይሆን አባትዬው ‹ሐዲስ ዓለማየሁ› ያሉት፡፡ ‹በሩቅ አይቶ የሚሳለም ግን የማያገኝ› ትውልድ የሚኖርባትን ኢትዮጵያ አይተው፡፡  
ጎሐ ጽዮን – ጽዮን ኢትዮጵያ አይደለችም እንዴ፡፡ የጽዮን ሀገር ናትና ኢትዮጵያ፡፡ ‹‹በስመ ኀዳሪ ይፄውእ ማኅደር – እንዲል በአዳሪዋ በጽዮን ስም ማደሪያዋ ኢትዮጵያም ጽዮን ተብላ ተጠርታለች፡፡ – የጽዮን ጎሕ – እዚያ ነው አዳዲስ ለውጠኞች የተቀበሩት፡፡ አብዮት ልጇን ትበላለች እንዲል መሆኑ ነው፡፡ ብዙዎቹ በዛብሆችና ሰብለዎች፣ ብሎም ጉዱ ካሣዎች – የጽዮን ጎሕ ውስጥ ነው የተቀበሩት፡፡ ዓባይ በረሃ ሳይወስደቸው፤ ግን ሳይሻገሩት፣ አፋፍ እያስቀራቸው፡፡ የጽዮን ጎሕ ውስጥ ገብተው ቀሩ፡፡ ችግሩ ደግሞ ደጀንና ጎሐ ጽዮን ከመለያየታቸው ላይ ነው፡፡ ደጀን ማዶ ጎሐ ጽዮን ማዶ፤ በመሐል በረሃ፡፡ ደጀኑ ሕዝብ ጎሑን አይከተል፣ ወይ ጎሑ ደጀኑን አያስከትል፡፡ ጎሕና ደጀን ለየብቻቸው ይሄዱና ደጀኑ ለውጥ አምጭዎችን ጎሐ ጽዮን ላይ ቀብሮ ዝም ይላል፡፡ ይህን ነው ያዩት – ዓለም አየሁ፡፡
ራሳቸው ሐዲስስ ቢሆኑ ይህንን ዐርባ ዓመት የተቀመጠ የጎጃም ጠላ የመሰለ ልዩ ድርሰት እንዳልደረሱ ተቆጥረው ባለፉት ዘመናት ጎሐ ጽዮን ላይ ተቀብረው አልነበር እድሜያቸውን የጨረሱት፡፡ አባትዬው የጻፉትን ድርሰት ልጅዬው ፊልሙን በቁም አልሠሩትም እንዴ፡፡    
ምርቅና ፍትፍት፣ ግርድና ምርት፣ ጥሬና ብስል የሚጋፉባትን፤ ደጀንና ጎሐ ጽዮን የተለያዩባትን – አዲሷን ኢትዮጵያ አይተው ነው- ሐዲስ ብለው የሰየሟቸው፡፡ እስመ ስሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ እንዲል፡፡ 
 

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሴቶች ዘርፍ ጥበቃ በነሦሊያና የክስ መዝገብ በተከሰሱት ማኅሌት ፋንታሁንና ኤዶም ካሣዬ ላይ “የተፈፀመ በደል የለም” ሲል ለፍርድ ቤት መልስ ሰጥቷል፡፡አቃቤ ሕግ ደግሞ የተከሣሾቹ ጠበቆች በማስረጃነት የተጠቀሰው…

The post በዞን ዘጠኝ ሴት እሥረኞች አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤት መልስ ሰጠ – VOA appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የሕወሃት መንግስት በመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ አዉጥቶ፣ ለሳምንታት ስለ ለካቲት 11 የሕወሃት 40ኛ አመት ሲለፍፍ ነበር። የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች በመቀሌ እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን፣ ሽር ጉዱም መላው የኢትዮጵያ ህዝበ እስኪታዘብ…

The post የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ የኦሮሞ ምድር ነው (የአድዋ መንፈስ) – አማኑኤል ዘሰላም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በሄኖክ ሰለሞን ትናንት በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት ከአስር አመት በታች የሆኑ ልጆች ህይወታቸው አለፈ።…

The post በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ የሶስት ህፃናትን ሀይወት አጠፋ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

አጭር የፍርድ ቤት ውሎ
የሁለቱ ሴት ታሳሪያንን አያያዝ እስመልክቶ ዛሬ ለ22ተኛ ግዜ የተሰየመው ችሎት ለመጋቢት 10 ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ተጠናቋል ፡፡
የመጀመሪያው ጉዳይ የሆነውና የማህሌት ፋንታሁን እና የኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ የተነሳው አቤቴታ ላይ መልስ የሰጡት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ዋና ሱፕር ኢንቴንዳንት ለተእግዜር ገ/ እግዜያብሔር ምንም አይነት የመብት ጥሰትና የጎብኚ ክልከላ እየተደረገባቸው አይደለም አንደማንኛውም ታራሚ በማንኛውም ሰው ይጠየቃሉ ሲሉ ሽምጥጠው ክደዋል፡፡
ሁለተኛው የሆነው አቃቤ ህግ በእጁ ያሉትን 12 የኦዲዬ ቪዲዬ ሲዲዎች ለጠበቆች አንዲሰጥ የጠየቁበት ቢሆንም አቃቤ ህግ መመልሱ በችሉት ወቅት ያዩታል እንጂ ፓሊስ ኤግዚቢት ለጠበቆች የመስጠት የሚያስገድደን ህግ የለም ብሏል፡፡ ( የአቃቤ ህግ ምላሽ ከስር ተያይዞ ይገኛል)
ሁለቱም ጉዳዬች ላይ ብይን እሰጣለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ ወንዶች ተከሳሾችም ተገኝነተው ብይኑን እንዲሰሙ አዟል፡፡

 

የዞን9 ማስታወሻ
የቀረበብንን ማስረጃ አይተን የመከላከል ህገ መንግሰታዊ መብታችን መጣሱን አጥብቀን እየተቃወምን መሰረታዊ ከፓለቲካ ነጻ ውሳኔ መስጠት መቻሉ የሚያጠራጥረው ፍርድ ቤት ቢያንስ በስነስርአት ጉዳዩች ላይ አንኳን ስልጣኑን እንዲጠቀምበት እናሳስባለን ፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን!
በነገው እለት የ 26 ተኛ አመት የልደት በአልህን ለምታከብረው ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ አንወድሃልን፡፡ አንኮራብሃለን
ዞን9

ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክ ኣባል ናቸው። በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሂወታቸው ልታልፍ ምንም ኣልቀረላቸውም ነበር። ይህ ድብደባ በ17/ 2007ዓ/ም ማታ 1 ሰዓት ኣከባቢ በ1ፖሊስ ድምብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የፈጥኖ ደራሻ ደንብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የመከላከያ ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች […]

ኢቢሲ የመኢአድን መልእክት ላለማስተላለፍ የሰጠው አንዱ ምክንያት፣ መልእክቱ የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን ይጻረራል የሚል ነበር።፡ “ ..የገዢ ፓርቲ ካድሬዎችና አመራሮ በፓርቲው መሪዎች፣ አባላቶችና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነና ግፍ የተሞላበት ድብደባ ፣ መሰደድና ሜታሰርና የመግደል ዕጣ ሲደርስባቸው ቆይቷል፤ ..” የሚለው የመኢአድ አባባ የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11፣ ንኡስ አቀንጽ 2ሀ ላይ የተመሰረተዉን ይጻረራል […]

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆነው አግባው ሰጠኝን ጨምሮ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮች ጠበቆች በፖሊስ ላይ አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ሊመሰርቱ ነው፡፡ ፖሊስ ዛሬ የካቲት 25/2007 ዓ.ም በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ላይ የመጨረሻውን ምርመራ ሊያሰማ ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም በቀጠሮው መሰረት አመራሮቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ባልቀረቡበት ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሻለሁ ብሎ መዝገቡን እንደዘጋ ለፍርድ […]

በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ…

The post በጄኔቫ የሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ “የተቃዋሚ ደጋፊዎች ናችሁ”ላላቸው ኢትዮጰያውያን ፓስፖርት አላድስም አለ። appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ብዙ ሰዎች ስለ እነ ትዕግሰቱ አወሉና ግብረ አበሮቹ መፃፍ ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡ ምክንያታቸውም ደረጃቸውን ከፍ ያደርገዋል የሚለው አንዱ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ከፍ ቢሉም ቢወርዱም እውነቱን ሰው አውቆት ፀሐይ ሞቆት መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሰለዚህ እፅፋለሁ፡፡ በቅርቡ የወጣ “የእኛ ፕሬስ ጋዜጣ ላይ አቶ ትዕግሰቱ በእርሱ ብሶ ቱግ ቱግ እያለ የሰጠውን ቅጥፈት የተሞላበት ቃለ መጠይቅ አይቼ […]

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም በሱዳናዊ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት ወጣት ማረፉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወጣቷ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ተወጋግታ መሞቱዋን የገለጹት የወረታ ነዋሪዎች፣ ሹፌሩ በቁጥጥር ስር ውሎአል ቢባልም በትክክል ስላለበት ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ጭኖ ይጓዝ የነበረውን መኪና …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከሳሽ ኣቃቤ  እና  ህግ በተከሳሽ አቶ ኣስገደ ገ/ሥላሴ መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር  ለምስክርነት የተጠሩት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊቀርቡ ባለመቻካቸው  በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ  ቢታዘዝም፤  ባለስልጣናቱ  ከለመዱት ምቹ ህይወት አኳያ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ። የህወሀት የደህንነት ሰራተኛው ብስራት አማረ  የመሰረተባቸውን ክስ  ተከትሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲከራከሩ  የቆዩት የቀድሞው የህወሀት ታጋይና …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት  ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት  ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ ስለለዩዋቸው አገልግሎቱን  ሳይሰጡ መልሰዋቸዋል። ኤምባሲው እንደደረሱ ጎይቶም በሚባል ሰራተኛ የተሰጣቸውን ፎርም ከሞሉና ፎቶግራቸውን ከሰጡ በሁዋላ በስዊዘርላንድ ለምን …

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀፍታ ሑመራ ወረዳ  በረኸት  ከተማ  ነዋሪ የሆኑት ቄስ ሕሉፍ ኸሕሳይ የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣ መረጃ አመለከተ። እንደ መረጃው ከሆነ  ቄስ ህሉፍ  በደረሰባቸው ዘግናኝ ድብደባ  በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙ ሲሆን፤ ለድብኢደባቸው ምክንያቱ  የአረና አባል መሆናቸው ብቻ ነው። የካቲት 17 ቀን 2007ዓመተ …

ከመሸ ብርሃኑ ተዘራን (ብሬ ላላን) በስልክ  ያገኘው ናቲ ላቀረበለት ጥያቄ እንዲ ሲል መልሷል ምንድነው ምሰማው  ስለ ጃኪ ጎሲ ድምፄን ሰረቁኝ እያለ ነው በማለት ጥያቄ ለብሬ ላላ አቀረብኩለት ብሬ ቀጠለ ናቲሻ በማለት…

The post ጃኪ ጎሲ እነ ብርሃኑ ድምፄን ሰረቁኝ አለ ለምን ? ያንቢቡት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

መንግሥታት በኢንተርኔት አማካይነት ከዜጎቻቸዉጋር የሚደረግ ግንኙነት E-Government በመባል ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ባደረገዉ ጥናት መሰረት ደቡብ ኮሪያ፤አውስትራሊያ፤ሲንጋፖር እና ፈረንሳይ ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀዳሚዉን ሥፍራ ይይዛሉ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት እና የዓማፅያኑ መሪ ሪየክ ማቸር በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ሸምጋይነት ትናንት እንደገና በአዲስ አበባ የጀመሩትን የሰላም ድርድር ዛሬም ቀጥለው ዋሉ። ደቡብ ሱዳን ከታህሳስ ፣ 2013 ዓም ወዲህ

የቱኒዚያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የድረገጽ ጸሐፊ በሆነዉ ቱኒዚያዊ ያሲን አያሪ ላይ የጦሩን ስም በማጥፋት ወንጀል እስራት ፈረደ። ያሲን የተከሰሰዉ የሀገሪቱ የጦር ኃይል መኮንኖች እና የመከላከያ ባለስልጣናት የሚፈፅሙትን የገንዘብ ብክነት አስመልክቶ ከሀገሩ ዉጭ ሆኖ በድረገጽ በመጻፉ ነዉ።

በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተውን የኤቦላ ስርጭት ለማብቃት የተደረገውን ዘመቻ ለመገምገም ትናንት በብራስልስ የተጠራው ዓለም ስብሰባ በበሽታው የተጎዱት ሀገራት ውስጥ የተኀዋሲው ስርጭት በጠቅላላ እስኪያቆም ድረስ መቀጠል እንዳለበት አሳሳበ።

የዓረና-መድረክ ኣባል በፖሊስ ድብደባ ደረሰባቸው ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክ ኣባል ናቸው። በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ…

The post በግፍ ላይ ግፍ በህወሓት.. ! – አምዶም ግብረ ስላሴ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.


“ሸላሚም እኛ፣ ከሳሽም እኛ! “
አብርሃም ሰለሞን የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ያሳደገው ኢሕአዴግ ራሱ (ወይም ዘመነ መንግስቱ) ነው፡፡ በቤተልሄም የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ IT መምህር ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ መልካም ዝና ነበረው፡፡ በ2006 በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ውድድር ላይ ይዞ በቀረበው የመምህራን ዳታ ቤዝ እና የመማሪያ ማኑዋል ዝግጅትን አሸናፊ መሆን ከቻሉ ሦስት ወጣቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ጥቅምት 16/2007 – በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሸላሚነት ሲካሄድ በነበረው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን IT ለማስተማር የሚረዳ የዴስክቶፕ ሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን በማዘጋጀት የሜዳልያ ተሸላሚ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ የዘንድሮውን የስራውን ውጤት በአካል ተገኝቶ ሰርተፍኬቱንም፣ ሜዳልያውንም መቀበል አልቻለም፤ በእሱ ፈንታ እናቱ በውክልና ተቀብለውታል፡፡ ምክንያቱም እሱ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ ቂሊንጦ ማቆያ ቤት ይገኛል፡፡
አብርሃምን ስለ አገሪቱ የወደፊት ተስፋ ሰጪ ስራ ሰርተሃል ብሎ በቀኝ እጁ የጨበጠው መንግስት፣ በግራ እጁ ደግሞ ለአገሪቱ የወደፊት ተስፋ አደገኛ አሸባሪ ነህ ይለዋል፡፡
 

 ከግራ ወደቀኝ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሀብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞን፡፡

“የማይተዋወቁ ግብረ – አበሮች”
በሽብር የሚከሰሱ ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በአንድ መዝገብ (እንደ ግብረ አበር) የሚታሰሩበት አሰራር የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ የነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ በመባል የሚታወቀው (መዝገብ ቁጥር 166/07) አንዱ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ አራት የተለያዩ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች 6 ተጠርጣሪዎች ተከስሰዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ 5 ተከሳሾች (ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ እና የሺዋስ አሰፋ) በፀረ- ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ  4 ሲከሰሱ፣ ቀሪዎቹ አምስቱ (ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳኑ፣ እና ተስፋዬ ተፈራ) በአንቀፅ 7/1 እና 9ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ዳጉ) በሌላ ክስ በወንጀለኛ መቅጫው 288/1 መሰረት ከመከላከያ ሰራዊቱ በመኮብለል ተከስሰዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ክሳቸው በአንድ መዝገብ ታጭቀው ቢመጡም ባብዛኛው እርስ በርስ አይተዋወቁም፤ በጋራ የሰሩት ስራም የለም፡፡
በፌስቡክ እንቅስቃሴው በስፋት የሚታወቀው እና የአረና ትግራይ ፓርቲ አመራር አባል የነበረው አብርሃ ደስታ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ከሆነው ሀብታሙ አያሌው በቀር የሌሎቹን ስም እንኳን አብረው ከመከሰሳቸው በፊት አለመስማቱን ይናገራል፡፡ ተሸላሚው አብረሃም ሰለሞንም ከተከሳሾች የሚያውቀው ዘላለምን ብቻ ነው፡፡ ‹‹እሱንም›› ይላል አብርሃም ‹‹በ2006 አንድም ቀን አግኝቼው አላውቅም››፡፡ ከተከሳሾች መካከል ብዙ ሰው ያውቃል የተባለለት 1ኛው ተከሳሽ ዘላለም እንኳን የሚያውቀው ሦስቱን ብቻ ነው – ዮናታን፣ አብርሃምን እና ባሕሩን ብቻ፡፡
“በስልክ የማውራት አሸባሪነት”
በሽብር የተከሰሱ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ እና በተለይ ከሚቀርቡ የማስረጃ ዓይነቶች አንዱ የስልክ ግንኙነት ነው፡፡ ከላይ በጠቀስነው መዝገብ ውስጥ ብቻ ክስ ሆነው የቀረቡትን የስልክ ግንኙነቶች እንመልከት፡-

  • 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ‹‹በ 2000 ተድላ ደስታ ከተባለ የሽብር ድርጅቱ አባልና አመራር ጋር በስልክ እና በፌስቡክ›› በማውራት
  • 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ዘመኑ ካሴ ከተባለ የግንቦት ሰባት ታጣቂ›› ጋር በጥር 14/2005 በስልክ በማውራት፤
  •  3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔ አለም ›› ጋር በየካቲት 29/2003 በስልክ በማውራት፤
  •  4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹የደ.ም.ሕ.ት. አመራር ከሆነው ጎይቶም በርሄ ›› ጋር ጥር 3/2006 በስልክ በማውራት፤ 
  •  5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔአለም›› ጋር ጥቅምት 14/2006 በስልክ በማውራት፤
  • 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ፣ የግንቦት ሰባት ክንፍ ከሆነው የአ.ዴ.ኃ.ን አባል ጋር ሕዳር 2003 በስልክ በማውራት፤

እነዚህ የስልክ ግንኙነቶች ያለሌላ ተጨማሪ ማስረጃ በብቸኝነት የክስ መመስረቻ መሆናቸው ደግሞ ክሱን ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ዜጎች የስልክ ግኑኝነቶችን በሙሉ እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል፡፡ በሽብርተኝነት በተጠረጠሩ ድርጅቶች ውስጥ በዐቃቤ ሕጉ ቃል ብቻ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎች ስለደወሉለት ብቻ የተደወለለት ሰው ‹‹አሸባሪ›› ተብሎ ይከሰሳል፡፡ ፈቅዶ ባልተደወለለት ስልክ ወንጀለኛ ነህ የሚባልበት አሰራር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስልም፡፡ አንዳንዶቹ የስልክ ጥሪዎች የተደረጉት ‹‹ሽብርተኛ ናቸው›› በተባሉ ድርጅቶች ውስጥ ባሉ እና በሚታወቁ ግለሰቦች ሳይሆን የአቃቤ ህግ ቃል ብቻ ያልሆነውን ነው ብሎ ስላቀረበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ሳይፈረድባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትም የዚያኑ ያክል ናቸው፡፡ በ2000 የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ አልወጣም ነበር፤ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችም አልነበሩም፡፡ ክሱ ላይ ግን በዚያ ወቅት የተደረገ የስልክ ግንኙነት ተጠቅሷል፡፡
በሁሉም የሽብር ክሶች ውስጥ copy/paste የተደረገች ውንጀላ አለች፤ ‹‹ራሱን [እከሌ ]ብሎ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ግንኙነት በመፍጠርና ተልእኮ በመቀበል ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ . . . ‹‹የምትል ነች፡፡ ይህች ቃል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ድርጊት ሳይጠቅስ የሚያስቀጣበት ውንጀላ  ነች፡፡ በዚሁ በነዘላለም መዝገብም ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሳለች፡፡ በስልክ አንድ ሰው ጋር ያወራሉ ከዚያ ተልእኮ ይቀበላሉ፡፡ ሽብር ማለት በቃ ይኽው ነው፡፡
“ሥልጠናዎች ሁሉ ሽብር ናቸው”
በነዘላለም መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 6ኛ እና 9ኛ ተከሳሽ(ዮናታን እና ባሕሩ) ክስ ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፡፡ይኸውም ‹‹ በመንግስት ላይ ያሉ ችግሮችን ለሕዝብ በተለያዩ የኢንተርኔትና የማህበራዊ ድህረ – ገፆች ላይ በመፃፍ ለግል ሚዲያዎች ግብአት የመስጠት ሥራ የሚሰሩ ቡድኖች አሉ፡፡ ለዚሁ ተግባር ተብሎ የወሰዱትን የኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ኮሙኒኬሽን ስኪል እና ሊደርሺፕ በመሰልጠን ተጠቅመዋል እናንተስ እንዲህ አይነት ስልጠና አትፈልጉም ወይ?›› በሚል አንደኛ ተከሳሽ ለሁለቱ ተከሳሾች ቀርበዋል የተባሉት ጥያቄዎች ወንጀል ተብለው ተፅፈዋል፡፡ ‹‹ሠልጥነዋል›› ተብለው በምሳሌው የተጠቀሱት ‹‹ቡድኖች›› ዞን ዘጠኞች መሆናቸው በሌላ ማስረጃ ተጠቅሷል፡፡ሥልጠናውን ዐቃቤ ሕግ 9ኛ ተከሳሽ ላይ ሲጠቅሰው መጀመሪያ ‹‹ተመሳሳይ ሥልጠና ለተመሳሳይ አላማ ›› ይልና ዝቅ ብሎ ‹‹የሽብር ድርጅቱን ተልዕኮ ለመፈፀም እንዲረዳቸው ባዘጋጁት ስልጠና ›› ይላል፡፡ የመንግስታችን ችግሮች መፃፍ ፣ ወይም ለመፃፍ መሰልጠን በምን መሥፈርት አሸባሪነት ተባለ?
“አብርሃም ሰለሞንን ማን መለመለው?”
የክስ መዝገቡ መጀመሪያ ላይ ‹‹[አብርሃም ሰለሞን] በ1ኛ ተከሳሽ  [ዘላለም] አማካኝነት ለሽብር ድርጅቱ በአባልነት ተመልምሎ . . . ›› ይላል፡፡ አንድ አንቀፅ ዝቅ ብሎ ደግሞ ‹‹[አብርሃምን] በአባልነት የመለመለው አንደኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር [እዮብ] አማካኝነት . . . ›› ይላል፡፡ አብርሃምን የመለመለው ዘላለም ወይስ እዮብ? (ብቸኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር) መልምሏል የተባለው አብርሃምን ብቻ አይደለም፡፡ 8ተኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማንም ጭምር እንጂ፡፡ እዮብ ሰለሞንን ሲመለምል ተናግሯል የተባለው ይህንን ነው፤
‹‹ኤርትራ ሀገር ግንቦት ሰባት የተባለ ጥሩ ድርጅት አለ፡፡ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሥልጠና ሠልጥነህ ከድርጅቱ ጋር ከተቀላቀልክ በኋላ ግንቦት ሰባት የሚሰጥህን ተልዕኮ ተቀብለህ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዋጋለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቡን በኃይል እየገዛ ነው ስለዚህ ታግለን መጣል አለብን፡፡ ››
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተጠርጣሪዎች ጋር ታስረው ቆይተው ኋላ ላይ ምስክር ለመሆን ሲስማሙ መለቀቃቸው የተለመደ ነው፡፡ የፀረ ሽብር ሕጉ ሽብርን ለማጋለጥ ለተባበረ ርሕራሔው ይኼን ይመስላል፡፡ ነገር ግን ክፍተት አለው፡፡ ተጠርጣሪዎች በአባሪዎቻቸው ወይም ሌሎች ላይ መስክረው መፈታት እንደሚችሉ ቃል ሲገባላቸው በሐሰትም ቢሆን ለማድረግ የሚስማሙበት ዕድል አለ፡፡ በዚህ መንገድ መልማዩ ምስክር ሆኖ የሚቀርብበት ተመልማዩ ላይ ይሆናል፡፡
በዚህ ዓይነት መንግስት ያልወደደውን ፖለቲከኛ (ዜጋ) ስልክ ሲደወል ደዋዩ አሸባሪ ነው በማለት፣ ወይም የራሱን ሰው ልኮ በማባበል ለ‹‹ሽብር›› መልምሎ ሲያበቃ መልማዩን ምስክር ተመልማዩን ተከሳሽ ለማድረግ ወይም ደግሞ በስጋት ሰብስቦ ካሰራቸው ሰዎች መሃከል ለነፍሳቸው ግድ የሌላቸው የሃሰት መስካሪዎችን እያሰለጠነ እየፈረደ ሊኖር ይሆን?!  

የሄሊኮፕተር እገዛ አልያም የውኃ ቦቴ መኪኖች ድጋፍ እየተጠየቀ ነው በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም፣ ትላንት ጠዋት የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ አሞራ ገደል በሚባለው አቅጣጫ መዛመቱ ተገለጸ፡፡ በሰሜን በኩል ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው የገዳሙ መውጫ ትላንት ጠዋት 2፡00 የተቀሰቀሰው ቃጠሎ፣ በአዱላላ ወረዳ ሠራተኞችና በነዋሪው ሕዝብ ርብርብ ማምሻውን መጥፋቱ ከተገለጸ በኋላ …

ዳንኤል አበራ

1. መቅድም: ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጴጥሮስ አሸናፊ

እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ

አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ እኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሊቁ እጅጉ

በዓለም ታሪክ ውስጥ አምባገነን ገዥዎች ለሥልጣናቸው የሚሰጡት ሕጋዊ ሽፋን ከሁሉም በላይ አዋቂዎች፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪዎች፣ የድሆችን እንባ ጠባቂና … ወዘተ ስለሆነም እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይሰይማሉ። አንዳንድ በአመጽ ሥልጣን ላይ የወጡ ቡድኖችና መሪዎች ብዙ ግዛቶችን በጭካኔ አጥቅተው ከያዙ በኋላ ሰው መሆናቸውን እስከመካድም ደርሰው ነበር። ሆኖም ግን መጨረሻቸው እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ውጤታቸው ታላቅ ውርደትና በሕዝብ ዘንድ መጠላትን፣ ውድቀትንና የሕዝብ እልቂትን ከማስከተልና የታሪክ አተላ ከመሆን አላመለጡም፣ አላለፉም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ (ከኢትዮጵያ)

ዛሬ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የወያኔ 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል መዘምዘሚያ በወያኔው አባል በቱጃሩ አላሙዲን የሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ እየተከበረ ነው። ዘፈንና ደስታ አለቅጥ ሲበዛ የሚያስከትለውን ምልኪያዊ ሀዘን የተረዱ አይመስሉም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

“አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

• ‹‹ቀድሞውንም እንዳያማ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ
Image
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡

ኢብኮ አላስተላልፍም ብሎ ለመመለሱ በዋነኛነት የጠቀሰው ምክንያት ‹‹ለማጀቢያነት ለተጠቀማችሁት ሙዚቃ የባለመብቶቹን ፈቃድ ስለመኖሩ ማረጋገጫ አላመጣችሁም›› የሚል ነው፡፡ ኢብኮ ሌሎች ጉድለቶችን ያልጠቀሰ ቢሆንም በጥቅሉ ‹‹የምርጫ ህጉን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ፣ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ህጎች ወይንም ማንኛውም ህግ የሚተላለፍ መሆኑን በቂ ምክንያት ካለው መልዕክቱን አላስተላልፍም የማለት መብት አለው….›› በሲል ፓርቲው የላከውን የቅስቀሳ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሚቸገር ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የፓርቲው የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ ገዥው ፓርቲ የግለሰብና የፓርቲ ስም እያጠፋ፣ የመደራጀት፣ ሀሰብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን በጣሰ መልኩ ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነ ገልጸው ሰማያዊ ፕሮግራሙ ላይ ያስቀመጣቸውን ሀሳቦች እንዲቀይር እየተጠየቀ መሆኑ ሚዲያዎቹ ለገዥው ፓርቲ ያላቸውን ወገንተኝነት በድጋሜ ያጋለጠ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

‹‹የመንግስት ሚዲያዎች ተግባር ቀድሞውንም እንዳያማ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ነው፡፡ ቢያንስ በዚህ ጊዜ እንኳን ፍትሓዊ መሆን ነበረባቸው›› ያሉት አቶ ስለሽ የመንግስት የሚባሉት ሚዲያዎች በወንጀል ሊያስከስስ የሚችለውን የኢህአዴግ ቅስቀሳ ያለ ምንም ምርመራ እያስተላለፉ ሰማያዊ ላይ ህገ ወጥ ቅድመ ምርመራቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚልና መልዕክቱ ላይ የተጠቃለሉትን የፓርቲው አቋሞች እንዲያስተካክል በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡