አንድነት ፓርቲ በመጪው ዕሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 በደብረማርቆስ፣ በአዳማ/ናዝሬት እና በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ፤ የቅስቀሳ ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ቡድኖች ከትላንት ጀምሮ ከዋናው ጽ/ቤት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ዛሬ በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚደረገውን ቅስቀሳ የሚያስተባብረው ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ በደብረ ማርቆስና በአዳማ የተጠናከረ ቅስቀሳ ከተሰራ በኋላ የፖሊስ የተሟላ […]

በቦስተንና አካባቢዋ ከ3ዓመት በፊት በወጣት ሀዲስ ግርማ መታስቢያነት የተቋቋመው የሀዲስ ግርማ የመታስቢያ ድርጅት የ3ኛ ዓመት ጉባዔ እሁድ ጁን 1 ቀን 2014 ዓ. ም. በረስል ዩዝ ኮሚኒቲ ሴንተር፣ ካምብሪጅ (Russell Youth Community Center, Cambridge, MA) በተለያዩ ዝግጅቶች በተሳካ ሁኔታ ተካሄዷል። በእለቱ ከተካሄዱት ፕሮግራሞች የመጀመሪያው እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበው በዚህ አመት በሀዲስ ግርማ መታስቢያ ድርጅት እና በወላጆች […]

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

እአአ በሰማንያኛዎቹ ዓመታት በሱዳን በኩል አድረገው ወደ እሥራኤል ለመሄድ ሲሞክሩ በጉዞ ላይ ለሞቱት የኢትዮጵያ አይሁዳውያን በሄርዝል ተራራ በቆመው የመታሰቢያ ሐውልት በያመቱ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የ1,500ዎቹ ስም በሐውልቱ ላይ ተቀረጸ።

ትናንት በፖላንድ መዲና ዎርሶ የአውሮጳ ጉብኝታቸውን የጀመሩት የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ሀገራቸው የምሥራቅ አውሮጳ ሀገራት ደህንነታቸውን እና ፀጥታቸውን ለማስጠበቅ በሚያደርጉት ተግባራቸው ላይ ከጎናቸው በመቆም

የሰባቱ የዓለም ዓበይት ኢንዱስትሪ መንግሥታት ጉባዔ በአሁኑ ሰዓት ቤልጅየም መዲና ብራስልስ ተጀመረ፣ ቡድን ስምንት በመባል ይታወቅ የነበረው ቡድን አባል የነበረችው እና ያሁኑን ጉባዔ ማዘጋጀት የነበረባት ሩስያ፣ እንደሚታወሰው፣ ከጥቂት

ከ 2 ሳምንት በፊት በዚህ ክፍለ ጊዜ ባቀረብነው ዝግጅት፣በብሪታንያ ከ 300 ዓመታት በፊት በፓርላማ ተመክሮበት ከጸደቀ በኋላ የተጀመረው፤ ለሕብረተሰብ ጠቀሜታ የሚሰጥ፤ «ሎንግትውድ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ሽልማት ፣ አሁንም ደንቡ የጸደቀበት 300ኛ

ጓዶች ዓረና ባደረገው እንቅስቃሴ በትግራይ ክልል ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አረጋግጧል። ይሄን ጉዳይ ህወሓትም ተረድቶታታል። እናም የህወሓት አመራር አባላት ዓረናን ለማዳከም አባላቶቻችን በጥቅም በመደለል፤ ካልተሳካ ደግሞ በማስፈራራት እንዲሁም በድንጋይ በመውገር ህዝብን የማነሳሳት እንስቅስቃሴያቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ሞክረዋል። አልሆነም። እናም አሁም የዓረና አባላትን (አስተባባሪዎችን) ለማሳሰር ዉሳኔ ተላልፈዋል። አሁን በግፍ ማሰር ጀምረዋል። አባላትን በማሳሰር ዓረናን ማዳከም ግን አይቻልም። ምክንያቱም […]

(በፀሐፊው ፈቃድ ከፌስቡክ ተወስዶ የተለጠፈ)፦ ዛሬ ግንቦት 27 30ኛው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ እንደሌሎቹ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮች ሁሉ ይህንን አባትም የትሩፋቱንና የዕውቀቱን ዜና በሰሙ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ያለፍቃዱ ይዘውት ሊቀ ጵጵስና ሾሙት፡፡ የዕለቱ ስንክሳርወደረሰ ድርሳናተ ብዙኃተ ወአቀመ እግዚአብሔር በመዋዕሊሁ ቀርነ ቤተ ክርስቲያንእንዲል በዘመነ ፕትርክናውም ብዙ ድርሳናትን የደረሰና የቤተ ክርስቲያንን ስልጣን ያጸና አባት ነው፡፡

በዚሁ ዕለትም የማርያምና የማርታ ወንድም የሆነውና ጌታችን ከሞት እንዳስነሳው በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ታሪኩ በሰፊው የተጻፈው አልዓዛር የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ይህ አልዓዛርም ጌታ ካስነሳው በኋላ ከሐዋርያት ጋር የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ የተቀበለ እና በኋላም ሐዋርያት እጅ በመጫን በቆጵሮስ አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት የሾሙት ነው፡፡ እርሱም መንጋውን በመልካም አጠባበቅ ጠብቆ በሹመቱ አርባ ዓመታትን ኑሮ በሠላም አረፈ፡፡አረፈየተባለለትም ይኼኛው ዕረፍቱ እንጂ ወደእግዚአብሔር ከመመለሱ በፊት፣ ለአገለግሎት ከመጠራቱ በፊት፣ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከመቀበሉ በፊት እንዲሁም የተሰጠውን የክህነት አደራ ከመወጣቱ በፊት የሞተውሞቱንአይደለም፡፡
እንደቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን እኛም እነዚህን ሶስት ነገሮችን በአባቶቻችን ዘመነ ፕትርክና ለማየት እንናፍቃለን፡፡ እነዚህም ለፍቅረ ሢመት ግድ ሳይኖራቸው ነገር ግን ትሩፋታቸውና ዕውቀታቸው ብቻ ታይቶ ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማሉ ተብለው ሳይወዱ በግድ የሚሾሙ የተሾሙት ለሥራ መሆኑን አውቀው በቃል በመጽሐፍ ምዕመኑን በማስተማር የሚተጉ፣ እንዲሁም በዘመነ ሢመታቸው ሁሉ የክርስቶስን መንጋ በመልካም አጠባበቅ የሚጠብቁ ኤጲስቆጶሳትንና ሊቃለ ጳጳሳትን፡፡
ካህናት አባቶቻችን ሳይወዱ ተገድደው በትሩፋታቸውና ዕውቀታቸው ብቻ የተገባቸው ሆነው ኤጲስቆጶስነት ሹመት የሚበቁበትን ጊዜ የማይናፍቅ እውነተኛ ምዕመን የለም፡፡ በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ ቦረዳ ገዳምን በአበምኔትነት እያስተዳደሩ እንዳሉት አባት ከአንዴም ሁለቴ ለኤጲስቆጶስነት ታጭተውተውኝ እኔ እዚሁ ጸሎት እያደረኩ ልኑርብለው እምቢ ያሉ ጥቂት ደጋግ እና ቀና አባቶች በዘመናችንም ቢኖሩም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በመጣ ቁጥር ሳይገባቸው ለኤጲስቆጶስነት ሹመት የሚቋምጡና ለዚህም በሥራ ዘርፉ የተሰማሩ እበላ ባዮችን ኪስ እንደሚያደልቡ በተደጋጋሚ የምንሰማው ለጆሮ ግን የሚሰሰቀጥጥ ወሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ባልደረሰ የምንልበት ደረጃ ላይ አድርሶናል፡፡
በተጨማሪም የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮችን ዜና ዕረፍት ስናነብ የብዙሃኑበዘመኑም ሕዝቡን በመልካም አጠባበቅ ጠብቆ በሠላም አረፈይላል፡፡ የእኛስ አባቶች ምን ያህል በበጎ አጠባበቅ ጠብቀውን ይሆን? እርግጥ ነው ለእረኞቻችን የምናስቸግር በጎች እንኖራለን፡፡ ነገር ግን የእኛ እረኞች የሆኑት እነዚህ አባቶችስ ምን ያህል ያስቸገርነውን እኛን ለማቃናት ሞክረዋል? ለስንቶቻችንስ አመጸኛነት ድጋፍ ሰጪ ሆነዋል? ስንቶቻችንን ከተሳሳትንበት መንገድ መልሰውናል? ለስንቶቻችንስ ከመንገድ ፈቀቅ ማለት በአንድም በሌላም ዓይነተኛ ምክንያት ሆነዋል? ስንቶቻቸውስ ከእውነት ጎን ተሰልፈው መንጋውን በመልካም አጠባበቅ በመጠበቅ ክፉ ዘመንን ለማሳለፍ ተግተዋል? ስንቶቻቸውን የበጎቹን ዘመን እጅግ እንዲከፋባቸው አድርገዋል? ስንቶቻቸውስ የተረከቡትን የእረኝነት አደራ እና የገቡትን ቃል አክብረዋል? ስንቶቻቸውስ ለእውነተኛቹ አባቶች እንደሚገባ በጸሎት በመትጋት መንጋቸውን ከሚያገሳው አንበሳ ከዲያብሎስ ጠብቀዋል? ስንቶቻቸውስ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ለሆነች ለቤተ ክርስቲያንን ልዕልና በጽናት ቆመዋል? ስንቶቻቸውስ ይህንን መንፈሳዊና ሰማያዊ እንዲሁም ክርስቶሳዊ ኃላፊነት ወደኃላ ችላ ብለውታል
እንደ አገባቡ ከሆነ አባቶቻችን ሊቃነ ጳጳሳት ምዕመናንን ከመባረክ፣ የሚነበቡ ሕያዋን መጻሕፍ ናቸውና በኑሮአቸው ከማስተማርም አልፈው ተቀድተው ከማያልቀው ዕውቀታቸው ደካሞችን የምያበረቱበትን ድርሳናት ቢደርልን ምኞታችን ነው፡፡ በተለይ ከቁጥራቸው ማነስና ከምዕመናን ብዛት አንጻር በአካል አግኝተው ትምህርታቸውን ለመከታተል ለማይችሉት እንዲሁም አረፍተ ዘመን ከገታቸው በኋላ ለሚመጣው ትውልድ ሕያው ትምህርት አበርክተው ቢያልፉ ምንኛ ደስ ባለን ነበር፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ስድስት ያህል ፓትርያርኮችን የሾመት ቢሆንም ከሌሎች አቢያተ ክርስቲያናት አባቶች አንጻር እነዚህ አባቶች ያበረከቱት ድርሳናት እና መጻሕፍት እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ለአብነት ያህል በአርባ ዓመት ዘመነ ፕትርክናቸው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ ሳልሳዊ ካበረከቱት ለቁጥር ከሚታክቱ መጻሕፍት አንጻር ሃያ አመታትን በመንበሩ በተቀመጡት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የተደረሰ ያነበብኩትን አንድም መጽሐፍ አላስታውስም፡፡ በእርግጥ የቀድሞዎቹን ባላውቅም አሁን ያሉት ሌሎች ኤጲስቆጶሳነትን ጨምሮ ብዙዎቹ የእኛ አባቶች የአስተዳደር ሥራ ላይ ብዙ ትኩረት የሚደርጉ ሆነዋል፡፡ እንዲያውም ፓትርያርኮቹማ ደብዳቤ መጻፍና መግለጫ መስጠትን ዋና ሥራቸው ያደረጉ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን ጌታ በመጨረሻ ሲመጣ እኛን ምዕመናንን ስንት መግለጫቸውን እንደሰማን፣ ስንት ደብዳቤአቸውን እንዳነበብን ወዘተ እንደማይጠይቀንና ዋጋ እንደማይሰጠን ሁሉ እኒህ አባቶቻችንም በዚህ ድርጊታቸው አይመዘኑም፡፡ ይልቁንም መንጋውን ምን ያህል ከመናፍቃንና ከቀሳጥያን እንዲሁም ከዘመኑ አላውያን ጠብቃችኋል? ምን ያህልስ የሕይወት ምግብ መግባትኋቸዋል? ተብለው መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ ለሁሉም ቸሩ እግዚአብሔር ይህን መልካም ምኞታችንን እንዲሰጠን አጥብቀን ልንለምነው ይገባል፡፡
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ይሄ ልጅ ለምን እዚህ እንደመጣ ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ ከሃያ ዓመት በኋላ ነው እንዲህ ቤት ውሎ ቤት ሲያድር ያዩት፡፡ ሥራ አለው፣ በትምህርት ተወጥሯል፤ ንግዱን እያጧጧፈ ነው ሲባል ነበር የሚሰሙት፡፡ በቤቱ ውስጥ የተሻለ የተማረ ሰው እርሱ በመሆኑ ሠርግና ልቅሶ ለምን አልመጣህም ብሎ የሚወቅሰው ቤተ ዘመድ አልነበረም፡፡ አንዳንዶቹም ስሙን ሰምተው እንዲሁ ያደንቁታል እንጂ አይተውት አያውቁም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድሮ በልጅነቱ እንዳዩት ናቸው፡፡

አሁን ግን ነገር ዓለሙን ሁሉ ትቶ እዚህ አያቱ ቤት መዋል ማደር ከጀመረ ሰነባበተ፡፡ አያቱ ደግሞ ይሳቀቃል ብለው ለምን መጣህ? ሥራና ትምህርትህንስ የት ተውከው? ብለው መጠየቅ ከብዷቸዋል፡፡ እጅግ በጣም የገረማቸው ደግሞ መቀመጫው ላይ ወስፌ እንደተተከለበት ሁሉ ለአፍታ ቁጭ ማለት የማይችለው ሰውዬ ደርሶ ቀኑን ሙሉ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሲቆዝም መዋሉ ነው፡፡

አንድ ቀን ግን ደፍረው መጠየቅ እንዳለባቸው ወሰኑና ወደ እልፍኛቸው አስጠሩት፡፡ ‹‹ልጄ በደኅህ ነው? እንደዚያ ለምግብ እንኳን ጊዜ የለኝም የምትለው ሰውዬ ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለህ የምትውለው›› አሉና ጠየቁት፡፡ አንገቱን ደፍቶ መሬቱን በመነጽሩ ጫፍ እየጫረ ዝም አላቸው፡፡ ‹‹የሆንከው ነገር አለ? ምናልባትኮ ለእኔ ቀላል ይሆናል፡፡ መቼም የዛሬ ልጆች ትንሹን ነገር ሁሉ አክብዳችሁ ነው የምታዩት፡፡ ሰውዬው እህል ሊሸከም ተጠርቶ ዋጋ ሲነጋገር ‹ለመሆኑ ሸክሙ ከባድ ነው ቀላል?› ብሎ ቢጠይቅ አሸካሚው ሰው ‹እንደ ተሸካሚው ነው› ብሎ መለሰለት አሉ፡፡ነገር እንዳያያዝህ ነው››

‹‹አያቴ ለአንተ ምንም አያደርግልህም፤ ምናልባትም ደግሞ አያስደስትህም›› አላቸው ጭኑን በመዳፉ እየመታ፡፡

‹‹ሲያደርጉት ነበር እንጂ ይህንን ማሰብ፤ ከሆነ ወዲያ መናገር ምን ያከብዳል››

‹‹ከወንድሜ ጋር ተጣላን› አላቸው ቀለል አድርጎ››

‹‹እና ወንድምና ወንድም መጣላቱ አዲስ ነገር ነው እንዴ››

‹‹ጠቡ ከበድ ያለ ነው››

‹‹ማቃለሉን ትታችሁ ማካበዱን እንዴት ቻላችሁበት››

‹‹መጀመሪያም የከበደ ነበር››

‹‹እንዴት እንዴት ሆኖ››

‹‹አንተኮ ሁሉን ታውቀዋለህ አያቴ፤ ዝም ብለህ ነው የምታስለፈልፈኝ››

‹‹ዕውቀት ብዙ ዓይነት ነው ልጄ፡፡ አሟልተህ የማታውቀው አለ፤ አዛብተህ የምታውቀው አለ፤ ጨርሰህ የማታውቀው አለ፤ የምታውቀውም ነገር አለ፡፡ ለመሆኑ ምንድን ነው ያጣላችሁ?››

‹‹እስከ ዛሬ ማንነቱን አላውቀውም ነበር፤ በእኔ ላይ ሲጫወት የኖረ መሆኑን አላውቅም ነበር፤ ሲጨቁነኝና ሲበድለኝ የኖረ፣ እንዲህ ሆኜ እንድቀር ያደረገኝ መሆኑን ዛሬ ዐወቅኩት›› አላቸው እያንገፈገፈው፡፡

‹‹ሌላስ ያወቅከው ነገር የለህም›› አሉት ጋቢያቸውን ከራሳቸው ወደ ትከሻቸው ወረድ እያደረጉ፡፡

‹‹ታላቅ ነኝ ብሎ ስንት ስቃይ ሲያደርስብኝ ነው የኖረው፡፡ ይደበድበኝ ነበር፤ ይቀማኝ ነበር፣ ይንቀኝ ነበር፣ ጉልበቴን ይበዘብዝ ነበር፤ ምርጥ ምርጡን ለራሱ ብቻ ይወስድ ነበር፤ ስሜን እንኳን በትክክል አይጠራኝም ነበር፤ ለራሱ በሚስማማው የማሾፊያ ስም ነበር የሚጠራኝ ፡፡››

‹‹ይህ ሁሉ ሲሆን ለመሆኑ አንተ ነበርክ››

‹‹የተወሰነው ደርሼበታለሁ፣ ሌላውን አንብቤያለሁ፣ ሌላውን ደግሞ ከሰው ሰምቻለሁ››

‹‹መልካም ይህንን ብቻ ነው የነገሩህ ሌላ ነገር አልነገሩህም፤ ላንተ ያደረገልህን ነገርስ አልነገሩህም፤ አንተ በእርሱ ላይ ያደረግክበትን ነገርስ አልነገሩህም?››

ዝም አለ፡፡

‹‹አየህ የምንሰማውና የምንናገረው የምንፈልገውን ብቻ ከሆነ ችግር ነው፡፡ ወይ ጨርሰን አለመስማት አለማየት ነው፡፡ እንሰማለን እናያለን ካልን ደግሞ ሁሉንም ማየትና መስማት ነው፡፡ የዛሬ ልጆች ችግራችሁ መርጣችሁ ነው የምታዩትና የምትሰሙት፡፡ በከፊል ሰምታችሁ በሙሉ ትፈርዳላችሁ፣ በጥቂት ዐውቃችሁ በብዛት ትደመድማላችሁ፤ መርጣችሁ ሰምታችሁ ሳትመርጡ ታወግዛላችሁ፡፡ ስማ ልንገርህ፤ አንተምኮ ብዙ ነገር አድርገህዋል፡፡ በድንጋይ መተህዋል፤ ደብተሩንና መጽሐፉን ቀዳደህበታል፤ የሚያጠናበትን ክፍል በድንጋይ እየደበደብክ ከሠፈሩ እንዲለቅ አድርገህዋል፡፡ ስንት የለፋበትንና የደከመበትን የሥዕልና የቅርጻ ቅርጽ ሥራውን ድምጥማጡን አጥፍተህበታል፡፡ ይህንንስ አልነገሩህም፡፡ አንተ ምንም ሳታጠፋ ከመላእክት ጋር ነው የኖርከው አሉህ? አንተ ተመታህ እንጂ አልተማታህም፤ ተሰደብክ እንጂ አልተሳደብክም አሉህ?እርሱስ ላንተ ያደረገልህ ነገር የለም? አላስተማረህም? የእናት የአባታችሁን ርስት ለመጠበቅ ደም አልከፈለም? አንተን የሠፈር ጎረምሶች በተተናኮሉህ ቁጥር የግንባር ሥጋ ሆኖ አልመከተልህም? በክፉው ቀን አዝሎህ ለስንት ቀን የተጓዘበትን፣ በረሃብ ቀን አንተን አስቀድሞ ያበላበትን፣ ይህንን አልነገሩህም፣ አልጻፉልህም?››

ዓይኑን ከግራ ቀኝ እያንከባለለ ያያቸው ጀመር፡፡

‹‹ሴትዮዋ ጆሮዬ ታሟል አልሰማም ብለው ከዘመድ ተጠግተው ይኖሩ ነበር አሉ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ዘመዶቻቸው ቡና እየጠጡ ያሟቸዋል፡፡ አልሰማም ብለዋልና ምንም ነገሩ ቢያበግናቸው ዝም አሉ፡፡ ሐሜቱ እየቀጠለ ሲሄድ ግን አልቻሉምና ‹‹ምነው እናንተ፣ ሳልሞት በቁሜ ታወራርዱኛላችሁ›› ብለው ተናገሯቸው፡፡ ሰዎቹም ደንግጠው ‹እማማ አልሰማም አላሉም እንዴ?› አሉና ጠየቋቸው፡፡ ሴትዮዋም ‹ክፉ ክፉውንማ እሰማለሁ› አሉ ይባላል፡፡ እናንተም ክፉ ክፉውን ብቻ ነው እንዴ የምትሰሙት፡፡ ዝንጀሮ የራሷ ጠባሳ አይታያትም እንደሚባለው እናንተስ የሠራችሁት ስሕተት የለም?

‹‹ልጄ የተነገረህን ተወው አልልህም፤ እንዴ ሰምተህዋልና፡፡ ነገር ግን ያልተነገረህን ፈልግ፡፡ ያልተነገረህ ብዙ ነገር አለ፡፡ ስለወንድምህ ያልሰማህው ብዙ ነገር አለ፡፡ ደግነቱንና መልካምነቱን የነገረህ የለም፤ ጥፋቱንና ድክመቱን ግንቅመም እየጨመሩ በደንብ አስጨብጠውሃል፡፡ ጎዱህ እንጂ አልጠቀሙህም፡፡ እኛ ድሮ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሂሳብ ስንሠራ ‹ተንጠልጣይ ሂሳብ› የሚባል ነገር ነበር፡፡ ሳይወራረድ፣ ሳይዘጋ እንዲሁ ከዓመት ዓመት ሲንከባለል የሚኖር ሂሳብ ነው፡፡ የእርሱ መዝጊያ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ውሳኔ ነው፡፡ በውሳኔ ይዘጋል፡፡ ያለበለዚያማ የርሱ አለመወራረድ አንሶ የቀጣዩን ዓመት ሂሳብም ይበጠብጠዋል፡፡ ያልተዘጋ ቁርሾም እንዲህ ነው፡፡ አልዘጋ ካለ ወስኖ መዝጋት ነው፡፡ ከዚያ ወደፊት መሄድ ነው፡፡ ወደማትቆጣጠረው ትናንት ሄዶ መከራ ከማየት ወደምትቆጣጠረው ነገ መሄድ ይሻልሃል፡፡

‹‹እኔ ልምከርህ፤ የሰማኸውን ብቻ ሰምተህ አትፍረድ፤ ያልሰማኸውን ደግሞ ፈልግ፡፡ አንዳንዴም ከሰማኽው ያልሰማኸው ይበልጣል፡፡ የለም ብለህ አትደምድም፤ ቢኖር ትደነግጣለህ፤ አለ ብለህ ባይኖር ግን ምንም አትሆንም፡፡

‹‹ልገድለው እያሰብኩ ነበር፡፡ መንገድ እየፈለግኩ ነበር፤ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነበር፡፡ አተረፍከኝ፡፡ እስኪ እውነትም ያልሰማሁት ነገር ካለ ልፈልገው፡፡ አሁን እንኳን አንተ ብዙ ያልሰማሁትን ነገር ነገርከኝ፡፡ ለካስ ያወቅኩ መስሎኝ ባላወቅኩት ነው ልፈርድ የነበረው››

ያን ምሽት እዚያ ቤት አላደረም፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡

ትዝ ይለኛል በ1997 ዓ.ም ይወጡ ከነበሩ ፕሬሶች ‹‹ነፃነት›› ጋዜጣ ትመስለኛለች በፊት ለፊት ገጽዋ ‹‹ንቢቱ መናደፍ ጀመረች!!›› የሚል ርዕስ ይዛ ነበር፡፡ የመለስን ‹‹እንከን የለሽ ምርጫ እናካሂዳለን›› የአደባባይ ቃል በጥይት ለመቀልበስ ሲሞከር የተሰጠ ርእስ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥም ዴሞክራሲን በወረቀት እንጂ በተግባር ለማረጋገጥ አልቻሉም፡፡ በአንድ እጃቸው ምዕራባዊያን እንዳይከፋቸው ዴሞክራሲን በሌላ እጃቸው ደግሞ የዴሞክራሲ መቀልበሻ ክላሽ ይዘው 23 […]

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግንኙነት) “….ያኔ እንተያያለን…” በትላንትናው ዕለት የአዳማ አንድነት ሰልፍ ፈቃዳችንን ከ20ቀናት ደጅ ጥናት በኋላ ወስደናል፡፡ግን ከአስገራሚ ገጠመኞቹ ጥቂቱንም ቢሆን ማካፈል ግድ ይለናልና እነሆ፡፡ፈቃዱን ከመስጠታቸው በፊት ከከተማው ጸጥታ ክፍል ሶስት ሰዎች መጥተው ከንቲባው ጽ/ቤት ተጠርተው ገቡ፡፡እኛ በዚህ ዕለት ካልተሰጠን ላንወጣ ተነጋግረን ገብተናልና “ቶሎ ድረሱልኝ” ያላቸው ሰዎች መምጣት ደስ ብሎናል እንጂ አልፈራንም፡፡ሆኖም ነገርየው […]

አንድነት በአዳማ ስለመሬት ስሪትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ጠራው ሰልፍ ከ20 ቀናት በኋላ ዕውቅና አገኘ፡፡ ግንቦት 5 ነበር ደብዳቤያችንን ለከንቲባው ጽ/ቤት ያስገባነው፡፡ ጥያቄያችንም ግንቦት 10 ሰልፍ ለማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም በከንቲባው ጽ/ቤት ቢሮክራሲ ለሰኔ 10 ሊፈቀድ ቀርቶ ሊያነጋግሩን እንኳን ባለመቻላቸው ወደ ከንቲባው የተላከው ደብዳቤያችን በከንቲባው አማካኝነት ከግንቦት 20 በኋላ ሊስተናገድ ከባንኮኒ ገብቶ ተቆለፈበት፡፡ ክትትላቸውን ያላቋረጡት የአዳማ አንድነት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። ይሄን ጊዜ ከኮሌጅ ተመርቃ፣ ሥራ ይዛ ምናልባትም ተድራ፣ የልጆች እናት ትሆን ነበር። አሁን ግን የለችም። ኮተቤ አካባቢ ነበር፤ ከአጋዚ ጦር አንዱ በተተኮስ ጥይት ተመታ ወደቀች። ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓ.ም። የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነው። በእጆቹ ድንጋይ አልያዘም። ተማሪ ነበር። ወደቤቱ ሲመለስ፣ በአካባቢዉ ግርግር ተፈጠሮ ስለነበረ፣ ሰላምና መረጋጋት እናመጣለን ባሉ […]

በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ወጣት መልካሙ በጎንደር የሚደረገውን የድንበር ማካለል የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን የሚያውቀውን […]

በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል:: በየጊዜው ለስራ ፍለካ ምክንያትና በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራቸውን እየለቀቁ ወደ ሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያኖችን ብዙ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያኖች ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል :: በተለይም በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸውና በሀገሪቱ ፖሊስ እና በሱዳን ማህበረሰብ ዘግናኝ […]

ከአምስት ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያዊያንን በተለያዩ ፕሮጀክቶች የደረሱት፣ ከ360 በላይ ትምህርት ቤቶችን፣ ሦስት ሆስፒታሎችን ወደ መቶ የሚጠጉ ክሊኪኮችን፣ የጤና ጣቢያዎችንና የጤና ኬላዎችን የገነቡት ካርልሄንዝ ብዮም አርፈዋል፡፡

ፀሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

——

ይህ የጎንደር ቅኝታችን ሁለተኛ ክፍል ነው፡፡ እነሆ ሽርሽራችንን በጥንታዊቷ መዲና ቀጥለናል፡፡

—–

በጎንደር የነገሡት ነገሥታት በታሪካዊ ሚናቸው በእኩል ሚዛን ላይ አይቀመጡም፡፡ አንዳንዶቹ በሰሩት ስራ ስማቸው ዘመንን ተሻግሮ ይዘከራል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ስልጣን አልባ ሆነው በስም ብቻ “ንጉሥ” እየተባሉ ይጠሩ ነበር፡፡ የሁላቸውንም ታሪክ መዘርዘር የኛ ዓላማ ባለመሆኑ እርሱን ለታሪክ መጻሕፍት እንተወው፡፡ ለበረካ ያህል ግን ሁለት ነገሥታትን በትንሹ እናውሳቸው፡፡

===ተረት መሳዩ ንጉሥ===

ከስሙ ጀምሮ ሁለመናው ይገርማል፡፡ ታሪኩ እንደ ተረት ያስደምማል፡፡ አንዳንዴ የሚሰራቸው ነገሮች ደግሞ ከባግዳዱ ኸሊፋ ሀሩን አል-ረሺድ ጋር ያመሳስሉታል፡፡

ይህ ንጉሥ “ባካፋ” ይባላል፡፡ አጼ ባካፋ የነገሠው በአድማ ነው፡፡ አጼ ዳዊት ሳልሳዊ በሚባለው በወንድሙ ላይ አምጾ ነው ስልጣን የተቆጣጠረው፡፡ ታዲያ ለአመጽ ሲነሳ መጀመሪያ ላይ በለስ አልቀናውም፡፡ በውጊያ ስለተሸነፈ ራሱን ሸሽጎ ከአንድ ደብር ለመኖር ተገደደ፡፡ በዚያ ደብር እያለም በአንድ መምህር ስር ቅኔና ዜማ መማር ጀመረ፡፡ እያደር ከዚሁ መምህር ጋር ሚስጢረኛ ሆነ፡፡ ታሪኩንም አንድ በአንድ አጫወተው፡፡

  በአንድ ውድቅት ሌሊት እርሱና መምህሩ ለመጸዳዳት ይወጣሉ፡፡ እዚያ እያሉም ባካፋ ለመምህሩ “መሪጌታ! የኔን ነገር እንዴት ነው የሚያዩት?.. ይህንን ወንድሜን አሸንፌ መንገሥ የምችል ይመስልዎታል?” የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ መምህሩም “የምትነግሥ ይመስለኛል፤ ነገር ግን ጸሎት ማብዛት አለብህ፣ በጸሎት ሀይል የማይቻል የለም፤ ታዲያ ቀኙ ያንተ ሆኖ አልጋውን በወሰድክ ጊዜ እኔን እንዳትረሳኝ” አለው፡፡ ባካፋም በፍጹም ላይረሳው ቃል ገባለት፡፡

ዓመታት አለፉ፡፡ ባካፋም ወንድሙን ድል አድርጎ ነገሠ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ድሪቶ የለበሰ ባላገር መጥቶ ከቤተ መንግሥቱ ፊት ቆመ፡፡ ዘበኞቹንም እንዲህ የሚል መልዕክት ለባካፋ እንዲያደርሱለት ለመናቸው፡፡

“ታስታውሳለህ ባካፋ የተባባልነውን

እኔ የአብረሃምን አባት ሆኜ አንተ ሚስቱን”

 ዘበኞቹ የባላገሩን ንግግር እንደ እብድ ወሬ ቆጠሩትና ለባካፋ ላለመንገር ለገሙ፡፡ አንዱ ነቄ ዘበኛ ግን ሰውዬው ቅኔ የተናገረ ስለመሰለው “ንጉሡ መልዕክቱን መስማት አለባቸው” በማለት ወደ አጼ ባካፋ ሄዶ ተናገረ፡፡ ባካፋም “እንዴ?! የቅኔ መምህሬ ናቸው፤ በቶሎ አስገቡልኝ” በማለት ዘበኞቹን አዘዛቸው፡፡ በዚህ መንገድ ባካፋ ከጥንቱ መሪ ጌታ ጋር ተገናኘ፡፡ ያኔ የገባውንም ቃል ተግባራዊ አደረገ፡፡

 በነገራችን የቅኔውን ሚስጢር አግኝታችሁታል አይደለምን?… የአብረሃም አባት “ታራ” ነው፡፡ የአብረሃም ሚስት ደግሞ “ሳራ” ናት፡፡ ስለዚህ መምህሩ ለማስተላለፍ የፈለገው “እኔ ሳራ አንተ ታራ” የሚል መልዕክት ነው፡፡ ይህም ሁለቱ ሰዎች ሲጸዳዱ የተነጋገሩትን የሚያስታውስ ነው፡፡

—-

በሌላ ጊዜ ደግሞ ባካፋ እንደ ሀሩን አል-ረሺድ ራሱን ለዋውጦ ሀገሩን ይጎበኝ ነበር፡፡ ከአንድ ምንጭ አጠገብ ሲደርስ አንድ እረኛ ገጠመውና “የዚህ ሀገር ንጉሥ እንዴት ነው?” አለው፡፡ እረኛውም “ጥሩ ነው፤ ተስማምቶናል፤ ሀገሩ ጥጋብ ነው፤ ደሀን አይበድልም” የሚል መልስ ሰጠው፡፡ ይሁንና ባካፋ ሆን ብሎ እረኛውን መተንኮስ ጀመረ፡፡ “ምን ጥጋብ ነው ትላለህ? እንዲህ ዓይነት ግፈኛ ንጉሥ ነግሦም አያውቅ፤ ደሀውንም እንደርሱ የሚበድል የለም” አለው፡፡ እረኛው “ሰውዬ! እኔ አልዋሸሁም፤ ይህንን ነገረኛነትን ተወኝ፤ ምላስህን ያዝልኝ” አለው፡፡ ባካፋ ግን ትንኮሳውን ቀጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ እረኛው ሽመሉን መዝዞ “እምቢ ካልከኝ በዚህ ዝም ትላለህ” በማለት ባካፋን እስኪበቃው ድረስ ደበደበው፡፡

 ከሳምንት በኋላ እረኛው ወደ ቤተመንግሥት ተጠራ፡፡ “ለምን” ብሎ ቢጠይቅ መልስ አልተሰጠውም፡፡ በመሆኑም ፍርሃት ወረረው፡፡ “ምን አጥፍቼ ይሆን?” እያለ ተጨነቀ፡፡ እንዲሁ በጭንቀት እንደተወጠረ ቤተመንግሥት ሲደርስ ከሳምንት በፊት የደበደበው ሰውዬ በዙፋን ላይ ቁጭ ብሎ አገኘው፡፡ እረኛው የባሰውኑ ተርበተበተ፡፡ ይሁንና ንጉሡ የፈገግታ ምልክት ሲሰጠው ልቡ መለስ አለችለት፡፡ ንጉሡም እንዲህ አለው፡፡

“ከሳምንት በፊት ለፈጸምከው ሐቀኝነት አንድ መቶ ከብቶችን ተሸልመሃል”

===የቤተመንግሥቱ ጭውውትና ታሪክ ቀያሪው ፋኖ==

በጎንደር ቤተ-መንግሥት የተደረገ አንድ ጭውውት እንጥቀስላችሁ፡፡

1ኛ ተናጋሪ (እቴጌ መነን)

አረ ለመሆኑ ምን ይሆን አሳቡ

ሸፍቶ የሄደው ከነቤተሰቡ?

2ኛ  ተናጋሪ (ራስ ዓሊ)

ሰውዬው ኩሩ ነው የተነፋ ልቡ

ይዞ ማዋረድ ነው ይበርዳል ጥጋቡ::

3ኛ ተናጋሪ (አንድ መነኩሴ)

ሰውዬው ብርቱ ነው ስሙ የተጠራ

ጎበዝ እኔ ነኝ ባይ ሀይልን የማይፈራ

በዘዴ በትዕግስት ማባበል ይሻላል
በሀይል ብንለው በጣም ያውከናል፡፡

4ኛ (እቴጌ መነን)

እንዲህ ስትሉ ነው ስሙ የገነነው

የፈራነው መስሎት አገር የሚያብጠው

ዘዴ መላ አታብዙ ጦር ይታዘዝና

ቢቻል ከነነፍሱ ይምጣ ይያዝና

እምቢ ካለም ይሙት በገዛ ጥፋቱ

ላንድ ወንበዴ ሽፍታ አይስጋ መንግሥቱ፡፡

——

ይህ ጭውውት በ1840ዎቹ በጎንደር ቤተመንግሥት እልፍኝ ከተደረገ ምክክር የተቀነጨበ ነው፡፡ ይህም “ቴዎድሮስ” በተሰኘው የደጃች ግርማቸው ተክለሃዋሪያት መጽሐፍ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ በጭውውቱ ውስጥ “ለምን ሸፈተ” ተብሎ እንደ አጀንዳ የቀረበው የያኔው ደጃች ካሳ ሀይሉ ነው፡፡ በዚያን ወቅት ካሳ ሀይሉ ከተራ ቤተሰብ ተወልዶ በአስገራሚ ሁኔታ የቤተ መንግሥቱ አባል ሆኖ ነበር፡፡ ታሪክ አለው፡፡

ደጃች ካሳ በወጣትነቱ ሽፍታ ሆኖ በቋራና በደምቢያ ይዘዋወር ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ሱዳንን ከሚቆጣጠሩት የቱርክ/ግብጽ ገዥዎች ጋር የድንበር ላይ ውጊያ ያካሄዱ ነበር፡፡ ታዲያ በአንዱ ውጊያ ላይ የዘመኑ ዋና መስፍን የነበሩት የራስ ዓሊ ልጅ የሆነችው ወይዘሪት ተዋበች ተማረከች፡፡ ይህም ወሬ ለካሳ ጆሮ ደረሰ፡፡ ካሳ በወቅቱ ሽፍታ ቢሆንም የኢትዮጵያዊያን መሸነፍና በምርኮ መጋዝ በጣም አበሳጨው፡፡ በመሆኑም በቱርኮች ላይ ድንገተኛ አደጋ ጥሎ አተረማመሳቸው፡፡

  ካሳ ይህንን ሲያደርግ ተዋበች ምርኮኛ መሆኗ በቁጭት ውስጥ ጥሎአት በመርዝ ጩቤ ሰውነቷን ወግታ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ በማድረግ ላይ ነበረች፡፡ ይሁንና ካሳ በቦታው ደርሶ መርዙ ወደ ሰውነቷ ጠልቆ ሳይገባ ከደሟ ውስጥ መጥጦ ተፋው፡፡ በዚህም የተዋበች ህይወት ተረፈች፡፡ ካሳም ተዋበችን በጀርባው አዝሎ ከውጊያው እየሮጠ ወጣ፡፡ ወታደሮቹም በቶሎ እንዲያፈገፍጉ ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡

ካሳ ነፍሲያዋን ያተረፈላትን ተዋበችን ለአባቷ ለራስ ዓሊ አስረከባት፡፡ ራስ ዓሊም በጀግንነቱ ተደስተው እሷኑ ዳሩለት፡፡ ሽፍትነቱን ትቶ በቤተመንግሥት እንዲኖርም አደረጉት፡፡ ይሁንና የቤተመንግሥቱ ህይወት በነጻነት መኖርን ለለመደው ካሳ የግዞት ያህል ሆነበት፡፡ በዚያ ላይ መኳንንቱ “የኮሶ ሻጭ ልጅ” እያሉ የሚያሳዩት ንቀት በጣም አቃጠለው፡፡ ተዋበችም በባሏ ላይ በሚደርሰው ንቀትና ማሽሟጠጥ በገነች፡፡ እናም በአንድ ውድቅት ላይ “አንተ ካሳ! ጎራዴህን ታጠቅና ተነሳ፤ ምንጊዜም ከጎንህ ነኝ” አለችው፡፡ ካሳም ሸፈተ፡፡

—-

እንግዲህ ከላይ የቀረበው ጭውውት ካሳ በሸፈተ በማግስቱ የተደረገ ነው፡፡ በዚያ ቀን በተደረገው ምክክር ደጃች ወንድይራድ የካሳን እጅ ይዞ እንዲመጣ ታዘዘ፡፡ ወንድይራድም ከቤተመንግሥቱ ቀርቦ እየጎረነነ ትዕዛዝ መቀበሉን አረጋገጠላቸው፡፡ ይሁንና የወንድይራድ ከልክ ያለፈ ጉራ ያልጣማቸው ራስ ዓሊ “አንተ ወንድይራድ! ካሳ እንደ ሌላው ሽፍታ አይምሰልህ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው አደገኛ ተዋጊ ነው” በማለት ምክር ቢጤ ቢወርውሩለት ዳጃች ወንድይራድ እንዲህ የሚል የንቀት መልስ ሰጣቸው፡፡

አይስሙ ጌታዬ ሰው የሚለውን

አያስፈራም ካሳ ይንዛ ጉራውን፡፡

ገና መጣ ሲሉት አገር ጥሎ ይሸሻል

ወይንም ካንዱ ደብር ገብቶ ይደውላል፡፡

እንኳን አንድ ሽፍታ ቀማኛ ወንበዴ

ብዙ እመልሳለሁ በጦር በጎራዴ፡፡

እኔ ነኝ ወንድይራድ ታማኝ አሽከርሽ

ያን የኮሶ ሻጭ ልጅ የምቀጣልሽ፡፡

የወንድይራድ ፉከራና ድንፋታ ከካሳ ጆሮ ገባ፡፡ ካሳም “እናቴን እንዲህ የሰደበውን ባለጌ ባላሳየው እኔ ካሳ አይደለሁም” በማለት መሃላውን ሰጠ፡፡ ሁለቱ ሀይሎች ተገናኙ፡፡ ውጊያው ገና ከመጀመሩ የወንድይራድ ፉከራ የአሸዋ ላይ ቤት ሆኖ ፈረሰ፡፡ እቴጌ መነን (የራስ ዓሊ እናት) የተመኩበት ዳጃች ወንድይራድም ተማረከ፡፡ ካሳም መሃላውን ተግባራዊ አደረገ፡፡ ወንድይራድን ቀንና ማታ ኮሶ እያጠጣ ገደለው፡፡

ከዚያ በኋላ ካሳ በሀገሩ ላይ ገነነ፡፡ ማን ይቻለው? ደጃች ውቤም ሆኑ ራስ ዓሊ፣ ደጃች ተድላ ጓሉም ሆኑ ደጃች ጎሹ ሁሉም ተራ በተራ ተሸነፉ፡፡ ካሳን ያሸንፋሉ ተብለው የተጠበቁት እቴጌ መነንም በናቁት አማቻቸው እጅ ምርኮኛ ሆነው ወደቁ፡፡ የጥንቱ የቋራ ሽፍታም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ ነገሠ፡፡ ንጉሥ ለስሙ ብቻ ቤተመንግሥት የሚቀመጥበት ዘመነ መሳፍንትም አበቃ፡፡ ኢትዮጵያም አዲስ ታሪካዊ ጉዞዋን ተያያዘችው፡፡

—-

ከዚያ ወዲህ ያለው የካሳ ታሪክ ሌላ ባህር ነው፡፡ አሁን በያዝነው አካሄድ እዚያ ውስጥ መግባት አንችልም፡፡ ስለዚህ የካሳን ጨዋታ በዚሁ እናብቃ፡፡ የጎንደሪቱ ወጋችን ግን በክፍል ሶስት ይቀጥላል፡፡ አለቃ ገብረሃና፣ አራት ዐይና ጎሹ፤ አያሌው ሞኙ፣ መላኩ ተፈራ፣ ኮማንደር “አያልነሽ”፣ “አያ ሻረው”፤ ይርጋ ዱባለ፣ ጃንተከል ዋርካ፣ የጀበርቲ ወግ እና ሌሎችም ጨዋታዎች ይቀሩናል፡፡ የከርሞ ሰው ይበለንና በሌላ ጊዜ ተመልሰን እንገናኛለን! ኢንሻ አላህ!!

አፈንዲ ሙተቂ

ግንቦት 22/2006

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ግርማ-ሞገሳሙ ሽማግሌ ከልብ የመነጨ ፈገግታ ለገሰኝ።ክንዱን እያያሻሸሁ ሳዋራዉ— አንዳድ ባልደረቦቹን ጠየቀኝ።ከሚጠይቀኝ ሰዎች አንዳዶቹን ከጥቂት ጊዜ በፊት አግኝቷቸዉ ነበር–» እና አከሉ ፀሐፊዋ—«ካርል የማስታወስ ችሎታዉ እየከዳዉ መሆኑን የተገነዘበ መሰለኝ።»

ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በዮጋንዳ መዲና ካምፓላ በተካሄደው 9ኛ «የኤሌክትሮኒክስ ወይም የኢ-ለርኒንግ ትምህርት በአፍሪቃ» ጉባኤ ላይ ከ68 ሀገራት የተውጣጡ 1400 የሚጠጉ ሰዎች ተገኝተዋል።

በአማካይ በያመቱ ከአምሥት ከመቶ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት በላይ በማስመዝገብ ላይ የምትገኘዋ አፍሪቃ በዓለም የተከሰተው የፊናንስ ቀውስ ያስከተለውን መዘዝ ከሌሎች አውሮጳውያት ሀገራት በተሻለ ሁኔታ መቋቋም ችላለች። ለዚህም እርግጥ፣

እአአ ግንቦት 24፣ 2014 ዓም ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ብራስልስ፣ ቤልጅየም በሚገኝ አንድ የአይሁዳውያን ቤተ መዘክር ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ሦስት ሰዎች የገደለው ተጠርጣሪ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ስር መዋሉ

የገዳ ሥርዓት አራማጅ ድርጅት የተባለ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ትናንት በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባዔ አካሄደ። የአዲሱ ፓርቲ አባላት ከአመራሩ ጋ በበርካታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዩኤስ አሜሪካ የተካሄደው የዳይመንድስ ሊግ የአትሌቲክስ ጨዋታ፣ ከ50 የሚበልጡ ሀገራት የተሳተፉበት እና 21 የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የታየበት በቦትስዋና የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪቃ ወጣቶች ውድድር ፣

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት፤ በቅርቡ ያወጣው የመጠርዝር ጥናት ውጤት እንደሚያስረዳው፤ በህክምና ርዳታ የሰዎች ዕድሜ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመራዘም ላይ ነው። ባለፉት 2 ዐሠርተ ዓመታት በዓለም ዙሪያ በአማካይ የ 9 ዓመት ጭማሪ አሳይቷል።

የኢጣሊያ ባህር ኃይል ዳግም በሺ የሚቆጠሩ የጀልባ ላይ ስደተኞችን ማዳኑን አስታወቀ። እንደ ባህር ኃይሉ ከሆነ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከ3000 በላይ ስደተኞችን ከኢጣሊያ የባህር ጠረፍ ተቀብሏል። ከሰሜን አፍሪቃ በኩል እንደመጡ የተነገረዉ አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ ሲሲሊያ መወሰዳቸውም ተነግሯል።