አስናቀች ተዋናይ የባህል ሙዚቀኛ፣ ክራር ተጫዋች፣ ድምጻዊት፣ የባህል ተወዛዋዥ፣ ዘመናዊ ዳንሰኛ፣ ገጣሚ ሁለገብ የጥበብ እመቤት ነበረች፣ ላትመለስ መስከረም አራት ሁለት ሽ አራት አመተ ምህረት ከዚህ አለም በሞት ተለይታናለች። በጀርመናዊዉ ፒት ቡደ በአስናቀች የክራር ድርደራ ተመስጠዉ፣ ዜማዋን አፍቅረዉ የአስናቀችን ሙዚቃ በዘመናዊዉ …

አስናቀች ወርቁ የመድረኳ ዕንቁ Read more »

ዘመኑ ሞላ ተወልዶ ያደገው ከዚሁ አዲስ አበባ ሲሆን፣ ባለትዳርና ያንዲት ሴት ልጅ አባት ነው፡፡ ልጁ ጎበዝ ተማሪ ስለሆነች በዚህ ዓመት ዩኒቬርስቲ እንደምትገባ በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
ዘመኑ ሞላ ነባር የሰላማዊ ትግል ታጋይ ሲሆን የኢዴፓ ነባር አባል በመሆኑ በ92 ዓ.ም በተደረገው ሁለተኛው አገራዊ ምርጫ አ.አ ክልል ተወዳድሮ ነበር፡፡
ቆይቶ ደግሞ ኢዴፓ የሚሄድበት መንገድ ስላላማረውና ስላልጣመው ከዚያ […]

አካባቢው አንድ ገጠር መንደር ነው፡፡ የዘመኑ የአካባቢው ገዢ ሕዝቡን ሰብስቦ ሲናገር ይውላል፡፡ ሕዝቡም ዝም ብሎ ያዳምጣል፤ እርሱ ያወራል ሕዝቡን ያዳምጣል። መናገር ሲስለቸው «አሁን ተራው የእናንተ ነው፤ ሐሳብ መስጠት ትችላላችሁ» ይላቸዋል፡፡
ሁሉም ዝም ይላል፡፡ «ተናገሩ» ይላል አሁንም በመደጋገም ። አሁንም ሕዝቡ ዝም አለ፡፡ “ጊዜው የዴሞክራሲ ነው ፤ የፈለጋችሁትን መናገር ትችላላችሁ፡፡ ተርበን፣ ሞተን፣ ቆስለን፣ ጓደኞቻችን ሞተው […]

በቅርቡ “በሽብርተኝነት”ተጠርጥረው የታሠሩትን እስረኞች «በምን ሁኔታ ላይ አንደሚገኙ ማወቅ አልቻልንም» ሲሉ ቤተሰተቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡
የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት የአቶ አንዱዓለም አራጌ ወንድም ወጣት አብርሃም አራጌ እንደሚለው “ወንድሜ የታሠረበትን የእስር አያያዝ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ በተደጋጋሚ ለመጠየቅ ሄጄ ምግብ ተቀብለው ዕቃ ከመመለስ ውጪ በአካል አግኝቼው አላውቅም”፡ ብሏል፡፡
የፓርቲው ማዕከላዊ ም/ቤት አባላት የሆኑት […]

አሣምነው ብርሃኑ ተወልዶ ያደገው ከዚሁ አዲስ አበባ ነው፡፡ የትምህርት ደረጃው በፊዚክስ ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ አለው፡፡ ባሁኑ ጊዜ በኢኮኖሚክስ በዲግሪ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተማረ ነበር፡፡ መደበኛ ሥራውም መምህር ነው፡፡
ቤተሰብ አሣምነው ብርሃኑ ገና ወጣት በመሆኑ ለሥራና ለትምህርት እንዲሁም ለነፃነት ተግቶ ከመሥራት ውጭ ትዳር ለመመሥረት አስቦ እንደማያውቅ ቤተሰቦቹ ገልፀውልናል፡፡
የፖለቲካ አቋምአሳምነው ብርሃኑ አንድነት ፓርቲን ከመቀላቀሉ በፊት […]

ክቡር ጠ/ሚንስትር የሰው ልጅ የአገሩን የአስተዳደር መረጃ ካለማጤን ስህተት መፈጠሩ አይቀሬ ቢሆንም በተጓደኝ የተፈፀመውንና የተደረገውን በማስታወስ የተሠራ ጥፋት መታረም ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር ባገራችን የሚታየውንና እየተፈፀመ ያለውን ግዙፍ ስህተት ቅኝ ገዥዎች እንኳን ይሠሩታል ብሎ ለመናገር የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመዳፍ ያነሳሳኝ ሀገራዊ ስሜትና ፍቅር እየቆጠቆጠኝ አላስቆም አላስቀምጥ ስላለኝ ሰሚ ባይኖርም የድርሻዬን ልወጣ በሚል ነው፡፡
ኢሕአዴግ ሥልጣን ከተቆናጠጠበት […]

ከጥቂት ወራት ወዲህ ገዢው ፓርቲ ስርዓቱ ላይ የሠላ ሂስ በመሠንዘር የሚታወቁ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞችን የማሠር ዘመቻውን ጀምሯል፡፡ የእስራት ዘመቻው ማቆሚያ የት ጋ እንደሆነ የታወቀ ነገር እስካሁን የለም፡፡ የእስር ዘመቻው ያነጣጠረው ግን ከኢህአዴግ አቋም በተቃራኒው የቆሙ ግለሰቦች ላይ መሆኑ የአገራችንን የወደፊቱን የፖለቲካ አቅጣጫ አሳሳቢ አድርጎታል፡፡
ከታሪክ እንደምንማረው በዓለም ላይ በርካታ አምባገነን መንግስታት ኖረው አልፈዋል፡፡ አውሮፓን ሲያምሱት […]

ካፕቴን ተሾመ ተንኮሉ ባለፈው ሰሞን፡ የአንጋፋው የኢትዮጵያ ስፖርት ፎደሬሽን በሰሜን አሜሪካ፡ በአረብ/አበሻው ቱጃር ሰበብ ታምሷል መባሉን ሰምቼ፤ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ አነስ ያለች ፅሁፍ ለዘወትር ወዳጄ ብሰድለት፤ በሃሳቤ መለስለስ ነው መሰለኝ ብዙም ሳይደሰት፤ “ወያኔን እየደጋገሙ ነጋ ጠባ መውቀስ ብቻውን ጠላት ከማብዛት …

ሰራዊቱ ከምድር ጦር እስከ አየር ሀይል – ካፕቴን ተሾመ ተንኮሉ Read more »

ኢህአዴግ የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት ጥያቄ ሲቀርብለት ዘወትር የሚያሳው መቃብሩን ነው።የአንድነት ጥያቄ ሲቀርብ ምላሹ “እኛ ከፈለሰፍነው አንድነት ውጭ ሌላው አንድነት በኢህአዴግ መቃብር ላይ ካልሆነ በስተቀር የማይታሰብ ነው”የሚል ነው።የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ሲነሳ “የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ህያው የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብቻ ነው”በማለት ወደ መቃብሩ ያመላክተናል።አንቀፅ 39 በታኝ መሆኑን ህዝብ ሲገልፅ “የህዝብ ልጆች የተሰውለት የትግሉ የማዕዘን ድንጋይ ነው፣እኔ […]

ለገዛ ራስና ለሃገር ነፃነት አርበኛ መሆን በመለስ ዜናዊ እና እሱ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች “ሽብርተኛ” ያስብላል፤ ያስከስሳል፤ ያሳስራል። አርበኝነት ክብር ነው። አርበኝነት የመልካም ዜግነት ከፍተኛው መገለጫ ነው። አርበኝነት የታላቅ ስብዕና መገለጫ ነው። በመለስ ዜናዊ እና እሱ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች “ሽብርተኛ” መባል የአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም ኢትዮጵያዊ ድርጅት አርበኝነት ማሳያ ሆኗል። እናም በመለስ ዜናዊ “ሽብርተኛ” መባልና የሚያኮራና የሚያስደስት ነገር […]

የግንቦት7 ንቅናቄ ሊ/መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2004 አዲስ አመት አስመልክተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ! በቅድሚያ በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና በራሴ ስም “እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገረን” እላለሁ። ያሳለፍነው 2003 ዓመተ ምህረት በዓለም ላይ ብዙ አስደናቂና ተስፋ ሰጪ ኩነቶች የታዩበት ዓመት ነበር። እኛ በነፃነት ስንኖር በቅኝ ግዛት ባርነት […]

ጥምረት ለፍትህ ለነጻነትና ለእኩልነት ባለፈው ቅዳሜ ጳጉሜ 3 ቀን በአሜሪካን አገር በዳላስ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ ለተገኙት ኢትዮጵያዊያን ንግግር ያደረጉት የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ዋና ጸሃፊ ፤ ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በህዝባችን ላይ እያደረስ ያለውን ሰቆቃ ለማስቆምና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ኦነግ ከግንቦት7 እና ለዲሞክራሲ ከሚታገሉ ሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። […]