ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  መንግስት ትናንት ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው በሚል ርእስ በኢቲቪ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ላይ አንድነት ፓርቲ የሼህ ኑሩን ግድያ ደግፎ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲጠራ ማድረጉን የግንቦት7 ልሳን የሆነው ኢሳት ቴሌቪዥንም አሸባሪዎችን ” አይዞአችሁ በርቱ” እያለ ድጋፍ እንደሰጣቸው አንድ ግለሰብን በማናገር አቅርቧል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ሶስት ተጠርጣሪ ገዳዮች ቀርበው የሚናገሩ ሲሆን፣ …

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደጋፊዎቹ የመረጃ ለውውጥ ለመረዳት እንደተቻለው ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ዙሪያ የግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሀላፊ ሚ/ር ያማማቶ እና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎች በመጋበዝ በኢትዮጵያ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን ማሰባሰባቸው ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን እንድታከብርና …

ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፈቃዱን የቀማው ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል በሚል ነው። ከታላቁ ሩጫ በተጨማሪ  እስላማዊ የምርምርና የባህል ማዕከል ፣ ጎህ ቻይልድ ዩዝ ውመንስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ፣ዋን ዩሮ ኢትዮጵያ ፣ ብራይት አፍሪካ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን እና ፓድ ኢትዮጵያ ሊትሬሲ ኢዱኬሽን ኤንድ ቮኬሽናል ሴንተር ናቸው። የድርጅቶቹን ሃብትና ንብረት በስማቸው በማዞር ሲጠቀሙ ፥ …

ግብፅ ውስጥ ከዛሬው የዕለተ ዓርብ (ጁምዓ) ጸሎትና ስግደት በኋላ አዲስ የተቃውሞ ማዕበል የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ከካይሮ በስተሰሜን 130 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ፣ ካፍር ኧል ሼክ በተሰኘው ክፍለ ሀገር፣ በፖሊስና በታጠቁ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር ደጋፊዎች በተደረገ ግጭት 10 ሰዎች ሲሞቱ ከዚያ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ቆስለዋል።

ሰላም በንግዱ ዘርፍ የተሰማራች እና የራሷ ሱቅ ያላት የ 19 ዓመት ወጣት ናት። ንግዷን በሙሉ ኋላፊነት እንዴት እንደምትወጣው ገልፃልናለች።

ካሜሩን በደቡቡ የሀገርዋ ከፊል የሚገኘውን የባካሲ ልሳነ ምድር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች። ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ካሜሩንን እና ናይጀሪያን እአአ ከ1993 ዓም ወዲህ በይገባኛል ጥያቄ ሲያወዛግብ የነበረው ይኸው አካባቢ

ዜግነታቸዉን ቀይረዉ ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶችን በታላላቅ የዉድድር መድረኮች ላይ መመልከት አዲስ መሆኑ ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ ጎልተዉ ይታዩ የነበሩ ኬንያዉያን አትሌቶች ተራዉን ለኢትዮጵያዉያኑ የለቀቁ ይመስላሉ።

በዓለማችን ሶስት ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በሁለት የአሜሪካን ዶላር የየቀን ኑሯቸዉን ይገፋሉ። የጀርመኑ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን Brot für die Welt ማለትም ዳቦ ለዓለም የተሰኘዉ የልማት ተቋም እንዲህ ያሉ የድሃ ደሃ የሚባሉ ወገኖችን ኑሮ ለመደጎም በተለያዩ ሀገራት ይንቀሳቀሳል።

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ እንደተለመደው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተሰናዳ ያለውን ‹‹ሸህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ አዘጋጅቶ አስተላልፏል፡፡ ይህ ዶክመንተሪ የገዥውን ፓርቲ ብፅእና ከመተረክም በላይ ጉልበተኝነትንና ፍረጃን ማእከል አድርጎ ከአኬልዳማ እና ከጃሀዳዊ ሀረካት የቀጠለ በፓርቲያችን እና በዜጎች ላይ የተቃጣ ህገ ወጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ የመንግስትነት ስልጣን የያዘ አካል […]

ለሐውልቱ ሥራ የተዋዋለው ተቋራጭ አድራሻውን አጥፍቶ ጀርመን ከረመ በውሉ መሠረት ከነሐስ የሚሠራውን ሐውልት በ186 ቀን ሠርቶ ማስረከብ ነበረበት ለጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ‹‹ዝክረ አበው›› እንዲያደርስ ታዝዟል ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለዩት የአምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ በአዲስ አበባ ወረዳ ሶስት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት ተወካዮች ‹በሀይማኖት መቻቻል› ዙሪያ የተጠራ የውይይት መድረክ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ተሰማ፡፡ በስብሰባው ላይ የታደሙት የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታዮች የመንግስት ተወካዮች እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ከአክራሪነትና አሸባሪነት ጋር ለማያያዝ ያደረጉትን ማብራሪያ አንድ አይነት አቋም …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡ ታጣቂ ሀይሎች አራት የኬንያ ተጠባባቂ ፓሊሶችንና ስድስት አሳ አጥማጆችን በመግደላቸው በሁለቱ ድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ የኬንያና የኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደህንነት ባለስልጣናት ጉዳዩን አስመልክቶ በመወያየት ላይ ሲሆኑ ጉዳዩ ያሳሰበው የኬንያ ተጠባባቂ ልዩ ሀይል ዛሬ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በገቡት ታጣቂ ሀይሎ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራቱ የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ የክልሉ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊው አቶ ውብሸት ፀጋዬ፣ የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሀላፊው አቶ ይገረሙ ፋሲቆ፣ የክፍያዎች ሀላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ፣ መሐንዲሱ አቶ ሞገስ ዩሀንስ እና ኮንትራክተር የነበሩት …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት ነገ ይካሄዳል የቤተ ሰዎቻቸው የንብረት ይገባናል ጥያቄ ውሳኔ አላገኘም በ1.5 ሚልዮን ብር ጨረታ የተሰጠው የመቃብር ሐውልታቸው አልተሠራም ለ፳ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው “የካንሰር፣ ቲቢና ኤድስ የሕክምናና ማገገሚያ ማእከል” ግንባታን እንደ ስጦታ ያበረከተው ‹‹ራእይ ለትውልድ›› እና በዓል አድማቂዎቹ ‹‹ዉሉደ ጳውሎስ›› የት ናቸው? አምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ፣ …

የግብጽ መንግስት ከስልጣን በተወገዱት ፕረዚዳንት መሐመድ ሞርሲ ደጋፊዎች ላይ የወሰደው ደም ያፋሰሰ እርምጃ የምእራብ ሀገሮችንና ሞርሲን የሚደግፉ የሙስሊም ሃገሮችን ወገዛ አስከትሏል።

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ አሁን ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው ታዋቂው ድርጅት ባወጣው 127ኛ ልዩ መግለጫ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አርሲ ዞን በመንገድ ሥራ ላይ በተሰማራው የጃይናው CGCOC (ሲጂሲኦሲ) ዲራ ማኛ መቻራ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ማህበር የሆነው የዳንዲ ደራርቱ አርሲ ሰራተኛ ማህበር አመራርና አባላት በአሰሪዎቻቸው …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩጵያ በህገ ወጥ የተሻገረውን 11 ቢሊዩን ዶላር ለማስመለስ እና የባለስልጣናትን የሀብት መጠን ይፋ ለማድረግ የተያዘው ቀጠሮ በመለስ ሞት ምክንያት ዳር ሳይደርስ መቅረቱን የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱሊማን ተናገሩ፡፡ አቶ አሊ በጠቅላይ ሚኒስተር መልስ ዜናዊ የስራ ትጋት እና አርቆ  አሳቢነት ምስክርነት ለመስጠት በ ኢቲቪ የፖሊስ …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትን ከአካባቢው ማግኘት የነበረበትን ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰብ እንዳልቻለ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ የመንግስትን የገቢ ግብር መሰበሰብ ያልተቻለው የአዲስ አበባና የአገሪቱ የንግድ ማዕከል በሆነው በመርካቶ አካባቢ እስከ ቅርብ ጊዜ ሲከናወን የቆየው የግብይት ስርዓት በአብዛኛው ሕገወጥ በመሆኑ ነው ብሏል። ይህንን ችግርም ለመቅረፍ ባለሰልጣኑ …

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ከነሃሴ 1/2005 እስከ መስከረም 25/2005 ዓ.ም ድረስ በዳኞች እረፍት ቀን ምክንያት ዝግ የሚሆን ሲሆን በነዚህ የእረፍት ጊዜያት በአዲስ አበባ ካሉት አስር ምድብ ችሎቶች አምስት ያህሉ በተረኝነት የሚሰሩ ሲሆን በድሬዳዋ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠቀሰው ጊዜም መደበኛ ስራውን የሚቀጥል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ …

የፌደራል ትራንስፖርት፤ መለስተኛ አውቶቡሶች በሌሊት ፣ ራቅ ካሉ አካባቢዎች ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይጓዙ፣ የሥራ እንቅሥቃሴአቸውም በ 150 ኪሎሜትር እንዲገደብ መወሰኑ ፣ቅሬታን ያስከተለ መሆኑ ተነገረ። የተሽከርካሪዎቹ የመጫን አቅም ከፋብሪካው

ጥበብ በፀጋዋ የተላበሰችዉ ሙዚቃ አቅፋ ያሳደገችዉ ዕንቁ የሙዚቃ አባት ጥላሁን ገሰሰ ለ53 ዓመታት በዘለቀው የመድረክ ቆይታው በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ልዩ ጣዕም ባላቸው ሙዚቃዎቹ፤ ዘላለማዊ የሆነ ስምን ተክሎ አልፎአል ።

የቱኒዚያዉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ፖርቲ የሌለዉ መንግስት እንዲመሰረት ከተቃዋሚዎች የሚቀርበዉን ጥሪ እንደማይቀበሉ አስታወቁ። የአናህዳ ፓርቲ ሊቀመንበር ራሺድ ጋኑቺ ግብጽ ዉስጥ የሚታየዉ ሁኔታ ለቱኒዚያ ማስፈራሪያ ሳይሆን የሀገሪቱን ቀዉስ ለመፍታት ፓርቲዎች ወደዉይይት እንዲገቡ የሚጋብዝ መሆኑን ዛሬ አመልክተዋል።

ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ክርስትናን መግደል የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡ ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች መቃጠል፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መቆነጻጸል የሚያበቃለት ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት ነበር፡፡ ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ክርስትና እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ እዚህ እሳት ላይ ሦስቱ ሕጻናት ተጥለው ነበር፣ እዚህ እሳት ውስጥ ቂርቆስና እየሉጣ ተወርውረው ነበር፡፡ ይኼ እሳት ቅዱስ ፖሊካርፐስን በልቶት ነበር፡፡ ክርስትና ግን ይኼው አለ፡፡

ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን አይደርሱበትም፡፡ ንብረታችንን ይወስዳሉ፣ እምነታችንን አያገኙትም፤ እኛን ይገድላሉ፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ ናት፡፡ ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር፡፡ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› ተብለናልና ተዘጋጅተን ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረጊስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን በርጋታ የሚሠራውን ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር ያወካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡ ዛሬ በምድር ላይ የለኮሱትን እሳት ብዙዎች በሰማይ እነርሱው ይቀበሉታል፡፡

አይቀርም፤ አምላካችንም ዝም አይልም፡፡ እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡፡

ግብጽ ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዘች ነው፡፡ ሀገርን ማናጋትና ማፍረስ ምንኛ ቀላል እንደሆነ እየተማርንም ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የአስተሳሰብ፣ የበሰለ አመራር፣ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና ብስለት፣ የታመነና የበሰለ ሚዲያ፣ መብቱንና ግዳጁን የተረዳና የሚወጣ ማኅበረሰብ፣ ልካቸውንና መልካቸውን የሚያውቁ የፍትሕ፣ የጸጥታና የውትድርና ተቋማት አጠቃላይ ውጤት እንጂ የምርጫ ሂደትና ውጤት ብቻ እንዳልሆነም እየተማርን ነው፡፡

የእሥራኤልና ፍልስጥኤምን የሰላም ድርድር አስመልክቶ በቅርቡ የተጠየቁት የእሥራኤል ፕሬዚዳንት ሺሞን ፔሬዝ ‹‹ድርድር ማለት እኛ መፍትሔ ነው ብለን የምናስበውን ለሌላ ለማሳመን የምናደርገው ውይይት አይደለም፤ ድርድር ማለት ሁለታችንም በጋራ የምንፈልገው ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ነው፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ‹እንትን ወይም ሞት‹ ብለው የተሰለፉ የግብጽ ልጆች ሀገራቸውን ወደ ማትወጣበት ኪሣራ እየተከተቷት ነው፡፡

አንድ ‹ተረት  በሥዕል› የሚባል መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ሁለት ውሾች መንገድ ላይ ሲሄዱ ከሥጋ ቤት መኪና የወደቀ ምርጥ ሥጋ ያያሉ፡፡ ሁለቱም ወደ ሥጋው ይፈተለካሉ፡፡ ሁለቱም ግን ሥጋው ጋ ከመድረሳቸው በፊት ይፋጠጣሉ፡፡ ሥጋውን እኔ ብቻ ነኝ መብላት ያለብኝ በሚል አባዜ ውስጥ ገብተው ከሥጋው ጎን መናከስ ጀመሩ፡፡ በእግር እየተገፋፋ፣በጥርስ እየተቧጨቁ ቀኑን ሙሉ ሲናከሱ ዋሉ፡፡ በመጨረሻም ተዳከሙ፡፡ ደማቸው ፈስሶ፣ ቆዳቸውም ተሰነጣጥቆ ምድር ላይ ተዝለፍልፈው ወደቁ፡፡

በዚህ መካከል እንዲት ቀን የሰጣት ቡችላ መጣች፡፡ ስታይ ሁለት ደቦል የሚያክሉ ውሾች መሬት ላይ ተጋድመው ያቃስታሉ፡፡ ከአጠገባቸውም ምን የመሰለ ጮማ ሥጋ ተጋድሟል፡፡ ብታያቸው ካሉበት የሚንቀሳቀሱ ዓይነት አይደሉም፡፡ መጀመሪያ ወደ ሥጋው ጠጋ አለች፡፡ በድካም ተገላብጦ ከማየት በቀር ለማስጣል ዐቅም ያለው አልነበረም፡፡ ሥጋውን መንጨት ስትጀምር ከሚያቃስት ድምጽ በቀር የከለከላት የለም፡፡ በመጨረሻም እየጎተተች ወሰደችው፡፡

ቀማኛ ሲጣላ

ተስማምቶ እንዳይበላ

መንትፋቸው ሄደች ዘዴኛ ቡችላ

የሚል በተረቱ መጨረሻ ላይ ሠፍሯል፡፡

በአብዮቱ ዘመን ልሂቃኑ መግባባት፣ ከሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ውጭም ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ማምጣት አቅቷቸው እርስ በርሳቸው ሲባሉና ሲናከሱ ሀገሪቱን ለወታደራዊው ጁንታ አስረከቧት፡፡ በተግባቦትና በውይይት፣ በዕውቀትና በልምድ እንዴት መፍትሔ እንደሚመጣ ከመሥራት ይልቅ ከማርክስና ሌኒን፣ ከማኦና ከኤንግልስ መጻሕፍት ውስጥ መፍትሔውን ሲፈልጉ በጠመንጃው መፍትሔ አመጣለሁ ለሚለው ደርግ ሁሉንም አስረከቡት፡

አብዛኞቹ የግብጽ የፖለቲካ ኃይሎች ሙባረክን ሕዝቡ ሲያነቃንቀው የተደራጁ ናቸው፡፡ የተግባባ ኃልይ፣ አቋም ያለው አባል፣ የተዘረጋ መዋቅር፣ የተጠና ፕሮግራም፣ በሕዝቡ ልብ ውስጥ የገባ ሃሳብ አልነበራቸውም፡፡ የሙስሊም ወንድማማቾች ግን ይህንን በበጎውም በክፉውም ዘመን ሲሠራ ነው የኖረው፡፡ ሀገሪቱ ወደ ምርጫ ስትሄድ የአንዳንድ ፓርቲዎች ሰዎች የተማሩ፣ የታወቁ፣ የተከበሩ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሠሩ ስለሆኑ ብቻ ሕዝብ ይመርጠናል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ የተደራጀ ኃይል፣ የተዘጋጀ መዋቅር፣ የተግባባ አባል ግን አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ከፓርቲያቸው በላይ ሰዎቹ የገዘፉ ነበሩ፡፡ ፓርቲዎቻቸውም የሚጠሩት በፓርቲያቸው ስም ሳይሆን የእገሌ ፓርቲ እየተባሉ ነበር፡፡ ምርጫው ሲመጣ በሚገባ የሠራውና የተደራጀው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አሸነፈ፡፡ ልሂቃኑም ሀገሪቱን አሳልፈው ሰጧት፡፡ ይኼው ዛሬ የመውጫ መንገዱ ጠባር በር ሆነ፡፡

ምንጊዜም ሀገራዊ መፍትሔ ውጤታማ የሚሆነው ሀገር ከመፍረሷ በፊት ከተከናወነ ነው፡፡ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሶማልያና በኮንጎ የምናየው ነገር ይኼንን ይነግረናል፡፡ ሀገር ከፈረሰች፣ ሰው ደም ከተቃባ፣ ሀገራዊ ተቋማትም የሚመጣውን ችግር ሊሸከሙት ከማይችሉበት ደረጃ ከደረሱ በኋላ መፍትሔው ከሁሉም ወገኖች እጅ ይወጣል፡፡ አንድ በሽተኛ ሊድን የሚችለው በተቻለው ፍጥነት በቶሎ ወደ ሕክምናው ቦታ ከደረሰ ነው፡፡ በዘገየ ቁጥር የመዳን ዕድሉ እየጠበበ ይሄዳል፡፡ ሀገራዊ ችግርም እንደዚሁ ነው፡፡

አውስትራልያውያን ‹መድኃኒቱ የትኛችንም ፋርማሲ ውስጥ የለም› የሚሉት ነገር አለ፡፡ ሰሞኑን በሀገራቸው የምርጫ ዘመቻው ተጀምሯል፡፡ ዋናው አጀንዳቸው የሆነውን የሕገ ወጥ ስደት ጉዳይ ሲከራከሩበት ነበር ይህን ያሉት፡፡ በሀገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች ሥልጣን በያዙ ቁጥር ሕገ ወጥ ስደትን ያስቆማል የሚሉትን መፍትሔ ሁሉ ወስደዋል፡፡ በየወሩ 1440 ስደተኞች በጀልባ ለሚገቡባት አውስትራልያ ግን የማንም ፓርቲ መድኃኒት ፍቱን መድኃኒት ለመሆን አልቻለም፡፡ ‹‹ችግሩን ለመፍታት የወሰድናቸው መንገዶችም አልፈቱትም፡፡ ሁሉንም መድኃኒት ሞክረናል፤ ግን በሽታው አልዳነም፡፡ ስለዚህ ሌላ መድኃኒት ነው የሚያስፈልገን፡፡ መድኃኒቱ ደግሞ በየትኛውም ፋርማሲ ውስጥ የለም›› ነው ነገሩ፡፡ አዲስን በሽታ በድሮ መድኃኒት ማከም በሽታውን ራሱን ማወሳሰብ ነው፡፡ እናስ? ከተባለ የተለመደውን የመድኃኒት ማዘዣ እየጻፉ የማያድን መድኃኒት ከመስጠት ይልቅ፣ አዲስ መድኃኒት እንፈልግ፣ እንፈልስፍ፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም የመድኃኒት ዐዋቂዎችን ዕውቀትም፣ ትጋትም፣ ዐቅምም፣ ቆራጥነትም ይፈለጋል፡፡

ነባር መድኃኒት የሚሠራው በሽታው መድኃኒቱን ሳይለምደው ወይም በሽታ ከዐቅም በላይ ከመሆኑ በፊት ነው፡፡ ያን ጊዜ ከሆነ ከአንዱ ፋርማሲ የተሻለውን መድኃኒት ገዝቶ መውሰድ ይቻላል፡፡ በሀገራችን እንደሚደረገው የሕንድ ነው፣ የቻይና ነው፣ የጀርመን ነው፣ የእንግሊዝ ነው፣ የአሜሪካ ነው፣ የደቡብ አፍሪካ ነው? ብለን የተሻለውን መድኃኒት ገዝተን እንውጣለን፡፡ በሽታው ከዐቅም በላይ ሲሆን ግን ሌላ አዲስ መድኃኒት ነው የሚጠይቀው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሽታው ራሱ አዲስ ስለሚሆን፡፡ ያለበለዚያ አዲሱን ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ይሆናል፡፡

ሞያ ከጎረቤት ነውና ሀገራችን ከጎረቤት ግብጽ መማር ያለባት ይመስለኛል፡፡ አሁን መድኃኒቱ ከሁሉም ወገኖች ፋርማሲዎች ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ ሀገራዊ ችግሮቻችንን ለማከም በድሮ መድኃኒቶች ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ አንዳንድ መድኃኒቶች በንጉሡ ጊዜ፣ በወታደራዊው መንግሥት ጊዜ፣ በነጭ ሽብርና ቀይ ሽብር ጊዜ፣ በአሲምባና በደደቢት፣ ተሞክረው ያልሠሩ ናቸው፡፡ በኢዲዩ፣ በኢሕአፓ፣ በመኢሶን፣ በኢጭአት፣ በወዝ ሊግ፣ በአኢሴማ፣ በአኢወማ፣ በ66ና በ97 ተሞክረው ማዳን ያቃታቸው ናቸው፡፡ በሽታው ግን አዲስ ነው፡፡

አሁን የሚበጀን የእኔ ፋርማሲ ውስጥ ያለው መድኃኒት ፍቱን ነው ማለቱን ትቶ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት ለመፍጠር መነሣት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁሉንም ዕውቀት፣ ትጋት፣ ቁርጠኛነትና ዐቅም ይጠይቃል፡፡ ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም፡፡ ያለበለዚያ ግን በግብጻውያን ላይ እንደምናየው ሁላችንም ወደ ጽንፍ ሄደን ‹እንትን ወይም ሞት› ካልን ሁላችንም ሥጋውን እናጣውና ያልታሰበ ቡችላ ነጥቆ የሚሄድበትን ዕድል እናመቻቻለን፡፡ መድኃኒቱ የሁላችንም ፋርማሲ ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ የሚበጀው የእኔን መድኃኒት ብቻ ካልዋጥክ አትድንም የሚለው አሮጌው መፍትሔ ሳይሆን መድኃኒቱን ሊያስገኙ የሚችሉትን አካላት ሁሉ ተጠቅሞ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት መፈለግ ነው፡፡   

  ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ33 ፓርቲዎች ትብብር ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው መንግስት እየተከተለ ያለው የሀይል እርምጃ በዜጎች ህገመንግስታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የተፈጸመ ህገወጥ አምባገነናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባዋል። በአገር ቤትና በውጪ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የነጻው ፕሬስ አባላት እና ማኅበራዊ ድረ-ገጾች በህዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል ያለመተማመን ለመፍጠር ከሚሰራጨው …

(ሊመለከቱት የሚገባ!)
በአማራ ክልል የሚገኙ በተለይም ወጣት ሴቶችን “ወረርሽኝ ገባ” በሚል ክትባት በመስጠት መውለድ እንዳይችሉ የማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመንግሥት መፈጸሙ አይዘነጋም። የዚሁ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን “የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ” ለፀበል ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ቃለምልልስ አድርጎላቸዋል። እነሆ!

The Secret ሚስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
የግጥም አፃፃፍ ዘዬን ያመጡ ነፍሳቸው ትባረክ። “ሚስጢሩ ቀላል ተደረገ” የሚለውን የሚስጢሩን ሁለተኛ ክፍል እነሆ! በአጭር መስመሮች ግጥም ማጠቃለል ቻልኩ። የዚህን ስራ የመጀመሪያ ክፍል ያነበቡ አስተያየት ሰጭዎች “አቀራረብህ መጽሐፉን ላነበቡ ይገባ እንደሆን እንጂ፤ ለሌላው አንባቢ ግልጽ ሊሆንለት አይችልም!” አሉኝ። ለትሁት አስተያየታቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካ በሰጠችው የአጎዋ የገበያ ዕድል ቀነ ቀጠሮ ማራዘም ላይ በሰፊው ሲመክር የነበረው 12ኛው የአጎዋ ጉባዔ አፍሪካ ዕድሉ እንዲራዘም መፈለጓን የአሜሪካ የህግ አውጭ ምክርቤት ተወካዮች ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቁላቸው በመጠየቅ ተጠናቋል፡፡ በ12ኛው የአጎዋ ፎረም የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ  ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ዓመታት ወደ አሜሪካ የላከችው ምርት በየዓመቱ በአማካይ 80 በመቶ …

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል እንዳስታወቀው፣ ሁለቱ ሲሊንደሮች የተገኙት በጽዳት ሰራተኞች ጥቆማ ነው። መንግስት ባእድ ነገሩን ማን እንዳስቀመጠው፣ በባእድ ነገሩ ውስጥ ምን እንዳለ ያስታወቀው ነገር የለም።

ታደሰ ብሩ
1. መንደርደሪያ

የወያኔ ሰዎች ጋር የፓለቲካ ሙግት መሰል ነገር ከገጠማቸው ውይይቱን ያለ ጥርጥር የሚረቱበት ወደሚመስላቸው ወደ “ሰላም” ጉዳይ ይስቡታል። ከዚያም አገራችን ለዘመናት ሰላም የራቃት የነበረ መሆኑን ያስቷውሷችሁና “እድሜ ለኢሕአዴግ ይኸው የሰላም አየር እየተነፈስን ነው” ይሏችኋል። ንግግራቸውን የመቀጠል እድል ካገኙ መረር ብለው “ነገር ግን ፀረ-ሰላም ኃይሎች አልተኙልንም። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በአገር ውስጥ፣ በዲያስፓራ ….” እያሉ የፀረ-ሰላም ኃይሎች ረዥም ዝርዝር ያቀርቡላችኋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አርኣያ ጌታቸው Araya Getachewአርኣያ ጌታቸው

የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው። ሌላው “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዩሱፍ ያሲን

የአሜሪካ ድምፅና የዶቼቬሌ አማርኛ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የቁጫ ሕዝብ የራሱን ማንነት የመወሰን ጉዳይ አስመልክቶ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎች መታሰራቸው ዜና በቅርቡ ተዘግቦ ሰምተናል። 40 የሚሆኑ የአካባቢ ሽማግሌዎች እነዚህ የተሳሩ ሰዎችን ለማስፈታት አዲስ አባባ ድረስ መምጣታቸውንም ተዘግቦዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

እ ጎ አ በ 2030 ምናልባትም ከዚያ ቀደም ብለው ሰዎች ወደ ማርስ ይጓዙ ይሆናል። ለጤና የሚስማማ አየር በሌለባት ፣ ሣር ቅጠል በማይታይባት፣ ቀይ አቧራ በሸፈናት ማርስ ፤ እንዴት ኅልውናቸውን ጠብቀው ይቆያሉ? በጤናስ መመለስ ይቻላል ወይ? ወደ ማርስ

በግብፅ መዲና በካይሮ፤ ከሥልጣን የተወገዱት የሙሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች በተቃውሞ ከመሸጉባቸው አደባባዮች እንዲነሱ ለማድረግ ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ፣ ቢያንስ 124 ሰዎች መገደላቸውን AFP አስታወቀ። በሌላ ዜና የሞቱት 95 ፤ የቆሰሉት ደግሞ

አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማስተጓጎል ከፍተኛ አበል በመክፈል ለአባላቱ ስልጠና ማዘጋጀቱን ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ተቀባይነት ማግኘቱንና በስኬት መቀጠሉን ተከትሎ ኢህአዴግ “አንድነት ፓርቲንና ንቅናቄውን እንዴት ማስቆም ይቻላል” በሚል በከፍተኛ አመራሮቹ ውይይት ካደረገ በኋላ በመላ ሀገሪቱ ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና […]

አፍሪቃ ያለፈውን አሠርተ-ዓመት ባልተቋረጠ የኤኮኖሚ ዕድገት በማሳለፍ ለውጭው ዓለም የመዋዕለ-ነዋይ ባለቤቶች ከመቼውም ይልቅ ማራኪ እየሆነች መምጣቷ በየጊዜው የሚጠቀስ ጉዳይ ነው።