ሾልከው ካመለጡ የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ሰነዶች የምንማራቸው ሃቆች
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2005 እስከ 2010 ባሉት ዓመታት ውስጥ የአሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሚስዮኖች ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የላኳቸው መልዕክቶች ከአሜሪካ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ቡድን እጅ ውስጥ ገብተው ሰሞኑን “ዊኪሊክስ” በተሰኘ ዓለም ዓቀፍ የመረጃ ድረገጽ ላይ ተዘርግፈዋል። በዚህም ምክንያት በከፍተኛ ምስጢርና ጥንቃቄ የተላኩ መረጃዎች ለአደባባይ እይታ በቅተዋል። ከእነዚህም ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ወደ አሜሪካ የውጭ […]