በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላት ይሰግዱ የነበሩ ሴት ሙስሊሞቸ ተደበደቡ፡፡
ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላታቸውን በመስገድ ላይ የነበሩ ሙስሊም ሴቶች በፖሊስ መደብደባቸውን የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። በጁምአ ሰላት ላይ የነበሩት ሙስሊም ሴቶች የተደበደቡት፤ “ሶላት መስገድ የምትችሉት በግቢ ውስጥ እንጂ ከግቢ ውጪ አንጥፋችሁ አትሰግዱም” ተብለው በውጪ እንዳይሰግዱ በፖሊሶች መከልከላቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ሙስሊም ሴቶቹ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት …