የግብጽ መንግስት ከስልጣን በተወገዱት ፕረዚዳንት መሐመድ ሞርሲ ደጋፊዎች ላይ የወሰደው ደም ያፋሰሰ እርምጃ የምእራብ ሀገሮችንና ሞርሲን የሚደግፉ የሙስሊም ሃገሮችን ወገዛ አስከትሏል።

አጎአ – አዲስ አበባ – 2013 ​​
አጎአ – ከንግድ አስከ አቅም ግንባታ
ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ሀገሮች ያወጣችው ከቀረጥና ታሪፍ ነፃ የንግድ ተጠቃሚነት ዕድል ሕግ አጎአ ከንግድ በተጨማሪ የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት በአዲስ አበባ ጉባዔ ላይ የተሣተፉ ኢትዮጵያዊያን የንግድ ማኅበረስብ አባላት አስታወቁ።

ኢትዮጵያ የአጎአ የንግድ ዕድልን ተጠቅማ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የምትልከው የምርት መጠን ቢጨምርም ከዚህም በላይ የማደግ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ መንግሥት ይገልፃል።

ለተጨማሪ ዝርዝር የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የቢላል ራዲዮ ጋዜጠኞች መታሠር ያሣዘነው መሆኑን ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነትና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ አስታውቋል፡፡

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ – /ፎቶ – ፋይል/ ​​
አጎአ እንዲሰፋ ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠየቁ
ዩናይትድ ስቴትስ ከሠሃራ በስተደቡብ ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች ያወጣችው በምኅፃር አጎአ የሚባለው ከቀረጥ ታሪፍ ነፃ የመናገድ፤ የአፍሪካ የዕድገትና የንግድ ዕድሎች ተጠቃሚነት ሕግ ረዘም ላሉ ዓመታት መቀጠል እንዳለበት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠይቀዋል፡፡
አጎአ – አዲስ አበባ – 2013 ​​
አዲስ አበባ ላይ በተከፈተው የአጎአ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ጠቀሜታው ሊሰፋ፤ ከገበያ ዕድልም ሊያልፍ ይገባዋል ብለዋል፡፡

የአሜሪካው የንግድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ማይክል ፍሮማን በበኩላቸው አጎአ አሜሪካና አፍሪካን በንግድና በምጣኔ ኃብት የሚገኛኙበትን ሁኔታ በእውነት የቀየረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አጎአ – አዲስ አበባ – 2013 ​​
ዝርዝሩን …

ሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ላይ እየተካሄደ ባለው 14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ድል በዓለሙ ሠንጠረዥ ሁለተኛ ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡

የግጭት አፈታት ​​
የግጭት አፈታት
በአንድ ቡድን ወይም በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር ግጭት ቋሚ መፍትሔ የሚያገኘው በድርድርና በውይይት አንዱ የሌላውን ጥያቄ ግንዛቤው ውስጥ ሲጨምር መሆኑን የግጭት አፈታት ስልት ምሁሩ አቶ ሰለሞን ጥላሁን ገልፀዋል። የግጭት አፈታት ​​​​ አቶ ሰለሞን ከትዝታ በላቸው ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ግጭት ተወልዶ እስከሚሞት እንዲባባስ ስለሚያደርጉትና ስለሚያረግቡት፣ እንዲሁም የማጥፊያው መንገዶች በሰፊው ተንትነዋል፡፡

ባለሙያው በማብራሪያቸው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ ተመጣጣኝ ያልሆኑ ግቦች ወደ መግባባትና ወደ ግጭት ሊያደርሱ እንደሚችሉም አመልክተዋል፡፡
የግጭት አፈታት ​​
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአፍሪካ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች
አጎአ በሚል ምኅፃር በሚጠራው አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በቀለለ ሁኔታ ለመናገድ እንድትችል መንገድ በሚጠርገው የንግድና የገበያ ተጠቃሚነት ዕድል መርኃግብር የአፍሪካ ሴቶች እንዳልተጠቀሙ ተገልጿል፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥም የአፍሪካን ሴቶች አቅም ማጎልበት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበር አሳስቧል፡፡

ማኅበሩ አዲስ አበባ ላይ አዲስ ቢሮ ከፍቷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምኃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የኦሮሞ ተወላጆች ዋሽንግተን ላይ ተሰለፉ
ከዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥትና በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰልፎችን አካሄደዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት ሰልፈኞች ከመልዕክቶቻቸው መካከል “በምሥራቅ ሐረርጌ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም፤ በኦሮሞ ምሁራንና ተማሪዎች ላየ እየበረታ ያለው የመብት ረገጣ ይቁም፤ በኦሮሞ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለው ከመሬት የማፈናቀል ሥራ ይቁም” የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ሰልፉ የተዘጋጀው በኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር መሆኑ ታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ሰልፎቹን የተከታተለውን የሶራ ሃለኬን ዘገባ ከያዘው የድምፅ ፋይል ይስሙ፡፡

ምሥራቅና በደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ በኤድስ ላይ ተጨብጧል የሚባለውን ግዙፍ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መርኃግብር ባለሥልጣናት አሞግሰውታል፡፡

ከኤድስ ጋር የተያያዘው የሞት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን እና ለኤችአይቪ እየተጋለጠ ያለው ሰው ቁጥርም በብዙ እየወረደ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ጠቁሟል፡፡

ይህ ክስተት መድኃኒት በብዛት የመገኘቱ ውጤት ነው የሚለው ይህ ሪፖርት ፈተናዎቹ ግን እንዳሉ እንደሚቀጥሉ አሳስቧል፡፡

ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ላይ በተካሄደው የአህጉሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከጋምቤላ በስተቀር በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች የኤችአይቪ ሥርጭት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር …