ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉ
የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ለሰባት ዓመታት እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ እዚያው ወኅኒ ውስጥ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቪኦኤ ገለፀዋል፡፡

ፖሊስ የሰጠውን ማስረጃ አይተናል ያሉት እስከፍርዱ ድረስ ከይግባኝ በፊት ቆመውላቸው የነበሩት ጠበቃ አቶ ጥላሁን ታደሰ ኢንጂነር ተስፋሁን ያረፉት ባለፈው ዓርብ ሌሊት መሆኑን አመልክተው የፖሊሱ መረጀ እራሣቸውን ማጥፋታቸውን እንደሚጠቁም ጠቁመዋል፡፡

ኢንጂነር ተስፋሁን እራሣቸውን አጥፍተዋል የሚለውን መግለጫ ለማመን እንደሚቸገሩ የሚናገሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ሕክምና እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበረና የጠየቁትን አለማግኘታቸውን እንደሚያውቁ፤ ከእህታቸው ጋርም በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረ ቤተሰብ እንደነገራቸው …

መጠለያ ​​
ኢትዮጵያ በምሥራቅ ተከሰተ የተባለውን ፖሊዮ እያጠናች ነው
ኢትዮጵያ እአአ ከ 2008 አም አንስቶ ማለት በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በፖልዮ ማለትም በልጅነት ልምሻ የተያዘ ሰው እንደተገኘ ማስታወቋን የአሜሪካ ድምጽ ሬደዮ ዘጋቢ ሜሪ አሊስ ሳሊናስ ያነጋገረቻቸው የሮተሪ-ኢንተርናሽናል ፖሊዮን የማጥፋት ዓለምአቀፍ ዘመቻ አባል ካሮል ፓንዳክ መግለፃቸውን ዘግበናል፡፡

የታመችው ያልተከተበች የአንድ ዓመት ተኩል ሕፃን መሆኗን ያስታወቁት ፓንዳክ ሶማልያ ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑ፣ በሰሜን ኬንያ ደግሞ ከአሥር በላይ የሚሆኑ የፖልዮ ህሙማን እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በምሥራቅ ተከሰተ የተባለውን ፖሊዮ እያጠናች ነው ​​
“አካባቢው ለሶማሊያ ቅርበት ያለው በመሆኑ የቫይረሱ ወደዚያ መዛመት የሚደንቅ አይደለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ውስጥ …

መሠረት ደፋር በስቶክሆልም ዳያመንድ ሊግ በ 3 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የዓመቱን የዓለም ፈጣን ጊዜ በማስመዝገብ አሸንፋለች። በሉዥኒኪ ሞስኩ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 5 ሺህ የወርቅ ሜዳልያ ከወሰደች ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ መሆኑ ነው መሠረት ይህን ድል የተቀዳጀችው።

በሐሙሱ የዳያመንድ ሊግ 3 ሺህ ሜትር አዲሱ የመሠረት ደፋር የዓመቱ ፈጣን ጊዜ 8 ደቂቃ ከ 30 ነጥብ 29 ሴኮንድ ነው።

ሌላዋ የኢትዮጵያ አትሌት ሲፋን ሐሰን የግሏን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ በሦስተኝነት ጨርሳለች።

መርሲ ቼሮኖ ከኬንያ የብሩን ሜዳልያ አጥልቃለች።

የዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም ስለ Martin Luther King, I have a dream ንግግር 50ኛ አመት በአል የሚዘክሩ ዜማዎችን እና ሙዚቃ ነክ ዜናዎችን ያስተናግዳል፡፡

መሐመድ አማን ​​
አዲስ አበበ ቢቂላ፣ አዲስ ምሩፅ ይፍጠር፣ አዲስ መሐመድ አማን
“ከአሁን በኋላ በዓለም አቀፍ ትራኮች የአጭር ርቀት ሩጫ አሸናፊነት በር ለኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም ተከፍቷል” ሲል በርቀቱ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ወርቅ በስምንት መቶ ሜትር ያገኘው መሃመድ አማን አስታወቀ።

“መሃመድ አማን የዚህ ዘመን አበበ ቢቂላና ምሩፅ ይፍጠር ነው” ሲሉ የተናገሩት ደግሞ አሰልጣኙ ንጉሴ ጊቻሞ ናቸው።

መሃመድ አማን ዛሬ ለጋዜጠኞች የሰጠውን መግለጫ የተከታተለውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
መሐመድ አማን ​​

ከሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን – ESFNA፤ የመላው ኢትዮጵያውያን ስፖርት ማኅበር – AESAONE እና ከጃኖ የሙዚቃ አባላት ጋር።