ከማናችንም ኢትዮጵያውያን በፊት ባለስልጣናት ህግ አውጪዎች ህግ አስፈጻሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች ለህግ ተገዢ ይሁኑልን::ምንሊክ ሳልሳዊ
በሃገራችን ውስጥ እየተከሰተ ያለው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እኛ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የአለም ህዝብ ትኩረት በመሳብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በገሃድ እየታየ ነው:: ይህ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የሚፈጸመው ቁልፍ ባለስልጣናት የፖሊስ መኮንኖችን በመጠቀም የህዝብን ሰላም ማደፍረስ እና ሽብር መንዛት የእለት ተግባራቸው አድርገው ተያይዘውታል::
ብልሃት በሌለው መልካም አስተዳደር የፖሊስ ባለስልጣናት የሚፈጽሙት ኢሰብኣዊ ተግባራት የህዝብን የመኖር ሁኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከቶታል::ከጥያቄ ምልክትም አልፎ ከባባድ ወንጀሎች በህዝብ የእለት ተለት ሂደት ውስጥ ራሱን መንግስት ያሰኛው ሕወሓት እየፈጸመ ነው::የኢትዮጵያ ህዝቦች ሃይማኖት እና የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይለያቸው በጋራ የሚያቀርቡትን ጥያቄ
ላይ መልስ መስጠት እየተቻለ በጉልበት እና በማስፈራራት በመግደል እና በማሰር የሚመጣ ለውጥ የለም:; የህዝቦች ትግል በየፈርጁ እየቀጠለ ይሄዳል::ማንኛውም ህዝብ ለለውጥ እስከተነሳ ድረስ የሚሞትለት አላማ እንዳለውም ማሰብ ያስፈልጋል::
ባለስልጣናት ህጋዊ የሆኑ ዜጎች እንዲታሰሩ እንዲገላቱ የሚያደርጉት ከተጠያቂነት አያድናቸውም:; ህገመንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ዜጎችን በአገራቸው እና ህጋዊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማዋከብ ስልጣን ላይ ያለው ጁንታ ህግን እንደማያከብር ፍንትው አድርጎ ያሳየበት ህገወጥ ተግባር በተደጋጋሚ እያየን ነው:: ራሳቹህ ያወጣችሁትን ህግ ያላከበራችሁ እኛ እንዴት እናክብርላችሁ?? መጀመሪያ አንድ መንግስት ባለስልጣኖቹ ህግን አክብረው ለህዝቡ አርኣያ መሆን አለባቸው:: እያየን ያለነው ግን ሕግ አውጪው እና አስፈጻሚው አካል ህግን እየጣሰ መሆኑን ነው:: ስለዚህ ብልሃት አልባ ዲሞክራሲ በሞላባቸው እና የሰውን ልጅ መብት ትርጉም በማያቁ ባለስልጣናት ከመመራት ሞትን መርጦ መታገል አማራጭ እየሆነ ያለበት ዘመን ላይ ደርሰናል::
ከማናችንም ኢትዮጵያውያን በፊት ባለስልጣናት ህግ አውጪዎች ህግ አስፈጻሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች ለህግ ተገዢ ይሁኑልን::ለእኛም አርኣያ ይሁኑ::በጉልበት እና በሃይል በብልሃት አልባ ዲሞክራሲ ሽብር እየነዙ ሃገር አይመራም!!!ምንሊክ ሳልሳዊ