ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለእናቶችና ህጻናት ጤንነት ታስቦ ከተለያዩ ለጋሽ ሃገራት በእርዳታ የተገኙትን አምቡላንሶች ከታሰበላቸው አገልግሎት ውጭ ለተለያዩ ፖለቲካዊ ስራ በመመደብ ሲጠቀሙባቸው እንደነበር በምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የሚገኙ አንድ የስራ ኃላፊ ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ኃላፊ እንደተናገሩት የወረዳ አስተዳዳሪዎች በቂ በጀት እንዲመድቡ መመሪያ ቢሰጣቸውም ችላ በማለት አገልግሎት መስጠት የነበረባቸው …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 15 ፣ 2007) ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን ውስጥ በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ። የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ በተንዛዛ የፍርድ ቤት ቀጠሮ በእስር ሲማቅቁ የነበሩት አራቱ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች፣ የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት፣ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሳሾችን አሰናብቷል። በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞው …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል አቶ ድሪባ ኩማ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በከተማዋ መቀነስ ያልቻለው መመሪያዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም የማይችል አመራር በመኖሩ ነው ሲሉ በስራቸው የሚገኙ አመራሮችን ወቅሰዋል፡፡ ከንቲባው ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር 2007 የተጠናቀቀውን የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ ባወጣው 137ኛ ልዩ መግለጫ፣ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውንና 83 የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰራቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል። በደብረማርቆስ ከተማ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የተገደለ መሆኑን የቅርብ ቤተሰቦቹ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የመኸርና የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉና በመዘግየቱ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሰለባ ለሆኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ግምቱ ከ386 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ7 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አፋጣኝ የሆነ የሕይወት አድን የምግብና ሌሎች …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የዞኑ አስተዳደር ህገ ወጥ ግንባታ ናቸው ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች ለማፍረስ መሞከሩን ተከተሎ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውና መደብደባቸው ተገለጠ። በሳምንቱ መገባደጃ በዞኑ በምትገኘው የቦሎሶሶሬ ወረዳ በተቀሰቀሰ በዚሁ ግጭት ከ20 በላይ ነዋሪዎች በላይ ነዋሪዎችና ህገ-ወጥ ናቸው የተባሉትን ግንባታዎች ለማፍረስ የተሰማሩ ከ10 በላይ አፍራሽ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ ፓርቲ የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወጣት ተስፋየ ታሪኩ፣ ቀድም ብሎ በእስር ቤት ውስጥ እየተደበደቡ መሆኑን ለፍርድ ቤት ማመልከቱን ተከትሎ ፣ ፖሊሶች ዘቅዝቀው በጠመንጃው ሳንጃ በሽፋኑ ጀርባውን ደብድበውታል፣ እጁና እግሮቹም ተጎድተዋል። ተስፋየን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ሬዲዮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ፣ የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል። ከ11 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ባለበት የሰራተኛውን የመጨረሻ የክፍያ ወለል ማስተካከል ፈታኝ መሆኑን የገለጸው ቢቢሲ፣ ወጣቱ በ50 …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር፣ አሚሶም ተልኮ ውጪ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአሚሶም ምድብ አራት የጦር አዛዥ የሆኑት አብዱራህማን አብዲ ዲምቢሊ ቅሬታቸውን አሰሙ። ጅቡቲያዊው የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱረህማን ፣ ካለ ህብረቱ ጦር ትእዛዝ በሂራን ግዛት የኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ደምስሰው አካባቢውን ከተቆጣጠሩት በኋላ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡ ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል። መዛኝ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዊ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኅብረት ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የሆኑትስዩም መስፍን በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይሞክራሉ ሲሉ ወቀሳቸውን አሰምተዋል። ሚካኤል ማኩዊ ” የኢጋድ አደራዳሪዎች ደቡብ ሱዳንን የሙከራ ምድር ለማድረግ ይሞክራሉ።አንዳንዶቹ በጭራሽ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።የግድ መፈረም አለባችሁ ብሎ ለተደራዳሪዎች አስገዳጅ ውል ማቅረብ፣ ካልፈረማችሁ እኛ …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ መቋረጥ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ለውጥ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለያዩ አጎራባች ወረደዎችና ቀበሌዎች ህዝቡ መኪና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና መኪና እንዳይተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በጋራ በመሰባስብና ድምጻቸውን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበቱ ሲሆን፣ ዛሬም ዩኒቨርስቲው በሚገነባበት …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፣ የተጠቀሰውን ድርጊት መፈጸማቸውን ነገር ግን ወንጀለኞች አለመሆናቸውን ተናግረዋል። በወጣቶቹ ላይ የቀረበው ክስ ግንቦት 7 የተባለውን አሸባሪ ቡድን ለመቀላቀል ሲሄዱ ማካይድራ በተባለው የድንበር ከተማ ላይ ተይዘዋል የሚል ነው። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤት በቅርቡ ከፍተኛ ቅጣት የጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጠየቁ 20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ቀስቅሰዋል በሚል በ14ኛ ወንከል ችሎት የተከሰሱት ከድር መሃመድ፣ ነዚፍ ተማም፣ ካሊድ መሃመድ፣ ፉአድ አብዱልቃድር፣ ኢብራሂም ካሚል፣ አብዱ ጁባር፣ ሁሴን አህመድ፣ ሃሚድ …

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በላከው ሪፖርት በከተማ ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ፣ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። በርካታ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ቀኑን ሙሉ በየማደያዎች ተሰልፈው የታዩ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል። በባህርዳርም እንዲሁ በቅርቡ ተመሳሳይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ድርድር፣ ፕ/ት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ተገኝተዋል። የድርድሩ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ሲሆን፣ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ፊርማቸውን የማያኖሩ ከሆነ ማእቀብ ይጠብቃቸዋል ተብሎአል። የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድርድሩን በተመለከተ የሚጋጩ መረጃዎችን እየለቀቁ ነው። የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ ድርድሩ ሳይጠናቅ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 7 ፣ 2007 በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ አድማ በታኝ ፖሊስ በአካባቢው የሰፈረ ሲሆን፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ መኖሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ በሚታሰበው ቦታ አካባቢ ዛሬም ግጭት እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። በትናንቱ ግጭት የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ፣ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በማንዱራ ወረዳ ቴዎድሮስ ስሜነህ የተባለ ሰው በፌደራል ፖሊስ አባላት ተደብድቦ ተገድሏል። ቴዎድሮስ ከትናንት በስቲያ በፌደራል ፖሊስ አባላት ከቤቱ ተይዞ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሲደበደብ አርፍዷል። ድብደባውን ተከትሎም ህይወቱ ወዲያውኑ ማለፉን ፣ የቀብሩ ስነስርዓት ትናንት መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ቴዎድሮስ የተቃዋሚ ሃይሎች አባል ነህ ተብሎ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃኪን ቲም ሰብዓዊ መብትን ከሚያፍኑ መንግስታት ጋር አብሮ መስራቱ ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ ከዚህ ዕኩይ ተግባሩ ይታቀብ ዘንድ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ ቢደርሰውም ፣ አሁንም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት አላቋረጠም ሲል ሂውማን ራይትስ ወች በሪፖርቱ ገልጿል። የጣልያኑ የመረጃ መረብ ጠላፊ ድርጅት ሃኪን ቲም ለተለያዩ መንግስታት የመገናኛ መረብ መጥለፊያ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያዊው ከአዲስ አበባ ተነስቶስ ስዊዲን ስቶኮልም አየር ማረፊያ መድረሻውን ባደረገው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው አውሮፕላን ውስጥ በዕቃ መጫኛ ውስጥ ለስምንት ሰዓታት ተደብቆ ስዊድን አራንዳ አየር ማረፊያ ገብቷል። የስዊድን ፖሊስ እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ጣሊያን ሮም ላይ አርፎ ነበር። የአየሩ ሁኔታ በጣም ቀዝቃዛ የነበረ ቢሆንም የጤንነቱ ሁኔታ ግን በጥሩ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአመታት በፊት ተጀምሮ በማዝገም ላይ ያለው የባህርዳር ሞጣ ደጀን መንገድ አሁንም በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በትራንስፖት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የስምሪት ተተኪ የስራ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ባለሙያ እንደተናገሩት መንገዱ በተደጋጋሚ በመበላሸቱ እና ለረዢም ጊዜ ባለመሰራቱ ህብረተሰቡ መቸገሩን ገልጸው፤ለመንገድ ስራ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ፣ ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ …

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለም ላይ የሚታየውን የአየር መዛባት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት እየገለጹ ነው። በምግብ እጥረቱ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትና ሌሎች ድሃ አገሮች ክፉኛ ሊጎዱ ይችላል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረው የምግብ እጥረት በባሰ ሁኔታ በያዝነውና በመጪው አመት ሊከሰት እንደሚችል ያስጠነቀቁት መንግስታቱ፣ …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 8, 2007) ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ወጣት ከሀገር በመሰደድ ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት መንግስት አስታወቀ። የወጣቶቹን ስደት ለመቆጣጠር ጠንካራ የተባሉ ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊ ቢያደርጉም፣  ከዚህም በፊት ስደት በማይታወቅባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍተኛ ወጣት በመሰደድ ላይ እንደሚገኝ በመንግስት የተቋቋመው የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። በድንበር በኩል ከሚደረጉ ስደተኞች …

ኢትዮጵያ በኑሮ ደረጃ ስሌት ከ38 የአፍሪካ አገሮች 32ኛ ደረጃ ያዘች ኢሳት ዜና (ነሓሴ 7, 2007) ከአፍሪካ የተሻለ የማህበራዊና የኢኮኖሚ አገልግሎት እንዲሁም የዜጎች አጠቃላይ የኑሮ ደረጃቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብለው ከተቀመጡት 38 የአህጉሪቱ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ32ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ ባደረገው አመታዊ ረፖርት ገለጸ። ሃገሪቱ ለዜጎቻቸው የሚያቀርቡት የጤና፣ የትምህርት፣ ኢኮኖሚያዊና፣ …

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2007 እኩለ ቀን ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን ባለው መረጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል። ረብሻው እስከ አመሻሽ ቀጥሎ ከደሴ የተነሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ደርሰው ጥበቃ እያደረጉ ነው። …

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትናንት ነሃሴ 6፣ 2007 ዓም በሃድያ ዞን በሆሳእና ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መታሰራቸውን የአይን እማኖች ገልጸዋል። በርካታ ወጣቶች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መደብደባቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ሆስፒታል የተኙት አመሻሹ ላይ ወደ እስር ቤት …

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰበት የዲስፖራ ክብረበዓል ትላንት በአዲስአበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በታላቅ ፌሽታ ተጀምሯል፡፡ ዝግጅቱ በተለያዩ ክንውኖች ለተከታታይ አምስት ቀናት ይቆያል ተብሎአል፡፡ ዲያስፖራ በልማት ለማሳተፍ በሚል ሽፋን የዲስፖራውን ህብረተሰብ ለመያዝ እንዲመች ታስቦ በተዘጋጀው በዚህ በዓል ላይ በግምት 2ሺ ገደማ የዲያስፖራ አባላትና በሀገር ውስጥ …

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ከዝናብ እጥረት ጋር በተያያዘ በተነሳው ድርቅ በርካታ ገበሬዎች ለችግር የታገለጡ ሲሆን፣ ይህም ሳያንስ የዞኑ ካድሬዎች አርሶአዳሪው ህዝብ ማዳበሪያ በብድር በግድ እንዲወስድ እያስገገደዱት መሆኑ ችግሩን አባብሶታል። የዝናብ መጠኑ መዋዠቅ ገብሬውን በስጋት ላይ የጣለው መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ዝናብ ጭራሽ …

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ለሕገወጥ አሸጋጋሪዎች የሚከፍሉት ከ150 እስከ 200 ዶላር ስለሌላቸው፣ ከ600 ኪሎሜትር በላይ ለሁለት ሳምንታት አንዲት የፕላስቲክ ኮዳ ውሃ ብቻ ይዘው በእግራቸው ድንበር አቋርጠው በፑትላንድ ራስገዝ የቦሳሶ የወደብ ዳርቻዎች ይደርሳሉ። የመን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ በሌሎች ሕገወጥ አጋቾች እጅ የሚወድቁት ስደተኞች፣ ለአጋቾች የሚከፍሉት ገንዘብ የሌላቸው …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 7, 2007 ዓም) በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት መቋጫ እንዳላገኘ በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት የህወሃት አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያይተዋል። ባለፈው እሁድ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በሚል በተደረገው ጥሪ መሰረት ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተካሄደው ስብሰባ የመሩት ከኢትዮጵያ የመጡት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያምና አቶ ዳንኤል አሰፋ የተባሉ የህወሃት  አመራር …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተቃውሞው ሰልፍ መንስኤ ከገንዘብ ምንዛሬ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ተኩል ላይ በተፈጠረው ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በነጋዴዎች በኩል የሚልኩትን ገንዘብ ለማስቀረት ከፌደራል የመጡ ፖሊሶች እርምጃ መውሰዳቸው፣ ለተቃውሞ ሰልፉ መነሻ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ተወላጆች፣ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢህአዴግ የድርጅት አባለት ግምገማ መጠናቀቁን ተከትሎ የግምገማ ውጤት እየወጣ ሲሆን፣ በዚህም ግምገማ መሰረት በርካታ የከተማዋ ወረዳ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታውቋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ከ50 በላይ አመራሮች ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ከ20 በላይ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ክ/ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሩዝ በማምረት የሚታወቀው የፎገራ መስክ ለሸንኮራ አገዳ ተክል ሊውል ነው መባሉን ተከትሎ ፣ ሩዝ በማምረት ኑሮአቸውን የሚገፉ አርሶአሮች ስጋት ላይ ወድቀዋል። በጣና ሃይቅ ዳር የሚገኘው ሰፊው የፎገራ ረግራጋማ ሜዳ ከማዳበሪያ ነጻ ሆነ ሩዝ በማምረት የሚታወቅ ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በአገሪቱ የሚታየውን የስኳር እጥረት ለመፍታት በሚል ሰበብ አርሶአደሮችን …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ መንግስት በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመያዝ በሚል ስሌት የሚሰጠው የቤት መስሪያ ቦታ፣ ተመሳሳይ ጥያቄ ላቀረቡ ፣ በአገር ውሰጥ ለሚኖሩ ዜጎች ባለመስጠቱ፣ ቅሬታ እየተፈጠረ መሆኑን ዘጋቢአችን ገልጿል። መንግስት የዲያስፖራ ቀን ለማክበር በሚል ሰሞኑን በክልሎችና በአዲስ አበባ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በተነሱት ውይይቶች ላይ ይህ የቅሬታ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ኤልኒኖ ከግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ በመከሰቱ በኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭት መዛባት መከሰቱን፣ ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሁለት ወራትም የዝናብ መዛባቱ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል። የኤጀንሲው ሃላፊዎች ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በግንቦትና በሰኔ ወራት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ ዝናብ የነበረ ቢሆንም በሐምሌ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠይቆባቸዋል፡፡ አመራሮቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን እየመለመሉ ይልካሉ፣ኤርትራ ድረስ ሄደው ስልጠና ወስደዋል፡፡›› የሚል ክስ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው አፍሪካ ፎረም ፌስቲቫል ላይ የተገኘው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ከምግብ፣ ከቡና፣ ከመጠጥ ሽያጭና ከተለያዩ ገቢዎች ያገኘውን ገንዘብ በኢሳት አካውንት ማስገባቱን ገልጿል። በእለቱ የኢሳት አላማ ለውጭ አገር ዜጎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ ለኢሳት በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርጉ አባላትንም መዝግቧል። በምግብ ዝግጅት ሴቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለጸው አስተባበሪ ኮሚቴው፣ …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ አሎ ቀበሌ የሚገኙ ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሃላፊዎች ‘ እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጆች ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው…ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ’ በማለት ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በመንጠቅ …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚታተመው ሳምንታዊ የሰብአዊ እርዳታ መጽሄት እንደዘገበው መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የታየውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ለጋሽ አጋራት አስቸኳይ እርዳታ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርቧል። ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጠርባቸው ይችላል ተብሎ ለተሰጋባቸው ቦታዎች መንግስት 700 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል። ዞን 3 በሚባለው የአፋር አካባቢ እንዲሁም ስቲ ዞን …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ፣ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱና ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፣ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው በመጠየቃቸው፣ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን …