የኢትዮጵያውያን ወጣቶች አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተነገረ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 8, 2007)
ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ወጣት ከሀገር በመሰደድ ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት መንግስት አስታወቀ።
የወጣቶቹን ስደት ለመቆጣጠር ጠንካራ የተባሉ ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊ ቢያደርጉም፣ ከዚህም በፊት ስደት በማይታወቅባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍተኛ ወጣት በመሰደድ ላይ እንደሚገኝ በመንግስት የተቋቋመው የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል።
በድንበር በኩል ከሚደረጉ ስደተኞች በተጨማሪ በቱሪስት ቪዛ እየተሰደዱ ያሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን እና እገዳ በተጣለባቸው ኳታርና የመን ሀጋዊ ሽፋን እየተሰጣቸው የሚሰደዱ ሰዎች መኖራቸውን የምክር ቢርቱ ሀላፊዎችን ዋቢ በማድረግ በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
ድርጊቱን ለመቆጣጠር የተወሰዱ እርምጃዎችም የተጠበቀውን ውጤት ሳያመጡ መቅረታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ገልጸዋል። በየመን የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት የስደተኞች ኮሚሽን ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር አሳስቦት እንደሚገኝ የድረጅቱ ባለስልጥናት ለኢሳት መግለጻቸውን የሚታወስ ነው።
ጦርነት በቀጠለባት የመን በየወሩ ወደ አራት ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን በስደት እንደሚገቡ የድረጅቱ ባለስልጣናት ለኢሳት መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ድርጅቱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን መንግስት ሲገልጽ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በበኩሉ ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ለማድረግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የማስተማር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ከ 200 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር መመለሱ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ድረስ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከየመን መውጫ አጥተው እንደሚገኙ ገልጿል።
ፍልሠትን ለምሣሌ ኬንያን እና ፊልፒንን ብንወሥድ መንግሥታቸው ጠንካራ ሠብአዊ መብት ጥበቃ ሥለሚያረግ ችላ አይሉም ግን እኛን ብንመለከት የዜጎች የመንቀሣቀሥ መብት ያገተ ድርጅት ነው ከዚህም አልፎ በኤንባሢዎች ዘንድ ጫናን በመፍጠር ቪዛ ማሥከልከል ጭምር ናቸው የዚህ የወያኔ ሥጋቱ በውጭ የተጠናከረ ብርቱ ሀይል ካለ ከሥልጣን የመውረድ እድሉ የሠፋ ነው ይህን አይፈልጕም የሥርአቱ አባል ብቻ የልማት ተቋዳሽ ያረገው ብቸኛው አብዬታዊ ልማታዊ ወያኔ ነው ዲሞክራሢን በልማትና በሽብርተኝነት ሸብቦ የያዘው አሥመሣይ መንግሥት ነው ህዝቡ ሀገሩን ከወያኔ በተሻለ እየለወጠ ይገኛል የህዝቡ ገንዘብ ነው 50% በላይ የሚሆነው በጅት በሙሥና እና ለትግራይ ክልልና ለሠራዊቱ በድብቅ የሚተላለፍ ነው እንዲሁም የሡ ካድሬዎች ውጭ ከወጡ አመት ያልሞላቸውን ዲያሥፖራ ብሎ ከዚሁ በጀት የሚፈልገውን እቅድ ላይ በግዳጅና ብር በማበደር የበላይ ሆኖ እያሽከረከረ ይገኛል የዚህ ማሣያ በርካታ የአበባ ልማት ከሥረው መሬቱም መክኖ ይገኛል ይህ ነው የልማታዊ መንግሥት ቅሪቱ።