በኩዌት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔው ጸናባት
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት …