ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌጁ ተማሪዎች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው ወደ ፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ከትናትና በስቲያ ያመሩ ቢሆንም ፤የስራ አመራር ቦርዱ ያለው ችግር እስኪጣራ ድረስ ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን እና ተማሪዎችም ከሐምሌ 8 ቀን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ አሳውቋል። ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበው ወደ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሺዋ ዞን የደብረ ብርሃን ከተማ ኗሪዎች የመንግስት ሹማምንት የሚያደርሱባቸውን በደሎች በመዘርዝር ለመንግስት አቅርበዋል። ክልሉ በቅርቡ በጀመረው የህዝብ ብሶቶችን መስሚያ መድረኮች ላይ ነዋሪዎች ” በአደባባይ እንደበደባለን ፤እንታሰራለን፤ በአገራችን በሰላም ለመኖር አልቻልንም” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡በተደጋማሚ በሚደርስባቸው በደል አገር ጥለው የሚሰደዱ ዜጎች መበራከታቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ሹመት የሚሰጠው በዘመድ ዝማድ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በያዝነው ወር ብቻ 500 ሲቪሎች፣ ከጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ዋርዴር እና ጎዴ በደህንነት ሀይሎች ተወስደው እስር ቤት ገብተዋል። አዲሱ የእስር ዘመቻ የተከፈተው በቅርቡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደሮች ከድተው እጃውን ለኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ከታሰሩት መካከል በርካታ ህጻናትና ሴቶች ሲገኙበት፣ አብዛኞቹም ጅጅጋ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 11 ሺ 93 ስዎች ከነፍስ ግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው  የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ  አካል ማጉደል እና …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል። እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ። አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ  በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ ትናንት በአመታዊ የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ  መፈክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል። ተማሪዎቹ ሲያሰሙዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል፦የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!፣የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!፣ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በቅርቡ ባካሄደው የአሰራር ሥርዓት ጥናት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነው ብሎአል፡፡ በፖሊስ ኮምሽኑ የተጠና የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ አዘገጃጀት አሰራር አለመኖር፣ ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም አለመፈፀም፣ በጀት መኖሩ ሳይረጋገጥ የግዥ ሂደቶችንማከናወን፣ በግዥ መመሪያው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ግዥ …

  ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣      መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ። አሸባሪው  መንግስት ነው፣  ፍትሕ ማዳን። ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ …

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሁለቱ ከተሞች በተካሄዱት ስብሰባዎች ህዝቡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተሰቃየ እንደሚገኝ በድፍረት ለመንግስት ተወካዮች ሲገልጽ ተሰምቷል። በእንጅባራ አንድ ነጋዴ ሲናገሩ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ለራሳቸው የሚጠቅሙ እንጅ ህዝቡ የሚያያቸው አይደሉም በማለት በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። ነጋዴው እንዳሉት እቃዎች ሳይገዙ እንደተገዙ ተደርጎ ይወራረዳሉ፣ ጥራት ያላቸው እቃዎች አይገዙም፣ የመንግስት መጋዘኖችም …

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ የድርጅቱ  ሠራተኛ እንደተናገሩት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቦርድ ሰብሳቢነት ወደመድን ድርጅት ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ዘረኝነትና ግልጽ የሆነ ዘረፋ በድርጅቱ ውስጥ በመንሰራፋቱ  በርካታ ባለሙያዎች ድርጅቱን ለመልቀቅ እየተገደዱ ነው። ችግሩን ቦርዱ ተመልክቶ ሠራተኛውን እንዲያወያይ በተደጋጋሚ …

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ …

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች …

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ  መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር  በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው …

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ጁሊየስ ማሌማ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር የተሰኘ ፓርቲ መስርቷል። ወጣቱ ፖለቲከኛ በነጮች የተያዙት የአገሪቱ መሬት ለህዝቡ እንዲከፋፈል እና  ዋና ዋና የማእድን ፋብሪካዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንደሚታገል አስታውቋል። ማሌማ ፓርቲው ጸረ ካፒታሊዝም መሆኑም ገልጿል። “እኛ ጥቁሮች በዚህ አገር ስንኖር የምናሳያው …

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት ለመቃወም ፓርቲው በጎንደርና በደሴ የጀመረውን ቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን፣ እና በመኪና ላይ በመሆን በየሰፈሩ በመዘዋወር በድምጽ ማጉያ የትግል ጥሪ እያስተላለፈ ነው። በደሴ ከተማ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ …

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በ10/ 90 ወይም በ20 / 80 የቁጠባ ስርአት የኮንዶሚኒየም ቤት ለመስራት የሚፈልጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን የመንግስት ንብረት በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲያስቀምጡ ትእዛዝ ማስተላለፉ የግል ባንኮችን የሚያዳክም ነው የሚል ትችት ሲቀርብ ሰንብቷል። ገንዘባቸውን በግል ባንኮች ያስቀምጡ የነበሩ ደንበኞች ደንበኝነታቸውን  እየሰረዙ በንግድ ባንክ ማስቀመጥ ከጀመሩ …

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሜሪካን ኤምባሲ በተካሄደው የአምባሳደሮቹ ስብሰባ ላይ በቅርቡ የተመሰረተውንና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበትን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ የቻለውን ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል። በተለምዶ ‘‘የኢትዮጵያ ለጋሾች ቡድን’’ የሚል መጠሪያ ያለውና የአሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በአባልነት የሚገኙበት የለጋሾች ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የተቃዋሚ …

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ልዩ ፖሊሶች በቶዮታ ፒክ አፕ መኪኖች ላይ ሆነው በየመንደሩ በመዞር ህዝቡን ሰብስበው እያነጋገሩ ነው። ወታደሮቹ ” የማንነት ጥያቄዎችን ያቀረባችሁት እናንተ ናችሁ ወይስ ጸረሰላም ሀይሎች ናቸው?” በማለት ጥያቄ ሲጠይቁ መዋላቸው ታውቋል። ድርጊቱ በሚቀጥሉት ቀናት በተማሳሳይ መንገድ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ …

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል። ወደ  አርባምንጭ እስር …

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚሆኑ አስቀድሞ ሲነገርላቸው የነበሩት የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ የአስተዳደሩን ኃላፊነታቸውን ከአቶ ኩማ እጅ ተረክበዋል፡፡ በተለይ ሪፖርተር ጋዜጣ የምክትል ከንቲባነት ሥልጣን እንደሚይዙ የተነበየላቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደተገመተው ወደስልጣኑ ያልመጡ ሲሆን በምክትል ከንቲባነት የቀድሞ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ተሹመዋል፡፡ ዛሬ ማለዳ በአዲስ …

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲው ያወጣውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ፣ ወረቀቶችን በትነዋል የተባሉ ሰዎች በየቦታው እየታሰሩ በመሆኑ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆምና የታሰሩትም እንዲፈቱ ጠይቋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ ፣ በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ  አቶ አምደማሪያም …

ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራጣ በማደበር ተከስሰው 25 ዓመት የተፈረደባቸው አየለ ደበላ በቅጽል ስማቸው አይ ኤም ኤፍ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል በከፍተኛ ስነስርዓት ተፈጽሙዋል፡፡ አቶ አየለ የባንክን ሥራ ተክተው በመሥራት፣ አራጣ በማበደር፣ ግብር ባለመክፈልና በሌሎችም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በ22 ዓመታት እስርና በባንክ ያላቸው 12 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ …

ሐምሌ ፩( አንድ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን 300 የሚሆኑትን   ደግሞ ማሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። …

ሐምሌ ፩( አንድ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ተጎራባች በሆነችው ገላን ከተማ ውስጥ 50 ኢንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ምክንያት ሥራ አለመጀመራቸውን ሪፖርተር ዘገበ። የከተማው ከንቲባ አቶ ሙሉጌታ ከበደ የሀይል አቅርቦቱ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ግንባታ ጨርሰው ወደ ሥራ የገቡ ባለሀብቶች ለሞራል ውድቀት እየተዳረጉ ነው፤›› ያሉት ከንቲባው፣ …

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በላከው መግለጫ   ቀኑ እንዲራዘም የተደረገው የከተማው ከንቲባ በእለቱ የተማሪዎች የምረቃ በአል ፣ የመንገድ ምርቃና የፖሊስ ሀይሉ በስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ ሀይል የለም በሚል ፓርቲውን በጠየቀው መሰረት ነው። ፓርቲው በከንቲባው የቀረበውን ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ …

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከእሰራኤል አገር በደህህነት ሙያ ሰልጥነው በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት  እና በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ከተመደቡት መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የደህንነት አባሎች ታሰሩ። አባሎቹ የታሰሩት መረጃውን ለኢሳት አቀብላችሁዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። እስካሁን ምን ያክል የደህንነት ሰራተኞች ተይዘው እንደታሰሩ አልታወቀም። ኢሳት ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች ባገኘው መረጃ ስልጠናውን አጠናቀው ወደ አገራቸው …

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማእከላዊ ስታትስቲክስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ  የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 85 ነጥብ 9 ሚሊዮን መድረሱን የገለጹ ሲሆን ፣ ከዚህ አሀዝ ውስጥ 81 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው። የ2005ዓም የህዝብ ብዛት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ2 ሚሊዮን ሰዎች ጭማሪ አሳይቷል።። የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ቁጥር በ500 …

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ግርማ ለፓርላማው ሁለት ሞሽን ያቀረቡ ሲሆን አንደኛው ሞሽን መንግስት በ2006 በጀት ዓመት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ከመንግስት ባንኮች ሊበደር ያሰበውን 16 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በግማሽ ያህል (8 ቢሊየን ብር) በመቀነስ በተለይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የብድር ድጋፍ እንዲውል የሚጠይቅ ነው፡፡ ሁለተኛው የብሮድካስት ባለስልጣን ብሮድካስትን …

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ በሆነ ምርጫ ተመርጠው ለአንድ አመት ያክል በስልጣን ላይ ከቆዩ በሁዋላ በህዝብ ተቃውሞና በወታደራዊ ግፊት ከስልጣን እንዲወርዱ ተደርጓል። ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ እርሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላትን ከመጥቀም ባለፈ የፈየዱት ነገር የለም በሚል ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብባቸው …

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰላም አስከባሪነት ስም ሶማሊያ የሚገኘው የኬንያ ጦር የሶማሊ ጎሳዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ  አድርጓል የሚል ክስ በሶማሊያ መንግስት ቀርቦበታል። ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የተጻፈ ደብዳቤ በስህተት ለጋዜጠኞች በመላኩ ዜናው ይፋ መውጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የኬንያ ጦር በኪስማዮ አካባቢ የተለያዩ ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲጋጩ በማድረጉ 65 ሰዎች መሞታቸውን ደብዳቤው ይጠቅሳል። …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ  ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባን ለ5 አመታት ሲመራ የነበረው የኩማ አስተዳደር  ሐሙስ ሰኔ 27 ጀምሮ  ለአዲሱ ኢህአዴግ መራሽ ካቢኔ ሥልጣኑን እንደሚያስረክብ ተጠቆመ፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር የሚተቸው የኩማ አስተዳደር የምርጫ 97 ቀውስን ተከትሎ ከተመሰረተው የባለአደራ አስተዳደር ስልጣኑን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በምርጫ ስም የተረከበ ሲሆን ባለፉት አምስት …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል በጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በመንግስት ሀይሎች  እንቅፋት እየተፈጠረበት መሆኑን አስታውቋል። ፓርቲው የመጀመሪያውን  የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም፤ መንግስት …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡ የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት። ጄቶችን ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነገጋገርን ነው። የጄቶችን ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና  ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው  987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ  …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ዜናውን ይፋ ካደረገው በሁዋላ የሟቹ ጓደኛ የሆነ አንድ ግለሰብ መረጃውን ለሟቹ ባለቤት በሚስጢር ማስተላለፉንና ባለቤቱ እና ልጆቹ በጋራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በመሄድ አስከሬኑን መለየታቸው ታውቋል። ባለቤቱ አስከሬኑን ለመለየት የቻለችው በሰውነቱ ላይ ባለው ልዩ ምልክት ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ ቤተመንግስት በመሄድ የባለቤቷን አድራሻ መጠየቋ ታውቋል።   ከቤተ-መንግስት …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በከባድ የማታለል ወንጀል የተከሰሱት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኀበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ የቀረበባቸው ክስ እንዲቋረጥ ለፍትህ ሚኒስትር ደብዳቤ እስከመጻፍ የደረሱት ከሊቀመንበሩ ጋር የቅርብ ትስስር ስለነበራቸው እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓርብ  በፖሊስ ተይዘው ችሎት የቀረቡት የ82 ዓመቱ አዛውንት ሊቀትጉሃን …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን በዋና ሥራ አስፈጻሚነትና በቢሮ ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ሽፈራው ዓለሙ፣ ሥራቸውን ከሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራቸውን   መልቀቃቸው ተዘገበ። አንዳንድ ወገኖች ሥራ አስኪያጁ  ሥራቸውን የለቀቁት ከጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ በፈቃዳቸው ነው ሲሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ የሙስና ክስ ስለተመሰረተባቸው ሥራቸውን ይለቁ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሰኔ 30 ቀን በጎንደር ከተማ አደባባይ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ በከተማዋና በዙሪያ ወረዳዎች የጥሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ እንደሚገኝ የሰሜን ኢትዮጵያ አደራጅ እና የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አእምሮ አወቀ ለኢሳት ገልጸዋል። በምእራብ አርማጭሆ በአብራሀ ጅራ ከተማ አለልኝ አባይ፣  እንግዳው ዋኘው፣ አብርሀም ልጃለም እና አንጋው ተገኘ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት የመከላከያና የደህንነት ተቋማት የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አዲስ አድማስ ዘገበ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል ባንክ ባለሙያ፤ እሣቸው በሚሠሩበት ባንክ ደንበኛ የነበሩ …

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዳማ በአቡበክር መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” መንግስት ድምጻችንን ይስማ፣ በሀሰት ክስ አንገዛም፣ አሸባሪዎች አይደለንም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በአሳሳ ከተማም እንዲሁ በአል ከራም መስጂድ ተቃውሞ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል። በወልድያም እንዲሁ ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰምተዋል። በሁለቱም ቦታዎች የተካሄዱት ተቃውሞዎች በሰላም ተጠናቀዋል። መንግስት የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን …

ሰኔ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን ሰሞኑን የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር 2 ሚሊዮን 900 ሺ መሆኑን ቢገልጽም፣ በ10 – 90 እና በ20 – 80 እየተባለ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተመዘገበው ህዝብ ቁጥር ኤጀንሲው ያቀረበው አሀዝ  ትክክል አለመሆኑን የሚያሳይ ነው በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ ቀድሞ …