ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ታወቀ አበበ ካሴ፣ በማእከላዊ እስር ቤት የሁሉም ጣቶቹ ጥፍሮች ተነቅለው፣ በዘር ፍሬው እና በመላ አካላቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት መረጃ ለማውጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ በመጨረሻ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተወረወረ በሁዋላ፣ የደረሰበትን ችግር ሁሉ ዘርዝሮ …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት በሂራን ክልል ቡሎ ቡርዴ እና በለድ ወይኔ ከተማ ውስጥ ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሽማግሌዎቹ፣ ከአምስት በላይ ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎች በኢትዮጵያ ወታደሮች በግፍ መገደላቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ምክትል የመከላከያ አዛዥ መሀመድ አደን ግድያው መፈፀሙን አምነው የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ይቅርታ …

ኢሳት (ነሐሴ 4፣ 2007 ዓም) 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤቶች የጤንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አንድ አለምአቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ገለጠ። ኢትዮጵያዉያኑ ከባለፈው አመት ታህሳስ ወር ጀምሮ በማላዊ መዲና ሊሎንግዌ በእስር ላይ መሆናቸውን ዶክተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ (Doctors Without Borders) የተሰኘ የፈረንሳይ ድርጀት አስታውቋል። በማላዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካይ የሆኑት ኒኮሌት ጃክሰን …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፣ 2007) ሰሞኑን በአፋር ክልል የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት መሞታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በክልሉ በክረምት ወቅት የሚጠበቀው ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለፅ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ክልል መዲና በሚወስደው ዋናው አስፋል መንገድ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፥ 2007) የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ ፣ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርሳቸውንና ቤተመንግስቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ሃይሎች ጋር ተስማማተው መስራት አልቻሉም የሚል ትችት ከቀረበባቸው በሁዋላ፣ ግንኙነቱ ወደ ባሰ ደረጃ መውረዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም “በቤተሰቦቼና እና በእኔ ላይ በሚደረገው አላግባብ ክትትል ተሰላችቻለሁ” የሚል ንግግር በሁለተኛው ዙር የኢህአዴግ ሂስ እና ግለ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብዩብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተደራዳሪን ከአገሯ አስወጥታለች። እርመጃው የተወሰደው የደቡብ ሱዳን መንግስት አንድ የተቃዋሚ አባል ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ ማገቱን ተከትሎ ነው። ደቡብ ሱዳን የድርድሩ ቦታና አደራዳሪው ስዩም መስፍን እንዲቀየር የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሰጡት ምክንያትም፣ አዳራዳሪዎቹ ራሳቸው በአገራቸው …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ ዓለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟሉ ሆቴሎችን ደረጃ ለመመደብ በተካሄደው ጥናት 98 ያህል ሆቴሎች ከደረጃ በታች ሆነው መገኘታቸው ይፋ ሆኗል። በዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተጠንቶ ባለፈው ቅዳሜ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት ለውድድር ከቀረቡት 136 ያህል ሆቴሎች ደረጃ ማግኘት የቻሉት 38 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለ5 …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውስትራሊያ የሜልቦርን የአርበኞች ግንቦት7 ጽ/ቤት ” ሀገራችን ስላለችበት ሁኔታ እንምከርበት” በሚል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብሎአል። የድርጅቱ የሜልቦርን ከተማ ተጠሪ አቶ ነብዩ መላኩ ፣ “የድርጅት አጥር ሳይከልለን ትግሉን እንርዳ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ በስካይፕ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ” ትግሉ …

ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን የየተመሠረተበትን 35ዓመት ህዳር 11 ቀን 2008 ዓ.ም ለማክበር በማሰብ፣ ከሚዲያ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ብአዴን የህዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ ብቃት የተላበሰ አመራር የለውም ብለዋል። በግዮን ሆቴል ብአዴን በጠራው የሚዲያና ኮምኒኬሽን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አቶ አለምነው መኮንን፤ …

ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የታየው ዝናብ እጥረትና የተከሰተው ድርቅ ኢሊኖ እየተባለ የሚጠራው የአየር መዛባት የፈጠረው ነው ብሎአል። በተለያዩ አካባቢዎች የእንስሳት መኖና እና የምግብ እጥረት ተፈጥሯል ብሎአል። ሚኒስቴሩ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የችግሩን አሳሳቢነት ይፋ ማውጣታቸውን ተከትሎ የሰጠው የመጀመሪያ መግለጫ ነው። ገዢው ፓርቲ አገሪቱ በምግብ ራሱዋን መቻሉዋን በተደጋጋሚ ሲናገር …

ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ3.25 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን የንግድ ሚኒስቴርን በመጥቀስ ኒው ፎልቶን ዘግቧል። አሁንም አገሪቷ ወደ ውጭ አገራት ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ ቡና ቀዳሚነቱን እንደያዘ ሲሆን፣ ከቡና ሽያጭ ገቢ 780 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 8.5 …

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ካለፈው ወር ጀምሮ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ባለመዝነቡ በርካታ የቀንድ ከብቶች ሲያልቁ፣ ነዋሪዎችም ቀያቸውን በመልቀቅ ምግብ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው።ኢሳት ያነጋገራቸው ዜጎች እንደገለጹት፣ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንዲደርስላቸው ለመንግስት ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ከመንግስትም ሆነ ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች የቀረበላቸው ነገር የለም። በርካታ አርብቶአደሮች ውሃና ምግብ እናገኛለን በሚል …

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማእከላዊ እስታትስቲክስ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በተለይ በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምግብ ኢንዴክስ 13 ነጥብ 9 በመቶ ሲጨምር፣ በአዲስ አበባ 26 በመቶ፣ አፋር 16 በመቶ፣ አማራ 6.7 በመቶ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 13.9 በመቶ፣ ኦሮምያ 21.2 በመተ እንዲሁም በትግራይ 5.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከፍተኛ ጭማሪ …

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የእርሻ ወቅቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች በመሬታቸው ላይ ለማረስ ሙከራ ሲያደርጉ፣ የሱዳን ባለሃብቶችና ታጣቂዎች ጥቃት እየፈጸሙባቸው ነው። አርሶ አደሮቹ “በገዛ አገራችን እርሻ እንዳናርስ በሱዳኖች እየተከለከልን ነው” ያሉ ሲሆን፣ በሱዳኖች በኩል የሚፈጸመውን በደል ለመሸከም እየከበዳቸው መምጣቱን ይገልጻሉ።ሱዳኖች መሬቱ የእነሱ መሆኑንና የኢትዮጵያ መንግስትም ማረጋጋጫ እንደሰጣቸው ይናገራሉ። የኢትዮጵያ …

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ም/ሰብሳቢ የነበረውና ከሶስት ሳምንት በፊት በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ፣ ‹‹ሰዎችን ለግንቦት ሰባት በመመልመል ወደ ኤርትራ ትልክ ነበር›› የተባለው አቶ ፍቃዱ በቀለ ከታሰረበት ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በዋስ ተፈቷል፡፡ በተመሳሳይ ክስ ተጠርጥሮ ከ25 ቀናቶች በላይ ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው …

ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮሚሽኑ ባለፉት 5 አመታት ፣ 5 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የተዘረፈ መሬት ማስመለሱን ገልጿል። 27 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንና 22 መኪኖችን ማስመለሱንም ገልጿል። ኮሚሽኑ ሙስናን ለመዋጋት ጥረት ቢደረገም ሙስና አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል። 90 ሺ የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን ማስመዝገባቸውን ኮሚሽኑ ቢገልጽም፣ መቼ ይፋ እንደሚያደርግ ወይም እስካሁን …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 20 ቀናት ሲጓተት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በአርባምንጭ የተካሄደ ሲሆን፣ ህዝቡ መንግስት አይካፈፍለን በማለት ቁጣውን ሲገልጽ ተሰምቷል። ጎታና ቱፋ ታድላ የተባለ ጸሃፊ የጋሞን ህዝብ የሚያንቋሽሽ መጽሃፍ ማዘጋጀቱን ተከትሎ፣ የአካባቢው ህዝብ መንግስት ጋሞን ከጎፋ ህዝብ ጋር ለማጋጨት ሆን ብሎ የተሸረበው ሴራ ነው በማለት ሲቃወመው ቆይቷል። “የአሜሪካው …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ብአዴን በባህርዳር ባካሄደው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ክልሉን የገጠሙትን ፈተናዎች አቅርቧል። ጉባኤው በዝግ የተካሄደ ሲሆን፣ አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች ድርጅቱ የገጠመውን ፈተና በዝርዝር አቅርበዋል። ዝምታን የመረጠው ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ እንዳልሆነ በርካታ አመላካች ነገሮች መኖራቸው የተብራራ ሲሆን፣ “ህዝብ አኩርፏል፣ ምን እናድርግለት ?” የሚል ጥያቄም ተነስቷል። በእየአመቱ በመቶ ሺዎች …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን አባላትን በቀላሉ ለመያዝ እንዲመች በሚል ስሌት የዲያስፖራ ቀን በኣል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በበአሉ ላይ ለሚገኙ የዲያስፖራ አባላት የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል። ከሰሜን አሜሪካ የመጡ የኦሮሞ ተወላጆች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት “በበዓሉ ላይ ከተገኙ በመረጡት አካባቢ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ወዲያውኑ ከሊዝ …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተከሰሱት 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ ፣3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ ፣4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን እና 5ኛ ተከሳሽ አቶ አንሙት የኔዋስ የመከላከያ ምስክር ሆነው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለዛሬ ሀምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ አውግዟል። “ስርዓቱ ለመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው እውቅና ሰጥቶ ሲደራደር” ከቆየ በሁዋላ ፣ አሸባሪ ብሎ መክሰሱ፣ ‹‹ሽብር›› የሚባለው ክስ ስርዓቱ ያልፈለገውን የሚያስርበት ፍርድ ቤቱና ህጉም የአገዛዙ ዋነኛ መሳሪያ ሆነው መቀጠላቸውን ያመላክታል ብሎአል። በኮሚቴው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሙስሊሙ …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ ጀዛን ከተማ ውስጥ በአንድ ሳውድ አረቢያዊ ዜጋ ላይ ዝርፊያና ግድያ ፈፅመዋል ተብለው የተከሰሱት ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ፣ አረጋዊ አልዶ ኃ/ማሪያም እና ሃዲሽ ዘላለም ናቸው። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን ተቀልተው የሞት ፍርድ ተፈፅሞባቸዋል ሲል የሳዑዲ አረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴሩን ጠቅሶ ታይምስ ላይቭ ዘግቧል። በሌላ ወንጀል …

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለም አቀፍ ደረጃ መጥፋቱ የሚነገርለት የሥጋ ደዌ ሕመም በአዲስ መልክ በኢትዮጽያ ማገርሸቱ አስደንጋጭ መሆኑን የኢትዮጽያ የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ሕክምና ማህበር በሂልተን ሆቴል ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይ ይፋ አደረገ፡፡ በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ መጥፋቱ የተረጋገጠው ከ15 ዓመታት በፊት መሆኑ የተነገረ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት ግን በኢትዮጵያ በዓመት …

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 28 2007 አ ም ) በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃዎች ላይ ሲያገለግሉ የነበሩ 6 ዲፕሎማቶች ስርአቱን በመክዳት እንደወጡ መቅረታቸው ታወቀ ። የአገልግሎት ጊዜያቸውን በማጠናቀቅና በተለያዩ ምክንያቶች ለኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ ሀምሌ 1 2007 ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸው ለጥሪው ምላሽ በመንፈግ ስርአቱን የከዱ ዲፕሎማቶች ከአሜሪካ አፍሪካና ህንድ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ምንጮች …

ሐምሌ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አቡበክር አህመድን ጨምሮ በ18 የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ “ድራማ ነው” በማለት ያጣጣለው ድምጻችን ይሰማ ፣የተሰጠው ፖለቲካዊ ፍርድ “ትግሉን የበለጠ እንድንቀጥልበት ያደርገናል” ሲል ገልጿል። የፍርዱን ኢ-ፍትሃዊነት የመንግስት ባለስልጣናትና ድራማውን የተወኑት አቃቢ ህግጋት እና ዳኞች ሳይቀር ያውቁታል የሚለው ድምጻችን ይሰማ፣ ውሳኔው …

ሐምሌ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ከዝናብ እጥረት ጋር ተያይዞ ድርቅ ተከስቷል።በሰሜን ሸዋ፣በዋግ ህምራና በወሎ በርካታ ቦታዎች ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቅ ገብቷል፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጉዳዩን በዝግ ስብሰባዎች ቢወያዩበትም ፣ መረጃው ወደ አደባባይ እንዳይወጣ ጥረት እያደረጉ ነው። በዋግ ህምራ አካባቢ ለሶስተኛ ጊዜ እርሻ እየተገለበጠ በመታረስ ላይ መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ …

ሐምሌ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዩ በቅርቡ በተካሄደው የፌደራል እና ክልል የፍትህ ምክክር መድረክ ላይ ፣ አቃቢ ህግ ክስ ሲመሰርት ከክሱ መግለጫ ጋር ስለ ተያዙ ኤግዚቢቶች ስለማይጠቅስ ፣ ንብረቶቹ በፖሊስ ጣቢያዎች ለረዢም ጊዜ ያለጥንቃቄ በመቆየታቸው በሚደርስባቸው የአያያዝ ጉድለት እንደሚበላሹ እና በፖሊስ አባላትም ያለአግባብ እንደሚዘረፉ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ይህን …

ሐምሌ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ ስር የሚገኙ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ አባላት ከ22 እስከ 7 አመታት በሚደርስ እስር እንዲቀጡ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ፍርዱን ፍርድ ነው ብለን ለመቀበል አስቸጋሪ ነው ብለውታል። ፍርድ ቤቱ አቶ አቡበክር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ …

ሐምሌ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው በሚገኙ በኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች የተመራውና በተያዘው በጀት ዓመት ከተማዋን ይመራሉ ተብለው የሚሾሙ የድርጅት ካድሬዎችን የሚለይበት የከተማና የክ/ከተማ ከፍተኛ የግምገማ መድረክ አጋማሹን ካድሬ አስደስቶ አጋማሹን ደግሞ አሳዝኖና አበሳጭቶ ተጠናቋል፡፡ በሃምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የተጀመረው ይህ ግምገማ በልዩ ትኩረት አጀንዳ ተቀርፆለት በተቀመጠለት …

ሐምሌ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ ለተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ መታሰቢያ ሀምሌ 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ደም ተለግሷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎችም ሳሙኤልን ለማስታወስ የተገኙ ግለሰቦች ደም ሰጥተዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዛሬው ቀን ደም መስጠት …

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 24, 2007) በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ 40 በላይ የአየር ሀይል ባለሙያዎችና ሰራተኞች በስልጣን ላይ ያለውን ሰርአት በመክዳት ወደተለያዩ ቦታዎች መሰወራቸው ታወቀ ። የኢሳት የአየር ሀይል ምንጮች እንደገለጹት የደብረዘይት አየር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ በወታደራዊ የስራ መደብ የሚያገለግሉትን ጨምሮ 14 ቴክኒሺያኖችና ለጊዜው በቁጥር ያልተገለጹ አብራሪዎች ባለፈው አንድ ወር በስራ ገበታቸው አልተገኙም። በዋና ማዘዢያ …

ሐምሌ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከተማው ባለስልጣናት ትናንት በቀበሌ 01 በድንገት በጀመሩት የቤት ማፍረስ እንቅስቃሴ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮምያ ፖሊስ በአካባቢው ሰፍሮ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከመቆጣጠር አልፎ ፣ ህጻናትንና ወጣቶችን እየደበደቡ አፍሰው ማሰራቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብዙዎች በእለቱ በጣለው ዝናብ የቤት እቃዎቻቸው ተበላሽቶባቸዋል። ” ቤታችን ለምን …

ሐምሌ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወጣት ባንተወሰን አበበ ያልምንም ተጨባጭ መረጃ ሃምሌ 6፣ 2007 ዓም ከታሰረ በሁዋላ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እንደተፈጸመበት ለኢሳት ተናግሯል። ባንተወሰን ከተያዘ ከሁለት ቀናት በሁዋላ ፍርድ ቤት ቢቀርብም፣ ዳኛው በዋስ እንዲለቀቅ ማዘዛቸውን ይሁን እንጅ ፣ ፖሊስ አልፈታም በማለት ፣ ሃምሌ 17 ከምሽቱ 12፣ 40 ላይ ከእስር ቤት አውጥተው …

ሐምሌ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዚህ አመት በአገሪቱ የታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየከፋ በመሄዱ፣ በጥቁር ገበያ እና በህገወጥ መንገድ የሚደረገው የዶላር ዝውውር መድራቱን ዘጋቢአችን ገልጿል። ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ ስራቸውን የሚሰሩ ነጋዴዎች ዶላር እንደልባቸው ለማግኘት ባለመቻላቸው፣ ዶላርን ከጥቁር ገበያና ከባንኮች በልዩ ሁኔታና በውድ ዋጋ ለመግዛት እየተገደዱ ነው። የተወሰነ መጠን ዶላር …

ሐምሌ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው ከስምንት ሽህ በላይ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል ውስጥ ከሚገኙት ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት እየተጠባበቁ ሲሆን አብዛሃኞቹ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ከወላጆቻቸው የተለያዩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የቀድሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ”እነዚህ አይሁዳዊያን ናቸው በየዕለቱም ይፀልያሉ” ሲሉ ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴሩ በበኩላቸው ”ውሳኔ በአፍጣኝ ያልተሰጣቸው በዘረኝነት ተፅዕኖ …

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀጣይ አምስት አመታት የስልጣን ድልድል ቅድመ አቋም ግምገማ ለመጀመሪያ ጊዜ ለውይይት በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው፣ 80 በመቶ የኢህአዴግ ሚኒስትሮች ችግር የምፍታት አቅም የላቸውም። ለግምገማ በቀረቡት የተለያዩ መስፈርቶች ብቃት አላቸው የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን ሲሆኑ፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ አብዛኞቹ ሚኒስትሮች ችግር ፈችዎች አይደሉም ተብለዋል። ቅድመ አቋም ግምገማውን ያካሂዱት ከአራቱም …

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በነዳጅ እጥረት ምክንያት የየዕለቱን ስራ ለመስራት የባጃጅ ኮንትራት በመያዝ ለአላስፈላጊ ወጭ መዳረጋቸውን የሚገልጹት የከተማ ነዋሪዎች ጠዋትእና ማታ በሚኖረው ረዣዢም ሰልፍ ምክንያት ስራ ቦታቸው በሰዓት ለመውጣትና ለመግባት መቸገራቸውን ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በነዳጁ መጥፋት ለረዢም ሰዓታት ስራ መፍታታቸው በኑሯቸው ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት በከተማዋ የሚገኙ …

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከምድረ ገጽ ጠፍቶ የነበረው ጊኒ ዎርም በሽታ እንዳዲስ ማንሰራራት መጀመሩ በአዲስ አበባው ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ላይ ተገልጿል፡፡ ዶ/ር ዳዲ ጅማ ፣ በኢትዮጵያ በሽታው በደቡብ ክልል እና በጋምቤላ በፍጥነት በሰዎች ላይ መታየት መጀመሩን የጤና ባለሙያዎችን መረጃ ዋቢ በማድረግ ወቅታዊውን ሪፖርት ከጥናታቸው ጋር …

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎች የሌላቸው እስኪመስል ድረስ እግረኞች ብቻ ሳይሆኑ አሽከርካሪዎችም ጭምር መንገድ ለማቋረጥ ሲሳናቸው ተስተውሏል። በርካታ የአዲስ አበባ መንገዶች ከዓመት እስከ ዓመት ተመሳሳይ ችግሮች ቢስተዋልባቸውም መንገድ ትራንስፓርት የፍሳሽ ማስወገጃዎችን በመስራትና የተበላሹትን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አልቻለም። የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ቢያሰሙም ችግራቸውን ሰምቶ …

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕ/ት ባራክ ኦባማ ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በውጭ አገር በተለይም በአሜሪካ የተቀመጠ ተቃዋሚ ድርጅት በሽብረተኝነት እንዲፈረጅ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አቶ ሃይለማርያም ” ሽብርተኝነትን በመዋጋት እንዲሁም ሰራዊታችንን በጸጥታ አስከባሪነት ስም ለመላክ የማንችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰን ነው” የሚል ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፣ ለዚህም የሰጡት ምክንያት “በኤርትራ …

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ12ኛው የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ መድረክ ላይ እንደተነገረው በበጀት አመቱ የተቋረጡ መዝገቦች በሙሉ ኦዲት ተደርገው ሲጣሩ፣ በአጠቃላይ የፍርድ ቤት መዝገቦች የተዘጉት በክራይ ሰብሳቢነት፣በዝምድናና በተያያዙ የገንዘብ ጉዳዮች መሆኑን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የደቡብ ክልል የፍትህ ቢሮ ኃላፊ በክልላቸው በስፋት በሚታየው ህገወጥ የሰወች ዝውውር ላይ በሰጡት አስተያየት …

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚኖሩ 43 አባወራዎች ከ200 በላይ ቤተሰቦች ቀደም ብለው ይኖሩበት የነበረውን ቀያቸውን በልማት ምክንያት ለቀው በተጠቀሰው ወረዳ እየኖሩ ቢሆንም በመንገድ ግንባታ ምክንያት ሕገወጥ ገንቢዎችን ለማዳን ተብሎ እነሱ በድጋሚ ሊፈናቀሉ መሆኑን በመጥቀስ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲታደጓቸው የተማፅኖ ደብዳቤ …

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውስትራሊያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኢትዮጵያዊው ወጣት ናስር ባሬ በሁለት የፖሊስ ባልደረቦች አካላዊ ጥቃትና የዘር መድሎ ተፈፅሞብኛል ብሎ ያቀረበው ክስ በወንጀል መርማሪዎች እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል አቶ ናስር ”ሁለት ፖሊሶች ከፍሳሽ ትቦ ላይ አጋድመው ረገጡኝ ጥርሶቼ ተሰባብረዋል፣እጄን ጠምዝዘው ዐይኔ ላይ የሚያቃጥል ካፕሱም እስፕሬይ ረጩብኝ፣የጎን አጥንቶቼን ረገጠውኛል ይህ ሳያንሳቸው …

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በስልጣን ላይ ያለውን ገዢ ፓርቲ ” በዲሞክራሲያዊ ምርጫ” የተመረጠ ነው ብለው መናገራቸውን ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ተቃውሟቸውን ባሰሙ ማግስት፣ ይህንን ንግግራቸውን የሚቃረን ንግግር በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተገኝተው አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ ስለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በመጀመሪያው ቀን የተናገሩትን ላለመድገም ጥንቃቄ ያደረጉ ሲሆን፣ ምርጫውን በተመለከተ …

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድርጊቱ የተፈጸመው ንብረትነቱ የቱርክ የሆነና በጥጥ ማምረት ስራ ላይ የተሰማራውን የቶረን የእርሻ ኩባንያ ገንዘብ ጭኖ በመጓዝ ላይ ባለ መኪና ላይ ነው። የኩባንያው ሃላፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሜሪካ ዶላርና ብር ይዘው በ7 የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ታጅበው ወደ ወንዶ ጎጊ ወረዳ በሚጓዝበት ወቅት፣ አንደኛው …

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው ከሁለት ሳምንት በፊት በአርባምንጭ ከተማ ሊደረግ የታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ በገዢው ሃይል የጸጥታ አባላት እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ፣ ከ120 በላይ ሰዎች ተይዘው በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረዋል። አንድ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነ ሰው የጋሞን ብሄረሰብ ታሪክ አንቋሾ መጽሄት አሳትሟል በሚል የተጀመረው ተቃውሞ እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ፣ …

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሜሪካዊው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ይህን የተናገሩት ” በአሜሪካና በኤርትራ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመወጋት የምታደርገውን ጥረት እያደናቀፉ በመሆኑ የእርስዎ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ምን ያክል ዝግጁ ነው ተብሎ ከኢቢሲ ጋዜጠኛ ” ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ጋዜጠኛው የድርጅቱን ስም በግልጽ ከመግለጽ ቢቆጠብም፣ ፕ/ት ኦባማ የሰጡት መልስ …

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሀምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የተወሰደው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝና በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ እንዳልቻሉና ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል በጎንደር መምህራን ኮሌጅ የአይ ሲቲ መምህርና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆነው መምህር አለላቸው አታለለ …