ዞን ዘጠኞች እንዲሁም ጋዜጠኛ አስማማዉ፣ ተስፍዳ አለም እና ኤዴም ፍርቅ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው በዝግ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል። ፖሊስ እንደገና ለ10 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠ ሲሆን ፣እስረኞቹ ጠበቃቸውን ለማየት እድል ያገኙት እዚያው ፍርድ ቤት ነበር። ዝርዝር ዘገባዉ ዳዊት ሰለሞን እና ብስራት ወ/ሚካኤል እንደሚከተለው አቅርበዉታል፡ ዳዊት ሰለሞን አስማማው፣ተስፋለም፣ኤዶም፣ዘላለም፣አጥናፍና ናትናኤል አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ሲደርሱ […]

ለህጋዊ ሰልፍ ሲቀሰቅሱ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙት የአንድነት አባላት በዋስ ተለቀቁ ባሳለፍነው ሐሙስ ካዛንቺስ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት ጋዜጠኛ ነብዩ ሐይሉ፣አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ዘላለም ደበበና ሹፌራቸው አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው የአስራ አንድ ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ እንዲመለሱ መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡ የእጅ አሻራ እንዲሰጡ ከተደረጉ በኋላ አራቱም ሰዎች የመታወቂያ ዋስ […]

‹‹ግለሰቦቹ ጉዳዩን ፖለቲካዊ በማድረግ ከተጠያቂነት ለማምለጥ እየተሯሯጡ ነው›› /የደብሩ አስተዳደር/ ላልተጠናቀቀው ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ወጪ የተደረገው 8 ሚሊዮን ብር የተጋነነ ነው ተብሏል (ኢትዮ – ምኅዳር፤ ቅጽ፪ ቁጥር ፷፮፤ ረቡዕ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) በሚሊዮን የሚቆጠር የምእመናን ገንዘብ ለብክነትና ዘረፋ እንደተዳረገበት የተጠቆመው የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ደብር ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታና ሒሳብ እንዲመረመር ከቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈውን …

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ አንድ አዲስ የፍጥነት መንገድ ትናንት ተመርቆ ተከፈተ። ከሁለት ሳምንታት በኋላ በይፋ ለተሽከርካሪዎች የሚከፈተውን መንገድ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋ ባንድነት መርቀው የከፈቱት ኢትዮጵያን የጎበኙት የቻይና ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኬኪያንግ ናቸው።

በዕድሜ ብዛት በኢትዮጵያ በማርጀት እና በመፈራረስ ላይ ያሉ ባህላዊ ቅርሶችን ለመጠበቅ ስዊድን ውስጥ አንድ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች እንክብካቤ ማህበር ተቋቁሞ ሥራ ጀምሮዋል። በቅርስ አጠባበቅ ሥራ ላይ ያተኮረው ይኸው ማህበር የተመሠረተው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር።

ይህን ሰልፍ ለማስተባበር ከአዲስ አበባ የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም እንዲሁም የምዕራብ ቀጠና አደራጅ አቶ ብርሃኑ ፈከና ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ የወረዳው ምክር ቤት ለሰልፉ እውቅና ለመስጠት ያንገራገረ ቢሆንም በነበረችው አጥር ጊዜ ቅስቀሳ ተደርጎ እጅግ የደመቀ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንደቻሉ ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ ጊዶሌ ከተማ በ19ኛው መቶ ክ/ዘመን የተቆረቆረች ሲሆን በ1938 ዓ.ም የመጀመሪያውን […]

መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ሰብስበው እሁድ ዕለት በተደረገው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኙ መምህራንን ፈትሸው እንዲያወጡና እንዲያጋልጡ የሚል መመሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ተማሪዎችን ሰብስበው የኔት ወርክ ችግር እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንደሚፈታ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይኖር ሌሎቹ ችግሮች ግን እንደሚቀጥሉ ለወላጆቻቸው […]

ባለፉት ፳፫ የስልጣን ዘመኑ እንዲሁም ከዚያም በፊት በ፲፯ የጫካ ዘመኑ ኢትዮጵያን ከካርታ፣ ህዝቧን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ወያኔ አርነት ትግራይ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያላፈሰሰው ደም የለም። በባዕዳን ሁለንተናዊ ድጋፍ በመታገዝና በአንቀልባ በመታዘል በተለያዩ የአገሪቱ አቅጣጫዎች በመገስገስ ላይ እያለ በተለያዩ ግዛት ያሉ ኢትዮጵያውያኖች የዚህን እኩይ ግስጋሴ ለመግታት አይከፍሉ መስዋእትነት ከፍለዋል፤ የጣሊያንን ወረራ ለመመከት በግንደ በረት በረሃ ለሃገራቸው ኢትዮጵያ […]

የአንድነት ፓርቲ ያቀረበውን እጅግ በጣም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አይኖቼ እምባ እያቀረሩ፣ ልቤን ደስታ ፈንቅሏት ነው እኔም እንደ ሰልፈኞቹ መፈክር እያሰማሁ ከናት ሀገሬ ውጪ ከምኖርበት ከተማ በቴሌቪዥን ከመኖሪያ ቤቴ ተቀምጬ ነበር የተመለከትኩት። እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! በማለት ይህቺን መጣጥፍ ለመክተብ ተነሳሳሁ። ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደጻፍኩት ግትር ኢትዮጵያዊ ነኝ። ያ እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ የተገኙት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በሚቀጥሉት ቀናት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የቀድሞው ምክትላቸዉ ሪይክ ማቻር የሰላም ውይይት ለማካሄድ እና ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ይገናኙ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ከኢራቅ ጠቅልሎ ከወጣ በኋላ የመጀመሪያውን ምክር ቤታዊ ምርጫ ኢራቃውያን ረቡዕ፤ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2006 ዓም አከናውነዋል። በከፍተኛ ጥበቃ ነው የኢራቅ ምርጫ የተከናወነው። በኢራቁ ምርጫ ለመምረጥ ከተመዘገበው ነዋሪ ሲሦው ድምፁን መስጠቱም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ተጠይቋል ።

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ፖሊስ ይዟቸው ላዛሪስ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ ደረሰባቸው፡፡
በተለይ ‹‹አንተን የሚጠብቅ ፖሊስ የለንም ተብሎ›› ፈተና እንዳይፈተን የተደረገው ዮናስ ከድር ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዮናስ ከድር መንቀሳቀስ እንደማይችል አብረውት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ገልጸውልናል፡፡ ሳምሶን የተባለና ኮድ ሁለት 16321 መኪና የሚይዝ ደህንነት ለምን አትፈታም እንዳለውና ዮናስም ‹‹የታሰርኩበት ምክንያት ህጋዊ ስላልሆነ ህጉ እስክልተከበረ ድረስ አልፈታም›› የሚል መልስ እንደሰጠው ታውቋል፡፡ ደህንነቱም ‹‹እኔ ነኝ እንዳትፈተን ያደረኩህ፡፡ ለእናትህም ደውዬ የነገርኳት እኔ ነኝ፡፡ ስትፈታም ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰህ አትገባም፡፡ ወደ ቤትህ ነው የምትመለሰው›› እንዳለው ታውቋል፡፡
በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም ድብደባ እንደረሰባቸው የታወቀ ሲሆን ደህንነቶችና የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ተጨማሪ ድብደባ እንደሚደርስባቸው እያስፈራሩዋቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህል በእስር ላይ የምትገኘው እየሩስ ተስፋው እዮኤል የተባለውን የእስር ቤቱ ኃላፊ ‹‹አንተ ነህ የምታስደበድበን›› ባለችው ወቅት ‹‹አሁንም ትደበደባላችሁ፡፡ ወጥታችሁ ተደብድባችሁ መመለስ ብቻ ነው ምንም አታመጡም›› እንዳላት ገልጻለች፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማጣራት ወደ እስር ቤት በሄደበት ወቅትም እስር ቤቱ ውስጥ የሚሰራ አንድ ፖሊስ ‹‹እኔ ነኝ ያስደበደብኩት፡፡ ምንም አታመጡም፡፡ ከፈለጋችሁ በደንብ እዩኝና ክሰሱኝ፡፡ አሁን ከእኔ ጋር መነጋገር አትችሉም ከግቢ ውጡ›› ብሎ እየገፈተረ እንዳስወጣቸው ገልጾአል፡፡ በላዛሪስት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት ሁለት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውና በዚህም ምክንያት መዳከማቸው የታወቀ ሲሆን ፖሊስና ደህንነት በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነው እንኳ ከፍተኛ ድብደባ እያደረሱባቸው መሆኑ እንዳሳዘነው አቶ ብርሃኑ ጨምሮ ገልጸአል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የርሃብ አድማ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ 32 የሶማሊያ ስደተኞች ያለ ምንም ምግብ፣ ልብስና ውሃ መታሰራቸውን ገልጸው ችግራቸው እልባት እንዲያገኝ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ መታሰራቸው ህገ ወጥ ሆኖ እያለ 5500 ብር ከፍላቭሁ ውጡ መባላቸውን በመቃወም ‹‹አንፈታም!›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ብርሃኑ ‹‹ደህንነትና ፖሊስ ታሳሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ድብደባ የሚያደርሱበት ምክንያትም ታሳሪዎቹ ህግን ለማስከበር በሚያደርጉት ጥረት ነው›› ብለዋል፡፡

እኛ የኦጋዴን፣ የኣማራ፣የኦሮሞ፣የትግራይና የደቡብ ብሄር ተወላጆች ኣዲስ ኣበባን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ የሚገኙ ድሃ የኦሮሞና ሌሎች ገበሬዎችን ግፍ በጥብቅ የምናወግዝ ሲሆን በቅርቡ በሃረማያ፣ በኣምቦ እና በሌሎች ኣካባቢዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን ግድያና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሊገልጹ በወጡ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የድብደባና የማጉላላት ዘመቻ በጥብቅ እናወግዘዋለን። ገዳዮቹም የጊዜ ጉዳይ […]


(መሪጌታ ዘድንግል ለደጀ-ሰላም እንደጻፉት/ PDF)
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “አሜሃ ይከውን ኃዘን ዘኢይበቊዕ ኃዘን = ያን ጊዜ ኃዘን ይሆናል ግን የማይጠቅም ኃዘን ነው” እንዳለ የማይጠቅም ኃዘን የሚያዝኑ ብዙዎች ናቸው። ከነዚያው ዘንድ ቅሉ ይሁዳ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። ይሁዳ በፈጸመው እኩይ ግብር ኃዘን በተሰማው ጊዜ የሄደው ወደ ካህናቱ አለቆችና ወደ ሕዝቡ ሽማግሎች ነበር። በደሉንም መናዘዝ የጀመረው በደልን ፀነሰው፣ ወልደውና አሳድገው ለመዓርገ ሞተ ነፍስ ላደረሱና ላበቁ ፈሪሳውያን ነበር። በማቴዎስ 23፥15  “አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፣ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት ወዮላችሁ” ተብሎ እንደተጻፈ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ይሁዳን በክፉ ግብራቸው አጥምቀው የነሱ ፈጻሜ ፈቃድ/ፈቃድ ፈጻሚ ለማድረግ ብዙ ደክመዋል። ጨርሶ የድኅነት በር እንዳይከፈትለት አድርገው ለገሃነም ዳርገውታል። “ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም” እንዳለ ወንጌለ ዮሐንስ። (ዮሐ 16፥12)

ወደ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ሄዶ ነው ይሁዳ ብሶቱን ለመግለጽ የሞከረው። የብዙ ጊዜ ሕልማችን ግቡን የመታው በዚህ ሰው ተሳትፎና ትብብር ነው ብለው ጊዜ ሰጥተው ሊያነጋግሩትና ሊያጽናኑት ፈቃደኞች አልነበሩም። እነሱ  ምን ገዷቸው። ቢገዳቸውማ ንጹሕ እንዲፈስ ደሙ በእኛ በልጆቻችን ላይ ይሁን ብለው ይምሉ ነበርን? እነሱስ ይሁን ወደው በፈጸሙት ነው። ልጆቻቸው ምን አደረጉ? ረ ወዲያ እነሱ ምን ገዷቸው።
ዛሬም ይህንኑ ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደገሙ ያሉ ሰዎች አሉ። እነዚህ በአየርም በመሬትም፣ በየብስም በባሕርም፣ በአራቱ ማዕዘን ሁሉ ይዞራሉ። ዓላማቸውም የሚቻል ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረቷ አፈራርሶ መጣልና ትውልዱ የሚረከበው ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር ማድረግ ነው። ይህን በማድረጋቸው ምን ይጠቀማሉ ቢሉ? ምን ገዷቸው የሚል ነው መልሱ። ቤተ ክርስቲያኒቱ ልብስ ጉርስ ሰጥታ፣ ጉባኤ ዘርግታ፣ መምህር መድባ፣ የአገልግሎት መድረክ ሰጥታ ለቁም ነገር ካበቃቻቸው በኋላ “ዘይሴሰይ እክልየ አንሥአ ሰኰናሁ ላዕሌየ፤ እህሌን የተመገበ ሰኰናውን በኔ ላይ አነሣ” እንዳለ ነቢዩ በሌሊት ከቤተ ጉባኤ እየወጡ ቤተ ክርስቲያን ሞታ የምትቀበርበትን ጉድጓድ ሲቆፍሩ ያድራሉ። በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳለ የበግ ለምድ ለብሰው ከእውነተኞቹ አገልጋዮች ጋር ተሰልፈው ይቆማሉ። እንኳን እግዚአብሔር እኛም አውቀናቸዋል። እስከ መከር አብረው ይደጉ የሚል አምላካዊ ቃል ስላለ የመከሩን ዘመን እየጠበቅን ነው እንጂ። ወይ ግሩም! መከሩማ ዕለተ ምጽአት አይደለምን የሚል ቢኖር አዎ እርግጥ ነው ግን እግዚአብሔር ሰይፈ በቀሉን በመናፍቃን ላይ የሚያነሣበት ጊዜ ሁሉ መከር ነው ብለን እንመልሳለን።  ጉባኤ ኒቂያ፣ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ፣ ጉባኤ ኤፌሶን የመከር ወቅቶች ነበሩና። ከስንዴው ጋር አብረው አድገው የነበሩ እንክርዳዶች በጥብዓተ ሃይማኖትና በነገረ ሃይማኖት ማጭድ እየታጨዱ በቃለ ግዘት ታስረው ወደማይጠፋው እሳት ተጥለዋልና።
ፈሪሳውያን ከቤተ መቅደስ እንዲወጣ ያደረጉት በይሁዳ እጅ ላይ የነበረውን ሠላሳ ብር ነው። (የሰጡት እነሱ መሆናቸው ሳይዘነጋ) የዛሬዎቹ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ግን እነሱ ከሚሞነጫጭሯቸው ምኑናት/የተናቁና የተዋረዱ መጣጥፎቻቸው በቀር ምንም አይነት ነገር በቤተ ክርስቲያን እንዲኖር አይፈልጉም።
እስቲ ከሞነጫጨሯቸው አንዱን እናንሣ።  «ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም» የሚለውን ጥያቄ በማንሣት በበዓለ ሃምሳ ቅድመ ጸሎተ ኪዳን የሚደርሰውን «ለአዳም ፋሲካሁ፤ የአዳም ፋሲካ» የሚለውን የምስጋና ክፍል ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት ነው በማለት ካህናቱ ምሥጢሩን ሳይረዱ፣ ምን ያህል ስህተት እንደሆነ ሳይገነዘቡ በልማድ በዜማ ስለሚሉት የዚህ ድርሰት ችግር ሳይታያቸው ያለምንም ቅሬታና መሳቀቅ አፋቸውን ሞልተው ያዜሙታል እያሉ የድንቁርናቸውን ጣሪያ ያሳዩናል። ምን ገዷቸው።  «ልጅ ለናቷ…» አይደል የተባለው።
ካህናቱ የዚህ ኃይለ ቃል ምሥጢር ካልገባቸው እነሱን ከሰማይ መልአክ ወርዶ አስተምሯቸው ነው? ወይስ እነርሱ ራሳቸው ከሰማይ ወርደው ይሆን? ይህ ሥርዓት የሚከናወነው በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ቢሆን ጥያቄያቸው ለውይይት በቀረበ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበትና ካህናቶቿና ምእመናኖቿ ባሉበት የሚከናወን ልዩ ሥርዓተ ጸሎት ነው።  አስተውሉ!  «ካህናቱ» የሚለው ቃል ከላይ እስከታች ያሉ አገልጋዮችን የሚወክል ቃል ነው። እንዳው በኔ ሞት አላዋቂ ማነው? መልሱን ለአንባቢ።
ፋሲካ ማለት ምን ማለት ነው?
1· እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ብሎት ነበር። «ትበልዕዎ በጒጒዓ እስመ ፋሲካሁ ለእግዚአብሔር = የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በፍጥነት ትመገቡታላችሁ» ዘጸ 12፥11፤  የእግዚአብሔር ፋሲካ የተባለው እስራኤል በቤታቸው የሠዉት በግዓ ፋሲካ ነው።
ዕዝራም «በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አደረጉ ካህናቱና ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር። ሁሉም ንጹሐን ነበሩ ለምርኮኞቹም ሁሉ፣ ለወንድሞቻቸውም ለካህናቱ፣ ለራሳቸውም ፋሲካውን አረዱ» ብሏል። ዕዝራ 6፥18-20፤
ስለዚህ በዚህ ክፍለ ንባብ መሠረት ፋሲካ ማለት አንደኛ፦ በዓልን የሚያመለክት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ለበዓሉ የሚቀርበውን መሥዋዕት ያመለክታል።
2· ደስታ ማለት ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ = ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች» ብሎ ዘምሯልና። የዚህ ክፍለ ንባብ ምንጭ «ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር = ሰማይ ደስ ይለዋል ምድርም ደስ ይላታል» የሚል ነው። ሥረወ ቃሉም የሚገኘው በኢሳይያስ 44፥23 ላይ ነው። ስለዚህ ፋሲካ ማለት ደስታ ማለት ነው።
3· ማዕዶት ወይም መሻገሪያ ማለት ነው።  «ፋሲካ ብሂል ማዕዶት ብሂል በዘቦቱ ዓዶነ እሞት ውስተ ሕይወት = ፋሲካ ማለት ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገርንበት ማዕዶት ማለት ነው» ብሎ እንደዘመረ ቅዱስ ያሬድ።
4· ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው። «ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ = ይህች ፋሲካ የሕግ መጀመሪያ ናት» እንዲል።
5· የትንሣኤው መታሰቢያ ነው። «ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኃኒነ = ፋሲካ የመድኃኒታችን የትንሣኤው መታሰቢያ ናት» እንዲል።
6· ትንሣኤ ማለት ነው። «ትንሣኤ ሰመያ ለበዓለ ፋሲካ = የፋሲካ በዓልን ትንሣኤ ብሎ ሠየማት» እንዲል። ትንሣኤም ሁለት አይነት ነው። ትንሣኤ ልቡናና ትንሣኤ ዘጉባኤ።
በውኑ መንፈሳዊ እረፍትና ደስታ ለማግኘታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእኛ ለመምጣቱ ምክንያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለችምን? ፀረ ማርያም አቋም ያላቸውና ነዳያነ አእምሮ የሆኑ ይህ አይዋጥላቸውም ይሆናል። ለነገሩ ምን ገዷቸው።
ከላይ ፋሲካ ማለት ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው ማለታችን ይታወሳል። የመጀመሪያውን ቃለ ብሥራት በመስማት እመቤታችን ዓለሙ በኃዘን እንዳይጠፋ «ይኩነኒ = ይደረግልኝ» በማለት ቀዳማዊት አይደለችምን። ከሷ ተወልዶ ዓለሙን ከወደቀበት መርገም እንደሚያድነው ሲነግራት እራሷን አሳልፋ አልሰጠችምን? ከዚህ በላይ ፋሲካ መሆንና መባል ከወዴት አለ? ልጇን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን ራሱን ለመስቀል አሳልፎ በመስጠቱ ፋሲካችን ስንለው እሷንም  ለእግዚብሔር ፈቃድና ዓላማ ለእኛም የዘለዓለም ሕይወት ምክንያተ ድኅነት ለመሆን ራሷን አሳልፋ ስለሰጠች የአዳም ፋሲካ እንላታለን።
ሌላው ይህን ክፍለ ጸሎት ለመንቀፍ የተዘጋጁ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ችግር አለባቸው።  የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፦
1፣ ይህ ጸሎት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጸለው በቃል ነው። በቃል ለማጥናት ደግሞ ትጋትና ማስታወስ አስፈላጊ ነው።  እነዚህ ሰዎች ሙሉ ጊዜያቸውን የሚያውሉት ለከንቱ ወሬና ለከርሣቸው የሚሆን ፍርፋሪ ለመፈለግ ስለሆነ አይሆንላቸውም። ከሊቃውንቱ ጋር አብረው ቆመው መጽሐፍ ዘርገተው ቢታዩ ደግሞ ውርደት ይመስላቸዋል። እነዕገሌ ሁሉ በቃላቸው ነው ምነው እናንተስ ከሚለው ጥያቄ መሸሽ ይፈልጋሉ።  ከማን አንሼ አይነት ነገር ይመስላል።
2፣ የአገልግሎት ፍቅርና መንፈስ ጨርሶ የላቸውም። እንቅልፋሞችም ናቸው። ተርእዮ ይወዳሉ። ሰው በሚበዛበት ጊዜና መድረክ እንጂ መገኘት የሚፈልጉት በተመስጦ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር በሚቀርብ አገልግሎት መገኘት አይወዱም። ማን ሊያያቸው። ቀድማችሁ ገብታችሁ አገልግሉ እንዳይባሉ አገልግሎቱን ማጥላላት ምርጫቸው ሆነ።
3፣ እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት አይመቻቸውም። ለምሳሌ «ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ ዓፅመ ገቦሁ» የሚለውን ሲጠቅሱ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ ነፃነታቸው ተደርጓልና» የሚለውን መጥቀስ አይፈልጉም። በትርጓሜያችን መጽሐፍ ጭብጡን አይለቅም  ለሸፋጭ ለለዋጭ አይመችም የሚል ሐተታ አለ። ለሸፍጣቸው ስለማይመቻቸው ለማጥፋት የቻሉትን ያህል ይደክማሉ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ፋሲካ» የተባለው በለበሰው ሥጋ ነው። ይህም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ «ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም = የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ» በማለት የተናገረውን የሚተረጉም ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን «በግ» እያሉ  ሲገልጹት እሱ ራሱ በርሱ ያመኑ ምእመናን «በጎች» በማለት ይጠራቸዋል።  ይህ ማለት የምእመናን «አባግዕ» መባልና መሆን የክርስቶስን ስፍራ ይይዛል ወይም ይተካል ማለት አይደለም።  ለዚህ ነው ሊቁ «ለአዳም ፋሲካሁ» ካለ በኋላ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ ነፃነታቸው ተደርጓልና» በማለት ማስረጃ ያስቀመጠው።
ቅዱስ ኤፍሬምም በቀዳሚት ውዳሴው «ትትፌሣሕ ገነት እመ በግዕ ነባቢ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም = ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር የአብ ልጅ የተናጋሪው በግ እናት ገነት/እመቤታችን ደስ ትሰኛለች» ብሏል። እናቱ ስትደሰት የማይደሰት ልጅ የለምና።    «ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ የገባለትን ቃል የፈጸመለት ከእመቤታችን ሰው በመሆን ነውና። እባብ የሞቱ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም የድኅነቱና የፋሲካው ምክንያት ናትና።
ሊቃውንት በየድርሳናቸው «ትምክሕተ ኵልነ፣ አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ፣ ትክምሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ = የሁላችን መመኪያ፣ አንቲ የባሕርያቺን መመኪያ ነሽ፣ አንተን በመውለዷ የባሕርያችን መመኪያ ናት» እያሉ የገለጿት የአዳም ፋሲካ/ደስታ በመሆኗ ነው። እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር በተመለከተ ጊዜ እሱን የሚፈልግ ጠቢብ ሰው አለማግኘቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ። መዝ 13፥2፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአዳም የገባው ቃል ኪዳን የሚፈጸምበት ዘመን ሲደርስ መልአኩን ልኮታል። «ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር = በስድስተኛው ወር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ» እንዳለ ወንጌለ ሉቃስ። ሲያበሥራትም «ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ = ደስ የተሰኘሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ» በማለት ነው።  ስለዚህም ድንግል ማርያም የአዳም ፋሲካ/ደስታ ናት።
ቅዱስ መጽሐፍ ሔዋንን «የሕያዋን ሁሉ እናት» (ዘፍ 3፥20) ብሎ ሲጠራት እመ ሕይወት ድንግል ማርያምን ፋሲካ ብንላት አላዋቂነት ነውን?
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

«ግድያ ይቁም» በሚል መርህ ተቃዋሚ ሰልፎች እንዲደረጉ፣ የተገደሉ ተማሪዎች ጉዳይ የሚያጣራ ገለልተኛ ኮሚሽን እንዲቋቋም. የተጎዱ ቤተሰቦች ለመርዳት ትብብር እንዲያደርጉና ለወደፊቲ ደሞክራሲና ነጻነት እንዲኖር የሚደረገዉ ትግል የወደፊት ስትራተጂ እንዴት መሆን እንደላእብት ምክክር እንዲደረግ ጠይቀዋል። ዶር መራራ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥሪ እንዳቀረቡትን ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር በዚህ ጉዳይ አብሮ መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ለማመቻቸት የነደፉት ሃሳብ እንዳለ የተቁሙት ነገር የለም። […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ እሁድ፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓም «የእሪታ ቀን» በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፍ አካሄደ። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ ብሶቶችን የሚያንፀባርቁ መፈክሮች፥ የተሰሙበትና አልባሳትም የታዩበት እንደነበር የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ እ ጎ አ ከ 1903 ዓ ም አንስቶ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት መሥርተው የሚገኙናበተለይ ከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የጋራ ትብብርን አጠናክረው የሚገኙ አገሮች ናቸው። በመንግሥታት ደረጃ ግንኙነቱ ያልሠመረው በደርግ

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ትላንት ማታ የአንድነትን ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ በፌስቡክ ማሳወቃቸው ይታወቃል። ዛሬ ጠዋት ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ ሰማያዊ አርማ ያለበት ልብስ በመልበስና የሰማያዊ ፓርቲ አርማ በመያዝ፣ አስቀድመው የሰልፉን አዘጋጆች ሳያሳውቁ ወደ አንድነት ጽ/ቤት ጥቂት የሰማያዊ ወጣቶች ይመጣሉ። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በሰልፉ እንዳይሳተፉ በአንድነቶች ተከለከሉ የሚል አንዳንድ ትሽቶች በሰማያዊዎች በሶሻል ሜዲያዎች ተለቀዋል። የሰማያዊ ፓርቲ፣ አንድነት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ጤና ይስጥልኝ ሃብታሙ አያሌው እባላለሁ። የአንድነት ለዲምክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙንተ ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ነኝ። የሚሊዮን ድምጽ ንቅናቄ በአንድነት ፖርቲ ቢጀመርም ንቅናቄው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነው። የዴሞክራሲ፣ የስላም፥ የፍትህ፣ የነጻነትነ የአገር አንድነት ጥያቄ የአንድነት ፓርቲ ብቻ ሳይሆነ የእያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። በአገራችን ኢትዮጵያ የመጻፍና የመናገር ነጻነት፣ የሃይማኖት ነጻነት፣ የመሬት […]

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የሰላማዊ ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ
በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሰነበቱትና ቀሪዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ሳምንታዊ የወጣቶች የውይይት ፕሮግራም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) የ‹‹እሪታ ቀን›› በሚል የጠራውን ሰልፍ በግንባር ቀደምነት በመቀላቀል ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል፡፡
ወጣቶቹ ሰልፉን እንደሚቀላቀሉ ያስታወቁት ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ውጤታማ እንዲሆን በምን መልኩ ልናግዝ እንችላለን?›› በሚል አጀንዳ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከውህደት በዘለለ በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በሌሎች የትግል ስልቶች መተባበርና አብሮ መስራት እደግፋለሁ የሚል አቋም እንደሚያራምድ በተለያዩ ሚዲያዎች መግለጹ የሚታወቅ ሲሆን ወጣቶቹ በሰላማዊ ሰልፉ የሚያደርጉት ተሳትፎ ፓርቲው ለትብብር ያለውን አቋም ያሳያል ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ለሰላማዊ ሰልፉ ድምቀት የሚያገለግሉ ሜጋ ፎኖች፣ ጥሩምባዎችና ሌሎችም ሰልፉን ለማድመቅ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ይዘው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]
Journalist Tesfalem Weledeyes, ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ

በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዕዩ ገራገር ነው። ‹ጥርስ ያሳብራሉ› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኤዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው። በኤዲቶሪያል ጠረጴዛዎችና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂምና በቀል አያውቅም። በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሞያውና የጋዜጠኝነት መርሕ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ጥቅም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው። ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው – ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ።

ሙሉውን አስነብበኝ …