ህወሃት የአንድ ቤተሰብ የፖለቲካ ስብስብ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ እዩልኝ … .. ሁለቱም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ ሌሎችን ለአብነት ያክል የቀድሞ የትግራይ ክልል ር / መስተዳደር የነበረው ያሁኑ የደህነት ሹም አቶ ፀጋይ በረሄ እና የትግራይ ክልል አፈ ጉባዔ የሆነችው የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ቅዱሳን ነጋ አርከበ ዕቁባይ የዚሁ ቤተ ሰብ ቤተ ዘመድ እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ይገኙበታል […]

የትናንት ለሊቱ የፍሎይድ ሜይዌዘርና የማኑ ፓኪያ የመካከለኛ ሚዛን የላስቬጋስ የቡጢ ፍልሚያ አለም እንዴት ሲያብድለት እንደከረመ መታዘባችን አልቀረም ይህ የቡጢ ፍልሚያ በታሪክ እጅግ ውድ የመግቢያ ትኬት የተሸጠበት, ውድ ክፍያ ተፋላሚዎቹ ያገኙበት, እጅግ የገነነ የሚዬ ሽፋን ያገኘ … ወዘተ ምናምን ብቻም አይደለም ይልቁንም ከውድድሩ ጋር ተያይዞ እጅግ የበረከቱ አስደናቂና አስገራሚ ነገሮች በሪንግ ላይ ለተኩል ሰአት እንኳን ካልቆየው […]

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ለመዘከር የወጣው ህዝብ ተቃውሞውን ወደ ኢህአዴግ መንግስት ካዞረ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ያስነሳው በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገለው ሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት የከፈተው ሰፊና አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ የህዝቡን አመለካከት ሊቀይር አለመቻሉ ከፍተኛ ካድሬዎችን ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ የታየውን ህዝባዊ ቁጣ  ሰማያዊ …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ታህሳስ ወር አርበኞች ግንቦት7ትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ መንገድ ላይ ተይዘዋል ባላቸው እሰረኞች ላይ ለደረጃ ምስክርነት አብረው ከታሰሩት መካከል እያሰለጠ ነው። አንዳንዶች ፖሊስ ራሱ ያዘጋጀውን ቃል በፍርድ ቤት ተገኝተው የሚሉ ከሆነ ከእስር እንደሚፈቱ ፣  ለመመስከር ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ እድሜ ልካቸውን በእስር ላይ እንደሚቆዩ እንደተነገራቸው …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው  ምርጫ ላይ  ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል። ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል። ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀገሪቱካሉት 879 በላይ  የጤናተቋማትውስጥመሰረተልማቶችየተሟሉላቸው 105 ብቻሲሆኑ፣ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 68 ሴቶች በየሰዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የአብዛኛው እናቶች ሞት የሚከሰተው በደም መፍሰስ፣ በተራዘመ ምጥና በከፍተኛ የደም ግፊት ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሺ እናቶች መካከል 420ዎቹ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

 መግቢያ የአሜሪካ መንግስት እ.አ.አ በ2009ዓ.ም በኢራቅ የሚገኘዉን አምባገነናዊ የሳዳም ሁሴን አገዛዝ ለማስወገድ ከሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ጋራ በመሆን ባካሄደው ወረራ የሳዳም ሁሴን አገዛዝን አስወግደው በፋንታው ጠንካራ የኢራቅ መንግስት ሳያቋቋሙና መልሶ ግንባታ ሳያካሄዱ በመቅረታቸው የእልቂቷ ምድረ-ኢራቅ እንዲትፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በቀደምት የሰው ልጅ ስልጣኔ የምትታወቀው የባቢሎን ምድረ ኢራቅ በአሁኑ ወቅት በተቃራኒው ተሰልፋ ምድረ እልቂት፡ ምድረ ጦርነት፡ ምድረ ዱንቅርና ሆናለች፡፡ ቀድሞውም በሳዳም አገዛዝ ወቅት የነበረው የ”ሱኒ-ሺዓ” ፖሎቲካ ውጥረት በአከባቢያዊ ጎሳ ግጭት ላይ ተደምሮ የሀገሪቱ ስጋት የነበረ በመሆኑ ከአሜሪካና አጋሮቿ ወረራ ቡኋላ በፈራረሰችውና በመንግስት አልባዋ ምድረ ኢራቅ ነግሶና ግሎ የስንቱን ንጽሃን ዜጎች ህይወት በቀላሉ ቀጥፏል፡፡ ይህ አስከፊ ጦርነት መንግስት አልባ ሊባል የሚትችል ኢቅን በማምጣቱ እንደ IS አይነቱ ሰው-በላ አረመኔያዊ ቡዱን በሃማኖት ሽፋን እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ የሰሞኑ የአረብ አብዮት ተከትሎ በሶሪያ መንግስት ላይ የተነሳዉን ህዝባዊ አመጽ ከህዝብ በመንጠቅ የኢራንና ሺዓ አከባቢያዊ የበላይነትን ለማስቆም በሳዑዲ ዓረቢያና ኳታር የሚመራው የገልፍ አረብ ሱኒ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር በመተባበር የበሽር አል-አሳድ አገዛዝን ለመገልበጥ ISን ጭምሮ የIS ገባር የሆኑ የተለያዩ ፅንፈኛ ቡዱኖችን አስታጥቋል፡፡ በዚህም IS በሰው ሀይል፡ በገንዘብ፡ በትጥቅና ሌሎች ወታደራዊ ሎጂስቲኮች በሚገባ ተደራጅቷል፡፡ ይህም የIS መቋቋም ጀርባ ማን እንዳለ ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል፡፡ የIS ጉዞ አልቃይዳን የማያስታውስ አለ? ኦሳማ ቢን ላዲንን የማያስታውስ አለ? የታሊባን ተዋጊዎችን የማያስታውስ አለ? የሴፕቴምበር 2001 የኒውዮርክ መንትያ ህንፃዎች ጥቃት የሚረሳ አለ? በዓለማችን ኣቻ ያልተገኘለት፡ አለ የተባለ ፖሎቲከኛ፡ ምሁር፡ የሃይማኖት […]

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን […]

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ለህብረቱ ታዛቢ ቡድን ገለጸ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም በምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን በተናጠል በምርጫው ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ቡድኑን ያነጋገሩት አቶ ወረታው ዋሴ እና አቶ እምዕላሉ ፍስሃ ህብረቱ ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡ የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ከአሁን ቀደም በተካሄዱት ሀገራዊ ምርጫዎች […]

<ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡…

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

‹ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ  ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡

‹ጀማል› ነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹ሙስሊም› ነው መባሉ ነው፡፡ 

ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረው ‹ጀማል› ይልቅ እዚሁ አዲስ አበባ ያለው መሐመድ ካሣ ይህንን ልዩ ፍቅር ከንጋት ኮከብ በላይ አጉልቶ አሳይቶኛል፡፡ ልቡ እስኪደክም ኀዘንተኞቹን ለማጽናናትና ለመርዳት የሚደክመው፤ ለምን ጉባኤ አይደረግም፣ መዘምራን ለምን አይመጡም፣ መምህራን ለምን አያስተምሩም እያለ ልቅሶ ቤቶቹን ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲያገለግል የነበረው፤ ተዝካራቸው መውጣት አለበት ብሎ ከካህናቱ ጋር የሚሟገተው፣ ድንበር ተሻጋሪውና ድልድይ ገንቢው መሐመድ ካሣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ከበቂ በላይ ማሳያዬ ነው፡፡ ያየሁት፣ የነካሁት፣ የበለጠኝ ማስረጃዬ፡፡ ፈጠራ አያስፈልገኝም፡፡
ኤፍሬም ሆይ በረከትህ ይደርብን፡፡

(ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ፤ መድሎተ ጽድቅ፤ ሚያዝያ ፳፻፯ ዓ.ም.) መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ቸርነት የተሰጠን መዳን በመስቀል ላይ የተፈጸመ መኾኑን እንደሚነግረን ኹሉ ያን መዳን ገንዘብ ለማድረግ እያንዳንዱ ሰው ከማመን ጀምሮ በተቻለው መጠን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሠርቶ ባሳየንና ባስተማረን መጓዝና መጋደል ያለበት መኾኑን ያስተምረናል እንጂ በክርስቶስ ድነናል እንጂ ንጽሕናን ለመጠበቅ መጋደል፣ እንዲኹም ሰውነትን በገድል ማስጨነቅ አያስፈልግም …

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የጥናት እና ምርምር ማእከል÷ ‹‹ሰማዕትነት ለክርስትና›› በሚል ርእስ ነገ፣ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 – 11፡00 ሰዓት በማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት አዳራሽ ጥናታዊ ውይይት ያካሒዳል፡፡ የጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብሩ፣ በየኹለት ወሩ (በዓመት ስድስት ጊዜ) በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ የሚዘጋጀው የነገረ ቤተ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላትና ደጋፊ በኖርዌይ ከተሞች ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ በኦሮሚያ ክልል ነቀምት አርጆና በደሌ ከተሞች የኦህዴድ  ብልሹ አሰራር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ተገለጸ የወያኔ መንግስት የ‹‹መራጮች ኔትወርክ›› የሚል ቡድን እያደራጀ መሆኑ ታወቀ፡፡ በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን ባለስልጣናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የምረጡን ቅስቀሳ ህዝቡ ስላልተቀበለው በከባድ ስጋት ላይ መውደቃቸው ታወቀ፣ posted by Aseged TameneFiled […]

  የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሰራዊት ክህደት እየጨመረ መሄዱ ስላሳሰባቸው የእያንዳንዱን ወታደር ንብረት እየፈተሹ በርካታ ወታደሮችን ማሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የማዕከላዊ እዝ አመራሮች በየዕለቱ የሚከዳው የሰራዊት ቁጥር ስላሳሰባቸው ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ/ም የእያንዳንዱን ወታደር የግል ንብረት ሲፈትሹ የዋሉ ሲሆን በፍተሻውም ከ180 በላይ የሚሆኑት የሲቪል መታወቂያ ካርድ ያላቸው ወታደሮች መገኘታቸውን አስረድቷል። […]

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዚህ ሳምንት ብቻ 9 ሺ 405 ወጣቶች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ሲጓዙ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ተይዘዋል። ፋሲል የኔአለም ዝርዝሩን ያቀርበዋልበሰሜን ጎንደር ዞን ቆላማ ወረዳዎች በተደረጉ 2 የዳሰሳ ጥናቶች በቀን  ከ150-250  በዓመት ደግሞ ከ 54,000 እስከ 90,00 ኢትዮጵያውያን   ወደ  ሱዳን ይሻገራሉ፡፡ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪፖርቱ ኢህአዴግ ምርጫውን ለማሸነፍ መልካም እድል መኖሩን ጠቅሷል። ኢህአዴግ መንግስት መሆኑና የመንግስትን ንበረቶችና ጽህፈት ቤቶች መጠቀሙ እንዲሁም   በቅስቀሳ ወቅት አንድ  ለአምስት  በሚል  አሠራር  በተጠቀመበት  የቅስቀሳና  የማሳመን አሠራር    በርካታ  ድምፆችን ለመውሰድ የሚያስችል እድል መፍጠሩን በ2002 ቱ ምርጫ ወቅት መታየቱን አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሚኒስትሮች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። በቅድመ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ነጻ ፕሬሱን በማዋከብ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ከሚያደርገው ቀጥተኛ ጥቃት በተጨማሪ ስልታዊ ጥቃትን በተጠናከረ መልኩ ስራ ላይ እያዋለ ነው። በነገው ዕለት የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ ታስቦ የሚውለው የፕሬሱ ስልታዊ አፈና በተጠናከረበት ወቅት መሆኑም ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ምንም ዓይነት ትችትና የተለየ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የኮምኒኬሽን ምክር ቤት  የኢሳት አባሎችን እና ቁልፍ የግንቦት ሰባት አመራሮችን የግል ላፕቶፓቸውን እና ለመረጃ መሰብሰብ የሚጠቀሙባቸውን ስልኮች ለማግኘት የሚያስችል እቅድ ማውጣቱ ታውቋል። በግምገማው ወቅት ኢሳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መሆኑ ተገልጿል። ኢሳት በመንግስት ላይ እየሰነዘረ ያለው ጥቃት ጉልህ ለውጥ የማምጣት አቅም …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም አንዲት ምጥ የተያዙ እናት በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጎምበራ የጤና ጣቢያ በሄዱበት ወቅት ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው!›› ተብለው ወደ ሆሳና ሪፈራል ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ ሪፈር ቢጻፍላቸውም በትራንስፖርት ችግር ነፍሳቸው ማለፉን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ለጎምበራ ጤና ጣቢያ የተመደበችው አምቡላንስ በጎምበራ ወረዳ ኦሌ ቀበሌ ለገዥው ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በመውጣቷ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቤተእስራኤላዊያኑ የተቃውሞውን ሰልፍ ያደረጉት ደማስ ፈቃደ የተባለ ቤተእስራኤላዊ  ወታደር በፖሊሶች መደብደቡን ተከትሎ ነው። አንድ ፖሊስ ወታደር ደማስን መደብደቡን የሚያሳይ በሚስጢር የተቀረጸ ቪዲዮበማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ ከሆነ በሁዋላ ፣ ቤተ እስራኤላውያኑ ቁጫቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ግጭት ፈጥረው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን የፈጸመውን ፖሊስ …

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

የወንዶች ዘመነ እርጠት የሚከሰተው ቴስቴስትሮን የሚባለው ሆርሞን መመረት ሲቀንስ ነው። ከሴቶች ዘመነ እርጠት ጋር ሲነፃፀር በወንዶች ላይ የሂደቶቹ መገለጫዎች ዘግይተው ይጀምራሉ ከዚያም ለውጣቸው የዘገየ ይሆናል። እድሜያቸው ከ25-75 ዓመት ያሉ ወንዶች ላይ የፍትወተ ስጋ ስራ/አገልግሎት ቀስ በቀስ መቀነስ ይታይባቸዋል በዚህ ጊዜ የሚኖረን የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በ 50% ይቀንሳል ይህ ቁጥር ከሰው ወደ ሰው ይለያያል።
የዚህ ችግር…

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

የወር አበባ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ እንዲወራ ከማይፈልጋቸው ጉዳዩች አንዱ ነው ነገር ግን በሰፊው ልናወራበት ልንወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው በተለይ የጤናዎ ጉዳይ ሲሆን፡፡ ስለ ወር አበባ የሰሙት ወይም እንዲያዉቁ ያደረገዎት ያደጉበት ማህበረሰብ ወይም አንደ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያሉ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ በየወሩ እየመጣ የሚጎነኝንን እንግዳ ስለ ጤናችን በማንኛውም እድሜ ላይ…

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

የስኳር በሽታ ዓይነት 2 በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰውን ያጠቃል። በስኳር በሽታ ከተያዙ 3 ሰዎች ውስጥ አንድ በሽታው እንዳለበት አያውቅም ይህ አደገኛ በሽታ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኝውን ካርቦሀይድሬት በትክክል እንዳይጠቀም ያደርገዋል የዚህም ውጤት በደማችን ውስጥ የስኳር መጠን ከፍ እንዲል ያደርገዋል። በደማችን ውስጥ የስኳር መጠን መብዛት የልብ ህመም፣የእይታ ማጣት፣የነርቭና አካል…

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

  የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላትና ደጋፊ በኖርዌይ ከተሞች ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ may 01. 2015 በመላው አለም የተከበረውን የወዝ አደሮችን ቀን ምክንያት በማድረግ በኖርዌይ ከተሞች በተለይም በኦስሎ በበርገንና በስታቫንገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል በዚህ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በአሁኗ ሰዓት በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን በደቡብ […]

የፈረንሳይ ወታደሮች ቅሌት በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ
የቦልቲሞሪ ረብሻ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን

በረከታቸው ይደረብንና የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (1932 – 1982 ዓ.ም.) ሚያዝያ 23 ቀን 1982 ዓ.ም. በሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጡት ትምህርት ጀግና በጦር ሜዳ ይወለዳል፤ በክፉ ቀን ከብዙ ፈሪዎች ከብዙም ጀግኖች መካከል ቅ/ጊዮርጊስ ተገኘ የተወደዳችኹ ምእመናን፤ በዚኽች በበዓለ ኀምሳ ውስጥ፣ ዛሬ ተጨማሪ በዓል የምናከብረው የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን …

  የአንድነት ፓርቲ ከታገደ በኋላ፣ በርካታ ተወዳዳሪዎች ለምርጫዉ አሰልፎ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው መድረክ ነው። መድረክ በኦሮሚያና በትግራይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ያሰለፈ ሲሆን፣ በደቡብ ክልልም በበርካታ ቦታዎች ይወዳደራል። በወላይታ ዞን አቶ ኃይለማሮያም ደሳለኝ በሚወዳደሩበት ወረዳ መድረክ እጩ ተወዳዳሪ አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆም፣ እጩ ተወዳዳሪው ከፍተኛ ወከባና ጫና ስለደረሰበት፣ ከዉድድሩ ራሱን ማግለሉን አሳዉቋል። በመሆኑም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ […]

  ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ሳይጀመርና ከሰልፉ በኋላ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ቤት ተበረበረ፡፡ ካሳንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ትናንት ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ቀርበው […]

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ […]

‹‹ሰይፍህን አንሣ፣ ክተት ሠራዊት፣ ዝመት ለፍቅር፣ ሰልጥን ለምሕረት፡፡›› (አርቲስት ዘሪቱ ከበደ) ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በቆንጨራ ለተጨፈጨፉ፣ በሚያሰቅቅና በሚዘገንን ኹናቴ እሳት በቁማቸው ለተለቀቀባቸው፣ ሀብት ንብረታቸው ለተዘረፈባቸውና ለጋየባቸው፣ የጦርነትና የእልቂት አውድማ በሆነችው በአገረ የመን ለሞቱና በጭንቅ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችንና በተለይም ደግሞ በሊቢያ በአይ ኤስ የአክራሪና ጽንፈኛ ቡድን የተሠዉትን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን አስመልክቶ በጥቂቱም ቢሆን የጥበብ ባለ ሙያዎቻችን በሥራዎቻቸው […]

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣ እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“ አገኘሁ እንግዳ ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት […]

ክንፉ አሰፋ

Obama Stop ISIS

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሔራዊ የኀዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም ባህርዳር ታስሯል) ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ገለፁ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው- የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና […]

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ በተባለ አካባቢ የኢህአዴግ ቡዱን የፖሊስ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በሚፈጥሩት ግጭት እየተገደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ልዩ ቦታው መርሳ በተባለ አካባቢ ሚያዚያ 12 /2007 ዓ.ም አቶ መሓመድ ዓሊ የተባለ ግለሰብ ምክትል ሳጅን ከበደ አበጀ ለተባለ የፖሊስ አባል በስራው ላይ እንቅፋት ስለፈጠረበት ይዞት በነበረው ዱላ ደብድቦ እንደገደለው ከምንጮቻችን ያገኘውነው […]

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ፣ የማረሚያ ቤቱ ሹሞች ፖሊሶችን ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚፈልጓቸው ከገለጹላቸው በሁዋላ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ፖሊሶች የሞባይል ስልኮች ተቀብለው ፍተሻ አድርገዋል። በፍተሻው ወቅት 18 ፖሊሶች ከኢንተርኔት የተለያዩ ፎቶዎች፣ ጽሁፎችንና ቀስቃሽ ዘፈኖችን በማውረድ በስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠው የተገኘ ሲሆን፣ ፖሊሶቹም ወዲያዉኑ እንዲባረሩ ተደርጓል። በተለይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በጀኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፊት ለፊት  ባደረጉት ሰልፍ በሊቢያና የመን በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ጥያቄያቸውን በተወካዮች አማካኝነት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣኖች ያቀረቡ ሲሆን፣ የፖለቲካ ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአፋጣኝ ወደ ሶስተኛ አገር እንዲሸጋገሩ፣ ሌሎችም እንዲሁ አሁን ካሉበት አገር ወጥተው በሶስተኛ አገር …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚያዚያ 30 ፣ 2007 ዓም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ አቶ አቡበክር አህመድ በተከሰሱት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት በተሰጠትእዛዝ፣ ውሳኔው ከምርጫው በፊት አይሰጥም። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የተባሉት የደህንነት ባለስልጣን ይህንኑ አቋም በቅርቡ ተደርጎ በነበረው የኢህአዴግ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  አለም ባንክ አካባቢ የሚገኙ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ3 ሺ በላይ አባወራዎች ያለፉትን 11 ወራት በስቃይ ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። የመንግስት ባለስልጣናት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለምርጫ ቅስቀሳ መምጣታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ያሉበት ህይወት ከሞቱት በታች መሆኑን በምሬት ገልጸዋል። ቤታቸው ከፈረሰባቸው …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የከተማዋ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ አመራሮች የመሳሪያ ፈቃድ የሚያወጡትን ነዋሪዎች፣ ለመሳሪያ ፈቃድ 260 ብር ፣ ለግዳጅ ቦንድ ግዢ 1 ሺህ ብር እንዲሁም ለቀበሌ መታወቂያ 300 ብር በማስከፈል ላይ መሆናቸውን ህዝቡን ምሬት ላይ ጥሎታል። በሱዳኗ የጠረፍ ገበያ ማዕከል በሆነችው የገላባት …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከምሁራንና ከዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጋር በጋራ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወረቀቶችን ያቀርባሉ። ምሁራኑ ኢትዮጵያ የገጠሙዋትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በማንሳት ተጨባጭ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይቱ ላይ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የዲሞክራሲ አቀንቃኞችና የውጭ አገር ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ …