ዜና ከፍቼ፤ በፍቼ የአንድነት ቢሮ በመንግስት ሃይሎች ተሰበረ:: ወጣቱ ሰባሪዎችን አሳፍሮ አባሯል:: ፍኖተ ነጻነት
የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን መኪናና በባጃጆችን በመጠቀም የተቀናጀ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የፍቼ ከተማ የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሹመኞች ህዝቡ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ ቤት ለቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ ቢገኙም ህዝቡ በነገው የተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለመግለፅ ተዘጋጅቷል፡፡ ዘግይቶ በደረሰን ዜና በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት የደህንነት ሀይሎች ሰብረው በመግባት በቢሮው ውስት ያሉትን አባላት ቢያባርሩም […]