(በኃይሌ ሙሉ) በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ አስተባባሪነት በአሥራ አራት ፓርቲዎች ሊመሠረት ታስቦ የነበረው ግንባር ሳይሳካ ቀረ፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከድርድሩ አግልለዋል፡፡

200 ሺሕ ሔክታር መሬት ይፈለጋል (በውድነህ ዘነበ) መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በ200 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ልማትና ሦስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡

– 400 ሚሊዮን ብር ዕዳ ይቀርበታል (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ለኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ካለበት ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ብር ከፈለ፡፡

ብርቱካን ፈንታ በ2002 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸው ውጤት ምን ያህል እንደሆነ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡ የመግቢያ ውጤቱ በዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ይወሰናል፡፡ ተማሪዎቹ የመልቀቂያ ፈተናውን ውጤት ከሐምሌ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ያወቁ ቢሆንም፣ እንደቀደሙት ጊዜያት ዩኒቨርሲቲ …

የዚህ ዓመት የዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ውጤት አይታወቅም Read more »

– ከሦስት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወርቅና ንብረት ዘርፈዋል (በታምሩ ጽጌ) የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሚያዚያ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ጣና ወርቅ ቤት ላይ ዝርፊያ አካሂደዋል በሚል ጥር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ክስ …

የጣና ወርቅ ቤትን የዘረፉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ Read more »

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የአምስት ዓመትየኢኮኖሚ እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል። አገሪቱን ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት የሚያስተዳድረው የኢህአዴግ መንግስት በጥቅምት ወር የሚመሰርተው አዲስ መንግስት በርካታ ስራዎች ይጠብቁታል። አገሪቱ ከውጭ የምግብ እርዳታ ነፃ እንድትወጣና ኢኮኖሚው በአማካይ በዓመት ከ11-14 ከመቶ …

የመለስ ኢትዮጵያን ከውጭ እርዳታ ነፃ የማድረግ የ5 ዓመት እቅድ Read more »

የኢትዮጵያ የዉሃ ሃብት ሚኒስትር አቶ አስፋዉ ዲንጋሞ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ”ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅት ላይ ለአድማጮች ጥያቄ በሰጡት መልስ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በቅርቡ እንደገና ስለተፈጠረዉ ዉዝግብ አስረድተዋል። አቶ አስፋዉ፣ ባለፈዉ ሃምሌ 5 በዋሽንግተን ዲስ ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያዉያን የኢትዮጵያ መንግስት በወንዙ …

የኢትዮጵያ ዉሃ ሃብት ሚኒስትር አቶ አስፋዉ ድንጋሞ ስለአባይ ወንዝ አጠቃቀም ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገለጹ። Read more »

ከአዜብ ጌታቸው ጠ/ሚሩ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ለራሳቸው ጋዜጠኞች የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ሳታደምጡ የቀራችሁ አይመስለኝም። መቼም በጠ/ሚርነት ተቀምጠዋልና እንኳን መገለጫቸው ግልምጫቸውም ዜና ሊሆን (News Worthy) ግድ ነውና እኛም ግድ ሆኖብን መስማታችን አልቀረም። ልብ ብላችሁ እንደሆነ ጠ/ሚሩ በሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁሌም …

መጀመሪያም ባዶ ቃል ነበር! ቃሉም የጠ/ሚሩ ነበር… Read more »

የዜና አውታሮች ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ እንደዘገቡት፤ ዓርብ፣ ከቀትር በኋላ፤ በግብጽና እሥራኤል ድንበር ላይ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ፣ ሰዎችን ካገር -አገር በሚያሻግሩ ቡድኖችና በፈላስያን መካከል ፣ ተካሄደ በተባለ የተኩስ ልውውጥ 4 ኤርትራውያን ተገድለዋል።

ከግርማ ካሳ እሁድ እለተ ሰንበት ቀን ነበር። አምላካቸዉንና ፈጣሪያቸዉን ሊያመሰግኑ ምእመናን የቤተ ክርስቲያኒቱን አዳራሽ አጣበዉታል። በአዳራሹ የነበረዉ ምእመን ፊቱን ወደ መንበረ ታቦቱ አዙሯል። በመንበረ ታቦቱ በቀኝና በግራ በኩል ነጭ የለበሱ ዲያቆናት ቆመዋል። በዲያቆናቱ መካከል ከመንበረ ታቦቱ በኋላ ምእመኑን ፊት ለፊት …

ኢትዮጵያ ውስጥ ኦስካር ሮሜሮዎች፣ አርተር ሱሌማኖቮች፣ አሊ ሲስታኒዎች አሉን? Read more »

20 ከመቶ የኤኮኖሚ ዕድገት ። ለአውሮፓውያን ይህ ህልም ብቻ ነው። አፍሪቃ ውስጥ ግን በተለይ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በገፍ ትቸበችብ በነበረችው በአንጎላ ይህ ከጥቂት ዓመታት በፊት ህልም ሳይሆን ተጨባጭ ሀቅ እንደነበረ የሚካድ አይደለም ።

አቡጊዳ — የጅቡቲ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጅቡቲ እንዳያርፍ መከልከሉን አዲስ ፎርቱን የተሰኘዉ በኢትዮጵያ የሚታተም የእንግሊዘኛ ጋዜጠ ዘገበ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 27 (ኦገስት 1) ጀምሮ በርራዉን በጅቡቲ ያቀመ እንደሆነ የዘገበዉ አዲስ ፎርቱን በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ድርድሮች እየተደረጉ መሆኑንም ዘግቧል። …

ጅቡቲ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳያርፍ ከለከለች Read more »

አቡጊዳ – ነሐሴ 9 ቀን 2002 ዓ.ም እራሱን ገለልተኛ አድርጎ የሚቆጠረዉ፣ ግን በብዙዎች የገዢዉ ፓርቲን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንደሆነ የሚነገርለት፣ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከ2002 ምርጫ በፊት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ገንዘብ ለድርጅቶች እንደሰጠ የሚዘግቡ ዘገባዎች በአዲስ አበባ እየተሰሙ ነዉ። የሪፖርተር ጋዜጣ፣ …

ምርጫ ቦርድ ሕገ ወጠ በሆነ መንገድ ገንዘብ እንዳከፋፈለ ተዘገበ ! Read more »

ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ወጣባቸው፤   (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 15/2010፤ ነሐሴ 8/2002 ዓ.ም):- በቅርቡ ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› በሚል ርእስ፣ ፈታሔ በጽድቅ በሚል የፈጠራ ስም የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን፣ የወ/ሮ እጅጋየሁ በየነን፣ የበጋሻው ደሳለኝን …

እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ የ “ሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች ”መጽሐፍ ደራሲን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ ናቸው Read more »

‹‹ሁለት መቀመጫ ያለው ቅንጅት የ40 ሰዎች ድጐማ ተሰጥቶታል››  አቶ ለገሰ ቢራቱ‹‹ቅንጅት የገንዘብ ድጐማ የተሰጠው ፓርላማ ባለው ወንበር ልክ ነው›› አቶ አየለ ጫሚሶ‹‹የምርጫ ቦርድ ሕጉን ጥሷል›› አቶ ተመስገን ዘውዴ‹‹ድጐማውን የሰጠነው በመስፈርቱ መሠረት ነው›› አቶ ተስፋዬ መንገሻ (በኃይሌ ሙሉ) ራሳቸውን ከቅንጅት ለአንድነትና …

ምርጫ ቦርድ ለቅንጅት የሰጠው የገንዘብ ድጐማ እያነጋገረ ነው Read more »

– በዓመት 340 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ዕቃዎች ይወረሱ ነበር (በብርሃኑ ፈቃደ) በጂቡቲ ወደብ ውስጥ ስድስት ወርና ከዚያ በላይ የቆዩ ዕቃዎች ከእንግዲህ እንዳይወረሱ የሚያስችል ስምምነት በመደረሱ፣ ወደብ ላይ የቆዩ ዕቃዎች ወደ አገር ውስጥ መግባት ጀመሩ፡፡

– ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ በፖሊስ ኃይል ተበተነ (በታምሩ ጽጌ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ሥር የሚገኙ የ27 ቀበሌዎች ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተፈቀደልንን የመሰብሰብ፣ የመደራጀት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመቃወምና የመደገፍ መብቶቻቸውን በወረዳውና በዞኑ ኃላፊዎች መነፈጋቸውን …

የሶዶ ወረዳ ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠልንን መብት ተነፈግን አሉ Read more »

(በጋዜጣው ሪፖርተር) የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማኅበር በበጀት ዓመቱ 415.6 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ አቅዶ 641.4 ሚሊዮን ብር ማትረፉንና የዕቅዱን 154 በመቶ ማግኘቱን፣ ካለፈው ተመሳሳይ የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 63 በመቶ የበለጠ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

(በኃያል ዓለማየሁ) የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የደቡብ ኮሪያ ስሪት የሆኑትን የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ እንደሚገነባ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) በማታለልና በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የጌት አስ ኢንተርናሽናል ኩባንያና የጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር ባለቤት አቶ ጌቱ ገለቴ የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና በሥራ ተቋራጮች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን መዳኘት የሚያስችለውን ሥራ ተረከበ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባወጣው መመሪያ መሠረት ትምህርታቸውን በ10+3 ፕሮግራም መጀመራቸውንና ለሦስት ዓመታት ከተማሩ በኋላ ‹‹ሥልጠናችሁ በደረጃ 4 ነው›› የተባሉ የእንጦጦ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች፣ ከነሐሴ 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ቀን ትምህርት ማቆማቸውን …

የእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ገለጹ Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ምርጫ 2002ትን ተከትሎ በአዲስ አበባ የአባላት ምልመላ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ለሥራ ጉብኝት ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል፡፡

(ገብር ሔር ዘመ/መንግሥት እንደጻፈው፤ ኦገስት 14/2010፤ ነሐሴ 8/2002 ዓ.ም)፦ በአንድ ወቅት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በሰሜን አሜሪካ ለሚሰራጨው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ የሰጡት መግለጫ ሰሜን አሜሪካንን ለአስራ ስምንት ዓመታት ላላነሰ ግዜ መኖሪያ ባደረጉት “ስደተኛ አባቶች” ዘንድ አቡዋራ ማስነሳቱን በተባራሪ ወሬ ሰምቼው …

በርግጥ መጋቤ ብሉይ የተናገሩት የእርቁ እንቅፋት ሊሆን ይገባ ነበር? Read more »

ኢትዮዽያ በስዊድን ያለውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከትላንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኤምባሲው ተልዕኮውን ሊወጣ ባለመቻሉ መዘጋቱንና ከዚያ ይልቅ በብራዚል መክፈት እንደሚሻል ገልጸዋል። የሲውዲን መንግስት ይህ የኢትዮዽያ መብት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል። …

ኢትዮጵያና ስዊድን Read more »

ከ6 ዓመታት በፊት እንደ ዘበት ተጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በለም ዙሪያ እንደ ሰደድ እሳት የተቀጣጠለና ፍቅርን ለእንግዳ ሰው የማሳየት ጥረት ተደርጎ የተወሰደው እንቅስቃሴ ነው፤ “Free Hugs” በአንድ አውስትራሊያዊ ወጣት የተጀመረውና በአያሌ አገራት ወጣቶች በስፋት ሲካሄድ የቆየው የፍቅር ማዕበል ባለፈው ወር …

የማያውቁትን ሠው በነፃና በወዳጅነት ማቀፍ Read more »

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀውና በቅርቡ በተካሄደው በዚህ የህፃናት ፊልም ፌስቲቫል የቀረቡትን ፊልሞች በሙሉ፥ ተጀምሮ እስኪጨረስ፥ የፃፉትን ታሪክ መጫወት ጨምሮ፥ እንደ ካሜራ ባለ ሞያና እንደ ዲሬክተር የሠሩት ዕድሜያቸው በ9 እና በ15 ዓመት መካከል የሚገኙ ታዳጊ ህፃናትና ወጣቶች ናቸው። «አሳትፉኝ፤» በተሰኘው ፕሮግራም …

የመጀመሪያ የህፃናት ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ Read more »

(VOA) — ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመጭው ጥቅምት አካሂዳለሁ ባሉት የመንግስት ለውጥ፤ እየተቀያየረ የሚሄደውን የኢትዮጵያን የወዳጅነት አቅጣጫ ተከትለው የሚዘጉና አዲስ የሚከፈቱ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች እንደሚኖሩ አስታወቁ። ከሚዘጉት መካከል የመጀመሪያ የሚሆነው በስዊድን የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንደሚሆን ተናግረዋል። “በኛና በስዊድን መካክል ትርጉም ያለው የልማት …

በስዊድን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሊዘጋ ነው Read more »

ለአባቶች ድርድር መሰናከል ምክንያት ሆኗል የተባለው የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ቃለ ምልልስ “ስለ ፓትርያርክ ከሥልጣን መውረድ እና መሻር” M.B Seife Silassie Yohannes about Patriarch Change in Ethiopian Orthodox Church from Deje Selam on Vimeo.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ዓለምአቀፍ ደረጃዎችን በጠበቁ መሣሪያዎች፣ መረጃ አሰባሰብ፣ አሠረጫጨትና አከመቻቸት የሚንቀሣቀስ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ ተ/ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዱላ ሻንቆ አስታወቁ፡፡ ኤጀንሲው የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አባል መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀው ከ11 የዞን ፅ/ቤቱ አንድ ሺህ በሚሆኑ ሠራተኞቹ ጭምር የሚያሰባስባቸውንና የሚያደራጃቸውን …

የኢትዮጵያ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ተአማኒ መረጃ እንደሚሰጥ ገልጸ Read more »

(በሔኖክ ያሬድ) የቀድሞ ሰው ከ3.4 ሚሊዮን ዓመት በፊት የድንጋይ መሣርያ ይጠቀም እንደነበርና መሣርያዎቹንም ተጠቅሞ የትላልቅ አጥቢ እንስሳት ሥጋና መቅኒ ይመገብ እንደነበር የሚያሳዩ ቅሪቶች መገኘታቸውን ነሐሴ 5 ቀን 2002 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም በ10 ሰዓት ይፋ ሆነ፡፡