በዝዋይ ማረሚያ ቤት በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ህገወጥ ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን!!! -ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በያሉበት እስር ቤቶች ፕሮግራም አውጥቶ በቡድን በቡድን በመሆን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን ለማድረስ ችሎ ነበር፡፡ ከእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችን በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሩ አላማ ያሉበትን የአያያዝ ሁኔታ ለመረዳት ጭምር ነው፡፡ በዚህም መሰረት በተለይ በዝዋይ በፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ላይ […]
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ) 


ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ “ሽፈራው – ሞሪንጋ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አሣተመ። ሞሪንጋ ወይም ባገራችን “ሽፈራው” እያልን በስፋት የምንጠራው ዕጽ፣ እጅግ እውቅናን አግኝቶ የኖረው በእስያ ውስጥ ነው። ሕንዶች ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ ባለጸጎች በመሆናችው በብዙ መልኩ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ዛሬ ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን ደሴቶች፣ በአፍሪካና በኦሴኒያ ውስጥ በብዛት እየለማና እየተስፋፋ ነው።