ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 11 በተለምዶ ጋሪሳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 470 ሰዎች ቦታው ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል ተብሎ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲፈናቀሉ ከተደረገ በሁዋላ፣ በካሬ ሜትር 1 ብር ከ46 ሳንቲም መሬታቸው እንዲጨጥ ተደርጓል። ጉዳዩ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ከቆየ በሁዋላ ሰሞኑን ከህዝቡ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲዎቹ ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲው መምህር አብረሃ ደስታ እና ሌሎች 6 የመብት ተሟጋቾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በአቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የተከሰሱት አስሩ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ ህገመንግስቱን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም። ሁሉም …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በላይኛው አዋሽ ተፋሰስ ከመስከረም 28 ቀን 2007 ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተፈናቀሉ በሺ የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ከእለት ዕርዳታ ባለፈ ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ገለጸዋል፡፡ የአካባቢው ተወካይ እንደገለጹት መንግስት በአካባቢው የገነባው የዝናብ መከላከያ ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ ምክንያት በጎርፍ በቀላሉ መሰበሩን ጠቅሰው በዚህ ምክንያት ማሳ ላይ የነበረ ምርታቸውን ጨምሮ …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ባለፉት 37 ቀናት ከ6 ሺ ያላነሱ ኤርትራውያን ብሄራዊ ውትድርናን በመሸሽ ተሰደዋል። ኮሚሽኑ እንደሚለው የስደተኞች ቁጥር ካለፈው ወር ጋር ሲነጸጻር በእጥፍ ጨምሯል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ብሄራዊ ወትድርና ዘመቻ ያስፈለገው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ  እንደሆነ ገልጿል። …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲ መንግስት ከተገለበጠ በሁዋላ በሱዳንና በግብጽ መንግስታት መካከል ያለው ልዩነት ሰፍቶ እርስ በርስ እስከመነቃቀፍ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፣ ሱዳን የሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማጮች የተባለው ፓርቲ እንደምታግድ በማስታወቁዋ ሁለቱ አገራት ወደ አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እያመሩ መሆኑን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጸዋል።ሁለቱ ሃገራት በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ተፈጥሮ …

– “በተለይም በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸነፍ ቃል የተያዘበት ቢሆንም [ቃለ ጉባዔ/የፓርቲው ሊቀመንበር መመሪያ?]፤ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበት እና ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የሕዝብ ክንፍ የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብ ይገባል ብለዋል [የፓርቲው ሊቀመንበር?]፡፡” “[አደራጃጀታችን] […]

አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን በህወሃት የሚመራው የኢትዮጵያ ገዢ መደብ በተናጠልም ሆነ በቡድን ደረጃ ተዳክሟል።በምድር ላይ ያለው እውነታ ይህንን ያመላክታል።ስርአቱ በመርበድበድ (in a state of panic ) ላይ መሆኑን የሚጠቁሙ ብዛት ያላቸው ምልክቶ እየታዩ ነው:: 1.ከ 23 አመታት በኋላ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሰብስቦ ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስበክ፤ 2.ከ~95 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ 1.5% ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በሆነበት “በፌስቡክና ትዊተር […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ባለፈው ወር ብቻ ከ5000 በላይ ኤርትራውያን ድንበር ተሻግረው በኢትዮጵያ ጥገኝነት መጠየቃቸውን አስታወቀ።በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ቁጥር

በሱማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሳን ሼይክ ሞሐሙድ እና በጠቅላይ ሚንስትር አብዲዋይል ሼይክ አኽመድ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ መባባሱ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡትን የሚንስትሮች ምክር ቤት መዋቅር ፕሬዚዳንቱ እንዳልተቀበሉት ተገልጿል።

መብረቅ የሚፈጥር ደመና ከሩቅ ሲታይ ፣ የተፈጥሮ ትርዒት በመሆኑ ዐይንን ሊስብ ይችላል። ከቅርብ ከሆነ ግን፣ ፍርሃትና ጭንቀት ነው የሚያስከትለው፤ የመብረቁ ብልጭታ አደጋ ሊያስከትል የሚችልበት ሁኔታ በመኖሩ! የምድር

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ የገንዝብ ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድና የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ከጅማ ዞን የተውጣጡ የተለያዩ ድርጅት ተወካዮችን በጊዜ አዳራሽ ሰብስበው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ህዝቡ በአስተዳደሩ ተስፋ መቁረጡንና ለውጥ የሚፈልግ መሆኑን ተናግሯል። የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስለው መድረክ ፣ አቶ ሙክታር ተሰብሳቢው የሚሰማውን እንዲናገር ፈቅደዋል። ነዋሪዎቹ በዞኑ ልማት የሚባል …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማክሰኞ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ኮቸሬ ከሚባል አካባቢ የመጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 4 ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ድንጋጤው የተፈጠረው ሰዎቹ በኢቦላ በሽታ ተይዘዋል በሚል እምነት ነው።  ዛሬ ረቡዕ ደግሞ 4ቱም ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ባለስልጣናት …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2006 ዓም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ረብሻ አስነስታችሁዋላ በሚል ከታሰሩት መካከል 4 ተማሪዎች በ2 አመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል። ሁለቱ የ4ኛ 5ኛ አመት የህክምና ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ድገሞ የ3ኛ አመት የነርሲንግ ተማሪዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚከተሉትን የአለባባስና የምግብ ስነስርአት መመሪያን …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ብሌስ ካምፓወሬን መንግስት በመገልበጥ ጊዜያዊ መሪ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን ለሲቪል አስተዳደር ያስረከቡት ሌ/ኮሎኔል አይዛክ ሲዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ጊዜያዊው ፕሬዚዳንት ሚኬል ካፋንዶ ኮሌኔሉን ጠ/ሚኒስትር አድርገው የሾሙት በስልጣን ጉዳይ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ተከትሎ ነው። ሁለቱም መሪዎች አገሪቱን ለአንድ አመት ያክል ካስተዳደሩ በሁዋላ ምርጫ ይካሄዳል። …

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት አንዱ አካል የሆነው የህሊና እስረኞችን የሶሻል ሚዲያ ንቅናቄ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ዘመቻ ሲሆን ከሚቀጥለው ከእሁድ ከህዳር 14 እስከ 20/2007 የሚቀጥል ፕሮግራም ነው። በዚህ ዘመቻ ሚሊዮኖች የፖለቲካ ይሳተፋሉ፤ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ተገቢ የሆነ አያያዝ እንዲኖራቸው፤ በሰላማዊ መንገድ የሚታሉትን ማሰርና ማዋከብ እንዲቆም ድምፃቸውን ያሰማሉ፤ ዘመቻው ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለመንግስት መስሪያቤቶች፣ ኤምባሲዎች፣ ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለአለም አቀፍ […]

ሥራቸውን በአግባቡና በትክክል የሚያከናውኑ ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አለኝታዎች፣ የዜጐች ኩራትና መተማመኛ ናቸው፡፡ በአንፃሩ ፍርድ ቤቶች ሥራቸውን በሕግና በታማኝነት የማይሠሩ ከሆነ ደግሞ የሕዝብ ሞራል እንዲወድቅ ሐሞቱም እንዲፈስ ያደርጋሉ፡፡ ተስፋ ያስቆርጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ በትክክል ሥራውን የሚሠራ ዳኛ የለም አንልም፡፡ ተገቢ ፍርድና ውሳኔ የሚሰጥ ችሎት በጭራሽ የለምም አንልም፤ አሉ፡፡ ምሥጋናም ይገባቸዋል፡፡ አጠቃላዩ ሁኔታ ሲታይ ግን ፍርድ ቤቶች ሥራቸውን እየሠሩ […]

የግብፅ መንግሥታት፣ ደካማ ኢትዮጵያን ለማየት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የኤርትራ ነፃነት ግንባሮችን መልምለው፣ አሠልጥነውና አስታጥቀው በኢትዮጵያ ላይ አዘመቱ፡፡ የኤርትራ ግንባሮች በበኩላቸው ጦርነቱ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲዳረስ ለማድረግ የተጠቀሙበት መንገድ የብሔረሰብ ንቅናቄዎችን መፍጠር እንዲሁም ሌሎች የእነሱን አርዓያ ተከትለው እንዲቋቋሙ ማገዝ ነው፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተመሠረተውን የፌዴሬሽን ግንኙነት ማፍረሱ በቀጣናው ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዘውዳዊውም […]

የደረጀ የሕክምና ሥርዓትና አቅርቦት ባለቸው የበለጸጉ አገሮች እና በወረርሽኙ በተጠቁት የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ለኢቦላ ሕሙማን የሚሰጠው ሕክምናና እንክብካቤ የውይይቱ ትኩረት ነው።

የሙከራ ሕክምናና ክትባቶች፤ በእስካሁኑ የበሽታው ሕክምና የሠሩና ያልሰመሩ ጥረቶች በተከታታይ ፕሮግራሙ ይቃኛሉ።

ዶ/ር ብስራት በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰርና የመድሃኒቶች መረጃ አገልግሎት ክፍል ዲሬክተር ናቸው።

አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት የአካባቢውን መሬት ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ነው።ኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል::
Image

ከታሰሩት መካከል አርሶ አደር ኪጣጣ ረጋሳ፣ ተማሪ ቶሎሳ ተሾመ፣ ድሬ ማሾ፣ ታሪኩ ቡልሾ፣ ያለው ባንቲ፣ ቢንያሳ ኢባ፣ ተስፋይ ቢይነሳ እና ነጋዴ መግስቱ ሞሲሳ ይገኙበታል።
እንዲሁም ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የጅምላ እስራቶች እየተከናወነ ነው። ብዙዎቹ በህጋዊ መንገድ የሚታገለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላት በመሆናቸው ብቻ መታሰራቸውን የሚገልጸው ሊጉ፣ በጅማ የድርጅቱ አመራሮች የሆኑት አቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድ፣ አቶ ሙሃመድ አሚን ካልፋና አቶ ነቢብ ጀማል ታስረው 2 አመት ከስድስት ወር እንደተፈረደባቸው ጠቅሷል።

ተፈጸመ ስለተባለው እስራት ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ተጠሪ አቶ በቀለ ነገአ ሰዎቹ በሃሰት እንደተፈረደባቸው አረጋግጠዋል። መሳሪያ የሌላቸውን ህገወጥ መሳሪያ ደብቃችሁዋል በሚል በሃሰት ተመስክሮባቸው መታሰራቸውን አቶ በቀለ አስረድተዋል

ከታሳሪዎች መካከል የአቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ለኢሳት እንደገለጹት ደግሞ ባለቤታቸው በሀሰት ተመስክሮባቸው ከታሰሩ ጀምሮ እርሳቸውም በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ከቤት ለመውጣት መቸገራቸውን ገልዋል። ወደ ጎረቤት ሄደው እሳት እንዳይጭሩ ከመከልከላቸውም ሌላ፣ ቤታቸው በደንጋይ የደበደባል። የባለቤታቸው ወንድም ተመሳሳይ ችግር ስላጋጠመው ስራውን ትቶ ወደ ከተማ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች መሞላቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
Minilik Salsawi Via ESAT

በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አየር ጤና በተለምዶ ሳሚ ካፌ በሚባለው አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ተሳፍራ ወደ ጦር ኃይሎች እየመጣች እንደነበር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ በመጓዝ ላይ የነበረችው ሟች ተማሪ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘች በኋላ መድረሷን ተናግራ ‹‹ወራጅ አለ›› ስትል፣ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አራት ወንዶችና ሾፌሩ ስለት በማውጣት አስፈራርተው እንዳገቷትም ተጠቁሟል፡፡

ሟች እንዳትናገር በማድረግ በሰዋራ ቦታ በታክሲው ውስጥ እንድታመሽ ከተደረገች በኋላ፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንደኛው ቤት ወስደው ለአምስት እየተፈራረቁ እንደደፈሯት ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ በራሱ ቤት ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲደፍራት እንደከረመም ምንጮቹ አክለዋል፡፡

ሁለተኛ ተጠርጣሪ ነው የተባለው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደጋጋሚ ሲደፍራት ከከረመ በኋላ፣ ከቤት አውጥቶ ጭር ባለ ቦታ ጥሏት መገኘቷንም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

ሟች ከፍተኛ የሆነ የማሕፀንና የፊንጢጣ ጉዳት አጋጥሟት ስለነበር በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና ያደረገች ቢሆንም፣ በደረሰባት ከባድ ጉዳት በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመታከም ላይ እያለች ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሟች በመሀል በአንደኛው ተጠርጣሪ ስልክ ወደ ቅርብ ጓደኛዋ በመደወል ስልኩን በመዝጋቷ ጓደኛዋ የደወለችበትን ስልክ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች፡፡

የሟች ቤተሰቦች የሞባይሉን ቁጥር ለፖሊስ አሳልፈው በመስጠታቸው ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ የክትትል ሥራ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርበው በወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሠረት የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

Reporter
Image

ማእከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ውስጥ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ባለፈው አንድ አመት ተመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ብቻ በ 10 ሺህ የሚገመቱ ሕጻናት በታጣቂ ቡድኖች ለውትድርና ተመልምለዋል።

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የአውሮጳ ህብረት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በምሥራቅ ዩክሬይን ዓማፅያን አንፃር አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማሙ። የህብረቱ ዲፕሎማቲክ ክፍል በዚህ በተያዘው የህዳር ወር መጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት አንድ የዩክሬይንን ዓማፅያን ዒላማ ያደረገ አዲስ ዝርዝር እንዲያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ጠይቀዋል።

ኩፍኝን ከዓለም ፈፅሞ ለማጥፋት የሚደረገዉ ጥረት መሻሻል አለማሳየቱን የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈዉ ሳምንት ይፋ አድርጓል። በምክንያትነት ከተጠቀሱት የበሽታዉ ከሰዉ ወደሰዉ ፈጥኖ የመተላለፍ ባህሪ አንዱ ሲሆን የክትባት አለመዳረስም ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።

ከመስከረም ወር አጋማሽ አንስቶ በቻይናዋራስ-ገዝግዛትሆንግኮንግ የተጀመረው የተቃዉሞ ሠልፍ እና አድማ አልተጠናቀቀም። አሁንም ሰልፈኞቹ የፋይናንስ ቦታዎችን ይዘው ይገኛሉ። ይሁንና ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ የተወሰኑ ቦታዎችን ከሰልፈኞች አስለቅቋል።

በየእሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃትእየሩሳሌም ውስጥ የተነሳው ብጥብጥ ይበልጥ ከሯል። ዛሬ ዳግም አዲስ ጥቃት ከተማዋን አናግቷል። ይህም በአይሁዳውያን ቤተ ፀሎት ላይ ነው። በዚህም ጥቃት 6 ሰዎች ሰዎች ተገድለዋል። ሁለት ጥቃት አድራሾች እና አራት ሲቪሎች።


‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ› የተሰኘውን መጽሐፍ በተመለከተ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ(እድሜያቸውን ያርዝምና) ከመልካም ሐተታ ጋር አዘጋጅተውታል፡፡ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ማን ጻፈው? ዘርአ ያዕቆብ ማነው? ትውልዱስ የት ነው? ፍልስፍናው ከየት መጣ? እውነት ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ የውጭ ሰው? ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ ለመከራከር በመጽሐፉ ውስጥ ማስረጃዎች አሉን? የሚሉትንና ሌሎች ጥያቄዎችን አንሥተው ይተነትናሉ፡፡ መጽሐፉንም ተርጉመውና አትተው አቅርበውታል፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ተጫኑና በነጻ አንብቡት፡፡

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል። አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት …

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማጅራት ገትር ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ኣመት ክልል ላሉ ዜጎች ክትባት የመስጠት ሒደት የተከናወነ ቢሆንም አፈጻጸሙ ከተጠበቀው ውጪ ሆኖአል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከ29 ዓመት በላይ መከተብ አያስፈልጋቸውም፣ ከተከተቡ የጎንዮሽ ችግር ያመጣባቸዋል መባሉ ግማሽ ያህል የህብረተሰብ ክፍል ቢሞትም ግድ የለንም እንደማለት ተደርጎ …

የሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፡፡ በሀገራችን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የተባለው ተረት ዕድሜው እጅግ ረጅም ነው፡፡ የሥርዓቶቻችንን ያህል አርጅቷል፡፡ በተግባር ሲተረጐም ግን ገና ዛሬ የተወለደ ነው የሚመስለው፡፡ በየቢሮው፣ በየማህበሩ፣ በየፓርቲው የምናየው ሀቅ ነው፡፡ “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ”፣ “እከክልኝ ልከክልህም” አብሮ ሲተረት የኖረ ነው፡፡ ማናቸውም ዕቅድና ስትራቴጂ ህዝብ […]

በቅርቡ የሚከተለውን ጽፌ ነበር፡ “አገር ቤት ላሉ ተቃዋሚዎች ደግሞ የሚከተለዉን መልእክት አስተላልፋለሁ። የምርጫ ፓርቲ ናችሁ። ነገር ግን በባዶ እግራችሁ ብስክሌት ከያዘ ጋር እንወዳደራለን ብሎ መነሳት፣ ራሳችሁን ከማስገመት በተጨማሪም ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ብቻ ነው የምትሆኑት። ምርጫ የምትሳተፉ ከሆነ፣ የምርጫ ዘመቻ ማድረግ አለባችሁ። ምርጫው ሰባት ወራት ነው የቀሩት። በሚቀጥለው አንድ ወራት ዉስጥ አገዛዙ ነገሮችን ካላስተካከለ […]

የሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፡፡
Minilik Salsawi

በሀገራችን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የተባለው ተረት ዕድሜው እጅግ ረጅም ነው፡፡ የሥርዓቶቻችንን ያህል አርጅቷል፡፡ በተግባር ሲተረጐም ግን ገና ዛሬ የተወለደ ነው የሚመስለው፡፡ በየቢሮው፣ በየማህበሩ፣ በየፓርቲው የምናየው ሀቅ ነው፡፡ “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ”፣ “እከክልኝ ልከክልህም” አብሮ ሲተረት የኖረ ነው፡፡ ማናቸውም ዕቅድና ስትራቴጂ ህዝብ ኑሮ ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ማለት የእርስ በርስ ሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፣ ማለት ነው፡፡

ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ የህዝብን የኑሮ ደረጃ ዝቅ ብሎ ወርዶ የሚያይ መሪ፣ አለቃ፣ ኃላፊ ማግኘት መታደል ነው፡፡ ያስቀናል፡፡ የዋጋ መናርና የታክስ ማሻቀብ አንድን ማህበረሰብ የጦርነትን ያህል ያጠፋዋል፡፡ ለዚህ ነው መሪዎች ሁሉ የህዝባቸውን ኑሮ በቅርብ ያስተውሉ የሚባለው፡፡ ህዝብ የሀገር ሙቀት መለኪያ ነው፡፡ ህዝብ የሚከፍለው ግብር ከሚያገኘው አገልግሎት ጋር ካልተመጣጠነ የቀዘቀዘች አገር ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነት እና በገሃድ የሚታየው ህዝብ ደሞዙ ከሚኖረው ኑሮ ጋር ስለማይመጣጠን ኖረ አይባልም፡፡ ህዝብ ከዕለት ዕለት ህይወት እየከበደው በመሄዱ ከሳቁ ምሬቱ፣ ከደስታው ሐዘኑ እየበረታ ሥርዓቱን፣ አገዛዙን፣ ገዢዎቹን፣ አስተዳዳሪዎቹን እጅግ ጠልቷቸዋል፡፡ ሀገሩም የእሱ አትመስለውም፡፡ ህዝብ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ለማግኘት ነግ-ሠርክ መሰለፉ ፤ አልፎ ተርፎም ከናካቴው ዕጥረት የሚከሰትበት ሁኔታ፣ ብሶቱ ወሰን የለውም በብሶት ተሞልቷል፡፡ ህዝብ በመኖሪያ ቤት ችግር እየተሰቃየ ሲሆን መሰረታዊ የኑሮ አስፈላጊ ነገር ጎሎበታል ፡፡

ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ይህንን የሚገልፅበት መንገድ እንዳያገኝና በፍርሃት ተሸማቆ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ “አዲስ ያይጥ – ወጥመድ በሰራህ ቁጥር” አዲስ አይጥ የምትወለድ ከሆነ፣ ወይ ወጥመዷ ላይ ወይ አጥማጁ ላይ ችግር አለ ማለት ነው” ይባላል፡፡ በሙስና የተሞላ ልማት ዘርዛራ ወንፊት ነው፡፡ ዕብቁንም፤ እንክርዳዱንም፤ እያሳለፈ፤ እያዩ እህል አለን እንደሚሉት አይነት የዋህነት ይሆናል፡፡ የዚህ ሁሉ መጨረሻው ድህነት ነው፡፡ ድህነት ሲመጣ ቃላት ይበዛል። ስብሰባ፣ ንግግር፣ የማይተገበር ቃል – መግባት እንደህይወት ይወሰዳል፡፡ እንደኑሮ ይለመዳል፡፡ይህ በወያኔዎች በተግባር እያየነው ያለው ሃቅ ነው::

ሃገራችን እና ወገናችን በጨለማ ውስጥ እየዳከረ ባለበት በዚህ የወያኔ አገዛዝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በመረባረብ የዜግነት ግዴታውን አውቆ ለህዝቦች መብት እና ነጻነት መታገል አለበን። ሃገሪቷ በዚህ አደጋ ውስጥ ባለችበት ሰአት ላይ ህዝብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለኑሮ ውድነት ለሞት ለስደት እየተዳረገ ኢትዮጵያዊነት እየተዋረደ ከመሆኑም ባሻገር ሃገሪቷን ወደ ፍርስራሽነት ለመቀየር የሚሮጡ ጥቂት ሆዳሞች ባሉበት ልንቀብራቸው ይገባል።

የግብፅ መንግሥታት፣ ደካማ ኢትዮጵያን ለማየት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የኤርትራ ነፃነት ግንባሮችን መልምለው፣ አሠልጥነውና አስታጥቀው በኢትዮጵያ ላይ አዘመቱ፡፡ የኤርትራ ግንባሮች በበኩላቸው ጦርነቱ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲዳረስ ለማድረግ የተጠቀሙበት መንገድ የብሔረሰብ ንቅናቄዎችን መፍጠር እንዲሁም ሌሎች የእነሱን አርዓያ ተከትለው እንዲቋቋሙ ማገዝ ነው፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተመሠረተውን የፌዴሬሽን ግንኙነት ማፍረሱ በቀጣናው ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዘውዳዊውም […]

በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር።

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር።

ቅዳሜለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኘው አርሊንግተን ቨርጂኒያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገራቸው ተቋማዊ አስተዳድር ባልተጠናከረበት መልኩ፤ ማህበረሰቦች ሊጫወቱት የሚገባቸው ሚና፣ እንዲሁም እርስ በርስ የመተባበር ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።

የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን…

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር : በትናንትናው ዕለት ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰብሰባ ጠርቶ በገዥው ፓርቲ ደህንነቶችና ፖሊስ የተበተነበት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የኢትዮጵያ ችግር ከአንድ ፓርቲ አቅም በላይ በመሆኑ በትብብሩ ምስረታ ወቅት የነበሩትንና ሌሎቹም ፓርቲዎች ትብብሩን በመቀላቀል የተቃውሞ ጎራውን እንዲያጠናክሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መግለጫው አክሎም አገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውንና የዜግነት ክብራቸውን ለማስመለስ በቀጣይነት ለሚደረገው ሰላማዊ ትግል ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት በጋራ ‹‹በቃን›› ብለው እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በአንጻሩ የፖሊስ ኃይልና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት በገዥው ፓርቲ ሴራ ተጠልፈው ከሰላማዊ ዜጎች ጋር እንዳይጋጩና ህገ መንግስቱንም እንዲያከብሩ እንዲሁም ገዥው ፓርቲም ካለበት ፍርሃትና ስጋት ወጥቶ ለለውጥ ዝግጁ እንዲሆን ትብብሩ አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል ‹‹በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውለው ገዥውን ፓርቲ ከማገልገል አልፈው በሰላማዊ ትግል የፖለቲካ ኃይሎች ላይ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ›› እንደሚነዙ ያስታወሰው ትብብሩ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ስላደረጉት አወንታዊ አስተዋጽኦ አመስግኗል፡፡ በቀጣይም ለህዝብ በመወገን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡