መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እድለኞቹ በአስተዳደሩ አታላይ ፕሮፖጋንዳ ማዘናቸውን ገልጰዋል። አስተዳደሩ ምርጫ 2007 ተከትሎ ከ32ሺ በላይ ቤቶች ላይ እጣ በመጋቢት ወር 2007 ያወጣ ሲሆን ቤቶቹንም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከማስረከብ አልፎ ቀጣዩን እጣ በሰኔ ወር 2007 እንደሚያወጣ ቃል ቢገባም አንዱንም መፈጰም ሳይችል ቀርቶአል። አስተዳደሩ የካርታ ስራ እንዳዘገየው ቢናገርም እውነቱ ግን ቤቶቹ …

መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንጋፋው ድምጸዊ አለማየሁ እሸቴ ደግሞ የህይወት ዘመን ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። ከለ380 በላይ ሙዚቃዎችን የሰራው ድምፃዊ ኣለማየሁ አሸቴ ከ ዘመናዊ ሙዚቃ ፋናወጊው ከግርማ በየነ እጅ ሽልማቱን ከተረከበ በሁዋላ ባደረገው ንግግር ፦“ምናለ ጊዜን መመለስ ብችል እና ካለፉት ጓደኞቼ ጋር ይህን ቀን ባከብረው” በማለት ብዙዎችን ስሜት ውስጥ አስገብቷል። አርቲስት …

መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራችን አትሌቲክስ ስፖርት ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳውና ለብዙ ሯጮች የችግራቸው ተጋሪ በመሆን አገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት የቀስተደመና ስፖንጅ ፋብሪካ መስራች እና ባለቤት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ በተወለዱ በ79 ዓመታቸው ሀሙስ መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ አቤሴሎም የቀብር ስነስርዓት ቤተሰቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት …

መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ገዢው ፓርቲ የሚያደርስበትን ተደጋጋሚ አፈና ተቋቁሙ ተጨማሪ የስርጭት መስመር የከፈተ ሲሆን ስርጭቱን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በሚከታተለው ናይል ሳት ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚቻል አስተዳደሩ አስታውቋል። የአዲሱ ስርጭት ሙከራ እንደተሳካ ዝርዝር መረጃውን የምናቀርብ መሆኑን ለመግልጽ እንወዳለን።

መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁለት ጎራ ተከፍለው ሲወዛገቡ የቆዩት የአፋር ክልል ባለስልጣናት ፣ የህወሃት ድጋፍ ያለው አቶ ስዩም አወልና የአቶ አሊ ሴሮ ቡድን በአሸናፊነት ከወጣ በሁዋላ፣ ላለፉት 20 አመታት የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ሃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ስዩም አወል አሁን ከያዘው ስልጣን በተጨማሪ የክልሉ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል። በተቃራኒ ጎራ የተሰለፈውና የተማረውን …

መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ቀበሌዎችን ወደ ዋናዋ ከተማ የሚጠቀልለው አዲሱ ማስተር ፕላን ወይም ፍኖተ ካርታ፣ አርሶደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ለጥቂት የዘመኑ ባለሃብቶች ለመስጠት ተብሎ የተዘጋጀ ነው በማለት ተቃውሞ ያሰሙ የኦሮሞ ወጣቶች መገደላቸውንና መታሰራቸውን ተከትሎ፣ ለአንድ አመት ያክል ከመጽደቅ እንዲዘገይ የተደረው እቅድ እንደገና ለማጸደቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ የኢህዴድ …

መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ውስጥ በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ በዓመት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በወባ በሽታ የሚጠቁ ሲሆን በአዲሱ ዓመት ብቻ ከሰባ ስምንት በላይ አዳዲስ ግድቦች በመሰራታቸው ተጨማሪ ሃምሳ ስድስት ሽህ የወባ ተጠቂዎች እንደሚኖሩ ጥናቱ ጠቁሟል። የውሃ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 19 ፣ 2008) በአለማችን የደህንነት ስጋት ይታይባቸዋል ተብለው ከተፈረጁት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ 42ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናት ያካሄደ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጠ። የዘንድሮውን አመታዊ ረፖርት ይፋ ያደረገው ጋሉፕ አናሊቲክስ የተሰኘውና በአለም አቀፍ ህግና ስርኦቶች መከበር ዙሪያ የሚሰራው ተቋም በ 141 የአለማችን ሃገራት ላይ በተካሄደው ጥናት ኢትዮጵያ 42ኛ ደረጃ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 19 ፣ 2008) የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ካለው 30ኛ ጉባኤ ጋር ተያይዞ በተጠራ መድረክ ላይ የተጋበዙት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ስብሰባ ረግጠው ወጡ። ስኞ እለት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት በተመለከተ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙትና በኋላ በቀረበው ሪፖርት ሳይደሰቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ወደ ስብሰባው አልተመለሱም። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት …

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶችና መንግስት በጋራ በፈረንጆች አቆጣጠር ሴፕቴምበር 24 ፣ 2015 ያደረጉት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እንደሚያስረዳው ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች እጅግ አሳሳቢ የሆነ የውሃና የምግብ እጥረት ተከስቷል። ችግሩም በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚጨምር ለኢሳት የደረሰው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል። በተለይ በሶማሊ ክልል ባለው …

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስካሁን 13 ሰዎች እንደሞቱ ቢገልጽም፣ የመጨረሻው መረጃ ይፋ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊልቅ ይችላል። ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሼህ አህመድ ከሳውድ አረቢያ እንደገለጹት፣ 13 ቱ ሟቾች የተለዩት ዘመዶቻቸው ባረጋገጡት መሰረት ነው። የሳውዲ መንግስት የሟቾችን ቁጥር ሙሉ በሙሉ ለማሳወቅ እንዳልቻለ የገለጹት ሼህ …

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ የስደተኞች ቢሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ በመግባታቸው ክስ ከቀረበባቸውና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ሃያ ስድስት የውጭ አገር ዜጎችን ወደየትውልድ አገራቸው መመለሱን አስታውቆ፣ ከእነዚህ መካከል 16ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ከኬንያ ጀምሮ ባሉት የመሸጋገሪያ አገራት ውስጥ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስርቤትና በታጋቾች በደልና ስቃይ እየደረሰባቸው ሲሆን …

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ገጠር መንገድ ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባደረገው አመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ ላይ ችግሩ አለመቀረፉን የገለጹት ባለሙያዎችና የድርጅቱ ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የሚያሳማው የጥራቱ ጉዳይ መሆኑን ተናገረዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁልጊዜ ሊያሻሽለው አልቻለም በማለት ባለሙያዎች ያቀረቡት የጥራት ጉዳይ መንገዶች ጥገና ተደርጎላቸው ከተሰሩ በኋላም ተገቢውን ጊዜ አገልግሎት …

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ ገዥው ፓርቲ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን አጋልጡ በሚል ከፍተኛ ግፊት ማድረጉን ተከትሎ ትርምስ መፈጠሩ ተሰማ፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑን መሪዎች ጨምሮ አንዳንድ ጋዜጠኞች በሙስናና ብልሹ አሠራር የሚጠረጠሩ መሆናቸው ይበልጥ ነገሩን አወሳስቦታል፡፡ ኢህአዴግ በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ …

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት ነባር ታጋይና በሁዋላም የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አብዴፓን) መስርተው ክልሉን ላለፉት 24 ዓመታት ሲመሩት የቆዩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ፣ ከስልጣን ተነስተው ወደ ፌደራል ሲዛወሩ እርሳቸውን ለመተካት በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ፣ ህወሃት የደገፋቸው ቡድኖች አሸናፊዎች ሆነው መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ቀድም ብለው ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ወጣቱ …

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኤልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕፃናትን ጨምሮ ከ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑንና አፋጣኝ የሆነ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአውስትራሊያው ቻይልድ ፈንድ በሪፖርቱ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ያለው የርሃብ ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና በተለይ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች …

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ፍሽስት ወረራ ወቅት ለተፈጸሙት ዘግናኝ ግፎች የጣሊያን መንግስትና ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁና የተዘረፉት ቅርሶችና ንብረቶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ዓለምአቀፍ ሕብረት ለፍትሕ ጥያቄውን አቀረበ። በጣሊያን ወረራ ወቅት የጣሊያን ወራሪዎች በዓለም ላይ የተከለከለውን ካለስተር ቦንብ ተጠቅመው ንፁሃን …

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግር በማጋለጥ እንዲሁም የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ፣ በየመን የጸጥታ ሃይሎች መታሰሩ ታውቋል። ጋዜጠኛ ግሩም በምን ምክንያት እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም። ኢሳት ባለቤቱን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። በየመን በመካሄድ ላይ ያለውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ …

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትርፋማነቱ በተለያዩ አለማቀፍ የንግድ ተቋማት እየተመሰገነ ቢመጣም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ” ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ክሶችን እያቀረቡ ነው። አየር መንገዱ ጀምሮት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ የታደጉት አቶ ግርማ ዋቄ ስራቸውን ከለቀቁ በሁዋላ፣ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ …

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ የነበረው ኢህአዴግ የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የቤት ፈላጊዎችን በማህበር ካደራጀ በሗላ ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ እንዲቆጥቡ በማድረግ ከ9 ዓመታት በሗላ የቤት መስሪያ ቦታቸውን ለቤት ሰሪዎች ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ ቤቱን መስራት የሚችሉት መንግስት ባወጣላቸው …

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለአዲስ አመት ዋዜማ በላፍቶ ሊያዘጋጀው የነበረው ኮንሰርት በመሰረዙ በአድናቂዎቹ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ ሳይረሳ ፣ አሁን ደግሞ ለመስቀል በአል ያዘጋጀው ኮንሰርት በድጋሚ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳይካሄድ መከልከሉን የፎርቺን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል። የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቶ ፈለቀ ነጋሽ የ አዲስ …

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን እንዳስታወቁት ወታደሮቺ የሚላኩት አልሸባብን እየተዋጉ ላሉት የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ድጋፍ ለመስጠት ነው። በመሆኑም እስከ 70 የሚደርሱ የ እንግሊዝ ወታደሮች በቅርቡ የሰላም አስከባሪ ልኡኩን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ብሪታኒያ ከዚህም በተጨማሪ እስከ 300 የሚደርሱ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን እንደምታሰፍር የቢቢሲ ዘገባ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) በማላዊ እስር ቤቶችን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ 36 ህጻናትን ጨምሮ 387 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው ለመመለስ ከአሜሪካ መንግስት በኩል ድጋፍ መገኘቱን የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) ዛሬ አርብ ገለጠ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የዘጠኝ ወራት የእስር ቅጣት ቢያጠናቅቁም ወደኢትዮጵያ የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ በእስር …

ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። ሰሞኑን በግብፅ መገናኛ ብዙሃን በግድቡ የውሃ መሙላት ሂደት በግብፅ ላይ የውኋ እጥረት ተፈጥሯል ሲሉ ላቀረቡት ዘገባ ምላሽን የሰጡት የሃገሪቱ ባለስልጣናት፣ በሳተላይት ቴክኖሎጂ በደተረገ ክትትል ግድቡን በውሃ የመሙላት ስራ እንዳልተጀመረ ሊረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። በግብፅ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ …

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል። በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል …

ኢሳት ዜና (መስከረም 13, 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለምግብ እርዳታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥርና የእርዳታ መጠን በቀጣዮቹ አራት ወራቶች በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን አካባቢ እንደነበር ያወሳው ድርጀቱ፣ የተረጂዎችን ቁጥር ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀመሮ ጭማሪን እንደሚያሳይ ገልጿል። በፈረንጆቹ አዲስ አመት ባሉ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በአል ለ1 ሺ 436ኛ ጊዜ በኢትዮጵያና በመላው አለም ተከብሯል። በሳውድ አረቢያ መካ በአሉን ለማክበር በስፍራው ከተገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሃይማኖቱ ተከታዮች መካከል ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተረጋገጥተው ህይወታቸው አልፎአል። ከ900 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሰንአ በአንድ መስኪድ ላይ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመሰጠቱ ፣ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ በመቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤ ግንባሩን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩን የገለጸ ቢሆንም፣ አሁንም ድርጅቱን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ፣ ግንባሩ የመልቀቂያ ጥያቄን እንደማያስተናግድ አስታውቋል። ድርጅቱን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ አባላት አርፈው እንዲቀመጡ ተነግሯቸዋል። ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ …

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 4ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ የወሰደው የከተማዋ አስተዳደር በአስር ክፍለ ከተሞች ሹምሽር አካሄዷል። ከቀናት በፊት በተጀመረው በዚሁ ሹም ሽር በ116 ወረዳዎች የሚገኙ ከ100 በላይ አመራሮች የተነሱ ሲሆን የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቱ ከትምህርት ብቃት ጋር የተገናኘ እንደሆነ መግለፁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሃ ሃገራት ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 90% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ከአፍሪካ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ሽፋን ያላት ኢትዮጵያም በአለም በአገልግሎቱ አሳሳቢ ተብለው ከተፈረጁ አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ድርጅቱ በአመታዊ ረፖርቱ ገልጿል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክና፣ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ከኢትዮጵያ የሚደረገውን ከፍተኛ የወጣቶች ስደት ተከትሎ የአውሮፓ ህበረት ልዩ የሉዑካን ቡድን በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ወደአዲስ አበባ መጓዙን ህብረቱ ዛሬ ረቡዕ ገለጠ። በሃገሪቱ የሶስት ቀን ቆይታ የሚኖረው ይኸው የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው የወጣቶች ስደት እና ችግሩ በሚቀንስበት ዙሪያ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሰፊ ምክክር ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአለም አቀፉ የስደተኞች …

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ከፍተኛ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮችን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ዛሬ ረቡዕ ከሃላፊነታቸው አነሳ። የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ እንዲሁም ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና፣ አቶ አበበ ጥላሁን ከባንኩ አመራርነት መነሳታቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ህብረት …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ ከ95 ሺህ በላይ ተሿሚ፣ ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች ሐብት ኮምሽኑ መመዝገቡን፣ እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ሐብት አስመዝጋቢዎች የቤተሰቦቻቸውን ሐብት አሳውቀው ማስመዝገባቸውን አረጋግጠዋል፡፡ «ይህ መረጃ ለምን ይፋ አይደረግም» ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ግዴታ እንደሌለባቸው በመግለጽ …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ እየታሸጉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማው አስተዳደር ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና …

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት እልባት ባያገኝም፣ በደቡብ ክልል እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡ ለሻሂ የሚሆን ስኳር ማግኘት አለመቻሉን እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ግን በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት የቡድን መሪ የሆኑ ነጋዴዎች፣ መንግስት የሚያከፋፍለውን ስኳር፣ እየጫኑ ወደ አልታወቀ ቦታ …

ኢሳት ዜና (መስከረም 11፣ 2008) የኢትዮጵያ የሐገር መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ በ23 መንግስታዊ ተቋማት ላይ ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ። የፌደራል የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱለይማን ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ፣ የሀገር መከላከያ ሚኒስቲር ህግን ባልተከተለ መንገድ የ 2 ሚሊየን ዶላር ግዢ መፈጸሙን አመልክተዋል ። በዚህ የሀገሪቱ ወታደራዊ ተቋም ህግን ባልተከተለ መንገድ ተፈጸመ የተባለውን ግዢ በተመለከተ …

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መንግስት የአለም ባንክ የቋንቋ አስተርጓሚውን ፓስተር ኦሞት አግዋን ጨምሮ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኦማር ሆጀሌ የተባሉ ለጋምቤላ ህዝብ መብት መከበር የሚታገሉ ሰዎች የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ለስብሰባ ወደ ናይኖቢ ኬንያ ሲያመሩ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ መያዛቸውን በመጥቀስ፣ ግለሰቦቹ የቀረበባቸው የሽብረተኝነት ክስ ውድቅ ሆኖ በአፋጣኝ እንዲፈቱ …

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ረሃብ ተከትሎ በርካታ ዜጎች ወደ ከተማ እየፈለሱ ሲሆን፣ እርዳታ ማግኘት ባለመቻላቸው ጎዳና ላይ ማደር መጀመራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያሰማሩዋቸው ባለሙያዎች በዞኑ 80 ሺ ህዝብ መራቡን ሪፖርት ሲያደርጉ፣ የዞኑ የመንግስት ባለስልጣናት በተቀራኒው በዞናቸው ምንም የተራበ ሰው …

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢህዴግ ድርጅት ጽ/ቤት ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ዙሪያ በከተማው 10 ክ/ከተሞች በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎችን በሚያወያይበት መድረክ ፣ ነዋሪዎች አወያይ ካድሬዎችን ያስደነገጡ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ የ10 ወረዳዎችን የህብረተሰብ ክፍል በያዘው የወረዳ 9 አዳራሽ በርካታ ጥያቄዎች …

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመኪና አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ የሰዎችን ሕይወት ቀጣፊ ከሆነባቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ አገር መሆኗን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ገልጿል።ድርጅቱ ከመቶ ሺህ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 3 ሺ 874 ሰዎች ለሞት እንደሚጋለጡና 80 % የሚሆነው የአደጋው ምንጭ የአሽከርካሪዎች ጥፋት ሲሆን፣ የተቀረው 20 በመቶ ደግሞ በመንገድ ችግሮች መሆኑን …

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለከተማ ቤቶች መስሪያ፣ ለልማት ወይም ህገወጥ ግንባታ በሚል አርሶ አደሮች ያለምንም ክፍያ ከይዞታ መሬታቸው እየተፈናቀሉ ማህበራዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በኦሮምያ ክልል በ አዳማ ከተማ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች ቦታቸውን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ በርካታ ቤቶችም …

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ቀድም ብሎ 60 ሰዎች መገደላቸውን ከጠቀሰ በሁዋላ፣ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ 126 ሰዎች በወረዳ አመራሮች ትእዛዝ መገደላቸውን ጠቅሷል። በማዣንግ፣ ጎደሬና ሚጤ በሃላፊነት ላይ የነበሩ የወረዳ አመራሮች ” ደገኞች ቦታችንን ለቀው ይውጡ፣ ደገኞች በማዣንግ ዞን ውስጥ የያዙትን የእርሻና የቡና ተክል መሬት ለማዣንግ …

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ዓርብ መስከረም 7/2008 ዓ.ም በድንገት በጠራው የተቋራጮች ስብሰባ፣ በክልሉ የሚገነቡ የጤና ተቋማትን በመስራት ላይ ያሉ ተቋራጮች በሙሉ ሰብስቦ ፤የግንባታ ስራዎች በመጓተታቸው ምክንያት ከልዩ ልዩ ግብረ ሰናይ መንግስታት የተገኘ የዕርዳታ ገንዘብ በየጊዜው ተመላሽ መሆኑ ቢሮውን አሳስቦታ ብሏል። ተቋራጮች በተቻላቸው ፍጥነት ግንባታቸውን በማጠናቀቅ በዕርዳታ …