ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን በማነጋገር እንደገለጸው፣ በአድማው የተሳተፉትን ሹፌሮችን ወደ እስር ቤት የወሰዱ ሲሆን፣ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ጫና በመፍራት ስራ እንጀምራለን ያሉት ደግሞ 500 ብር ቅጣት ካልከፈሉ እንደማይጀምሩ ተነግሯቸዋል። ከፖሊስ የሚደርሰውን ወከባ በመፍራት ብዙ ሹፈሮች አሁንም ራሳቸውን ደብቀዋል። አንድ የባጃጅ ባለሃብት መንግስት ለምን አድማ አደረጋችሁ በሚል እየተበቀለ ነው ብለዋል።

ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያዋ የድንበር ከተማ ሜሩ ኢዞሎ አቅራቢያ በቦረና እና ሜሩ ጎሳዎች መሃከል በተቀሰቀሰ ግጭት አስር የአካባቢው ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የከተማው አሽከርካሪዎች ግጭቱ እጅግ አስፈሪ እንደነበርና ሁኔታዎቹ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጸው የሜሩ ብሔር አባላት ወደ ከተማቸው የሸሹ ሲሆን የቦረና ጎሳ አባላትም …

ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናት ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት7 አባሎች በሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ ውስጥ ገብተዋል በሚል የፖሊስ አባላት በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ሲያድኑ ከዋሉ በሁዋላ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። በአካባቢው ሰሞኑን በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመ የተባለ ጥቃትና ወጣቱን የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ለአሰሳው ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎች …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደሚሉት ከድርቁ ጋር ተያይዞ የውሃ ችግሩ በመባባሱ ፣ ህዝቡ ውሃ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። የውሃ ችግሩ በመባባሱና በየአካባቢው የሚታየው የውሃ ጀሪካም ብዛት ” ሳምንቱን ” ቢጫው ሳምንት” አስብሎታል በማለት ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የውሃ ችግሩ ከሰቆጣ በተጨማሪ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ክልሉን እመራዋለሁ የሚለው …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአርባምንጭ ምንጮች እንደተናገሩት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ኢህአዴግን የሚያወግዙና ወጣቱ ለመብቱ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ከበተኑ በሁዋላ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች በጅምላ ለማሰር ከትናንት ጀምሮ አሰሳ አካሂደዋል። አሰሳውን ተከትሎ የ70 አመት አዛውንት እናትን ጨምሮ ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የሰማያዊ …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኑዌር ዞን ዋና ከተማ ከሆነቸው ንያንግ 30 ኪሜ ራቅ ብሎ በሚገኘው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው አንዱራ የአነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ሲፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ሰራተኛ የሆኑት ኢንጂር ሙሉጌታ ደሳለኝ እና የጋምቤላ የእርሻ ቢሮ ሰራተኛ የነበሩት ወ/ሮ ሃይማኖት ተገድለዋል። …

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ምንዳዬ ጥላሁን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ ፍርድ ቤቱ ለተለያዩ አካላት ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በድጋሜ ደብዳቤ ጽፈዋል። ቃሊቲ እስር ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ቃሊቲ አለመታሰራቸውን ጥቅምት 12 ፣ 2008 ዓም …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ገዳሪፍ አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ውጊያ 16 ሱዳናዊያን መገደላቸውን፣ 12 መቁሰላቸውን እንዲሁም 7ቱ ታግተው መወሰዳቸውንና የደረሱበት እንደማይታወቅ ከ300 በላይ የቁም ከብቶችም መዘረፉን የቀድሞው የአገሪቱ ጦር አዛዥና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ለፓርላማ ሪፖርት አቅርበዋል። ኢስማት አብዱረሕማን ” ሽፍቶች” ያሉዋቸው መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የኢትዮጵያ አርሶ …

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ “የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ” በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር …

Prof. Merara Gudina
የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው። መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያተ ውሃ ያማያነሳ ነው ያሉት አቶ ሃይለማርያም ፣ ፓርቲዎቹ ያልተሳተፉት በሕጋዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት አይደለም በማለት መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ከየትኛው መንግስት ጋር እንደሚወያዩ እናያለን ሲሉ ዝተዋል፡፡

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሽመልስ ፣ አቶ በረከት ስምኦን ከኮምኒኬሽን ሚኒስትርነት ተነስተው በአቶ ሬድዋን ሁሴን ከተተኩበት ካለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ከአቶ ሬድዋን ጋር መስማማት ባለመቻላቸው በስራ ገበታቸው ላይ የሚገኙት አልፎ አልፎ ነበር፡፡ የሁለቱ ሚኒስትሮች አለመግባባት በኢሳት ከቀረበ በኃላ ችግር የለብንም ለማለት ለአንድ ቀን አብረው መግለጫ በመስጠት ጎን ለጎን …

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ብአዴን ወጪውን የሚሸፍነው በዋነኝነት ከነጋዴዎችና ከነዋሪዎች ነው። በርካታ የክልሉ ነጋዴዎች ገንዘብ እንዲለግሱ የጥሪ ወረቀት ደርሶአቸዋል። ድርጅቱ ከህወሃትና ከኦህዴድ ባላነሰ መልኩ በአሉን እንደሚያደርግ እየገለጸ ሲሆን፣ አገሪቱ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ አንዣቦባት ባለበት እንዲሁም የኑሮ ውድነቱ የህዝቡን ኑሮ ፈተና ውስጥ በጣለበት ሰአት ይህን ያክል ገንዘብ ህዝቡን …

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መነሻቸውን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻዎች በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ሕይወታቸውን ለአደጋ አልጋልጠው በጦርነት ሰላሟ ወደራቃት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ቁጥር መጨመሩን ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት በምህጻረ ቃል /UNHCR/ አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ብቻ ከ70 ሺ በላይ አዲስ ስደተኞች የመን መግባታቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ ጥቂት የሶማሊያ ዜጎች ሲገኙበት አብዛኞቹ ስደተኞች ኢትዮጵያዊያን ናቸው። …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ አምሳሉ ተሾመ የተባለው ታጋይ ሰዎችን በመመልመል ወደ በረሃ ተልካለህ ተብሎ በመጠርጠሩ፣ ፖሊሶች ሊይዙት ሲሞክሩ፣ እጄን አልሰጥም በማለት በያዘው ሽጉጥ አንድ የመቶ እልቅና ያለው መኮንንና ሌላ አንድ ተራ ፖሊስን በመግደል፣ እንዲሁም 4 ታጣቂዎች በማቁሰል በመጨረሻም በያዘው ሽጉጥ ራሱን አጥፍቷል። ወጣቱ …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድቡብና ጋምቤላ የድንበር ከተማ በሆነቸው ቴፒ ራሳቸውን ያደራጁ ወጣቶች በመልካም አስተዳደርና ህዝቡን አፍኖ በመግዛት ለስቃይ ዳርገውታል ባሉዋቸው የመንግስት ታጣቂዎች እና ሹማምንት ላይ የሚያደርሱትን የሃይል ጥቃት መቆጣጠር እየተሳነው የመጣው መንግስት ካለፈው አርብ ጀምሮ፣ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ጥቃቱን በማስፋት ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ሰንብቷል። የመንግስት ታጣቂዎች፣ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች ሰብረው …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት 3 ያህል እስረኞች ማምለጣቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ እስረኞቹ በተለምዶ ሰባራ ባቡር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ፍርድ ቤት ፊት ለፊት አስፓልቱ ላይ ከመኪና ወርደው ወደ ፍርድ ቤቱ በሚገቡበት ወቅት መጥፋታቸውን የአይን እማኞች …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊጉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ለኬንያ መንግስት የ131 የኦሮሞ ተወላጆችን ስም በመዘርዘር በሽብረተኝነት የሚፈለጉ በመሆኑ ተላልፈው እንዲሰጡት ጠይቋል። በቅርቡ ኬንያ ውስጥ የደረሱበት ያልታወቁት የ80 አመት አዛውንቱ አቶ ደባሳ ጉዮ፣ ከ35 አመታት በላይ ከኖሩበት ኬንያ ታፍነው መወሰዳቸውን ገልጿል። ድርጅቱ …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባርና የሲዳማ ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ” የህዝቦች የነጻነትና የዲሞክራሲ ጥምረት” የተባለ የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን ለኢሳት በላኩት መግለቻ አስታውቀዋል። ጥምረቱ በመግለጫው ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን እድል በራሳቸው መወሰን የሚችሉበትን፣ በነጻ …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ክፍል ባወጣው ዘገባ፣ አገሪቱ ለገጠማት አስከፊ ረሃብ አንዳንድ የምእራብ አገራት እርዳታ እያደረጉ ቢሆንም፣ እርዳታው አሁንም በቂ አይደለም ብሎአል። አንዳንድ መንግስታት ለልማት በሚል ለመንግስት ሊሰጡት ያሰቡትን እርዳታ፣ለተጎጂዎች ለማዋል እያሰቡ መሆኑንም መጽሄቱ ገልጿል። በሶማሊ ክልል በኤሚ ወረዳ የሸበሌ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላቱ 700 …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ጥቅምት 13 2007 ዓም በተካሄደው በዚህ ዝግጅት ላይ ነዋሪነታቸው በኪዊንስላንድ ግዛት የሆኑ የሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የታደሙበት ሲሆን ለንደን ከሚገኘው የኢሳት ማሰራጫ ጣቢያ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ ተገኝታ ከነዋሪዎቹ ጋር ውይይት ተካሂዷል። ዝግጅቱን በቡራኬ የከፈቱት በብሪዝበን የደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዎርጊስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ ቀሲስ መንግስቱ ሃይሉ ሲሆን እሳቸውም …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ጌትነት ደርሶ ” ‹‹ሽብር ተፈፅሞብኛል እንጅ አሸባሪ አይደለሁም››፣ ‹‹ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ ሳልሆን ወያኔና ግብረ አበሮቹ ነበሩ እዚህ መቆም የነበረባቸው›› ሲል፣ አቶ ዘመነ ምህረት ደግሞ ” ‹‹የተከሰስኩት ድርቡሽ እንኳ ያልደፈረውን የጎንደር ጥምቀት ላይ ፈንጅ ልታፈነዳ ነበር ተብዬ ነው፡፡ ምርመራ ላይ ግን ለምን የመኢአድ አባል …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሳውድ አረቢያ በጸሎት ስነስርአት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ከፍተኛ አደጋ ተከትሎ መንግስት የሃዘን መግለጫ ባለመውጣቱና ሰንደቅ አላማም ዝቅ ብሎ ባለመውለብለቡ የሃይማኖቱ አባቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት፣ የእስልምና ምክር ቤቱ ሟቾቹን ለመዘከር የጸሎት ስነስርዓት አድርጓል። በአብዛኛው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መጅሊሱ፣ ያካሄደውን የጸሎት …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ፓስተር ኦሞት አግዋ ፡ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኡመር ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው በድጋሜ ለጥቅምት 25 ተቀጥረዋል። ቀጠሮ የተሰጠው ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ አሽኔ አስቲን የምክር ቤት አባል በመሆናቸው፣ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በመታሰራቸው ፣ ጉዳዩን ለማየት ነው። እነፓስተር ኦሞት የታሰሩት የውጭ …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሶስት መቶ መንገደኞችን ጭኖ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በደብሊን አድርጎ ወደ አሜሪካ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ድሪምላይን 787-8 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በድንገት አንድ ሞተሩ አየር ላይ ቢጠፋም በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን በሰላም ማረፍ ችሏል። መንገደኞቹ ከጀርመን ፍራንክፈርት በተላከ ተቀያሪ …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ግብጽ ሉዞር ላይ በባቡር አድርገው በህገወጥ መንገድ የግብጽን ድንበር ተሻግረው የገቡ አስራ አንድ ሶማሊያዊያን እና አስር ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዛቸውን የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ምንጭ ጠቅሶ ዮም ሰበን ዘግቧል። በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው ወደ ሊቢያ የሚገቡ ስደተኞች በቅርብ ጊዜያት ውስጥ እየበዙ መሆናቸውንና ከ2 ሺ 215 በላይ …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሞያሌ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ወጣቶችን ለውትድርና ለመመዝገብ በድምጽ ማጉያ የታገዘ ቅስቀሳ ቢያካሂዱም፣ አንድም ለምዝገባው ፈቃደኛ ሆኖ የሄደ ወጣት አለመኖሩን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ወጣቶቹ የተደረገላቸውን የስብሰባ ጥሪ ባለመቀበላቸውም፣ መንግስት በሞያሌና አካባቢዋ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመመዝገብ ያቀደው እቅድ ሳይሳካ ቀርቷል። አምና 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወጣቶችን ለወትድርና …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ያለው ብአዴን ፣ በአማራ ክልል የሚኖረው ህዝብ ለበአሉ ማድመቂያ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያስገደደ ነው። ነጋዴዎች ከብአዴን ጽ/ቤት የተጣለባቸውን ክፍያ ያለፍላጎታቸው በግድ እንዲከፍሉ ታዘዋል። ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በክልሉ ባንዣበበት በዚህ ወቅት፣ ብአዴን እንደ ህወሃትና ኦህዴድ መቶ ሚሊዮኖችን አፍስሶ በአሉን ለማክበር መሞከሩ ፣ ከታሪክ …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሳምብሩ ምስራቃዊ ኢዞሎ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሎሲሳ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገቡ ያላቸውን አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሩን አስታውቋል። ባለፈው እሁድ ሃያአራት፣ ሰኞ ደግሞ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአካባቢው በታጣቂዎች በከበባ መያዛቸውን ገልጸዋል።ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ካለምንም ሕጋዊ ፍቃድ ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡና አስራ አምስቱ ኢዞሎ …

ኢሳት (ጥቅምት 10 ፡ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እስከተያዘው አመት ማጠናቀቂያ ነሀሴ ወር ድረስ ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ማክሰኞ አሳሰበ ። በሀገሪቱ ተከስቶ ያለው የምግብ እርዳታ ፍላጎትም ከአራት አመት በፊት በአፍሪካ ቀንድ ተከስቶ ከነበረው አጠቃላይ መጠን ጋር ሲነጻጸር ከፍ ብሎ መገኘቱን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ከለጋሽ ሀገራት የተጠየቁት …

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ እንደዘገበው የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት 10 ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ከግል የውጭ አበዳሪ ባንኮች ከተበደረ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመበደር በድርድር ላይ መሆኑን ረዩተርስ ዘግቧል። አዲሱ ብድር የኢትዮጵያን እዳ ከ32 ቢሊዮን ዶላር ወይም …

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአሜሪካ ጊቢ ፣ በአዲስ ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአመታት ከኖሩበት ቤት ያለበቂ ካሳ እና ተለዋጭ ቤት ቤቶቻቸው እየፈረሰባቸው ነው። መንግስት ቤታቸው ለሚፈርስባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ተላዋጭ አድርጎ ቢሰጥም፣ ተከራዮች ግን ኪራዩን የመክፈል አቅም የላቸውም መንግስት ከህዝቡ ጋር ሳይማከር የሚወስደው እርምጃ፣ …

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ዓመት ከአምስት ወር በሽብር ክስ ተከሰው በእስር ሲንገላቱ የነበሩት የዞን 9 አምደ መረብ ጸሐፍት ውስጥ ብቻውን እንዲቀር ተደርጎ የነበረው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ክሱን ውጪ ሆኖ እንዲከታተል የሃያ ሽህ ብር የዋስትና መብት የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት19ኛ ወንጀል ችሎት በመፍቀዱ ከእስር ተለቋል። በተጨማሪም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ህገወጥ እስር አስመልክቶ የእንግሊዝ ባለስልጣናት ነገ በሚጀመረው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ሊያነሱት እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ጠይቋል። የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስብሰባው ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው እንደመሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ለኢትዮጵያ …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል። ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች “መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው አቶ አበበ ካሴ እስር ቤት ውስጥ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ በእነ አበበ ካሴ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ ታጠቅ አስማረ የተከላካይ ጠበቃ ለማቅረብ ዛሬ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ለልደታ ፍርድ …

ኢሳት ዜና (ጥቅምት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ተቋማት ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ንብረታቸው መታሸጉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። የንግድ ተቋማት መታሸግን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች መሰረታዊ የፍጆታ እቅርቦቶችን ለማግኘት ተቸግረው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ወፍጮ ቤቶች ሱቆችና ምግብ ቤቶች ከታሸጉበት የንግድ ተቋመት መካከል እንደሚገኙበት …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ጋዜጠኞችንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ ጉዞ ላይ ፣ የትግል ተሞክሮ እንዲያካፍሉ የተጋበዙት የቀድሞ ታጋዮች በርካታ ጓዶቻቸው መጠለያ በማጣት በየከተማው በላስቲክ ቤት መንገድ ላይ እንደሚኖሩ ለጎብኝዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ህዝብ እንደኖረው ለመኖር ዕድሉን …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሱ የተገደለው በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ተጣልቶ ነው። ፖሊሶች አንድ የግሮሰሪ ሰራተኛን ሲደበድቡ ፣ ወጣቶች በብስጭት በፌደራል ፖሊሱ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በከተማዋ ከፍተኛ ግርግር መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገዳዮችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው። የከተማው ወጣቶች የፌደራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ የሆነ ጫና …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታላላቆቹ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መካከል ዘ ኒውዮርክ ታይምስና ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የዜና ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆን፣ ዘ ኒዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ድርቁ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። “ያሲን ሙሃመድ ከአነስተኛ የእርሻ ማሳው ላይ እየወሰደ ጫት ይቅማል፣ ለምን ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጫት ረሃብን ያስታግሳል “የሚል …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስብሰባ አውካችሁዋል በሚል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱና የቀድሞ የፓርቲው አባል አቶ እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ሳያሰሙ እንደተቀጠሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ አቶ እስማኤል ዳውድና አቶ አለነ ማህፀንቱ እስር ቤቱ” መኪና ላገኝ ስላልቻልኩ” ተከሳሾቹን ላቀርብ አልቻልኩም፤ በማለቱ የተነሳ መዝገባቸውን እየተመለከተ የሚገኘው የአራዳ …

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለሚደረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አልተሳካም። ፕሮጀክቱ በ2001 ዓም ተጀምሮ በ3 አመታት ውስጥ መጠናቀቅ ነበረበት። ከብሮድካስት ባለስልጣን የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው ስራው ሊሳካ ያልቻለው በሙስናና በብልሹ አሰራር ምክንያት ነው። ሀገር አቀፍ የሬዲዮና የቴሌቭዥን የማስፋፊያ …

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ ለታየው አጠቃላይ የዋጋ ንረት መባባስ አንድ ምክንያት መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ አንድ የጥናት ሰነድ ጠቆመ፡፡ በምግብ ነክ ምርቶች ላይ ማለትም በምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፓስታና ሞኮረኒ፣ በዳቦ ምርቶች ላይ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ አንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ እጥረት ምክንያት ከማማረት አቅማቸው …

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በሌለችበት፣ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ፣ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ የተሰናበቱ ሲሆን፣ ሁለተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ኃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ቢሆንም ማአከላዊ ምርመራ በኃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል …

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነታቸው ያልተገለጸው የ61 አመቱ ኢትዮጵያዊ አምሰተልፊን በምትባል ከተማ ውስጥ የተያዙ ሲሆን፣ ግለሰቡን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የሚልውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ የ90 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። ግለሰቡ በደብረማርቆስና መተከል አውራጃዎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸውንና ማሰራቸውን በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ መሰብሰቡን ፖሊስ አስታውቋል። በግለሰቡ ላይ ቀድም ብሎ …

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ፣ዲፕሎማትና የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት የቀድሞ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ለንደን ውስጥ መንገድ ላይ በመውደቃቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። አምባሳደር ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 7ቀን 1927 ዓ.ም በወቅቱ ሥጋ ቤት ሠፈር ተብሎ በሚጠራውና በአሁኑ ወቅት ኦርማ ጋራዥ በሚባለው አካባቢ የተወለዱ ሲሆን የሦስት ልጆች …

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 5፡ 2008) የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድቤት በሽብርተኛ ወንጀል ክስ፣ የክስ ሂደታቸው በመታየት ላይ የነበሩ አራት ጦማሪያን ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ዛሬ አርብ ወሰነ። በጦማሪያኑ ላይ የመጀመሪያ ዙር ውሳኔውን ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው ፍርድ ቤቱ በጦማሪያኑ ክሳቸውን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በአንድ አመት በላይ የቆየው የእስር ጊዜያቸው አብቅቶ በነጻ እንዲሰናበቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል። ይሁንና …

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 4 ፣ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች ላይ የሚፈጽመው በደል ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፌደሬሽን ገለጠ። በኢትዮጵያዊያን ሊሰሩ የሚችሉ ቀላል ስራዎች በውጪ አገር ዜጎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ያስታወቀው ፌደሬሽኑ 20 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸው በማህበር እንዳይደራጁ ተጽዕኖ አሳድረው እንደሚገኙ አመልክቷል። በተለይ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ተሰማርተው …

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው አመት ጀምሮ እንደ አዲስ በተጀመረው የሰራዊት ምልመላ የተፈለገውን የሰራዊት ቁጥር ማግኘት የተቸገረው መንግስት፣ ሰሞኑን ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመኪና ላይ ሆነው ወጣቱ ለውትድርና እንደሚዘገብ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ለእያንዳንዱ ቀበሌና ወረዳ የተሰጠው ኮታ ሊሟላ ባለመቻሉ፣ መንግስት በስራ ስልጠና ስም ወጣቶችን በመቀስቀስ ያለፍላጎታቸው እንዲዘምቱ …

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞተር ሳይክል ሰዎችን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ህይወታቸውን የሚመሩ 500 ያክል ወጣቶች ስራ እንዲያቆሙ በመታዘዛቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞቹ በድንገት አቁሙ በመባላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ተቸግረዋል። መንግስት አማራጭ ስራ ሳይፈጥር በድንገት ስራ አቁሙ ማለቱ ተገቢ አይደለም በሚል ወጣቶቹ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተዋል። አንድ …