ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡእ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ  ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል። ሱዳን ትሪቢውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው የጭስ …

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጦር ሠራዊት M-23 በሚል መጠሪያ በሚታወቀው አማጺ ኅይል ላይ መልሶ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሯል። በታንክ፣ በሄሊኮፕተር ፤ አዳፍኔና ከባድ አውቶማቲክ ጠብመንጃ ፣ ወታደሮቹ ከጎማ ከተማ በስተሰሜን ፣ የአማጽያኑን ምሽግ መደብደባቸውን የዜና አውታሮች አስታውቀዋል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼ ቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አዉሮፕላኖች የሚመጡልንን እቃዎች በወቅቱ ባለመረከባችን ተጉላላን ሲሉ አንዳንድ የአየርመንገዱ ደንበኞች አማረሩ።

የእንግሊዝና የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የልማት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጡት ድጋፍ በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ ሲል አንድ ድርጅት ከሰሰ።

በማናዬ በላይ
      VII.        የአምበድከር እና ጋንዲ አለመግባባት
    ማህተመ ጋንዲ ከአምበድከር በብዙ እድሜ የሚበልጥ ቢሆንም ሁለቱም የህንድ አይከኖች በተመሳሳይ ወቅት በህንድ ፖለቲካ ስርዓት ዉስጥ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በትምህርት፣ በአንደበተ ርቱዕነት፣ በፍልስፍና አምበርከር ከጋንዲ ብዙ ርቀት የተጓዘና ለዉድድር የሚቀርብ ባይሆንም በወቅቱ በፖለቲካ ተቀባይነት እና በድጋፍ ጋንዲ ከአበድከር እጅጉን የበዛ ድጋፍ ነበረዉ፡፡ በዛ ወቅት ከጋንዲ የተለየ ሀሳበ መያዝ በራሱ ከህዝብ ጋር ከማጋጨት በተጨማሪ በወቅቱ በህንድ እንደ ፋሽን ተይዞ ለነበረዉ ፖለቲካዊ ግድያ ሊዳርግ ይችላል፡፡ የከፍተኛ ካስት አባል መሆኑ እንዲሁም ህንድ ጀግና በተጠማችበት ጊዜ የመጣ መሆኑ ጋንዲን ለእዉቅናዉ ጠቅሞት ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ጋንዲን ተቃዉመዉ ሃሳባቸዉን በግልፅ ከሚያንፀባርቁ ግለሰቦች መሀከል ዶ/ር አምበድከር ዋንኛዉ ነበር፡፡
    ጋንዲ የሁሉም ሂንዲ ሹድራን ጨምሮ ወኪል ነኝ ብሎ ስለሚያስብ ከሱ ዉጭ ያለ ማንኛዉንም መሪ አይቀበልም አምበድከር በበኩሉ የሹድራና እና የሌሎች ካስት ሂንዱ ጥያቄ አንድ ካለመሆኑ ባሻገር የሚጋጭ በመሆኑ ጋንዲ ሊወክለን አይችልም የሚል ቆራጥ እሳቤ ነበረዉ፡፡ በዚህ መሰረት እንግሊዞች ይህንን ተቀብለዉ ይመስላል ለንደን ላይ በ1930-32 ስለ ህንድ ፖለቲካል ስርዓት ለመወያየት ለተከናወነዉ ስብሰባ አምበድከር የሹድራ መሪ ሆኖ እንዲሳተፍ ደብዳቤ ይደርሰዋል ይህንን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋንዲ ጥሪ አምበድከር እና ጋንዲ ቦምቤ ተገናኝተዉ የተወያዩ ሲሆን ዉይይቱ ባለመስማማት የተቋጨ ነበር፡፡
    ዶ/ር አምበድከር ለሹድራ ጭቆናና የበታችነት ዋንኛ ተጠያቂ አድርጎ የሚያቀርበዉ የካስት ስርዓቱን ሲሆን ለዚህ መወገድም አበክሮ ይሰራ ነበር፡፡ የሹድራን የአገልጋይነት እና የበታች ሆኖ የመኖርን ስርዓት ሕግ በሚመስል መልክ የሚገልፀዉ የማኑስምሪትን (የሂንዱ የሐይማኖት መጻሕፍ) በማቃጠል በወቅቱ እንደ ታቡ የማይወራበትን የሂንዱ ሐይማኖት መሰረት የሆነዉ ካስት ይወገድ ዘንድ በግልፅ በመስበክ፤ ይህንንም ለማሳካት የፖለቲካ ስልጣን ወሳኝ መሆኑን በማመን ወደ ፖለቲካዉ ገብቶ ጫና በመፍጠር በመጨረሻ ዉጤታማ የሆነበትን ሕገ መንግስት ለማፀደቅ በቅቷል፡፡
    የጋንዲ እሳቤ ከዚህ የተለየ ነበር እሱ የካስት ስርዓት የህንድ ማኅበረሰብ እሴት አድርጎ የሚያስብ የማኅበረሰብ በደል ያልቆጨዉ ለመሰረታዊ ለዉጥ ሳይሆን በጥቃቅን ነገሮች ጥያቄዎን ለማድበስበስ  የሚጥር ነበር፡፡ እንደ ምሳሌ ጋንዲ መሰረታዊ ችግሩን ለማስወገድ ከመስራት ይልቅ አይነኬ የሚለዉን የዚህ ማኅበረሰብ ስያሜ በሀሪጃን (የአምላክ ልጆች) በሚል እንዲቀየር እንዲሁም ካስትን ከማስወገድ ይልቅ ከካስት ዉጭ ያሉትን የመጨረሻዉን ሹድራ ካስት ሰጥቶ ማመሳሰልን የሚሰብክ ነበር (አይነኬዎች በመጨረሻዉ ዝቅተኛ ቫርና ያሉት እና ካስት የሌላቸዉን ሂንዱ ይጨምራል)፡፡ ጋንዲ ለካስት ስርዓት ይህንን ያህል ተቆርቋሪ ሆኖ የሚታገለዉ በወቅቱ የነበረዉን ፖለቲካዊ ተአማኒነት ላለማጣት እንጂ አምኖበት አልነበረም፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነዉ ጋንዲ ከሶስተኛዉ ከነጋዴ ስራ የሚመደቡ የካስት አባል ቫይሲያ አባል ሲሆን የኖረዉ ግን የብርሀሚን ካስት የሚሰራዉን ፕሪስት በመሆን ከመሆኑ ባሻገር ልጁም ቢሆን ይሰራ የነበረዉም ከንግድ ዉጭ የጋዜጠኝነት ስራ ነበር ይህም በሂንዱ የሐይማኖት መጻሕፍት ከፍተኛ ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ፡፡ ጋንዲ በዚህ ስርዓት እንደማያምን የሚያሳየዉ ሌላዉ የሚሰጣቸዉ መግለጫዎች እና ጽሑፎች ሲሆን በወቅቱ በጋንዲ መስራችነት ይታተም የነበረዉ ያንግ ኢንዲያ በኋላም ሀሪጃን የእንግሊዝኛ ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ የአይነኬነትና ካስት ተቃዋሚ ሆኖ መግለጫ ይሰጥና በአካባቢዉ ቋንቋ ጉጂራቲ በሚፅፈዉ ጽሑፍ ደግሞ አክራሪ ሂንዱ በመሆን ለካስት ስርዓት እንደሚታገል ይገልፅ ነበር፡፡ 
    ጋንዲ በወቅቱ ተደማጭነቱን ተጠቅሞ ከሚያደርገዉ ፕሮፖጋንዳ በተጨማሪ በወቅቱ ሹድራ ተለይተዉ በራሳቸዉ ዉክልና ያገኙ ዘንድ በዶ/ር አምበርከር ተደጋጋሚ ጥያቄ በራምሴ ማክዶናልድ የተሰጠዉን ዉሳኔ ተቃዉሞ በተደጋጋሚ ለጠ/ሚሩ የጻፈዉ ደብዳቤ ተቀባይነት እንዳላገኘ ሲያዉቅ በወቅቱ በእጁ የነበረዉን ትልቅ መሳሪያ ተጠቀመ፡፡ ጋንዲ ይህ ዉሳኔ ካልተቀየረና ሹድራዎች ከሂንዱ ተለይተዉ የተለየ የምርጫ ክልል ከተሰጣቸዉ እስክሞት እፆማለሁ በማለት በ1932 ያዉጃል፡፡ በዚህ ወቅት ከያቅጣጫዉ በአምበድከር ላይ ጫና ይደርስበታል ጋንዲ ከሞተ ህንድ በእርስ በርስ ጦርነት እንደምትታመስ ግልፅ ሆነ፡፡ አምበድከር ጋንዲ መጣ ጋንዲ ይሄዳል የኔ ህዝቦች ግን ለዘላለም ኗሪ ናቸዉ በሚል ለአምስት ቀናት በእንቢተኝነት ቢቆይም በወቅቱ የነበረዉ የሀገሪቱን ዉጥረት መቋቋም ባለመቻልና የሚመጣዉን ዉጤት በመፍራት ከኮንግረስ መሪዎች ጋር ከስድስት ቀን የጋንዲ ፆም በኋላ ፖና ፓክት ተብሎ የሚጠራዉን ስምምነት ፈረሙ፡፡ በዚህ ስምምነት የተለየ ምርጫ ለሹድራ መሰጠቱ ቀርቶ በሂንዱ ዉስጥ ሪሰርቬሽን እንዲሰጣቸዉ ተስማሙ፡፡ እንደ አንዳንዶች ገለፃ ይህ ባይሆን ኖሮ ህንድ አሁን ካለችበት ማኅበራዊ ችግር ቀድማ ትወጣ ነበር፡፡ ችግሩ መልኩን ቀይሮም ቢሆን አሁንም አለና (ከፍተኛ ሂንዱዎች አሁንም የፖለቲካ ስርአቱ ተቆጣጣሪ ናቸዉ)፡፡ ጋንዲ ለካስት ስርዓት ለረጂም ጊዜ ሲታገል ከቆየ በኋላ በመጨረሻ በ1946 አቅራቢያ ካስት ያለፈበት ስርዓት ነዉ በሚል ከአምበድከር ጋር አብሮ ቆሞ ሲታገል ነበር፡፡ ዘግይቶም ቢሆን የአምበድከረን ሀሳብ መቀበሉ አሁን ላለዉ የተሻለ የህንዳዉያን ንቃተ ህሊና እና ፖለቲካ ለዉጥ አስተዋፅኦ ነበረዉ፡፡ ለአብዛኛዉ ህንዳዊ ጋንዲ ማለት ብዙ ነዉና እሱ ካለ አለ ነዉ ሌላዉ አፉን ሊዘጋ ይገባል፡፡
    በእድገት እሳቤ ላይም ቢሆን ዶ/ር አምበድከር እና ጋንዲ የተለያየ እሳቤ ነበራቸዉ፡፡ ጋንዲ ወደ ተፈጥሮ እንመለስ የሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ አራማጅ ከመሆኑ ባሻገር ሆስፒታል፤ ባቡር ትራንስፖርት፤ ኢንዱስትሪ አላስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያምን ነበር፡፡ ዶ/ር አምበድከር በበኩሉ ወደ ተፈጥሮ እንመለስ ጥሪ ማለት ወደ ባዶነት፣ ወደ ሰቆቃ እና ረሀብ አብዛኛዉን ማኅበረሰብ መክተት ነዉ ይል ነበር፡፡
    በእርግጥ በብዙዎች አዕምሮ ሊመጣ የሚችለዉ ታዲያ ለምን ጋንዲ በአለም ላይ ታዋቂ ሆነ የሚል ነዉ፡፡ በወቅቱ ህንድ ጀግና የተጠማችበት ጊዜ ነበር፡፡  እንዲሁም የህንድን ፖለቲካ ስርዓትን የተቆጣጠሩት የከፍተኛ ካስት አባል ሂንዱዎች አስበዉበት ለዚህ አላማ ማለትም ጋንዲን ታዋቂ ለማድረግ የሰሩት ፕሮፖጋንዳ እንደ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል፡፡ የህንድ ማኅበረሰብ አሁን ስለ ዶ/ር አምበርከርም ይሁን ጋንዲ ትክክለኛ ግንዛቤ አላቸዉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ለጋንዲ የሚያደርጉትን ለአምበድከርም ያደርጋሉ፡፡ የዶ/ር አምበድከር ወሳኝ ቀናት እንደ ዉልደት፤ ሞት ፤ ቡድሂዝምን የተቀበለበት ቀን በመላዉ ህንድ በአብዛኛዉ ማኅበረሰብ ይከበራል፡፡ የተወለደበት የሞተበት፤ ሰላማዊ ትግል ያከናወነበት ቦታ ዋንኛ የቱሪስት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ችግሩ ያለዉ በሌላዉ ዓለም ሲሆን አብዛኛዉ ማህበረሰብ ህንድን ከጋነዲ ጋር እንጂ ከዶ/ር ባባሳሂብ አምበድከር ጋር አያይዞ አያነሳትም፡፡ ይህም ሥነ-አመክንዮ ያለዉ አይመስልም፡፡
    ‹‹በጭቆናና በበደል የተፈተነ የፍትህ እና እኩልነት አባት – ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር›› በሚል ርዕስ ማናዬ በላይ በአራት ተከታታይ ክፍሎች ያቀረበልን ጽሑፍ በዚሁ ተጠናቋል፡፡
    ጸሐፊውን ለማግኘት [email protected] ላይ ይጻፉላቸው፡፡

    ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በሶስት መርከብ ስሚንቶ አስጭነው አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ። በተከለከለ ፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ አገር ቤት የገባው ስሚንቶ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አዜብና ግብረአበሮቻቸው እንደዛቁበት ያረጋገጡት ምንጮቹ፣ አያይዘውም ጉዳዩ በደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እጅ እንደገባ አስታውቀዋል። በሕገወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ […]

    ከመስፍንነጋሽ

    ወንድሜ ጁዋር መሀመድ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሞ ፖለቲካ እና አሁን ደግሞ ስለኦሮሞ-ኢስላም ያቀረባቸው ንግግሮች ኮርኳሪ ሆነዋል። ኮርኳሪነታቸው የሚመነጨው ግን ሐሳቦች አዲስ ስለሆኑ አይደለም፤ በአቀራረባቸውም ቢሆን ያልተለመዱ አይደሉም። “የአግራሞቱ” ወይም የንዴቱ ምንጭ ጃዋር የገነባው ወወይም እየገነባው የመሰለን የፖለቲካ ማንነትና በቅርብ ያንጸባረቃቸው አቋሞቹ እጅግ የሚቃረኑ ስለሚመስሉ ነው።

    ሙሉውን አስነብበኝ …

    /መሰፍን/ማርያም

    የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ ሌላእንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤

    ሙሉውን አስነብበኝ …

    /መሰፍን/ማርያም

    የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ ሌላእንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤

    ሙሉውን አስነብበኝ …

    የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11 ቀን ,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡ በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮች ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ […]

    [email protected] ሐምሌ 11 ቀን 2005 ዓ.ም ሐምሌ 7 ቀን ደሴና ጎንደር የኢትዮጵያዉያንን ትኩረት ስበውት ነበር። በነዚህ ከተሞች የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ በአገዛዙ ካድሬዎች የደረሰባቸዉን ጫናና ማስፈራሪያ ወደ ጎን በማድረግ፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲ የነጻነት ጥያቄዎቻቸውን አሰምተዋል። «አምባገነንነት፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት በቃን» ብሎ ሕዝቡ እንደተነሳ፣ በገልጽ የተያበት ሁኔታ ነዉ የነበረዉ። የኢትዮጵያዊ ጨዋነት መንፈስ በገሃድ […]

    ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘወትር አርብ የሚደረገውን ስግደት ተከትሎ ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከ10 ያላነሱ የወለድያ ከተማ ነዋሪዎች ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል ኢብራሂም ገበየሁ፣ ከድር ሙሀመድ፣ ወ/ሮ ሀያት ይማም፣ ወ/ሮ ነሲሳ አህመድ፣ ወ/ሮ ሀያት አህመድ ይገኙበታል። ወ/ሮ ሀያት አህመድ ሁለት ወር ያልሞላት አራስ ስትሆን፣ ወደ …

    ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው  በህገ ወጥ የዘመቻ እስር የሚሊዮኖች ድምፅ አይታጠፍም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ የጸረ ሽብር አዋጁ በህገ መንግስቱ እውቅና የተቸራቸውን መብቶችን የሚጨፈልቅና ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መሰረዝ ይገባዋል የሚሉ ዜጎች ወደ ዋናው የፓርቲው በጽ/ቤት በመምጣት የተቃውሞ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚጠይቅ ‹‹ከሚሊዮኖች ለምን አንዱ አይሆኑም›› የሚል …

    ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ባወጣው መግለጫ በኦሞ ሸለቆ የሚገኙ የሙርሲና የቦዲ ነዋሪዎች አካባቢያቸው ለሸንኮራ ገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል በሀይል ቀያቸውን እንዲለቁ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን ገልጿል። ድርጊቱ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መንግስት እርዳታና  እውቅና እየተካሄደ መሆኑም ገልጿል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት የልማት ተራድኦ የውጭ ግንኙነት ክፍል ቃል አቀባይ …

    ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪዩተርስ ሚስጢራዊ ሰነድ አገኘሁ በማለት ባወጣው ዘገባ ምንም እንኳ የኤርትራ መንግስት የሶማሊያ ታጣቂ የሆነውን አልሸባብን አልደግፍም ቢልም ፣ ቡድኑ ግን ኤርትራ ታጣቂውን ሀይል መደገፉዋን በመቀጠሉዋ የተጣለባት ማእቀብ እንዳይነሳ አቤት ብሎአል።  ኤርትራ አብዲ ኑር ሰኢድ በተባለ የሶማሊያ ተወላጅ በኩል እርዳታ እንደምታደርግ ማረጋገጡን ቡድኑ ጠቅሷል። በቀረበባት ክስ ላይ ኤርትራ አስተያየቱዋን …

    ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ አፍሪካው የነጻነት አባትና የመጀመሪያው ጥቁሩ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ 95 ኛ አመት የልደት በአላቸውን በሆስፒታል አልጋቸው ላይ ሆነው አክብረዋል። ማንዴላን እንኳን አደረሰዎት ለማለት በሆስፒታሉ የተገኙት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የማንዴላ ጤና መሻሻል እንዳስደሰታቸው ታናግረዋል። ” እንኳን አደረሰህ” ስላቸው በፈገግታ መልሰውልኛል ብለዋል ጃኮብ ዙማ። የአገሪቱ ነዋሪዎች የማንዴላን የ67 አመታት …

    ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።

    እሥራኤል በኃይል በያዘቻቸው የፍልስጤም ግዛቶች የሠፈራ መርኀ ግብሯን አለማጠፏ፣ የመካከለኛውን ምሥራቅ ውዝግብ በሰላም ድርድር ለመፍታት ፣ በየጊዜው የቀረቡ እቅዶችን ሁሉ መቅኖ እያሳጣ ነው ።

    የኢትዮጵያ ወታደሮች ከባይደዋ መዉጣታቸዉን አሶሲየትድ ፕረስ ትናንት አመልክቷል። መንግስት መፍትሄ ይፈለጋል ቢልም ወታደሮቹ ከተጠቀሰችዉ ስልታዊት የሶማሊያ ከተማ መዉጣታቸዉም በአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪዎችና የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች ላይ ጫና እንደሚያስከትል እየተነገረ ነዉ።

    ደቡብ አፍሪቃዉያን ዛሬ የነጭ ዘረኛ አገዛዝ ታጋዩን የኔልሰን ማንዴላን 95ኛ የልደት በዓል በታላቅ ድምቀት አክብረዉ ዉለዋል። የነፃነት ታጋዩ አዛዉንት ግን ከአንድ ወር በላይ በሃኪም ቤት አልጋ ላይ ይገኛሉ። በጤናቸዉ ረገድ መሻሻሎች መኖራቸዉን ፕሬዝደንት ጄኮብ ዙማም ሆኑ ልጆቻቸዉ እየገለጹ ነዉ።

    ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።

    መ/ር ፍሥሐ ጽዮን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው አቡነ ጢሞቴዎስን የሚተካ ዋና ዲን እስኪሾም ኮሌጁ በጊዜያዊ ሓላፊ ሊመራ ይችላል ጥቅመኛው፣ ሀኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው …

    መ/ር ፍሥሐ ጽዮን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ ይጠበቃል ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሌጁ አስተዳደርና በደቀ መዛሙርቱ መካከል …

    ዓረና ትግራይ ፓርቲ ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ ፓርቲው ለእሁድ ሓምሌ 14, 2005 ዓም በመቐለ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል። ፓርቲው ‘አሉ’ በሚላቸው የህዝብ ችግሮች (ኑሮ ውድነት፣ የወጣቶች ስደት፣ የግብር አከፋፈል ችግሮችና የሙስና ሁኔታ፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የመሳሰሉት የህዝብ ችግሮችና በዓረና ትግራይ የሚቀርቡ አማራጭ መፍትሔ ሓሳቦች ከመቐለና አከባቢው ህዝብ ነዋሪዎች መወያየት እንደሚፈልግ አስታውቋል። ሁላችን ተጋብዘናል፤ እንሳተፋለን። […]

    የምክክር ጉባኤውን ተከትሎ በሀ/ስብከቱ እና በክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ ይካሄዳል የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችን በቢሮ ዕቃዎች ለማደራጀት የ1.6 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧል በ1.6 ሚልዮን ብሩ ጽ/ቤቶቹን ለማደራጀት የተቋቋመው የዕቃ ግዥ ኮሚቴ÷ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በሙስና ቀለበት ውስጥ በማስገባት የለውጥ ሂደቱን ለመቆጣጠር በሚያልሙ የለየላቸው ሙሰኞች የሚንቀሳቀስ መኾኑ ሀ/ስብከቱን ለከፋ ትችት እየዳረገው …

    ከማከብራቸው የዲሞክራሲ አክቲቪስት መካከል አንዱ የሆኑት፣ አቶ ተድላ አስፋዉ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ለተናገራቸው አንዳንድ አባባሎች የሰጡትን ምላሽ አነበብኩ። አቶ ጃዋር የተወለደው በአርሲና በሃረርጌ ድንበር አካባቢ ነዉ። በዚያ አካባቢ ነዉ አርባ ጉጉ (ምእራብ አርሲ) እና በደኖ (ምስራቅ ሃረርጌ) የሚገኙት። ወያኔ/ኢሕአዴግና ኦነግ ስልጣን በጨበጡ ጊዜ፣ በአርባ ጉጉና በደኖ የተፈጸሙትን ሁላችንም የምናወቀዉ ነዉ። አካባቢዉን ከክርስቲያኖችና ከ«አማራዎች» ለማጽዳት ፣ […]

    ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራው አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ የተሰኘው ድርጅት ለኢሳት በላከው መረጃ ከ10 ቀናት በፊት ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በ ኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቀምቢ ወረዳ በጋራ ወሎ ቀበሌ በነዋሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የ38 አመቱ ጎልማሳ ኢብራሂም ሄኖ፣ የ26 እና 27 አመት ወጣቶች ሙሀመድ ሙሳና ሙሀመድ …

    ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝነት በማድረግ ላይ ያለው የልኡካን ቡድኑ መሪ ባርባራ ሎክብሂለር ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የማምለክና የመሰብሰብ መብታቸውን በመጠቀማቸው መታሰራቸው ተገቢ ባለመሆኑ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ የፖለቲካ ልዩነትን ለማፈን እየዋለ መሆኑን የገለጸው የልኡካን ቡድኑ፣  የአገሪቱ ህገመንግስት ጥሩ ቢሆንም …

    ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌጁ ተማሪዎች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው ወደ ፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ከትናትና በስቲያ ያመሩ ቢሆንም ፤የስራ አመራር ቦርዱ ያለው ችግር እስኪጣራ ድረስ ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን እና ተማሪዎችም ከሐምሌ 8 ቀን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ አሳውቋል። ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበው ወደ …

    ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።

    ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን በማሰብ ላይ የሚገኘው የነጻ ነጻ የአፍሪቃ መንግሥታት ማኅበር –የአፍሪቃ ኅብረት ፣ እንደ ኤኮኖሚውና ንግዱ ግንኙነት ፣ ከአውሮፓው ኅብረትም ሆነ ከአባል ሃገራቱ ጋር በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የሚያደርገው ትብብር ምን ይመስላል?

    ውሳኔው በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ።

    የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ፀሃፊ የፀረ ሽብሩ ህግ ይሰረዝ የሚል ድምፅ ለማሰባሰብ አዲስ አበባ ውስጥ የተንቀሳቀሱ 51 አባላቱ ያለአንዳች ምክንያት ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን ተናግረዋል ።

    ናይጀሪያ የሱዳኑን ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽርን ለዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ይዛ ባለመስጠቷ እየተወቀሰች ነዉ። ፕሬዝደንት አልበሽር በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ናይጀሪያ ላይ በተካሄደዉ የአፍሪቃ ኅብረት የHIV/AIDS ጉባኤ ላይ መገኘታቸዉን የአገሪቱ የመብት ተሟጋቾች ተቃዉመዋል።

    ከተፈሪ በላይ (የዲሲ ነዋሪ)

    ይህን መጣጥፍ እንዳዘጋጅ የገፋፋኝ ጋዜጠኛ አቶ ክንፉ አሰፋ በኢትዮ ሚድያ በኢትዮጵያ ዛሬና EMF ድረ ገጽ ላይ ዲሲን ለቀቅን አስመልክቶ “ዲሲ 2013” በሞል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ነው። ከጽሁፉ መግነቢያ ላይ ተገለጸወን ሃተታ ማለትም ፈረንጆች በአገራችን ኢትዮጵያ በቆዩ ቁጥር የሚጽፉት ያጣሉ የሚልወን አባባል ባልቀበለውም ወግ ለማጣፈጫ እንደገባ ቅመም ልቁጠረውና ልለፈው።

    ሙሉውን አስነብበኝ …

    ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከአርባ ሁለት በላይ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች፣ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ዛሬ እንደታሰሩ ፍኖት ነጻነት ዘገበ። ከታሰሩት ዉስጥ ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ አብዛኞቹም ወጣቶች ናቸው። በጎንደርና በደሴ የተደረጉ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ 23ቱ ወረዳዎች ያሉ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በወረዳዎች ሁሉ በመሰማራት፣ ሕዝቡን በማነጋገር ፔቲሽኖች ሲያስፈርሙ ነዉ […]

    የዛሬ ሃያ ዓመት ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እንደተመረቅኩ የመምህርነት ሥራዬን የጀመርኩት እነዋሪ በምትባል በሰሜን ሸዋ ውስጥ ከምትገኛና ከአዲስ አበባ 165 ኪሎ ሜትር በምትርቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ እነዋሪ ከመርሐቤቴ እስከ ዜና ማርቆስ የሚኖረው ቆለኛና ደገኛው ጅሩዬ የሚገናኙባት የቀለጠች የገበያ ከተማ ናት፡፡ በተለይም በፍራፍሬ ምርቷ ትታወቃለች፡፡ ኤፍሬም እሸቴ የእነዋሪን ሙዝ ‹ከማጠሯ መጎጠሯ› እያለ ይቀልድባት ነበር፡፡
    ከእነዋሪ እየተነሣሁ እስከ ዠማ ወንዝ ድረስ ለሠርግም፣ ለንግሥም ቆላውን እወርድ ነበር፡፡ ገበሬዎቹ ከቆላው ይመጡና እኔን በቅሎ ላይ አውጥተው በትከሻቸው ላይ ውጅግራ ጠበንዣቸውን ደልደል አድርገው ተሸክመው የጋቢያቸውን ግማሽ ጠቅልለው አናታቸው ላይ በማስቀመጥ፣ ከግራና ከቀኝ በቅሎዋን እየነዱ፣ ያንን እንደ ያሬድ መዝሙር በጆሮ የሚንቆረቆረውን ወጋቸውን እያወጉ፣ እንደ ዝንጀሮ ገደሉን በኩራት ይወርዱታል፡፡ ተረታቸው፣ ቀረርቷቸው፣ ፉከራቸው፣ ዘፈናቸው፣ የታሪክ ትረካቸው፣ ስለ ጀግኖቻቸው የሚገጥሙት ግጥም አሁንም በጆሮዬ እንደ መስክ ነፋስ ሲያልፍ ይሰማኛል፡፡ 

    አንድ ቀን ታድያ አይዋ ሰጥ አርጌ የሚባሉ ቆፍጣና ገበሬ አብረውን ወደ ዠማ ሲጓዙ ታች በሌ ስለሚባል ሽፍታ አወጉኝ፡፡ ታች በሌ በተለይ በሞረቶች ዘንድ በጣም የታወቀ አስቂኝ ሽፍታ ነው፡፡ አንድ ሰው ያላሰበበትን፣ ያልተዘጋጀበትንና ያለ ዐቅሙ የሆነውን ነገር ጀመረ ሲባል ዠማዎች ‹‹ምን የእርሱ ነገርኮ የታች በሌ ሽፍትነት ነው›› ይሉታል፡፡ አንድ ሰው በስሜት ብቻ ተነሣስቶ እንዴው የጀብደኛነትን ሥራ ሲሠራ፣ አንድን ነገር አስቦ ከመሥራት ይልቅ ከሠራ በኋላ ሲያስብ ዠማዎች እንዲሁ ‹ታች በሌ› ይሉታል፡፡ ለምን?
    ታች በሌ የዠማ ሰው ነው፡፡ የኖረው ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት በሸዋው አስፋ ወሰን ዘመን ነው  አሉ፡፡ በዚያ ዘመን ሞረትን ይገዙት የነበሩት ጥዱ የተባሉ ኃይለኛ በላባት ነበሩ፡፡ እንዲያውም ጥዱና አስፋ ወሰን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩም የሚፈታተኑም ኃይለኞች ስለነበሩ ግጥሞቻቸው ዘመን ተሻግረው ደርሰውናል፡፡ አስፋ ወሰን ሞረትን ማስገበር ስለፈለጉ
    ለሞፈር ለቀንበር የሚሆነኝን
    ሳልቆርጠው አልቀርም ዘንድሮ ጥዱን፤
    ብለው ለአዝማሪ ነገሩ አሉ፡፡ ይህን የሰሙት ጥዱም
    አስፋ ወሰን ይፋት ጠንክረው ይረሱ
    ሞረት ጥዷል ብለው ከሚመላለሱ፤
    ብለው መለሱላቸው ይባላል፡፡
    ጥዱ ኃይለኛ አስገባሪ፣ አስጨንቆ ገዥ ነበሩና ብዙ ገበሬዎችን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ጫማ ረግጠው ይገዙ ነበር፡፡ ከተገዥዎቹ ገበሬዎች አንዱ የነበረው ታች በሌ መረረው፡፡ በልጅነቱ በሰሜን ሸዋ በረሃዎችና ጫካዎች ሸፍተው ገዥዎችን ስላስጨነቁ ሽፍቶች እየሰማ ነበርና ያደገው መሸፈት አማረው፡፡ አንድ ቀን ከብት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መሸፈቱን ነግሮ የአጎቱን ቁመህ ጠብቀኝ መንትፎ ሸፈተ፡፡ ሸፍቶም ጫካ ገባ፡፡ አገሩም ‹ታች በሌ ሸፈተ› እያለ ከሚዳ እስከ እነዋሪ አወጋ፡፡ አንዳንዱ አደነቀ፤ ዘፈነለት፤ አንዳንዱ ተጠራጠረ፣ አንገቱን ነቀነቀበት፡፡ ‹በምን ልቡ ነው የሸፈተው›› ያሉም ነበሩ፡፡ ጥዱም እገለዋለሁ ብለዋል ተባለ፡፡
    ታች በሌ ዠማ ወንዝ በረሃ ውስጥ ወርዶ አንድ ጫካ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ መጀመሪያ ስሙ በድፍን ሸዋ ሲገንን፣ ስሙ በየሠርግ ቤቱና በየድግስ ቤቱ የዘፈን መቋጠሪያ ሲሆን እየታየው ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር፡፡ ዋል አደር ሲል ግን ታች በሌን ጥያቄዎች ጭንቅላቱን እየሞሉ ያስጨንቁት ነበር፡፡ ለመሆኑ በቂ ስንቅ ይዘሃል? የሸፈትከውኮ በጀግናው ጥዱ ላይ ነው፤ ለመሆኑ በቂ ጥይት ታጥቀሃል? ለመሆኑ ቢመጡብህ የምትሸሽበት የማምለጫ ስርጥ መርጠሃል? አንተ መንደርህ እያለህ አንድ ቆቅ እንኳን አድነህ የማታውቅ እንዴት ጥዱን ለመዋጋት ጫካ ገባህ? ለመሆኑ ዛሬ የታጠቅከውን ቁመህ ጠብቀኝ ተኩሰህበት ታውቃለህ? ቢበላሽ ማን ይጠግንልሃል? ከዛሬ በፊት ለመሆኑ ጫካ ውለህ አድረህ ታውቃለህ? ከአውሬ ጋር ታግለህ ታውቃለህ?
    እነዚህ ጥያቄዎች ጭንቅላቱን ሲወጥሩት ታች በሌ መልስ አልነበረውም፡፡ የዠማን በረሃ ወደ መርሐ ቤቴ ሲያልፍበትና ወደ ጅሩ ሲወጣበት እንጂ ውስጡ ገብቶ ሥር ማንሥሩን አይቶት አያውቅም፡፡ እንዲያውም አሁን ሲያስበው ትንሽ ፍርሃት ሳይኖርበት አይቀርም፡፤ እንደ ሌሎቹ እንኳን ቅራት (ከብትን በረሃ ውስጥ ሌሊት መጠበቅ) ለብቻው አድሮ አያውቅም፡፡ ደግሞ አሁን ሸፍቷልና የሚያወያየው እንኳን የለም፡፡ እየዋለ እያደረ ሃሳብ ሲበዛበት ታች በሌ ይጨንቀው ነበር፡፡ ሽፍትነት ሲያስቡትና ሲሸፍቱት አንድ አልሆነለትም፡፡ እርሱ እዚህ በረሃ ውስጥ ምን እንደሚያደርግ ጨንቆታል፣ እዚያ መንደር ውስጥ ግን በስሙ ይዘፈን ይሆናል፡፡ የልቡን ማን አየለት፡፡ ለእርሱ ከሚዘፍኑለት ስንቅና ትጥቅ ቢያቀብሉት ነበር የሚሻለው፡፡
    ታች በሌ ለአንድ ሳምንት በረሃው ውስጥ ተቀመጠ፡፡ ስንቅና እድሜ እያደር ይቀላል እንዲሉ የያዘው ነገር ሁሉ እያደር ያልቅበት፣ እርሱም ብቸኛነትን አልለመደውም ነበርና እያደር ሆድ ይብሰው ጀመር፡፡ አንዳንዴም ሲያስበው መሸፈት እንዳልነበረበት ራሱን ይሞግታል፡፡ አሁን እንዴት አድርጎ ወደፊት መጓዝ እንደሚችል ያስባል፤ ግን ምንም ሃሳብ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ሰው ምን ይለዋል? አንዳንዴ የተወለደበትን ቀን ትቶ የሸፈተበትን ቀን ይረግማል፤ አንዳንዴ ደግሞ እንኳን ሸፈትኩ ይላል፡፡ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ጥዱም ሆኑ የጥዱ አንጋቾች ወደ አካባቢው ዝር ሊሉ አልቻሉም፤ ታድያ ሳይዋጋ ሽፍታ ተብሎ እስከ መቼ ሊቀመጥ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነኮ ጥቂት ቆይቶ ይረሳል፡፡
    ታች በሌ እየቆየ ነገር ዓለሙ መረረው፤ መሸፈቱንን እንጂ ለምንና ምን ሊያደርግ እንደሸፈተ ለኅሊናው ማስረዳት አልቻለም፤ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግና ከዚያስ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ እገሌ ሸፈተ ሲባል እንጂ ሽፍትነት ምን እንደሆነ፣ ሸፍቶ ምን እንደሚደረግ በልቡ ምንም ነገር አልያዘም፡፡
    አንድ ቀን ታች በሌ ድንገት የሚኖርበት መንደር ያለች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ሰዓት ከች አለ፡፡ አገርም ጉድ አለ፡፡ ካህናቱም ጨዋውም እያየው አፉን ይዞ ቀረ፡፡ ታምር ተሰምቶ የሰንበት ቂጣ ሊታደል ሲል ታች በሌ ድንጋይ ይዞ ሕዝቡ እግር ሥር ወደቀና ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ብሎ በዚያ መከረኛ ላይ አላክኮ ካህናቱ ድንጋዩን አነሡለት፡፡
    አንድ ሰሞን የታች በሌ ነገር የሞረቴ ሁሉ አፍ ማሟሻ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሞረቴ መሸፈት ቀላል አልሆነም፤ ‹‹ደግሞ እንደ ታች በሌ ሲርብህ እንዳትመጣ›› የሚባለው ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው ሸፈተ ሲባል አቅራሪዎቹ
    ምከሩት፣
    ምከሩት፣
    ምከሩት፣
    ይህንን ታች በሌ ለምን አትመክሩትም፤
    ይህንን ታች በሌ ለምን አትነግሩትም፤
    ልብ ካልሸፈተ እግር አይሸፍትም ….. ሃ!
    እያሉ ይመክሩት ነበር፡፡ ታች በሌ ሳያስቡ ለሚወስኑና ሳያስቡ ለሚያደርጉ ሁሉ የሚሰጥ ቅጽል ሆነ፡፡
    ታች በሌያዊ አስተሳሰብ የሀገራችን ተቋማት አንዱ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ስብስቦች ሳይታሰቡ ተመሥርተው ሃሳብ የጠፋባቸው ናቸው፡፡ ለሃሳብ ተቋም ከመመሥረት ይልቅ ለተቋማቱ ነው ሃሳብ እየተፈለገ ያለው፡፡ ቁጭት ሁሉ፣ ብስጭት ሁሉ፣ ስብስብ ሁሉ፣ ገንዘብ ሁሉ፣ አጋጣሚ ሁሉ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ተቋም፣ ማኅበር ለመመሥረት መዋል የለበትም፡፡ እነ ዕገሌ ስለ መሠረቱ፣ እነ እገሌ ስለተሰባሰቡ፣ የዕገሌ አካባቢ ሰዎች በስማቸው ፓርቲ ስለመሠረቱ፣ የዚህ ዓይነት ሞያ ሰዎች ማኅበር ስላቋቀቋሙ፣ የዚያ ሀገር ሰዎች ኮሙኒቲ ስለ ፈጠሩ፣ እንቶኔና እንቶኔ ኩባንያ ስላቋቋሙ እኛም ማቋቋም የለብን፡፡  
    መጀመሪያ ሃሳብ ይቅደም፡፡ ማሰብ ማለት ደግሞ ሃሳብን ብልጭ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ይህማ ታች በሌን መሆን ነው፡፡ ብልጭ ያለውን፣ ቁጭት የፈጠረውን ሁሉ ሳያስቡበት ተጣድፎ ማድረግ፡፡ ማሰብ እንዲህ አይደለም፤ ግራ ቀኝ የታሰበበት፣ የተጠናና የተነበበበት፣ ከቀደምቶች ልምድ የተቀሰመበት፣ ከተሳካላቸውም ካልተሳካላቸውም ትምህርት የተወሰደበት፣ እንዴት እንደሚኬድ፣ ግቡ ምን እንደሆነ፣ የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ፣ የሚያስፈልጉ ነገሮች ምን እንደሆኑ፣ ከነ ማን ጋር መተባበር እንደሚገባ፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል፤የፍልስፍና መስፈንጠሪያው ምን እንደሆነ አጥልቆና አልቆ መመርመር ነው- ማሰብ፡፡
    አንዳንድ ሰው አስቤያለሁ ሲል ‹‹ይህ ነገር በአእምሮዬ መጥቶልኛል›› ማለቱ ነው፡፡ ይህኮ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያጋጥመው ነው፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቱ መረጃዎች ወደ አእምሮው ሲገቡ ልክ በቁልፍ እንደሚነሣ መኪና ቅንጭሌውን ሊያስነሡት ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን መኪናው በቁልፉ ስለተነሣ ብቻ ሄደ እንደማይባለው ሁሉ ሰውዬውም አሰበ አያስብለውም፡፡ መጀመሪያ የመኪናው ባትሪ ቀጥሎ ሞተሩ መነሣት አለበት፡፡ ሞተሩ ደግሞ ሌሎችን ሁሉ አንቀሳቅሶ ሙሉ መኪናው መሥራት አለበት፡፡ ያን ጊዜ መኪናው ሄደ ይባላል፡፡
    ሰውም ሃሳብ ብልጭ ስላለለት፣ የሆነ ቁጭት ስለተፈጠረበት፣ ከሆነ ሰው አንዳች ነገር ስላገኝ፣ በአጋጣሚ አንድ መረጃ ስለደረሰው፣ ቅናት ስላደረበት፣ ዕድል ስለተፈጠረለት፣ ዘመዶቹ ክፈት እንረዳሃለን ስላሉት ብቻ ተቋም፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ማኅበር መመሥረት የለበትም፡፡ አንዳንዶች የሆነ ነገር ለማድረግ አስበው ከመሰባሰብ ይልቅ ተሰባስበው ምን እንናድርግ? ብለው ያስባሉ፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች እንደ ታች በሌ ሳያስቡ የሸፈቱ ናቸው፡፡ የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡፡ ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡ የስብሰባ፣ሞቅታ የፈጠራቸው ኮሚቴዎች ሃሳብ አጥተው ሲላጉ አባሎቻቸውን አንጠባጥበው መቼ እንደፈረሱ እንኳን ሳይታወቅላቸው ይፈርሳሉ፡፡ ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡
    አንዳንዶችም አሉ፤ ምን እንደሚጽፉ ሳያስቡ መጽሐፍ ለመጻፍ የሚነሡ፡፡ ምን እንደሚገጥሙ ሳያስቡ ግጥም ለማሳተም የሚውተረተሩ፡፡ ምን እንደሚያቀርቡ ሳያስቡ ፊልም ለማዘጋጀት ገንዘብ የሚያሰባስቡ፡፡ የተለየ ሃሳብ ሳይኖራቸው የሬዲዮ የዐየር ሰዓት የሚገዙ፡፡ ምን እንደሚጠይቁ ሳያስቡ የቃለ መጠይቅ ማይካቸውን ተጠያቂው ላይ የሚተክሉ ቀልደኞች፡፡ ለነገሩ በሠፈር አንድ ሱቅ ሲከፈት የሠፈሩ  ሰው ሁሉ አጥሩን እየቀደደ ሱቅ መሥራት የተለመደበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ያዋጣል ወይ? ከጎረቤቴ በምን እለያለሁ? እኔ ምን አዲስ ነገር አመጣለሁ? ብሎ ሳያስብ ነው ሱቁን ቦግ የሚያደርገው፡፡ ሱቁን ከሠራና ዕቃ ካስገባ በኋላ ነው ማሰብ የሚጀምረው፡፡ ይህ ነገር ወደ ተቋሞቻችንም ተጋብቷል፡፡ ምን ተቋሞቻችን ብቻ ትዳሮቻችንም እንዲህ እየሆኑኮ ነው፡፡ ማግባት የሚፈልግ እንጂ እንዴትና ለምን እንደሚያገባ፣ የጋብቻው ጠባይና አካሄድ ምን እንደሚመስል አስቀድሞ የሚያስብ ጥቂቱ ነው፡፡  የሆነ ቦታ ለመሄድ እያሰብኩ ነው፤ የሆነ ነገር ሳልከፍት አልቀርም፤ አንድ የሆነ መጽሐፍ ልጽፍ እያሰብኩ ነው፤ የሚላችሁ ሰው ሳያስብ አንዳች ነገር ሊያደርግ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
    አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ ገበያ መውጣታቸውን እንጂ ምን ሊገዙ እንደወጡ፣ ቤት መሥራትና መግዛት እንጂ ምን ዓይነት ቤት እንደሚገዙ ወይም እንደሚሠሩ፣ ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡ ለዚህ ነው ታች በሌያዊ የሆነውን መንገድ ትትን ሃሳብ ከተቋም ይቅደም የምለው፡፡ ሃሳብ ከድርጊት ይቅደም፡፡ ሃሳብ ከመመሪያም፣ ከዐዋጅም፣ ከማፍረስም፣ ከመሥራትም፣ ከመሸለምም፣ ከመቅጣትም፣ ከመሄድም ከመምጣትም ይቅደም ፡፡
    አንድ ሰው እንዲያውም ይህንን ነግሮኛል፡፡ የአንድ ገበሬ ውሻ ሁልጊዜ መንገድ ዳር እየቆመ አላፊ አግዳሚውን መኪና ለመያዝ እየተከተለ ይጮኻል፡፡ የገበሬው ጓደኛ ይኼ የውሻው ጠባይ ይገርመዋል፡፡ አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ  አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡