ከሐምሌ አንድ እስከ ሐምሌ ሰድስት 2013 እ ኤ አ፣ ለኢትዮጵያውያን ሰላሰኛውን ዓመት ለሚያከብረው የእግር ኳስ ውድድር በዲሲ ተገኝቼ ነበር። ይህ በዓል በኢሳት ተነግሮ ሰለነበር በዓለም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሣይቀር ዲሲን እንደ ቁለቤ ገብርኤል ልንሣለማት እንደ ድሬ ሼክሁሴን ሙዳ ልንላት ተገኝተናል። በአገራችን ከማንኛውም ክፍለሃገር ዛሬ ጎረቤት አገር ከተባለችው ኤርትራ ሣይቀር የሐረሩን የቁልቤ ገብርኤል የባሌውን ድሬ ሼክሁሴን እስላም […]

ከአዲስ አበባ ወደ አውስትራልያ ልጓዝ ነው፡፡
ትነሣላችሁ የተባልነው ከምሽቱ አራት ሰዓት ከ15 ነበር፡፡ ‹ነበር› ካልኩ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ የመሳፈሪያው አዳራሽ ውስጥ ተቀምጠን ግን የመሳፈሪያው ሰዓት በረረ፡፡ ሰዓቱ እኛን ጥሎን በሌላ አውሮፕላን ይብረር፣ ወይም የመሳፈሪያውን ሰዓት ያደረገው የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሳይመጣ ይቅር የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደግነቱ የአየር መንገዱም ሠራተኞች የተሰጣቸው መመሪያ ‹‹የመሣፈሪያ ሰዓት ካለፈ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሳታስነቁ ወዲያ ወዲህ ማለት ነው› የሚል ሳይሆን አይቀርምና አንዳቸውም ምን አልተነፈሱም፡፡
መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ ለማግኘት የሚታወቅ መንገድ (system) ስለሌለ የሚታወቅ ሰው መፈለግ ነው፡፡ አንዱን የማውቀውን ሰው ጠጋ ብዬ ስጠይቀው ለንደን ላይ አውሮፕላናችን መጠነኛ ችግር እንደገጠመው ሹክ አለኝ፡፡ ምናልባት በዚያ ተደናግጠው ይሆናል ብዬ ይቅር አልኳቸውና መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላም ሕዝቡን ወደ ስታዮም እንደሚገባ ተመልካች አንጋግተው ይዘውት ወረዱ፡፡ ‹‹ሕጻናት ያላችሁ፣ የቢዝነስ ክፍል አባላት፣የሼባ ማይልስ የወርቅ አባላት›› ብሎ ነገር የለም፡፡ ‹‹እየየ ሲዳላ ነው›› አሉን፡፡ የሰው ጎርፍ ወደ ታችኛው ፎቅ በደረጃው ፈሰሰ፡፡ 

በአውቶቡሱ በኩል ተሸጋግረን ወደ አውሮፕላኑ ገባን፡፡ የመቀመጫ ለውጥ እንጂ የሰዓት ለውጥ አልነበረውም፡፡ ለነገሩ ብዙ ጊዜ በሀገሪቱ የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና አልተገረምንም፡፡ ‹መሣፈሪያ አዳራሹ ውስጥ መቀመጥ ሰለቸን› ያልናቸው ይመስል አውሮፕላኑ ውስጥ አንድ ሰዓት አስቀመጡን፡፡ ደግነቱ አብራሪው እየደጋገመ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ከተለያየ ሀገር የሚመጡ ተሸጋጋሪ መንገደኞች እየተጠበቁ መሆኑንም ይነግረናል፡፡ መቼም የመጣውን አስቀምጦ ያልመጣውን መጠበቅ የተለመደ ነውና አላዘንኩበትም፡፡ ሠርግም ላይ፣ ስብሰባም ላይ፣ ጉባኤም ላይ፣ ግብዣም ላይ በሰዓቱ አክብረው የመጡት የዘገዩት እስኪመጡ እንዲጠብቁ በሚደረግበት ባህል ውስጥ ስላለን የሚገርም አይደለም፡፡
ከመቅረት መዘግየት ይሻላል ብሎ አውሮፕላኑ ወደ ዱባይ ተነሣ፡፡ ከጎኔ አንዲት እንደኔ አፍሪካዊት የሆነች፣ እንደ እኔ ግን ኢትዮጵያዊት ያልሆነች ሴት ተቀምጣለች፡፡ እርሷ እቴ ወደ አውሮፕላኑ እየገባች ሳይሆን አይቀርም ዕንቅልፍ የጀመራት፡፡ ደግሞ ስፋቷ ለሚኒ ባስ ታክሲ የመጨረሻው ወንበር እንጂ ለአውሮፕላን ወንበር የሚሆን አይደለም፡፡ ከመደገፊያው ተርፎ እኔ ጋ እየመጣ አስቸገረኝ፡፡ ሦስት ትራስ ደራርባ፣ በዚያ ላይ ፎጣ መሳይ ነገር ለብሳ ትለጥጠዋለች፡፡
እኔን መከራ ያሳየኝ ዕንቅልፏ አይደለም፡፡ እየተረፈ የሚመጣው ሰውነቷ አልበቃ ብሎ እንደ ፔንዱለም ስትወዛወዝ ትከሻየ ላይ እየመጣች ዘፍ የምትለው ነገር ነው፡፡ ሴትዮዋ የመጣችው ‹ሶሪ› ከሌለበት ሀገር ነው መሰለኝ ትከሻዬን ገጭታው ስትመለስ ከጥቁሩ ፊቷ መካከል ብልጭ የሚል ባለ ቀይ ድድ ጥርሷን ብቻ አሳይታኝ ‹ካለፈው የቀጠለ› ብላ ወደ ዕንቅልፏ ትገባለች፡፡ ትቆይና ደግሞ ክላሲካል ትለቃለች፡፡ ‹‹ፉርርርርርር›› የሚል የኩርፊያ ክላሲካል፡፡
መቼም በዚህ ክላሲካል ታጅቦ እንኳን ዕንቅልፍ መተኛት ቅዠት መቃዠትም አይቻልምና ከያዝኳቸው መጻሕፍት አንዱን አወጣሁ፡፡ ‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የሚል ካሕሣይ አብርሃ በተባለ የኢሕአሠ(የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ሠራዊት) ታጋይ የተጻፈ መጽሐፍ፡፡ መጽሐፉ ከሥነ ጽሑፍ አንጻር ብዙ የሚቀሩት ነገሮች ቢኖሩም የዚያን ዘመን ወጣቶች ታሪክ በማሳየት አንጻር ግን ማራኪ ነው፡፡  መቼም ሰው በአውሮፕላን ሲሄድ አውሮፕላኑ እንዳይወድቅ እንጂ ከአውሮፕላኑ ውስጥ ሰው እንዳይወድቅ የሚሰጋ አይመስለኝም፡፡ እኔ ግን አንድ ገጽም ሳላነብብ በቀኝ ትከሻዬ በኩል የሆነ ነገር ዘፍ አለብኝና ሰጋሁ፡፡ ተጠንቅቄ ዘወር ስል ሴትዮዋ ሳታስፈቅደኝ ትከሻዬን ተንተርሳዋለች፡፡ እንደምንም ታግዬ ሳስለቅቃት ነቅታ ጥርሷን ብልጭ ታደርግና ዕንቅልፏን ከተቋረጠበት ትቀጥላለች፡፡
አሁን ምን ተብሎ ይጸለያል? እኔ እስካሁን በቀኝ ትከሻ በኩል ዘፍ ለምትል ሴት መከላከያ የሚሆን ጸሎት የነገረኝ ሰው የለም፡፡ ከኔ መለስ ሳደርጋት በወዲያኛው በኩል ወደተቀመጠው ፈረንጅ ሄዳ ዘፍ አለች መሰል ‹ኦ ማይ ጎድ› ሲል ሰማሁት፡፡ ‹‹እስኪ ያንተ ጸሎት ከሠራ እኔም እጠቀምበታለሁ›› ብዬ ጠበቅኩት፡፡ ሲብስበት ጊዜ ከወንበሩ ተነሥቶ ወደ መጸዳጃ ቤት አመራ፡፡ የፈረንጅ ነገር፣ ለሁሉም ችግር ወደ መጸዳጃ ቤት ነው፡፡ ‹ከአፍርንጅ የምንለይበት›› የሚለው የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገራችን መጽሐፍ ትዝ አለኝ፡፡   
‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የዚያ ዘመን ወጣቶች ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ለነጻነት የነበራቸውን ታጋይነት፣ ላመኑበት ነገር ይከፍሉት የነበረውን መሥዋዕትነት፣ በሌላው ዓለም ያዩትንና ያነበቡትን በሀገራቸው ለማምጣት የነበራቸው ሕልም፣ ለአብዮት የነበራቸውን ጽኑ ፍቅር ያሳያችኋል፡፡ ያንን የመሰለ ትውልድ በጦርነት፣ በእሥርና በግድያ፣ በስደትና በጉስቁልና ማጣት ሀገሪቱን ምን ያህል እንደ ጎዳት ታዩበታላችሁ፡፡ ውጊያና ትግል፣ ስብሰባና ግምገማ፣ ኮንፈረንስና የእርምት ንቅናቄ፣ ተሐድሶና የፖለቲካ ትምህርት፣ ቋንቋው የነበረ አንድ ትውልድ እንዴት እንደጠፋ ትታዘባላችሁ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የአመራር እጦት፣ የብስለት መጥፋት፣ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ የትግል ስልት፣ የግለሰብን ነጻነት ያጠፋ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ ችግሮችን ሁሉ በመሣሪያ አፈሙዝ ለመፍታት የነበረው አመለካከት፣ ራስን በምሁራዊ አምባ ላይ አስቀምጦ ሌላውን የመናቅ አባዜ፣ ከተማ ላይ ተቀምጦ የገጠርን ትግል የመምራት ድንግርግር፣ በሀገሪቱ ትውልድ ላይ ያመጣውን ምስቅልቅልም ታያላችሁ፡፡
እነዚህን መሰል መጻሕፍት ሳነብ እጅግ የሚገርመኝ ነገር ያ ትውልድ ፈጽሟቸዋል ብለን የምናስባቸው ስሕተቶች ዛሬም እንደገና እየተመላለሱ መፈጸማቸው ነው፡፡ አሁንም ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ስንሞክር፣ አሁንም ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ ፓርቲዎች ከግለሰብ ነጻነት በላይ ሲሆኑ፣ አሁን የፓርቲ መሪዎች ችግሮችን በመከፋፈልና በመለያየት ሲፈቱ፣ አሁንም ሕዝብና ፀረ ሕዝብ፣ አንድነትና ፀረ አንድነት፣ አብዮታዊና ሊበራል፣ ኮሙኒስትና ካፒታሊስት የመከፋፈያ መሣሪያዎቻችን ሲሆኑ፣ አሁንም በጠላት መቃብር ላይ ሕንጻ የመሥራት አባዜ አልለቀን ሲል፣ አሁንም የተቃራኒያችንን አመለካከት ለማዳመጥ ትዕግሥት ሲያንሰን፣ ምን ያህል ከዚያኛው ዘመን ስሕተት እንዳልተማርን ያሳዩናል፡፡
ተዋጊዎቹ ወጣቶች በአንዳንዶቹ ውጊያዎች አይስማሙም፣ በአንዳንዶቹ ውጊያዎች ደግሞ ከአመራሮቻቸው ተቃራኒ የሆነ መረጃ አላቸው፣ ፓርቲውና ድርጅቱ እየተሳሳተ ያዩታል፣ ስሕተቶቹ የሚያስከፍሉትን ዋጋ በርግጠኛነት እያገኙት ነው፤ ነገሮች እንደማይሁኑ ሲሆኑ እየታዘቡ ነው፤ በተሳሳተ አመራር፣ በተሳሳተ የመፍትሔ ጉዞ፣ በተሳሳተ አሠራር የተነሣ ውድ የሀገሪቱ ልጆች ሕይወታቸውን ከጎናቸው ሲሠው እያዩ ነው፡፡ ነገር ግን ድርጅት፣ ፓርቲ፣ አመራር የሚባሉት ሰዎች አይሳሳቱም፣ እነርሱ ያሉት ሁሉ ቅዱስ ነው፣ እኔ ካየሁት ያላየው አመራር ይበልጣል፤ እኔ ስሕተት መሆኑን ባውቅም ፓርቲው ትክክል ነው ካለ ትክክል ነው፤ ሁለትና ሁለት ተደምሮ አራት የሚሆነው ፓርቲው ወይም ድርጅቱ አራት ነው ካለ ብቻ ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን ሦስትም አምስትም ሊሆን ይችላል ብሎ የማሰብ አባዜ ዋጋ ሲያስከፍል እናያለን፡፡ ዛሬም ግን ይሔው አስተሳሰብ በዚህች ሀገር ውስጥ ሥሩን ተክሎ ቅጠል አውጥቶ፣ አብቦና አፍርቶ እየታየ ነው፡፡ ካለፈው ተምሮ እርሱን ለማረም የሚተጋ አይታይም፡፡
አውሮፕላናችን ሁለት ሰዓት ያህል ዘግይቶ ዱባይ ገባ፡፡ እኔ ዱባይ የገባሁት ቀጣዩን አውሮፕላን ለመያዝ 15 ደቂቃ ብቻ ሲቀረኝ ነው፡፡ ምድር ከወረደ በኋላ የበረራ አስተናጋጆች የተወሰን ሰዎችን ስም ጠርተው ውጭ የአየር መንገዱን ሰዎች እንድናነጋግር አሳሰቡን፡፡ እሺ ብለን ስንወጣ አገኘናቸው፡፡ የሆነች ወረቀት ሰጡንና እንዲህ ያለ ቦታ ሄዳችሁ የሆነ ሰው ታገኛላችሁ ሩጡ አሉን፡፡ መቼም አበበና ማሞ፣ ምሩጽና መሐመድ ከድር፣ ኃይሌና  ቀነኒሳ ከተወለዱበት ሀገር የመጣን ነን ብለን ወደተባለው ቦታ ሮጥን፡፡ ሲዖል ይዘጋላችሁና የነገሩን ቦታ ሁሉ ዝግ ነው፡፡ አንዳች ሰው በአካባቢው የለበትም፡፡ ‹አይ አየር መንገዳችን፤ እነ ክበበው ገዳ የት ሄደው ነው እርሱ እንዲህ ያለ ቀልድ የሚቀልደው› ብዬ ተገረምኩ፡፡ ማንን እናናግር፡፡ በኋላ አንድ የአውሮፕላን ማረፊያውን ፖሊስ አገኘነውና ችግራችንን ስንነግረው በፍተሻ ማለፊያው በኩል አድርጎ ወደ ምድር ቤት ወሰደን፡፡
 ምድር ቤት ወርደን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ስንደርስ እነርሱ ምን አለባቸው አራት ሆነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ምናለ አንዳችሁ እንኳን እዚያ ተገኝታችሁ ብትረዱን›› አልኳቸው፡፡ ‹‹እገሊትኮ ነበረች›› አሉን፡፡ ትኬታችንን ተቀብለው አየት አደረጉና ‹‹አሁንማ ረፍዷል ቀጣይ አውሮፕላን ካለ እንይላችሁ›› አሉን፡፡ ለእነርሱ እየተባበሩን ነው፡፡ ስሕተቱን የፈጸሙት እነርሱ፣ የዘገዩት እነርሱ የምንቀጣው እኛ፡፡ እንዴው ግን እስከ መቼ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የደንበኞቹ ግንኙነት የባላባትና የጢሰኛ የሚሆነው? በባላባቶች ፍርድ ‹‹ምን ባላባት ቢያጠፋ ጢሰኛ ይክሳል›› ይባላል፡፡ አየር መንገዳችንም እንዲህ ሆነብንኮ፡፡ ‹‹ይቅርታ፣ እስኪ ዐረፍ በሉ፣ ችግሩን እንፈታዋለን›› ከአማርኛችን ውስጥ የሌሉ ይመስል ምነው ከአንደበታቸው አልወጣ አሉ?
‹‹እናንተ ባጠፋችሁ ቁጥር እኛ መቀጣት አለብን?›› አልኳቸው ኃላፊ የመሰሉትን ሴትዮ፡፡ምንም አልመሰላቸውም፡፡ ከሌላው አየር መንገድ ጋር በስልክ ተነጋገሩ፡፡ ደግነቱ ያኛው አውሮፕላን አርፍዷል፡፡ ‹‹ትደርሳላችሁ ሂዱ አሉን፡፡›› ሄድን፡፡ እንደተባለውም ደረስን፡፡ ዛሬ ከአየር መንገዳችን ጋር የሚወዳደሩም የሚፎካከሩም አየር መንገዶች በበዙበት ጊዜ እንዲህ በደንበኞች አገልግሎት ላይ መቀለድ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ለአየር መንገዳችን ኃላፊዎች ደጋግሞ ማሳሰብ ይገባል፡፡ የያዛችሁት አየር መንገድ ‹የኢትዮጵያ› ነው፡፡ የእናንተ አይደለም፡፡ እናንተ በምትፈጥሩት ስሕተት ግን የምትቀጣው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ዛሬ እነ አልጀዚራ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራ ክፉ ነገር ፍለጋ አሰፍስፈው በሚጠብቁበት ዘመን እናንተ ተባባሪ ሆናችሁ ክፉ ዜና የምትሰጡበትን ምክንያት እንኳን እኛ እናንተም የምታውቁት አልመሰለኝም፡፡
አሁን ከዱባይ ወደ ብሩናይ ለመጓዝ በሮያል ብሩናይ አውሮፕላን የመንገደኞች ማስተናገጃ ክፍል እገኛለሁ፡፡ ‹‹ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም›› ይባል ነበር፡፡ እዚህ ግን ፉርሽ ተደረገ፡፡ አየር መንገዳችን ያቃለለንን መንገደኞች የብሩናይ አየር መንገድ ሰዎች ጋብዘውና ተከባክበው ካሱን፡፡ ‹‹ብሩናይ የሚባል ስም ከዚህ ጉዞ በፊት ሰምቼ አላውቅም፡፡ በዙሪያየ የተቀመጡት እስያውያን ናቸው፡፡ ሰውነታቸው ቀጨጭ፣ ዓይናቸው ሰለምለም፣ ልብሳቸው ደመቅመቅ፣ ፀጉራቸው ወረድረድ ያሉ ሕዝቦች፡፡ በአካባቢው ያለሁት አፍሪካዊ እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ከዐርባ ደቂቃ በኋላ እንነሣለን ተብሏል፡፡ እስኪ ቀጣዩን መንገድ ደግሞ ሰላም ያድርገው፡፡
ዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዐረብ ኤምሬት  

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት […]

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል። እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ  ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል። በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ  የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5  አደራጃጀት …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2003 እና በ2004 ዓ.ም ግንባሩ 88 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ቀድሞ በባንክ አካውንት ውስጥ ከነበረው ሒሳብ ጋር ሲደመር ገቢው 171 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም ይፋ አድርጓል፡፡ 46 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከ“አዲስ ራዕይ” እና “ህዳሴ” ከተሰኙ ሕትመቶች ሽያጭ ነው ፡፡ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ  የመኪና ጋራጅ  ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት  ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር። ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን …

ከተመስገን ደሳለኝ

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ

…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይ ምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ፤ ወደ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ዉይይት ላይ መገኘታቸዉ ታውቋል። በዉይይት መድረኩ የተለያዩ ምሁራንና የሲቪክ ማሕበራት ተሳታፊዎች እንደነበሩ ለመገንዘብ ተችሏል።

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ፤በዛሬው ዕለት የግብዕን ጊዜያዊ መንግሥት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሞና ኦማርን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመለከተ።

ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።ስልኩም—

መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው […]

ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1997 የተደረገዉ ምርጫ ዉጤት ደም ባፋሰሰ ግጭት ካሳረገ ወዲሕ መንግሥትን በአደባባይ ሠልፍ መቃወም ለኢትዮጵያዉያን ዝግ ሆኖ ነበር።

«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ ተቀበለው» ነበር ያሉት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣ ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣ የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው። ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣ በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ […]

በቅድሚያ ርዕሰ-ጥያቄው አንፃራዊ መልስ የሚሻው በጣም አሳሳቢ እና :- የአገር ፍቅርን:-የሚገድል ዝምታ በኢትዮጵያውያን ላይ ሃያ ሁለት ዓመታት በመንገሱ ነው።ይህ አቢይ ጉዳይ እና ወሳኝ በመሆኑ ዝምታውን ለመስበር ደግሞ ወቅታዊነቱን እንረዳለን።የኢትዮጵያውያን እስልምና ዕምነት ተከታዮችን አንድነት እና ጥንካሬ በአፅንኦት ይመለከቷል:: እኛ ኢትዮጵያውያን ከሁሉም በፊት አስቀድሞ:- “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ነው።”{መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ-፻፲፩ ከቁጥር-፲ ፤መጽሐፈ ምሳሌ ም፩ ቁ፯ […]

በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . . አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና […]

መድረክ ነገ ሐምሌ 14 በመቀሌ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ሲቀሰቅሱ የነበሩት የአረና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ህሺ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀኔ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የአረና ፓርቲ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ለነገው ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳይደረግ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች ክልከላ ቢያደርጉም በነገው እለት […]

ባለፈዉ የካቲት ኬንያ ዉስጥ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ የፕሪዝዳንትነቱን ሥልጣን ከያዙ በኋላ አዲስን ካቢኔ ሾመዋል። ኬንያታ የሾምዋቸዉ ባለስልጣናት በአብዛኞቹ ከአሁን ቀደም በኬንያ የፖለቲካ መድረክ እንብዛም ያልተሳተፉ መሆናቸም ተነግሮአል። ይህ የኬንያታ አዲስ ጅማሮ ኬንያዉያን አዲስ ተስፋን አሰንቆላቸዋል።

ያሬድ ክንፈ ከኒዮ፣ ስዊዘርላንድ (ጥቂት ፎቶግራፎች ይዘናል)

በዓሉን ካደመቁት ሕፃናት በጥቂቱ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. July 20, 2013)፦ ረቡዕ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጁላይ 17፣ 2013) በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ክፍል ፭)
ውዴ:-

ባለፈው ከሳሚ ጋር ስለመጠለያ ጣቢያ ስንጨዋወት ስሙን መቀየር ስላልፈለገው ጓደኛቸው ያጫወተኝን እየነገርኩሽ ነበር ያቆምነው፡፡የሳሚ ታሪክ ይህንን ይመስላል፡፡ እሱን አንብቢና ስደተኛ በአውሮፓ የሚጠብቀውን ህይወት ገምቺ፡፡
 
ከዚያ
ጊዚያዊ ካምፕ የመቆያዬን ጊዜ ጨርሼ ወደተመደብኩበት ቋሚ መኖርያ ስሄድ ካገሬ ሥሰደድ ያልተሸኘሁትን አይነት ሽኝት በዚያ ካምፕ ባገኘኋቸው ወገኖቼ ተደረገልኝ። በውድቅት ሌሊት የምሔድበት መኪና የሚቆምበት ቦታ ድረስ መጥተው መልካም ምኞታቸውን ገለጡልኝ። እኔም አፀፋውን መለስኩና ወደዚያ ከተማ ሄድኩ። ከነዚህ የአጭር ጊዜ ወዳጆቼ ጋር እስከአሁን እንደዋወላለን። ወዴት እንደሄዱ ሳላውቅ ደብዛቸው የጠፉም ሞልተዋል።
ከትልቁ ጊዚያዊ መጠለያ ወደዚያ ስንሄድ አንድ አበሻ ብቻ ነበር የማውቀው። እሱም ከኔው ጋር ተመድቦ በአንድ ባቡር አብሮኝ የነበረ ነው። እዚያ የደረስነው ጥር አጋማሽ ላይ ስለነበር የነበረው አየር እጅግ ይገርም ነበር። መሬት የሚባል ነገር አይታይም። በሙሉ ነጭ ነው፣ ዛፉም የእግዜር ስሪት አይመስልም፣ ከመንጣቱና ከቅርፁ የተነሳ ሰውሰራሽ ይመስላል። ብርዱ ለመግለፅ በሚያስቸግር መልኩ ተስፋ ያስቆርጣል።
ከባቡር እንደወረድን የመጠለያው ሰራተኞች ፎቷችን ያለበትን ወረቀት ይዘው ስለነበር ገና ከደረጃው ስንወርድ በስማችን እየጠሩ ተቀበሉን። ወደውጭ ባየሁት ነጭ መልክዓምድርና የሚያቃጥል ቅዝቃዜ የተፈጠረብኝን ስጋት ለማርገብ ስለከተማውና ስለምንኖርበት ቦታ እየተርበተበርኩ እንደምንም ብዬ በምችላት ጥቂት እንግሊዝኛ መጠየቅ ጀመርኩ። ሁኔታዬን የተረዳው ሰራተኛም “አይዞህ ሁሉም ሲመጣ እንዳንተው ይሆንና ትንሽ ሲቆይ ይለምደዋል” አለኝ።
ከመኪናው አስገብቶን ለ30 ደቂቃ ነዳው። ግራ በመጋባት አብሮኝ ካለው ልጅ ጋር ተያየን። ወዴት ነው የምትወስደን ብለን ጠየቅነው። “እዚሁ ነው! የናንተ መጠለያ  ከከተማው ወጣ ይላል፣ አይዟችሁ ባካባቢው የሚኖር ማሕበረሰብ ስላለ የገበያ ችግር የለም” አለን።

ሶስት የዶከካቸው ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃዎች እንደመልክዓ ምድሩ ነጩን በረዶ ተሸከመው ተኝተዋል። በመካከላቸው ባለ ክፍት ቦታ ላይ እንደጨው ክምር የተቆለለ በረዶ ሶስተኛውን ሕንፃ ሸፍኖታል። የሰውየው መኪና እየተንደረደረ ሄዶ እዚህ ግዙፍ የበረዶ ክምር ስር አረፈ። አወረዱንና ቢሮው ወደሚገኝበት ወደመኻለኛው ሕንፃ አስገቡን። በስርዓት አስተናገዱን። የመጠለያውን ሕግ አነበነቡልን፣ ለሶስት እንድንኖር ብቻውን ይኖር ወደነበረ ወደ አንድ ኤርትራዊ ክፍል አመላከቱን። የክፍሉን ቁልፍና የምንበላውን እንድንገዛ ገንዘብ ሰጡን። ሁሉን ጨርሰን ቢሯቸውን ለቀን ወደውጭ ወጣን።
ስገባ አንድ ሕንፃ ብቻ ነበር ያየሁት፤ ስለ ሶስት ሕንፃዎች ሲነግረኝ ግር አለኝ ። ‘እዚህ ከመምጣትህ በፊት ሌላ ቦታ ኖረህ ነበር ማለት ነው?’ብዬ ጠየቅኩት።
አዎ፤ እዛ ሶስት ወር ኖሬ አመመኝ ብዬ ነው ወደዚህ የቀየሩኝ። አውቆ መታመም እችልበታለሁ፤ በስደተኛውም ዘንድ  አውቆ ማበድና መታመም የተለመደ ነው። አመመኝ ብዬ ጠብ ስል ደንግጠው ወደዚህ መደቡኝ። ያ ቦታ በጣም ከባድ ነበር። ሰው የምርጫዎቹ ጥርቅም ነው ይባል ነበር። እዛ ተመድቤ የሄድኩ ቀን ግን እንዳልሆነ ታረዳሁ። እኔና ጓደኛዬም እንደተራራ በተከመረው በረዶ ስር ቆመን ተኮራረፍን፣ አብዝተን ተከዝን፣ ተስፋ ቆረጥን። ተስፋ ከመቁረጣችን የተነሳ የሚያቃጥለውን ብርድ ረስተን እውስጡ ተገትረን ቀረን። ወደምንሔድበት ግራ ገባን። ራቅ አድርገን ስናይ ከጎናችን ያለውን የበረዶ ክምር አብዝቶ የሚበልጥ ነጭ ተራራ እይታችንን ይገድበዋል። ቀና ስንል የከፋው ሰማይ ምን እንደያዘ’ንኳ እንዳያስታውቅ ሆኖ በቅርብ ርቀት በጉም ተጠቅጥቋል። የሚታዩን ሶስቱ ሕንፃዎች ድኃዋ አገራችን ላይ ለእህል መጋዘንነት የሚታነፁትን አይወዳደሩም። ውስጣቸው ያሉት ስደተኞች ለምንም ግድ ያላቸው አይመስሉም። ይወጣሉ ይገባሉ። በረዶውን በትልቅ ጫማቸው እየሰነጠቁ ያልፋሉ ያገድማሉ እኛም ላይ እንደትንግርት ያፈጣሉ።
ያንን መጠለያ ካለፈው የሚለየው የጥገኝነት ጥያቄ መልስ የሚሰጠን በዚህ ቦታ ተቀምጠን በመጠበቅ ነበር። ብዙ ጊዜ እንደሚያስጠብቁን ሳስበው ደግሞ ቦታው የበለጠ እየቀፈፈኝ ሄደ። ከዚህ የባሰ የሚያስጠብቁ አገሮች እንዳሉ ግን እሰማ ነበር። እዚያ የሚኖሩት ስደተኞች እንደበፊቱ ከብዙ አገር የመጡ አይደሉም። ከአፍጋኒስታን፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሌ፣ ከኢራን፣ ከኢራቅና ከኮንጎ የተሰደዱ ይበዛሉ።
ቢሆንም ግን በዚያኛው መጠለያ አበሻው እራሱን አግሎ ለብቻው ነው የሚኖረው። እዚያ መጠለያ የሄድን ቀን ከቆምንበት የበረዶ ክምት ስር እንደተገተርን አንድ አበሻ መጣና ጨበጠን። ስሙንም ነገረን። ከመጣሁ ሰባት ወሬ ነው ሲለን እንደጀግና በተደሞ ተመለከትነው። እዚህ ነጭ ጫካ ውስጥ፣ የበረዶ ግግር መኃል ሰባት ወር! ጓደኛዬም አብሮኝ ተገረመ። መልስ አግኝቶ እንደሁ ስንጠይቀው አላገኘሁም አለን። እንዲያውም አመትና አመት ተኩል እምደሚያስጠብቁ አረዳንና እዛው ጥሎን ሄደ። 
“ይሄ ደግሞ ምን ጋግርታም ነው፣ እንግዶች ነን፣ እቤት እንግባ’ንኳ አይልም ‘ንዴ” እያልን እየወረድንበት ባይናችን ሸኘነው። እየዘፈነ ጥሎን ሄደ። አማትረን አማትረን ያገኘነው ሰው ሰው አልሆን ሲለን ተያይዘን ጉዞ ጀመርን፣ ወደሱፐር ማርኬት። ባናውቀውም ይሆናል ብለን ወደገመትንበት አቅጣጫ መራመድ ጀመርን። መኪናዋ ይዛን ስትመጣ በረዶው ላይ የተወችውን የጎማ ምልክት ተከትለን መራመድ ጀመርን።
በነጩ ምድር ላይ ኮቴያችንን ሿ ሿ ሲል እየሰማን በፀጥታ ስንራመድ ሱፐር ማርኬት አገኘን። በቃ እንዲህ ጀመርነው ኑሮውን። ገዛዝተን ስንመለስ የተመደብንበት ክፍል ውስጥ የሚኖረውን ልጅ ከቤት አገኘነው። ቁጭ ብሎ እኛን ይጠብቃል። እንግዳ ይመጣብሓል ተብሎ የተነገረው ቀደም ብሎ ስለነበር አልጋችንን ብቻ ሳይሆን ምግባችንንም አዘጋጅቶልን ነበር የጠበቀን። አበሻዊ አቀባበል ሲገጥመን የገዛነውን ከነፌስታሉ ገለል አድርገን ክሽን አድርጎ ያሰራውን ዶሮ መብላት ጀመርን። እኛ ስለመጠለያው እየጠየቅነው፣ እሱ እየመለሰ በልተን ጨረስን። አንድ ኢትዮጵያዊና ብዙ ኤርትራዊ በመጠለያው እንደሚኖር ነግሮን ማታ ሊያስተዋውቀን እንደሚወስደን ነግሮን ክፍሉን ጥሎልን ውልቅ አለ። እኛም አመስግነን አልጋችንን ማንጠፍ ጀመርን።
‘ከኤርትራዊ ጋር ኖረኻላ? እንዴት ናቸው ኤርትራውያን? እንዴት ነበር አንተ የነበርክበት መጠለያ?’ ስለ ኤርትራውያን ስደተኞች ለማወቅ ያለኝን ጉጉት በጥያቄ መዓት በማቅረብ ገለፅኩለት።
እንዲህ ሲል መተረክ ጀመረ። እዚያ መጠለያ ውስጥ ሶስት ኢትዮጵያውያኖች ብቻ ነበርን። አንዱ ያ ጋግርታሙ ስለሆነ እንደሌለ ቁጠረው፣ አንዱ አብሮኝ የሄደው ልጅ ሲሆን ዘመድ አለው መሰል ወዲያው መጠለያውን ለቆ ወደከተማ ሄደ። እኔም ኬዜ ኤርትራዊ ስለሆነ ለመምሰል ጥረት አላደርግም። ኤርትራዊ ነኝ ማለት እንዴት እንደሚከብድ ይገርምሃል፤ ስጠየቅ ወይ ዝም እላለሁ ወይ ኢትዮጵያዊ ነበር  የምለው። ታዲያልህ ለሶስት ወራቶች ስኖር የገጠሙኝ ስደተኞች በአብዛኞቹ ኤርትራውያን ናቸው። ከተሰደድኩ<

አቡነ ጢሞቴዎስ ጉዳያቸው ከሚታይበት ስብሰባ ላለመውጣት ሲለመኑ ውለዋል ኣቦይ ስብሐት አቡነ ጢሞቴዎስን ለማግባባት በቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል ፓትርያሪኩ ስለ አቡነ ጢሞቴዎስ ብዙ ከመናገር ተጠንቅቀዋል፤ ተቆጥበዋል ደቀ መዛሙርቱና መምህራኑ ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር እየገለጹ ነው የንቡረ እድ ኤልያስ ምደባ ግዙፍ ከሚያስነሣው ግዙፍ ጥያቄ ጋራ የምረቃው ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል. . .

ኢትዮጵያንና ህዝቧን የአብሮነትን መሠረት ለመሸርሸርና ብሎም ለማጥፋት ሌተ ቀን የማይተኛዉ የህወሀት ኢህአዴግ አሸባሪ መራሹ መንግስት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ዜጎችን ማሰቃየት ከጀመረእነሆ ፪፪ አመት ተቆጥሮዋል።ነገር ግን የ፪፪ አመት ቆይታዉ ህዠብን ከማሸበር፣ ከመግደል፣ከማሰር ከማሰደድ፣ከመግረፍና ከማፈናቀል አልፎ በተመቸዉና የጥፋት ምርቃናዉ በመጣለት ቁጥር በዘረኞች መሪዎቹአማካይነት በፈለገዉ ሰዐት ከራሱ ህግና ስርአትዉጪ ከእንቅልፋ እንደሚነቃና የሚያደርገዉን እንደማያቅ ህፃን ልጅ የተለያዮ ህጎችን […]

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በረመዳን ጾም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ተቃውሞ ይበርዳል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ ተቃውሞው ከሳምንት ሳምንት እያየለ በመምጣቱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ከሀሙስ ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ አባላት ክትትል ስር የነበሩት የወልድያ ሙስሊሞች በዛሬው እለት በመስጊዳቸው ውስጥ ታግተው መዋላቸውና አንዳንዶች መደብደባቸውን ሌሎች ደግሞ መታሰራቸው …

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ባህርዳር፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና አዲስ አበባ ለህዝባዊ ሰልፎች ሲመረጡ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ደብረማርቆስና አዲስ አበባ በድጋሜ ለህዝባዊ ስብሰባዎች ተመርጠዋል። ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና …

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጠናቅሮ ለክልሉ ባለስልጣናት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንተመለከተው የክልሉ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብና የቅርስ ዘረፋ እንዳይካሄድ በመከላከል በኩል በቂ ጥረት አላደረገም። በክልሉ ከ3000 በላይ የቅርስ መገኛ ተቋማት ቢኖሩም  ሙዝየም በማሰራት ቅርሶቻቸውን በጥንቃቄ ለእይታ የቀረቡት 13 ብቻ መሆናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በተለያዩ …

ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡእ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ  ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል። ሱዳን ትሪቢውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው የጭስ …

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጦር ሠራዊት M-23 በሚል መጠሪያ በሚታወቀው አማጺ ኅይል ላይ መልሶ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሯል። በታንክ፣ በሄሊኮፕተር ፤ አዳፍኔና ከባድ አውቶማቲክ ጠብመንጃ ፣ ወታደሮቹ ከጎማ ከተማ በስተሰሜን ፣ የአማጽያኑን ምሽግ መደብደባቸውን የዜና አውታሮች አስታውቀዋል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼ ቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የእንግሊዝና የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የልማት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጡት ድጋፍ በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ ሲል አንድ ድርጅት ከሰሰ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አዉሮፕላኖች የሚመጡልንን እቃዎች በወቅቱ ባለመረከባችን ተጉላላን ሲሉ አንዳንድ የአየርመንገዱ ደንበኞች አማረሩ።

በማናዬ በላይ
      VII.        የአምበድከር እና ጋንዲ አለመግባባት
    ማህተመ ጋንዲ ከአምበድከር በብዙ እድሜ የሚበልጥ ቢሆንም ሁለቱም የህንድ አይከኖች በተመሳሳይ ወቅት በህንድ ፖለቲካ ስርዓት ዉስጥ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በትምህርት፣ በአንደበተ ርቱዕነት፣ በፍልስፍና አምበርከር ከጋንዲ ብዙ ርቀት የተጓዘና ለዉድድር የሚቀርብ ባይሆንም በወቅቱ በፖለቲካ ተቀባይነት እና በድጋፍ ጋንዲ ከአበድከር እጅጉን የበዛ ድጋፍ ነበረዉ፡፡ በዛ ወቅት ከጋንዲ የተለየ ሀሳበ መያዝ በራሱ ከህዝብ ጋር ከማጋጨት በተጨማሪ በወቅቱ በህንድ እንደ ፋሽን ተይዞ ለነበረዉ ፖለቲካዊ ግድያ ሊዳርግ ይችላል፡፡ የከፍተኛ ካስት አባል መሆኑ እንዲሁም ህንድ ጀግና በተጠማችበት ጊዜ የመጣ መሆኑ ጋንዲን ለእዉቅናዉ ጠቅሞት ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ጋንዲን ተቃዉመዉ ሃሳባቸዉን በግልፅ ከሚያንፀባርቁ ግለሰቦች መሀከል ዶ/ር አምበድከር ዋንኛዉ ነበር፡፡
    ጋንዲ የሁሉም ሂንዲ ሹድራን ጨምሮ ወኪል ነኝ ብሎ ስለሚያስብ ከሱ ዉጭ ያለ ማንኛዉንም መሪ አይቀበልም አምበድከር በበኩሉ የሹድራና እና የሌሎች ካስት ሂንዱ ጥያቄ አንድ ካለመሆኑ ባሻገር የሚጋጭ በመሆኑ ጋንዲ ሊወክለን አይችልም የሚል ቆራጥ እሳቤ ነበረዉ፡፡ በዚህ መሰረት እንግሊዞች ይህንን ተቀብለዉ ይመስላል ለንደን ላይ በ1930-32 ስለ ህንድ ፖለቲካል ስርዓት ለመወያየት ለተከናወነዉ ስብሰባ አምበድከር የሹድራ መሪ ሆኖ እንዲሳተፍ ደብዳቤ ይደርሰዋል ይህንን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋንዲ ጥሪ አምበድከር እና ጋንዲ ቦምቤ ተገናኝተዉ የተወያዩ ሲሆን ዉይይቱ ባለመስማማት የተቋጨ ነበር፡፡
    ዶ/ር አምበድከር ለሹድራ ጭቆናና የበታችነት ዋንኛ ተጠያቂ አድርጎ የሚያቀርበዉ የካስት ስርዓቱን ሲሆን ለዚህ መወገድም አበክሮ ይሰራ ነበር፡፡ የሹድራን የአገልጋይነት እና የበታች ሆኖ የመኖርን ስርዓት ሕግ በሚመስል መልክ የሚገልፀዉ የማኑስምሪትን (የሂንዱ የሐይማኖት መጻሕፍ) በማቃጠል በወቅቱ እንደ ታቡ የማይወራበትን የሂንዱ ሐይማኖት መሰረት የሆነዉ ካስት ይወገድ ዘንድ በግልፅ በመስበክ፤ ይህንንም ለማሳካት የፖለቲካ ስልጣን ወሳኝ መሆኑን በማመን ወደ ፖለቲካዉ ገብቶ ጫና በመፍጠር በመጨረሻ ዉጤታማ የሆነበትን ሕገ መንግስት ለማፀደቅ በቅቷል፡፡
    የጋንዲ እሳቤ ከዚህ የተለየ ነበር እሱ የካስት ስርዓት የህንድ ማኅበረሰብ እሴት አድርጎ የሚያስብ የማኅበረሰብ በደል ያልቆጨዉ ለመሰረታዊ ለዉጥ ሳይሆን በጥቃቅን ነገሮች ጥያቄዎን ለማድበስበስ  የሚጥር ነበር፡፡ እንደ ምሳሌ ጋንዲ መሰረታዊ ችግሩን ለማስወገድ ከመስራት ይልቅ አይነኬ የሚለዉን የዚህ ማኅበረሰብ ስያሜ በሀሪጃን (የአምላክ ልጆች) በሚል እንዲቀየር እንዲሁም ካስትን ከማስወገድ ይልቅ ከካስት ዉጭ ያሉትን የመጨረሻዉን ሹድራ ካስት ሰጥቶ ማመሳሰልን የሚሰብክ ነበር (አይነኬዎች በመጨረሻዉ ዝቅተኛ ቫርና ያሉት እና ካስት የሌላቸዉን ሂንዱ ይጨምራል)፡፡ ጋንዲ ለካስት ስርዓት ይህንን ያህል ተቆርቋሪ ሆኖ የሚታገለዉ በወቅቱ የነበረዉን ፖለቲካዊ ተአማኒነት ላለማጣት እንጂ አምኖበት አልነበረም፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነዉ ጋንዲ ከሶስተኛዉ ከነጋዴ ስራ የሚመደቡ የካስት አባል ቫይሲያ አባል ሲሆን የኖረዉ ግን የብርሀሚን ካስት የሚሰራዉን ፕሪስት በመሆን ከመሆኑ ባሻገር ልጁም ቢሆን ይሰራ የነበረዉም ከንግድ ዉጭ የጋዜጠኝነት ስራ ነበር ይህም በሂንዱ የሐይማኖት መጻሕፍት ከፍተኛ ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ፡፡ ጋንዲ በዚህ ስርዓት እንደማያምን የሚያሳየዉ ሌላዉ የሚሰጣቸዉ መግለጫዎች እና ጽሑፎች ሲሆን በወቅቱ በጋንዲ መስራችነት ይታተም የነበረዉ ያንግ ኢንዲያ በኋላም ሀሪጃን የእንግሊዝኛ ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ የአይነኬነትና ካስት ተቃዋሚ ሆኖ መግለጫ ይሰጥና በአካባቢዉ ቋንቋ ጉጂራቲ በሚፅፈዉ ጽሑፍ ደግሞ አክራሪ ሂንዱ በመሆን ለካስት ስርዓት እንደሚታገል ይገልፅ ነበር፡፡ 
    ጋንዲ በወቅቱ ተደማጭነቱን ተጠቅሞ ከሚያደርገዉ ፕሮፖጋንዳ በተጨማሪ በወቅቱ ሹድራ ተለይተዉ በራሳቸዉ ዉክልና ያገኙ ዘንድ በዶ/ር አምበርከር ተደጋጋሚ ጥያቄ በራምሴ ማክዶናልድ የተሰጠዉን ዉሳኔ ተቃዉሞ በተደጋጋሚ ለጠ/ሚሩ የጻፈዉ ደብዳቤ ተቀባይነት እንዳላገኘ ሲያዉቅ በወቅቱ በእጁ የነበረዉን ትልቅ መሳሪያ ተጠቀመ፡፡ ጋንዲ ይህ ዉሳኔ ካልተቀየረና ሹድራዎች ከሂንዱ ተለይተዉ የተለየ የምርጫ ክልል ከተሰጣቸዉ እስክሞት እፆማለሁ በማለት በ1932 ያዉጃል፡፡ በዚህ ወቅት ከያቅጣጫዉ በአምበድከር ላይ ጫና ይደርስበታል ጋንዲ ከሞተ ህንድ በእርስ በርስ ጦርነት እንደምትታመስ ግልፅ ሆነ፡፡ አምበድከር ጋንዲ መጣ ጋንዲ ይሄዳል የኔ ህዝቦች ግን ለዘላለም ኗሪ ናቸዉ በሚል ለአምስት ቀናት በእንቢተኝነት ቢቆይም በወቅቱ የነበረዉ የሀገሪቱን ዉጥረት መቋቋም ባለመቻልና የሚመጣዉን ዉጤት በመፍራት ከኮንግረስ መሪዎች ጋር ከስድስት ቀን የጋንዲ ፆም በኋላ ፖና ፓክት ተብሎ የሚጠራዉን ስምምነት ፈረሙ፡፡ በዚህ ስምምነት የተለየ ምርጫ ለሹድራ መሰጠቱ ቀርቶ በሂንዱ ዉስጥ ሪሰርቬሽን እንዲሰጣቸዉ ተስማሙ፡፡ እንደ አንዳንዶች ገለፃ ይህ ባይሆን ኖሮ ህንድ አሁን ካለችበት ማኅበራዊ ችግር ቀድማ ትወጣ ነበር፡፡ ችግሩ መልኩን ቀይሮም ቢሆን አሁንም አለና (ከፍተኛ ሂንዱዎች አሁንም የፖለቲካ ስርአቱ ተቆጣጣሪ ናቸዉ)፡፡ ጋንዲ ለካስት ስርዓት ለረጂም ጊዜ ሲታገል ከቆየ በኋላ በመጨረሻ በ1946 አቅራቢያ ካስት ያለፈበት ስርዓት ነዉ በሚል ከአምበድከር ጋር አብሮ ቆሞ ሲታገል ነበር፡፡ ዘግይቶም ቢሆን የአምበድከረን ሀሳብ መቀበሉ አሁን ላለዉ የተሻለ የህንዳዉያን ንቃተ ህሊና እና ፖለቲካ ለዉጥ አስተዋፅኦ ነበረዉ፡፡ ለአብዛኛዉ ህንዳዊ ጋንዲ ማለት ብዙ ነዉና እሱ ካለ አለ ነዉ ሌላዉ አፉን ሊዘጋ ይገባል፡፡
    በእድገት እሳቤ ላይም ቢሆን ዶ/ር አምበድከር እና ጋንዲ የተለያየ እሳቤ ነበራቸዉ፡፡ ጋንዲ ወደ ተፈጥሮ እንመለስ የሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ አራማጅ ከመሆኑ ባሻገር ሆስፒታል፤ ባቡር ትራንስፖርት፤ ኢንዱስትሪ አላስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያምን ነበር፡፡ ዶ/ር አምበድከር በበኩሉ ወደ ተፈጥሮ እንመለስ ጥሪ ማለት ወደ ባዶነት፣ ወደ ሰቆቃ እና ረሀብ አብዛኛዉን ማኅበረሰብ መክተት ነዉ ይል ነበር፡፡
    በእርግጥ በብዙዎች አዕምሮ ሊመጣ የሚችለዉ ታዲያ ለምን ጋንዲ በአለም ላይ ታዋቂ ሆነ የሚል ነዉ፡፡ በወቅቱ ህንድ ጀግና የተጠማችበት ጊዜ ነበር፡፡  እንዲሁም የህንድን ፖለቲካ ስርዓትን የተቆጣጠሩት የከፍተኛ ካስት አባል ሂንዱዎች አስበዉበት ለዚህ አላማ ማለትም ጋንዲን ታዋቂ ለማድረግ የሰሩት ፕሮፖጋንዳ እንደ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል፡፡ የህንድ ማኅበረሰብ አሁን ስለ ዶ/ር አምበርከርም ይሁን ጋንዲ ትክክለኛ ግንዛቤ አላቸዉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ለጋንዲ የሚያደርጉትን ለአምበድከርም ያደርጋሉ፡፡ የዶ/ር አምበድከር ወሳኝ ቀናት እንደ ዉልደት፤ ሞት ፤ ቡድሂዝምን የተቀበለበት ቀን በመላዉ ህንድ በአብዛኛዉ ማኅበረሰብ ይከበራል፡፡ የተወለደበት የሞተበት፤ ሰላማዊ ትግል ያከናወነበት ቦታ ዋንኛ የቱሪስት ቦታዎች ሆነዋል፡፡ ችግሩ ያለዉ በሌላዉ ዓለም ሲሆን አብዛኛዉ ማህበረሰብ ህንድን ከጋነዲ ጋር እንጂ ከዶ/ር ባባሳሂብ አምበድከር ጋር አያይዞ አያነሳትም፡፡ ይህም ሥነ-አመክንዮ ያለዉ አይመስልም፡፡
    —
    ‹‹በጭቆናና በበደል የተፈተነ የፍትህ እና እኩልነት አባት – ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር›› በሚል ርዕስ ማናዬ በላይ በአራት ተከታታይ ክፍሎች ያቀረበልን ጽሑፍ በዚሁ ተጠናቋል፡፡
    —
    ጸሐፊውን ለማግኘት [email protected] ላይ ይጻፉላቸው፡፡