‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንግስት ዘላቂነት የለውም!›› ሙስሊሙ 40 ዓመት የሞላውን የተቃውሞ መፈክር ዛሬም ዳግም ያነሣል!
‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንግስት ዘላቂነት የለውም!››ድምፃችን ይሰማ መግለጫ
ሙስሊሙ 40 ዓመት የሞላውን የተቃውሞ መፈክር ዛሬም ዳግም ያነሣል!
አገር አቀፍ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የሚኖሩን ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
ቅዳሜ ነሐሴ 28/2008
ትግላችን ከአምስት ዓመታት በፊት ሲጀመር ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ይዞ የተነሳ ሲሆን ጥያቄዎቹን ለማስመለስም ሰላማዊ እና ህጋዊ መንገዶችን ተከትሎ ዘልቋል። ይህም ሆኖ መንግስት ለጥያቄዎቻችን መልስ ከመመለስ ይልቅ የሀይል እርምጃ መውሰድን እና በአምባገነንነቱ መቀጠልን መርጧል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም በሙስሊምነቱ ብቻ ከድብደባ እስከ ቶርቸር፣ ከእስርና ስደት እስከ ሞት፣ ከቁርአንና ሂጃብ መቃጠል እስከ መስጂድ መደፈር ድረስ ጥቃት አስተናግዷል። ዛሬ ላይ ትግላችን ማዕቀፉን በማስፋት በሶስት ጥያቄዎች ሳይገደብ ብሄራዊ ጭቆናን ለመታገል እና ሙሉ መብታችንን በዘላቂነት ለማስከበር በሚል ዓላማ ቀጥሏል።
ትግላችን የአምባገነኖችን ምርኩዝ ሰብሯል!
አምባገነኖች ህዝብን ረግጠው ለመግዛት የሚጠቀሙበት ዋነኛው መሳሪያ ፍርሀትን በህዝብ ውስጥ መልቀቅ ነው። ህዝብን ከብዙ አቅጣጫ ሊያስፈራሩት ይሞክራሉ፡፡ ሞትንና አካል የሚያጎድልን ከባድ ቅጣት በመቅጣት፣ ‹‹የውጭ ጠላት መጣላችሁ›› በማለትና ህዝቡን ከፋፍሎ እርስ በርስ እንዲፈራራ በማድረግ ህዝብን ፀጥ ለጥ አድርገው ይገዛሉ፡፡ የኢህአዴግም መንግስት ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በአገራችን አስፍኖት የነበረው ይህንኑ ስልት ነበር።
መንግስት በሀምሌ 2003 ግልጽ ያወጣው ቀጥተኛ የሆነ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ህዝበ ሙስሊሙ ቤት ለቤት አውርቶት ወይም በጋዜጣና መጽሄት አንብቦት የሚቀር ጉዳይ አልሆነም። ፍርሀትን ሰብሮ መውጣት እና መብትን መጠየቅ ግድ ሆኖበታል። በዚህም የአምባገነኑን ስርዓት ትልቅ ምርኩዝ ዳግም ላይጠገን መስበር ችሏል። የሙስሊሙን ጥያቄ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን በጥርጣሬና በፍርሀት እንዲያዩት፣ ብሎም የመንግስትን ፍትህ አልባ እርምጃ እንዲደግፉ የሞከረ እና ሌሎችም በርካታ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን የሰራ ቢሆንም አንድ ጊዜ የተሰባበረ ፍርሀት ዳግም በህዝባችን ላይ ላይሰፍን ብን ብሎ ጠፍቷል። በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተቀጣጥሎ የምናየው እና ኢትዮጵያዊያን በአምባገነናዊው ስርዓት የጭካኔ እርምጃ ሳይበገሩ፣ ለንብረታቸውና ለነፍሳቸው ሳይሳሱ እያደረጉ ያለው ተጋድሎ ለዚህ ከምንም በላይ ማስረጃ መሆን ይችላል።
መንግስት ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ በአገራችን አስፍኖት የነበረው የፍርሀት ድባብ ተገፏል፡፡ አምባገነንነትን ያሰፈነው የፍርሀት መጋረጃ ተቀዷል። የአገሪቱ ሁለት ትላልቅ ብሄሮች (የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች) በተቃውሟቸው ሰፊ የአገሪቱን ክልል እያዳረሱ ነው። ከስህተቱ መማር የማያውቀው ስርዓት ግን አሁንም የህዝቦችን ጥያቄ ከመስማትና ከመመለስ ይልቅ በአረመኔያዊ እርምጃው ህዝባችንን በማሸማቀቅ ዳግም ፍርሀት ለማንገስ ሲማስን ይስተዋላል። የሙስሊሙን ህብረተሰብ የእምነት ተቋማት በመድፈር እና እሴቶቻችንን በማውደም በአምልኮ ቦታችን ውስጥ ሳይቀር በግፍ መግደሉን ቀጥሎበታል። ይህ ሁሉ ከንቱ ልፋት የህዝባችንን የመታገል አቋም ይበልጥ ቢያጠናክረው እንጂ ዳግም ፍርሀት በጫንቃችን ላይ ሰፍኖ ዘላቂ መብታችንን ለማስከበር ከምናደርገው ትግል እንድናፈገፍግ አያደርገንም።
የኢህአዴግ መንግስት የተነሳበትን የህዝብ ቁጣ ለመቀነስ፣ ብሎም አቅጣጫ ለማሳት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጓል። ራሱ ያቀነባበራቸውን ‹‹የሽብር ስራዎች›› የሚተርኩ ዶኩመንታሪዎችን ሰርቶ በመገናኛ ብዙሃን ለቋል። ጥይት ከመተኮስ አልፎ ቦንብ እስከመወርወርም ደርሷል። ታህሳስ 01/2008 በአንዋር መስጊድ በተላላኪዎቹ የቦንብ ጥቃት እንዲሰነዘር አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ በምዕራብ ሀረርጌ መሰላ ወረዳ መስጊድ ላይ ቦንብ በመጣልና የእምነት ተቋማችንንም በማቃጠል ከሀያ በላይ ሙስሊሞች ገድሏል። ይህ እርምጃ ባለፉት አምስት አመታት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የደረሰውን በደል ከፍ የሚያደርግ እና ሙስሊሙን እና እስልምናን በተመለከተ ስርዓቱ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ እና አቋም የሚያሳይ ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው እለት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳ ቃጠሎ እና የተኩስ እሩምታ በርካታ ታሳሪዎች ስለመጎዳታቸው የተሰማ ቢሆንም መንግስት በጉዳዩ ላይ የተጣራ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለማጣራት የሞከሩትን በማባረርም ከአንድ ሰው ውጭ ህይወቱ ያለፈ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በትንሹ ከ22 ሰዎች በላይ ህይወታቸው እንዳለፈ የወጡ መረጃዎች መኖር እና የመንግስትም የማጣራት እገዳ ታክሎበት አንዳች ተንኮል መኖሩ የሚያጠራጥር አይመስልም፡፡ ዜጎች በሃሰት ክስ እስር ቤቶች ገብተውም ሰላም እንደማያገኙ እስከዛሬ የነበሩት በርካታ ክስተቶች ምስክር ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ክስተት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ማእበል አማካይነት ስርዓቱ የገባበትን ጭንቀት እና ከማይወጣበት አሮንቃ ውስጥ መዘፈቁን፣ መጨረሻውም ሩቅ አለመሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብም ከአምስት አመታት በፊት የጀመረውን ህዝባዊ እምቢተኝነት አቀጣጥሎ ለመቀጠል እንደሚገደድ ግልጽ ነው፡፡
‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንገግስት ዘላቂነት የለውም!››
ዛሬ በአገራችን ሙስሊሙንም ጨምሮ የተነሳው ተቃውሞ በመሸንገያ ለውጦች የሚቆም አይሆንም። ለህዝቡ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ጥያቄ በጥይትና በቦንብ ምላሽ ለመስጠት መሞከር ከንቱ ጥረት መሆኑን ስርዓቱ ሊረዳው በተገባ ነበር። ይህ አይነት እርምጃ ህዝብን ለበለጠ ቁርጠኝነት የሚያበቃ እና ከመታገል ውጭ አማራጭ እንደሌለው ግልጽ በማድረግ የሚያጠናክር እንጂ ከትግሉ እንዲያፈገፍግ አያደርገውም። ህዝባዊ ጥያቄ ተጨማሪ አፈና በማድረግ፣ ተጨማሪ የአፈና መዋቅር በመዘርጋት፣ ተጨማሪ ደም በማፍሰስ፣ ተጨማሪ የማስመሰል ለውጦች በማሳየት የሚቆም አይደለም። ጥቂት ግልገል ካድሬዎቹንና የበታች ባለስልጣናቱን ለእርድ በማቅረብ የሚገላገለውም አይሆንም። ከዚህ እውነታ በመነሳት ከዛሬ 40 አመታት በፊት ለአጼው ስርዓት መንኮታኮት በር ከፋች በነበረው እና ህዝበ ሙስሊሙ ባደረገው ትዕይንት ላይ ተሰምቶ የነበረውን መፈክር ዛሬም ላይ ለስርዓቱ እናስታውሳለን – ‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንግስት ዘላቂነት የለውም!››
አዎን! የህዝብን ድምፅ ማዳመጥ እና ለጥያቄው ፍትሃዊ መልስ መስጠት አንድን መንግስት ታማኝ እና ጠናካራ ያደርገዋል። በተቃራኒው የህዝብን ድምፅ አለመስማት ደካማ ያደርገዋል፡፡ የደካማ ስርዓት ማክተሚያ ደግሞ ሩቅ አይሆንም፡፡ ‹‹ብሶት የወለደው›› ኢህአዴግ ሌላ ብሶት የወለደውን ህዝባዊ ማእበል በዘላቂነት መቋቋም የሚችልበት ሁኔታ በፍጹም አይኖርም።
ህዝበ መስሊሙ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል!
የጀመርነው የዙልሂጃ ወር ትልቅ የአምልኮ ወር ነው። በዚህ ወር ለዲናቸው ሲሉ ራሳቸውን ለእሳት አሳልፈው የሰጡትን፣ ‹‹እኔ ፈጣሪ ነኝ›› ይል የነበረን አምባገናዊ ስርዓት ለብቻቸው ገጥመው የረቱትን፤ ልጃቸውን ለእርድ አቅርበው ለመሰዋት ቁርጠኛነታቸውን ያሳዩትን፣ በሰላታችን ሁልጊዜ በተሸሁድ እሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የምናስታውሳቸውን የነብዩላህ ኢብራሂምን ታሪክ እንዘክራለን። በዚህች አላፊ ዱኒያ ላይ ስንኖር ፊት ለፊታችን የሚደቀኑብንን እንቅፋቶች ለማለፍ የሚያስችልን ታሪካዊ ክስተት በማስታወስ ለየትኛውም ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት በማንበገርበት ወኔ እና ጽናት ራሳችንን እናንጻለን። ለሙሉ መብታችን መከበር የምናደርገውን የትግል ቁርጠኝነት እናድሳለን፡፡ ብሄራዊ ጭቆናን በዘላቂነት ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን። ይህንንም በተመለከተ አገር አቀፍ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የሚኖሩን ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በቅርቡ በምዕራብ ሀረርጌ መሰላ ወረዳ በመስጂድ ሳሉ የስርዓቱ የሽብር ሰለባ ለሆኑ ሙስሊሞች አላህ ጀነተል ፊርደውስ እንዲወፍቅልን እየለመንን ለቤተሰቦቻቸውም ጽናቱን እንመኛለን። በዚህ ዓመት የሀጅ ስርዓት ላይ ለመሳተፍ ለበቁ ሙስሊሞችም አላህ ጉዟቸውን እንዲቀበላቸው እየተመኘን ‹‹ሀጁን መብሩር!›› እንላለን።
በሁሉም የአገራችን ማዕዘናት በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት እየተዋደቁ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለፍትህ መዋደቅ ልዩ ክብር መሆኑን በመግለጽ ዛሬ ላይ የሚፈሱ ደሞች እና የሚከሰከሱ አጥንቶች ለነገይቱ ፍትሃዊት ኢትዮጵያ በር ከፋች በመሆናቸው ለፍትህ የምናደርገው ትግል ላይ በአንድነት ጸንተን እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Like ☑ Comment ☑ Share ☑

ወገን እያለቀ ነው በየቦታው በአጋዚ ጋኔኖች እና በአልበሽር ወታደሮች
የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን ሰአት ጀምረህ በያለህበት እንደ አረብ አብዬት በፌስቡክ ከነዳጅ ስርተህ እራስህን ወይም መሳሪያ ወደ ወስጥ ተከፈፈሏል ፣ቀምተህ ፣ቀደመህ ቅለባቸው ከጫፍ እስከ ጫፍ ተነስ!!! ኮድ 2348 ሰ/ደ/ም/ም ትግ/አአ ኮር
የመጨረሻው ሰዓት የዳግም አድዎ ዘመቻ ጥሪ ፣ ቁጥር 26 አሰቸኳይ አዋጅ ( Very Urgent last Call for all oposition party’s to come up under one umberrela of great Adowa freedom movement to save Ethiopia first!!!) የሽግግር ደንብ ሁሉ በ24 ሰአት የመረጃ አገልግሎት በኢሳት ሬድዮ ይተላለፈል። ኢሳትን፣ ግንቦት 7 ፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት ተሳፈዎቻችን ናቸው እርዱ እባካቹ!!! ጥሪው ለሁሉም ድርጅቶች እና ኢትዮጵያዊ የማዳን ጥሪ ነው። ከአሁን በጛላ ደም እያፈሰሱ፣ እስርቤት እያሰቃዩ አስመስሎ ሥልጣን ላይ መቆየት በኢትዮጵያ ምድር ከቶም አይሞከርም። ።ወያኔዎች ደም እና ገንዘብ መጣች ጋኔኖች መሆናቹ አለም አወቋል።በምንም መለኪያ የትግራይ ኩሩ ህዝብ አይወክልም ከአደዎ ውቅሮ 1000 ተጠቃሚዎች በስተቀር። ሰለዚህ የትግራይ ሆይ ከአንተ ላይ እነዚህን እንክርዳዶች ነቅለህ ጣል ከትግራይ ነፃ አውጭ ልዩ ኮሚቴ ጋር በትግራይ እና በአዲስአበባ ላይ በማጋለጥ ኢትዮጵያዊ ግዴታቹን ተወጡ።የትግራይ ህዝብ ሆይ አንተን አፍን ይዘው አንተን መስለው አብረው ሁላችንም እነዚህ ጋኔኖች ደማችንን ጠጡ። አሁን ማድረግ ያለብህ በወታደር ቤት ላሉት ልጆችህ መሣሪያውን ወደ እነሱ አዙር በላቸው እና ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ተመሳሰለህ እራስህን ነፃ አርግ። ይህ ትዕዛዝ መፈፀም የግድ ነው የመጨረሻው ሰአት ላይ ደረሰናል። ለነገ ልጆችህ መኖሪያ ስትል የግድ በትርጉሙ ከእግዚአብሔር የወርቅ ስጦታ መጠሪያ ተብለህ የምትጠራ ኢትዮጵያአዊ የተባልክ ሁሉ፣ አረንጓዴ፣ ብጫ፣ቀይ መለያህ ከአለም በፈት ክርስትናን ተቀብለህ የወንድሞችህን የምትኮራበትን መስሊም እምነት አሰጠልለህ ዛሬ ለአለም የበረከትክ በአንድነት ተነስ። አየር ሀይል፣ በቴኮንዶ የሠለጠንክ፣ በጦር፣ በፓሊስ ውስጥ የጎበዝ አለቃ ምረጥ ፣ ፈጣረህን ለምነህ ከሁን በኋላ ዝም ብሎ መሞት የለም መሳሪያ ቀምተህ ታሪክ ፈፅም።
1ኛ ምንም አይነት ክፍተት በአገራችን ሳይፈጠር የሽግግር መንግስት ለ5 አመት ፔሬዝዳንት በደ/ር ብርሐኑ ነጋ እና ጦሩ በሙሉ በጄ/ር ከማል ገልቹ እና የትግራይ ነፃ አውጭ ይመራል። ከ 5 አመት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያሳተፈ በአንድ አይን አስተዳደራለሁ የሚል ብቻ ተመርጦ ይረከባል ከበዛ ሥልጣን ለ8አመት ብቻ ነው።
2ኛ የኤፈርት ገንዘቦች እና ቅርንጫፎች የባለሥልጣን ዘመድ ስም በሙሉ፣ በፓለቲካ ጥገኞች በኤርትራውያን ስም በውጭ የተሠማራቹት ዝረዝር፣ የባለሥልጣኖች ስልኮች እና ወሬ አቀባዬች ማስረጃ የቴሌ ማህደር መረብ ተረክበን እየተመዘገበ ነው። በቀኑ የማይቀር ፍርድ ላይ እንደርሳለን።
3ኛ ኮማንደር ሐጎስ ኩሩ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ልጅ እናመሰግናለን። ኮማንደር እርምጃው ይቀጥል ሞት ምን እንደሆነ በራሳቸው ላይ እና በቤተስባቸው ይዮት።
ሳሞራ በኤድስ በሸታ ተስፋ የቀረጠው እና 14 ጀኔራሎች ቅድሚያ ይመታሉ።
“If any government terrorizing or killing his own people is a terrorist” George W Bush . A good example from Africa Military dictator EPRDF is qulified.
***Evile EPRDF military dictator, why you need inhuman Genocide on Ogaden, Gambella,Tigray, and now in Oromo or Amhara peoples of Ethiopian???
By force to stay in power? No… your time of 25 years is over… no more counting days and years after all.
4ኛ በራሪ ወረቀት በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ድንበር በኩል ለጦሩ በትኑ አፈሙዝህን አዙር።
5ኛ በአየር መንገድ፣ በባንክ ቤቶች ውስጥ የባለሥልጣኖች እንቅስቃሴዎች ማስረጃ ይመዝገብ።
6ኛ የአዲስ አበባ 30,000 ነዎሪ ተፈናቅሏል እንደ ዝንብ ተቆጥረው። አሁን ደግሞ ኦሮሞ ህዝብ ነቅላቹ ውጠልኝ ስላለ የሚቀጥለው 5ፎቅ መሠራት የማይችል ደሀ 2 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊ በዚህ 2009 የወረወራል። የአዲስ አበባ ህዝብ ነው መሰዎአትነት ከፍለህ ነገን ማየት የምትችለው ዛሬ ከወገንህ ተቀላቅለህ ጎበዝ አለቃ መርጠህ ተቀላቀል።
7ኛ በሚስጥር ሰሞኑን 4 የምስራቅ አፍሪካ አገራት የወያኔን ሤራኘት በሱማሌ ለሞቱት ወታደሮች የደም ካሳ $15,000 እንደማይከፍሉ አረጋግጧል። በሱማሌ እና በሱዳን ሠላም እንዳይሰፈን ረዥም ጊዜ ምክንያት ወያኔዎች መሆናቸውን አረጋግጧል። አገራቱ ሠሞኑን በሚስጥር መስረያ ሰሞኑን ለህዝባችን ኢሕአዴግን የሚያናግርበት ቋንቋ ያስገባሉ። ህዝባዊ የመንግስት ሽግግር ትግሉ ቶሎ ያልቃል በማለት ለምእራብ አገሮች ኬንያ ላይ በሚስጥር አሳውቀዎል።
8ኛ የኦሮሞ ወገኖቻችን ለምን ይገደላሉ? ሲባል የእስላም ሸብርተኞች ስለሆኑ ነው እያሉ ለምእራቡ አለም ወሬ ሰሞኑን ሶነዙ ነበር። ሰለዚህ ማንኛውም መሰሊም ወገኖቻችን በውጭ አገር ያላቹ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከጥንት ጀምሮ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ በፍቅር ተሰብስቦ እንደሚኖር ሁሉም በኩራት ለነጮቹ ያለንን መከባበር አስረዱ። እኛ ያበደ አረብ ኩሩ ሙስሊሞቻችንን ስም ማጥፋት አይችልም በተቻለ መጠን በኢትዮጵያውያን መስጊድ ላይ ብቻ በኩራት ዱአቹን በጥንቃቄ አርጐ የሚመጣውን ሰም ማጥፋት እና መገለልን ሁላችንም እሺአላ ክርስቲያኑ እና መሲሊም ሕዝበችን አብረን እንታገላለን።
ንጉሡ ሞቱማ አምቦ ኮር አዛዥ
ግልባጭ።
_ለኮማንደር ሐጎስ የልዩ ወያኔዎችን ከትግራይ ህዝብ ነጥሎ የሚያወጣ ኮር አዛዥ ዋና ተጠሪ
_በየክፍለ አገሩ ያላቹ ኮር አዛዥች በሙሉ።
ማሳሰቢያ
ለአዲስ አመት የመዝናኛ ዝግጅት ለማድረግ የተዘጋጁ የወያኔ ደጋፊዎች እንዳላችሁ ይታወቃል ህዝብ በወያኔ እየተጨፈጨፈ ባልደረቀ ደም ላይ ለመጨፈር መዘጋጀት ወገን ላይ ኢ ሞራላዊ ጠባሳን ስለሚፈጥር ማንኛውን ጭፈራ እንድትሰርዙ በሞት ለተለዩን ንፁሀን የኦሮሞና አምሃራ ህዝቦች ደም ስም ትጠየቃላችሁ።
dele la amhara Hezebe.this is the time all amhara stand fighte tigra wayne
Saudi Wahhabi Missioneries