ገዢው ፓርቲ በርካታ የአዲስ አበባ የወረዳ አመራሮቹን ሊቀንስ ነው
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢህአዴግ የድርጅት አባለት ግምገማ መጠናቀቁን ተከትሎ የግምገማ ውጤት እየወጣ ሲሆን፣ በዚህም ግምገማ መሰረት በርካታ የከተማዋ ወረዳ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታውቋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ከ50 በላይ አመራሮች ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ከ20 በላይ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ክ/ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር …