የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል

ሐምሌ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዚህ አመት በአገሪቱ የታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየከፋ በመሄዱ፣ በጥቁር ገበያ እና በህገወጥ መንገድ የሚደረገው የዶላር ዝውውር መድራቱን ዘጋቢአችን ገልጿል።
ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ ስራቸውን የሚሰሩ ነጋዴዎች ዶላር እንደልባቸው ለማግኘት ባለመቻላቸው፣ ዶላርን ከጥቁር ገበያና ከባንኮች በልዩ ሁኔታና በውድ ዋጋ ለመግዛት እየተገደዱ ነው። የተወሰነ መጠን ዶላር ለማግኘት ለባንክ ባለስልጣናት ኮሚሽን መክፈል ግዴታ መሆኑን ነጋዴዎች እየተናገሩ መሆኑን ዘጋቢያችን ተናግሯል።
አገሪቱ ወደ ውጭ ልካ ከምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ይልቅ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚልኩት ገንዘብ የተሻለ ገቢ እያስገኘ ነው። አገሪቱ በቅርቡ ከግል አበዳሪ ተቋማት 1 ቢሊዮን ዶላር መበደሯ ይታወቃል።

1 Comment on “የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል”

  1. አዎ የወያኔ ካድሬዎች በየ ባንኩ ተመሽገው ውድነትን እየፈጠሩ ይገኞሉ ለዚህም ማሥገኛ በመቶኛ ከሚፈቀደው 2-4 ብር የሚሠላ ግዴታ በካድሬ ደላሎች ይከፈላል ፥ በአጠቃላይ የአንድ የዋህ ነጋዴ ወጪ ሂሣቡ ከ100ፐርሠንት አልፋል ለዚህም ነው ወያኔ በፈጠረው ብዝበዛ ህዝቡ የኑሮ ውድነት እንደሽእሣት የላፈው ይገኛል።
    እናም የወያኔ ኑሮ በነዚህ መሠል ምዝበራ እና በ ኮድ4: ኮብራቸው ለነዳጅ እያሉ እየተንበሻበሹ ይንኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*