የቀድሞ ህወሃት መስራች የነበሩና በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመድረክ ፓርቲ አባል የሆነው የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ ከመንገድ ላይ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ

አቶ አስገደ ከፍርድ ቤት ሆነው በስልክ ለፍትህ ጋዜጣ እንደገለፁት ከሆነ፣ ከሳሻቸው የቀድሞው የሕወሓት አባል የሆነው ብስራት አማረ ሲሆኑ ጉዳዩን የያዘቺው ዳኛ ደግሞ የቀድሞዋ የህወሓት ታጋይ ኪዳን አብርሃ ናት ተብሎአል።

ክስ የቀረበባቸውም ከዚህ ቀደም በፃፉት “ጋሀዲ” በተሰኘው መፀሀፍ እንደሆነ አቶ አስገደ ተናግረዋል፡፡

አቶ አስገደ ከአሁን በፊት በዚህ ጉዳይ ቀዳማዊ ወያኔ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተዘግቶ የተሰናበቱ ቢሆንም፤ ሰሞኑን ከመንገድ ላይ መጠሪያ በያዘ ፖሊስ ተይዘው በመቀሌ ከተማ ሰሜን ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው በስምንት ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለጥር 2 ቀን 2004ዓም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተቀጥረዋል።

አቶ አስገደ በህወሀት ላይ ጠንካራ ትችቶችን በመሰንዘር ይታወቃሉ።