ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍትህ ሚኒስቴር የተጣለባቸው እገዳ ምንም አይነት ስነልቦናዊ ጫና እንደማይፈጥርባቸው ተናገሩ
ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፍትህ ሚኒስቴር በሽብረተኝነት ክስ ለሚከሰሱ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና አባላት ጠበቃ በመሆን የሚታወቁትን አቶ ተማም አባ ቡልጉን የዲሲፒሊን ግደፈት ፈጽመዋል በሚል ለአንድ አመት ከ7 ወር አግዷቸዋል። መታገዳቸውን ከሚዲያ የሰሙ ጓደኞቻቸው እንደነገሩዋቸው የገለጹት አቶ ተማም፣ በህጉ ቢሆን ነሮ የእግድ ደብዳቤው ከሚዲያ በፊት ለእርሳቸው መድረስ ይገባው …