ህወሃት/ ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ወራራ ሊፈጽም ይችላል ተባለ
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007)
የኤርትራ መንግስት ከጎረቤት ኢትዮጵያ ወታደራዊ ወረራ ሊፈጸምብኝ ይችላል ሲል ዛሬ ሰኞ ገለጠ።
በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ (ህወሃት) ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገሪቱ ላይ እያቀረበ ያለው ፀብ-ጫሪ መግለጫና ንግግር እየጨመረ መምጣቱን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ማመልከቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
የተለያዩ ሃይሎችን ድርጊት ከኤርትራ ጋር ለማቆራኘት ጥረት ሲያደርግ የቆየው የህወሃት ገዢ ፓርቲ ከተያዘው ክረምት ወቅት ጀምሮ ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ሲል የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስተቴር በመግለጫው አመልክቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጎረቤት ኤርትራ ለተለያዩ ተቃዋሚ ሃይሎች ወታደራዊ ድጋፍን እያደረገች ነው ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ከአንድ ወር በፊትም ከኤርትራ ሰርገው ወደሰሜን ኢትዮጵያ የገቡ ታጣቂ ሃይሎች ተደምስሰዋል ሲል የኢትዮጵያ መንግስት መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ፣ ለድርጊቱም ኤርትራን ተጠያቂ አድርጓል።
ከኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የቀረበን ማሳሰቢያና ዛቻ ተከትሎም ኤርትራ ለመጀመሪያ ጊዜ የወረራ እቅድ መኖሩን የገለጸች ሲሆን ከኢትዮጵያ ወገን የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ኣዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አመልክቷል።
ሁለቱ ሃገራት ከአስር አመት በፊት ካካሄዱት የድንበር ግጭት በኋላ የሁለቱ ድንበር አካባቢ ሰላምና ጦርነት የሌለበት ቀጣና ተደርጎ ይገለጻል።
War is not good
ait lemotuwa ye dimet afincha Tashetalech ??
mot le weyane
amara malet le hodu blo enatu yemishet.viva oromya.when oromya is free all neftegna go to your land dry land gonder.
Tyz
ከቻልክ ለቀረበው ዜና አግባብነት ያለው ትችት ሰጥ ። ዜናው የሚነገረው ሌላ አንተ ትችት የምትሰጠው ስለሌለ ርዕሰ ።ምንም የማታወቅ ገልቱ መሆንህን ይፋ አታውጣው አታውጣ።የሆነ ነገር ስትናገር መጥነህ ተነገር ።ካልሆነ ቅል ራስ መሆንህን የሳብቅብሀል።እውነት ሰለ ኦሮሞ የምታውቅ ከሆነ የብሄሩ አገር የት ነው? የኦሮሞን ብሔር የዘር ሐረግ ያላቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንድሞችህ በክልል ሦስት እንዳለ አታውቅም ።ዘረኞች ዘረኝነት ለማንገስ አትፍጠኑ።ሌላም ቤት እሳት መኖሩን አትዘንጉ። ለኦሮሞ ሕዝብ ዘረኝነት ምርጫው አይደለም ።