የሚኒስትር ሬድዋን አማካሪ መኮብለላቸው ተሰማ

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል።
አቶ አንዱዓለም በ2007 ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል።
አቶ አንዱዓለም ከሀገር ከመኮብለላቸው በፊት ቀደም ብለው ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ወደ አሜሪካ ማሻገራቸውን ጋዜጣው ዘግቦ፣ ግለሰቡ ከሚኒስትሩ በተጨማሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ያማክሩ ነበር ብሎአል።

1 Comment on “የሚኒስትር ሬድዋን አማካሪ መኮብለላቸው ተሰማ”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*