ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን በመጥቀስ ሪፖርተር እንደዘገበው በማዕድን ሚኒስቴር ላይ በ2006 ዓ.ም. አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት አገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ ማጣቷን አረጋግጧል፡፡ የማዕድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 678/2002 የከበሩ ማዕድናት ላይ ስምንት በመቶ ፣ያልከበሩ ማዕድናት ላይ ደግሞ ስድስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ መጣሉን ሪፖርቱ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17, 2007) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራት የፓርቲ አባላት ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አራቱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከተከሳሾች ፍርድ ቤት ካስተላለፋቸው ከሁለት ወር በላይ በእስር ቤት በመቆየታቸው ምክኒያት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። አራቱ ተከሳሾች ማክሰኞ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወጡ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17 2007) በቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተቃውሞ እንደገጠማቸው የእንግሊዙ ዘጋርዲያ ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ረቡእ ዘገበ። አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና የምትታወቅ ሃገርን ለመጎብኘት መወሰናቸው ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ላይ መሆናቸውንም ጋዜጣው አስነብቧል። የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ …

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያሬድ ንጉሴ የተባለ ባለፈው ወር አውሮፓ የገባ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ለኢሳት እንደገለጸው በቅርቡ 25 ኢትዮጵያውያንና 2 ኤርትራውያን ሆነው ከሱዳን ወደ ሊቢያ ሲጓዙ፣ ደንጎላ በምትባል ቦታ ላይ በሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት የመጣ ኢትዮጵያዊ የደህንነት ሰራተኛ የ48 አመት ጎልማሳ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ከመኪና አስወርዶ በሽጉጥ እንደገደለው ገልጿል። …

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ባለፉት ጥቂት ወራት በተቃዋሚ መሪዎች ላይ የተፈጸመው ግድያና በመላ አገሪቱ በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ላይ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነው ብሏል። የአፍሪካ ህብረትና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን መርምረው ሪፖርት አለማድረጋቸውንም ድርጅቱ ወቅሷል። ምርጫው እስከሚካሄድበት ጊዜ …

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ አገር የሚገኘው ሪፕሪቭ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስቲር ዴቪድ ካሜሩን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። አቶ አንዳርጋቸው ለአንድ ሳምንት መታሰራቸው ረጅም መሆኑ ሳያንስ ለአንድ አመት ታስረው መቆየታቸው ለማሰብም የሚከብድ ነው ሲል የህግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሪፐሪቭ ዌብሳይት …

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ሰሞኑን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ዕቅዱ የተለጠጠ መሆኑን አምነው ሙሉ በሙሉ ላለመሳካቱ ምክንያት ያሉዋቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል፡፡ የመጀመሪያው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በባህርይው መዋቅራዊ ለውጥን ታሳቢ ያደርጋል፡፡ ይህ ዕቅድ በራሱ ተለጥጦአል ብለዋል፡፡ የፋይናንስ ምንጭ ማፈላለጉ …

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይሲስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ድርጊቱን ለማውገዝ በስፍራው ተገኝታ የነበረችው ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ ከ3 አመት ልጇ ጋር ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ያለ ማዘዣ በፖሊስና በደኅንነት ኃይሎች ተወስዳ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በሁዋላ ሰኔ …

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ ውጤቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት የ105 ወንበሮችን ጉዳይ ግልጽ ባለማድረጉ አንዳንዶች “ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ለመካፋፈል አስቦ ያደረገው ሊሆን ይችላል” በማለት አስተያየት ሲሰጡ ቢቆዩም፣ ቦርዱ ግን ኢህአዴግ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፋል በማለት የመጨረሻ ውሳኔውን ሰጥቷል። ዋናዎቹ የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ ምርጫውን ” አሳፋሪ” ነው …

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ችሎቱን የተከታተሉት በአቶ ማሙሸት የሚመራው መኢአድ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለኢሳት እንደገለጹት አቶ ማሙሸት፣ ሰኔ 10፣ 2007 ዓም በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፍርድ ቤት የወሰነ ቢሆንም፣ ፖሊስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቦታል። ፖሊስ፣ አቶ ማሙሸት ቢፈታ በምስክሮቼ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ሊያደርስባቸው …

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ የግል ባለንብረቶች ወደ አዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤቶች ታፔላ ለመቀየር በሄዱበት ወቅት ከተለመደው የታፔላ ማስቀየሪያ አገልግሎት ክፍያ ውጪ ባልተጠበቀ ሁኔታ የ1ሺ ብር ቦንድ ካልገዛችሁ የሚል ግዳጅ ተጥሎባቸዋል ። “አሁንስ ወዴት እንሂድ? ለማን አቤት እንበል?” በማለት የታክሲ ባለንብረቶች ሲያማርሩ …

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይካሄዳል። በጀርመን በፍራንክፈርት፣ሙኒክ፣ዱስልዶርፍ እና በርሊን የሚካሄድ ሲሆን፣ በፍራንክፈርት የሚደረገው ተቃውሞ ለ24 ሰአታት ይቆያል። በጣሊያን ሮማ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በእንግሊዝ …

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙዎች ዘንድ አስቂኝ ተብሎ የተተቸውን የ2007 ዓም ምርጫ ተከትሎ በኦሮምያ ብቻ ከ640 በላይ የመድረክ ደጋፊዎች ሲታሰሩ፣ 66 በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣7 አባለት በጥይት ቆሰልዋል፣ 2 አባላት ደግሞ መገደላቸውን መድረክ አስታውቋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በሺዎች እንደሚቆጠር መረጃዎች ያመለክታሉ። መድረክ እንዳለው በምርጫ 2007 ማግሥት በመድረክ …

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክረምቱ ወቅት 119 የሚሆኑ የብአዴን አባላት በድሬዳዋ ከተማ የደህንነት እና መረጃ መሰብሰብ ስልጠና ተሰጥቷቸው በክልሉ ከተሰማሩት መካካል አንዱ የሆነው ሰራተኛው እንደገለጸው፣ ማንኛውም ደህህነት ሰራተኛ የስለላ ሪፖርቱን ተክሌ ለተባለ የደህንነት ሰራተኛ ሲያቀርብ መቆየቱን ለኢሳት ተናግሯል። ስልጠናውን ከወሰዱት የደህንነት ስራተኞች መካከል አንዳንዶች በምስራቅ ጎጃም ደብረማርቆስ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ …

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የማህበራዊ ጥናት መድረክ በቅርቡ ባካሄደው ጥናት በአዲስአበባ የግሉ የጤና ዘርፍ ከፍተኛ የጥራት መጓደልን ይዞ የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ እየጠየቀ መሆኑን ገልጿል። ጥናቱ በአዲስአበባ ከሚገኙ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች መካከል በ34ቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን አገልግሎት ክፍያ (ዋጋን) በተመለከተ በመንግስት ሆስፒታሎች የካርድ ክፍያ አማካይ ዋጋ 5 ብር ሲሆን፣ በግል ክሊኒኮች …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት አካላት ናቸው ብሎአል። ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ብሎ እንደማይጠይቅም አስታውቋል። “ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምርጫው በአሳፋሪ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የመድረክ ደጋፊዎችን ቤቶች መቃጠላቸውን፣ መደብደባቸውንና ማሳደዳቸውን የአርባምንጭ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ በላካ ቀበሌ ብዙ ሰዎች አካላ ጎደሎ ሆነዋል፣ ቤቶቻቸውም ተቃጥሎባቸዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የቀበሌ አመራሮች ከሰኔ 15 በሁዋላ መግቢያችሁን ፈልጉ እየተባሉ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዳዊት ጉበዜ እና አዛውንት እናቱ ወ/ሮ …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ ቦርድ የታገደው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ማሙሸት አማረ ከሳምንታት እስር በሁዋላ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢያስተላልፍም፣ ውሳኔው ለሁለተኛ ጊዜ በፓሊስ ተጥሶ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ግንቦት 26/2007 ቦሌ የሚገኘው ችሎት አቶ ማሙሸት የቀረበባቸው ክስ እንደማያስከስሳቸው …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ሰበብ አስባቦች የሚጣልብን ቅጣትና እገዳ ተገቢ አይደለም በሚል ሰኔ 8፣ 2007 ዓም ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ አድርገው የነበሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ሾፌሮች፣ ፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸውን የሚሰማ እና መፍትሄ የሚሰጥ አካል ይኖራል ብለው ሲጠብቁ፣ በተቃራኒው ከስራ መታገዳቸውን ተናግረዋል። ሾፌሮች እና ባለሃብቶች እንደሚናገሩት “የመንግስትን ትእዛዝ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ለመብት የሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና የጸረ ሽብር ግበረሃይል አባላት በከተማዋ ተገኝተው እጃቸው አለበት ብለው የጠረጠሩዋቸውን የቴፒ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 7 ፖሊሶችን ይዘው አስረዋል። ባለስልጣኖቹ የከተማውን ህዝብ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በነጻነት እጦት እየተሰቃየ መሆኑንና ወጣቶች እርምጃ የሚወስዱት ከዚህ ተነስተው …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንት በፊት አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል በቡርካባ ግዛት ጃሚዮ በሚባል ቦታ ላይ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ከ30 በላይ ወታደሮችን ከገደለ በሁዋላ፣ በርካታ ቁስለኞች ሞቃዲሹ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ቁጥር ሁለት ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። አሚሶም በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የሰፈረው የአፍሪካ ህብረት ጦር በአልሸባብ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በጋምቤላ እርሻ ስራ ተሰማርተው የሚፈለግባቸውን የመሬት ኪራይ እዳ ባልከፈሉ 150 ባለሀብቶች ላይ ያወጣው የማሳሰቢያ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ የጋምቤላን መሬት የተቀራመቱት ከ90 በመቶ የሚልቁት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከ2006 እስከ 2007 ሰኔ ወር ድረስ ያለባቸውን ውዝፍ እዳ አጠቃለው እንዲከፍሉ በወጣው የማስጠንቀቂያ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ አንድ ተጀምሮ ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ ከፍተኛ አመራሮችን፤አዛዦችን እንዲሁም ተራ የፖሊስ አባሎችን አካቷል። ከጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የግምገማው ይዘት በፖሊስ ስነምግባር ዙሪያ ነው። በግምገማው ወቅት አንድ ባለ ሳጅን ማዕረግ ያለውና አንድ ኮንስታብል ፖሊስ በስልካቸው ውስጥ የግንቦት ሰባት፤የሰማያዊ ፓርቲና የሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶች መረጃዎች በስልካቸው ውስጥ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ 2007 ቅስቀሳን ተንተርሶ በህዝቡ ዘንድ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢህአዴግ፤ በከተማዋ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች ለረዢም አመታት ለኖሩ የይዞታ ባለመብቶች ከምርጫው በፊት ሰጥቶት የነበረውን በባለ ቀለም የብአዴን አርማና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መልሶ በመውሰድ ውሳኔውን ለመሻር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ “በየክፍለ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአረና ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው አምዶም ገብረስላሴ በፌስ ቡክ ገጹ እንደጻፈው ፣ የ48 አመቱ አቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገድለዋል። አቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃያዎቹ መጨረሻ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ጸሃፊ ሳሙኤል አወቀ ሰኔ 8/2007 ዓም ምሽት ላይ ሁለት ግለሰቦች ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው በፈጸሙበት ድብደባ ህይወቱ አልፎአል። የሳሙኤል ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች ድርጊቱን የመንግስት ሃይሎች እንደፈጸሙት ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሳሙኤል ጀግና እና ለአገሩ የሚቆረቆር ጠንካራ …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊምቦ ገዋታና በቦንጋ የተራዘመው ምርጫ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ ቀስቃሽና አደራጅ የሆነው ምትኩ ወልዴ ፣ ትናንት ከቀኑ 6 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ፖሊሶች ከቤት አውጥተው የደበደቡት ሲሆን፣ ግለሰቡ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ቦንጋ ሆስታል ከገባ በሁዋላ፣ ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል። …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ ማይካድራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸውን እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል። ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች በወዱት እርምጃ ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ ወጣቶች መገደላቸውን፣ ከ10 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ መቁሳላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። የቅማንት ተወላጆች የራስ አስተዳደር መብት ይሰጠን በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት “ጥያቄያቸው በክልሉ ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ሊታይላቸው” …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፕሮቪደንት ፈንድ ያላቸውን የግል ድርጅት ሠራተኞችን ገንዘብ በመውሰድ በጡረታ እንዲተዳደሩ ለማድረግ የተረቀቀው የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ማሻሻያ በበርካታ ሰራተኞች ዘንድ ተቃውሞ ማስከተሉን ተከትሎ በተለይ ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች የግል ድርጅቶችን በገፍ እየለቀቁና ለመልቀቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ እያቀረቡ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት እየተሰራበት ያለው አዋጅ ቁጥር 715/2003 ለማሻሻል በምርጫው ማግስት …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007 ዓም) የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዝ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ሐሙስ ለንባብ ባበቃው እትሙ ዘገበ። ገዢው የኢሃዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በብቸኝነት ለድል መብቃቱም በመንግስት ላይ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ ማስገደዱንም ጋዜጣው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በማእከላዊ ሶማሊያ በተደረገው ጦርነት ታጣቂ ሃይሉ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል። አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት የመመዝገብ ሥራዎችን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ቢሆንም ባሉበት ጫናዎች ምክንያት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኮምሽኑ የባለስልጣናትን ሀብት እንዲመዘግብ ስልጣን ሲሰጠው በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመን ይፈጥራል ተብሎ ነው፣ ይሁን እንጅ ኮምሽኑ …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት15 ምርጫ ከመካሄዱ 2 ሳምንት በፊት መንግስት ዋና ዋና የሚባሉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እንዲቀንስ ቢያደርግም ፣ ከምርጫው በሁዋላ ተመልሶ መውጣቱን ዘጋቢያችን ገልጿል። ምስር በኪሎ ከ50 ብር በላይ፣ በርበሬ ከ120 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ዘይትና ስኳር ተመልሰው ከገበያ መጥፋታቸውን የስጋና የወተት ምርቶች እንዲሁም በሁሉም የእህል ዘሮች …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 200 ኢትዮጵያውያንን የጫኑ 2 ጀልባዎች ከ24 ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ በሁዋላ ጅቡቲ በሰላም ደርሰዋል።ኢትዮጵያውያኑ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወደ አዲስ አበባ ይጓጓዛሉ። በየመን አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። በአገሮቱ ከሚኖሩት ከ80 ሺ በላይ ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩት ከ2 …

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የቴፒ ወጣቶች ቡድን በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የወሰደውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ሶስት ፖሊሶች ከተገደሉና በርካታ እስረኞች ካመለጡ በሁዋላ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታጣቂዎች መሽገውበታል ወዳለው አካባቢ በመሄድ ውጊያ የከፈቱ ሲሆን፣ ወጣት ታጣቂዎች አስቀድመው ዝግጅት አድርገው በመቆየታቸው በርካታ ወታደሮች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በርካታ ወታደሮች …

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማእከላዊ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት በወጣው መረጃ በዚህ አመት የታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ጭማሪ ሲያሳያስ ፣ የምግብ ያዋጋ ግሽበት 6.9 በመቶ ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ 8 .2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። በዚህ አመት በግንቦት ወር የታየው የዋጋ ግሽበት አምና ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ9.4 …

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አቶ ዳዊት አስራደ ሰኔ 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል። ፖሊስ አቶ ዳዊትና ሌሎች ተከሳሾች ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ለ14 ቀን ታስረው እንዲቆዩ …

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ለመላ አገሪቱ በወረደ ጊዚያዊ አደረጃጃት፣ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንዲሁም በተለያዩ የግንባሩ ጽ/ቤቶች በተሰጠ መመሪያ መሰረት የተዋቀረው የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ኮሚቴ የድጋፍ ሰልፍ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል። ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ህዝቡ በድጋፍ እንዲመሰክር እና ሚዲያዎቹ በቀጥታ እንዲዘግቡት መመሪያ ከወረዳ በሁዋላ፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ተሰብስቦ ሰላማዊ …

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ2008 ዓም ከመደበው በጀት ውስጥ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ፍትህና ደህንነት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል። የፌዴራል መንግሥት የመደበኛ ወጪ ዝርዝር እንደሚሳየው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 9. 5 ቢሊየን ብር፣ የፌዴራል ፖሊስ 1. 6 ቢሊየን ብር፣ ፍትሕና ደህንነት 3. 5 ቢሊየን ብር ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡ መከላከያ በ2007 ዓም ከተያዘለት …

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኤርትራ ይፈጸማሉ ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፋ እንደሚያደርግ ካስታወቀ በሁዋላ፣ ኤርትራ መልስ ሰጥታለች። የድርጀቱ ሪፖርት በሃሰት የተሞላና ነው ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ፣ ድርጅቱ ጥቃቱን የሰነዘረው በመንግስት ላይ ሳይሆን ለሰው ልጅ ክብርና ማንነት ከፍተኛ ከበሬታ በሚሰጠው ስልጡን በሆነው ማህበረሰብና ህዝብ ላይ ነው …

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ከአምስት አመት በፊት አውጥቶት በነበረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከወጪ ንግድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰበስብ ገልጾ ነበር፣ ይሁን የገንዘብ ሚኒስትሩ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት የታቀደው እቅድ አለመሳካት ብቻ ሳይሆን የውጭ ንግዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መሄዱን ገልጸዋል። አቶ ሱፊያን አህመድ የ2008 በጀት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፓርላማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በውጭ …

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም አረመኔው የአይ ኤስ አይ ኤስ ቡድን በዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ በራሱ በመንግስት ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎችን በእለቱ በአሰቃቂ ሁኔታ በኃይል ከመደብደብና ከማዋከቡም በተጨማሪ አልፎ ተቃውሞ አነሳስተውብኛል ብሎ ያሰባቸውን በቦታው ያልተገኙ …

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሁለት አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት የደቡብ ሱዳን ግጭት ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይፈለግለታል ቢባልም እስካሁን ጦርነቱን የሚያስቆም መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም። በቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዋና መሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ለወራት ከተቋረጠ በሁዋላ እንደገና ለማስጀመር የሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ተወካዮች አዲስ አበባ ገብተዋል። ቀድም ብሎ በተቀመጠው …

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ግጭት ከተፈጠረ በሁዋላ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ለግጭቱ መነሳት መንስኤ ሆነዋል፣ ጥቃትም ፈጽመዋል ያላቸውን ሁለት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አግዷል። ተማሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። አንደኛው ተማሪ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት መኪና በድንጋይ ወረውሮ ሰብሯል የሚል ክስ ሲቀርብበት ሌላው ተማሪ ደግሞ ጩቤ ይዞ ተገኝቷል የሚል …

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በተከሰሱት በአብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አቅርቦ ማሰማት ጀምሯል። አቃቢ ህግ “ምስክሮቼ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል” በሚል ችሎቱ ምስክሮችን በዝግ እንዲያሰማ እንዲፈቅድለት ጠይቋል። ተከሳሾች በበኩላቸው የአቃቢ ህጉን መከራከሪያ አጥብቀው መቃወማቸውን …