Author: BefeQadu Z Hailu
አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይ ነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙ ሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡
Join the #FreeZone9Bloggers Tweetathon on May 14

- Free the Zone 9 bloggers… because blogging is not a crime!#FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g65ijg
- “We blog because we care” #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g65ijg
- Join us and sign the @globalvoices letter calling for the release of journalists and bloggers in #Ethiopia #FreeZone9Bloggers bit.ly/1njZMRH
- Send your photo to the #FreeZone9Bloggers Tumblr and support their release! bit.ly/1g6qmWT
- Blogger arrests in #Ethiopia are a violation of the African Charter on Human and Peoples’ Rights #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/QlzRuG
- The African Charter protects the right to free expression #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/QlzRuG
- Blogger arrests in #Ethiopia violate the International Covenant on Civil and Political Rights #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g1MUNM
- Blogger arrests in #Ethiopia violate Articles 9 & 14 of the ICCPR #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g1MUNM
ዞን ዘጠኝን ይጠይቁ #AskZone9
የዞን 9 ጦማሪያን ሁለተኛ ክስ ላይ ያለኝ የህግ አስተያየት
- በህቡዕ መደራጀት
በህቡዕ መደራጀት ወንጀል ነው???
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31
“ማንኛውም ሰው ለማንኛውም አላማ የመደራጀት መብት አለው፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ የተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ”
ይላል፡፡ ከዚህ አንቀፅ በግልፅ እንደምንረዳው በህቡዕም ሆነ በግልፅ መደራጀት መብት ነው፡፡ መደራጀት የሚከለከለው “ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ” ከሆነ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም “ፖሊስ” (በተግባር ከሳሹ ኢሃዲግ ቢሆንም) በዞን 9 ጦማሪያን ላይ ባቀረበው ክስ በህቡዕ መደራጀትን በራሱ ወንጀል ለማስመሰል መሞከሩ ከህግ አግባብ ውጪ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱን የሻረና የናደ ተግባር ነው፡፡ አላማውም ማንኛውንም መደራጀት ማስፈራራትና ሰዎችን ከመደራጀት እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ሲጀመር ዞን9 የጦማሪያን ስብስብ እንጂ ህጋዊ ሰውነት ያለው የተደራጀ አካል ወይም ድርጅት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው አቃቤ ህግ ዞን 9ን በቀጥታ ሊከሰው ያልቻለው (በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት የሌለውን አካል መክሰስ ስለማይቻል)፡፡ መሰባሰብን እና መደራጀትን በቅድሚያ መለየት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ስብስብ መደራጀት አይደለም፡፡
ከዚህ በፊት በልጆቹ ላይ ፖሊስ መስርቶት የነበረውን “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት” የሚለው ክስ እንደማያዋጣ እንደገባው ሁሉ አሁንም ይሄኛው ክስ አያዋጣም፡፡
2. ሁለተኛው የክሱ ነጥብ “ከሽብርተኛ ቡድን ጋር አብሮ መስራት”
ይህ ሽብርተኛ የተባለው ቡድን የትኛው እንደሆነ ባይገለፅም በኢትጲያ ውስጥ ሽብርተኛ የተባሉት ግንቦት 7፣ ኦነግ፤ ኦብነግ እና አልቃይዳ ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህም ልጆቹ ከነዚህ ድርጅቶች ከአንዱ ጋር ሰርተዋል ብሎ ፖሊስ ካመነ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል መለት ነው፡፡ ስለዚህም ማስረጃ ላሰባስብ በሚል ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አስቂኝ ነው፡፡ መጀመሪያ አስሮ ማስረጃ ማሰባሰብ ማለት ወንጀል መፈብረክ እንጂ ወንጀልን መክሰስ ዐያደለም፡፡
ከነዚህ ከላይ ከጠቀስኳቸው ድርጅቶች ውስጥ አንደኛው የውጭ ሀገር ድርጅት ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ብሄር ተኮር ድርጅቶች ስለሆኑ ፖሊስ ሊል ያሰበው ምናልባት ግንቦት 7ን ሊሆን ይችላል ወይም ባለፈው ክስ “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት” ያሉትን ድርጅት ደረጃውን ወደ አሸባሪ ድርጅት ከፍ አርገውት ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በግሌ ልጆቹ በብሎጋቸው የፃፉት ሰላምን፤ አንድነትን፤ ፍቅርን፤ የሰባዊ መብት መከበርን፤ ዶሞክራሲን እንጂ አንድም ቀን ሽብርን ሲፅፉ አይቼ አላውቅም፡፡ እነዚህ ነገሮች ሽብር ከተባሉም ሽብር መልካም ነገር እንጂ መጥፎ ነገር አይደለም፡፡
ስለዚህም እጠይቃለሁ የዞን 9 ጦማሪያን ወንጀል ሰርተዋል ብዬ አላምንምና ባስቸኳይ ይፈቱ፡፡ Zone9
#freezone9bloggers
የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ዞን 9 በድጋሚ የዞን 9 አባላት ያወሰድዋቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌላ እያረጋገጠ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲሁም ኢሜሎችን በመላክ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያቸወን በማቅረብ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን፡፡
- ፍትህ ሚኒስትር Ato Desalyn Terasa 0115-51-50-99 /ext/286 0115-15 35 28
- እምባ ጠባቂ Ato Liul Seyum / Ato Gezagegn Tsfaye ,Public Relations 0111-58-06-52/ 0115-54-33-36 0115-53 20 73
- የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር Ato Aidsu Petros 0116293040, 0116293071
- የፕሬዘዳንቱ ቢሮ Ato Gebru Abreha / Ato Adnew Abra 0111-22-67-67 , 0111-24-46-14
0115-51-20-41
- ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት +251115512744
- የኢትዩጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን 0 11-550-41-14
#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Stoptourture
We are alive we will survive this and we will keep being alive. #FreeZone9blogger #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamw #StopKillingOrmoStudents #OromoProtest #Ethiopia
ዞን 9 ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁለት አመታት በነበረው ቆይታ የተለያዩ አጋርነቶችነ ከተለያዩ አካላት ጋር ፈጥሮአል፡። በዚህም በተለያየ ጊዜ እነደግለሰብም አንደቡድን ተወካይ በመሆን አባላቱ አገሪትዋ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብጥ ጥሰት አያያዝ አስመልክቶ ለተለያዩ ቦታዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ ኢንተርኔት ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚያደርጋቸውን አስተዋእጾም አስመልክቶ በቡድንም በነጠላም በተለያዩ ቦታቸዎች ላይ በመገኘት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ ይህ መንግስት ሲፈልግ የሚፈቅድላቸው ሲፈልግ ወንጀል የሚያስመስለው ተግባር ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ህገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ዜጎች በመጓዛቸው ስራቸውን እና ልምዳቸውን በማካፈላቸው እነዲሁም ራሳቸውን ብቁ በማድረግ የሚሰሩትን የሰብአዊ መብት እነቅስቃሴ ለሌሎች መናገራቸውን ወንጀል ለማስመሰል የሚደረገውን ጥረት አሁንም ቢሆን እንደዞን 9 አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ከዚህ በፌትም እነደተናገርነው በህግ እስካልተከለከለ ድረስ ህጋዊ እንቅስቃሴዎቸን መንግስት ስላልወደዳቸውና ህገ ወጥ ስላስመሰላቸው የምናቆምበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሁሉም የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆች በፓርላማ በህገ ወጥነት ከተፈረጁ ተቋማት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም የላቸውምም፡። ለዞን ዘጠኝ ስራም ምንም አይነት የፋይናንስ ድጋፍ አግኝተን አናውቅም፡፡ (በመሰረቱ የፋይናንስ ድጋፍ የማያስፈልገው የበጎ ፍቃደኝነት ስራ ነው የምንሰራው ) ከዚያ ውጪ ግን በፓርላማ ህገ ወጥ እስካልተባሉ ወይም ከልካይ ህግ እስካልመጣ ድረስ ከተለያዩ በተባበሩት መንግስታት እውቅና ካላቸው የመብት ተሟጋች ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት ወንጀል ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አንቀበለውም፡።
የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው እነደነበር ታወቀ
አርብ አመሻሹን እና ቅዳሜ ጠዋት የታሰሩት የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና (እሁድ ጠዋት) ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታወቀ፡፡ ቤተሰብም ሆነ የህግ ባለሞያ ባላወቀበት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ክስ ላይ
“ውጨ ሃገር ከሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ነን ከሚሉ ጋር በገንዘብና በሃሳብ በመተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ሃገርን ማሸበር” ወንጀል መጠርጠራቸው የተገለጸ ሲሆን
1. ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሃይሉ ለሚያዚያ 30
2. ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለግዮርጊስ ዘላለም ክብረት ለሚያዝያ 29
3. አጥናፍ ብርሃኔ ኤዶም ካሳየ ናትናኤል ፈለቀ ሚያዝያ 30 ተቀጥረዋል፡፡
The journalists and bloggers are charged of “Working with foreign human right activist organizations agreeing with idea, finance and inciting violence through social media to create instability in the country” with three different files.
Hence;
1. Mahlet Fantahun
2. Abel Wabela
3. Befeqadu Hailu are appointed for May 8 2014
1. Tesfalem Weldyes
2. Asmamaw W/Giorigis
3. Zelalem Kebret are appointed for May 7 2014
1. Atenaf Berahene
2. Edom Kassaye
3. Natnael Feleke are appointed for May 8 2014
#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem#FreeAsemamaw #Ethiopia
የዞን ዘጠኝ የቅርብ ወዳጅና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ ታሰረች
According to the latest information we got, Journalist, campaigner and close friend of Zone9 have been arrested and her house was searched this late morning. For the last few months Edom had been in serious interrogation and surveillance from “Intelligence officers” questioning her details on the activities of the Zone9. Zone Nine again wants to confirm that Edom and other Bloggers has never been a part of any illegal activity and we request the government to release all immediately.
የታሰሩ የዞን9 ጦማርያንና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ማእከላዊ ምርመራ እነደሚገኙ ተረጋገጠ
በድጋሚ የዞኑ አባላትና ወዳጆች ምንም አይነት ህገ ወጥ ስራ ላይ ያልተሰማሩ በመሆናቸው መንግስት እርምት ወስዶ በአስቸኳይ አንዲፈታቸው እንጠይቃለን!
Zone9 has confirmed that Six Zone9 bloggers and journalist Tesfalem Woldeyes are in Addis Ababa central investigation center (meakelawi) since their arrest last night. during the arrest their house was searched and police took laptops, Newspapers and books from their home. Families were not allowed to meet them.We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with any illegal activities and we again request the government to release them immediately.
ስድስት የዞን 9 ጦማርያን በመንግሥት ተያዙ፣ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን
We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with illegal activities and we request the government to release them immediately.
Zone9.
አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት መሳሪያዎችና ኢትዮጵያ
Why couldn’t #Ethiopia/n government welcome the new journalists’ Forum optimistically?
Ethiopian Journalists Forum is a young independent journalists association that undergone its founding assembly two months ago. The Forum, therefore, has – according to law – three months of time since its assembly to be counted as one of registered associations to work towards its goal while processing to acquire license. It is now in this period of grace. However, government media (especially Addis Zemen) launched a campaign against the Forum even before it gets its license and start functioning.
The Ethiopian government has never been a friend to any civil society. The ‘charity law’ that extremely limits foreign financing of civil societies that work on rights issues and the 70/30 project cost regulation which also indirectly limits awareness creating activities, both, were passed because the government undermines (or even dislikes) the role of civil societies in the democratization process. In this regard, we can’t expect love of a new association from a ‘head’ that killed thousands of civil societies in passing restrictive rules and regulations.
In addition to that, the independent media and Ethiopian government never had a friendly relationship; the former strongly criticize the latter which gags them in a negative response to it. So, ‘journalists association’ means to our government the sum of two evils. In this premise, it’s no wonder that the Ethiopian government is not optimist about the upcoming Forum. But, why is it so pessimist about an association that isn’t even proved will stand strong?
Addis Zemen published many stories that label the new journalists’ Forum as agent for ‘color revolution’. ETv produced a documentary without directly mentioning the Forum but by condemning both the ‘color revolution’ and media use as a tool promoting it. It hated the Forum enough to label it before its establishment. But, its fear of civil societies and the media are not the only factors that made the government this much overwhelmed of the Forum. The already existing journalists’ Associations have fueled the fire.
Anteneh Abraham is an all-time president of Ethiopian National Journalists Union (ENJU). His Association always has the same stand with the government. It claims there are no journalists who are jailed for what they have written. The president, as the saying goes ‘more catholic than the pope’, is more EPRDFite than EPRDF in itself. He was the first person to accuse this newly born Forum for being a ‘foreign agent’ in Addis Admass newspaper. Why? Because Anteneh knew that the Forum will reveal ENJU’s real identity.
ENJU is a relatively and undeservedly accepted union of journalists in a few international societies. It’s even a member of International Forum of Journalists (IFJ) and yet it never considered the imprisonment and exiling of journalists a challenge to the media. All the journalists it has as members are from Walta and Fana Broadcasting Corporate (FBC) – both are mouthpieces of the government as they are businesses run by TPLF heads.
The new Forum, while processing the license, has been informed from the ‘Charity Agency’ that there is a compliant from the existing Associations. The compliant is not clear for me yet. But, it is a compliant from ENJU and others.
These Associations, wearing two hats, want to fool the international community and get recognition while at the same time attend for sweet dishes with the ruling party i.e. serving the needs of it. This can’t sustain if EJF comes to life. Therefore, to stop or not to stop this Forum before formation is a battle for life for these fake journalists’ Associations. They won’t stop it unless one of them are successfully defeated. Unfortunately, the fake Associations have one thing that the Forum hasn’t: they have the government’s support.
በሕገመንግሥታዊ መብቶቻችንን ተጠቅመን ስለሕገመንግሥታዊነት መነጋገራችንን እንቀጥላለን!
ኢሕአዴግን እንበይነው!
ሁሉንም ተቃዋሚ እንደአንድ መመልከትም ሆነ በአንድ አዕምሮ እንዲያስብ መጠበቅ የገዢው፣ የተገዢዎች፣ የተቃዋሚዎች ሁሉ የጋራ ችግር ነው። ሚሊዮን ችግሮች እና ሚሊዮን ተቃዋሚዎች ባሉበት አገር ውስጥ ተቃዋሚዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ሊሆኑ አይችሉም። ይሁን እንጂ ሁሉም ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን በቅጡ ያውቃሉ ብሎ ለማለትም ያስቸግራል፤ ምክንያቱም “በስመ ተቃዋሚ ሲሳሳሙ” ማየት የተለመደ ነው። ተቃዋሚዎችን በተቃውሞ አካሔዳቸው መግባባት ላይ መድረስ እንዲያቅታቸው ከሚያደርጋቸው ችግር አንዱ ኢሕአዴግን የሚበይኑበት (define የሚያደርጉበት) መንገድ መለያየቱ ወይም ግልጽነት ማጣቱ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።
ብያኔ ለምን ያስፈልጋል?
40 ዓመት ወደኋላ መለስ ብለን የአብዮቱን ልጆች ለመከፋፈል እና ለእርስበርስ እልቂት የዳረጋቸው ዋነኛውን፣ የሚታገሉትን አካል (ደርግን) የበየኑበት መንገድ ነው። የኢሕአፓ እና የመኢሶን ዋነኛ ልዩነት፣ የኢሕአፓና አንጃ እያለ የሚጠራቸው አባላቱ መካከል የተከሰተው የሐሳብ መሰነጣጠቅ፣ ብሎም እርስበርስ መጨራረስ ደርግን የሚበይኑበት መንገድ መለያየትን ተከትሎ የተወለደው ደርግን ለማስወገድ የመረጡት መንገድ ነው። ሁለቱ (የተቀናቃኝ ወገን ብያኔ እና የመቀናቀኛ መንገድ ምርጫ) ተሰናስለው የሚኖሩ ጉዳዮች ናቸው። በጥንቃቄ ሳይጤን የሚገበቡበት ገደል አይደለም።
ኢሕአዴግ፣ በዚህ ረገድ ራሱን ግልጽ የማድረግ ችግር የለበትም። ተቀናቃኞቹን አንዱን አሸባሪ፣ አንዱን የአሸባሪ ደጋፊ፣ ሌላውን ለዘብተኛ እያለ የሚኮረኩምበትን መንገድ አስቀምጧል። ኢሕአዴግ መሣሪያ ታጣቂ እንደመሆኑ ተቀናቃኞቹን ባይበይናቸውም ቅሉ ማሽመድመጃ መንገድ አይቸግረውም። ለተቃዋሚዎች ግን ‘ኢሕአዴግ ምንድን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሕልውና ጉዳይ ብቻም ሳይሆን ወዴት እና እንዴት እየሄደ እንደሆነ የሚያውቁበት ወሳኝ ጥያቄ ነው።
የበኩር ጥያቄ፤ ኢሕአዴግ ምን ያስባል?
ኢሕአዴግ እንደማንኛውም ገዢ ፓርቲ በፖለቲካዊ ብልጫ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ የሚኖር ፓርቲ ነው? እያጭበረበረ የሚኖር ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? ሕዝባዊ ይሁንታ ባገኘ መንገድ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ኃይሉን መከታ በማድረግ ሥልጣኑን ያለመጋራት የተቆጣጠረ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ በኃይል ሥልጣኑን እያስጠበቀ ያለ ፓርቲ ነው? ወይስ ምንድን ነው?…ብዙ ዓይነት ትርጉሞች (ሁሉም እውነት ያላቸውን) ማስቀመጥ ይቻላል። የራስንና አንድ ወጥ ትርጉም ማስቀመጥ የሚበጀው የሚከተሉትን የትግል ስልት ለማወቅ እና የሚጠብቁትንም (what to expect) ለማወቅ ነው።
በአማራጭ ፓርቲዎች መካከል እና ለዴሞክራሲያዊነት በሚደረጉ ነጻ (የአራማጆች እና የሲቪል ማኅበረሰብ) ትግሎች ምን ዓይነት መሆን አለባቸው የሚለውን መወሰን የሚቻለው የሚታገሉለትን ነገር በማወቅ (ለምሳሌ ለዴሞክራሲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ) ከሚለው በተጨማሪ ተቀናቃኝ አካላትን በሚገባ በማወቅና በመበየንም ጭምር ነው። የኢሕአዴግን ማንነትም በቅጡ መበየን የሚያስፈልገው አላስፈላጊ ጊዜ፣ ገንዘብና ጥረት ላለማባከን እና የጠበቁትን ውጤት ለማግኘት ነው።
‘ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በኃይል ተቆጣጥሮ በኃይል እያስጠበቀ ያለ ድርጅት ነው’ ብለን ካልን ሠላማዊ ትግል የሚባለው ሁሉ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ግን ይህንን ለማለት የሚያስችል በቂ መረጃ አለ ወይ? ኢሕአዴግ ብረት ታጣቂውን ደርግ ለመገርሰስ ከኃይል ውጪ አማራጭ ነበረው? የሥልጣን ባለቤት ከሆነ በኋላ ሥልጣኑን ያላስረከበው በፓርቲው እምቢተኝነት [ብቻ] ነው ወይስ የተቀናቃኞቹም እጅ (ድክመት) አለበት? ኢሕአዴግን ከኃይል መለስ ባለ ነገር ከሥልጣን ለማውረድ የሚያስችሉት በሮች ሁሉ ተዘግተዋል? ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አባላት ያሉትን ፓርቲ ‘ጠላት’ ብሎ ለመፈረጅ የሚያስችል ሁኔታ አለ? ይህ መሰሉ ድምዳሜ እና ፍረጃ በታሪክ ከተሠሩ ስህተቶች አንፃር ምን ያክል የተማረ/የታረመ ነው?
‘ኢሕአዴግ በኃይል ያገኘውን ሥልጣን በሕዝባዊ ይሁንታ (እንበል ምርጫ) ቀጥሎበታል’ ካልን ደግሞ ለስርዓት ለውጥ የሚደረጉ ትግሎች ፍፁም ሠላማዊና ግልጽ መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ነው። ይህም እልፍ ጥያቄዎችን ይወልዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ እውን የሥልጣን ርክክብ ማድረግ ይቻላል? ከምርጫ ውጪ የሥልጣን ሽግግር የሚመጣባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ? ኢሕአዴግ ሕዝባዊ ይሁንታ ካለው ትግሉ (ለውጡ) ለምንድን ነው? በሠላማዊ መንገድ የሚመጣው ለውጥ ምን ዓይነት ነው?… ወዘተ።
እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች እንደምሳሌነት ብንወስድም፣ ሌሎችም ጥያቄዎች በተለያዩ ብያኔዎች ላይ ተመሥርቶ ማውጣት ይቻላል። በምሳሌው ውስጥ የተካተቱትን ሁለት ብያኔዎች ተንተርሶም፥ ሁለቱን ብያኔዎች የሚሰጡ አካላት አብረው ሊሠሩባቸው የሚችሏቸው እና የማይችሏቸውን ጉዳዮች አብጠርጥሮ ማውጣትም ያስፈልጋል እንጂ በብያኔ ተለያይተናልና አብረን የምንሠራበት መንገድ የለም ማለት ላይሆን ይችላል። ይህን ባለማወቅ የሚደረግ ትግል ግን መነሻውንም፣ መድረሻውንም የማያውቅ ተራ ጥላቻ የሚመራው ጉዞ ነው።
መበየን ቀላልም፣ ከባድም፤ ትንሽም፣ ብዙም ነው
ኢሕአዴግን የተለያዩ አካላት የተለያየ ብያኔ ይሰጡታል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያዊ (ብሔራዊ) ስሜት የለውም ከሚሉት ጀምሮ ለኢትዮጵያ የመጨረሻው የመድኅን ስጦታ ነው እስከሚሉት ጽንፎች ድረስ የሚደርስ ብያኔዎች አሉት።
እኔ በግሌ ኢሕአዴግ በተለያዩ ሒደቶች ውስጥ የተለያየ ምልከታዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እያጎለበተ የመጣ ቡድን ነው ብዬ አምናለሁ። ፕሮፌሰር ክላፋም እንዳሉት፥ ‘ሕወሓት በብሔር ዓይን ኢትዮጵያን እየተመለከተ መጥቶ ገዢ ሆነ፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ (በኢትዮጵያዊ ዓይን) ኤርትራን ጦርነት ገጠመ፤ ይህም ሁለተኛ ዕይታ ሰጠው’። ምናልባት እዚህ’ጋ መጨመር ቢያስፈልግ ሕወሓት (የጠቅላላው ኢሕአዴግ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ እንደመሆኑ) ከምርጫ 97 በኋላ ኢትዮጵያዊ (ኅብረብሔራዊ) ስሜት ማዳበር ባይችል እንኳን ያለሱ ብዙ እርምጃ መጓዝ እንደማይችል ተረድቷል። ስለዚህ ኢሕአዴግ በሦስት ደረጃዎች ውስጥ አልፎ እዚህ ደርሷል ባይ ነኝ፤ ሁሉንም ነገር በዘውግ-ብሔር ዓይን የሚመለከትበትና የሚተረጉምበት ደረጃ (አንድ)፣ ኢትዮጵያዊ ኅብረብሔርተኝነትን ለአጀንዳ ማስፈፀሚያነት (ለምሳሌ ለጦር መቀስቀሻነት) የሚያውልበት ደረጃ (ሁለት)፣ እና ያለኢትዮጵያዊ ኅብረብሔራዊ ስሜት እና መሰል እርምጃዎች (ምሳሌ የባንዲራ ቀን) መራመድ እንደማይችል የተረዳበት ደረጃ (ሦስት) ናቸው። ይሁን እንጂ የዘውግብሔርተኝነትን እና ሕብረብሔርተኝነትን ሚዛን የሚያስጠብቅበት ግልጽ አካሔድ የለውም፤ ይልቁንም እንደ ሕዝባዊው ስሜት አነፋፈስ ተስማምቶ ለመንፈስ ብቻ እየተፍጨረጨረ ነው።
ኢሕአዴግን ከላይ ልበይነው የሞከርኩት በኢተዮጵያዊነት ስሜቱ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ሥልጣን ላይ ያለውን አመለካከትም በአካሔዱ ለመተርጎም ብሞክርም በርግጠኝነት ልበይነው አልቻልኩም። ኢሕአዴግ ከስኒ ማዕበል በላይ አቅም የሌላቸውን ተቃዋሚዎች ይቀበላል። ከዚያ በላይ ያሉትን ግን በቀና ልቦና እንደሚቀበል አላሳየም፤ ሆኖም በሙሉ አቅም ተፈትኗል ማለትም አይቻልም። የደኅንነት፣ የኮሙኒኬሽን እና የመከላከያውን ቁልፍ ሚናዎች በሕወሓት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዲሁም ኢኮኖሚው በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር ስር ማድረጉም ሥልጣኑን በሠላማዊ መንገድ ለመልቀቅ ያለውን ዝግጁነት አጠራጣሪ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ እስከመጨረሻው ድረስ ተገፍቶ ያልተሞከረ በመሆኑ ለሠላማዊ ትግል በር ተዘግቷል ሊባል በማይቻል መወላወል ውስጥ አስቁሞናል።
ብያኔ ቸኩለው የሚገቡበት ጉዳይ አይደለም። ርዕሱን ከብዙ ገጾች ማየት ያስፈልጋል። ነገር ግን ያለብያኔ ቋሚ አቅጣጫ መያዝ አይቻልም፤ ባይሆን ብያኔንም አቅጣጫንም በየጊዜው መከለስ ያዋጣል።
‘Blame the Victim’: The Quest for Freedom vs. Professionalism of Media in Ethiopia?
“…Tafari and others draw three periods of the private press in Ethiopia. The first period was the chaotic period from 1991 to 1997 with a blooming of new newspapers and anarchy journalism. The second period, 1997-2005 saw the establishment of professionally and ethically integrated newspapers like Reporter, Addis Admas, Fortune and Capital. The last period goes from 2005 when press freedom again came under threat after editors and journalists were imprisoned and persecuted after alleged transgressions following the May 2005 elections…”
“David Ben-Gurion once said, ‘The test of democracy is freedom of criticism.’ Freedom of criticism has long been recognized as an essential, inalienable human right; a right that is thought to transcend political and geographical borders and applies regardless of culture, language, and national origin. In Ethiopia, as democracy begins to grow despite a history of corruption and totalitarianism, freedom of expression has proven to be an unsteady notion […]
“If Ethiopia hopes to move toward a more democratic State, it is critical to open the lines of communication between the government, media, and citizens. Freedom of expression is the only way to achieve an accountable and transparent government free from corruption and tyranny, while developing a professional and unbiased press. The press, in other words, must have the freedom to criticize the government.”
Edited by: Soleyana Shimeles
የትግራይ ሕዝብ ከሕወሓት የተሻለ “ወዳጅ” አለው?
ከዚህ በፊት ‘የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት ምንና ምን ናቸው?’ ብዬ በጠየቅኩበት ጽሑፌ፤ እጅና ጓንት ናቸው ብዬ ነበር። ስለብዙኃኑ ትግራዋዮች እያወራን ከሆነ አሁንም ያው ነው መልሴ። በዚያ ጽሑፍ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስኩት ሕወሓት በሚያገኘው ሙሉ ድምፅ አይደለም፤ ያንን የሚያክል ድምፅ አዲስ አበባ ውስጥም የትም ፈጭቶ የትም አግኝቶታል። ሕወሓትን የሚወዱት አማራጭ አጥተው ነው ብዬ ነበር የተከራከርኩት። ምክንያቱም ደግሞ ትግራዋይ ያልሆነው ሰው ሁሉ ትግራዋዩን በሕወሓት መነፅር ስለሚመለከተው ተገፍቶ ነው ባይ ነበርኩ በዚያ ጽሑፍ (በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ‘ምን ዓይነት አማራጭ አጥቶ ነው?’ የሚለውን ነው የምጠይቀው) ።
እርግጥ ይሄ ብቻ በቂ ምክንያት አይደለም። ሕወሓት ለሁለት ዐሥርት ዓመታት የዘራው የጥርጣሬ ፕሮፓጋንዳ ትግራዋዮች ሕወሓትን ባይወዱት እንኳ ለሌሎች የሚኖራቸው ጥርጣሬ ከሱ ጉያ እንዳይወጡ ያስገድዳቸዋል። (ፀረ-ቅኝግዛት ተንታኞች የጥገኝነት አባዜ የሚሉት ዓይነት።)
ይህንን ድምዳሜ የእነአብርሃ ደስታን የግለሰብ እና አረና ፓርቲን የቡድን ቁርጠኛ ትግል አጣቅሶ ፉርሽ ለማድረግ የሚሞክር አይጠፋም ብዬ እገምታለሁ። ችግሩ፣ የአረና ተቀባይነት ከጥቂት የልሒቃን ትግራዋዮች አልፎ ብዙኃኑ ውስጥ ሰርጿል ወይ የሚለው ጥያቄ ሲመጣ ነው።
ወደ ጽሑፌ ርዕስ ስመለስ ‘ወዳጅ’ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩበት ሕዝቡ የሚወደው ለማለት እንጂ ድርጅቱ የሚወደው ለማለት አይደለም። የአንድ ወገን ፍቅር ነው። አዎ፣ ሕዝብ ሆነን ስናስበው ሕዝቡ የሚወደው “የተሻለ” አማራጭ የለውም።
ሕዝብ ማለት (ቢያንስ ለዚህ ጽሑፍ) በደረሰበት የማኅበረሰባዊ ዕድገት (social evolution) ደረጃ ብቻ የሚያስብ፣ ስሜታዊ፣ ማኅበራዊ እንስሳ ማለት ነው። ሕዝብ ደምበጫ ውስጥ የኦሮሞ ስም ይዞ የመጣ ሰው አይመርጥም፣ ሰላሌ ውስጥ የትግራዋይ ስም ይዞ የመጣ ሰው አይመርጥም፣ አዲግራት ውስጥም እንደዚያው ነው። ይህ የወገን ፍለጋ እሳቤ የሰለጠኑት ዓለማትም ውስጥ የተቀረፈ ነገር አይደለም። አሜሪካ ውስጥ የሳኡዲ አረቢያ ስም የያዘ ፕሬዚደንት ቢያንስ በቅርቡ አይመረጥም። ስለዚህ ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ይህን የሕዝብ ፍላጎት ያሟላል። ያውም ነፍጥ አንስቶ ሕዝቤን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ለመታገል እስከሚደርስ ጀብደኛ ታሪክ (legend) በማሟላት። ስለዚህ ለአረና እና ሌሎችም አማራጭ ፖለቲካ ይዘው የትግራይን ሕዝብ ልብ ለመግዛት የሚታገሉ ፖለቲከኞች ዐብይ ፈተናቸው ይህንን የትግራዋዮች እና ሕወሓት የልብ ለልብ ግንኙነት የሚያሻክር ማስረጃ አሳይቶ፣
ከዚያ የተሻለ ነገር እንደሚያቀርቡ ማሳመን መቻል ነው። ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ይመስላል።
ሕዝብ ጥቅሙን ወዳድ ነው። ፖለቲከኞችም የሚሟገቱት የሕዝብ ጥቅም በሟሟላት ስም ነው። ስለዚህ የሕዝብ ጥቅም በማሟላትም ረገድ ቢሆን የሕወሓት ተፎካካሪዎች ቀላል ፈተና አይኖራቸውም። ሕዝብ ቅቡልነት (legitimacy) የሰጠው መንግሥት የሚያደርገውን ሁሉ ለጥቅሜ ነው ብሎ ያምናል። ሕወሓት ደግሞ በትግራይ ውስጥ የብዙኃኑ ቅቡልነት ይጎልበታል ብሎ ለመከራከር የሚያስችል በቂ መረጃ የለንም። ስለዚህ ተቃዋሚዎች ለሕዝቡ ጥቅም የሚበጅ የተሻለ አማራጭ ይዘው ከመወትወታቸው በፊት በሕዝቡ ውስጥ ቅቡልነት ለማግኘት መድከም አለባቸው። ቅቡልነት ደግሞ ሕዝቡ ቀድሞ የተቀበለውን ቡድን ስም አፈር ድሜ በማስበላት ብቻ አይገኝም፤ እንዲያውም ይህንኛው ወደኋላ ሊባርቅ (backfire) ይችላል። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ወካይነታቸውን እና ሕወሓት ከሕዝቡ ጉያ ወጥቶ ርቆ መሄዱን የሚያስመሰክሩባቸው ብዙ መንገዶችን መፍጠር አለባቸው።
ሌላውና የማይናቀው ሕወሓትን የተሻለ አማራጭነት በትግራይ ውስጥ የሚያጎላው ደግሞ ጉልቤነቱ ነው። የሕወሓት በኢሕአዴግ ውስጥም ሆነ በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ከዕኩልነት የበለጠ ኃይል ሌላውን ሕዝብ፣ አራማጆችን ወይም የሕግ የበላይነት የሚያሳስባቸውን ሰዎች ያሳስብ እንደሆነ እንጂ ብዙኃኑ ትግራዋዮችን አያሳስብም። ሕዝብ ይወክለኛል የሚለው ቡድን የበላይ ኃይል ሲኖረው አይጠላም። የአረና ፈተናም ይኸው ነው። የትግራይ ሕዝብ አረና ከሕወሓት የተሻለ ፖለቲካዊ አማራጭ ይዞ መጥቷል ቢሎ ቢያስብ እንኳ ሕዝቡ በሌሎች ሕዝቦች ላይ የሚኖረውን [የጦር] ኃይል የበላይነት ያስነጥቀኛል ብሎ ካሰበ ለመምረጥ ይቸገራል። ይህ የትግራይ ሕዝብ የተለየ ባሕርይ አይደለም፣ የሁሉም ሕዝቦች ባሕርይ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በአገራት መካከል ያሉ ሽኩቻዎችም ባብዛኛው በዚሁ የበላይነት ጥያቄ እንጂ የዕኩልነት ጥያቄዎች የተነሱ አይደለም።
ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ የሕዝብን የጋራ የአስተሳሰብ ፍሰት እንጂ የሕወሓትን እውነተኛ ወካይነት ያረጋግጣሉ ብሎ መደምደምም አይቻልም። ሕወሓት የሚደነቀው የሕዝቡን ሥነ ልቦና በመረዳት መጠቀሚያ ማድረጉ ነው። በዚህ መሐል ግን በርካታ ለማረም የሚቸግሩ ስህተቶችን ሰርቷል። ከስህተቶቹ ሁሉ የከፋው በፌደራሊቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሌሎች ሕዝቦች የትግራይን ሕዝብ በሕወሓት ዕዳ እንዲጠመድ (በጥርጣሬ ዓይን እንዲታይ) ማድረጉ ነው፣ በምላሹም የትግራይ ሕዝም ሌላውን የማያምን የሕወሓት ጥገኛ አድርጎታል። እነአረናም ይህንን ክፍተት በመሙላት እና የሁሉም ወገን ሕዝቦች ለዘመናት የነበራቸውን ትስስር ባለበትና በተሻለ የዕኩልነትና ወዳጅነት ስሜት ለማስቀጠል የሚያስችል ፕሮግራም መቅረፅ ይጠበቅባቸዋል። እስከዚያው ድረስ ግን ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ የቅርብ ወዳጅ መስሎ መኖሩን ይቀጥልበታል።
እኔ የምፈልገው ኢሕአዴግ ወርዶ ማየት ብቻ ነው!
ትላንት የጥላቻ ንግግርን የተመለከተ ጥናት ማሟያ ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም፥ ቀብዱን ግን እነሆ፦
ርዕሱ በኢሕአዴግ እና በደጋፊዎቹ አተረጓጎም “የጥላቻ ንግግር” ተብሎ ሊመደብ ይችላል። አንድ የዴሞክራሲ ሕልመኛ ርዕሱ ላይ የተጠቀሰውን ዓ/ነገር ቢናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ጥላቻ ሰባኪ አያሰኘውም ባይ ነኝ እኔ ግን። እኔ ራሴ ርዕሱ ላይ የተጻፈውን ያለምንም ጥላቻ ከውስጥ ፍላጎቴ ነው ያፈለቅኩት።
ከዴሞክራሲ ዐብይ ባሕርያት አንዱ ገዢ ፓርቲዎች ወርደው የሕዝብ ምርጫ በሆኑ ተቃዋሚዎች መተካት የሚችሉበት እና ገዢ የነበሩ ተቃዋሚ ሆነው የሚሮጡበት ስርዓት ማመቻቸት ነው። ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊነት መፍጨርጨሯ ሐቀኛ ነው ልል የምችለው ኢሕአዴግ ወርዶ ተቃዋሚ ሆኖ ሳየው ነው።
የጥላቻ እና የፍቅር ንግግሮች የሉም ማለት አልችልም። ነገር ግን የጥላቻም ይሁን የፍቅር ንግግሮች ዋጋቸው ከአንድ ክበብ አያልፍም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ነክ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች በባሕሪያቸው መድባቸው ብባል በሦስት እመድባቸዋለሁ፦
1ኛ) አፍቃሬ-ኢሕአዴግ፣
2ኛ) ኢሕአዴግን-አያሳየኝ እና
3ኛ) I-don’t-know-what-to-doዎች በማለት።
የመጀመሪያዎቹ [አፍቃሬ-ኢሕአዴግ]ዎቹ ዋነኛ ሥራቸው በማንኛውም መንገድ ኢሕአዴግን ማንቆለጳጰስ እና ከተቃዋሚዎች ክፉ ዓይን መጠበቅ ናቸው። አዳም ሲፈጠር ጀምሮ “በስም መስጠት ነው (naming)” ነው ሥራውን የጀመረው እንዲሉ እኔም በዚህ ምድብ የምፈርጃቸውን ጥቂቶች ልዘርዝር፤ ኢቴቪ፣ ዛሚ ኤፍኤም፣ ኢትዮ-ቻናል፣ ትግራይ ኦንላይን እና ወዘተ ናቸው።
ሁለተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኙት [ኢሕአዴግን-አያሳየኝ]ዎች ደግሞ የሚደግፉት (የሚያፈቅሩት) የተለየ የተቃዋሚ ቡድን የላቸውም፣ የሚራሩለት እንጂ። ነገር ግን ያለምንም ጥርጥር ኢሕአዴግን አይወዱም። ስለዚህ ሥራቸው ኢሕአዴግን መተቸት ነው። እነዚህ ውስጥ ኢሳት፣ ፋክት፣ ኢትዮጵያን ሪቪው እና ወዘተ ይገኛሉ።
ሦስተኛው ምድብ [I-don’t-know-what-to-do]ዎች ውስጥ ያሉት ደግሞ በመሐል ቤት ይዋልላሉ። ለዚህ ቡድን አሪፍ ምሳሌ የሚሆኑት ደግሞ አዲስ አድማስ ጋዜጣ እና ሸገር ኤፍ ኤም ናቸው። በተረፈ ጥቂቶች ብቻ ለመፈረጅ የማይመች የሚዲያ ሥራ እና ሊረዱት የሚከብድ የአቋምና አቀራረብ ልዩነት ያሳያሉ።
ለምን እነዚህን ፍረጃዎች እና ስየማዎች ማድረግ አስፈለገኝ? ምክንያቱም የጥላቻ ንግግሮች በማን፣ እንዴት እንደሚተረጎም ቀላል ማስረጃ ስለሚሆነኝ ነው። ምድብ አንድ ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውንም ዓይነት ኢሕአዴግ ላይ የተሰነዘረ ትችት የጥላቻ ንግግር ነው።
ምድብ ሁለት ውስጥ ለሚገኙትም ከኢሕአዴግ አፍ የሚወጣ ሁሉ ክፉ ነገር ነው። ሦስተኛው ምድብ ከቻለ ሁሉንም ለማስደሰት ካልቻለ ሁሉንም ላለማስከፋት ይፈጨረጨራል። በመሐል ቤት እውነት ማደሪያ ታጣለች። ሁሉም ለዓላማው እጇን ይጠመዝዛታል።
በአገራችን የጥላቻ ንግግር የሚባሉት ሁሌም ከጥላቻ የመነጩ ላይሆኑ ይችላሉ። በባሕላችን የሰውን ስህተት ፊት ለፊቱ መንገርን እንደአለመከባበር የሚያስቆጥር ስህተት ነው። ስለዚህ የአንድን ሰው ጉልህ እንከን እንዲህ ነህ ብሎ መንገር በጣም አስደንጋጭ ነው የሚሆነው። እንዲያውም በጠብ ወቅት ብቻ የሚከሰት ነገር ነው። ስለዚህ በትልቁ (በፓርቲና በፖለቲካዊ አመለካከት ላይ) ሲሰነዘር የእርምት አስተያየት መሆን ቀርቶ የትችት ማዕረግ እንኳን አያገኝም። የጥላቻ ይመስላል (ይባላል)።
ነገር ግን፤ ድክመትን እየሸሸጉ ብርታትን እንደመንገር ያለ አደገኛ ንግግር (dangerous speech) አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ለግለሰብም ይሁን ለቡድን ግብዝነት ይዳርጋል። ድክመት ሲነገረው እልል ብሎ በፈገግታ ተጉመጥምጦ የሚውጥ ግለሰብም ይሁን ቡድን ገጥሞኝ አያውቅም፤ ከትችቱ አለመማር ግን እየሰሙ አይቻልም፤ ከስህተት ላለመማር መፍትሔው እንደኢሕአዴግ ተቺውን ማፈን ብቻ ነው። ትችት ካደመጡት ግን ምናልባት ለመዋጥ ጊዜ ይወስድ ይሆናል እንጂ ዘልቆ መቆጥቆጡ አይቀሬ ነው።
ይሄ ሁሉ ግን ስለጠሉ ብቻ የሚተቹ፣ ስለወደዱ ብቻ የማይሞገሰውን የሚያወድሱ የሉም ማለት አይደለም። ጥላቻና ፍቅርም ምክንያታዊ አይሆኑም ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ክርር ያሉት የሥነ ልቦና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የጥላቻ ንግግርን መብት ከሐሳብን የመግለጽ መብት ለይቶ ለማስቀረት ሁነኛው መፍትሔ የማንፈልገውን ብቻ ሳይሆን የምንፈልገውንም ጭምር ማወቅ አለብን፤ አራማጅ ተራማጅነታችንም በመርሕ እንዲመራ ማድረግ መድኃኒቱ ነው።
አድዋን መዘከር፤ በአርበኞቹ መንገድ!
‹‹መላዋ አፍሪካ በአውሮጳ መንግሥታት ቅርምት የምትጠናቀቅበት ቀን ቀርቧል፤ አውሮጳውያኑ በአሜሪካ ያሳኩትን የዘር የበላይነት በአፍሪካ ለመድገም ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሜሪካ ቀይ ሕንዶችን በማስወገድ ለራሳቸው ዝርያ መኖሪያ መፍጠር የቻሉበትን ብቃት በአፍሪካ ለመድገም የጥቁር አፍሪካ ዝርያዎችን በቅርቡ ማጥፋት ይጀምራሉ፡፡››
![]() |
| ከብርሃኔ ንጉሤ ትዊተር ገጽ የተወሰደ |
‹‹ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን መፃኢ ዕድል የወሰነ ነበር፡፡ በዚህም የአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው፡፡ ምክንያቱም በቀጣይ መቶ ዓመታት የአውሮፓ የበላይነት እና አገዛዝ በአፍሪካ አክትሟል፡፡ የዘመናዊት አፍሪካ የሉዓላዊነት መሠረት ድንጋይ የጣለው አድዋ ላይ ነበር፡፡››
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተራራው ላይ ይቆማል ተብሎ የነበረውን ግዙፍ ‹ላንድማርክ› በተመለከተ ምን ደረጃ ደርሶ እንደነበር ያሬድ ሹመቴን ጠይቄው ነበር፡፡ ቢዘገይ እንኳን፣እስከ120ኛው በዓል ድረስ እንደሚጠናቀቅ ያለውን መረጃ አጣቅሶ ተስፋ ሰጥቶኛል፡፡
Uganda Law Provoked Ethiopian Discussion
There is no place for hate, discrimination in my beloved Africa. It’s not Governments’ business to make dress code or anti-gay laws. #Uganda.
Your Excellency, what’s your government’s position on same sex-relation? As far as I know, it’s illegal in Ethiopia.
Should we take this tweet as your opinion or the government office you are representing? If not, best to use ‘views are my own’ tag.
Being a minister of women and children, [it’s] not morally right to advocate against anti-gay law. How about in Ethiopia?
Yesterday’s tweet is not about gay rights, it is against hate and discrimination. We must care for one another. That is our first priority.
What so ever… Do you know how to resist such impositions? Have you listened to Museveni speech? Work on Women!!!
Nobody spoke about hate, madam minister; being pro-criminalization does not mean we hate the people. If the act is wrong something has to be done about it. It’s as simple as that. [It] has nothing to do with discrimination or hate.
Why are you pro-criminalization, though? You have to oppose legalization. But, advocating for criminalization is too far.
Law will only be enforced if there are consequences. That’s what differentiates it from moral values. Even if it’s not legal, what’s to keep people from going ahead and doing it, anyways, if there is no law prohibiting it?
Because, they love each other. Legalizing certain types of love is one thing, but, criminalizing it is to the extreme. By the way, what is your reason to opt to criminalize certain types of love that you are not part of? You are enjoying your sexual orientation and you want to prohibit others because they do not love what you love?
Can you honestly tell me there is a difference between not legalizing it and allowing it? Let’s be realistic here.
If it is not legal their relationship will not have a legal effect at all. No registration. No Communal property.
There is no place for hate, discrimination in my beloved Africa.
There is always a way we should figure out to live and let live in harmony regardless of our differences.
ብዙአየሁ “የማ[ላ]ቃትን” ሴት አስናፈቀኝ
“የሚጣፍጥ ሕመም ስሜት ነው፣ ቅር የሚል ደስታ፣
ሙሉው ጎዶሎ ነው ትርጉሙ ትዝታ፤”
ወትሮም፣ እመንገዴ ላይ “ትዝታ” ሙዚቃ የተከፈተ እንደሆን ሁሉም ነገር ቅዝቅዝ፣ ፍዝዝ፣ ድንግዝ ይልብኛል። አረማመዴ፣ የጄ ውዝዋዜ፣ ሁለ ነገሬ ስክን ብሎ ልክ እንደ ዝግታ የተንቀሳቃሽ ምስል እንቅስቀሴ (slow motion) ይሆንብኛል።
“ከኔ አንጀት ይመስል፥ የተሰራው ክሩ
ይረበሻል ሆዴ፥ ሲገረፍ ክራሩ፤”
የላይኞቹን የግጥሙን [የሕዝብ?] ስንኞች ከመስማቴ በፊት የብዙአየሁ 2ተኛው ትራክ የሰጠኝ ስሜት ይህንኑ ነው። መጀመሪያ ላይ ያደመጥኩት ጠዋት፣ ጠዋት ማኪያቶ የምጠጣበት ካፌ ውስጥ ነበር። የዚህ ጽሑፍ ከፊሉ የተጻፈውም እዚያው ነው። ዲጄውም የኔ ዕጣ ሳይገጥመው አይቀርም፤ ይደጋግመዋል። አስተናገጋጆቹም አብረው እያዜሙ ያስተናግዳሉ። በኋላ ላይ ግን በየታክሲው ሁሉ አደምጠው ጀመር።
አሁን በዚሁ ዜማ የተሰየመው ‘ሳላይሽ’ የተሰኘው ሙሉ አልበም አለኝ፤ ነገር ግን ከዚህንኛው ዘፈን በቀር ትዝ የሚለኝ ሌላ ዘፈን የለም። እርግጥ ዘፈን ሳደምጥ የሆነ ሥራ እየሠራሁ ወይም የሆነ ዐሳብ እያሰብኩ ስለሚሆን ሙሉ ልቤን አልሰጠውም። ልክ እንደዚህኛው ልቤን የሚገዘግዘኝ ካልመጣ በቀር የሰማሁት ምን እንደሆነ የማወቅ ዕድሉም ላይኖረኝ ይችላል።
ሙዚቃ ለኔ ስሜት ቆስቋሽ ከሆነ አሪፍ ሙዚቃ ነው ማለት ነው። የሚቀሰቅሰው ስሜት የምንም ይሁን፣ የምን በዜማው ሰው ማስቆዘምም ሆነ የሙድ ማፍታታት ማድረግ ከቻለ አለቀ! በእነሰርፀ ፍሬ ስብሐት ግምገማ ግን ከዚህ የተለየ ሊሆን ይችላል።…
ወደተነሳንበት ወግ ስንመለስ ብዙአየሁ እንዲህ ይላል፦
“ተስለሻል እንዴ ባይኔ በመሐሉ፣
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ፤”
ዓይኔን ጨፍኜ ትታየኛለች እንዴ ብዬ ሳስብ አትታየኝም። ከዚያ ዘፈኑን የወደድኩት በዜማው ውበት እንጂ በገዛ ትዝታዬ አይደለም ብዬ አልኩ፤ ጥያቄው ግን “ትታየኛለች/አትታየኝም” ብዬ ያልኳት በስመ ፆታ ሔዋን ነው ወይስ…? ከዚህ ጥያቄ በኋላ ነው የዚችን ጽሑፍ ርዕስ “የማላውቃትን” ካልኩት በኋላ ‘ቃ’ን ለይቼ በሳጥን ቅንፍ ውስጥ ያሰርኳት፤ ብትወጣም ስህተት የለውም እንደማለት።
ግጥም ያለው ዜማ ስንሰማ የምንወደው ግጥሙን ነው ዜማውን የሚለው ጥያቄ ሁሌም እንደፈተነኝ ነው። ብዙ ጊዜ ራሴን፣ ከዘፈን ግጥሞች ጋር አቆራኝቼ አገኘዋለሁ። ለምሳሌ የአብዱ ኪያርን ዜማዎች የምወዳቸው በግጥሞቹ ነው። ግን ደግሞ መልሼ ግጥሞቹን ያለዜማ ስሰማቸው ጣዕም አልባ ይሆኑብኛል። ስለዚህ ዜማ የሚወደደው ከግጥሙ ተጣምሮ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ያጠጋጋኛል።
ሙዚቃ በጥቅሉ ባይኖር ኖሮ ዓለማችን የተለየ ማኅበራዊ ገጽታ ይኖራት ነበር ብዬ አምናለሁ። ገጽታው ምን ዓይነት ሊሆን እንደሚችል አልገምትም፤ እኔ ግን የምወደው ዓይነት የሚሆን አይመስለኝም።
ትዝታ ግን አሁንም ይለያል። ትዝታን የኢትዮጵያውያን typical መለያ አድርጌ እወስደው ነበር። ያለፈ ነገር እንወዳለን። ዛሬ የፈለገ ቢሻል እንኳ “የዛሬን አያርገውና…” ማለታችን አይቀርም፤ “ድሮ ቀረ” ከአፋችን አይጠፋም። ከዛሬ ይልቅ የድሮው ትዝታ ይመስጠናል፣ ልጆቻችንን ዘመናዊ ዥዋዥዌ እያጫወትን የራሳችን የአፈር ሸርተቴ ይናፍቀናል። ተረስቶ እንዲቀር አንፈልግም። የትዝታ ዜማ ነገር ግን አሁንም ይለያል። ሌሎቹ ዓለማት ባይኖራቸው እንጂ ቢኖራቸው ኖሮ እንደሚወዱት አያጠራጥርም። በተለይ ጎልማሳ ለሆነ ሰው፣ ትዝታ ፍቱን መድኃኒት ነው። እንደኛ ሕመሞቹን ያለ ምንም ሥነልቦናዊ ዕርዳታ ለሚያክም ሰው፣ የትዝታ ዜማ ከሙድ አራቂነትም በላይ ነው። ለዚህም ነው የትዝታ ንጉሡ ማሕሙድ ‘መዝገበ ቃላቱ ትዝታ ባይኖር ኖሮ የፍቅር ዕድሜው ያጥር ነበር’ ያለን በዜማው።
በቃ የብዙአየሁ ዜማ ማለት ከላይ የቀባጠርኩትን ሁሉ የሚያስቀባጥር ነው።
‹ጠላፊው› vs. ‹አጋቹ› – ኢትዮጵያ vs. ስዊዘርላንድ
ዛሬ በጠዋቱ ዜናው በሙሉ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ሲጓዝ የነበረን 202 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ‘መጠለፍ’ ጉዳይ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ‹ጠላፊው ካርቱም ላይ የተሳፈረ ሰው ይመስላል› ቢሉም በመጨረሻ አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ከነጭራሹ እንዳላረፈና ጠላፊውም ረዳት ፓይለቱ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ረዳት ፓይለቱ ለምን ይሄን ተግባር እንደፈፀመ ሲጠየቅም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ስጋት ላይ እንደጣለው በመግለፅ፤ ሲዊዘርላንድ ጥገኝነት እንድትሰጠው ጠይቋል፡፡
ይህ ከሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንደገለፀው ግን ጉዳዩ ጠለፋ (Hijacking) ሳይሁን እገታ ( Hostage Taking) ነው ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ረዳት ፓይለቱ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንዳይሰጥ ስዊዝን ተማፅኗል፡፡ ሁለት የህግ ጥያቄዎች አሉ፡
1. ጠለፋ ወይስ እገታ?
2. በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን (Legal Jurisdiction) ያለው አካል ማነው? ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?
እነዚህን ጉዳዮች የሚፈቱልን ሁለት አለማቀፍ ሕጎች አሉ (ኢትዮጵያም ስዊዘርላንድም የሁለትም የሕጎቹ ፈራሚ ሀገራት ናቸው)፡፡
1. Convention for the Suppression of Unlawful Seizure of Aircraft – Hijacking Convention on Hijacking – 1970 &,
2. International Convention Against the Taking of Hostages – Convention on Hostage taking – 1983.
በነዚህ ሁለት ሕጎች መሰረትም የረዳት ፓይለቱን ሁኔታ (Situation ) እንይ፡፡
1ኛ. ጠለፋ ወይስ እገታ?
ከላይ በመጀመሪያ የጠቀስነው የHijacking Convention ‘ጠለፋ’ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይፈታዋል:
Any person who on board an aircraft in flight:
unlawfully, by force or threat thereof, or by any other form of intimidation, seizes, or exercises control of, that aircraft, or attempts to perform any such act, or is an accomplice of a person who performs or attempts to perform any such act commits an offence [of Hijacking].
በሌላ በኩል ከላይ በሁለተኝነት የጠቀስነው የHostage taking convention ‘እገታ’ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይተረጉመዋል፡
Any person who seizes or detains and threatens to kill, to injure or to continue to detain another person in order to compel a third party, namely, a State, an international intergovernmental organization, a natural or juridical person, or a group of persons, to do or abstain from doing any act as an explicit or implicit condition for the release of the hostage commits the offence of hostage-taking.
የኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት ተግባርም ጥገኝነት ለማግኝት ያደረገው ማስገደጃ መሳሪያ በመሆኑ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንዳለው ተግባሩ ለእገታ የቀረበ ሲሆን፤ ተጠያቂነቱም ከእገታ ጋር በተያያዘ ይሆናል ማለት ነው፡፡
2ኛ. ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?
ጉዳዩ ‘እገታ’ ነው ካልን በጉዳዩ ላይ ተገቢ የሆነው ሕግ አለማቀፉ የፀረ እገታ ሰምምነት (Hostage taking convention) ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም መሰረት በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው የየትኛው ሀገር መንግስት ነው? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው፡፡
ሕጉን ጠቅሰን ብናልፍ ይሻላል፡፡ ዓለማቀፉ የHostage taking convention በአንቀፅ አራት ላይ እንዲህ ይደነግጋል፡
State shall take such measures as may be necessary to establish its jurisdiction over the offence and any other act of violence against passengers or crew committed by the alleged offender in connection with the offence, in the following cases:
A. when the offence is committed on board an aircraft registered in that State (በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ስልጣን ይኖራታል);
B. when the aircraft on board which the offence is committed lands in its territory with the alleged offender still on board (በዚህ መሰረት ደግሞ ስዊዘርላንድ ስልጣን ይኖራታል ማለት ነው).
ስለዚህም በጉዳዩ ላይ የሁለት ሀገሮች የዳኝነት ስልጣን ያለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ ባለቤት በመሆኗ፣ ስዊዘርላንድ ደግሞ አውሮፕላኑ በግዛቷ በማረፉ ስልጣን አላት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ማን ቀዳሚ ስልጣን ይኖረዋል? የሚለው የሚወሰነው ተጠርጣሪውን (በአሁኑ ጉዳይ ረዳት ፓይለቱ) በቁጥጥር ስር ቀድሞ በማዋል የሚወሰን ሲሆን በአሁኑ ጉዳይ ላይ የዳኝነት ስልጣኑ የስዊዘርላንድ ነው ማለት ነው፡፡
መውጫ፡
ኢትዮጵያ ተጠርጣሪው ተላልፎ እንዲሰጣት (Extradition) በፀረ እገታ ሰምምነቱ አንቀፅ 7ና 8 መሰረት መብት ቢኖራትም ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ የአሳልፎ የመስጠት ስምምነት (Extradition agreement) ስለሌላቸው (እኔ እስከማውቀው ድረስ) ተላልፎ የመሰጠት ጉዳዩ ብዙም አድል የለውም፡፡ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤትም ከአሁኑ ክስ ለመመስረት ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነ መልለጫ ሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም:
ረዳት ፓይለቱ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኝ በስዊዘርላንድ የወንጀል ሕግ SR 311.0 አንቀፅ 185 መሰረት ከ3 ዓመት እስከ 20 ዓመት (እንደ ነገሩ ሁኔታ) የሚደርስ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ‘ድንገት’ ተላልፎ ለኢትዮጵያ ቢሰጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 507/1 መሰረት ከ15 አስከ 20 ዓመታት እስር ይጠብቀዋል ማለት ነው፡፡
Is Ethiopianism Re-examined or Replaced by Ethnopianism?
‘Ethiopiawinet’ is an Amharic term equivalent to ‘Ethiopianism’. But, the context it is recently being discussed in social media is very different from it has been used in English and historical scripts. The old Ethiopianism (as written in the scripts) is more theological thought than political, and pan-Africanist concept than Ethiopian nationalist. The debate now ranges from denying the existence of it (as a self-standing identity) to worshiping it (as the only thought to save Ethiopian unity). The former is mainly opinion of ethno-nationalists who have concerns that the term might be used as pseudo-Abyssinian. They think the so-called ‘Ethiopianism’ is not inclusive of all but is just an identity built on the cultures and religion of Ethiopian highlanders. I am guessing the debate ends with a new definition of what Ethiopianism is (should be). It seems Ethno-nationalism (which I would like to call Ethnopianism) is its biggest challenge.
Encyclopedia Britannica described Ethiopianism as “religious movement among sub-Saharan Africans that embodied the earliest stirrings toward religious and political freedom in the modern colonial period. The movement was initiated in the 1880s when South African mission workers began forming independent all-African churches, such as the Tembu tribal church (1884) and the Church of Africa (1889). An ex-Wesleyan minister, Mangena Mokone, was the first to use the term when he founded the Ethiopian Church (1892). Among the main causes of the movement were the frustrations felt by Africans who were denied advancement in the hierarchy of the mission churches and racial discontent encouraged by the colour bar. Other contributing factors were the desire for a more African and relevant Christianity, for the restoration of tribal life, and for political and cultural autonomy expressed in the slogan “Africa for the Africans” and also in the word Ethiopianism.
“The mystique of the term Ethiopianism derived from its occurrence in the Bible (where Ethiopia is also referred to as Kush, or Cush) and was enhanced when the ancient independent Christian kingdom of Ethiopia defeated the Italians at Adwa in 1896.”
It was Garvey who first demanded ‘Africa for Africans’. A Study of Ethiopianism in Rastafarianism with a Focus on the Concept Of Ethiopia as Zion (by Jennifer Skowera) stated that ‘the man most responsible for bringing the ideals of Ethiopianism to Jamaica is Marcus Garvey. Barrett describes the man as “. . . the prophet of African redemption . . . [and through him] the spirit of Ethiopianism came into full blossom” (77).’
The term was first coined in a desperate attempt of strengthening Africans and black people who were under colonization and slavery around the world. It is a huge ideal which conceived free and united Africa. That dream was big and isn’t fulfilled yet.
Every sane African loves the idea of United Africa and even most pragmatic politicians want to come to it through regional integration of the east, of the west, of the north, of the south and of the center. As compared to this dream, it is difficult to grasp that how African countries are splitting into many for little differences. In east Africa alone, the number of countries is doubled within two decades.
These things happen because immature but accidentally influential politicians misunderstand systematic-inequality as inability to co-exist. In the process of states making and independence, some people were disproportionately favored. However this doesn’t mean that [due to historical injustices,] the favored and disfavored ones can’t exist together, many a self-claimed freedom fighters come and plant hate among people. In this way, the dream of African Union walks two steps away as Africans walk to have it a step.
The case in Ethiopia isn’t different. Ethiopia is a small Africa where state fails to bond its people beyond tribal differences.
Discussions on Ethiopianism (as in unity and pride) give more sense to other Africans than us. That’s why we need to stop and realize that unity is not the enemy of equality. Unity isn’t becoming one but untied for better. Perhaps, it is because we aren’t united that dictatorship isn’t gone.
የፖለቲከኞቻችን ሰው ፊት አቀራረብ (Presentability)
ፖለቲካ ጥበብ ነው፤ አንዳንዶች ‘የማመቻመች ጥበብ’፣ አንዳንዶች ‘የማጭበርበር ጥበብ’፣ ሌሎች ‘art of possible’ ይሉታል። አንዳንዴ እውነተኛ የሕዝብ ተቆርቋሪዎች እያሉ አስመሳዮች ያሸንፋሉ፤ ሐሳብ አፍላቂዎቹ እያሉ ሰራቂዎቹ ይመሰገናሉ። ሌሎች ፖለቲካ ጫወታ (game) ነው ይሉታል። ለብዙዎች የጨቀየ ጫወታ ነው፤ ለጥቂቶች ግን ጥበብም ጫወታም ነው። ተጫዋቾቹ ደግሞ በጨዋታው ሕግ (rule of the game) መሠረት መጫወት አለባቸው።
በእኛ አገር ‘ፖለቲካ’ እና ‘ፖለቲከኝነት’ ዛሬም አፍላ ነው። እስከዛሬ ጉልቤው ገዢ ነው፣ ገዢው ወሳኝ ነው። ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ጥበብ የሚጠይቅ የፖለቲካ ፉክቻ የለም። በአገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕድሜ 40 አይሞላም። በጠብ መንጃ ተነድቶ ሥልጣን ላይ የወጣ እንጂ በፖለቲካ ፉክክር ተንጓሎ የወጣ ፓርቲ የለም።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃዋሚ እና ገዢ ተብለው ፉክክር ውስጥ የገቡት በኢሕአዴግ ዘመን ነው። ሆኖም ከምርጫ 97 በኋላ ኢሕአዴግ በዴሞክራሲ ጉዳይ ላይ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረጉ ፓርቲዎች ትግሉን ከዜሮ እንዲጀምሩ አስገድዷቸዋል፤ ያውም በጠበበ ምኅዳር።
ከምርጫ 97 ወዲህ በተደረጉ የፖለቲካ ሽኩቻዎች ውስጥ ኢሕአዴግ በዝረራ ያሸነፈባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። ለዚህ መንስኤው ከኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊ ንፉግነት ባሻገር የተቃዋሚዎቹም ድክመት ተጠቃሽ ነው። ተቃዋሚዎች ፕሮግራሞቻቸውን በማስተዋወቅ እና ደጋፊ በማበርከት ረገድ ጉልህ ችግር አለባቸው። ሕዝቡ ተቃዋሚ መሆናቸውን አውቆ እንዲሁ እንዲመርጣቸው ይፈልጋሉ እንጂ የሚመርጥበትን ምክንያት ሊያስረዱት አይከጅሉም። ስለተቃዋሚዎች ድክመት ብዙ ተብሏል፤ እኔም አሁን አንዱን ነቅሼ ላወራ ነው – ሰው ፊት አቀራረብ (presentability)።
የተቃዋሚ አመራሮች ለፖለቲካ ክርክር፣ ለጋዜጣዊ መግለጫ ወይም ለቃለ ምልልስ ሕዝብ/ካሜራ ፊት ሲቀርቡ የሚኖራቸው አለባበስ፣ ንቃተ-ፊት እና አነጋገር ዝርክርክነት ሰዎች “ሲሪዬስሊ” እንዳይወስዷቸው ከሚያደርጉ እንቅፋቶች አንዱ ነው። እዚህጋ ሁለት ትችቶች ሊነሱ ይችላሉ፤ አንደኛው ‘ፖለቲከኞች ማስመሰል አለባቸው ወይ?’ የሚለው ነው። የጫወታው ሕግ የሚጠይቅ ከሆነ አዎ! ሰዎች መጀመሪያ በሚያዩት ነገር ተማርከው ጆሮ ይሰጣሉ፣ አነጋገሩን አድምጠው ነገሩን ያጤናሉ። የመጀመሪያውን ፈተና ያላለፈ ቀጣዩን የመደመጥ ዕድል አያገኝም፣ ያንን ዕድል ያገኘ አነጋገሩን ካላሳመረ ነገሩን ገዢ አያገኝም። ሦስተኛው ደረጃ ላይ ያለው የመጨረሻው እና ወሳኙ ፈተና ነው።
‘የለም፤ ይህንን መጽሐፉን በሽፋኑ የሚዳኙትንም ጭምር መታገል አለብኝ’ የሚል ፖለቲከኛ፣ ፖለቲከኛ ሳይሆን አራማጅ (ለውጥ አማጭ) ነው መሆን የሚችለው።
ሮብ ያንግ የተባለ “Power Dressing” የተሰኘ መጽሐፍ ደራሲ ከፎርብስ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ፖለቲካን በሚያህል የአገር ዕጣ ፈንታ በሚወሰንበት ጉዳይ ስለአለባበስ ማውራት ብዙ ሰዎችን ያሳፍራቸዋል፣ ግን አማራጭ የለም ብሏል። “Politics wants to present itself as a serious institution about substantive issues, rather than a popularity contest based on what the contenders look like. But the fact is that fashion… can be mighty powerful political currency.”
አንዱና ትልቁ ችግር ፖለቲከኞች ራሳቸውንና ሕዝቡን ከአለባበሱ እና አቀራረቡ አልፈው ለመመልከት ቢሞክሩም ሕዝቡ የእነሱን አለባበስና አቀራረብ አስቀድሞ መገምገሙን አለማቆሙ ነው። ስለዚህ በጥቃቅን የአቀራረብ (presentability) ሳቢያ ትልቁ ቁምነገር ሰሚ ከሚያጣ፣ ትንሽ ዋጋ መክፈል ያዋጣል።
የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በተለይ ተቃዋሚዎች ይህንን ጉዳይ በቅጡ ያጤኑት አይመስልም። አቶ ይልቃል (ኢ/ር) ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው የሰጧቸው ቃለምልልሶች ላይ የወጡ ፎቶዎቻቸው በሙሉ ጉስቁልቁል ያሉና ኮታቸው ተዛንፎ ወይም ከትከሻቸው የሰፋ መስሎ ነው። ዛሬ (የካቲት 6/2006) መግለጫ ሲሰጡ ያየኋቸው የሁለት ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ጠረጴዛው ኋላ ሳያቸው ለአቀራረባቸው እንዳልተጨነቁ ያሳብቅባቸዋል። አለባበሳቸው የአዘቦት ዓይነት ነው፤ ‘ፎርማል’ በሚባል ሁኔታ እንኳን አልለበሱም። አንዱ ሲናገር ሌለኞቹ አንዱ አገጩን ተደግፎ፣ ሌላኛው በዚህንኛው ንግግር ያልተደሰት በሚመስል አኩርፎ፣ አንደኛውም ጉስቁል ባለ መልኩ ተቀምጠው ያደምጡታል። በኔ እምነት፣ አንዱ ሲናገር ሌላኛው በተቻለ መጠን የፊት ገጽታውን ሳያዘባርቅ፣ ቀጥ ብሎ ቢቀመጥ ሌላው ቢቀር የታዳሚዎችን ሐሳብ ከተናጋሪው አይሰርቅም።
ሌላው ጉዳይ የንግግር ዘዬ ጉዳይ ነው። በፖለቲካ አምባ፣ አንደበተ ርቱዕነት ወሳኝ ቁም ነገር ነው። እነ ልደቱ አያሌው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሀብታሙ አያሌው የዚህ አንደበተ ርቱዕነት ማሳያ ናቸው። ይህ የሚያውቁትን አሳምሮ፣ የማያውቁትን አድበስብሶ የማሳለፊያ ጥበብ ለፖለቲከኞች ቁልፍ በመሆኑ ሌላው ዓለም ሥልጠና ሳይቀር ይወስዱበታል። የመጨባበጥ ሒደት፣ የእንግዶች /ካሜራ/ ፊት እንቅስቃሴ፣ የእጅ ውዝዋዜ ሳይቀሩ ይጠናሉ። ግለሰቦችን በአንቱታ እና ትክክለኛ ማዕረጋቸውን ሳያዛንፉ መጥራትም ራሱን የቻለ በልምምድ የሚገኝ ጥበብ ይጠይቃል፤ ትርፍም አለው።
የእኛ ፖለቲከኞች ለዚህ ቁብ አይሰጡትም። መወዳደሪያ እሴት ነው ብለው የሚያስቡም አይመስሉም። በመንግሥት በጀት ፕሮቶኮል የሚቀጠርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሳይቀሩ በኔልሰን ማንዴላ ቀብር ላይ ከሰው ሁሉ የተለየ አለባበስ ለብሰው የታዩት፣ እዚህ ግባ የማይባል ንግግር ያደረጉት በዚሁ ሳቢያ ነው። አነዚህ የአቀራረብ ቅንብሮች ተደማምረው ነው አንድን መሪ ሞገስ ያለው (charismatic) ነው፣ አይደለም የሚያስብሉት። ሰዎቹ፣ ብንወዳቸውም ብንጠላቸው አገራችንን ወክለው ሲቀርቡ ሞገስ ቢኖራቸው መልካም ነው።
በጥቅሉ ሲታይ ግን ተቃዋሚዎች ከገዢው አንፃር የመሪ-ሞገስ አልባ ናቸው ማለት ይቻላል። ገፅታ አይቶ በሚዳኝ ሕዝብ ውስጥ እየኖሮ ለአቀራረብ አለመንጠንቀቅ ዋጋ ያስከፍላል። ያንን ዋጋ ደግሞ ተቃዋሚዎች አይችሉትም።
ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ልማታዊ አራማጅነት
ምስራቃውያን “ልማታዊ መንግሥታት ናቸው” የተባሉት በምዕራባውያን ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ራሱ ነው “ልማታዊ” በማለት ራሱን መጥራት የጀመረው። ከዚያ በኋላ ቃሉ፣ በመንግሥት ኃላፊዎችና በተለይም በኢቴቪ በተደጋጋሚ ከመነሳቱና ካለቦታው ከመደንጎሩ የተነሳ የሚወክለው መንግሥት የሚከተለውን የኢኮኖሚ ስርዓት መሆኑ ቀርቶ በቀላሉ ሲታይ “የሚጠፉ ጥፋቶችን እንዳላየ አልፎ፥ ስለሚለሙ ልማቶች ብቻ ማውራትን”፣ ወይም በጥልቁ ሲመረመር “ገዢው ፓርቲን ከነቆሻሻው መደገፍን” ይመለከታል። ራስን ማዕረግ የመስጠት ጦሱ ይኸው ነው።
ኢሕአዴግ ደጋፊዎቹን ወጣቶች “የልማት ሠራዊት” ነው የሚላቸው፤ ቀሪው እንደጥፋት ሠራዊት ነው የሚቆጠረው። ሌላው ቢቀር ሁለቱንም አለመሆን አይፈቀድለትም። ኢሕአዴግ ራሱን ብቻ ልማታዊ አድርጎ የመቁጠሩ ነገር በስህተት የመጣ አይደለም፤ የፖለቲካ ፍልስፍና ጉዳይ ነው። በተለይ ሰሞኑን ፓርቲው በመንግሥትነት ስሙ ተጠቅሞ በሚያዘጋጃቸው ስብሰባዎች ላይ የታይዋን እና ደቡብ ኮርያ ስም ተደጋግሞ በምሳሌነት ይጠቀሳል፤ ሁለቱም “ለልማት ሲባል ዴሞክራሲን ሰውተው ነው እዚህ የደረሱት” በሚል። ልማታዊነት ለዴሞክራሲ አያጣድፍም እንደማለት።
ክፋቱ ኢሕአዴግ እምነቱን በፀባይ ለማሳመን አለመፈለጉንም ይጨምራል። እንዲህ እያለ እያወራም ግን ‘ዴሞክራሲያዊ ነኝ፣ ያለመሆን ፍላጎትም የለኝ’ እያለ በአደባባይ እየዋሸ ያታልላል። ግን መልሶ፣ “ሁሉም ነገር ወደልማታዊነት ግንባር” ይላል – በራሱ የልማታዊነት ብያኔ። የለም፣ እኔ በራሴ ብያኔ እሠራለሁ ብሎ ነገር የለም። ለምሳሌ፤
ልማታዊ ተቃዋሚዎች
ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች “ልማታዊ” እንዲሆኑ ይፈልጋል። “ልማታዊ ተቃዋሚዎች” ማለት የሁለት አሐዙ ዕድገትን ያለመጠየቅ የሚያምኑ፣ ስለፖለቲካው ምኅዳር መጥበብ ትንፍሽ የማይሉ እና ሌላው ቀርቶ በምርጫ ሲሸነፉ በኢቴቪ ቀርበው ይህ እንደሚሆን ቀድመውም ያውቁ እንደነበር የሚመሰክሩና የተሸነፉት በራሳቸው ድክመት መሆኑን የሚናገሩ… ናቸው። የሚወዳደሩት ውድድሩን ለማድመቅ ነው -ልክ እንደታላቁ ሩጫ ብዙኃን። ምሳሌ የአቶ መሳፍንት መኢብንን እና የአቶ አየለ ጫሚሶን ቅንጅትን መጥቀስ ይቻላል። በአጭሩ እነዚህ ፓርቲዎች፣ ተቃዋሚም፣ አማራጭ ፓርቲም አይደሉም፤ ደጋፊ ፓርቲዎች ናቸው።
“ደጋፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች” (AKA ልማታዊ ፓርቲዎች) ዋነኛ ሥራ ራስን ተቃዋሚ ነን ብሎ ለሕዝብ መንገር፣ በገዢው ፓርቲ የተከፋውን ሕዝብ ልብና ቀልብ ማግኘት፣ ቀልቡን ለሰጠው ሕዝብ ፓርቲዎቹ ስለሚታገሉለት ሳይሆን ኢሕአዴግ ስለሚሠራቸው ሥራዎች ማውራት፣ ለኢሕአዴግ ድምፅ ማስገኘት ካልተቻለ “ልማታዊ ካልሆኑት ፓርቲዎች” ድምፅ መቀማት/መከፋፈል ናቸው።
ገዢው ፓርቲ እነሱን በማበርከት የአጥቂነት ሚናውን እየተወጣ ነው። እነሱ ደግሞ የማያገኙት የሥልጣን ጥማቸው የኢሕአዴግ ጉዳይ አስፈፃሚ አድርጓቸዋል።
ከኢሕአዴግ መሥመር በማይጋጠም አቅጣጫ የሚሄዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ሕልውናቸውን አደጋ ላይ በሚጥል ቀጭን ሽቦ ላይ እንዲራመዱ ይደረጋሉ።
ልማታዊ ጋዜጠኝነት
ልማታዊ ጋዜጠኝነትም በገዢው ብያኔ መሠረት የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ እርምጃዎችን አዎንታዊ ፋይዳን ብቻ ማውራት ነው። ለምሳሌ ከጣሊያን ብድር ለማግኘት ተብሎ ለሳሊኒ ያለጨረታ ፕሮጀክት መሰጠቱ ምን ያክል ገንዘብ ድሀዪቱን አገር ያከስራታል የሚለውን ማውራት ልማታዊ አይደለም። ፕሮጀክቱ መጀመሩ፣ ሲጠናቀቅ የሚኖረውን ፋይዳ ማውራት ግን ልማታዊ ነው።
በኢትዮጵያ 35 በመቶ የመረጃ ጥያቄዎች በሕዝብ ግንኙነት አባሎች ይጨናገፋሉ የሚለው ልማታዊ አይደለም፣ 65 በመቶ የሚሆኑ የመረጃ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ የሚለው ግን ልማታዊ ነው። የሁለቱ ዜናዎች ልዩነት የትኩረት አቅጣጫቸው ነው። የመጀመሪያው ሊስተካክል የሚገባውን ሲያወራ፣ ሁለተኛው የተሳካውን ያወራል። ሁለቱም ውስጥ ተቃራኒው ቢኖርም የዜናዎቹ አንባቢዎች ግን እንዲያተኩሩ የተፈለገውን ብቻ የማስተዋል ዕድላቸው ሰፊ ነው። ስለዚህ ልማታዊ ጋዜጠኝነት በተሳሳተ ብያኔው ሙገሳ አዝማሪነት ሆኗል ማለት ነው። እናም፣ ዜናው ላይ የተጠቀሰው ጥናት በመንግሥት ስለተሠራ እንጂ የመረጃ ንፍገቱ ከ35 በመቶ በላይ ነው፤ ለምሳሌ የግል ጋዜጠኞች የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ካልሆነ በቀር መረጃ ጠይቀው የሚሰጣቸው የለም የሚል አስተያየት የሚያስተናግድ ጋዜጠኛ ከመጣ ጭራሹኑ ቦታ የለውም።
ልማታዊ አራማጅነት
አራማጅነት (activism) በባሕሪው ምናባዊ በሆኑ መሠረታውያን ላይ የቆመ የለውጥ እንቅስቃሴ ነው። አንድ አራማጅ ይህ ለውጥ እንዲመጣ እፈልጋለሁ ካለ፣ የሚመጣውን ለውጥ የመጨረሻ ግብ እያለመና ሁሉንም ነገር ከዚያ ግብ (ወይም ለዚያ ግብ ከሚኖረው ፋይዳ) አንፃር እየመዘነ የሚሄድ ነው።
ለምሳሌ እንደኛ ባለ ጠቅላይገነንነት (authoritarianism) ስርዓት ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲመጣ የሚሠራን አራማጅ እንውሰድ። ይህ አራማጅ በነባራዊው ሁኔታ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውጥ እንደማያመጡ ያምናል እንበል። እንዲያውም እነሱ ራሳቸው ሚናቸውን ለመወጣት ለውጥ ይፈልጋሉ፤ ዴሞክራሲ ይፈልጋሉ። ጋዜጠኞችም ሐሳባቸውን ለመግለጽ ነጻነት ይፈልጋሉ፤ እነሱም ዴሞክራሲ ይፈልጋሉ። ስለዚህ አራማጁ የሚያስቀምጠው መለኪያ እነዚህን እውን የሚያደርጉትን መለኪያዎች ነው።
ነገር ግን፣ በኢሕአዴግ የእያንዳንዱ ዜጋ “የልማታዊ” መሆን የውስጠ ታዋቂ መመሪያ መሠረት ገዢውን ማበረታታት እንጂ መተቸት ያስቀስፋል። አራማጁ ስለፖለቲካ ምኅዳር ሲያወራ፣ ገዢው ስለመሠረተ ልማቱ አውራ ይለዋል፤ ስለመሠረተ ልማቱ የአገነባብ ሒደት ሁሉንም በዕኩል አሳታፊነት/ጠቃሚነት ጉዳይ ሲያወራ፣ ስለተገኘው ስኬት አውራ ይባላል። ስለዚህ እንኳን ለሌሎች ዴሞክራሲን በአማጭነት ሊያግዝ የራሱንም ማስጠበቅ ይቸገራል። በዚህ አራማጁን “ልማታዊ” የማድረግ አካሄድ አራማጁ የኢሕአዴግ ሕልም አስፈፃሚ ብቻ ነው መሆን የሚችለው።
አራማጆች በኢትዮጵያ መሠረታዊ መነሻቸውን ሳይስቱ ከቆዩ (“ልማታዊ” አንሆንም ካሉ፥) በገዢው ስያሜ ይሰጣቸዋል። የመጀመሪያው ‘አሸባሪ’ ነው። ‘ፅንፈኞች፣ የኒዮ ሊበራል ተላላኪዎች፣ ፀረ-ልማቶች…” የሚሉትም ይገኙበታል። እነዚህ ስያሜዎች ምናልባትም እራሱን እንደፈጣሪ መልዕክተኛ ለሚቆጥር አራማጅ አስበርጋጊ ናቸው። ስያሜዎቹ፣ ከተራ ውንጀላ ወደ ክስ መዝገብነት ሲቀየሩ የበለጠ ያሸማቅቃሉ።
በመጨረሻም፣ ልማታዊ አራማጆች ይፈጠራሉ። እነርሱም ልማት ስለሚያመጣቸው ነጻነቶች፣ ሕገ መንግሥቱ ስለሰጣቸው መብቶች፣ ባልተለወጠ መንግሥት ስር ዜጎች ራሳቸውን እንዲለውጡ ይተውታሉ። በልማታዊ መንግሥት፣ በልማታዊ ተቃዋሚዎች፣ በልማታዊ ጋዜጠኞች፣ በልማታዊ አራማጆች እና በተሳሳተው የመሸነጋገያ “የልማታዊ” ትርጉም፥ ባለህበት አዝግምi
የሌለውን ልማት መካድ
በዚያ ላይ ደግሞ በቅርቡ የኢኮኖሚስቱ ኢንተሊጀንስ ዩኒት እ.ኤ.አ. በ2014 ፈጣን ዕድገት ያስመዘግባሉ ብሎ ከገመታቸው ዐሥር አገራት ውስጥ ኤርትራ ሳትቀር 8 በመቶ እንደምታድግ (በ9ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ) ኢትዮጵያ ግን ዝርዝሩ ውስጥ መግባት አልቻለችም፡፡ ይህ ማለት የተጀመረው ዕድገትም፣ ልማት ደጃፍ ላይ ሳይደርስ ሊሸረሸር እንደሚችል እና መንግሥት የባለሙያዎቹን ምክር በመስማትና ሕዝባዊ ተሳታፊነትን በማሳደግ ለዘላቂ ልማት የሚያደርስ የኢኮኖሚ ግንባታ መስመር ማስመር እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በኢኮኖሚ ስርዓቱ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን እየቆጠሩ ‹‹ልማት መካድ›› የሚል ባጅ መለጠፍ ‹‹ልማታዊ›› አይደለም፡፡
መታወቂያዬ ላይ “ኢትዮጵያዊ” ተብሎ እንዲጻፍ እፈልጋለሁ
ራስን “ኢትዮጵያዊ” ብሎ መጥራት ነውር እንዲመስል ጠንክረው የሚሠሩ አሉ። አልተሳካላቸውም ብዬ አልዋሽም። ምክንያታቸው እስከዛሬ የነበረው ኢትዮጵያዊነት አማራ ለበስ ነው፤ የዘውግ ብሔርተኝነት አንጂ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት (ማንነት) ብሎ ነገር የለም የሚለው ነው። መነሻ ነጥቡ እውነት ላይ ቆሞ፣ መድረሻው ግን ተራ ድምዳሜ ነው። በዘመን ጥፋት ዘንድሮን መቅጣት! እርግጥ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን ዘውጋቸውን የሚያስቀድሙ ብሔረተኞች ሊሆኑ ይችላሉ። እኔንና መሰሎቼን ግን እነሱ ሸንጎ በሉት ጨፌ ውስጥ አስገድዶ የመክተት ወንጀል ነው። የራስን ማንነት በዘውግ ብሔር መግለጽ መብትም ምርጫም የሆነውን ያክል በኢትዮጵያዊነት መግለጽም ነውር ሊደረግ አይገባውም።
እኔን እንደ ምሳሌ
እኔ ባጋጣሚ ከተውጣጡ ብሔሮች ነው የተወለድኩት። ያደግኩትም ከዚያ በበለጠ አካባቢ በመጡ ቤተሰቦች መሐል ነው። የአብሮ አደግ ጎረቤቶቼ ቤተሰቦች ሙስሊም ጉራጌዎች፣ ወሎዬ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያን የወለጋ ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች… ናቸው። ልጅ እያለን ማን “ምን” እንደሆነ ትዝ ብሎን አያውቅም። ስናድግ ግን ስለዘውግ ማንነቶቻችን እንድንማር ብቻ ሳይሆን አንዱን እንድንመርጥ ተገደድን። (መማሩን ወደን መገደዱን ግን ከመጥላት ሌላ አማራጭ የለንም።)
ሁሉንም በቅጡ አልችላቸውም እንጂ የአማርኛም፣ ኦሮምኛም፣ ሶማልኛም፣ ትግርኛም፣ ጉራግኛም… ዘፈኖች ስሰማ ባለሁበት በስሜት እወዘወዛለሁ፤ በፍቅር የምበላቸው ምግቦች (ኪሴ ሁሌም አይፈቅድልኝም እንጂ) ክትፎ፣ ጨጨብሳ፣ (እና በተውሶ ፒዛ እና በርገር ሳይቀሩ) ናቸው። አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ ሐረርን የጎበኘሁት እና ሌሎችንም ልጎበኝ ቀናት የምቆጥረው የራሴ የሚል ውስጣዊ ስሜት ስላለኝ ነው። ለጉዞ ስወጣ “የእነርሱን ልጎብኝ” አልልም፤ “የአገሬን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ልጎብኝ” ብዬ ነው። ከኢትዮጵያ መውጣት የማልፈልገው እንደኢትዮጵያ የሚመጥነኝ እና የምመጥነው (fit የማደርግበት) ስፍራ እንደሌለኝ ስለማምን ነው። ልዩነታችን ጌጤ ነው። እኔ የሁሉም፣ ሁሉም የኔ ናቸው ብዬ ከልቤ አምናለሁ።
ነገር ግን ለፖለቲካ ግብአት ሲባል ኢትዮጵያዊ ማንነት ብሎ ነገር የለም አንዱን ማንነት ምረጥ ስባል ያመኛል። እንዳጋጣሚ በቤተሰቦቼ ካገኘሁት የዘውግ ማንነቶች ውስጥ የቱን ነው የምመርጠው? ካሳደጉኝ ጎረቤቶቼ የወረስኩትን ማንነትስ ለምን እቀማለሁ? አማራው ማንነቴስ? ኦሮሞው ማንነቴስ? ጉራጌው፣ ትግሬው፣… ማንነቴስ? ከድምር እኔነቴ አንዱን ብቻ መርጬ እኔ እንትን ነኝ አልልም፤ ነጠላ ማንነቶቼን በተናጠል አልወዳቸውም። ከድምሩ አንዱ ሲጎድል ያመኛል። ድምሩ ማንነቴ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት እንደገና ይጤን
በታሪክ ሒደት ተጠቃሚ የነበሩ የዘውግ ማንነቶች አሉ። በተለይ አማርኛ ተናጋሪዎች (አማራዎች) ግምባር ቀደሞቹ ናቸው። ይህን መነሻ ይዘው ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ጋር ቀላቅለው የሚደመድሙ ግን የራሳቸውን ትርጉም ይገምግሙ። የኔ ኢትዮጵያዊነት ግን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካርታ የታቀፉ ማንነቶችን ሁሉ ያቀፈ፣ የሚያስተናግድ እና የሚያከብር ኢትዮጵያዊነት ነው።
ይህ ማለት ግን፣ አንድ ሰው አንድ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ በመሆኑ፣ የሚያውቀው ባሕልም የዚያን ዘውግ ብሔር ብቻ መሆኑ ኢትዮጵያዊ አያደርገውም ማለት አይደለም። ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ነው። ነገር ግን ራሱን በዚያ የዘውግ ብሔር ማንነት ለመግለፅ ከፈለገ መብቱ ነው። የዘውጉ ብሔር ኢትዮጵያዊነት በሕግም (እንበል ከየትኛውም የአፍሪካ አገራት በረዘመ) የታሪክ ዕድሜም የፀደቀ ነው። ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ላንዱ የዘውግ ብሔር የተለየ ውስጠኝነት (belonging) የማይሰማው ሰውም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን መነፈግ የለበትም።
ባለኝ መረጃ፣ መታወቂያ ላይ ብሔር የሚጻፈው አዲስ አበባ ብቻ ነው። እንዳጋጣሚ ደግሞ ከዘውግ ብሔርተኝነት ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን የሚመርጠው የአዲስ አበባ እና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ ነው። አንድ ሰው ቀበሌ ሄዶ “እኔ ኦሮሞም፣ አማራም፣ ሶማሌም… አይደለሁ፤ ብሔር የሚለው ላይ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ይጻፍልኝ” ብሎ ቢሟገት ፖለቲካዊ ወንጀል እንደሠራ ተቆጥሮ ስሙ በጥቁር መዝገብ ይሰፍራል። መታወቂያውን ሊከለከል ወይም ቤተሰብ ካለው የአንዱን በውርስ ተለጥፎ በግድ ሊሰጠው ይችላል። ይህ ጭቆና ነው።
ብዙዎች “ኢትዮጵያዊነት” በሚሉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሁሉ የሚያቀርቡት በፌዴራሊዝሙ እንደተሰነዘረ ጥቃት አስመስለው ነው። እንደዚያ የምር ማመናቸውን ግን እጠራጠራለሁ። እኔ ፌዴራሊዝሙ ላይ ከጥቃቅን ማስተካከያዎች በቀር ችግር የለብኝም። በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር አስፈላጊ ነው ከሚሉትም ወገን ነኝ። ይህ ሁሉ “ኢትዮጵያዊነት” እንዲያብብ እንጂ አንዲጠወልግ አያደርገውም። ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠወልገው የዘውግ ብሔረተኞች የከረረ ጥላቻ እና የተዛባ፣ ያልታረመ የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ነው።
ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ የየትኛውም የዘውግ ብሔር ሙሉ አድርጎ አይገልጸኝም። ስለዚህ መታወቂያዬ ላይ “ኢትዮጵያዊ” ተብሎ ይጻፍልኝ።
“የደወሉላቸውን ደንበኛ ማግኘት አይችሉም”
የኢትዮ-ቴሌኮሟ ቅርፀ-ድምፅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰሞኑን “የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ትላለች። ዛሬ (ጥር 29/2006) ግን ማለዳውን ሙሉ ስልኮች ሁሉ “ዝም፣ ጭጭ” ብለው ነው ያረፈዱት። አዲስ አበባን ከስሪ-ጂ (ሦስተኛው ትውልድ የስልክ በይነመረብ ግንኙነት አቅም) ወደ ፎር-ጂ (አራተኛው ትውልድ አቅም) ለማሳደግ፣ ሌሎቹን ክልሎች ደግሞ ወደ ሦስት ትውልድ ለማሳደግ ሥራዎች እየተጣደፉ እንደሆነ በሚደሰኮርበት በዚህ ሰዓት ኔትዎርኩ እንደ ክሪስማስ ዛፍ ብልጭ ድርግም ይል ገብቷል።
በነገራችን ላይ እኛ 1·1% የኢንተርኔት ፔኔትሬሽን (ተዳራሽነት) ላይ ቁጭ ብለን 28% ደረስኩ ብላ እንቁልልጭ የምትለን ኬንያ፣ በሁሉም ቴሌኮም ድርጅቶቿ የሚቀርቡት የስልክ አገልግሎቶች ከ3ጂ በላይ ናቸው። (Keeping up with the Joneses has become mission impossible).
ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም
ዛሬ የገጠመኝ ደግሞ ለየት ይላል። ሌላ ሰው’ጋ እደውላለሁ ብዬ አብሮኝ ያለው ሰው’ጋ ደወልኩ፤ ቢጠራም አይነሳም። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ስመለከተው የደወልኩት አብሮኝ ያለው ሰው’ጋ ነው። “እንዴ የደወልኩት ላንተ ነው፤ አንተ ደግሞ አይሰማህም እንዴ?” ብዬ ሌላኛው ስልክ ላይ መደወሌን ቀጠልኩ። እሱ ደግሞ ኧረ እኔ’ጋ አልደወልክም ብሎ ስልኩን ሲያሳየኝ እኔ ከሌላኛው ሰው’ጋ ማውራት ጀምሬ ነበር። ከዚያ አብሮኝ ያለው ሰው የስልኩን ስክሪን ዓይኔ ላይ አምጥቶ ደቀነው። “befeqe is calling…” ይላል። “ኧረ እኔ ከሌላ ሰው’ጋ እያወራሁ ነው!” አብሮኝ ያለው ሰው ስልኩን ሊያነሳ ሲሞክር እምቢ አለው። ሁኔታውን ‘ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም’ ብለነዋል።
ስልኮቹ በተመሳሳይ ሰዓት ካልተገናኙ (synchronized ካልሆኑ) ማውራት አይቻልም። እንዲህ ዓይነቱ መቀዣበር የሚፈጠረው ስልኮች ሲጠለፉ ነው። ኢትዮቴሌኮም (ወይም ወዳጆቹ) ስልኬን አይጠልፉም ብዬ ባልጠረጥርም የሁሉንም ሰው ስልክ ይጠልፋሉ ብሎ መጠርጠር ይከብደኛል። ፍላጎቱ ቢኖራቸውም አቅም ያንሳቸዋል። የኔትዎርኩ ችግር ደግሞ ባገር የመጣ ነው።
ጠለፋና ማስፋፋት
ሑዋዌይ በአሜሪካ የደኅንነት ቢሮ የጠለፋ ሶፍትዌሮችን እና ሀርድዌሮችን ይጠቀማል በሚል ከገበያ አግዶታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ከዜድቲኢ ጋር አብሮ የሚሠራው የቢሊዮን ዶላር የኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሸልሞታል። ለኛ መንግሥት መሪዎች የአሜሪካው ዜና የምስራች ነው። እንዲያውም ሳስበው ዶ/ር ደብረፅዮን የሑዋዌይን ኃላፊ “እስኪ የሚወራባችሁን ነገር እኛ ላይ ተግብሯትና ይህን ሕዝብ ሲያወራ እንስማው” የሚሉት ይመስለኛል።
ግሎባል ኢንተርኔት ሴኩሪቲ በሪፖርቱ እንደነገረን ተንቀሳቃሽ ስልኮች በኢትዮጵያ ከ3% (እ.ኤ.አ. በ2008) ወደ 18% በ2012 ተዳርሷል። እድገቱ ሸጋ ነው፤ ከጎረቤቶቻችን አንፃር ካላየነው ማለቴ ነው። ከነዚህ ወስጥም ኢንተርኔት የሚሠሩት ስልኮች 6·2% ብቻዎቹ ናቸው።
እንደ ትራንስፎርሜሽን እና ዕድገቱ ዕቅዱ ከሆነ ግን 40 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተንቀሳቃሽ ይኖራቸዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን እንደነገሩን ደግሞ ሌሎች 16 ሚሊዮን የሚደርሱ 3 እና 4ጂ የሚሠሩ ስልኮች ሲጨመሩ 56 እናዳርሳቸዋለን ተብሏል። ማስፋፊያው ሲጨረስ 85% ሕዝቡን የሚያዳርስ የተንቀሳቃሽ ስልክ እናቀርባለን ተብሎ ታቅዷል። ‘See Separate’ የተባለ ድርጅት ግን በ2015 እ.ኤ.አ. ቁጥሩ 99·6 ሚሊዮን ይደርሳል ከተባለው ሕዝባችን ውስጥ 34·2 ሚሊዮን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚኖሩ (ከዕቅዱ’ጋ ሲነፃፀር 22 ሚሊዮን ያነሰ እንደሚሆን) በሒደቱ (projection) ገምቷል።
የታቀደው ግብ ቢመ’ታ መልካም ነበር። ግን ከታቀደው በታች ተፈፅሞም፣ ጥራቱ ተጓድሎም እንዴት ይሆናል? እስከዛሬ በሁሉም ዘርፎች ላይ የዘገየንባቸው ነገሮች ላይ ከሚሰጡ እልፍ ሰበቦች ውስጥ ‘በተዳራሽነት ብዛት ላይ ስናተኩር ጥራት አመለጠን’ የሚለው ይገኝበታል። ሁለቱም ላይ ካላተኮርን ሌላ ምን ላይ አተኩረናል ሊባል ነው?
ከሁሉም ግን ስጋቴ የደወሉላቸውን ደንበኛ ማግኘት፣ በፈለጉት ጊዜ የማይችሉ 56 ሚሊዮን የስልክ ደምበኞች እንዳናፈራ እሰጋለሁ።
ተቋማዊ አምባገነን
አምባገነን መንግሥታት ሁሉ አንድ አይደሉም:: አንዳንዶች ፍጹም አውቶክራቲክ የሆነ አስተዳደር ሲኖራቸው ሌሎቹ ደግሞ ‘ዴሞክራቲክ’ የሚመስሉ ተቋማትን በመመስረት አምባገነንነት በመንግሥታዊ አስተዳደሩ ብቻ ሳይወሰን ተቋማዊ (Institutionalized dictatorship) ይዘት እንዲኖረው ያደርጋሉ:: በእነዚህ ተቋማት ውስጥ አምባገነኖች በሥራ ላይ የሚያውሏቸው ሁለት ዋና ዋና መሣሪያዎች አሏቸው፦ ጥቅማጥቅሞችን (ኪራይ) ማካፈል እና የጥቅም ተጋሪዎች ለሆኑት ሰዎች ጊዜያዊ የፖሊሲ ማስተካከያ (Policy concession) እና የአሰራር ሂድት ለውጥ በማድረግ ጥቅማቸውን ማስከበር ናቸው:: እነዚህም በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚ እና በመሳሰሉት ተቋማት ሲንጸባረቁ ይታያሉ:: አምባገነኖች እነዚህን ተቋዋማዊ አደረጃጀቶች የሚጠቀሙት ታቃዋሚን እና ተቃውሞን በስልታዊ መንገድ ለማርገብ ሲሆን ሂደቱ እንደ ተቃዋሚው ጥንካሬ ይወሰናል:: ለምሳሌ ተቃዋሚው ድካማ ከሆነ አምባገነኑ ጥቅሞችን በስፋት የማጋራት ግዴታ ስለሌበት ፖሊሲዎችን እና የውስጥ አስራሮችን ብቻ በመጠቀም ሥርዓቱን ያጠናክራል:: በተቃራኒው ተቃዋሚው ጠንካራ ከሆነ ደግሞ ጥቅማጥቅሞችን በማብዛትና ፖሊሲዎች ላይ ጊዜያዊ ለውጥ በማድረግ ተቃዋሚው እንዳያምጽ በሩን ይዘጋል (assurance for non-rebellion opposition):: ተቃዋሚው ደግሞ በጣም ጠንካራ ከሆነና የአምባገነኑን መንግስት ለመጣል የሚያበቃ ኃይል እና እድል እንዳለው የሚያረጋግጥ መረጃ ካለ ስርዓቱ ከጥቅማጥቅሞችን እና ከጊዜያዊ የፖሊሲ ለውጦች በተጨማሪ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ያቀርባል:: አምባገነን መንግሥት ተቃውሟቸውን በይፋ የሚገልጡ እና ጠንካራ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚላቸው ላይ ትኩረት መስጠትና ጫና ማድረግ ይመርጣል:: ጫናውን በቀጥታም ሆነ በተዛዋዋሪ መንገድ ያድረገዋል :: ዋነኛው መንገድ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች በራሱ ቁጥጥር ውስጥ ካሉ ተቋማት በተለያየ መንገድ (systematically፟) ማስወገድ እና ከደረጃ ዝቅ ማድረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ መወንጀል ፣ ማሰር ፣ማስፈራራት እና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ ነው:: የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ለምሳሌ ያህል፦
በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የሥራ እድል መስጠት ፣ በሥራ መደቡ ላይ ላሉ ደግሞ እድገት፣ የተሻለ ደሞዝ፣ የስልጠና እድል ማግኘት እንዲሁም የተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች መስጠት:: የግል ሥራ ለሚሰሩ የተፋጠነ እና ለሌላው የማይሰጥ የብድር አገልግሎት የሥራ ፈቃድና በአጠቃላይ ለሥራው ሂድት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በሟሟላት ሁኔታዎችን ማመቻቸት:: በትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚያልፉት፣ በሚፈልጉት የትምህርት ተቋም እንዲቀጥሉ፤ ከትምህርቱ ጋር የተያያዘ ክፍያ መሰረዝ (በከፊል እንዲከፍሉ ማድረግ) ለተጨማሪ የትምህርት የተመቻቸ እድል መስጠት:: ይህንን አንፈልግም ብለው እራቸው ከስራዓቱ ጥገኝነት ለመለየት ቢሞክሩም መኖርም መስራትም አስቸጋሪ ስለሚሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት ጥገኛ የመሆናቸው እድል ሰፊ ነው::
የሥርዓቱ የሙሉ ጊዜ ተጠቃሚዎች የዕለት ከዕለት ኑሯቸው በስርዓቱ ህልውና የሚወሰን ስለሚሆን በስርዓቱ ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ለማንሳት አይፈልጉም:: ቢፈልጉም አይችሉም። ምክኒያቱም እነሱ አብዛኛው ነገር የተሟላላቸው ስለሆኑ የሚያሳስባቸው ነገር መጠነኛ ስለሆነ በአደባባይ ከመናገር በማልጎምጎም መጨረስን ይመርጣሉ:: ቅሬታ አለን ብለው ማሰማት የሚፈልጉም ቢኖሩ ችግሩ አሳስቧቸው ሳይሆን የአምባገነኑ ስርዓት ለተቃዋሚ ድምጽ እድል ይሰጣል ለማሰኘት ብሎም ለዚህ ተግባራቸው እንዲመሰገኑበት ብቻ ነው:: ሌላው እና ዋነኛው የስራቱ ተጠቃሚዎች መገለጫ ስርዓቱን እና ተቃዋሚን በአንድ ሚዛን በመመዘን ተቃዋሚውን ጥፋተኛ በማድረግ በተደጋጋሚ ጥላሽት በመቀባት ማጥላላት ነው::
በመጨረሻም ባገኙት አጋጣሚ ተዋስዖ ትኩረት በማስቀየር ሰዎችን ሰለአምባገነኡ ሥርዓት ትኩረት እንዳይሰጡ ማድረግ እና በተቻላቸው መጠን የሃሳብ አንድነት እንዳይፈጠር ማድረግ ነው::
የፎቶ ኤግዚቢሽን
![]() |
| ፒያሳ – ራስ መኮንን ግርጌ |
![]() |
|
የቴኒክ ብልሽት:- መጽሔቱ በአንድ እትሙ ሽፋን ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኢምፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ የውስጥ ገጹን ጽሑፍ ደግሞ በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፡፡
|
![]() |
| የቴኒክ ብልሽት (ቀጣይ):- መጽሔቱ በውስጥ ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኤክስፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ (የሽፋን ገጹን ጽሑፍ ከላይ ይመልከቱ፡፡) |
![]() |
| Not Yet Arrived in 2014. In front of Bole Friendship Building |
![]() |
| ሁሉም ሰዎች አንድ ጋዜጣ (ልዕልና ከመታገዱ በፊት) – አሁን እነዚህ ካፌዎች በረንዳቸው ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል:: |
![]() |
| ይህ ማስታውቂያ ተዘቅዝቆ ነው ወይስ ተልጦ ወይስ ግራ ቀኝ ተዛውሮ ወይስ ሁሉም? (ራስ መኮንን አለፍ ብሎ) |
![]() |
| የቤተልሔም ሕንፃ /መገናኛ/ (ጀርባ – ፊቱን ከታች ይመልከቱ) |
![]() |
| ቤተልሔም ሕንፃ ከፊቱ (በነገራችን ላይ ይህ ሕንፃ መስታወቱ አንፀባራቂ በመሆኑ እንዲቀየር ማስጠንቀቂያ ከተጻፈበት ወራት አልፈዋል::) |
![]() |
| Guess Where? You got it right; it is in front of Bole Medhanialem – የጄኔራሎቹ ሰፈር |
![]() |
| ለልማቱ ነው – ምናለበት? |
![]() |
|
ቃሊቲ (የጠጠር ማምረቻውን ስም ሳየው ያስቀኛል:: አንድ ሰሞን
ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅን ድንጋይ ማምረቻ ይሉት የነበረው ይመጣብኛል፡፡) |
![]() |
| Got it Wrong: የኮሌጁ የመጽሔት ማስታወቂያ ኮሌጅ የሚለውን ጠንቅቆ አልጻፈውም! |
![]() |
| “ኢ-ልማታዊ መጽሐፎች” (ግልጽ በሆነ ምክንያት የትምህርት ቤቱን ስም ከመጥቀስ እታቀባለሁ) |
![]() |
| “የልማት መስዋዕት” – ለገሃር ከለታት አንድ ቀን |
![]() |
| Legend making: ቦሌ ቴሌ |
![]() |
| ሶኒክ ስክሪን – ፒያሣ |
![]() |
| Legend Making: ቦሌ – ሰን በርድ ካፌ (አሁን ጀግና አይሞትም የሚለው ቅርጽ ተነስቷል) |
![]() |
| ሐዋሳ አውቶቡስ ተራ – “ከኤድስ ለማምለጥ በየሱስ ማመን ነው” Really?! |
![]() |
| ሻሸመኔ – “የረዳኝ እግዚአብሔር ነው መኝታ ቤት” (ይህን ሳየው “እህቴ የላክሽልኝን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ አዋልኩት ሬስቶራንት” ብሎ አብርሃም አስመላሽ የቀለደው ቀልድ ይታወሰኛል::) |
ጥር መጣ ሙሽራ ቀንጥሱ
በጥር ወር ገበሬው ሰብሉን ሰብስቦ የሚጨርስበትና ሠርግ የመደገስ አቅሙ የሚጎለብትበት ወቅት ነው። በዚሁ ተለምዶ ከተሜውም ለሠርግ ጥርን የሚመርጠው ይላሉ የአገራችን የልምድ አንትሮፖሊጅስቶች።
እንደሠርግ እጅ፣ እጅ የሚለኝ ነገር እየጠፋ ነው። ወይ ባሕላዊ አይሆን፣ ወይ ዘመናዊ እንዲሁ የጨረባ ተስካር ብቻ ሰው ሰብስቦ እዩኝ ማለት – ማለት የኛ አገር ሠርግ ትርጉም ሆኗል። ደግሞ የወገኝነቱ አበዛዝ!
ባለፈው ሒልተን ሆቴል ፊት ለፊት አፍሪካ ፓርክ አጠገብ ሙሽሮች የፎቶ ስርዓት እያደረጉ ነበር። ይህ እንግዲህ ከሠርጉ ዕለት ውጪ ለማስታወሻ የሚነሱት ፎቶ ላይ መሆኑ ነው፤ አጃቢ የለም። አስፋልቱ ላይ ሙሽሪት ተዘርፍጣ፣ ሙሽራም እሷን እየተንከባከበ የሚያስመስለውን ድርጊት እያደረገ ፎቶ ሲነሱ አይቼ ሳበቃ በማየቴ እኔ አፈርኩ። ሚስቴ እንዲህ ዓይነት ነገር እናድርግ ከምትለኝ ጋብቻው ይሰረዝ ብትለኝ ውለታ እንደዋለልኝ እቆጥረዋለሁ።
የከተሜ ሠርጎች ከሠርጉ በፊት የስቱዲዮ ፎቶ መነሳትን ባሕል አድርገውታል። ስቱዲዮ ውስጥ፣ የተለመዱ የፎቶ አነሳስ ወጎች አሉ። ጥንዶቹ በፍቅራቸው ዘመን አድርገዋቸው የማያውቋቸውን (ለምሳሌ ሙሽራይቱ የሙሽራውን ከረባት እየጎተተች) ለማስታወሻ ፎቶ ይነሳሉ። እኔ የምለው፤ እነዚህ ጥንዶች ወደፊት ማስታወስ የሚፈልጉት ሆነው የማያውቁትን ነገር ነው እንዴ? ስቱዲዮዎቹ በውሸት ጥርብ ግድግዳዎች፣ እንስሳት፣ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ጌጣጌጦች ያሸበረቁ ዓይነት ሲሆኑ ጥንዶቹ በኪራይ ልብስ “የውቡ ቤት” ፈርጥ ሆነው ይነሳሉ። ይህንኑ ፎቶም ለልጆቻቸው ማስታወሻ ብለው ሊያሳዩ ያቆያሉ።
ሠርጎች ባብዛኛው ወግ የሚበዛባቸውና ለታይታ የሚደረጉ ሆነዋል። አማራጭ አጥተው ከተጋቡ አስመሳይ ተፋቃሪዎች ጀምሮ ዕድሜ ልካቸውን ከፍለው የማይጨርሱትን ብድር ተበድረው ድል ያለ ድግስ የሚደግሱ ሠርገኞች ድረስ ቲያትሩ ብዙ ነው። አንዳንዶች ሠርግ የሚደግሱት “እወቁልኝ” ለማለት ሳይሆን “እዩልኝ” ለማለት ይመስለኛል። “አታገባም ብላችሁ ያማችሁኝ እነከሊት እርር በሉ አገባሁ…፣ ባለፈው በመርሴዲስ አገባሁ ብለሽ የተቆላሽብኝ እከሊት፥ ያው እኛም በሊሞ ተጋባን…” እየተባባሉ ይመስለኛል።
በዚህ ወር ካየኋቸው ሠርገኞች መካከል ቦሌ መንገድ ላይ ባመሻሹ ብርድ እየተፈጁ በክፍት ጂፕ መኪና ቆመው ሲሄዱ ያየኋቸው ጥንዶች በጣም ካሳዘኑኝ ውስጥ ይመደባሉ።
ካሜራ በሌለበት፣ ማንም ሥራዬ ብሎ በማያስተውላቸው ሁኔታ ምን ልሁን ብለው ነው በብርድ የሚገረፉት? የታይታ ፍቅር ተመልካች በሌለበትም ያደክማል።
ትዳር ቀላል ኃላፊነት የሚጠይቅ እርምጃ አይደለም፤ ትዳር ሠርግ ብቻ የሚመስላቸው ግን እልፍ ናቸው። መሠረታዊ የቤት ዕቃ ያላሟሉ ሰዎች ለሠርግ ድግስ ሊሞዚን በ30 ሺሕ ብር ይከራያሉ። 500 ሰው ጠርተው ውስኪ ይራጫሉ። ለዚህ መደገፊያ “ሠርግና ሞት አንድ ነው”፣ “ዓለምሽ ዛሬ ነው…” እያሉ ይዘፍናሉ። ኑሯቸው ግን የሚጀምረው ከሠርጉ ዕለት ቀጥሎ ነው። ጥንዶች የተጋቡ ዕለት የሕይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀልበስ ወደሚያስቸግር አቅጣጫ እንደሚቀይሩ ሠርጉ እስኪያልፍ አይገባቸውም።
አንዱ ላገባ፥ ሌላው ገደል ገባ!
ከሠርግ ሰቀቀኖች ሁሉ የሚከፋው የወዳጅ ጓደኞች ፈተና ነው። በተለይ ሚዜ ተደርገው የሚመረጡ ሰዎች በዚህ የኑሮ ውድነት ኪሳቸው ይነቀላል። ሚዜዎች የራሳቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ ስለሚገደዱ ለወዳጅነታቸው ሲሉ ተበድረውም ተለቅተውም ቢሆን አላስፈላጊ ወጪ ውስጥ ይዘፈቃሉ። የወጪው አበዛዝ ደግሞ ወሰን የለውም። የየራሳቸው ሁለት ወይም ሦስት አልባስ እና ከሠርጉ ጋር የተያያዙ ሌ ሎች ወጪዎች ይኖራሉ። ለሚዜነት የተተዉ ጓደኞች ሳይቀሩ የመለመላሉ። እኔ በግሌ፣ ጓደኞቼን ሲያገቡ እንዳያስቸግሩኝ ከምጠይቃቸው ጉዳዮች አንዱ ለሚዜነት እንዳያጩኝ ነው።
የሕዝብ መብት ነፋጊ ሙሽሮች
ዛሬ፣ ዛሬ በየአደባባዩ ቅድሚያ እየወሰዱ አደባባይ ሦስቴ የሚሽከረከሩ ሙሽሮች የከተማ ትራፊክ ሲያጨናንቁ ማንም አሌ አይላቸውም፣ እነሱም አይጨንቃቸውም። ከሁሉም ከሁሉም የሚያበሽቀው ግን ከተማውን ሁሉ በጡሩምባቸው መረበሻቸው ነው። የነሱ ሠርግ የከተሜው ሁሉ ጉዳይ ይመስል መንገደኛውን ሁሉ በጩኸት በመረበሽ ይዝናናሉ። በተለይ በዚህ ወር ቅዳሜና እሁድ አደባባይ አካባቢ ጥቂት ሰዓት መቆየት ያማርራል።
በአገራችን፣ በተለይም በከተሞች የተፋቺዎች ቁጥር ከተጋቢዎች ቁጥር ጥቂት ነው የሚያንሰው። ጥንዶች ሠርጋቸው እንዲያምር የሚከፍሉትን ያክል መስዋዕትነት ያክል ትዳራቸው እንዲሰምር ቢተጉ ኖሮ የፍቺ ቁጥር በእጅጉ ይቀንስ ነበር። መደምደሚያዬ ነው።
Are Revolutions Meant to be Betrayed?
Revolutions are usually portrayed as the most heroic acts that can be done by a generation. Some say that they are simply shortcuts for evolution which bring immediate changes by shaking the status quo that, otherwise, might take long to; others say they are only good in clearing the way for real changes.: Only a few say revolutions are means in which you throw away the evils you know to put in the evils you don’t know.
During revolutions, things happen so fast that one can’t actually have control nor even clear understanding of what is going on. Post revolutionary eras are mostly unpredictable. Pre-revolution is the best course of any revolutionary progress; it engages wide range of popular participation and is determined to a goal of laying tyranny down. That’s not the same for post revolution era.
Revolutionaries don’t usually talk to each other what kind of change they’ve to bring. Even if they do, they care less for the differences existed between them. They just work together to topple whom they call an obstacle for their esteemed change.
This working together towards different goal brings a problem when they succeed. It’s true that predators agree until they will have to split their prey. After a revolution, come other successive revolutions. This is either because each revolutionary wants to take the key position to bring about their change or because the thrown ones want to come back in different colors.
Revolutions are participatory. Like the man behind the Jan 25/2011 Egypt revolution, Wael Ghonim, said it, they help in realizing “the power of the people is greater than the people in power”. However, no one can surely tell not only whether the revolutionary people owns the fruit of the revolution or not; but also whether the change is for good or not. Now – 3 years after the revolution, in Egypt, Wael Ghonim’s name is labeled as “foreign agent” and he is living in Dubai. If he goes back to Egypt, he will join his friends in jail. Friends of Mubarek are now back in power.
In Ethiopia’s 1974 revolution, most of the youth who risen up to throw the feudal monarchy were killed. The feudal system was broken for good (one goal achieved) but the revolutionaries were considered the enemies of the revolution for the years after. The people who toppled a monarchy were silenced by a militia rule.
In Kenya, too, not a few citizens believe the Mau Mau uprising was betrayed by Jomo Kenyatta who was “not actually a freedom fighter but an ordinary man who accidentally joined the fighters in prison”. Now, 50 years after Kenya earned its independence, political power and the economy is dominated by two giants (Kenyatta and Odinga) who accumulated all snatching from their people. This eventually created a huge gap of social equity. In fact, the fight has got Kenya independence but Kenyans are two: the rich and the poor. The former indirectly ruling the latter. I don’t think Mau Mau fought for that.
On the other hand, many a social scientists argue that it is hardly possible to measure the effect of a revolution within a short period unless for centuries. This argument, however, doesn’t answer how revolutions effect change that gradual evolutions can’t in this long period of time. Revolutions are meant to answer popular questions shortly.
In Ethiopian contemporary politics, the deliberately weakened oppositions are not less dictators than EPRDF wherever and whenever they can. I always bother about the destiny of Ethiopia thinking ‘what if the people who are giving up with the authoritarian behavior of the regime revolt?
Is it worth the risk to revolt against EPRDF? Is there any other way to bring plurality of administration toppling this one-party rule?
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ፎረም ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግሥትና መገናኛ ብዙኃን (የሲምፖዚየሙ አያዎ)
ሲምፖዚየሙ ከነጉድለቶቹም ቢሆን የተለያዩ አመለካከት አራማጆች በአንድ መድረክ የተሟገቱበት መልካም ጅምር ነው፡፡ ቀጣይነቱ ግን በቀጣዮቹ ተመራቂ ተማሪዎች ምርጫ እና በት/ቤቱ የበላይ ተቆጪ ኢሕአዴግ ፈቃድ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡
ዓይኔ ነው ላይኔ?
ሰፈሬ “የማርያም ጠበል” የሚባል አለ፤ የማርያም ቤተክርስትያን ታቦት ትላንት ጠበሉጋ መጥቶ ያድርና ዛሬ ይመለሳል። ስለዚህ መንገዴ በሰው ተጥለቅልቋል። ዘማሪዎችና ከነሱ በጎላ ድምፅ ሰባኪው ሲያስተምር በቅርብ ርቀት ከታቦት ማደሪያው አካባቢ ይሰማኛል። በመሐል የሆነ ቃል የሰማሁ መሰለኝ። ጆሮ ሰጠሁት፣ አዎ ደገመው። ስለልማት እያወራ ነው። ስለየቱ ልማት?
—
* ልማታዊ ዴሞክራሲ ድኅረ መለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው። ኢሕአዴግ ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›ን በ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› መተካቱን ተከትሎ ኢሕአዴግ የሚለውም ኢሕለዴግ በሚል ቢተካ ጥሩ እንደሆነ በጥምቀት በዓል ላይ የተገኙ አንዳንድ ምዕመናን ተናግረዋል። (በነገራችን ላይ፣ ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ› በዚህ ወር ሕትመቱ ተቋርጧል፤ ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› ሆኖ ይመለስ ይሆን?)
What about the right to be heard?
Following the 2010 national election, I have crunched the numbers of votes in Addis Ababa to find out that ’11 out of 23 seats should’ve be taken by oppositions had it been proportionally that our voices are counted or represented.’ Knowing that almost half of Addis Ababa’s election participants in 2010 voted to oppositions, it is sad to also know that their voices are represented by only a single man in the house of representatives.
In addition, no one has the confidence to say the dissidents in Ethiopia either have other means to express their alternatives as to how they want their country should be built or even how they want to live their life. The public school of discourse, which is the media, and civil societies are incapacitated.
Nevertheless, the question is not limited to have a means of expressing oneself. People manage their ways of doing it anyway. That’s how and why social media are now playing pivotal role in breaking news and creating hot discussions especially in authoritarian countries including Ethiopia. So, the question remains to be: ‘is the government listening?’
The constitution grants the freedom to expression and when it is violated, people shout out referring to the article. If democracy is about popular participation and if Ethiopia didn’t shut its doors for democracy then how is it possible to ensure that the people’s voices are heard?
Freedom of speech is crucial. However, what is most crucial is to be heard. Where is this ‘right of people to be heard’ by the government they appointed? Or, where is the obligation of the government to hear its people? Because, last time I checked, people speak to be heard.
የዶጋሊ ድል
የውጭ ጸሐፊዎች ስለአድዋ ሲጽፉ የአድዋ ጦርነት እያሉ ነው የሚጽፉት፤ እኛ ግን የአድዋ ድል ነው የምንለው፡፡ ማስታወስ የምንፈልገው ድሉን እንጂ ጦርነቱን አይደለም፡፡ የዶጋሊ ድልንም በብዛት የጻፉት የውጭ ጸሐፍት ባብዛኛው ‹የዶጋሊ ጦርነት› እያሉ ነው የሚተርኩት፤ ልዩነቱ እኛም እነሱኑ ተቀብለን ታሪኩን የዱጋሊ ጦርነት እያልን ማስታወሳችን ነው፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ በእኛ ድል አድራጊነት እስከተጠናቀቀ ድረስ ልክ እንደአድዋው ሁሉ ‹የዶጋሊ ድል› ብለን መተረክ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥም የዱጋሊ ድል ታሪካዊ ፋይዳ ከአድዋ ድል የሚተናነስ አይደለም፡፡
ልክ የዛሬ 127 ዓመት ወደኋላ፣ ጥር 18/1879 በራስ አሉላ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር፣ አውሮጳውያን ብዙም ያልተዘጋጀ እያሉ የሚጽፉለትን ነገር ግን በ23 የጦር አመራሮችና በ477 ወታደሮች የተገነባውን ሠራዊት በ10,000 ጦርና ጋሻ እና ጥቂት ቆመህ ጠብቀኝ የታጠቁ አርበኞች ድል ነሳቸው፡፡ ይህ ጦርነት ነበር የአድዋውም፣ የማይጨዉም ጦርነት የቂም መንስኤ እና የድል ዕድል፡፡
ዶጋሊ፣ በዛሬዋ የኤርትራ ምድር ላይ የምትገኝ መሬት ናት፡፡ ደርግ የዶጋሊ ድል በዓልን ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበርማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በዶጋሊ የመታሰቢያ ኀውልት እንዲቆም አድርጎ ነበር፡፡ ጣሊያኖችም በጦርነቱ ለተሰዉ ወታደሮቻቸው ሮም ላይ የመታሰቢያ ኀውልት አቁመውላቸዋል፡፡ የዶጋሊው የድል ኀውልት ግን የሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሕግሓኤ) ደርግን አሸንፎ ኤርትራን ሲቆጣጠር ኀውልቱን አፍርሶታል፡፡
አመክሮና በቀለ ገርባ
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ስራ አስፈፃሚ የነበሩት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ8 ዓመት እሥር የተበየነባቸው ሲሆን፤ ይግባኝ ጠይቀው እስሩ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከ5 ዓመቱ የእስር ጊዜ ውስጥም 3ቱን ዓመት በመጨረሳቸው በአመክሮ ይፈቱ ዘንድ ለማረሚያ ቤቱ ያመለከቱ ሲሆን ማረሚያ ቤቱም ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› በማለት እስከአሁን ሊፈታቸው አልቻለም፡፡ ይህም ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡
አንዳንድ ህጋዊ ሁኔታዎች ስለጉዳዩ፡
አመክሮ ምንድር ነው?
ሌላውን ትርጉም ትተን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ‹በተወሰነ ጊዜ በአመክሮ መፈታት› በሚለው ክፍል በተለይም በአንቀፅ 202 እንደደነገገው፡
“ተቀጭው ከተወሰነበት የእስራት ጊዜ ከሶስት እጅ ሁለቱን እጅ ወይም ፍርዱ የእድሜ ልክ እስራት ሲሆን ሀያ ዓመት በፈፀመ ጊዜ አግባብ ባለው አካል ወይም በጥፋተኛው አሳሳቢነት ጥፋተኛውን ከቅጣቱ ነፃ ያወጣዋል፡፡”
ይህም ማለት አመክሮ 2/3ኛውን የቅጣት ጊዜውን የጨረሰ ታራሚ ከእስር የሚፈታበት አሰራር ነው፡፡
አመክሮ ለማግኝት ምን መስፈርት ማሟላት ያስፈልጋል?
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ 202 ላይ አመክሮ ለማግኝት አንድ እስረኛ ማሟላት የሚያስፈልገውን መስፈርቶች ይዘረዝራል፡፡ ይህም፡
– ‹ታራሚው በስራ ጠባዩ የተረጋገጠ መሻሻል አሳይቶ እንደሆነ…›
– ‹ካሳ የመክፈል ግዴታ ተጥሎበት ከነበረና ካሳውን መክፈሉ የተረጋገጠ እንደሆነ…›
– ‹አመሉና ጠባዩ መልካም አኗኗር ለመኖር የሚያስችለውና በአመክሮ መፈታቱ መልካም ውጤት ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የታመነ እንደሆነ..› ይደነግጋል፡፡
ማረሚያ ቤት ወይስ ፍርድ ቤት?
ታራሚን በአመክሮ የመልቀቅ የመጨረሻው ስልጣን የፍርድ ቤት፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን ማረሚያ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በታራሚው አሳሳቢነት ለፍርድ ቤት ሲያቀርብ ነው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚሰጠው፡፡ እዚህ ላይ ማረሚያ ቤቱ ትልቁን ስልጣን ይዞ እናገኛለን፡፡ ማረሚያ ቤቱ ለፍርድ ቤት ማቅረብ ካልፈለገ ሊተወው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ማረሚያ ቤቱ በሕግ ስር ያለ አካል እንደመሆኑ መጠን በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 202 ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን ላሟላ ታራሚ አመክሮ ሊከለክል አይችልም – የታራሚው መብት ነውና!
በቀለ ገርባስ?
አቶ በቀለ ገርባ ከተፈረደባቸው የአምስት ዓመት እስር ውስጥ 2/3ኛውን ወይም 3 ዓመት የሚሆነውን ጨርሰው የአመክሮ ጥያቄያቸው በማረሚያ ቤቱ በኩል ለፍርድ ቤት እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁም ማረሚያ ቤቱ ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተሰምቷል፡፡
1ኛ. አመክሮ መስጠት የማረሚያ ቤት መብት ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡ መስፈርቱን ያሟላ ታራሚ አመክሮ የማግኝት መብት ያለው መሆኑ በሌላ በኩል አመክሮ ሰጭውን አካል ላይ ግዴታ ይጥላልና፡፡
2ኛ ሌላው አቶ በቀለ ገርባ መስፈርቱን አሟልተዋል ወይስ አላሟሉም የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ 2/3ኛውን የእስር ጊዜ መጨረስ የሚለውን Objective መስፈርት እንዳሟሉ ግልፅ ሲሆን፡፡ ችግሩ የተፈጠረው Subjective መስፈርቱ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይህም ማለት በእስር ወቅት መልካም ፀባይ አሳይተዋል ወይስ አላሳዩም የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ታራሚ በእስር ወቅት ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን ካሳየ የቅጣት ማስጠንቀቂያ ከመፃፍ እስከ ብቻውን ማሰር (Solitary Confinement) ድረስ ያሉ እርምጃዎች በማረሚያ ቤቱ ሊወሰዱበት ይችላሉ፡፡
አቶ በቀለ ገርባ ከፀባያቸው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ቅጣት ያልተወሰደባቸው ከመሆኑም ሌላ መልካም ፀባይ እንዳሳዩ ከማረሚያ ቤቱ እንደተነገራቸው ራሳቸው ገልፀዋል፡፡ በቀለ ገርባ ሁሉንም መስፈርት አሟልተዋል ማለት ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሆን አቶ በቀለን በአመክሮ ከመፈታት ያገዳቸው?
አንዳንድ ነገሮች…
ባለው አካሄድ አብዛኛው ታራሚዎች በአመክሮ ይፈታል፡፡ ከሌባ እስከ ሙሰኛ፡፡ High Profile በሆኑ ክሶች የተከሰሱ ሰዎች ሳይቀሩ በአመክሮ ሲፈቱ እንደነበር እናስታውሳለን ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ 24 ወራት ተፈርዶበት 16 ወራትን ጨርሶ በአመክሮ ተፈቷል፡፡ አቶ አሰፋ አብርሃ 9 ዓመት ተፈርዶባቸው ሰባት ዓመታት ታስረው ከብዙ ውዝግብ በኋላ በአመክሮ ተፈተዋል፡፡ በሌላ በኩል በቅንጅት ክስ ስር ተከሰው የነበሩት አቶ ዳንኤል በቀለና አቶ ነፃነት ደምሴ 30 ወራት የተፈረደባቸው ሲሆን 20 ወራትን በእስር አሳልፈው አመክሮ ቢጠይቁም ማረሚያ ቤቱ ‹ፍርዳችሁን ጨርሳችሁ ውጡ› በሚል ምክንያት አመክሮ ከልክሏቸው ነበር፡፡
እንግዲህ አቶ በቀለ ገርባ በሕጉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እያለ በአመክሮ የመፈታት መብታቸው አልተከበረም ወይም ማረሚያ ቤቱ ግዴታውን ሊወጣ አልፈለገም!
ምክንያት:
በጉልበተኞች የምትተዳደር ሀገር ዜጋ ስለሆኑ!
#FreeBekeleGerba
The Right, the Left and the Wrong Wings
In our political discourse, right wing is usually referred to as a political belief in which a person/group believes in individual rights over group rights whereas left wing is a political ideology where group rights come first. The worst part of this conventional definition is that you’ll be decided whether you’re a left or right wing (and nothing else) activist/politician only after your opinions on ethno-national versus national political movements are reflected. Those politicians who struggle focusing on ethno-nationals questions are generally considered as leftists. On the other hand, people who focus on multi-national issues are considered as rightists. Having this definition, the two wings consider each other as sinners. This is what I call Wrong-Wing.
It is, therefore, time to re-label what we have wrongly-labeled already. What is EPRDF? What are the major oppositions? Who is right-wing? Who is left wing? Who is wrong-winged? And most importantly, what wing are you?
የአዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት” አዝማሚያ
አዲስ ዘመን ጋዜጣ (በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በሕግ ይፍረስ ተብሎ ያልፈረሰው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር ተሰርቷል ያለውን) ጥናት፣ በፊት ገፁ ላይ፣ ባለፈው ረቡዕ ይዞ ወጥቶነበር፡፡ ጥናቱ፣ እንደአዲስ ዘመን አገላለጽ ‹‹የአዝማሚያ ጥናት›› ነው፡፡ ከዚህ በፊት የአዝማሚያ ጥናት የሚባል ነገር ሰምቼ አላውቅም፡፡ በእንግሊዝኛም ፈልጌ ስላጣሁት አገር በቀል የጥናት ዓይነት ሊሆን ይችላል ብዬ በደንብ አነበብኩት፡፡ ከአነበብኩት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ‹የመጽሔቶቹ ጽሑፍ አዝማሚያ ምንድን ነው?› የሚለውን ለማጣራት የተደረገ ሙከራ እንደሆነ ነው፤ እናም እኔም በበኩሌ የጥናቱን (ጥናት ከሆነ) አዝማሚያ ምን እንደሚሆን ለመመርመር ደግሜ አነበብኩት፡፡
- የመንግሥትን ኃላፊዎች የግል ስብዕና የሚነኩ፣
- የአመጽ ጥሪዎችን የሚጠሩ፣
- ሽብርተኝነትን የሚያበረታቱ፣
- የፖለቲካ ስርዓቱን የሚያጨልሙ፣
- የኢኮኖሚ ዕድገቱን የሚክዱ፣
- ሕገ መንግሥቱን የሚያጣጥሉ፣
—
“ይሉሽን በሰማሽ፥ ገበያ ባልወጣሽ”
ቦሌ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚሠሩ ሕንፃዎችን ሳይ ተስፋ ይታየኛል፤ የባቡር መንገድ ዝርጋታው፣ ሌላው ሌላውም እንደሚታከክ ቁስል ያለ ደስታ ይሰጠኛል፤ የማያድን ብቻ የሚያስታምም ዓይነት! ቢያንስ ለገጽታችን እንኳን አሪፍ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ውስጤ ግን እውነቱን ያውቀዋል፤ ሕዝብ ገጽታ እየበላ አይኖርም፡፡ ያ – የጉግል ሐሰሳ ላይ የሚመጣው የተራበ ሰው ሆድ በመስታወት ሕንፃ አይሞላም፡፡ በተለይ ደግሞ ባለሥልጣናት እንደነጋዴ ሕንፃ እንደሚገነቡ ትዝ ባለኝ ቁጥር የዚያ ሰው ረሀብ ለጥቂት ጥጋበኞች ሕንፃ ያቆማል እንጂ መቼም እንደማይቆም ይገባኛል፤ ተስፋ ያስቆርጠኛል፡፡
Throwing a Party in Ethiopia
A couple of years ago, a Canadian writer came to Addis to give a short training for amateur writers including myself. This trainer gave us an assignment of short writing on the first day of the training and we came up with different very short stories from which he chose a few to show some basics.
Among the stories chosen by him, there was one which has a girl character who is managing to attend in a party thrown for her friend’s birthday. The writer of this story, in her narration, explained the ambition of the girl to go to the party and how her mother said “No” angrily as soon as her daughter popped the question.
The trainer wasn’t comfortable of this statement because he thought mothers just don’t say ‘No’ whenever their daughters (and sons) ask them to go to parties. He said the girl’s mother had to ask what kind of party it is before she had to rush to deny permission.
One thing this Canadian didn’t know is the contextual meaning of ‘party’ in Ethiopia. It definitely means that it is an event where alcoholic drinks, smokes are presented accompanied by music and where girls and boys go wrong. It occurs in no Ethiopian’s mind that a party could be like an event or a place where freinds gather and have fun without getting wasted. Even night clubs are referred as ‘party bet’ (party house) colloquially.
So, any healthy mother, who knows the meaning of party in Ethiopia doesn’t let her daughter go to the parties.
What caught my attention since then and throughout is that how wronged our concept of having fun is. The most famous recreation means in Ethiopian cities, next to watching football especially for men, is drinking. Alcohol. (Of course I am talking about the urban life, which I know.)
It starts traditionally. Most type of ‘digis’ (can we call them parties?) have alcoholic drinks like ‘tella’ and ‘tej’. In our bigger cities, beer and other alcohols are joining them. Children who see this want to experience the feeling of getting drunk but aren’t usually allowed to by their parents. They would do it anyway without the knowledge of their parents.
Many youngsters tell their parents they want to crush at their cousin’s place (or friends house, let’s say, to do school assignment) and at the same time the same cousin/friend asks their parents permission to crush on the former’s place and both go to the clubs. If this doesn’t work, there are many people who are making a living out of the youngsters wish to party.
Many self-appointed DJs are always busy throwing day parties for students who never had chance to party in clubs at night. The day parties are usually thrown on weekdays so as to make sure the students parents have no way to know where their children are. The youngsters manage to convince their teachers that wether they are sick or one of their siblings are dead to be absent from school. They party and get wasted, in the real sense of getting wasted.
However the audience of day-parties are mostly highschool students, there are no restrictions on the kind of drinks offered as long as they can afford it. Places are usually reserved for privacy where one can be able to smoke weed, kiss one another and at times have sex. There are also parties where everyone has the right to kiss anyone – and they do that to raise money for another event.
Money isn’t a factor for many of the youngsters. Many parents who send their children to private schools, also give their children much pocket money in competition with other children’s parents without having any idea how it will be spent.
This becomes a habit and many youths have already lost their ways forever. Yet, their parents don’t know what is going on; their school leaders are reluctant about it; and, most of all, the government covered its ears not to hear the defeaning voices of the dying generation.
የኢትዮጵያ የጋዜጠኛ ማኅበራት = የመንግሥት ገደል ማሚቶዎች?
“ሲፒጄ የሃገራችንን ስም ለማጥፋት ስለሚፈልግ ነው እንጂ፣ በጻፈው ጽሑፍ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም፡፡ 3 ጋዜጠኞች የታሠሩት አሸባሪ ተብለው ነው” ~ አቶ አንተነህ አብርሃም (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት /ኢብጋኅ/ ፕሬዚደንት)“[ሲፒጄ] ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ ናት ብሏል፡፡ ይሄ ከዚህ በፊትም ሆኖ የማያውቅ ግነት ነው፡፡ የታሰረ የለም።” ~ አቶ ወንደወሰን መኮንን (የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማኅበር /ኢነጋማ/ ሊቀመንበር)“በጻፈው ተፈርዶበት የታሰረ አለ ከተባለ ዶክመንቶችን ማገላበጥ ያስፈልጋል፡፡ ማንም ደግሞ አልታሰረም። ይህ አልሆነም፡፡ ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀላል፡፡” ~ አቶ ሽመልስ ከማል (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ)
‹‹…ሊቋቋሙ ይችላሉ መብታቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነማን ናቸው የሚያቋቁሙት፣ እንዴት ነው የሚቋቋሙት፣ ከጀርባ እነማን አሉ —- ይሄን ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ትልቅ ጉዳይ አይደለም፤ ኖረንበታል፡፡ ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም፡፡…››
To OR Not To: Ethnic-based Political Party
As Posner (2004) notes, elites struggle to win the maximum rights and privileges for their ethnic groups. This condition fuels ethnic competition with the hope of gaining influence in national politics (Wantchekon 2003). On the other hand, for Chandra (2004, 2006) the quality of democracy will not be affected by the domination of ethnic-based parties. Another scholar, Birnir (2007) also voiced similar argument and claimed that ethnic-based parties might contribute for the improvement of the quality of democracy.
የአዲስ አበባ ፍተሻ ከሽብር ያተርፋል?
ሰሞኑን፣ በተለይ የዌስት ጌት ሞል ላይ በአልሻባብ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ጥበቃው ተጠናክሯል። በወቅቱ በድንጋጤ ሲዘነዘሩ ከነበሩ አስተያየቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ጥቃት የማይፈፀመው በደኅንነቱ ሥራ መጠናከር ነው የሚለው አስተያየት አመዝኖ ተደምጧል። መንግሥትም ፀረ–ሽብር እንቅስቃሴ ላይ አተኩሬ የምሠራው ይህንኑ ፈርቼ ነው የሚመስል ትንታኔ በኢቴቪ በኩል አሾልኳል።
ይሄ ሁሉ ይባል እንጂ፣ የዌስት ጌቱ ድንጋጤ አዲስ አበባን ዛሬም በፍርሐት እያራዳት ነው። በተለይም ደግሞ የእግር ኳስ ፈንጠዝያው ዕለት ራሳቸው ላይ ባርቆባቸው ሞቱ የተባሉት አሸባሪዎችና በአልሻባብ ስም በትዊተር ገፅ ፒያሳ እና ቸርችል ቦምብ ቀብረናል ብለው ያልታወቁ ሰዎች የነዙት ወሬ ድንጋጤውን አባብሰውታል። ከዚያም በኋላ ኳስ ግጥሚያዎች ባደባባይ ስክሪኖች እንዳይተላለፉ በማገድ መንግሥትም መፍራቱን አረጋግጧል።
በዚህ ድንጋጤ ወቅት ምክንያቱ በቅጡ ባይገባኝም፣ ብዙ የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ሰለባ ይሆናል ብለው የገመቱት ኤድና ሞልን እንደሆነ በግልጽ ሲናገሩ ነበር። ምናልባትም የመዝናኛ ስፍራ ስለሆነና የውጭ ዜጎችም ስለሚበዙበት ዓይን ውስጥ ይገባል በሚል ይሆናል። ኤድና ሞልም መልዕክቱ አሳስቦት ይሁን በመንግሥት ትዕዛዝ “የተጠናከረ ፍተሻ” ጀምሯል።
በነገራችን ላይ አንድ ቀን፣ አንድ ሰው ኤድና ሞል ውስጥ በፌስታል ይዞት የገባውን ዕቃ ረስቶ በመውጣቱ ሁካታና ድንጋጤ ተከስቶ ፊልም እስከማቋረጥም ደርሶ እንደነበር ሰምቻለሁ።
የኤድና ሞል ፍተሻ የተጠናከረ ሰሞን ጥበቃዎቹን ‘ያ ሁሉ አብጠርጥሮ መፈተሽ ለምን እንደሆነ’ ስጠይቃቸው እዚያ የሚገቡ ኮረዶችና ጎረምሶች ሐሺሽ ይዘው እየገቡ አስቸግረዋቸው እንደሆነ ነገሩኝ። ባይዋጥልኝም ለፍተሻ መተባበሬ አልቀረም። የኤድና ሞል ፍተሻ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶ አሁን ላፕቶፕ ይዘው የሚገቡ ሰዎች የያዙት ላፕቶፕ መሆኑን ለማረጋገጥ አብርተው ማሳየት አለባቸው።
በሌላ በኩል ጥበቃዎቹ ለሚያደርጉት ክትትል መጋነን የደኅንነት አባላት እጅ አለበት የሚል መረጃም ደርሶኛል፤ ደኅንነቶቹ፣ ፍተሻው የላላበት የሚመስላቸው ቦታ በጋዜጣ ሽጉጥ ጠቅልለው ያሳልፉና ለአስተዳደሩ ፍተሻው ደካማ መሆኑን የሚናገሩበት አጋጣሚ አለ። ስለዚህ ጥበቃዎቹ ይህ እንዳያልፋቸው ሁሉንም አብጠርጥረው በመፈተሽ ያሳልፋሉ።
ይህ ዓይነቱ ፍተሻ፣ በሁሉም ሆቴሎች፣ ሕንፃዎችና አንዳንድ ካፍቴሪያዎች ሳይቀር እየተጠናከረ ነው። መልካም ነው፤ ለደኅንነታችን ሲባል የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች በሙሉ ቢያታክቱም በቀና መቀበል ይኖርብናል። ችግሩ፣ ‘ደኅንነታችን በርግጥ በዚህ መንገድ ይጠበቃል?’ የሚለው ነው።
የዌስት ጌት ጥቃትን ብንመለከት የተፈፀመው በቡድንና በተደራጀ መሣሪያ ሲሆን በኤድና ሞልና ሌሎች የሚደረጉ ፍተሻዎች ግን በሠላማዊ መንገድ፣ በነጠላ ገብተው ጥቃት ለማድረግ ያሰቡ ሰዎችን ብቻ ለማስቆም እንጂ የተደራጁ ሰዎችን ለመግታት አያስችልም።
ጎረቤታሞቹ ጁፒተርና ራዲሰን ብሉ ሆቴሎች ግን እንዲህ ዓይነቱ ወሬ የመጣ ሰሞን የፍተሻ ድንኳኖቻቸውን ከሎቢዎቻቸው ውጪ በመትከል የተሻለ አማራጭ ተከትለዋል። ይህ የተደራጀ አደጋ ከመፈጠሩ በፊት ገና ከደጅ ለመከላከል ያስችላል።
The Dark Triad in Ethiopian Political Discourse
The dark triad psychological personalities are personalities that are characterised by a duplicitous interpersonal style associated with cynical beliefs and pragmatic morality. These personalities are Narcissism, Machiavellianism and Psychopathy AND I am arguing they are abundant in Ethiopian political sphere in general and in the political discourse in particular.
1) Narcissism
“Narcissism is a term that originated with Narcissus in Greek mythology who fell in love with his own image reflected in a pool of water. Currently it is used to describe the pursuit of gratification from vanity, or egotistic admiration of one’s own physical or mental attributes, that derive from arrogant pride.” (Wikipedia)
It is exactly this narcissism that created many resistant Ethiopian politicians who don’t trust anyone else but only themselves. AND, I think this is a behavior that all dictators are made from.
Ethiopians have missed a lot of democratization opportunities because either the politicians or other stakeholders are, I am afraid to say, narcissist.
We can briefly remember the golden opportunities we had lost for the past 50 years.
In the 1960s, during the students movement and after the revolution, the different parties created with similar ideologies and also the splits within each party were all caused due to the narcissist behavior of the actors. They were quick to label and disintegrate anyone else coming with a new narrations of problems and alternatives of solving them in a different way to that of theirs. Eventually, they revolutionaries end up killing each other almost clearing a generation.
Four decades later, following the historic Ethiopian election of 2005, the ruling party as well as opposition leaders were too narcissist to make people’s question for change true. First, the incumbent resisted to share power because of its ideological belief that only its way and no one else’s keep Ethiopia stable. Consequently, jailed hundreds of party leaders and killed other hundreds of street unarmed protesters.
The oppositions played their role when they are released with “pardon”. Each leader of the parties that formed the coalition, kinijit, had wanted to take advantage of popular acceptance opportunity and their narcissism helped them remember neither the demands nor the benefits of the people.
2) Machiavellianism
The term ‘Machiavellianism’ is coined after the writer of II Principe (The Prince), the Italian Niccolo Machiavelli, and is generally defined as the employment of cunning and duplicity in statecraft/general conduct or simply as an unemotional tendency to manipulate others.
Machivellianism is especially seen in Ethiopian politics when it comes to ethno-national questions. Most politicians/activists who are actually psychopathic (the third dark triad) where as they present themselves to the public as “most concerned to the social fabric”. However, they don’t believe in anything except themselves, they manipulate their societies using the words of the most accepted religion in their target area.
This lack of innocence of the Ethiopian politicians has dragged the most burning questions of the country (ethno-nationals’ equality and poverty questions) backwards since they were first raised publicly 50 years ago. Through all the years for the past half of a century, the same questions are raised whenever needed to manipulate the public but only the leaders of the questions, who are Machivellianists, have changed their lives out of it.
3) Psychopathy
Psychopathy is a mental disorder to many; it is enduring dissocial or antisocial behavior, “a diminished capacity for empathy or remorse, and poor behavioral controls or fearless dominance.”
It is nothing else but psychopathy that leaves many leaders of Ethiopia have no empathy when they took thousands of lives to retain their power and they argue on numbers.
They don’t feel anything about how many people are living below the poverty line when they enjoy lexury spending the wealth of their society.
The policies they make consider least to the built values of the society. They only care about figures and facts and not about any emotions that can keep the society well.
Different players of the politics are suffering from either of or maybe all the three triad. There is always a healthy level of each of these three behaviors. The problem: our politicians and activists do not have limits of any kind. They are extremists.
#HRDay2013: Ethiopian government must reveal who, why, where and how citizens in jail are imprisoned
I always come across through Siye’s statement in that he mentioned ‘the prison [in Ethiopia] speaks Oromiffa’ – to mean most of the prisoners are Oromos. When my friends and I visited journalist Wubshet Taye before he was moved to Zeway, he told us the same thing. Many Oromos are imprisoned. That’s not the question! The question is why are they imprisoned?
Is it because they committed crimes? Is it because they believed Oromia should secede? If so, it’s their constitutional right. Is it because they were working with OLF? In fact, had people were allowed to work legally against a system that they don’t legitimize then they wouldn’t have any reason to do it underground with an ‘illegal group’. And we the people, at least, deserve to know the detail.
Ethiopia has signed the African charter for human and people’s rights. The concept of ‘people’s rights’ is unique to Africa and concerns about the rights of groups including ethnics. It’s, therefore, the duty of the government to unconditionally respect these rights and our right to know if they are protected or not.
This is not the only problem. In the last September, on the public demonstration called by UDJ party, a girl appeared with a slogan that reads ‘My father is not a terrorist’. We talked to the girl and no one knows her father and even the case he was jailed. Given the history of government’s brutality on its critiques, we can’t help analyzing this “terrorist” as one victim of the conspiracies made against innocents.
Ethiopian prisons are like ‘bermuda’. There is no independent institution that knows what’s going on in there. It is the government itself that’s capable of doing this.
I know this sounds ridiculous to most of you but as people who believe in peaceful struggle, we don’t have an option other than trying hard to push the government reveal the prison information. In the end, I hope we will have a little picture of what is happening in Ethiopian prisons.
Therefore, this is my call for Ethiopian social media activists to hold this question up through the months between the past and the coming international human rights days.
Ethiopian prisons must release periodic reports to the public on who (specially groups the prisoners are from), why they are jailed, where and how they are held.
We have the right to know if our prisons are places where citizens are corrected for the mistakes they have made in life; not a place where citizens have to pay for standing differed with ruling party.
A New Journalists Association is Under-formation in Ethiopia
![]() |
| The Press Release (Amharic) |
- for the respect of Freedom of Expression granted in the FDRE constitution article 30;
- for the benefit of journalists;
- for promoting professional excellence of journalists through trainings;
- for strengthening the relationship/communication among journalists;
- for facilitation of financial, material and legal support whenever needed;
- for recognizing journalists who are contributing positively to the sector;
- The term ‘Forum’ might be confusing with a political coalition that is referred by the same term – Forum;
- The committee should not be called ‘founding’ but ‘coordinating’ as it is working to coordinate;
- Working for the respect of ‘Freedom of Expression’ should not be the role of the ‘Forum’ rather practicing it;
#HRDay2013፤ ከሰው በታች የሆኑ ሰዎች አሉ ብለው የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም አሉ
ሰውዬው ያወራልን ሌሊት ወደጅብነት ስለሚለወጡ ሰዎች ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላችንም አፍረን ስናፈገፍግ ከመሐላችን አንዱ “እንዲህ ዓይነት ነገር እውነት ነው ብለህ ታምናለህ?” ብሎ ጠየቀው፡፡ እሱ ሆዬ በሙሉ መተማመን እኛን እንዳላዋቂ በመቁጠር ሌሊት ወደጅብነት የሚለወጡ ሰዎች እንዳሉ ያስረዳን ጀመር፡፡
ይህንን ትዝታዬን የቀሰቀሰው ትላንት ጋዜጠኛ Masresha Mammo የጻፈው ማስታወሻ ነው፡፡ ርዕሰ ጉዳዩ የተለየ ስለነበር እኔ ግን ለዚህች ጽሑፌ የሚጠቅመኝን ገንጥዬ አጣቅሳለሁ፡፡ ማስረሻ እንዲህ ይላል፤
‹‹…ተወልጄ ያደግኹት ከእንጦጦ ተራራ ስር ቀጨኔ በምትባል ሰፈር ውስጥ ነው፡፡ […] ቀጨኔ ላይ ያለው ማኅበረሰብ ወደአዲስ አበባ የተሰደደው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሲል አልነበረም፡፡ ቡዳ ነው የሚል ስም ስለተለጠፈበት ‹ልጆቻችንን በልተው ጨረሷቸው› በሚል ግድያው ስለበዛበት ነበር፡፡ አንድ ቀጥቃጭ አባቱ፣ ወይም ሸማኔ ወንድሙ፣ አሊያም ሸክለኛ እናቱ በዚሁ ሰበብ ሲገደሉበት፤ በምላሹ እሱም ደሙን ተወጥቶ ይሸሻል፡፡ ይሰደዳል፡፡…
‹‹ይኼ ማኅበረሰብ ለሺሕ ዓመታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የጀርባ አጥንት ኾኖ ቆይቷል፡፡ በቴክኖሎጂ ላልሰለጠነችው ኢትዮጵያ ማረሻ እና ወገል ያቀርባል፣ እንዳይበርዳቸው ልብስ ይሠራላቸዋል፣ ለመመገቢያቸው የሚኾኑትን ሸክላዎች እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች ሁሉ ይሰጣቸዋል፡፡ ያለዚህ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን ወደኋላ ዞር ብላችኹ አስቧት፡፡ [ማኅበረሰቡ] በሚኖርባት በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ግን ስሙ ቡዳ ነው፡፡
‹‹ቡዳ ማለት ደግሞ፤ ቀን ቀን ጋቢ ለብሶ የሚኖር፣ ማታ ማታ ወደ ጅብነት የሚቀየር ማለት ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ እና አመለካከት የሚመራው በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ነበር፡፡…››
ማስረሻ ‹‹ነበር›› ይበል እንጂ ዛሬም ድረስ ከዚህ ባልተለየ መንገድ የሚያምኑ ‹‹ምሁራን›› ሳይቀሩ አሉ፡፡ ልዩነቱ በዚህ ዘመን በተለይ በከተማ እንዳይገዳደሉ ሕግ ያግዳቸዋል፤ በገጠር ግን አሁንም በግልጽ አለ፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሄድኩበት የገጠር አካባቢ ውስጥ ካሉ ‹‹ቡዳ›› ወይም ‹‹ባለእጅ›› ከሚባሉ ሰዎች/ቤተሰብ አባላት ጋር እንዳልገናኝ እና ‹‹ዓይናቸው እንዳልገባ›› አብረውኝ ያሉ ሰዎች ሲጠብቁኝ እና ሲያከላክሉኝ ነበር፡፡ ዛሬም እናቴን ብቻ ሳይሆን ወጣት ጓደኞቼን ሳይቀር ቡዳ የሚባል ነገር የለም ብዬ ማሳመን ይከብደኛል፡፡
ይህ ሰዎችን የማግለያ ሰበብ ነው፡፡ ሰዎችን ንዑስ-ሰው አድርጎ የመቁጠር አባዜ ነው፡፡ የሰብኣዊ መብት ዋና ፅንሰ ሐሳቡ ደግሞ ሰዎች ሁሉ ዕኩል ናቸው የሚለው ነው፡፡ ያንን የማያምኑ ሰዎች ባሉበት አገር በመንግሥት ጥረት ብቻ ሰብኣዊ መብት አይከበርም፡፡
—
እዚህ ጽሑፍ ላይ የተሰጡ ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ!























