አሳፋሪነቱ እየተባባሰበት የመጣው “ፍርድ ቤት” የመብት ጥሰትንም ሆነ የሲዲ ማስረጃዎች ጥያቄን አልቀበልም አለ
ሁለት የጎንዬሽ አቤቱታዎችን አስመልክቶ ዛሬ የተሰየመው ችሎት ከሌላ ጊዜው በባሰ ሁኔታ የወንጀል ስነስርአትና የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ላይ ሲቀልድ ውሏል፡፡ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን በጎብኚዎች የመጠይቅ መብታቸው መነፈጉን በቀን 20 ደቂቃ ብቻ ከሌሎች እስረኞች ከቅርብ ቤተሰብ ውጪ ሌላ አንዳይገባ እንደተከለከሉ መሰረታዊ መብቶቻቸው እስር ቤት ውስጥ አንደሚጣሱ ባለፉት ስድስት ወራት በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የከረሙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የመብት ጥሰቱን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አልቀረበም፣ ከማረሚያ ቤቱ ጋር ያለውን አስተዳደራዊ ችግርን የመፍቻ መንገድ አልተጠቀሙም በማለት በውሳኔው የህገ መንግስቱን አንቀጽ 21 ሽሮታል፡፡ አያያዛቸው መሰረታዊ መብቶቸን የሚያስጠብቅ ይሁን ብሎ የተለመደውን የለበጣ ትእዛዝ አንኳን መስጠት ያቃተው የዛሬው “ፍርድ ቤት” የሁለቱን ወጣት ሴቶች መሰረታዊ የመብት ጥያቄ እነደዋዛ አጣጥሎታል፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ የነበረው አቃቤ ህግ የሲዲ ማስረጃዎቹን ለተከሳሾች ሊሰጥ አንደሚገባ ሲጠይቅ የወንጀሉ ኤግዚቢት ነው በማለት ያቀረበውን መከላከያ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ለተከሳሾች ሊሰጥ አይገባም ሲል ሌላ አስገራሚ ብይን አሰምቷል፡፡ ብይኑን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች የወንጀል ኤግዚቢት ከሆነ ሲዲው በአቃቤ ሀግ እጅ መገኘት አንደማይገባና በህጉ መሰረት ፍርድ ቤቱ እጅ መቀመጥ አንዳለበት በመሆኑም ሲዲው የት አንደሚገኝ የጠየቁ ሲሆን “ፍርድ ቤቱ” በጠበቆች ስላልተጠየቀ ሲዲው ሬጅስትራር ጋር መሆኑ እና አለመሆኑን እነዳላጣራ አስገራሚ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ይህንን አስተያት ተከትሎ የህግ ባለሞያው ዘላለም ክብረት ለፍርድ ቤቱ አጠር ያለ የወንጀል ስነስርአት ሂደትን የሚያስረዳ ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ “በዚህ ሂደት ፍርድ ቤቱ በግልጽ ሲዲው የማስረጃው አካል ነው ወይስ ኤግዚቢት ነው የሚለውን አሁን ይንገረን ፡፡ ኤግዚቢት ነው ከተባለም አቃቤ ሀግ የማስረጃ አካል አድርጎ እንዳያቀርበው አሁን ብይን ይሰጥልን በማለት ጠይቋል”፡፡ “ፍርድ ቤቱም” ይህንን መወሰን ያለበት አቃቤ ህግ ነው የሚል የእለቱን አስገራሚነት የጨመረ መልስ ሰጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ አቃቤ ሀግ ማስረጃ ነው ካለም በማስረጃ መስማቱ ወቅት በሂደት የሚታይ ነው ያለ ሲሆን ብይኑን ከጠበቆች እና ከተከሳሾች በቀረበበት ተከታታይ ጥያቄዎች ሲያምታታ ተስተውሏል፡። ተከሳሾች ተቃውሞ ካላቸው ይግባኝ ማቅረብ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ አቃቤ ህግ ያለውን ብቻ በመስማት ተከሳሾች ላይ ተጽእኖ እያደረጋችሁ ነው ሲል “ፍርድ ቤቱን” ከሷል፡፡
በእስር ላይ አንድ አመት ሊሞላቸው አንድ ወር የቀራቸው የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በጠንካራ መንፈስ እና ፈገግታ ችሎቱን የታደሙ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ውጥንቅጥ ምንም አይነት መገረም አልታየባቸው፡፡
የዞን9 ማስታወሻ
ከዚህ በፌት በተደጋጋሚ አንዳልነው የዞን9 ጦማርያን ፍርድ ቤት የሚሄዱት የፍትህ ስርአቱን ህጋዊ እውቅና እና ቅቡልነት ለማሰጠት ሳይሆን በቃል ስንለው የከረምነውን የፍትህ ስርአቱን ውድቀት በተግባር ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሁሉንም የህግ አማራጮች በመጠቀም ፍርድ ቤቱን በማጋለጣችን በእስርም ሆነ በስደት የምንገኘው የዞን9 አባላት በኩራት አንገታችንን ቀና በማድረግ የምንናገረው ጉዳይ ነው፡፡ በየቀኑ የራሱን መሰረታዊ መስፈርት እና ጥቃቅን የወንጀል ስነስርአት ህግ አንኳን መከተል ያቃተውን ፍርድ ቤት የሚመሩት ዳኞች ከችሎቱ ሲወጡ እና ከህሊናቸው ጋር በግልጽ ሲነጋገሩ የስራ አስፈጻሚው መሳሪያነታቸውን ቀን ከቀን በአሳፋሪ ሁኔታ እያጠናከሩ መሆኑን እነደሚያውቁት እርግጠኞች ነን፡፡ ራሳቸውን ከችሎቱ አግልያለው ብለው አስካሁንም ችሎቱን እየሰበሰቡ ባሉት አቶ ሸለመ በቀለ ለሚመራው ችሎት በተደጋጋሚ ጥሪ ስናደርግ እነደነበረው የፍትህ ስርአቱን ስም የማደስ እድላቸውን እየተጠቀሙበት ካለመሆኑም በተጨማሪ የነርሱ ከፍትህ እና ከታሪክ በግራ በኩል መቆም ከማሳየቱም በላይ የወጣት አስረኞቹን ልእልና ቀን ከቀን ከፍ ብሎ እነዲታይ እያስቻሉ ነው፡፡
አገራቸውን በጨዋነት የሚያገለግሉ ምሁራን የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች አምባገነንነት እና የተቃውሞ ድምጽ ማፈኛ መሳሪያ የሆነው የፍትህ ስርአት ያልፈታቸው ጨዋዎች መሆናቸውን በማስመስከራቸው እንኮራለን፡፡ የህሊና እስረኞቹ በማንኛውም መስፈርት ቢለኩ ከደረጃቸው በታች በሆኑ ዳኞች ፌት መቆም ያልነበረባቸው የቤተሰብና የአገር ኩራቶች ናቸው ፡፡

የፍትህ ስርአቱን ውድቀት ማጋለጡ ይቀጥላል፡፡

ዞን9

አጭር የፍርድ ቤት ውሎ
የሁለቱ ሴት ታሳሪያንን አያያዝ እስመልክቶ ዛሬ ለ22ተኛ ግዜ የተሰየመው ችሎት ለመጋቢት 10 ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ተጠናቋል ፡፡
የመጀመሪያው ጉዳይ የሆነውና የማህሌት ፋንታሁን እና የኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ የተነሳው አቤቴታ ላይ መልስ የሰጡት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ዋና ሱፕር ኢንቴንዳንት ለተእግዜር ገ/ እግዜያብሔር ምንም አይነት የመብት ጥሰትና የጎብኚ ክልከላ እየተደረገባቸው አይደለም አንደማንኛውም ታራሚ በማንኛውም ሰው ይጠየቃሉ ሲሉ ሽምጥጠው ክደዋል፡፡
ሁለተኛው የሆነው አቃቤ ህግ በእጁ ያሉትን 12 የኦዲዬ ቪዲዬ ሲዲዎች ለጠበቆች አንዲሰጥ የጠየቁበት ቢሆንም አቃቤ ህግ መመልሱ በችሉት ወቅት ያዩታል እንጂ ፓሊስ ኤግዚቢት ለጠበቆች የመስጠት የሚያስገድደን ህግ የለም ብሏል፡፡ ( የአቃቤ ህግ ምላሽ ከስር ተያይዞ ይገኛል)
ሁለቱም ጉዳዬች ላይ ብይን እሰጣለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ ወንዶች ተከሳሾችም ተገኝነተው ብይኑን እንዲሰሙ አዟል፡፡

 

የዞን9 ማስታወሻ
የቀረበብንን ማስረጃ አይተን የመከላከል ህገ መንግሰታዊ መብታችን መጣሱን አጥብቀን እየተቃወምን መሰረታዊ ከፓለቲካ ነጻ ውሳኔ መስጠት መቻሉ የሚያጠራጥረው ፍርድ ቤት ቢያንስ በስነስርአት ጉዳዩች ላይ አንኳን ስልጣኑን እንዲጠቀምበት እናሳስባለን ፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን!
በነገው እለት የ 26 ተኛ አመት የልደት በአልህን ለምታከብረው ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ አንወድሃልን፡፡ አንኮራብሃለን
ዞን9


“ሸላሚም እኛ፣ ከሳሽም እኛ! “
አብርሃም ሰለሞን የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ያሳደገው ኢሕአዴግ ራሱ (ወይም ዘመነ መንግስቱ) ነው፡፡ በቤተልሄም የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ IT መምህር ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ መልካም ዝና ነበረው፡፡ በ2006 በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ውድድር ላይ ይዞ በቀረበው የመምህራን ዳታ ቤዝ እና የመማሪያ ማኑዋል ዝግጅትን አሸናፊ መሆን ከቻሉ ሦስት ወጣቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ጥቅምት 16/2007 – በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሸላሚነት ሲካሄድ በነበረው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን IT ለማስተማር የሚረዳ የዴስክቶፕ ሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን በማዘጋጀት የሜዳልያ ተሸላሚ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ የዘንድሮውን የስራውን ውጤት በአካል ተገኝቶ ሰርተፍኬቱንም፣ ሜዳልያውንም መቀበል አልቻለም፤ በእሱ ፈንታ እናቱ በውክልና ተቀብለውታል፡፡ ምክንያቱም እሱ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ ቂሊንጦ ማቆያ ቤት ይገኛል፡፡
አብርሃምን ስለ አገሪቱ የወደፊት ተስፋ ሰጪ ስራ ሰርተሃል ብሎ በቀኝ እጁ የጨበጠው መንግስት፣ በግራ እጁ ደግሞ ለአገሪቱ የወደፊት ተስፋ አደገኛ አሸባሪ ነህ ይለዋል፡፡
 

 ከግራ ወደቀኝ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሀብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞን፡፡

“የማይተዋወቁ ግብረ – አበሮች”
በሽብር የሚከሰሱ ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በአንድ መዝገብ (እንደ ግብረ አበር) የሚታሰሩበት አሰራር የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ የነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ በመባል የሚታወቀው (መዝገብ ቁጥር 166/07) አንዱ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ አራት የተለያዩ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች 6 ተጠርጣሪዎች ተከስሰዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ 5 ተከሳሾች (ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ እና የሺዋስ አሰፋ) በፀረ- ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ  4 ሲከሰሱ፣ ቀሪዎቹ አምስቱ (ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳኑ፣ እና ተስፋዬ ተፈራ) በአንቀፅ 7/1 እና 9ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ዳጉ) በሌላ ክስ በወንጀለኛ መቅጫው 288/1 መሰረት ከመከላከያ ሰራዊቱ በመኮብለል ተከስሰዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ክሳቸው በአንድ መዝገብ ታጭቀው ቢመጡም ባብዛኛው እርስ በርስ አይተዋወቁም፤ በጋራ የሰሩት ስራም የለም፡፡
በፌስቡክ እንቅስቃሴው በስፋት የሚታወቀው እና የአረና ትግራይ ፓርቲ አመራር አባል የነበረው አብርሃ ደስታ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ከሆነው ሀብታሙ አያሌው በቀር የሌሎቹን ስም እንኳን አብረው ከመከሰሳቸው በፊት አለመስማቱን ይናገራል፡፡ ተሸላሚው አብረሃም ሰለሞንም ከተከሳሾች የሚያውቀው ዘላለምን ብቻ ነው፡፡ ‹‹እሱንም›› ይላል አብርሃም ‹‹በ2006 አንድም ቀን አግኝቼው አላውቅም››፡፡ ከተከሳሾች መካከል ብዙ ሰው ያውቃል የተባለለት 1ኛው ተከሳሽ ዘላለም እንኳን የሚያውቀው ሦስቱን ብቻ ነው – ዮናታን፣ አብርሃምን እና ባሕሩን ብቻ፡፡
“በስልክ የማውራት አሸባሪነት”
በሽብር የተከሰሱ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ እና በተለይ ከሚቀርቡ የማስረጃ ዓይነቶች አንዱ የስልክ ግንኙነት ነው፡፡ ከላይ በጠቀስነው መዝገብ ውስጥ ብቻ ክስ ሆነው የቀረቡትን የስልክ ግንኙነቶች እንመልከት፡-

  • 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ‹‹በ 2000 ተድላ ደስታ ከተባለ የሽብር ድርጅቱ አባልና አመራር ጋር በስልክ እና በፌስቡክ›› በማውራት
  • 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ዘመኑ ካሴ ከተባለ የግንቦት ሰባት ታጣቂ›› ጋር በጥር 14/2005 በስልክ በማውራት፤
  •  3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔ አለም ›› ጋር በየካቲት 29/2003 በስልክ በማውራት፤
  •  4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹የደ.ም.ሕ.ት. አመራር ከሆነው ጎይቶም በርሄ ›› ጋር ጥር 3/2006 በስልክ በማውራት፤ 
  •  5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔአለም›› ጋር ጥቅምት 14/2006 በስልክ በማውራት፤
  • 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ፣ የግንቦት ሰባት ክንፍ ከሆነው የአ.ዴ.ኃ.ን አባል ጋር ሕዳር 2003 በስልክ በማውራት፤

እነዚህ የስልክ ግንኙነቶች ያለሌላ ተጨማሪ ማስረጃ በብቸኝነት የክስ መመስረቻ መሆናቸው ደግሞ ክሱን ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ዜጎች የስልክ ግኑኝነቶችን በሙሉ እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል፡፡ በሽብርተኝነት በተጠረጠሩ ድርጅቶች ውስጥ በዐቃቤ ሕጉ ቃል ብቻ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎች ስለደወሉለት ብቻ የተደወለለት ሰው ‹‹አሸባሪ›› ተብሎ ይከሰሳል፡፡ ፈቅዶ ባልተደወለለት ስልክ ወንጀለኛ ነህ የሚባልበት አሰራር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስልም፡፡ አንዳንዶቹ የስልክ ጥሪዎች የተደረጉት ‹‹ሽብርተኛ ናቸው›› በተባሉ ድርጅቶች ውስጥ ባሉ እና በሚታወቁ ግለሰቦች ሳይሆን የአቃቤ ህግ ቃል ብቻ ያልሆነውን ነው ብሎ ስላቀረበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ሳይፈረድባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትም የዚያኑ ያክል ናቸው፡፡ በ2000 የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ አልወጣም ነበር፤ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችም አልነበሩም፡፡ ክሱ ላይ ግን በዚያ ወቅት የተደረገ የስልክ ግንኙነት ተጠቅሷል፡፡
በሁሉም የሽብር ክሶች ውስጥ copy/paste የተደረገች ውንጀላ አለች፤ ‹‹ራሱን [እከሌ ]ብሎ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ግንኙነት በመፍጠርና ተልእኮ በመቀበል ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ . . . ‹‹የምትል ነች፡፡ ይህች ቃል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ድርጊት ሳይጠቅስ የሚያስቀጣበት ውንጀላ  ነች፡፡ በዚሁ በነዘላለም መዝገብም ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሳለች፡፡ በስልክ አንድ ሰው ጋር ያወራሉ ከዚያ ተልእኮ ይቀበላሉ፡፡ ሽብር ማለት በቃ ይኽው ነው፡፡
“ሥልጠናዎች ሁሉ ሽብር ናቸው”
በነዘላለም መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 6ኛ እና 9ኛ ተከሳሽ(ዮናታን እና ባሕሩ) ክስ ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፡፡ይኸውም ‹‹ በመንግስት ላይ ያሉ ችግሮችን ለሕዝብ በተለያዩ የኢንተርኔትና የማህበራዊ ድህረ – ገፆች ላይ በመፃፍ ለግል ሚዲያዎች ግብአት የመስጠት ሥራ የሚሰሩ ቡድኖች አሉ፡፡ ለዚሁ ተግባር ተብሎ የወሰዱትን የኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ኮሙኒኬሽን ስኪል እና ሊደርሺፕ በመሰልጠን ተጠቅመዋል እናንተስ እንዲህ አይነት ስልጠና አትፈልጉም ወይ?›› በሚል አንደኛ ተከሳሽ ለሁለቱ ተከሳሾች ቀርበዋል የተባሉት ጥያቄዎች ወንጀል ተብለው ተፅፈዋል፡፡ ‹‹ሠልጥነዋል›› ተብለው በምሳሌው የተጠቀሱት ‹‹ቡድኖች›› ዞን ዘጠኞች መሆናቸው በሌላ ማስረጃ ተጠቅሷል፡፡ሥልጠናውን ዐቃቤ ሕግ 9ኛ ተከሳሽ ላይ ሲጠቅሰው መጀመሪያ ‹‹ተመሳሳይ ሥልጠና ለተመሳሳይ አላማ ›› ይልና ዝቅ ብሎ ‹‹የሽብር ድርጅቱን ተልዕኮ ለመፈፀም እንዲረዳቸው ባዘጋጁት ስልጠና ›› ይላል፡፡ የመንግስታችን ችግሮች መፃፍ ፣ ወይም ለመፃፍ መሰልጠን በምን መሥፈርት አሸባሪነት ተባለ?
“አብርሃም ሰለሞንን ማን መለመለው?”
የክስ መዝገቡ መጀመሪያ ላይ ‹‹[አብርሃም ሰለሞን] በ1ኛ ተከሳሽ  [ዘላለም] አማካኝነት ለሽብር ድርጅቱ በአባልነት ተመልምሎ . . . ›› ይላል፡፡ አንድ አንቀፅ ዝቅ ብሎ ደግሞ ‹‹[አብርሃምን] በአባልነት የመለመለው አንደኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር [እዮብ] አማካኝነት . . . ›› ይላል፡፡ አብርሃምን የመለመለው ዘላለም ወይስ እዮብ? (ብቸኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር) መልምሏል የተባለው አብርሃምን ብቻ አይደለም፡፡ 8ተኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማንም ጭምር እንጂ፡፡ እዮብ ሰለሞንን ሲመለምል ተናግሯል የተባለው ይህንን ነው፤
‹‹ኤርትራ ሀገር ግንቦት ሰባት የተባለ ጥሩ ድርጅት አለ፡፡ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሥልጠና ሠልጥነህ ከድርጅቱ ጋር ከተቀላቀልክ በኋላ ግንቦት ሰባት የሚሰጥህን ተልዕኮ ተቀብለህ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዋጋለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቡን በኃይል እየገዛ ነው ስለዚህ ታግለን መጣል አለብን፡፡ ››
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተጠርጣሪዎች ጋር ታስረው ቆይተው ኋላ ላይ ምስክር ለመሆን ሲስማሙ መለቀቃቸው የተለመደ ነው፡፡ የፀረ ሽብር ሕጉ ሽብርን ለማጋለጥ ለተባበረ ርሕራሔው ይኼን ይመስላል፡፡ ነገር ግን ክፍተት አለው፡፡ ተጠርጣሪዎች በአባሪዎቻቸው ወይም ሌሎች ላይ መስክረው መፈታት እንደሚችሉ ቃል ሲገባላቸው በሐሰትም ቢሆን ለማድረግ የሚስማሙበት ዕድል አለ፡፡ በዚህ መንገድ መልማዩ ምስክር ሆኖ የሚቀርብበት ተመልማዩ ላይ ይሆናል፡፡
በዚህ ዓይነት መንግስት ያልወደደውን ፖለቲከኛ (ዜጋ) ስልክ ሲደወል ደዋዩ አሸባሪ ነው በማለት፣ ወይም የራሱን ሰው ልኮ በማባበል ለ‹‹ሽብር›› መልምሎ ሲያበቃ መልማዩን ምስክር ተመልማዩን ተከሳሽ ለማድረግ ወይም ደግሞ በስጋት ሰብስቦ ካሰራቸው ሰዎች መሃከል ለነፍሳቸው ግድ የሌላቸው የሃሰት መስካሪዎችን እያሰለጠነ እየፈረደ ሊኖር ይሆን?!  

በሴት ተከሳሾች የመብት ጥሰት አቤቱታ ላይ “ፍርድ ቤቱ” ሌላ ቀጠሮ ሰጠ
በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ ለዛሬ

Edom Kassaye and Mahilet Fantahun

ተቀጥሮ የነበረው “የፍርድ ቤት” ውሎ የመብት ጥሰቱን አስመልክቶ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በጽሁፍ ለመስማት ነበር ፡፡ ነገር ግን እስር ቤቱ አስተዳደሮች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው የጽሁፍ ምላሹ ስላልተፈረመበት ማቅረብ አልቻልንም በማለት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ነኝ ብለው የቀረቡት ዋና ሳጅን ድሪባ ሰበታ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሳጅን ድሪባ የእስር ቤቱ የህግ ባለሞያ እና የሴቶች ክፍል ሰራተኛ ነኝ ፍርድ ቤቱ ከፈቀደ በቃል ምላሽ ልስጥ ያሉ ሲሆን አግባብ ያለው የአስተዳደር ሰው አይደሉም በሚል “ፍርድ ቤቱ” ሳይቀበላቸው ቀርቷል፡፡
በዚህም መሰረት “ፍርድ ቤቱ” የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር መልሱን በጽሁፍ ይዞ እንዲቀርብ ለየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡( March 4) በተያያዘ ዜና ዓቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ያለውንና ከወንጀል ክሱ ጋር አያይዞ ካቀረበው የማስረጃ ዝርዝር መካከል የሲ.ዲ ማስረጃውን በተመለከተ የተከሳሽ ጠበቆች እስካሁን ስላልደረሳቸው አንዲደርሳቸው በጽሁፍ ጥያቄ አቅርበዋል ፡፡ የጠበቆቸን ጥያቄ ተከትሎ አቃቤ ህግ የሲዲ ማስረጃዎቸቹን ለጠበቆች አንዲያደርስ “ፍርድ ቤቱ” ትዝዛዝ ሰጥቷል፡፡
የዞን9 ማስታወሻ – የሴት እስረኞች መንገላታት በተደጋጋሚ ተገልጾ እና ትእዛዝ ተሰጥቶበት ከመንግሰት በባሰ ጨቋኝ የሆነው “የቃሊቲው መንግሰት” አፈና ያልተሻሻለ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ የፓለቲካ እስረኞች አያያዝ የዞን9 ተከሳሾችን ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጋዜጠኛ ርእዬት አለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የሁሉም ጥያቄ መሆኑ መብት ጥሰቱ በተዘዋዋሪ መንግሰት የሚክደውን ፓለቲካ እስረኛ የለም የሚለውን ሃሳብ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠንካራ አርምጃ በመውሰድ በሌሎች ጉዳዬች ላይ ያጣውን እምነት አመኔታ እና ስልጣን ቢያንስ የታራሚዎቸን መብት በማስከበር እንዲያሳየው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በዚህ የተገለለ የጭቆና አያያዝ ውስጥ ሆነው አንኳን ፈገግታቸው ለአፍታም ያልተገደበው ሴት እስረኛ እህቶቻችን እንደሆነ ከጭቆናው በላይ መሆናቸውን ካስመሰከሩ ቆይተዋል፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንናገራለን !
ዞን9

ፍቃዴ ለቅቄያለሁ ያሉት ዳኛ ደግመው ተሰይመዋል! 

ለሶስት መቶ ቀናት በእስር ላይ የቆዬት ጦማርያን ለ20ኛ ጊዜ “ፍርድ ቤት” ቀርበዋል፡፡ 

ትላንትና የካቲት 11 ቀን ገዥው ህወሃት 40ኛ ልደቱን ባከበረበት በተመሳሳይ ቀን በነሶልያን ሽመልስ የክስ መዝግብ “ፍርድ ቤት” የቀረቡት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

“የፍርድ ሂደቱ” ጠዋት ሊጀመር ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ያለቅጥ ዘግይተው የተሰየሙት ዳኞች ተከሳሾቹ ለከሰአት ስምንት ሰአት ለሚጀምረው ችሎት አንዲገኙ ለከሰአት ተቀጥረው ነበር፡፡ ከሰአት ስምንት ሰአት ላይ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ባሉት ሰአታት ልደታ ፍርድ ቤት ጊዜያቸውን ያሳለፉት ጦማርያን ከሰአት በኋላ “ፍርድ ቤት” ቀርበዋል፡፡ ችሎቱ ላይ ባለፈው ቀጠሮ አቤቱታ ቀርቦባቸው አቤቱታውን “ፍርድ ቤቱ” ባይቀበለውም በገዛ ፍቃዴ ከችሎቱ ለቅቄያለሁ ያሉት ዳኛ ሸለመ በቀለ መልሰው ችሎቱን ሰብስበዋል ፡፡ ከችሎቱ ለመነሳታቸውም ሆነ ላለመነሳታቸው የተሰጠ ማብራሪያ ሳይኖር ከሁለተኛ ተከሳሽ ከጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ጀምሮ እያንዳንዳቸው ተከሳሾች በስም እየተጠሩ የተጠረጠሩበትን ወንጀልመፈጸም እና አለመፈጸማቸውን ቃል አንዲሰጡ የተጠየቁት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሲመልሱ

በፍቃዱ ሃይሉ – እኔ ክሱን ከአምስት ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ አንብቤዋለሁ ምንም የሚገባ ነገር አላገኘሁበትም ሲል ዳኛው አቋርጠውት አሁን ምንም አይነት ዝርዝር ውስጥ አልገባም በማለታቸው “የሽብር ወንጀል ለመፈጸም አላሰብኩም አልፈጸምኩት አልፈጽምም ሽብር ተፈጽሞብኛል” ሲል መልሷል፡፡ ከበፍቃዱ በማስከተል ቃሉን የሰጠው ጦማሪ ናትናኤል “ህግ የሚከበርበት አገር ቢሆን ኖሮ ዛሬ እዚህ ቦታ መቆም የነበረባቸው አሳሪዎቼ ናቸው ፣ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም “ያለ ሲሆን ጦማሪ አጥናፍ “ወንጀል አልፈጸምኩም” ፣ ጦማሪት ማህሌት “ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም” ብላ ቃሏን ስትሰጥ ጦማሪ አቤል በበኩሉ “ክሱ ግልጽ አይደለም” ሲል ዳኛው ምንም አይነት ተጨማሪ ነገር ሳያስፈልግ ቀጥታ ቃል እንዲሰጥ ማሰጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም አቤል “የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት የሽብር ተግባር አልፈጸምኩም አላሴርኩም” ሲል በቀጥታ ክሱ ላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ ጠቅሶ ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ጦማሪ ዘላለም በበኩሉ የተከሰሰበት ወንጀል አንዲብራራለት የጠየቀ ሲሆነ “ፍርድ ቤቱ” ወደኋላ አንመለስም የሚል ማስፈራሩያ በማሰማት በቀጥታ ቃሉን እንዲሰጥ ሲነገረው “የተከሰስኩበት ክስ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃሌን መስጠት አልችልም” በማለት በመናገሩ ቃሉን ሳይሰጥ ቀርቷል ፡፡ በህጉ መሰረትም ጥፋተኛ አይደለሁም አንዳለ ተቆጥሮ ተመዝግቧል፡፡
ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ -” ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም እኔ ነጻ ሰው ነኝ ” ስትል ጋዜጠኛ አስማመው “ወንጀል አልፈጸምኩም” ጋዜጠኛ ተስፋለም ደግሞ “እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም እኔ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም” ብሏል፡።

የእምነት ክህደት ቃል መስጠቱነ ተከትሎ አቃቤ ህግ ምስክሮቸን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሎ በጠየቀው መሰረት ከአርባ ቀን በኋላ ለመጋቢት 21-23 ለሶስት ቀናት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማቅረብ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የተከሳሾች ጠበቆች በበኩላቸው አለ የተባለው የሲዲ ማስረጃ ግልባጭ ስላልተሰጠን አንዲሰጠን ብለው የጠየቁ ሲሆን “ፍርድ ቤቱ” እንዲሰጣቸው ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የተከሳሾች አያያዝ 

ባለፈው ችሎት ወቅት ጦማሪ አቤል ዋበላ ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ መልስ አንዲሰጥ መጠየቁ የሚታወስ ሲሆን የጦማሪው ጠበቃ ተከሳሹ ከማረሚያ ቤት አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ችግሩን ስለፈቱት አቤቱታውን መቅረቱን ለ”ፍርድ ቤቱ” ተናግረዋል፡፡ ጦማሪ አቤልም በበኩሉ ተጨማሪ የመብት ጥሰት አስካልደረሰብኝ ድረስ ባለፈውን አቤቱታዬን ትቼዋለሁ ያለ ሲሆን ባለፈው ተቀምቶ የነበረው የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያም ተመልሶለታል ፡፡ ነገር ግን የሴት ተከሳሾች አያያዝ አንደአዲስ አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያያቸው ሰው ገደብ እንዳልተነሳ እና አሁንም በጥቂት ሰዎች ብቻ አንደሚጠየቁ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ በማቅረባቸው የእነሱን አያያዝ አስመልክቶ ማረሚያ ቤቱ መልስ አንዲሰጥ ለመጋቢት 18 ጠዋት ቀጠሮ ተሰጥቶ ችሎቱ ተጠናቋል ፡፡

የዞን9 ማስታወሻ 

ሶስት መቶ ቀን እስር እና ከሃያ ቀጠሮ በኋላ የተጀመረው ይህ መደበኛ “የፍርድ ሂደት” እንደተለመደው መጓተቱ ሳያንስ በአንድ ወር በላይ የሚፈጅ ቀጠሮ መሰጠቱ ለክሱ ፓለቲካዊነት አንዱ መገለጫ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ሶስት ወር በፈጀ ምርመራ ሂደት ውስጥ ተገኙ የተባሉትን ማስረጃዎች ለማቅረብ የ40 ቀን መዘጋጃ ጊዜ አንደማያስፈልግ ለማንም ሰው በግልጽ የሚታይ ሃቅ ነው ፡፡ በመሆኑም ባለፈው የቀረበው አቤቱታ ላይ አንደተገለጸው ዳኛውም ሆነ የፍትህ ስርአቱ አላግባብ መታሰራችን እና መከሰሳችን ሳያንስ አንድን “የፍርድ ሂደት” በማራዘም አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት መቀለጃ እየሆነ አንደሆነ እያሳዬን ነው፡፡ የዞን9 ነዋሪያንና አንባቢዎችም ይህ ፍትህ ስርአቱ ስም የሚደረግ ቀልድ አንደማይጠፋቸው አናምናለን ፡፡

የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በመልካም ጤንነት በጠንካራ ስነልቦና እና በራስ መተማመን ስርአቱን ፊትለፊት እየተገዳደሩ ያሉ ኩሩ ልበ ሙሉ ወጣት ዜጎች ናቸው ፡፡ የተለየ ሃሳብን በሚያራምዱ ጥቂት ወጣቶች የተሸበረውን መንግሰት የምናፍርበት ያህል በጓደኞቻችን አንኮራለን ፡፡

የዞን9 ኩራት ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በድጋሚ መልካም ልደት
ስለሚያገባን እንጦምራለን ፡፡ 

Blogger Befeqadu Hailu drawing by Melody Sundberg

ዞን9
#Ethiopia #FreeZone9Bloggers @FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsmamaw 

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለ16 ጊዜ ያህል ለስድስት ወራት ፍርድ ቤት የተመላለሱት እና ለ9 ወራት በእስር የሚገኙት የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ዛሬ ለ17ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል ፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን አንዲሰጡ የተጠበቀ ቢሆንም በተቃራኒው ተከሳሾች አቤቱታ አለን አቤቱታችን የእምነት ክህደት ቃል ከመስጠታችን በፌት መቅደም አለበት ብለው ተከራክረዋል፡፡ ዳኛው ዛሬ የእምነት ክህደት ቀጠሮ ነው ሌላ አቤቴታ አንቀበልም ቢሉም ፍርድ ቤቱ የራሱን ቃል አጥፏል ስለዚህም የመሃል ዳኛው አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብታችንን ስለነፈጉን እንዲሁም ራሱ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትእዛዝ ሽሮ ያልተሻሻሉ ክሶችን በማካተት መከላከል የማንችልበት ሁኔታ ላይ ስላስቀመጡን መሃል ዳኛው የፍትህ ሂደቱን ዳኛ ሸለመ በቀለ ከቦታቸው ካልተነሱልን የእምነት ክህደት ቃላችንን ለመስጠት አንቸገራለን የሚል አቤቱታቸውን አቅርበዋል ፡፡
በዚህም መሰረት አቤቱታው ያልተጠበቀ የሆነባቸው ዳኛ የመገረም ፌት ያሳዬ ሲሆን አቤቱታው ላይ ለመወሰን ለነገ ጠዋት በ3 ሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ችሎቱ ነገ ጠዋት ለ18ተኛ ጊዜ ደግሞ ይሰየማል፡፡


አዲስ ዜና 
ሶስት ዞኖች እነዳሉት የሚታወቀው የቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በአስቸኳይ አራተኛ ዞን እየተገነባ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በሶስቱ ዞኖች ውስጥ በአማካይ ከ100 በላይ ያልተፈረደባቸው የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን የሚከታተሉ እስረኞች ሚገኙበት ሲሆን አሁን አራተኛው ዞን ግንባታ በፍጥነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 

News update – Ethiopian government prison administration is expanding kilinto prison. according to the sources the prison is establishing new 4th Zone in addition to those three zones existing now. Currently, more than 100 male cell mates are under custody in each existing Zone.

‪#‎FreeZone9bloggers‬ ‪#‎FreeEdom‬ ‪#‎FreeTesfalem‬ ‪#‎FreeAsemamaw‬ ‪#‎Ethiopia‬

ሰበር ዜና —–ክሱ ተሻሻሏል ሲል “ፍርድ ቤቱ” ወሰነ smile emotለስድስት ወራት የክሱን ፎርማት ይዘትና ህጋዊ መሰረት ሲያጠና የከረመው “ፍርድ ቤት” ክሱ ተሻሽሏል የሚል ብያኔውን ዛሬ በተደረገው 16ተኛ የዞን9 የጦማርያን እና ጋዜጠኞች ችሎት ላይ በንባብ አሰምቷል ፡አንዲሻሻሉ ከታዘዙት አራት ነጥቦች መካከል ሶስቱ መሻሻላቸውን አይቻለሁ ያለው “ፍርድ ቤቱ “
1. ቡድን በሚል የተጠቀሰው ተከሳሾቹ ያቋቋሙት የህቡህ ቡድን አንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተረድቷል ቡድኑ ዝርዝር ሁኔታ በማስረጃ መስማት ወቅት ተቀባይነት ሊኖረው ወይም ደግሞ ውድቅ ሊሆን የሚችል ስለሆነ ክሱ ውስጥ መካተት አለበት ሲል ወስኗል ፡፡
2. ስልጠናን አስመልክቶ ‹‹ተከሳሾች ከ2004 ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በግንቦት 7 አመቻችነት ስልጠና መውሰዳቸውን የተሻሻለው ክስ አስፍሯል፡፡ ስለሆነም ጊዜውና በማን የሚለው ስለተጠቀሰ ክሱ መሻሻሉን ፍርድ ቤቱ ተቀብያለው ብሏል፡፡
3. ለሽብር ተግባር ዋለ የተባለውን 48.000 ብር አስመልክቶ ክሱ ውጨ አገር የሚገኙ የቡድኑ አባላት ናቸው በሚል ስለሚያብራራው ተቀባይነት አግኝቷል ያለ ሲሆን ስራ ክፍፍልን አስመልክቶ በቂ ዝርዝር ባለመቀረቡ ከስራ ክፍፍል ፍሬ ነገር ውጪ ያሉት የክሱ ፍሬ ነገሮች ተካተው ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለመሆናቸውን ፍርድ ቤቱ ጠይቋል፡፡
በተከሳሾች ጠበቃ የፍርድ ቤቱ የሶስቱን ፍሬ ነገሮችን መቀበል ያልተጠበቀ መሆኑን ገልጸው ከደንበኞቻቸው ጋር ለመመካከር ጊዜ ጠይቀዋል ፡፡ በዚህም መሰረት ችሎቱ ለከሰአት 8.00 በድጋሚ ተቀጥሮ የጠዋቱ ችሎት ተጠናቋል፡፡
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ብዙም ያልተገረሙት ተከሳሾች ወንዶቹ የምሳ እረፍታቸውን በልደታ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲያሳልፉ፣ ሴቶቹ ወደ ቃሊቲ ተመስደው ተመልሰዋል፡። በጠንካራ መንፈስ ላይ የነበሩት እስረኞች ብይኑ በችሎት ሲሰማ ከፈገግታ እና ሳቅ ባለፈ ምንም አይነት መደናገጥ አልታየባቸውም ፡። በቆይታቸውም እርስ በርሳቸው ሲያወሩ ሲወያዬ እና ወዳጅ ዘመዶችን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል፡፡
በከሰአቱ ችሎት በቂ የመወያያ ግዜ ለማግኘት ስላልተቻለ ጠበቃ አምሃ አጭር ቀጠሮ በመጠየቃቸው ችሎቱ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ለጥር 28 ተቀጥሮ ተጠናቋል፡፡
ማስታወሻ
የዞን9 ጦማርያን ፍርድ ቤቱ እድሉን ተጠቅሞ የፍትህ ስርአቱን ነጻነት የሚያረጋግጥበትን ወርቃማ እድል አንዲጠቀም ደጋግመን መጠየቃችን ይታወሳል፡፡ ከማስረጃው 90 በመቶው ጦማራችን ላይ የወጡ ጽሁፎች በመሆናቸው ክሱ ሃሳባቸንን በነጻነት በመግለጻችን ብቻ የተቀናበረ ፓለቲካዊ ክስ መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል ፡፡ አሁንም አልረፈደምና ዞን9 ጦማርያንን እና ጋዜጠኞችን በነጻ በማሰናበት የፍትህ ስርአቱ ራሱን እንደቁምነገር የሚያስቆጥርበትን እድል አንዲጠቀም ደግመን እናሳስባለን፡፡ የፍትህ ስርአቱ መስተካከል ከጦማርያኑ እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ከታሰሩለት አገራዊ አጀንዳ አንዱ ነውና !

አብርሃም ሰለሞን ይባላል ፡፡ በነ ዘላለም ወርቃለማው የክስ መዝገብ ከአራቱ የፓለቲካ አመራሮች በተከሰሱበት መዝገብ ስድተኛ ተከሳሽ የሆነው አብርሃም ሰለሞን መምህር ነበር ፡፡ አብርሃም ከመታሰሩ በፊት ቤተል ትምህርት ቤት መምህር ነበር ፡፡ በሞያውም የፈጠራ ስራዎች ላይ ማተኮር ይወድ ስለነበር አገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሽልማት አሸናፊ በመሆን ከተመረጡ መምህራንም መካከል አንዱ ነው ፡፡ 
ነሃሴ ላይ ከታሰረ በኋላ ጥቅምት ላይ በተደረገው አገር አቀፍ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ሽልማት ተሸላሚ በመሆኑ በጥቅምት ወር በተደረገው የሽልማት ስነስርአት እናቱ ወክለውት ሽልማቱን ተቀብለዋል ፡፡ ይህ በሽብር የተከሰሰ ወጣት አስተማሪ አይሲቲን በቀላሉ እና በሚገባ መልኩ ማስተማር የሚረዳ የፈጠራ ውጤት ባለቤት በመሆኑ ነው ሽልማት ያገኘው ፡፡ የሽልማቱ ቲሸርት እና ሜዳልያን ይዘው ሊጠይቁት የሄዱት እናቱ ሜዳልያውን ማስገባት ባይችሉም ቲሸርቱን አስገብተውለት ተመልሰዋል ፡፡ በማስተማር እና በፈጠራ ስራ የተሰማራው ይህ መምህር አንድም እውነተኛ ሽብተኛ ተከሶበት በማያውቀው ክስ ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ዞን2 ይገኛል፡፡ በእርሱ የመምህርነት ደሞዝ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦቹም እሱን ቅሊንጦ ድረስ እየሄዱ በመጠየቅ እየተንከራቱ ይገኛሉ ፡፡ 

ቢያንስ ኢንተርኔት ላይ ሼር በማድረግ የማናውቃቸው ብዙዎች ለሚከፍሉት ዋጋ እውቅናን እንስጥ

1.    ቶሎ እርምጃ ወስደን ነገሮች በፍጥነት ባይከናውኑ ኖሮ ይህንን መልአክት አሁን ከቅሊንጦ ሆኜ የምጽፈው ይሆን ነበር፡፡


ዓርብየአዳማ ከሰዓቱ ሙቀት ያየለ ነበር ለሥራ ነጠል እንድታደርገኝ መርጬያት የነበረችው ጥግ ሙቀት ሲያይልባት ወጣ ገባ ማለት ጀምሬያሁ ቅዳሜ ማታ ቴዲ አፍሮ በሚያዘጋጀው ኮንሰርት አንድንገባ አዲስ አበባ እየደዋወልኩ ስጠይቅ  ኤዲ (ኤዶም ካሳዬ)  እንደማትገኝ ስትነግረኝትንሽ ቅር ብሎኝ ነበር ቢሆንም ቀን ቴስትኦቭ አዲስ የምግብ ፌስቲቫል ላይ ሳልናገር ተከስቼ የዞን ዘጠኝ ጓደኞቼን እና ሌሎችጓደኞቻችንን ሰርፕራይ ለማድረግ ዱለታ ላይ ነኝ፡፡

የቀኑ መገባደጃ ላይ አንድ አጭር የስልክ መልእክት ወደ ስልኬ ገባ ፡፡ዞላ(ዘላለም ክብረት) ነበር ፡፡ ስልክ መልእክቷ  እጥር ምጥንያለች ብትሆንም አንዳንድ ጊዜ የዞን9 አባላት ኦንላየን ያለው የግል ቡድናችን ውስጥ ውይይቶቻችን በድምጽ ብልጫመወሰን ሲኖርብን  ወይም ደግሞ የሞቀ ክርክር እየተደረገ አንድ ሰው ኦፍላየን ሲሆን “ኀረ ወደኢንተርኔት ና እና ሃሳብ ስጥ” አይነት ነገር መልእክት ስልካችን ላይ እንላላካለን፡፡ ከዞላ የመጣውም አጭር መልክት ተመሳሳይነት ነበረው፡፡  ግን ይሄኛው በጣም ያጠረ ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከዞላ ድጋሚ ሌላ ቴክሰት ተደገመ ፡፡  “they may arrest me” ይላል መልእክቱ ፡፡በድንጋጤ ወደ ኢንተኔት ስመጣ ሶሊ በሁሉም በኩም መልእክት ስትልክ ደረስኩ ፡፡ አብረው የነበሩትአጥኔክስ እና የበፍቄ ስልካቸው አይመልስም፣ ማሂ ከቢሮ ተወሰደች፣ አቤልም እንደዛው፡፡ የሆነ የከፋ ነገር እየተከናወነ ነው ዘግይተው ነው አንጂ እኔ መድረሳቸው እንደማይቀር ተስማማን፡፡


የዚያን ሰሞን ወከባችን ሲበዛና ምን ይሻላል የሚለው ውይይት ሲደጋገም ዞላ ‹‹ምንም በሌለበት ኢሕአዴግ እኛን ካሰረ አብዷል ማለት ነው›› ብሎ ይከራከር ነበር፡፡አሁን በአይኔ የማየው የመታሰር ስጋት መልእክት የመጣው ከዞላ ነው፡፡ የማህበራዊሚዲያን ፈጽሞ የማያውቀው ደህንነት ናቱን ሲያዋክበው “ናቲ ለደህንነትየትውውቅ ኮርስ እየሰጠ ነው” ብለን አንቀልድበትም ነበር፡።  ናቲን አብረኽን ስራ የሚል ማስፈራራትም ጉትጎታም ሳይቀር ሲያዋክበው ነበር ፡፡ ጓደኞቹን አሳፎ ከሰጠ እሱ ምንም እንደማይሆን ሊወተውተውም ሞክሯል፡፡  አሁን የዞላን ንግግር እና እርግጠኝነት ሳስበው በእኛእስኪደርስ ጠበቅን እንጂ ካበዱስ ቆይተው ነበር እላለሁ፡፡ 

የዛው ሰሞን  የዞን 9 አባላት የተጠናከረውን የደህንነቶች ክትትልተንተርሶ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የመታሰር እድል ያላቸው በሚል ከፋፍለን  ለማስቀመጥ ሞክረን ነበር ፡፡ አገር ቤት ካለነው የመጀመሪያውን ደረጃ አጥናፍ እና በፍቄ ሲይዙ ማሂ እና እኔ መታሰር ስጋታቸው  የመጨረሻው ላይነው ብለን ታስበን የነበርነው ነን ፡፡ ማሂ መያዝ ዜና ይሄንን ግምታችንአፈር ድሜ ያበላ ነበር፡፡ ከዚህ ዜና በኋላ ኦን ላየን ካሉ ጓደኞቼ ነገሩን በማጣራት  ፈላጊዎቼ እስኪመጡ ሳልጠብቅ  ከስራ ቦታ ላፕቶፔን ብቻ ይዥ ተነስቼ ወጣሁ ፡፡ ስራ ቦታ ሰው ድንገት ከፈለገኝ ለስራ ወደ አዋሳ መሄዴን እና ቶሎ አንደምመለስ ተናግሬ ነበር ፡፡ ወደቤት መሄድ የማይቻል ሃሳብ ሆነ ቀኑም እየተገባደደ በመሆኑ ከስራ ቦታዬ ዞር ያደርገኛል ወዳልኩት አካባቢ ላፕቶፔን ይዥ በፍጥነት አቀናሁ ፡፡ ሥልክ ማጥፋት እና መቀየር፣ በሌላ ሥም አልጋ መከራየት፣ እንቅልፍ አልባ እጅግ በጣም ረጅም ሌሊት በአምባገነኖች በትር በሃዘን ልባችን የተሰበረበት ምሽት ነበር፡፡ የእኔ ነገር ያንን ምሽት ገና ስላለየለትም የኤዶም ስልክም ዝግ በመሆኑ ግራ እየተጋባንም( እስሩ ለዞን9 ብቻ ነው የመጣው የሚል የዋህ ሃሳብም ነበረን)  አንቅልፍ በአይናችን ሳይዞር ነጋ፡፡ ይህ ሌሊት ባለፈ በማግስቱ በእለተ ቅዳሜ አንዲት ነጭ ሸሚዝ እንደለበስኩ ላፕቶፔን ብቻ አንጠልጥዬ የጎረቤት አገር ኤርፓርት ላይ ሶል ተቀበለችኝ ምንም አይነት ኮምንኬሽን ስላልነበረኝ የኤዶምን መታሰር እርግጥ ዜና እና  የአስማማውን መታሰርም እዛው ሰማሁ፡፡  ቶሎ እርምጃ ወስደን ነገሮች በፍጥነት ባይከናውኑ ኖሮ ይህንን መልአክት አሁን ከቅሊንጦ ሆኜ የምጽፈው ይሆን ነበር፡፡  (በመትረፌብዙ ባለማድረጌ ከእነሱ ጋር መሆንን ብናፍቅም)፡፡  

 ”   ከጥቂት ሰአታት በኋላ የእግር ኮቴ ስንሰማ ተሽቀዳድመን በቀዳዳ ስናይ ማህሌትን ወደ ሌላ ክፍል ሲያስገቧት አየሁ ፡፡ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አለቀስኩ “


አርብ እለት መስሪያ ቤቴ ጎተራ ስደርስ 1.30 አካባቢ ነው በዚያ ጠዋት ቢሮ መግባት ስላልፈለኩ ለአንድ ሰአት ያህል ትዊተር ላይ ወሬ ስለቃቅም ቆየሁና 2.30 ላይ ቢሮ ገባሁ ፡፡ ጠዋቱ የተለየ ስራ የለውም ነበር የእቅድ ዶክመንቶች ማገላበጥ የስልጠና ዝግጅት እና የመሳሰሉትን ስሰራ ቆየሁ ፡፡ አዲስ ሰራተኛ ስለሆንኩ ብዙውን ጊዜዬን የስራውን ባህሪይ ለማወቅ ነው የማጠፋው ፡፡ ምሳዬን ከበላሁ በኋላ የምሳ እረፍት እስኪያልቅ ከሶሊ ጋር ስካይፕ አወራን፡፡  ከሰአት በኋላ አንዲት የስራ ባልደረባዬ መጥታ ደሞዝ መውጣቱን እና አዲስ ጭማሪ መኖሩን ነገረችኝ ፡፡ አዲስ ደሞዝ ጭማሪ ላይ መጣሽ እድለኛ ነሽ እያሉኝ በደስታ የተሞላ የቢሮ ካባቢ ላይ ስንሳሳቅ ቆየን፡፡  10 ሰአት አካባቢ አንድ ከአመታት በፌት ትምህርት ቤት የማውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የደህንነት ሰራተኛ ነኝ እያለ የሚያዋራኝ ወዳጄ ደወለልኝ፡፡ በዚያን ሰሞን በዞን9 አባላት ጓደኞቼ ላይ አንድመሰክር አንደ ጓደኛ አንደመምከር አንደደህንነት በማስጠንቀቅ ሲያባብለኝ ከርሟል፡፡  አንገናኝ ሲለኝ መልሼ እደውልልሃለሁ ብዬው ዘጋሁት ፡፡ ከዚያ አንዲት ሴት ጓደኛዬን ከቢሮ ከመውጣቴ በፌት የት አንደሆነች ጠይቄያት ብሄራዊ አካባቢ መሆኗን ስትነግረኝ ሃሮ ካፌ አንገናኝ ብያት ዘጋሁት ፡፡ ስካይ ላይ ከሶሊ ጋር ስለደሞዝ ጭማሪ እና የመሳሰሉት አውርተን ማታ እቤት ስገባ ትዊተር ላይ እናወራለን ብያት ተሰነባብተን ከቢሮ ለመውጣት ተዘጋሁ፡፡ ከመውጣቴ በፌት የእስክንድር ጽሁፎች ስብስብ ከሆነው ፒዲኤፍ ላይ ቀንጭቤ ትዊተር ላይ ለጥፌ መውጣቴ ትዝ ይለኛል፡ እየወጣሁ እያለ ደህንነቱ ጓደኛዬ ድጋሚ ደውሎ አንገናኝ አለኝ ፣ ብሄራዊ እየሄድኩ አንደሆነ እና ሰው አንደቀጠርኩ እዛ ከመጣ አንደማገኘው ነግሬው ዘጋሁት፣ ሃሮን አላውቀውም ብሎ ጣፋጭ ካፌ ልንገናኝ ተስማማሁ፡፡


ብሄራዊ ስደርስ ጓደኛዬ ስላልደረሰች ጣፋጭ ካፌ  እሱን አንደማገኘው እና ስትደርስ አንድትነግረኝ ነግሬያት ወደጣፋጭ ካፌ ገባሁ ፡፡ ቤቱ በጣም ሙሉ ነው ስደውልለት ትራፌክ ይዞኝ ነው መጣሁ አለኝ፡፡ ከአንድ ከ30 ደቂቃ በኋላ መጣ፡፡ ፌቱ ላብ በላብ ሆኗል፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ የትምርህት ቤት ወዳጄ አብሮኝ የበላ አብሮኝ የጠጣ አብረን የሳቅን ብዙ ነገር ያወራን ነው ፣ ለደህንነት እሰራለሁ ከማለቱ ከ2 አመት በፌት ጀምሮ በደምብ ነው የማውቀው) ስለነፍሰጡር ባለቤቱ ደህንነት ጠየኩት ደህና ናት አለኝ፡፡ ፌቱ ግን መረበሽ ይታይበታል፡፡ ያዘዘውንም ማኪያቶ ሳይጠጣ ሂሳብ ከፍሎ ለመሄድ መዘገጃጀት ጀመረ ፣ ለምን እንደፈለገኝና ምን እነዳጣደፈው ስጠይቀው ክላስ አለብኝ መሄድ አለብኝ አለ፡፡ቀና ስል በመስኮቱ ማዶ አንድ ሰሞን ሲያናግረኝ የነበረ አንድ ሌላ የደህንነት አባል አየሁ ያን ጊዜ የሆነ ነገር አንዳለ ጠረጠርኩኝ |፡፡ ወዲያው ስልኬ ጮኽ።  ሶሊ ነበረች ( ያኔ ስለእስሩ ሰምታ ቼክ ልታደርገኝ አንደነበር አላወኩም) ስልኬን ይዜ ስነሳ ተከትሎኝ ስልክ የሚያወራ መስሎ አጠገቤ መጣ፡፡ ደህና ነኝ መልሼ እደውልልሻለሁ ብያት ዘጋሁት ፡፡


ወዲያው ልሂድ ብሎ ወጣ ጣፋጭ በር ላይ ተሰነባበትን ፡፡ ወዲያው አስፓልቱን ስሻገር አንድ መኪና መንገድ ዘጋብኝና ሁለት ተራ ወንበዴዎች የመሰሉ ሰዎች አንድገባ አዘዙኝ፡፡ አልገባም አልኩኝ ፡፡አንደኛው እጄን ጠምዝዞ አስገድዶ ወደመኪናው መራኝ ያኔ መከራከሩ እንደማያወጣ ገባኝ፡፡ ከኋላ አስገብተውኝ ግራና ቀኝ ተቀመጡ፡፡ መኪናዋን ይኸው የትምህርት ቤት ወዳጄ ይዟት እንዳየሁ አስታወስኩ፡። ቆሻሻና ዳሽ ቦርድ የሌላት  መኪና ናት፡። ከነሹፌሩ የቀን ስራ ሲሰሩ ውለው ያላባቸው የሚመስሉ ሶስት ወጣቶች አሉ፡፡ ጋቢና ያለው ወጣት “ኤዲ አንዴት ነሽ ?” አለኝ ጸጥ አልኩኝ፡፡ ፓሊስ ጣቢያ ለጉዳይ አንደፈለጉኝ እና ቶሎ አንደምለቀቅ ተናግሮ ሊያረጋጋኝ ሞከረ፡፡  ሹፌሩ ያለምንም ማቅማማት ጥቁር አንበሳ እና ባንኮዲሮማ ህንጻ ጋር ያሉትን መብራቶች እየጣሰ ጉዞ ወደፒያሳ ሆነ፣ ምን እነዳጣደፈው እንጃ ።። ቤተሰቦቼ ጋር አንድደውል ይፈቀድልኝ ብልም ስልኬን ወስደው ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ ፡፡ ማአከላዊ ስንደርስ 12.50 አካባቢ ሆኗል፡፡ መደበኛ ምዝገባ ተደርጎልኝ ንብረቶቼን አስረከብኩ ፣ እርቃኔን ከሆንኩ በኋላ ቁጭ ብድግ እያልኩ ሰውነቴ ሁሉ ተፈትሿል፡፡ ከታሰሩ ሴቶች ጋር ስቀላቀል እራትና የሌሊት ልብስ ሰጡኝ፡። ከጥቂት ሰአታት በኋላ የእግር ኮቴ ስንሰማ ተሽቀዳድመን በቀዳዳ ስናይ ማህሌትን ወደ ሌላ ክፍል ሲያስገቧት አየሁ ፡፡ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አለቀስኩ ፡፡ ቤተሰቦቼ ልጃችን ምን ዋጣት ብለው አንዴት አንደሚነጋላቸው እየተጨነኩ ነጋ፡፡


“I saw Mahlet being taken to another room, I cried for the first time” – Edom Kassaye


That Friday morning I spent an hour on updating myself on Twitter and entered office at 8:30 AM. Since I was a new employee, I spend much of my time in understanding my job’s description. After I ate my lunch, I skyped with Soli.  In the afternoon, a colleague came and informed me that the salary is released and there is also a new incremental change in our salary. My colleagues shared their happiness with me and congratulated me for being a staff at this time. Around 4 PM a friend of mine, who is my school friend years ago and who now said he is working as security agent for the government, called and asked me to meet him. I hang up the call by letting him  know that I will call him back. Before I get off from work, I called to my friend and agreed to meet around National Theater at Haron Cafe. I had a brief skyping with Soli and informed her about the incremental change in our salary and had an appointment with her to talk through twitter when I get home. Lastly, I twitted a quote from Eskinder’s writing, and then, I got off from work. While I was in my way to meet my friend, my friend- the security agent-called me. I informed him about my appointment because he insisted I agreed to meet at Tafac’h Cafe.  
     

When I arrived at the Café, he was not around.  He came after 30 minutes. he was sweating. (Btw this person was a good friend of mine with whom I had good times for the last two years, I had always considered him as a friend)  I asked him about his pregnant wife and he answered that she is doing good. Yet, from his face I learned that he was disturbed.  Before he finished his Macchiato, he wanted to pay the bill and go. When I scanned the surrounding, I saw another security agent, who had been contacting me and suspected that there is something going on. In meantime, Soli called me and when I try to talk with her a bit away from him, he followed me as if he is also speaking through phone.  So, I informed Soli that I will call her back and hang up the phone.( At that time, I did not know that Soli was aware of the crackdown and she called me to check the situation I am in.)


 When I crossed the main traffic road, after finished talking to him, a car closed my way and two security agents-who look liked like gang of robbers- asked me to enter into the car. But I denied. One of them wringed my hand and forced me in the direction of the car. They forced me to enter the car in the backseat in the middle of two of them. I remembered that my school friend used to drive this car.

The car was very dirty, so us my detainers. There were three security agents in the car, who sweated as if they spent the whole day as daily laborers. The guy, who sat nearby the driver, asked me “Edi, how are you doing?”. I remained silent. He tried to cool me down by saying that they want to talk to me at the police station and I will be released sooner.I asked them to call to my family but they denied me and confiscated my phone. It was around 6:50 PM when we arrived at Me’akelawi. I went through regular registration, submitted all my belonging materials, and investigated while I was naked. When I joined the women inmates, they gave me night close and a dinner. After few hours, we heard footsteps and when I saw through a hole, I saw mahlet being taken to another room. Then, for the first time since I get detained I cried. I was stressed by thinking of what my family would think of my disappearance and did not able to sleep the whole night. 


1.    እናቴ ስትገባ ቤቱ በፓሊስና በደህንነት ተከቦ እኔም ፓሊሶች ይዘውኝ ስታይ በጣም ደንግጣ ራሷን ስታ ወደቀች  

አርብ እንደማንኛውም የስራ ቀን ታናሽ እህቴን ስሜ ከቤት ወጣሁ፡፡ የዚያን እለት ያለወትሮው የወረዳችን ሰራተኛ ቤት መጥቶ መጽሃፍ አንድገዛለትና ከስራ ስወጣ ይዥለት አንድመጣ ከስራ የምወጣበትን ሰአት ጠይቆኝ ነበር፡፡ ተስማምቼ የመጸሃፉን ርእስ ነግሮኝ ገዝቼልህ እመጣለሁ አልኩት ፡፡ የምመለስበትን ሰአት ሰምቶ ሄደ፡፡ በጣም ያልተለመደ ነገር አንደሆነ ተሰምቶኝ አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ (ያንን ሰው ከዚያ በኋላ አላየሁትም መልእክትም አልደረሰኝም) ፡፡ በእለቱ  አሁን በእስር ላይ የምትገኘው የርእዮት አለሙ እህት  ቹቹ ጋር ተደዋውለን በማግስቱ የፕሮፌሰር መስፍን ልደት ስለነበር ልደት ለማክበር አንደምንሄድ ተስማማን ፡፡ ስጦታውንም አብረን ለመግዛት ተቀጣጠርን፡፡


አርብ የምሳ መውጫ ሰአት በጊዜ ስለሆነ በጊዜ ወጥቼ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ሄደን የመጨረሻውን ምሳዬን ጣይቱ ታደምኩኝ፡፡ ከሰአቱ ምንም የተለየ ነገር አልነበረውም ፣የተለመደውን ቢሮ ስራ ስሰራ ቆየሁ ለአንድ ጓደኛዬ ስልክ ቴክስት መላኬ ትዝ ይለኛል አሁን  የላኩትን መልእክት ይዘት ሳስበው  ለተወሰነ ግዜ አንደማንገናኝ ታውቆኝ ነበር ማለት ነው እላለሁ፡፡  በግምት ከቀኑ 10-10.30 አካባቢ ሁለት ሲቪል የለበሱ ወንዶች ቢሮዬ ገብተው እንደሚፈልጉኝ ነገሩኝ፡፡ ከቢሮ ይዘውኝ ወጡና በወንጀል አንደምፈለግ የሚገልጽ የፍተሻ ማዘዣ አሳዩኝ፡፡ ወረቀቱ ላይ የአቤሎ የበፍቄን የአጥናፍ እና የናቲን ስሞች አየሁ ፡፡ ውጪ ሰንወጣ ደግሞ በተጨማሪ ሎሎች አራት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ውጪ ቆመው ነበር፡፡  ከዚያ የቆመው የፖሊስ ፒክ አፕ መኪና ውስጥ አስገቡኝ ውስጡ አራት የታጠቁ ፓሊሶች እና እኔ ሆነን መኖሪያ ቤቴን ለማስፈተሽ ጉዞ ወደ ቤተሰቦቼ ቤት ሆነ፡፡  ወደኋላ ሳይ በቤት መኪና ሆነው የሚከተሉን ሲቪል ለባሾችም ነበሩ ፡፡

ስነደርስ ተቆልፈው የነበሩትን የጊቢና የቤት በሮች ከፍተን ገባን እነሱም ፎቶ ማንሳት ጀመሩ ፡፡ በሰአቱ ከስራ ወደቤት የገባ ማንም የቤተሰብ አባል አልነበረም ፡፡  በግምት ከአንድ ከ30 ደቂቃ በኋላ እናቴና አባቴ መጡ ፡፡ እናቴ ስትገባ ቤቱ በፓሊስና በደህንነት ተከቦ እኔም ፓሊሶች ይዘውኝ ስታይ በጣም ደንግጣ ራሷን ስታ ወደቀች፡፡ ከዚያ በኋላ ጊቢው ረብሻ በረብሻ ሆነ ፡፡ የሰፈር ሰዎች በሙሉ ነበሩ ፡፡ ፈተሻው ሲያልቅ ልብሷን አዘጋጁላት ብለው ለቤተሰቦቼ ነገሯቸው፡። ልብሴ ተዘጋጅቶልኝ ሰፈር ሰውና ቤተሰብ ለቅሶ ታጅቤ ከወላጆቼ ቤት በፓሊስ መኪና ወጣሁ ፡። ጉዞ ወደ ማእከላዊ ሆነ ።


ፒያሳ አካባቢ ስንደርስ አንግዳ የሆነ የመረበሽ ስሜት ተሰማኝ ምናልባትም ማእከላዊ እየቀረበ መምጣቱም እስሩም እውነት መሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡ ማእከላዊ ስንደርስ መሽቷል፡። ተፈትሼ ስገባ ማእከላዊ ውስጥ ለስምንት ወራት የቆዬ ሁለት የሶማሌ ክልል ተወላጅ ተቀበሉኝ ፡፡ እነዚህ ልጆች በማእከላዊ ቆይታዬ አላማጅና አጽናኜ ሆኑ ፡፡


As any working day, on Friday I kissed my younger sister and left  home for work. In that day, one of the employee of our Worda administration office came and unusually asked me to buy a book for him.and healso asked me when I will get off from work. I agreed with his request and collected the title of the book and informed him my returning time after work. I now remember that I felt that it was very strange request (I did not see this person again nor received any message from him).  Later on, I called to Chuchu, a younger sister of the imprisoned Journalist Reeyot Alemu, to buy a gift for Prof. Mesfin since the next day was his birthday. We have agreed to go together to celebrate his birthday.


I had my last lunch with a friend of mine at Taitu Hotel in Piassa. I spent my afternoon while working my usual task. I remembered that I sent a text message for one of my friend. When I thought about the content of my message now, I feel  that I was unconsciously knew that we might not meet again. When it was around 4:30 Pm, two security agents, who wore civilian dress, came and told me that they want to talk to me. While I was in my way to get out off from my office, they gave me a searching warrant. On the warrant, I was able to see my friends name particularly Abelo, Befeqe, Atnaf and Nati. When we went out of my office, I saw additional four security agents, who were in civil dresses. They let me to enter a police pick up car and there were four militant police and went to home for searching. When I try to see the surroundings, I learned that there are security agents who followed us in private vehicles too.


When we arrived home, I opened the doors and they started taking pictures. At that moment, my families are not yet back from work. After half an hour, my mother and father came. When my mama entered home and realized that there were police officers and I was encircled by security agents she was stroked and failed down. After that there was a huge disruption. All our neighbors came to our home. After the search was completed, the police officers ordered my family to prepare my cloths. After my family prepared my cloths, I entered into the police vehicle while my neighbors and family members were crying.


When we were around Pissa, I felt some distribution feeling. May be it is because that I was near to Me’akelawi and I realized that my detention became true. It was too late when we arrived at Me’akelawi. After I went to through the procedural searching and regulation, I meet two women, who are from Somali region, these women became my helper and source of comfort in my stay there.


                         

        

1.    ‹‹በእውነት ማዕከላዊ ስገባ እረፍት ነው የተሰማኝ››


አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ቢሮዬ ውስጥ ከአንዲት ህንዳዊት መምህርት ጋር እያወራሁ፣ ስለ ህንድ ባህል እየነገረችኝ ነበር፡፡ የፌስቡክ እና የትዊተር ገጾቼ እንደተከፈቱ ናቸው፡፡ ያን ዕለት ክላስ አልነበረኝም፤ ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በነበረው የተቃውሞ ሁኔታ ምክንያት አልገቡም ነበር፡፡ የአመቱ ክላስ እየተገባደደ ስለነበር በቀጣይ ክላስ ላይ ለተማሪዎቼ የምሰጣቸውን አሳይመንት አዘጋጅቻለሁ፡፡

ከህንዳዊቷ መምህርት ጋር እያለሁ አንድ የግቢ ጥበቃ ባልደረባ (የእኔ ተማሪ ነው፤ ህግ ይማራል) ቢሮየ መጥቶ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እንደሚፈልጉኝ ነገረኝ፡፡ እኔም እሺ ብዬ ለመሄድ ስዘጋጅ አንድ ወዳጄ  ማሂ መያዝዋን ሰምቶ ኖሮ  ማሂን ፖሊሶች ከቢሮዋ  ያዟት ብሎ ደወለልኝ፡፡ አንድ ነገር እንዳለ ጠረጠርኩኝ፡፡ በዚህ ጥርጣሬዬ ላይ እንዳለሁ አንድ የግቢ ደህንነት መጥቶ ለሁለተኛ ጊዜ ዶ/ር ቢሯቸው ይፈልጉሃል አለኝ፡፡ ሁኔታው ገባኝ፡፡ በፍቄ እና አጥኔክስ ጋር ስልክ ስሞክር የሁለቱም ስልኮች አይሰሩም፡፡ በዚህ ጊዜ ለሶሊ ሁኔታውን ገልጬ ጂሜል ቻት ላይ መልዕክት አስቀመጥኩላት፡፡ የቤተሰብን አድራሻም ሰጠኋት፡፡ዋት ዋት ዋት ?? የሚለውን የቻት መልእክቷን እያየሁ ነው የወጣሁት፡፡   ወዲያው ደግሞ ለጆማኔክስ ስልክ ደወልኩለት፤ ጆማ ትንሹዋን ገጽ እያት ብዬው ስልኩን ዘጋሁ፡፡ ይህቺ የስልክ ግንኙነቴም የመጨረሻየ ሆነች፡፡


ከቢሮዬ ወጥቼ የተፈለግሁበት የዶ/ር ቢሮ ስገባ ሁለት ሰዎች ቢሮ ውስጥ አሉ፡፡ አላውቃቸውም፡፡ ዶ/ሩ ስለሁኔታው የሚያውቁ ይመስለኛል፡፡ ( በነገራችን ላይ ከቢሯቸው ታሰርኩት የዬኒርሲቲው ምክትል ፕሬዘዳንት በፌርማቸው ስራ ገበታህ ላይ ባለመገኘት ብለው አንዳባረሩኝ እዚህ ቅሊንጦ ከገባሁ ሰማሁ ፡፡ ) በር ላይ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡ ሁለቱ ብቻ የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ሌሎች ሲቪሎች ናቸው፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስጠይቃቸው የብርበራ ትዕዛዝን የሚገልጽ ወረቀት አሳዩኝ፡፡ የእኔ እና የእነበፍቃዱን ስም ወረቀቱ ላይ አየሁት፡፡


ከቢሮ ወጥተን በሁለት መኪኖች ወደእኔ ቤት ተወሰድኩኝ፡፡ ሰዓቱ 12፡00 ሊሆን ተቃርቦ ስለነበር ከ12፡00 በኋላ ብርበራ ማድረግ ክልክል መሆኑን ነገርኳቸው፡፡ በአጭር ጊዜ እንደሚጨርሱ ነግረውኝ ወደቤት ሄድን፡፡ ቤት እንደደረስን በር ስከፍት ጀምሮ በቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ ጀመሩ፡፡ ቤቴ ውስጥ ብዙ እቃ አልነበረም፡፡ መጽሐፎችን እያገላበጡ የፈለጉትን ያዙ፡፡ ብርበራውን እያደረጉ እያለ 12፡00 ሞልቶ ስለነበር ከዚህ በኋላ መበርበር ህገ-ወጥ ነው ስላቸው አንዴ ጀምረነዋል፣ ስለዚህ እንቀጥላለን አሉኝ፡፡ ፍተሻውን አከናውነው ከቤት ወጣን፡፡


ከቤት እንደገና ኮምፒውተርህን እንፈልገዋለን ስላሉ ወደ ቢሮ ተመለስን፡፡ ቢሮ ስንገባ መሽቶ ስለነበር ጨልሟል፡፡ ቢሮ ላፕቶፔን ይዘው ወጡ፡፡ ከዚያም በሁለት መኪኖች ታጅቤ ጉዞ ወደአዲስ አበባ ሆነ፡፡ ጉዞ ላይ አንድ ደህንነት ሊያነጋግረኝ ሞክሮ ነበር፡፡ ስንት ዶላር በላሽ እያለ ሊያሽሟጥጥ ሲሞክር ከፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው አለቃው ማውራት እንዲያቆም ነገረው፡፡ ከዚያም በዝምታ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ሆነ፡፡ አዲስ አበባ ስንደርስ መሽቶ ነበር፤ መኪናው ላይ ሰዓቱን እንዳየሁት ከሆነ ሰዓቱ 3፡00 ሊሞላ ደቂቃዎች ብቻ ቀርተውታል፡፡ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ስደርስ ሌሎች ሰዎች ተቀብለው ወደውስጥ አስገቡኝ፡፡ በቃ አሁን ማዕከላዊ ነኝ አልሁኝ፡፡ በእውነት ማዕከላዊ ስገባ እረፍት ነው የተሰማኝ፡፡    


“Truly speaking, I feel relieved when I entered Maekelawi.” Zelalem Kibret


It was around 5pm and I was having a chat in my office with one Indian lecturer and she was telling me about Indian culture. My Facebook and Twitter pages were open. I didn’t have class that day. The students’ boycotted class because of a protest unrest in the university. Because the academic year was almost over, I prepared the assignment that I’m giving to my students next year.


While I was with the Indian Lecturer one of the campus police member (who is also my student) came to my office and told me that the vice president of the university is waiting for me in his office. One of my friends called me and told me that the police have taken Mahi from her office while I was preparing to go to the vice president. I suspected something. For the second time, one of the campus securities came and told me that the Dr. is waiting for me. Now I got it. When I tried to call Befqe and Atnex their phones are not working. At this time, I informed Soli about the situation and left her a message on Gmail chat. I also gave her my family’s address. I saw her last reply “What? What? What?”, while leaving the office. Immediately I called to Jomanex. I hanged up telling him to see the little page.( the page that we use to exchange information online) This was my last telephone conversation.


When I get to the Dr.’s office, there were two people. I don’t know them. I think the Dr. knows about the situation. (By the way, I heard while I’m here at Kilinto that even though I was arrested from his office,  this university vice president Dr dismissed me from my job with his signature because I’m absent from work.) There were also other people on the gate. Only two of them wear police uniform. When I asked them for court warrant they showed me the warrant for searching. I saw Befeqadu et.al’s and my name on the paper.


We left the office and I was taken to my house in two cars. Since it was passed 6pm I told them that it is not allowed doing the searching after 6pm. They told me that it won’t take much time. They started video recording form the moment I opened my door. There was not much stuff in my room. They took some of the books. I told them it is illegal to do searching after 6pm but they said they won’t stop before finishing. We left my house after the searching is complete.


We returned back to my office because they wanted to take my laptop. It was dark by the time they get to the office to take my laptop. Then we started our journey to Addis Ababa being escorted by two cars. One of the security guys wanted to talk to me while we were on the road. He tried to mock at me saying how much dollar I get but his boss siting on the front seat told him to stop. Then we continued our journey to Addis with silence. It was late when we reached Addis. As I looked at the clock in the car it was few minutes to 9pm. Other people guided me into Maekelawi. I said, “now I’m at Maekelawi”. Truly speaking, I was feeling relieved. 



               


1.    ‹ያዘዝኩትን ማክያቶ ሳልጠጣው ነው የወሰዱኝ››

ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የቢግ ባንድ ሙዚቃ ስለነበር እሱን ለማየት ፕሮግራም ይዤ ነበር፡፡ ላፕቶፔን ይዤዋለሁ፤ ብዙ ጊዜ ላፕቶፔ አይለየኝም፡፡ በዚህ ምክንያት ተስፍሽ እኮ ቢሮውን ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው ይሉኛል ጓደኞቼ፡፡ ብሄራዊ ስደርስ ከታክሲ ወርጄ ታይም መጽሔትን ገዛሁና በአምባሳደር በኩል ወደ አራት ኪሎ የሚያደርሰኝን ታክሲ ያዝኩ፡፡ አራት ኪሎ ስደርስ ሰዓቴን ተመልክቼ የሆነ ካፌ ማክያቶ የምጠጣበት ጊዜ እንዳለኝ አሰብኩ፡፡ ከዛም ምርፋቅ ካፌ ገብቼ ማክያቶ አዝዤ ተቀመጥኩ፡፡


ወዲያው ብሄራዊ የገዛሁትን ታይም መጽሔት አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ አንድ አንቀጽ እንዳነበብኩ ሦስት ሲቪል የለበሱ ሰዎች አጠገቤ ቆመው ተስፋለም ብለው ጠሩኝ፡፡ ቀና ብዬ ሳያቸው አላውቃቸውም፡፡ ምን ፈልጋችሁ ነው አልኳቸው፡፡ ለጥያቄ እንፈልግሃለን አሉኝ፡፡ እኔም እናንተ እነማን ናችሁ፣ መታወቂያ አሳዩኝ እስኪ ብዬ ጠየኳቸው፡፡ ምንም አይነት ድንጋጤ አልነበረኝም፤ እስር አንድ ቀን ሊመጣ እንደሚችል አስብ ነበር፡፡ መታወቂያ ስጠይቃቸው ከካፌው በር ውጭ የነበረን አንድ የደንብ ልብስ የለበሰ የፌደራል ፖሊስ አባል ይዘው መጡ፤ መታወቂያ አሳየኝ፣ የደንብ ልብሱንም ተመልክቼ ሁኔታው ገባኝ፡፡


ከካፌው እንድንወጣ ሲያደርጉኝ ያዘዝኩትን ማክያቶ አልጠጣሁትም ነበር፡፡ ሳነበው የነበረውን መጽሔትና ላፕቶፔን ነጥቀው ወደበር ይዘውኝ ወጡ፡፡ በር ላይ ሌሎች ሰዎችም አሉ፡፡ ጥግ ላይ አቁመውኝ ስልክ ይደዋወላሉ፡፡ ደሞ በምን ይሆን የያዙኝ እያልኩ አሰብኩ፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲያሳዩኝ በእነ በፍቃዱ ኃይሉ የሚል ነገር አይቼ በዞን ዘጠኞች ጉዳይ ነው አልኩና የበለጠ ተረጋጋሁ፡፡ ትንሽ እንደቆምን መኪና መጥቶ ወደቤቴ እንድንሄድ አዘዙኝ፡፡ መኪናዋ ሳይረን እያሰማች ወደቤት ሄድን፡፡ መንግስት በዚህ ደረጃ በጠላትነት ይመለከተናል ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ ከካፌው እንድወጣ ስደረግም ሆነ ከካፌው በር ላይ ቆመን ሳለ፣ እንዲሁም ወደቤት ሲወስዱኝ ማንም ቀና ብሎ የሚያይ የለም፡፡ ገረመኝ! ወይ ህይወት አልኩኝ ለራሴ፡፡


ቤት እንደደረስን ቶሎ ወደ ቤት አልገባንም፡፡ ቤቱ ሲፈተሽ ታዛቢ ያስፈልጋል ስለተባለ ታዛቢ ፍለጋ ሰው እያስቆሙ ይጠይቃሉ፡፡ ብዙ ሰው እምቢ ሲላቸው አየሁኝ፡፡ ከ30 ደቂቃዎች በላይ በር ላይ ቆመናል፡፡ ሰው በግርታ ይመለከተናል፡፡ ታዛቢ የተባሉ ሰዎች ተገኙና ወደቤት ገባን፡፡ በር ስከፍት ጀምሮ ቪዲዮ ቀረጻ ያደርጋሉ፡፡ ቤት ብቻየን ስለምኖር ብዙም ያስጨነቀኝ ጉዳይ አልነበረም፡፡ የሚደነግጥ ሰው አልነበረም፡፡ ቤት ውስጥ ያልፈተሹት ነገር የለም፤ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ምኝታ ቤት፣ ሽንት ቤት አልቀራቸውም፡፡


ቤቴ ሲፈተሽ ሰዓቱ እየመሸ ነበር፤ 3፡00 አካባቢ ሆኗል፡፡ ፍተሻው እየተገባደደ እያለ አንዱ ደህንነት ‹ራት በልተሃል› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ማክያቶየን ሳልጠጣ እንዳመጣችሁኝ ታውቅ የለ ስል መልሼ ጠየቅሁት፡፡ ከዚያ ራት ብላ፣ ከጎረቤት ይምጣልህ ማንን ነው የምትግባባው አለኝ፡፡ በመሐል ሌላኛው ደህንነት እኛም እርቦናል ከውጭ ይታዘዝ ሲል ሀሳብ አቀረበ፡፡ አይ ከጎረቤት ይምጣለት ተባለና አንዲት ህጻን ልጅ ያላት ጎረቤቴ በሳህን አመጣችልኝ፡፡ እኔም ጎረቤቴን አይዞሽ ሰላም ነው፣ ጋዜጠኛ ስለሆንኩ ነው የያዙኝ አልኳት፡፡ ከዚያ በፊት ጋዜጠኛ መሆኔን አታውቅም ነበር፡፡ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው ስል ደህንነቶች ‹ምን አስር ጊዜ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ትላልህ› እያሉ አንባረቁብኝ፡፡ እኔም አዎ ጋዜጠኛ ነኝ መብትና ግዴታየን አውቃለሁ፣ የያዛችሁኝም ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው አልኳቸው፡፡


ፍተሻው ተጠናቅቆ ከቤት ልንወጣ ስንል የቤቱ በሮችና መስኮቶች መዘጋታቸውን ማረጋገጥ አለብኝ አልኳቸው፡፡ ከዚያም ‹የቤቱ ቁልፍ…› ብዬ ስናገር፣ ከአፌ ተቀብለው ቁልፉ ከማን ከማን እጅ ነው የሚገኘው አሉኝ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ቢያንስ መታሰሬን የሚሰማ ሰው ላገኝ ነው አልኩኝ፡፡ ከዚያም አንድ ቁልፍ ከጓደኛዬ ጽዮን (ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ) ጋር መኖሩን ስናገር የሚያውቋት ደህንነቶች ሰው ልከው ነገሯት፡፡ ቤታችን ቅርብ ለቅርብ ነው፡፡ ጺዮን ሁኔታውን ስታውቅ በድንጋጤ ደረጃውን በፍጥነት እየወረደች ስትመጣ ተመለከትኩኝ፡፡ ምን ልታደርጉት ነው፣ እነማን ናችሁ…እያለች አካባቢውን ቀወጠችው፡፡ ሰው ተሰባሰበ፡፡ እኔም አይዟችሁ ጋዜጠኛ ስለሆንኩ ነው የያዙኝ እያልኩ ለማረጋጋት ሞከርኩኝ፡፡


የሰውን መሰብሰብ ያልወደዱት ደህንነቶች በመኪና ወዲያውኑ ግቢውን አስለቅቀው ይዘውኝ ነጎዱ፡፡ ጉዞው ወደ ማዕከላዊ ነበር፡፡ ማዕከላዊ እንደደረስን ብዙ ሰው (ደህንነቶችና ፖሊሶች) ግቢውን ወረውታል፡፡ ሌሎች የታሰሩ ሰዎችም መኖራቸውን ጠረጠርኩ፡፡ ምክንያቱም እኔን ለመያዝ ስምንት ሰው ተመድቧል፡፡ ያ ሁሉ ሰው ደግሞ ሌሎች ሰዎችን ይዞ መጥቷል ማለት ነው፡፡ እኔ ማዕከላዊ ስደርስ በዕለቱ ከታሰሩት ሰዎች ሁሉ ዘግይቼ ማዕከላዊ የደረስኩ እኔ መሆኔ ገባኝ፡፡ ውስጥ ገብቼ ስሜ ሲመዘገብ መዝገቡ ላይ የበፍቃዱን ስም አየሁት፡፡ አሁን ጉዳዩ የበለጠ ገባኝ፣ በዞን ዘጠኞች ነው ማለት ነው አልኩኝ፡፡ የበለጠ ተረጋጋሁ፡፡ ከምዝገባ በኋላ አንድ ሰው ብቻ ወደሚገኝበት ክፍል አስገብተው ቆለፉብኝ፡፡



“They took me before I drink the macchiato I ordered.” Tesfalem Woldeyes

I had a plan to attend the Big Band music show at Yared Music School. As usual I have my laptop with me. My friends always make fun of me saying “Tesfish moves carrying his office.” I bought Time magazine around the National Theatre and went to Ambassador Cinema to catch a taxi to Arat Kilo. By the time I got to Arat Kilo I thought that I have a time for a macchiato. Then I went to a café called Mirfaq and ordered one.


I started to read the Time magazine I bought. I read only just a paragraph when I heard my name being called by three civil wearing guys. I couldn’t recognize any one of them. I asked “What do you need?” “We need you for a question?”, they answered. “Who are you? Show me your ID.”, I continued asking. I was not frightened at all. I had the feeling that imprisonment will come one day. They brought a uniformed federal police member when I asked for their id. I understood the situation when I saw his uniform.


By the time we leave the café, I didn’t drink the macchiato I ordered. They snatched the magazine I was reading, my laptop and took me out. There were other people on the gate. They took me to one corner and started making calls. “Why do they arrest me?”, I keep on thinking. When they showed me the court warrant I saw Befeqadu Hailu et.al so I feel more relieved knowing that it is a case related to Zone Niners. After a while, they ordered me to go to my house. We went to my house while the siren of the car was on.  I never thought that the government had this much enmity against us. I noticed that nobody gave attention when I was taken out of the café, when we were waiting at the gate as well as when they took me to me house. I was stunned! “Oh! Life!”, I said.


We did not get in immediately when we get to my house. They were asking people to witness the searching. I saw many people refusing to be a witness. We stayed for more than 30 minutes. People were looking at us with some confusion.  They found the so called witnesses and we get into my house. They started video recording starting from the moment I opened my door. Since I’m living by myself, I was not worried at all cause there is no one to be disturbed. They searched everything in my house; newspapers, magazines, bedroom even the toilet.


It was getting late; around 9pm, when they searched my house. When they were about to finish one of the security guys asked “have you eaten your dinner?” “Don’t you know that you brought me here before I drink my macchiato?” I replied with a question. Then he said, “Have your dinner. Let’s ask your neighbours. Who do you know more?” One of the other security guys proposed in the middle for a meal to be ordered because they are also hungry. It was finally decided to get food from my neighbours and a woman who has a little kid brought me food. I comforted my neighbour saying “come down it’s ok. They arrested me because I’m a journalist.” She didn’t know that I am a journalist. When I said because I’m a journalist; “Why are you saying I’m a journalist again and again?” the security guys shouted on me. “Yes, I’m a journalist. I know my rights and responsibilities. You arrested me because I’m a journalist”, I told them.


When we were about to leave, I told them that I have to make sure the doors and windows are closed. Then when I said “the key …”, they quickly followed who else has the key. I feel happy. At least I will get someone who knows I’m arrested. When I told them I have extra key with my friend, Journalist Tsion Girma, the security guys who know her send someone to call her. Our houses are close to each other. I saw Tsion rushing down the stairs and coming to me in shock. “Who are you? What are going to do with him?” she controlled the scene. People gathered. I tried to calm down the people saying that they arrested me because I’m a journalist.


The security guys were not comfortable with the gathering so they rushed me out of the compound. We were heading to Maekelawi. I saw lots of security guys and police at Maekelawi. I suspected that there might be more people arrested today. Given that there were eight people assigned for me I can easily guess that these people might have brought more. I realized that I was a late comer from those who were arrested that day. I saw Befeqadu’s name when my name was being registered. This was confirmation that I’m arrested with a case related to Zone Niners. I was calmer than ever. After the registration, they took me to a cell with only one person and they locked the rood at me. 



                   

1.    ‹‹ቤቴ ሲፈተሽ ህጻናት እንዳያዩ ለማድረግ እሞክር ነበር›› 


በግምት ከቀን 10፡30 አካባቢ ቢሮ ውስጥ አብረውኝ ከሚሰሩ ልጆች ጋር ጨዋታ ይዘን ነበር፡፡ እኔ ከጓደኛዬ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ከጓደኞቼ ጋር ስንነጋገር ሁለት ሰዎች ወደውስጥ ገብተው ‹ናትናኤል ማነው› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ወዲያው አንዱ ጓደኛዬ ወደእኔ እየጠቆመ እሱ ነው አለ፡፡ ጉዳዩ የገባው ሰው ከመካከላችን አልነበረም፡፡ እኔም ለሁለቱ ሰዎች ናትናኤል መሆኔን አረጋገጥኩላቸው፡፡ ከዛ አንዴ ፈልገንህ ነው አሉኝ፡፡ ቆይ ላፕቶፔን ልዝጋው ስላቸው እንዲያውም ላፕቶፕህን እንፈልገዋለን ብለው ላፕቶፔን ያዙ፡፡ እሽ አለቃየን ልንገረው ስላቸው ደግሞ አለቃህን መንገር አይጠበቅብህም አሉኝ፡፡ ከዚያም ከቢሮ አስወጥተው ብቻየን አንድ ወንበር ላይ ኮሪደር ላይ አስቀመጡኝ፡፡ ማንነታቸውን ስጠይቃቸው የፍርድ ቤት ማዘዣ አሳዩኝ፡፡ የእነ የበፍቃዱ እና የአጥኔክስን ስም ወረቀቱ ላይ አየሁት፡፡ ያን ጊዜ ገባኝ፡፡


ኮሪደር ላይ አስቀምጠውኝ ብዙ ቆየን፡፡ የስራ መውጫ ሰዓት ስለነበርም ባልደረቦቼ ከስራ ሲወጡ እየተመለከቱኝ ግር ሲሰኙ ስንብት እያደረኩላቸው ይሄዳሉ፡፡ ዙሪያ ገባዬን አየሁት፡፡ ምንም የተለየ ነገር ያለ ሳይመስል ህይወት ቀጥሏል፡፡ ለእኔ ግን ዓለም እየዞረች እንደሆነ እየተሰማኝ ነው፡፡ ከዚህ በፌት ልታሰር እችላለሁ ብዬ የጠረጠርኩበት የደነገጥኩበትም ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን የእውነት እየታሰርኩ ነው ብዬ አሰብኩ ፡፡ የሚጠብቁት መኪና መጣላቸውና ጉዞ ወደ እኔ ቤት ሆነ፡፡ ወደቤት ስንሄድም ከተማውን፣ ሰውን አስተዋልኩት፤ ህይወት ቀጥላለች፡፡ ቤት እንደደረስን የእኔን ክፍል እንዳሳያቸው አዘዙኝ፡፡ ግቢው ውስጥ የነበሩ ህጻናትን ወደጥናታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ሞከርኩ፡፡ ህጻናቱ ግን በግርታ ደጋግመው ወደ እኔ እየመጡ ነው፡፡ የህጻናቱ ጉዳይ የበለጠ ረበሸኝ፡፡ በበኩሌ ቤቴ ሲፈተሽ ህጻናት እንዳያዩ ለማድረግ እሞክር ነበር፡፡ በቪዲዮ ካሜራ እየቀረጹ ፍተሻውን እያደረጉ እያለ አባቴ መጣ፡፡ ብዙም መረበሽ ሳይታይበት ኮቱን አውልቆ ተረጋግቶ ተቀመጠ፡፡ ችግሩ የተፈጠረው ቀስ በቀስ ነው፤ አክስቴ እና ሌሎች ሰዎች ሲሰሙ ግቢው ተረበሸ፡፡ ላረጋጋቸው ሞከርኩኝ፡፡


ፍተሻው እንዳለቀ ራት በላሁ፡፡ ልብስ በኩርቱ ፔስታል ይዤ ከቤት ስወጣ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ተረባበሸ፡፡ በተለይ ልጆቹ እጄን እየጨበጡ ለማስቀረት ሲሞክሩ ተረበሽኩ፡፡ ብዙዎችን እያቀፍኩ እየሳምኩ ተሰናበትኳቸው፡፡ መኪና ውስጥ አንዱ ፖሊስ የእጅ ካቴና አውጥቶ ወደ እኔ ሲመለከት ጉዳዩ ገባኝና ሁለቱን እጆቼን አመቻችቼ ሰጠሁት፡፡ ድርጊቴ ለራሴም ገርሞኝ ነበር፡፡

ማዕከላዊ እንደደረስኩ ምዝገባ ላይ የማሂን ስም መዝገቡ ላይ አነበብኩ፡፡ አሁን ጓደኞቼም እንደተያዙ አወቅሁ፡፡ ምዝገባው ተጠናቅቆ ወደእስር ቤት ክፍል ተወሰድኩኝ፡፡ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁ ከኋላየ በሩ ተቆለፈ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኝ ባለሁበት ፌስታሌን እንደያዝኩ ቆምኩ፡፡ ከዛ ከውስጥ ከነበሩ እስረኞች መካከል ሁኔታየን ያየ አንድ ከጋምቤላ ክልል የመጣ እስረኛ ‹አይ ኢትዮጵያ!› ሲል ተሰማኝ፡፡ ውስጥ ያሉት ሰዎች አረጋጉኝና ትንሽ አወራን፡፡ በቃ ማዕከላዊ ገባሁ አልኩ ለራሴ፡፡


“When my house was searched I tried to cover up so that the kids won’t see” Natnael Feleke

I think it was around 4:30pm and I was chatting with my colleagues in the office. Two guys walked in asked “who is Natnael” when I was sitting on my friend’s chair and talking. Immediately one of my friends pointed as me and identified me. None of us have a clue about what is going on. I confirmed to the two guys that I am Natnael. Then they told me that they wanted me. I said “wait let me close my laptop” and they said they also wanted the laptop and they took it. Then I told them that I need to inform my boss and they said I don’t need to. Then they fetched an extra chair and left me alone on the corridor. When I asked who they are they showed me a court warrant. I saw Befqe’s and Atnex’s name on the paper. Then I got it.


I sat on the corridor quite for some time. I stated to greet my colleagues that were passing on the corridor leaving the office and heading home. I can see their confusion. Normal life continued as if nothing happened. However, I was feeling the world is moving. There are moments where I thought of, even shocked in thinking of being imprisoned. Now I realized that it is the real moment to be imprisoned. The car that the guys were waiting for arrived and we started heading to my house. On our way home, I noticed the people and the city; life goes on. They ordered me to show them my room once we get home. I tried to push the children in the compound to go to their study. The children refused the kept on coming to me. I was disturbed by the children.


When my house was searched I tried to cover up so that the kids won’t see. My father arrived while they were searching using the video recorder. Without any major sign of disturbance he took of his coat and sat down calmly. Slowly the mood started to be disrupted when my aunt arrived and other people in the compound heard about what’s going on. I tried to calm them down.


I ate my dinner after they finished the searching. Everyone in my family started to feel bad when I was about to leave the house holding my cloth in a plastic bag. I also felt the same especially when the kids started to pull me back by holding my hands. I hugged and kissed most of them. In the car when one of the police brought a handcuff I gave him both of my hands.  I was surprised by my own action.


I read Mahi’s name on the registration folder. I realized that they are also imprisoned. I was escorted to a prison cell after the registration. I hear the door being locked in my back the moment I got into the cell. I did not know what I was supposed to do so I stood where I am for a while. Then I overheard one guy who came from Gambella region saying “Oh Ethiopia”, noticing my confusion. The guys inside the cell talked to me for a while. I’m in Maekelaw, I said it for myself. 




1.    ‹‹ለሁለት አመት ያላየሁትን ጓደኛዬን ላገኘው ቀጠሮ ነበረኝ›› 


እኔ እና አጥኔክስ 10፡45 አካባቢ ከቀነኒሳ ሆቴል እየወጣን ነበር፣ ያን ቀን አብረን ነው የዋልነው፡፡ መንገድ ላይ እንዳለን ስልክ ተደውሎ ማሂ በፖሊሶች መያዟን ሰማን፡፡ ወዲያው የማሂን መያዝ በተመለከተ ቲዊት ላደርግ ስልኬን ስነካካ የማላውቃቸው ሰዎች ሁለታችንንም ከበቡን፤ ስልካችንና ላፕቶፓችንንም ነጠቁን፡፡ ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አላደረግንም፡፡ ዙሪያ ገባየን ሳይ ሰው የተለመደ እንቅስቃሴውን ቀጥሏል፡፡


የሚገርመው ለሁለት አመታት ያህል አግኝቼው የማላውቀው ጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝ ወደዚያ እየሄድኩ ነበር፡፡ ከጓደኛየ ጋር ብዙ ጊዜ ለመገናኘት ፈልገን አልመችህ ሲለን ረጅም ጊዜ ሳንገናኝ ቆየን፡፡ በዛ ዕለትም ሳላገኘው ወደእስር ተጋዝኩኝ፡፡ የነጠቁኝ ስልክ በተደጋጋሚ ሲደወል እና መልዕክት ሲገባ ይሰማኛል፡፡ የቀጠርኩት ጓደኛየ ይሆናል እያልኩ አስባለሁ፡፡

ሰዎቹ እኔን እና አጥኔክስን መኪና ውስጥ አስገብተው ወደ ቦሌ መድሃኒያለም ወሰዱን፡፡ ከዚያም ሌላ መኪና መጣችና አጥኔክስን ከእኔ ለይተው ወደሌላኛዋ መኪና ወሰዱት፡፡ አጥኔክስ ጋር ሲለያዩን አይዞን፣ አይዞን ተባብለን ተለያየን፡፡ ከዚያ እኔን የያዘችው መኪና ወደ እኔ ቤት ይዛኝ ከነፈች፡፡ የቤት ብርበራ ሊደረግ መሆኑ ገባኝ፡፡


ቤት ደርሰን የእኔን ክፍል እያንዳንዷን ነገር መፈተሽ ጀመሩ፡፡ አንደኛው በተለያየ ጊዜ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች እያነበበ አየዋለሁ፡፡ ፍተሻው ቀጠለ፡፡ የሚፈትሹት ሰዎች ቀስ በቀስ እየወደዱኝ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ማነጋገር ጀምረዋል፡፡ ቤቴ ውስጥ ያለኝ ብዙ ሀብት መጽሐፍ ነው ማለት እችላለሁ፡፡ የቆዩ መጽሐፎችን ሳይቀር እያገላበጡ እያዩ የሚፈልጉትን ይይዛሉ፡፡ እኔ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች እያገላበጡ ‹ለምን አታሳትማቸውም› ማለት ሁሉ የጀመሩ ነበሩ፡፡ የእውነት ሰዎቹ እየወደዱኝ ነበር (በሳቅ)፡፡ ፈታሾቹ ሳጥን ውስጥም መጽሐፍ፣ ካርቶን ውስጥም መጽሐፍ፣ ጠረጴዛ ላይም መጽሐፍ ሲያገኙ እየተገረሙ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ የእኔን ክፍል ፈትሸው ሲጨርሱ ዋናው ቤት ገቡ፡፡ እናቴም አባቴም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ የዛን ሰሞን ሁኔታ ስላላማረኝ፣ ሊያስሩኝ እንደሚችሉና ቤቱም ሊፈተሽ እንደሚችል እነግራቸው ስለነበር ሳይዘጋጁ አልቀሩም፡፡ ቢሆንም ግን መደንገጣቸውና ፣ ማልቀሳቸው አልቀረም፡፡ ቤት ውስጥ ማየት የሚፈልጉትን እያዩ እያለ እራት እንድበላ አሳሰቡኝ፡፡ እራት ቀርቦልኝ እንዴት ይበላልኝ!


ፍተሻው አልቆ ከቤት ስወጣ ቤተሰቦቼን ለማረጋጋት ያህል ‹በጥርጣሬ ነው የያዙኝ፣ ሰኞ እወጣለሁ ይለቁኛል› አልኳቸው፡፡ ከዛም በመኪና ይዘውኝ ማዕከላዊ ወሰዱኝ፡፡ ማዕከላዊ እንደደረስኩ ሰውነቴ ድንዝዝ ሲል ይታወቀኛል፡፡ በቃ ራሴን የመጣል ስሜት ነበር የወረረኝ፡፡ ደሞ ድካሙ! ማዕከላዊ ተመዝግቤ ሌሎች እስረኞች ወዳሉበት ክፍል አስገቡኝ፡፡ በሩ ከኋላዬ ሲዘጋ ቀፈፈኝ፡፡ ወዲያው ውስጥ ያሉት እስረኞች ስለራሴ ጠየቁኝ፤ ነገርኳቸው፡፡ ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፡፡


“I had an appointment to meet a friend whom I never met for two years” Befeqadu Hailu


It was around 4:45pm when Atnex and me leave Kenenisa Hotel. We were together the whole day. While walking, we received a call and found out that the police has arrested Mahi. Immediately while I was about to tweet about Mahi’s arrest using my phone some strange people surrounded us and snatched our phones and laptops. We didn’t make any strange move. When I look around, people are busy with their routine life and things continue as normal.


Surprisingly I was about to meet a friend that I have not seen for the last two years and I was heading there. My friend and me have been planning to meet a number of times but we couldn’t do so because of lots of inconveniences. To add on this, I’m being taken to the prison on this day as well. I can hear my phone ringing and text message coming while it’s in the hands of the guys. I was thinking it was my friend.


The guys put Atnex and me into a car and take us to the Bole Medhanialem church. Then another car came and they took Atnex to another car. When they took him, we comforted each other. Then the car I was in started its way to my house’s direction. I felt that they are about to do house searching.

When we get to my house, they started to search each and every thing in my room. One of them is reading the articles I wrote.  The searching continued. I feel that the people who are searching my house have started to like me. They even started a conversation with me. The wealth that I have in my house is books. They started to pick the old books and keep some of them that they want to. They started to go through some of my articles and even started asking “why are you not publishing?” 

Truly, the guys started to like me. The searchers were surprised to find books in lockers, books in the cartoon boxes and books on the table. They moved to the main house once they finished searching my house. Both my parents were there. It seems that both of them were ready since I have been sharing with them my suspicion about the changing situation and the possibility of me being arrested. In spite of all this, they couldn’t avoid being shocked and crying. While they were looking at things in the house they reminded me about having my dinner. Dinner was served, but how could I eat it.

When we were about to leave I tried to calm down my family. I said “they are arresting me as a suspect. I will leave on Monday. They will release me” They drove me to Maekelawi. When we get there I feel my body becoming drowsy. I just wanted to throw my body. It was very tiresome. They put me into a cell where there are other prisoners after they register me. I feel disgusted when the shut the door behind me. Immediately the prisoners inside the cell started to ask me about myself and I told them. They tried to calm me down.




1.    ‹‹ከዛ ቤት በህይወት የምወጣ አልመሰለኝም ነበር››  


ስያዝ ከበፍቄ ጋር ነበርኩ፡፡ አገር ሰላም ብዬ በነጋታው ለሚደረገው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ለመግባት ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ቲዊት እንደራረግ ነበር፡፡ በፍቄ ጋር ከሆቴል ወጥተን በእግራችን እየተጓዝን እያለን ተከበብን፡፡ ደንግጨ ነበር፡፡ ግን ምንም ሳልል ዝም ብዬ የሚሆነውን ሳይ ስልካችንንና ላፕቶፓችንን ነጥቀው መኪና ውስጥ አስገቡን፡፡ ደቂቃዎች ቀድሞ የመጣው የማሂ መያዝ የነገሩን አይቀሬነት ግልጽ አድርጎልኝ ስለነበር ለመረጋጋት ሞከርኩ፡፡ መኪና ውስጥ በፍቄ ጋር ተጠጋግተን ተቀምጠን ትንሽ እንደሄድን ሌላ መኪና መጥቶ ነጣጠሉን፡፡ ከበፍቄ ስለይ ግን በጣም ደነገጥኩ፡፡


መኪናዋ ወደ አድዋ ድልድይ ይዛኝ ከሄደች በኋላ አካባቢው ላይ ካለ ፖሊስ ጣቢያ አስገቡኝ፡፡ ትንሽ እንደቆዩ ከጣቢያው አስወጥተው ወደቤቴ ወሰዱኝ፡፡ የሚገርመኝ ወደቤቴ ሲወስዱኝ ብዙ ጊዜ ቤቴ አካባቢ የምትቆም መኪና ነበረች ከፊት እየመራች የወሰደችን፡፡ መኪናዋን እኔ ብቻ ሳልሆን እነ በፍቄና ናቲም ያውቋታል፡፡ መኪናዋ እኔን ለመከታተል የተመደበ ሰው ነበር የሚይዛት ማለት ነው፡፡


ቤት ስንደርስ አባቴ ወደ ግቢ ሊገባ ሲል ተገጣጠምን፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ እናቴ ‹ዛሬ ደግሞ ጎረቤቱን ሁሉ ሰብስቦ ነው የመጣው› እያለች ስትናገር ይሰማኛል፡፡ እናቴ ሁኔታው እንዳልገባት አወቅሁ፡፡ እውነቱን ሲያውቁ ደግሞ ቤተሰብ መረበሽ ታየባቸው፡፡ ፍተሻው እየተደረገ እያለ ለመረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ግን ሰውነቴን ድካም ድካም ይለኛል፡፡ አድካሚው ፍተሻ ሲገባደድ እራት ስጡት አሉ ለቤተሰብ፡፡ በዚህ ጊዜ እህቴ ‹ልትወስዱት ነው እንዴ› ብላ ቀወጠችው፡፡ በጣም አለቀሰች፡፡


እራት ቀርቦ ልበላ ብሞክር እንዴት ከጉሮሮየ ይውረድ! መመገብ አልቻልኩም፡፡ እህቴ እያለቀሰች እራት እንድበላ ታጎርሰኝ ነበር፡፡ አንዴ፣ ሁለቴ እንደጎረስኩ በቃኝ አልኳት፡፡ ድብልቅል ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ ፍተሻው አልቆ ከቤት ይዘውኝ ሲወጡ እናቴና አባቴ ተከትለውኝ ወጡ፡፡ መኪና ውስጥ ገብቼ ስንቀሳቀስ ‹ማርያም ትከተልህ የእኔ ልጅ!› የሚለው የእናቴ ድምጽ ይሰማኛል፡፡ ማዕከላዊ ስንደርስ ሰውነቴ የበለጠ እየዛለ ነበር፡፡ ዝም ብሎ ሰውነቴን ይደነዝዘኛል፡፡ ምዝገባው ተደርጎ ወደ እስር ክፍል ስወሰድ ኮሪደሩ ራሱ ያስፈራ ነበር፡፡ የእስር ክፍሉ ተከፍቶ ገባሁ፡፡ በሩ ከኋላዬ ሲዘጋ ባለሁበት ቆሜ ቀረሁ፡፡ ይቀፍፋል! ማዕከላዊ የእውነት ይቀፍፋል! ቤቱን ሳየው አንደገና ደነገጥሁ፡፡ ከዛ ቤት በህይወት የምወጣ አልመስልህ አለኝ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ነበሩ፡፡ አንዱ በሙስሊሞች ጉዳይ የታሰረ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ተይዞ የመጣ የጋምቤላ ክልል ተወላጅ የሽብር ተጠርጣሪ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ውስጥ የመጀመሪያው ቀን ላይ እንቅልፍ በዓይኔ ዞር ሳይል ነው ያደርኩት፡፡ ፊቴን ወደ ግድግዳው አዙሬ በሀሳብ ተውጨ ሌሎቹስ ምን እያሰቡ ይሆን እያልኩ ሳሰላስል ነው  የነጋው፡፡  


“I thought that I wouldn’t leave that place alive” Atnaf Birhane

I was with Befqe when I was arrested. I was in a calm mood and was twitting with my friend about Tedy Afro’s concert the following day. We got surrounded the moment Befqe and me started to walk leaving the place where we were. I was scared. I was just watching what they were doing without saying a word and they took our phones and laptops and put us into a car. I heard about Mahi’s arrest few minutes ago so I was expecting this at any moment. I tried to calm down myself thinking about this. Befqe and me were sitting very close to each other in the car. After a short drive, another car came and they put us in different cars. I was very shocked when they depart me from Befqe.


The car I was in headed to the police station around Adwa Bridge. After spending some time at the police station they took me to my house. What surprises me was the car I was in was following another car which I have noticed several times parked around my house. Both Befqe and Natty also know about this car. Now I concluded that the car was assigned to spy on me.


We met my father at the gate of our house. While entering the house I overheard my mother saying “today he brought all the neighbours with himself”. I noticed that my mother have no clue about what’s going on. Later on, when they understand what is going on, my family members couldn’t hide how disturbed they are. I tried to calm down myself while the searching is being carried out. But I couldn’t resist the level of exhaustion I’m feeling. When they are done with their tiresome searching they told my family to give me a dinner. “Are you taking him?”, my sister screamed. She cried a lot.

I struggled to eat my dinner! I literally couldn’t eat. My sister was trying to force me to eat the food. She fed me (gursha) two times and then I stopped.  I couldn’t figure out what I’m really feeling. My parents followed us when the guys started to escort me out after the searching is complete. When the car moves I heard my mother’s good wish saying “may the Virgin Mary follows you, my son.” 

My body was extremely drained when we get to Maekelawi. I feel some sort of exhaustion awkwardly. We passed through a scary corridor while I was being taken to the prison cell after the registration. I get into the prison cell. When the slammed the door behind me I stopped inside the cell for a moment. It’s disgusting! Honestly speaking Maekelawi is disgusting! I was shocked when I looked around the cell. I thought that I wouldn’t leave that place alive. There were two other prisoners in the cell. One of them is arrested to the case related to the Ethiopian Muslims movement. The other one is a guy from the Gambella region caught in South Sudan for terrorism related cases. I spend the first night in Maekelawi without having a single moment of sleep. I kept on contemplating about my other friends (about others) and a new day started while I was engulfed by this thinking. 





1.        #‎FreeZone9bloggers‬  #FreeAsemamaw  #Ethiopia 
‹‹እናቴ እንዳትደነግጥ ብዙ ጥሬያለሁ››

እኔ የተያዝኩት ከሁሉም በኋላ ነው፡፡ ልጆቹ መያዛቸው በታወቀ ጊዜ እኔ ጋ የሚደወለው ስልክ ስፍር ቁጥር አልነበረውም፡፡ የማደርገው ጠፍቶኝ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች መረጃ ፍለጋ እኔ ጋ ይደውላሉ፡፡ ሌሊቱን እንቅልፍ አልነበረኝም፡፡ ጠዋት ላይ ወደቢሮ ገብቼ የምሰራውን ሰርቼ ወዲያው ወደማዕከላዊ ለመሄድ (ልጆቹን ልጠይቅ) ከቢሮ ወጣሁና ታክሲ ያዝኩ፡፡ ፌርማታ ደርሼ ስወርድ አንድ ሲጠጣ ያደረ የሚመስል ሰው ድንገት አጠገቤ ደርሶ ‹አስማማው!› ሲል ጠራኝ፡፡ መጀመሪያ ዝም አልኩት፤ ደግሞ ሲጣራ አቤት አልኩት፡፡ ወዲያው አንዲት መኪና እግሬ ስር መጥታ ቆመች፡፡ ለካ ታክሲ ውስጥ ስገባ ጀምሮ ሲከታተሉኝ ኖሯል!

ከመኪና ውስጥ የነበሩ ሰዎች ድንገት አፋፍሰው መኪና ውስጥ አስገቡኝ፡፡ በቀኝና ግራ ጥብቅ አድርገው ይዘው መኪናውን አንቀሳቀሱት፡፡ የእውነት አሸባሪ የያዙ ነበር የሚመስሉት፡፡ መኪና ውስጥ እያሉ በመጠራጠር መታወቂያየን እንዳሳያቸው ጠየቁኝ፤ ሰጠኋቸው፡፡ ከዚያ ቀጥታ በአዲሱ ገበያ አድርገው ወደላይ ይዘውኝ ከወጡ በኋላ የሆነ ቦታ ጥግ ላይ መኪና ውስጥ አስቀመጡኝ፡፡ ትዕዛዝ እስኪቀበሉ መሰለኝ፡፡ ሰዓቱ እየረፈደ ሲሄድ አንዱ ደህንነት ቁርስ መብላት እንደሚፈልግ ገልጾ ቁርስ ቤት ይዘውኝ ሄዱ፡፡ እኔ መኪና ውስጥ እያለሁ መብላት የሚፈልጉት በሉ፡፡


ትዕዛዝ ሲያገኙ ወደቤቴ ለፍተሻ ይዘውኝ ሄዱ፡፡ ወደቤት ስንሄድ ካቴና እጄ ላይ አስገብተው ነበር፡፡ እናቴ ይህን እንድታይ አልፈለግሁም፡፡ ትደነግጣለች፣ በዚያ ላይ ነርቭ አለባት፡፡ ስለዚህ እናቴ እንዳትደነግጥ ለማድረግ መጣር ነበረብኝ፡፡ ወደቤት ስገባ የታሰረውን እጄን ከእናቴ ደብቄ ነበር፡፡ እናቴ እንዴት በዚህ ሰዓት መጣህ እያለችኝ ሰዎቹ ተከታትለው ገቡ፡፡ ጓደኞቼ ነበር የመሰሏት፡፡ ሶፋ ላይ ስቀመጥ ሁሉ ካቴናውን እናቴ እነዳታይ እጥር ነበር፡፡


አባቴ  ሰዎቹን ቀና ብሎ እያየ ቁርስ እንዲበሉ ያግባባ ነበር፡፡ ጉዳዩ የገባው ዘግይቶ፣ እህቴ ወደውስጥ እንዳትገባ ስትከለከል ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እናቴም አወቀች፡፡ ፍተሻው ረጂም ጊዜ ነው የወሰደው፡፡ ያላገላበጡት ነገር የለም፡፡ በስልክ ቶሎ እንዲጨርሱ ሲያጣድፏቸው ይሰማኛል፡፡ እነሱ ደግሞ የጋዜጠኛ ቤት ነው፣ ብዙ ይቀረናል እያሉ ረጂም ጊዜ ወሰዱ፡፡

ፍተሻው ሲያልቅ ምግብ ብላ ስለተባልኩ፣ እርቦኝም ስለነበር በላሁ፡፡ ልብስ በፌስታል ተዘጋጀልኝ፡፡ ከዚያም ወደማዕከላዊ ይዘውኝ ሄዱ፡፡  


“I tried my best to make sure that my mother would not be shocked” Asemamaw Hailegiorgis


I was the last to be arrested. Once their arrest becomes is known, I received enormous amount of phone calls. I did not know what I was supposed to do. Lots of people called me asking for information. I couldn’t sleep the whole night. I get to my office in the morning and quickly finished my work and left my office and grab a taxi heading to Maekelawi to visit my friends. When I get off at a taxi station, someone called my name; “Asemamaw”. The guy looks he spent the whole night drinking. I ignored his first call. I answered when he called me again. Immediately I saw a car pulling over just next to me. I just realized that they were following me starting from the taxi ride.


The guys who were inside the car rushed me into the car. The hold me tightly from both sides and started driving. It looks like they just arrested a real terrorist. Once we were in the car they asked me for an ID in a very doubtful mind. I gave them.  Then they drove to the direction of Addisu Gebeya and parked the car at some random corner and left me in the car. I think they were waiting for an order. One of the security official said he wanted to have his breakfast and they took me to a snack house. Those who wanted to eat had their breakfast while I was in the car.


Once they got the order, they took me to my house for a search. I was handcuffed when we were heading to my house. I did want my mom to see this. She will be shocked. She has nerve related health problem. So I had to try my best to make sure that she would not be shocked. I was hiding my handcuffed hands from my mom’s eyes when we entered the house. My mother was wondering how I get back home at this time of the day while the guys followed my steps into our house. She though that they are my friends. I kept on trying to hide the handcuff after I sat down on the sofa.

My father started to invite the guys for breakfast. He realized it is a serious issue when my sister was disallowed to get in. My mother also started to figure out what is going on slowly. It was a long searching. They were searching every corner. I can see that they are being told to hurry up through a phone. They replied that they need more time because it is a journalist’s house.


I was asked to eat something when they are done. I was hungry and I ate. My extra cloth was packed in plastic bag. Then they took me to Maekelawi.



‪#‎FreeZone9bloggers‬ ‪#‎FreeAbel‬

የታሰርኩ ለታ – አቤል ዋበላ

ከመስሪያ ቤት ቀን 9፡00 ላይ የሻይ እረፍት እንወጣለን፡፡ ያን ቀን የሻይ እረፍት ሰዓት ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ስልክ እያወራሁ ነበር ፡፡
( ከወዳጄ ማህሌት ሰለሞን ጋር ) የሻይ እረፍታችን ስላበቃ እና እኔም ስራ ስለነበረብኝ ወሬያችንን ሳንጨርስ ወዳጄን ተሰናብቼ ወደቢሮየ ገባሁ፡፡ አለቃዬ በጣም ጥሩ ሰው ነው፤ ሰርቶ ለማሰራት የሚታትር ሰው ነው፡፡ መካኒካል ኢንጅነሪንግ ላይ ብዙ ስራዎችን ለመስራት እቅድ ነበረን፡፡በደረጃ እድገት ወደዚህ ቢሮ ከተዘዋወርኩ ገና አራት ወራት ቢሆነኝም በጣም በብዙ መልኩ ተግባብተን የነበረ መልካም ሰው ነው፡፡
ቢሮዬ አለቃየ ጋር ሆነን ስለስራ እየተጨዋወትን እያለ ሁለት የማላውቃቸው ሰዎች አንዴ ልናነጋግርህ ፈልገን ነበር ብለው ከቢሮ አስወጡኝ፡፡ የፌስቡክ እና ትዊተር ገጾቼ አልተቀምባቸው አንጂ ኮምፒውተሬ ላይ እንደተከፈቱ ናቸው፡፡
ከሁለቱ ወጣቶች ጋር ከቢሮ ስወጣ አለቃየን አየት አደረኩት፡፡ ግር መሰኘቱ ግን ከፊቱ ላይ ይነበባል፡፡ ሰዎቹ ኮሪደር ላይ አነጋግረው ይለቁኛል የሚል ግምት ነበረኝ፡፡ ከቢሮ እንደወጣሁ ግን የህንጻውን ደረጃ እንድወርድ በትዕዛዝ ነገሩኝ፡፡ እኔም ሁኔታው ገባኝ፡፡ ደረጃውን እየወረድኩ እያለ አለቃየ ተከትሎኝ ሲያየኝ አየሁት፡፡ ደረጃውን ስጨርስ ከእይታዬ ጠፋ ያንን መልካም ሰው ከዚያ በኋላ አላየሁትም፡፡ ከህንጻው እንደወረድን ሁለት መኪኖች ቆመዋል፡፡ መኪና ውስጥ ከተቀመጡት ሁለት ፖሊሶች ውጭ ሰባት ሲቪል ያደረጉ ደህንነቶች ናቸው ያጀቡኝ፡፡ የአየር መንገዱ ሰራተኞች የይለፍ መታወቂያን (ፓስ) ተቀብለውኝ ከግቢ ወጣን፡፡ ከዚያም ወደ ቤት መሄድ እንዳለብን ስላዘዙ ወደዚያው ሄድን፡፡
ቤት በእነዚያ ሁሉ ሰዎች ታጅቤ ስገባ አከራዬ በጣም ደነገጠች፡፡ ድምጼን እንኳ ሰምታው የማታውቅ ሰው በፖሊስ ታጅቤ ስገባ መደንገጧ አልገረመኝም፡፡ ሰዓቱ መሽቶ ነበር፤ 12፡00 አልፏል፡፡ ቤቴን ከፍቼ ስገባ ሶኬቱን አሳየን አሉኝ፡፡ ሶኬቱን እንዳሳየኋቸው መብራት አብርተው ቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ ጀመሩ፡፡ እየበረበሩ እያለ ከምኝታዬ ስር በሁለት ኩርቱ ፔስታል የታሰረ ነገር አግኝተው በጥርጣሬ ሳብ አድርገው አወጡት፡፡ ሊበተን የተዘጋጀ ወረቀት ቢጤ ያገኙ መስሏቸው ነበር መሰለኝ፡፡ ፔስታሎችን ፈትተው ሲያዩዋቸው መጽሐፍት ብቻ ናቸው፡፡ ከመጽሐፎች ውስጥ መርጠው ያዙ፡፡ ፍተሻው ብዙ ጊዜ አልወሰደም፡፡
ጠዋት ከቤቴ ስወጣ እንቁላል ጠብሼ ነበር፡፡ ግን አላሰኘኝም ነበርና አልበላሁትም፡፡ ቀኑን ሙሉ ስራ በዝቶብኝ ስለነበር በጣም ደክሞኝ በጣምም እርቦኝ ነበር፡፡ ቤቴ ስገባ ጠዋት የሰራሁት እንቁላል ትዝ ቢለኝም አልበላሁትም፡፡ እነዳለ ትቼው ከሰዎቹ ጋር ወደ ማዕከላዊ ተጋዝኩኝ፡፡ ሌላ ቀን እህቴ ቤቴ ሂዳ እቃ ስታወጣ የሰራሁትን እንቁላል አግኝታዋለች፡፡
ወደ ማዕከላዊ እየተወሰድኩ እያለ ደህንነቶች እያወሩኝ ነበር፡፡ ‹ያን የመሰለ ቢሮ ውስጥ እየሰራህ እንዴት…› ሲሉኝ ምንም ወንጀል እንዳልፈጸምኩ እነግራቸው ነበር፡፡ ማዕከላዊ እንደደረስኩ ናቲን እና አጥናፍን አየኋቸው፡፡ ተረጋጋሁ፡፡ ከዚያ ሌሎች እስረኞች ወዳሉበት ክፍል አስገቡኝ፡፡ እስረኞቹ አንዳንድ ጥያቄዎች ስለራሴ ጠየቁኝ፡፡ ተግባባን፡፡ ከዚያም የበረደ ሽሮ ሰጡኝ፡፡ እርቦኝ ስለነበር እሱን ያለማቅማማት በልቼ እስርን ተቀላቀልኩ፡፡
“I was very hungry.”  Abel Wabella


Our afternoon tea break time is at 3pm. That day, I was having a long conversation over the phone during our tea break. But I had to cut short my phone conversation and returned back to the office because the tea break was over. I have a very nice boss. He is so enabling that we even have lots of unexecuted plans in our mechanical engineering section. Even though it’s only four month since I got promoted to this office, I find my boss very kind person with whom I had positive collegial relation full of mutual understanding.


While I was having a work related conversation with my boss in my office, two strange people came and take me out of the office mentioning that they have something to talk to me. I had both my Facebook and twitter accounts open on my computer even though they were idle.


While walking out with these young strangers, I had a glance over my boss. One can easily read his confusion from his face. I assumed that the guys will let me go once they talked to me on the corridor. But, once I left the office, they ordered me to walk down the stairs. It by then, that I began to understand and realize, what is happening. I noticed that my boss was seeing me off while I was walking down the stairs. I lost sight of this kind man when I finished the stairs and never seen him since then. I saw two cars outside of the building. Except the two uniformed police men who were sitting in the cars, I was escorted by seven civil-wearing security people. They took away the Ethiopian Airlines employees ID that I have which is used as a pass and we left the compound. Then they ordered that we go to my house.


The lady who rent me the house was really shocked when she saw me being escorted by all these people. I was not surprised. I can imagine how she would feel when she saw her tenant who never bothered her even once is being surrounded by the police. It was past 6pm so it was getting dark. When I opened my door they asked me for the power plug and I showed them. Immediately they plugged in their camera light and started video recording. While they were searching, they found two plastic bags under my bed and they pulled it very suspiciously. They must have thought that they found a leaflet to be disseminated. When they opened the plastic bags they found books. They picked some books. It was a quick search.


That morning, I prepared egg for my breakfast. But I didn’t have the appetite so I didn’t eat it. Having a very busy day at the office, I was very exhausted and very hungry. I recalled the egg I prepared in the morning but I couldn’t eat it. I left it as it is and escorted to Maekelawi with the guys. In another day my sister found that breakfast I prepared when she went to my house to move my stuff.

While we were heading to Maekelawi, the security guys were talking to me. “How can you do this while you have such a nice job …” I returned to them that I did not commit any crime. I saw Natty and Atnaf when I get to Maekelawi. I feel relieved. They took me to a room where there were other prisoners. The prisoners asked me some questions about me. We understood each other. They offered me a cold shiro. Since I was very hungry I ate it without any hesitation and joined a prisoner’s life.

ማስረሻ ማሞ

እኤአ ጁላይ 10/2010 ጠዋት፤ ግማሽ ሰው ግማሽ ሰካራም ኾኜ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ጭንቅላቴ በምሳር እንደተፈለጠ እንጨት ውስጡ ብርግድ ብሎ ደርቋል። የኾነ ነገር ጠጥቼ ራስ-ካላደረግኹት፤ ከፍላጩ የሚወጣው ስንጣሪ ቀኑን ሙሉ ሲረብሸኝ እንደሚውል አስቤ እንደ መጋዣ እየተጎተትሁ ተነሳሁ። መገለጥ ያቃታቸውን ዐይኖቼን በአይበሉባዬ ጨምቄ ዞር ስል ተስፋለም ወልደየስ ጧ ብሎ ተኝቷል። የቀኝ እጁ ከአልጋው ጠርዝ ላይ ከርፈፍ ብሏል። ግማሽ ፊቱ በብርድ ልብስ ተሸፍኗል። አተኛኘቱ አስቀናኝ። ልክ እንደ ሕጻን ልጅ ያለበትን አያውቅም። አእምራቸው በክፋት ያልተሞላ ሰዎች ብቻ ይመስሉኛል እንዲዘህ የሕጻን ልጅ እንቅልፍ መተኛት የሚችሉት። ተስፋለም አልጋ ላይ ሳይኾን የኾነ ደመና ላይ የተንሳፈፈ ይመስላል።
ይኼን የመሰለ ሰላማዊ የኾነ እንቅልፍ የተኛ ሰላማዊ ልጅ፤ ከእንቅልፉ እንዳለቀሰቅሰው ብዬ በሩን በቀስታ ከፍቼ ወጣሁ። ለነገሩ በሩ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ከማውቃቸው ሳይነኩ በቋቋታ ከሚያሳብቁ በሮች የተለየ ነው። ቋ የለ፤ ሲጥ የለ ማንንም ሳይረብሽ ተዘጋ። ሳሎኑን በረጅም እግሮቼ ሁለቴ አጠፍኩት። ራሴን ፍሪጅ ውስጥ አገኘሁት። ቀዝቃዛውን ውኃ ከእነ ጆጉ ጠመድሁት። ጉሮሮዬን ቸሰሰሰሰሰሰ እያደረገው ሲወርድ ኤርታሌ ላይ ዘላለማዊ በረዶ የወረደበት የሚመስል ዐይነት ድምፅ ጭንቅላቴ ውስጥ ተሰማኝ። ዐይኖቼ በትንሹ ተዘረጉ። ወዲያው የቡና ማሽኑን አውጥቼ ቡና ጣድኹ። ከሳሎኑ ፊት ለፊት በጓሮ በኩል አንዲት ሰታቴ የምታክል የዋና ገንዳ አለች። የጃኩዚ ታላቅ ወንድም፤ የዋና ገንዳ ታናሽ እህት ትመስላለች። ጠርዟ ላይ ቆሜ ሰታቴዋ ላይ አፈጠጥኹባት። ልግባ አልግባ ብዬ ከራሴ ጋራ ሙግት ገጠምኹ፤ ሐሳቤን ሰርዤ ከቤት ውጭ ካሉት ወንበሮች አንደኛውን ስቤ ተቀመጥኹ።
ቂጤ መቀመጫውን ሳይዝ የቡና ማሽኑ በፉጨት ጠራኝ። ቀድቼ ተመልስኹ፤ ሲጋራ ለኩሼ ቁጭ አልኹና እንዲህ ግማሽ ሰው ግማሽ ሰካራም ያደረገኝን ነገር ማሰብ ጀመርኩ። የቅዳሜ ምሽቱ አስረሽ ምቺው ነበር ለዚህ ያበቃኝ። ሦስት ሎንግ አይላንድ አይስ ቲ አከታትዬ ነበር የጠጣኹት፤ ቢራና ተኪላው ሳይቆጠር። ተስፋለም አጠጣጤን ተመልክቶ እንደታላቅ ወንድም ሲቆጣኝ ነበር ያመሸው። አንዳንዴ ቶሎ ስክር ብሎ፤ ቶሎ ጭፍር አድርጎ፤ ቶሎ ጥቅልል ብሎ መተኛት ያምረኛል። እንዲህ ነኝ። የትንሹ ተስፋለም ምክር ልክ እንደነበር የገባኝ ግን ሲነጋ ነው። ጭንቅላቴ ሙቀጫና ዘነዘና ፈጥሮ ሲወቅጠኝ ይሰማኛል።  
ከአንድ ሰዓት ቁዘማ በኋላ ሶፊ ከኋላዬ መጥቶ “ዛሬ ምን ተገኝቶ በጠዋት ተነሳህ እባክህ?” አለኝ። ሁሌ ቀድሞኝ ስለሚነሳ በነገር መጎሸሙ ነው። ሶፊ ሥራ ይኑርበትም አይኑርበት ማልዶ መነሳት ዋና መለያ ጠባዩ ነው። ከእንቅልፋችን ሳንነሳ ቁርስ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ይላል። ከራሱ ደስታ ይልቅ የሌሎች መደሰት የሚያስደስተው ዐይነት ሰው ነው።  ኮቴውን እንኳ ሳልሰማ ስለመጣ ትንሽ ደንገጥ አልኹ። ቡናውን ቀድቶ ወሬ መሰለቅ ጀመርን። እኔና ሶፊ ለእግር ኳስ ብዙም ግድ የለንም፤ ነገር ግን የኔዘርላንድስና የስፔንን ጫዎታ እንዲያመልጠን አልፈለግንም። የት እንደምናይ መከርን። ‘ሐበሻ የሚባዛበት ሰፈር ጎራ ብንል ይሻላል’ በሚል ወደ ካባላጋላ ስለመሄድ እያወጋን እያለ ተስፋለም መጣ። ጠዋት ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ ልክ እንደ ሰባት ዓመት ልጅ ለንቦጩን መጣል ይወዳል። ሁለታችንም ዐይተነው ሳቅንበት።
 ለማናደድ ፈልገን “ዛሬ ቁርስ የመሥራቱ ተራ ያንተ ነው” ብለን አዘዝነው።
“እኔ እንደናንተ መሥራት ስለማልችል ራሳችሁ ሥሩ” ብሎ ወተት ይዞ ቁጭ አለ። ጣቶቹ ብዕር ለመጨበጥና ኪይቦርድ ለማንጣጣት ብቻ የተፈጠሩ ይመስል ቢላን ከሽንኩርት ጋራ ማገናኘት ይከብዳቸዋል። ተስፋለም የሚወደው፤ መጻፍ፣ መዘገብ፣ ኤዲት ማድረግ፣ ዲዛይን ላይ አፍጦ መዋል፣ ኹነት ማሳደድና አዲስ የሥነ ጥበብ ሥራዎችን ማየት ነው። ለጋዜጠኝነት ሞያ ያለውን ፍቅር ስመለከት ድንቅ ይለኛል። የጋዜጠኝነት መርሆዎችን የምሩን ይወስዳል። መርኾቹ ሲጣሱ ይጨቃጨቃል። ማንም ሰው ጽሑፍ አምጥቶ ሲያሳየው የመሰለውን አስተያየት ከመስጠት ወደኋላ አይልም። ዋና አዘጋጅ ኾንኽ ሪፖርተር ለእርሱ ጉዳዩ አይደለም። ካሳየኸው “ይኼን ቁረጠው፣ ይኼን አስቀድመው፣ ይኼን ከኋላ አድርገው፣ ያኛውን አውጣው፤ እንዲያውም ይኼኛው የአንተ እምነት እና አስተያየት እንጂ ከጽሑፉ ጋራ አይሄድም” ምናምን ይልኻል። መረጃ ላይ ያልተንተራሰ ጽሑፍ አያስደስተውም። ከምንም በላይ የሚያስገርመኝ ግን ዜና ለመስበር ያለው ጉጉትና ጥድፊያ ነው።
“አንደኛ ብሬክ ማድረግ አለብን” ይላል ሁሌ።     
“ኳስ ኢትዮጵያን ቪሌጅ እንይ ብለናል” አልኹት፤
“ይመቸኛል፤ ቹፒ አልተነሳችም እንዴ?” ብሎ ጠይቀኝ።
“ተነስታ ቢኾን ታያት አልነበር?”
“አንተ ደግሞ ቀጥ ያለ ጥያቄ ስትጠየቅ፣ ቀጥ ያለ መልስ ስጥ” ብሎ በስጨት አለብኝ። ለምን እንደኾነ አላውቅም በቀን ውስጥ ተስፋለምን አምስት ስድት ጊዜ ካላበሳጨኹት ደስ አይለኝም። ሲናደድልኝ ደስ ይለኛል።
ቹፒ ሳቃችንንና ወሬያችንን ሰምታ መጣች። ቹፒ ትክክለኛ ስሟ ሕሊና ዓለሙ ነው። ጋዜጠኛ ናት። ስለ ዩጋንዳ ኮሚዲቲ ኤክስቼንጅ አመሠራረት እና በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማወቅ የ15 ቀን ጥናት ልታደርግ ነው የመጣችው። ቁርስ ተበላ፣ ስለ አዋዋል ዕቅድ ወጣ። ሙኞኞ ወደ ተባለው የካምፓላ ሆቴል ለመሄድ ተወሰነ። ጊዜውን ዋና በመዋኘት ለማሳለፍና የኳስ ሰዓት ሲደርስ ወደ ካባላጋላ ለመመለስ።
ሙኞኞ ካምፓላ አሉኝ ከምትላቸው ትላልቅ ሆቴሎች ውስጥ አንዱ ነው። አንዱ ነው ማለት ግን በጥራቱ ከሌሎቹ ጋራ ይመሳሰላል ማለት አይደለም። የአዲስ አበባው ሻራተን ከሌሎች እንደሚለየው ሁሉ ይለያል። ባራዳ ቋንቋ ጉደኛ ነው። ከ2000 በላይ አልጋዎችን ታቅፎ ከቪክቶርያ ሐይቅ ስር ተንጣሏል። ወደ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡ ሆቴል ውስጥ ሳይኾን የኾነ መንደር ውስጥ የገቡ ይመስላል። አራት አራት ፎቅ ያላቸው ብዙ አፓርትመንቶች ተሰባጥረው ተቀምጠዋል። ለፈረሶች የተከለለ ትልቅ ስፈራ አለው። የአፍሪካ መዲናዋን አዲስ አበባን 1/4ኛ የሚኾኑ መኝታዎች የታቀፈውን ሆቴል ሳስብ “ደሞ ሆቴል” ብዬ አሸሙሪያለሁ በአዲስ አበባ። ያየኹት ቀን። (አገሬው በሙሉ ሙሴቬኒ ከዚህ ሆቴል ጀርባ ኾኖ ሽልንግ ያትማል እያለ ያንሾካሹካል)።  
ቹፒ ስለ ሙኞኞ ሲወራ ጉጉቷ ናረ። ሆቴሉ ውስጥ የፈለጉበት ቦታ ተዘዋውሮ ማየት ይቻላል፤ ከመዋኛ ስፍራው በስተቀር። ለሚዋኙ 20ሺሕ፣ ለማይዋኙ 10ሺሕ ዱብ ዱብ አድርገን ገባን። ሺሕ ሲባል ያስደንግጣል፤ 8 ዶላርና 4 ዶላሩን እኮ ነው ቁልል አድርገው የሚጠሩት። ሺሕ ሽልንግ ገብቶ ሺሕ ሽልንግ ሲወጣ ግን ይደብራል። ያው ወፍ እንዳገሯ ነው ነገሩ፤ እኛም በሺሕ እንቆጥራለን።
ለማንኛውም ግን ዋና የማልችለው እኔ ነኝ። ዐሥር ሺሕ በባዶ ከፍዬ ገባሁ። አንድ አራቴ ነው መሰለኝ፤ በቁስቋምና በመቀጠያ ወንዞች ውስጥ በልጅነቴ ተንቦጫርቄያለሁ። እርም ብዬ የተውኩት ግን አብሮ አደግ ጓደኛችን ‘ሴጣን ባሕር’ ተብሎ ከሚጠራው ወንዝ ውስጥ ሲዋኝ ሞተ የሚባለውን ዜና ከሰማሁ ጀምሮ ነው። አጋነንኹት አይደል? እርም ብዬ የሚለው እንዴት ብሎ አራቴ ለዋኘ ሰው ይሠራል? ያው ወሬ ለማጣፈጥ ያህል ነው። ለነገሩ ሰይጣን እና ውኃ በአንድነት ወደ ሞት ከሚወስዱኝ ቢቀርብኝስ ብዬ ነው የተውኹት። ውኃ አልፈራም፤ ግን ደግሞ ዋና አልችልም።
ተስፋለም፣ ቹፒና ሶፊ ዋና ገንዳው ውስጥ ገብተው ውኃ ሲራጩ፤ እኔ መጽሐፍ እያነበብኹ በደፍንደቃቸው ደስ እያለኝ ቆየሁ። ተስፋለም ያደገው ጦር ኀይሎች አካባቢ ከሚገኘው ቶሎሳ ሰፈር ነው። እርሱም እንደኔ ዋና አይችልም። እየደፈቁ እያወጡ ያስተምሩታል። ይስቃል፣ ይቦርቃል።
ለተስፋለም አንድ ነገር የማትችል ከኾነ አልቻልክም ነው። መቻል የሚባለው ነገር ከመሞከር ይመጣል። ስለዚህ እየተሳሳተ ይዋኛል። እየዋኘ ይሳሳታል። ውኃው ሲያስጨንቀውና ትንፋቀሽ ሲያጥረው መሬት ላይ እንዳለ ሰው ቀና ብሎ ለመቆም ይታትራል። መጽሐፍ ማንበቤን ትቼ ውኃው ሲንገዳግደውና ፊቱን አስር ጊዜ ሲሞዥቅ እያየኹ እስቃለሁ። 
ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲኾን ሙኞኞን ጥለን ከመውጣችን በፊት በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ጸሐይ ስትጠልቅ ለማየት ሄድን። ነፋሱ ከቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ሙዚቃ እያባዘተ ጆሯችንን ይዳብሳል። ጸሐይዋ ሐይቁን ሰንጥቃ እያጥበረበረች ውስጡ ገብታ ትዋኛለች። ውኃው ውስጥ ስትኾን ስብርብር ትላለች-እንደሚሽኮረመም ልጃገረድ። ድንገት ዞር ስል ሐበሻ ባልና ሚስት ትንሽ ትንቡክ ያለ የሦስት ዓመት ልጅ ይዘው መጡ። ማለፍ አልቻልኩም። ማጫወት ጀመርኩ። ጉንጩን ግምጥ አደረግኹት። ተስፋለምም ተከተለኝ። ከልጁ ጋራ ትንሽ ጊዜ ፈጨን። እናቱና አባቱ ኤርትራውያን ናቸው። ከልጃቸው ጋራ ጊዜ ስለሰጡን አመስግነናቸው ወጣን። ጥድፊያ ወደ ራትና ኳስ።
ከሙኞኞ ወደ ካባላጋለ መሄድ ፈተና ኾነ። ከሰላማ ሮድ የሚመጡ የሚኒባስ ታክሲዎች ሰው እንደ ጎመን አጭቀው እብስ ይላሉ። እጆቻችንን በተደጋጋሚ ከመዘርጋታችን የተነሳ ትከሻችን ሊረግፍ ምንም አልቀረውም። ስልችት አለን። “አማራጭ የሌለበት ውብ አገር” እያልን ማጉረምረም ጀመርን። ከሙኞኞ ግቢ ውስጥ አንዲት ራቫ ፎር እንደ ዓሊ እየተጎተተች ቀረበችን። ያ ትንቡክ ያለ ሕጻን ከኋላ ወንበር ላይ ተሰፍቶ ጥርሶቹን ብልጭ አደረጋቸው። መኪናዋ ቆመች። ለሊፍት መኾኑ ሲገባን ሮጥ ሮጥ ብለን ገባን። ሶፊ ከአንድ ሰዓት በፊት ጥሎን ሄዷል።
“እስከ ካንሳንጋ መንገድ እናቅልላችሁ” አለች ሚስትየዋ የትግርኛ ቅላጼ ግምድ ባደረገው አማርኛ። በግዕዝ የምታዋራን ነበር የምትመስለው። የኾነ የሚጣፍጥ ነገር አለው።
“ትልቅ ነገር ነው ለእኛ፤ በጣም ነው የምናመሰግነው፤” አለ ተስፋለም። ባልየው እስከ ካንሳንጋ ነዳን።
ካባላጋላ ከካንሳንጋ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል። ቹፒ ርቧት ስለነበር ‘ታክሲ እንያዝ ወይም ቦዳ ቦዳ እንፈናጠጥ’ አለች። የለም እንደርሳለን በሚል ወገምናት። ሁለት ለአንድ መሸነፏ ሲገባት ዝም አለች። ደስ እያላት ግን አልነበረም። የምስራቅ አፍሪካ የሐበሻ ምግብ ወዳጆች ከሚያዘወትሩት የአብነት ምግብ ቤት ሄድን። መብላት የፈለግነው ክትፎ ነበር። አብነት በዘወትር ቀለስላሳ አንደበቱ ከወገቡ ስብር ብሎ “ክትፎ ጨርሰናል፤ ሌላ ምን ይኹንላችሁ?” አለን፤ የአብነት ምግቡ ብቻ ሳይኾን አጎነባበሱም ገበያ ስቦለታል።  
“ክትፎ ነበር የፈለግነው፤’ ብለን ወጣን። ክትፎ ቀን ከሌት ወደማይጠፋበት ቤት አመራን። ሆቴሉን ማቢራ ይሉታል፤ ከውስጡ ያለውን የክትፎ ፋብሪካ ደግሞ ሌዋውያን የሚል ስም አውጥተውለታል። የሌዊ ሰዎች ክትፎ ስለማወቃቸው እርግጠኛ ባልኾንም፤ ‘በስማቸው ታዋቂ የክትፎ ፋብሪካ እንደተከፈተላቸው አያውቁ’ እላለሁ ሁሌ ለራሴ። ክትፎው ከቀረበበት ሰዓት አንስቶ በላን ሳይኾን አጋበስን ነበር የሚባለው። ቹፒ የእግር ኳሱ ሰዓት አልፎ እንዳንደርስ የሚለው አስጨንቋታል። ተስፋለምም እንደዚያው። በተለይ ቦታ እናገኛለን የሚለው ጉዳይ በጣም አሳስቧቸው ነበር።
እኔ ደንበኝነቴን ተማምኜ አንዱን አስተናጋጅ ወደ ፊት ቦታ ፈልግ ብዬ አስሞስነዋለሁ እያልኹ ሳስብ ነበር። አልነገርኳቸውም። እየተጣደፍን በልተን ወጣን። ካንሳንጋ ሁሌ ባለፍኩበት ቁጥር ሁለት ቦታዎችን ያስታውሰኛል። ቺቺኒያንና ሰባተኛን። ሁለቱን ሰፈሮች አደባልቆ የያዘ ቦታ ነው። ዩጋንዳዊ ስልክ ደውሎልህ ‘ካባላጋላ ነኝ’ ብለህ ከመለስክ “አምሮሃል ማለት ነው ዛሬ” ይልኻል። “ምን?” ስትለው “ሄሄሄሄ” ብሎ ይመልስልኻል። ዩጋንዳውያን “የእንትንን” ስሙን አይጠሩትም፤ ግን እንደ ጉድ ይበነግጉታል። ከካባላጋላ ባሮች ውስጥ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወሲብ የሚሸጡ ሴቶች ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልተው ይጠብቁኻል። ወጣ ስትል መንገድ ላይ የሚጠበስ ዶሮና ቻፓቲ (ቂጣ) በእንቁላል እየሞለሞሉ የሚሰጡ ባለ ትናንሽ ብረት ምጣዶች ትኩስ ትኩሱን ያቀርቡልኻል። በአቅምህ ገዝተህ እንድትበላ እነ እናት ጓዳዎች በስጋ ያበደ ሩዝ፣ በዓሳ የጣፈጠ ማቶኬ፣ ሜዳውን ከለል አድርገው ይሰጡኻል።
ቹፒ ግርግሩን ማቋረጥ ምጥ መስሎ ስለታያት አሁንም ቦዳ ቦዳ ካልያዝን አለች። አንሰማሽም አልን። ካምፓላ ላይ ከአንድ ኪሎ ሜትር በታች ለኾነ ርቀት ቦዳ መያዝ ጥጋብ ነው። እጇን ጠበቅ አድርገን ይዝን ወደ ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት አሻቀብናት። ስንደርስ ሬስቶራንቱ ጢም ብሎ ሞልቷል። የወቀሳ ዐይኖቿን ለመሸሽ ወደ ፊት ራመድ አልኩ። አንዱን አስተናጋጅ ጠርቼ ከስክሪኑ ፊት ለፊት ቦታ እንዲፈልግ በትዕዛዝም በልመናም ድምፅ ጆሮው ውስጥ ነገርኹት። ጥቂት ቆይቶ ተመለሰ። የማይታሰብ መኾኑን ነገሮኝ፤ ወንበሮች ይዞ መጣና “በግማሽ በኩል ስክሪኑን፤ በግማሽ በኩል ደግሞ ከጠባቧ ክፍል ውስጥ ያለውን ቲቪ እያያችሁ ተደሰቱ” አለን። ምርጫ የለም። የተገኘችውን ዕድል ፈጥነን ተጠቀምንባት።
ኳሱ ተጀመረ። በተጀመረ በዐሥር ደቂቃ ውስጥ ሶፊ መጣ። የያዝኹለትን ወንበር ሰጠኹት። ጫዎታው የጠበቅነውን ያህል አስደሳች አልነበረም። ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ማየቱንም አልወደድነውም ነበር። ሁለተኛውን ግማሽ ጫዎታ ሌላ ቦታ ሄደን እናያለን ብለን ዶለትን። ተስፋለም ራቅ ብሎ ቁጭ ብሏል። ተስፋለም እያንዳንዷን ሰከንድ ይዘግባት ይመስል በትኩረት ይከታተላል። ቹፒ ከእኛ ጀርባ ኾና ታያለች። እኔና ሶፊ አጠቃላይ ኹኔታው ስላልተመችን ምን ጊዜ ፊሽካ በተነፋና በወጣን ብልን እየተቁነጠነጥን ነው። የኾነ ብረሩ ብረሩ የሚል ስሜት ወጥሮ ይዞናል። ሁለታችንም ጃኬታቾችን ደረብን።
የኳስ ሰዓቱ 44፡10 ላይ ያሳያል። ድንገት መሬትን የሚንጥ፣ ጆሮን የሚያናውጥ፣ ውስጥን ወደላይ የሚገለብጥና ሁለመናን የሚጎረብጥ ፍንዳታ ተሰማ። ሶፊ ከፊቴ ካለው ወንበር ላይ ሚዛኑን ስቶ ሲንሸራተት እንደ ሕልም የቀኝ እጁን አፈፍ አድርጌ ስይዘው ብቻ ይታወቀኛል። ባጋጣሚ ወደ ስክሪኑ ፊቴን አዙሬ ስለነበር ከስክሪኑ ጥቁር ጭስ ሲወጣ ብቻ ተመልክቻለሁ። ሰከንዶች የዓመታት ያህል ረጅም የኾኑ ይመስል ነበር። በእውንና በሕልም መካከል ያለሁ መስሎ ተሰማኝ።
እንደአጋጣሚ ኾኖ ፊቴን ወደ ትልቁ ስክሪን አዙሬ ነበር። ዐይኔ ያየው የስክሪኑ ጨርቅ ሲነድና ሲጨስ ነው። ወዲያው ግቢው በጭስ ታፈነ። ምን እየተከናወነ እንደኾነ ለማወቅ ግራ ተጋባን። አንዱ ጮክ ብሎ “ ስክሪኑ ነው የፈነዳው” እያለ ይጮኻል። ባዶ ጨርቅ ብቻውን ዝም ብሎ ሊፈነዳ እንዴት ይችላል? የሚለውን እያሰብኩ ዞር ስል ግማሽ ፊቱ የተቦጨቀ ሰው የአሳንሳ ተይዞ ሲያልፍ ተመለከትሁ። ቦምብ እንደኾነ የገባኝ ያኔ ነበር። ወዲያው ጭንቅላቴ ውስጥ የመጣው ሌላ ተጨማሪ የተጠመደ ቦምብ ሊኖር ይችላል የሚለው ነበር።
ሶፊን፣ ተስፋለምንና ቹፒን “ይኼን ግቢ በፍጥነት ለቀን መውጣት አለብን! ሌላ ቦምብ ሊኖር ይችላል!” ብዬ በትዕዛዝ ጮክኹባቸው። እንዲከተሉኝ ነግሬ ወደ ውጪ በር ልወጣ ስል የፕላስቲክ ወንበሮቹ መንገዱን ዘግተውታል። ወንበሮቹ እየጠለፏቸው ብዙዎች ይወድቃሉ፤ ይነሳሉ። ያገኘሁትን ቀዳዳ ተጠቅሜ የውጪው በር ላይ ደረስኹ። ዞር ስል ማንም አልተከተለኝም። ተበሳጨሁ። የምላቸውን ስላልሰሙኝ አረርኩ። ተመልሼ ወደ ውስጥ ስገባ ተስፋለምና ሶፊ የተጎዳ ሰው እየረዱ ነው። ቹፒ አንዲት ፈረንጅ ለማረጋጋት ጥረት ታደርጋለች። ለቅሶ፣ ዋይታና እሪታ ግቢውን ዋጠው። ጉዳት የደረሰባቸው ፈረንጆችና ሐበሾች በድንጋጤ ይጮኻሉ። አንዳንዶቹ ራሳቸውን ስተዋል። እኔም እነርሱን ወደማገዝ ተሻገርኹ።  
ተስፋለም ከጋዜጠኝነት ውጪ ሌላ ነገር ያን ያህል ይሳካለታል ብዬ አላስብም ነበር። በዚያች ቅጽበት የነፍስ አድን ጥሪ ላይ ተልእኮ ያለው ባለሞያ ይመስል ነበር። እያንዳንዱን ጉዳት የደረሰበትን ሰው በሙሉ በቻለው መጠን ለመርዳት ይራወጣል። ደንግጧል። በዚያ ድንጋጤው ግን የሚገርም ብርታት ይነበብት ነበር። እየተጋገዝን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በወንበር ላይ እያመቻቸን ማስቀመጥ ጀመርን። የአንዳንዶቹን ቀሚስና ሱሪ እየቀደድን የሚደማውን የሰውነት ክፍላቸውን ማሰር ያዝን።
ያ ያልታሰበ ቦምብ የፈነዳው እኛ ተቀምጠን ከነበረበት ከአንድ ሜትር ተኩል ርቀት ላይ ነበር። ሞትን በዚህ ቅርበት እንደምናየው አንዳችም ግምት አልነበረንም። ባንድ በኩል ወደዚህ ቦታ ቀድመን አለመምጣታችንንና ሰዓቱን በዎክ ማሳለፋችንን እንደ መልካም አጋጣሚ ማሰብ ጀመርኩ። አስተናጋጁን በጠየቅኹት መሠረት ቦታ አግኝተን ቢኾን ኖሮ ሄደን የምንጣደው ቦምቡ ከተጠመደበት ቦታ ላይ ነበር። ስድስት ኤርትራውያንን እና አንድ ኢትዮጵያዊን በሞት ተነጠቅን። ዐሥራ ሦስት ሰዎች በከባድና ቀላል ጉዳት አደጋ ሰለባ ኾኑ። በፍጥነት ቦታውን ለቀን ራሳችንን ለማረጋጋት ወደ ሌላ ሆቴል ሄድን።
ተስፋለም ወደ ጋዜጠኝነቱ ከተመለሰ ቆየ። መንገድ ለመንገድ ለሚያውቃቸው የዓለምአቀፍ ጋዜጠኞችና ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች የነበረውን ሁኔታ መዘገቡን ቀጠለ። ከሞት ጋራ ፊት ለፊት መገናኘቱን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም። ዜናው በፍጥነት ለዓለም መድረስ ስላለበት በስልኩ ከተለያዩ ሰዎች ጋራ ማውራት ቀጠለ። ከሞት ጠርዝ ላይም ቆሞ “ብሬክ” ስለማድረግ ያስባል፤ ለእርሱ ዋናውና ትልቁ የጋዜጠኝነት ግብ መረጃን ለሕዝብ በፍጥነት ማድረስ ነው። ሲጨርስ ወደ ድንጋጤው ተመለሰ። ያ ቅጽበት ስለ ሰው ልጅ ውስብስብ ባሕርይ የተረዳሁበት አጋጣሚ ነበር። አራታችንም ከአንድ ሆቴል ውስጥ ቆዝመን ተቀመጥን። ሁላችንም ማልቀስ ጀመርን። ሌላ ዜና ሰማን። ካምፓላ ውስጥ ታዋቂ ከኾነው የራግቢ ክለብ ውስጥ ሌላ ቦምብ ፈንድቶ ከአምሳ ሰዎች በላይ መሞታቸውን ሰማን። ሽብርንና ሽብርተኞችን መርገም ጀመርን። አልሻባብ የሚባለውን ቡድን እንደ ጭራቅ ጠላነው። አልሸባብን የፈጠሩብንን ፖለቲከኞች አምረን መውቀስ ጀመርን።
የተቀመጥንበትን ሆቴል ለቀን ቹፒ ይዛው ወደነበረው ሆቴል ተጓዝን። ሁሉም ነገር ሕልም እንጂ እውነት አይመስልም። የለበስነው ልብስ በሰዎች የተቆራጠ ስጋና ደም እንደተበከለ ያወቅነው ዘግይተን ነው። የተስፋለም መነጽሩ ሳይቀር በቁርጥራጭ ስጋ ተሞልቷል። ፊቱ ላይ ደም ተለጥፏል። ተስፋለም ራሱን በመስታዎት ማየት ሲጀምር እንባው ይወርድ ጀመር። ቁጭት፣ እልህና ንዴት ያንገበግበው ጀመር።
ተስፋለም በየዓመቱ ቀኑን እያስታወሰ “ሞትን ለጥቂት ያመለጥንበት” የሚል መልእክት በፌስ ቡክ ይልክልን ነበር። ዛሬ ተስፋለም የዓለም እግር ኳስ ጫዎታን ለማየት አልታደለም፤ ከሽብርተኛው አልሻባብ ቦንብ የተረፈበትን ቀን ለማሰብም ጊዜና ፋታ የሚሰጠው መንግሥት አላገኘም። እንዲህ ዐይነቱን ጠንቃቃና ለሞያው ከፍ ያለ ክብር የሚሰጥ፣ ሽብርና ሽብርተኞችን አምርሮ የሚጠላ ዜጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ዐመጽ ለማነሳሳት በሚል ጠርጥሬዋለሁ ብሎ አስሮታል። ገና በምን እንደሚከሰውም አይታወቅም። ዜና ከመስበር ውጪ ዕቃ ለመስበር እንኳ ፍላጎት እና ምኞት የሌለውን ተስፋለምን በዐመፅ መጠርጠር ለመንግሥት የሞት ሞት ነው። ተስፋለምን ባሰብኩት ጊዜ . . . . .ተነግረው የማያልቁ ብዙ ትዝታዎች በውስጤ ይጎፈላሉ::

ይህ ጽኹፍ በቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጠኛ ማስረሻ ማሞ ከወራት በፊት ተጽፎ የነበረ ቢሆንም ለብዙ አንባቢያን ይደርስ ዘንድ በገጻችን አውጥተነዋል::


በላይ ማናዬ

 በታላቁ መጽሐፍ የተጠቀሰ አንድ ታሪክ ላይ አንዲት እናት ልጇን በጓደኛዋ ስለመሰረቋ እናነባለን፡፡ ይህቺ እናት ልጄን ተሰረቅኩ ብላ ወደ ጠቢቡ ሰለሞን አቤት ትላለች፡፡ ጠቢቡ ሰለሞንም ሁለቱን ሴቶች ተሰረቀ ከተባለው ህጻን ጋር ተያይዘው እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡ ጠቢቡ ንጉስ ሰለሞን እውነተኛ እናት የትኛዋ እንደሆነች ለማወቅም የራሱን የምርመራ ዘዴ ሲጠቀም እናስተውላለን፡፡ በዚህም ሁለቱ ሴቶች የተካሰሱበትን ጉዳይ ሰለሞን በጥበብ ትክክለኛ ዳኝነት ሰጥቶ ያሰናብታቸዋል፡፡ ህጻኑም እውነተኛ እናቱን ያገኛል፡፡ ይህ ፍትህ የተሰጠው ከብዙ መመላለስ በኋላ አልነበረም፤ አፋጣኝና ትክክለኛ ፍርድ ነበር የተሰጠው፡፡
 እንደ ጠቢቡ ሰለሞን በአንድ ጀንበር በጥበብ ተከሳሽንና ከሳሽን ሰምቶ ትክክለኛ ውሳኔ የሚሰጥ የዳኝነት አካል እንዲኖረን በባዶ የምመኝ ሰው አይደለሁም፡፡ ነገር ግን ማነኛውም ተከሳሽ የተከሰሰበት ጉዳይ ተጣርቶ በፍጥነት ውሳኔ እንዲሰጠው፣ ፍትህ እንዲያገኝ እፈልጋለሁ፡፡ የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል ይባላል፡፡ ትክክለኛ አገላለጽ ነው፡፡ እውነትም በሀገራችን በዚህ አገላለጽ መሰረት ውሳኔ ተጓትቶባቸው፣ ፍትህ የተነፈጉ ብዙዎች ናቸው፡፡
 ማክሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2007 . በእነ እስማኤል ኑርሑሴን የክስ መዝገብ 1 አመት 6 ወር በላይ በእስር ሲሰቃዩ የቆዩ 12 ተማሪዎች እና 1 መምህር በመጨረሻ ብይናቸው ሲሰማ የሆነው ‹‹የዘገየ ፍትህ እንደተነጠቀ ይቆጠራል›› የሚለውን አባባል ያስረገጠ ነበር፡፡ ምክንያቱም ተከሳሾቹ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የተበየነው 6 ወር እስር ብቻ ነበር፤ በእስር የቆዩት ግን 1 አመት 6 ወር ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየን ተከሳሾቹ አፋጣኝ ፍትህ ባለማግኘታቸው ብቻ ተጨማሪ አንድ አመት እስርን በግፍ አሳልፈዋል ማለት ነው፡፡ በእነ እስማኤል ኑርሑሴን የክስ መዝገብ ያለአግባብ ከተፈረደባቸው ጊዜ በላይ በእስር ያሳለፉት ሰዎች ከጅግጅጋ፣ ከሲቪል ሰርቪስ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማ፣ ከደሴ፣ ከሐዋሳና ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች ተለቅመው የታሰሩ 12 ሙስሊም ተማሪዎችና 1 አስተማሪን የተካተቱበት ነበር፡፡ በአጠቃላይ የተጓተተው ክስ ሂደት ብይን ለማግኘት 18 ወራትን ወስዷል፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ደግሞ ተከሳሾቹ በእስር ላይ ነበሩ፡፡ በግንቦት 2005 . ክስ የተመሰረተባቸው እነዚሁ ተማሪዎች በተለያዩ ሰበባሰበቦች ምክንያት ችሎቱ እየተጓተተ በመቆየቱና የፍትህ ስርዓቱ የዜጎችን መብት ማስከበር በማይችልበት ደረጃ በመኮላሸቱ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳ ክሳቸው ከሚያስፈርድባቸው በላይ በእስር እየቆዩ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ሲያሳስቡ ቆይተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ሰሚ ጆሮ አላገኙም ነበር፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለረጂም ጊዜ ተስተጓጉለዋል፡፡ ሊሰሩት የሚችሉት ነገር ሁሉ ተደናቅፎ መቆየቱም እሙን ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ፍትህ አገኙ ወይስ ተነፈጉ?
በነገራችን ላይ አፋጣኝ ፍትህ ማግኘት መሰረታዊ መብት (The right to speedy trial) ነው፡፡ በህግም ጥበቃ ያለው መሆኑን በተለያዩ ሀገራት ህጎች ተደንግጎ ይታያል፡፡ በአሜሪካ (The Sixth Amendment to the U.S. Constitution) በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል፡፡ በእርግጥም አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ከድሮ ጀምሮ የነበረ መሰረታዊ መብት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በእንግሊዝ በንጉስ ሄነሪ ሁለተኛ (1154–1189) ጊዜ እንግሊዛውያን አፋጣኝ ፍትህ ማግኘት እንዳለባቸው በህግ ተደንግጎ ነበር፡፡ 1215 .. ደግሞ ንጉሱ በእጁ የሚገኙ የፍትህ ጥያቆችን ማዘግየት እንደማይችል በማግና ካርታ (Magna Charta) በግልጽ ደንግጎ ነበር፡፡ ይህ ፍትህን በአፋጣኝ የማግኘት መብት በኢፌዴሪ ህገመንግስት ላይ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡ በህገመንግስቱ አንቀጽ 37 ላይ ‹‹ፍትህ የማግኘት መብት›› ሲገልጽ እንኳ አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብትን በተመለከተ የሚለው ነገር የለም፡፡ ብዙ ዜጎች በህግ ጥላ ስር ውለው ክስ ተመስርቶባቸውም ይሁን ክስ ሳይመሰረትባቸውየፍትህ ያለህእያሉ በየእስር ቤቱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ዜጎች የፍርድ ቤት ውሳኔው ራሱ ፍትሃዊ ነው በማይባልበት ሁኔታ እንኳ አፋጣኝ ብይን (‹‹ፍትህ››) ሲሽቱ ቢታይም የፍላጎታቸው ሲሞላላቸው አይታይም፡፡
 ባለፈው ሚያዝያ 17 ቀን 2006 . ለእስር የተዳረጉት የዞን 9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች እንሆ ከታሰሩ 8 ወራት አልፈዋል፡፡ እስካሁንም ግን ክሳቸውን በውል አላወቁትም፡፡ ክስ ሳይመሰረትባቸው በምርመራ ሰበብ ወራትን አሳልፈው፣ ክሱ ተመሰረተ ከተባለ ጀምሮ የተመሰረተው ክስ እንዲሻሻል በሚል ሌላ ሰበብ እስካሁን ክሳቸው ምን ላይ እንዳረፈ በግልጽ አልታወቀም፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ጦማሪዎቹና ጋዜጠኞቹ በእስር ላይ ናቸው፡፡ ከቀናት በፊት እስረኞቹ በሚገኙበት ቂሊንጦ እስር ቤት ተገኝቼ በጠየኳቸው ጊዜ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስና ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ በዋናነት አፋጣኝ ‹‹ፍትህ›› ማግኘት እንደሚሹ ነበር በአንክሮ የነገሩኝ፡፡ ናትናኤል ፈለቀ ይህን በተመለከተ፣ ‹‹ትክክለኛ ፍትህ አገኛለሁ የሚለው ተስፋዬ በጣም መነመነ ነው ነገር ግን ቢያንስ አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ እሻለሁ፡፡ ክሳችንን በውል ሳናውቀው ወራት ተቆጥረዋል፤ የሚታይ ጠብ የሚል ነገር እያየን ግን አይደለም›› ማለቱን አስታውሳለሁ፡፡ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስም በተመሳሳይ፣ ‹‹ፍትህ መጠበቁ ሞኝነት አንደሆነ ይገባኛል ውሳኔው ምንም ይሁን ምን ግን አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ እፈልጋለሁ›› ብሎ ነበር፡፡ ዳሩ ግን አሁን ባለው የተንዛዛ አሰራር ፍርድ ቤት መኖሩ፣ ዳኞች መሰየማቸው ብቻ ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ አያደርጋቸውም፡፡ የፍትህ ተቋማት የስርዓቱ አገልጋዮች በሆኑበት ሀገር አፋጣኝ ፍትህ ቀርቶ በተንዛዛው ሂደት ውስጥ አልፎም ቢሆን ትክክለኛ ፍትህን ማግኘት ቅዠት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ዜጎች ፍትህ ያገኙ ዘንድ አጠቃላይ ስርዓቱን የመቀየር ወይም የማረቅ ትልቅ ስራ ይጠይቃል፡፡

‹‹ ስሜ አቤል ዋበላ ነው፡፡ አዲሱ አመት ሲጠባ በአዲስ መንፈስ አዲስ ህልም ለአገሬ ማለም የነበረኝንም ማጠናከር እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያችን የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የሀብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዩነቶች አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት ከነልዩነታችን በጋራ ለታላቅነት የምንጠቀምባት ለሁላችንም ዕኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት ሁላችንም እንደየ ችሎታችን ለጋራ ደህንነታችን ነፃነታችን እና ብልፅግናችን የምንሰራባት ብቻ ሳይሆን በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዕኩል የሚያፈቅራት ኢትዮጵያ እንድትሆን እመኛለው፡፡ ይህ የእኔ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው፡፡››
ከላይ የሰፈረው ጽሁፍ ዞን ዘጠኝ ባዘጋጀው አራተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ(Online Campaign) ላይ የተጠቀምንበት ነበር፡፡ የዘመቻው ርዕስ ‹ኑ አብረን ኢትዮጲያዊ ህልም እናልም › ሲሆን የተካሄደውም በ2005ዓ.ም መገባደጃ ወር ጰግሜ ላይ ነው፡፡ በአጋጣሚ ዘመቻው መንግስት የማናውቀውን ‹ወንጀል› እየፈለገብን እንደሆነ ከሁነኛ ምንጮች ከተረዳንበት ወቅት ጋር ገጥሟል፡፡ ለነገሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀደም ፓርላማ ቀርበው ‹‹ኢህአዴግ ሀሳብ የሚፈራ ድርጅት አይደለም››ሊሉ እንደፎከሩት ሳይሆን የሃሳብ ልዩነት እንደሚያስበረግገው ስለምናውቅ መስጋታችን አልቀረም፡፡ ከሌሎች ምንጮችም እርግጠኛ ያልሆኑመረጃዎች ደርሰውን ነበር፡፡ ይሄኛው ግን እርግጥ የሆነ ጅቡ ከበራፍ ላይ እንደቆመ የሚያበስር ነው፡፡
እንደ ሌሎች ዘመቻዎች ሕገ መንግስታዊነት፣ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ….. የመሳሰሉ ለሃገራችን “ቅንጦት” የሚመስሉ ርዕሶችን ማንሳት አልፈለግንም፡፡ አሁን የድራማው ዘመን ተቀይሮ እውናዊ  ሆኗል፡፡ ይህም የኔ የምንለው ትውልድ ምን አይነት ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደተዘፈቀ በብርቱ እንድናስብ አደረገን፡፡ ለዚህም ነበር ሁሉን የሚያሳትፍ የትውልድ አቻዎቻችንን የሚጠራ ሰፊ ርዕስ የመረጥነው፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ውጤቱ አርኪ ነበር፡፡
ስርዓቱ ግን ስለሃገራችን ያገባናልማለታችንን የትውልድ አቻዎቻችንን መፈለጋችንን አልወደደውም፡፡ የዘውጉን እውናዊነት ለማጠናከር ትምህርት ሊሰጠን ወደደ፡፡ መምህራን፣የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ቤተ ሙከራ ተዘጋጀ፡፡ አንደ አጋጣሚ ብቻ ሆኖ ከዞን ዘጠኝ ኢ-መደበኛ የጦማሪያን ቡድን ስድስታችን እና ሌሎች ሶስት ጋዜጠኞች (ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዎርጊስ) ለተማሪነት ተመረጥን፡፡ ትምህርቱም ሚያዚያ17/2006 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ውንጀል ምርመራ ዘርፍ (በተለምዶ ማዕከላዊ) ተጀመረ፡፡
ትምህርት አንድ
የመጀመሪያው ትምህርት የሀገራችን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ትንታኔ የሚሰጥ ወዳጃችን በዞን ዘጠኝ የሚደረጉ ሙከራዎችን አድንቆ ተጨማሪ መስራት ያለብንን ስራዎች ሊጠቁመን ‹‹ እናንተ ብዙ ጊዜ የምታተኩሩት የከተማ ፖለቲካ ላይ ነው፡፡ እስኪ ወደገጠር ጫንጮ እንኳን ሂዱ ከገበሬው ጋር ጠጅ እየጠጣችሁ ብሶቱን አድምጡና ጻፉ፡፡›› እንዳለን አስታውሳለሁ፡፡
እኛም ይህን ትችት ሙሉ ለሙሉ ተቀብለን በተግባር ባናደርገውም ከከተማ ወጣ ብሎ ለመመለስ ዕቅድ ይዘን ነበር፡፡ ማእከላዊ ግን ይህን ድካማችንን አቅልልሎ ሁሉንም አይነትኢትዮጵያዊ መልኮችን ከየአቅጣጫው አመጣልን፡፡ እነ ኡባንግን ከጋምቤላ፣ እነዚያድን ከደጋሃቡር፣ እነ አብድልከሪምን አቤኒሻንጉል፣እነ አያያዎን ከጎንደር፣እነ ቄስ ብርሃኔ ከአክሱም፣ እነ ሼህ መሀመድን ከጅማ አሰባሰበልን፡፡ የእስር ቤቱን ጨለማ ቀን እና ጨለማ ሌሊቶች ከልብ በሆኑ ወሬዎች አደመቅናቸው፡፡ ፖለቲካዊ ብልጣብልጥነት ያልነካካው ከጭቆናው የመጀመሪያ ረድፍ ገፈት ቀማሾች የሚቀዳ እውነትን አደመጥን፡፡በሰውነት ከመከበር አንስቶ እስከ የምድሪቱን ፍሬ በዕኩልነት መጠቀም ጥሮ ግሮ ኑሮን ለማሸነፍ የሚያስችሉ ዕድሎች ፍትሕአዊነት፣ ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሀሳብን መግለጽ በወረዳና ቀበሌ ደረጃ የሚያስከፍለው ዋጋ፣ ከስር ባሉ የቢሮክራሲው አካላት የሚፈፀም ተቋማዊ ግፍ በአጠቃላይ አድርባይነትና አስመሳይነት በመላው ሀገሪቱ እንዴት እንደሰፈነና ብዙሃኑም ኑሮውን በቀቢጸ ተስፋ እንደሚገፋ ተረዳን፡፡ ሁሉም የጎላው ምስል ግን ዛሬም ፌደራሊዝሙ መሰረታዊ የሆኑትን የስልጣንና የሀብት (Power and Resource)ጥያቄዎች እንዳልመለሰ በጉልህ ይናገራል፡፡
ከመታሰሬ በፊት በነበረኝ ግምት በርካታ የኦሮሞዎ ተወላጆችን በማረሚያ ቤት እንደማገኝ ጠብቄ ነበር የመጀመሪያው ሰሞን  ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ከታሰሩ አንዳንድ ሙስሊም ኦሮሞዎችበስተቀር ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች አልነበሩም፡፡ ይሄ ግን ብዙ አልቆየም፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በሚነካው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን የተነሳ በተፈጠረው ግርግር በርካታ ኦሮሞ ተማሪዎች ከየዩንቨርስቲው ተለቅመው መጡ፡፡ ያን የስቃይ ቤት በሳቅ ጨዋታቸው አደመቁት፡፡ ውይይታችንም ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን ዳሰስን፡፡ እኛም ብዙ ተማርን፡፡ በእነርሱ መሪነት በህብረት የምናዜማቸው የኦሮሚኛ ዘፈኖች የነበርንበትን አስቸጋሪ ሁኔታ አስረሱን፡፡
ከሁሉም ከሁሉም biyya Toodhuufen silaala yaa Biyaa Dubro maagala (የጠይም ቆንጆዎች መፍለቂያ ሀገሬ መጥቼ አይሻለሁ) የሚለውን እንጃ የኔን ቀልብ የሳበ ዜማው አንጀቴን ሰርስሮ የገባ ነበር፡፡ አገሬ ጠያይም ቆንጆ ልጆችሽ በነፃነትና በእኩልነት እንዲኖሩብሽ አልማለሁ፡፡ይህ የኔ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው፡፡   
ትምህርት ሁለት
ሁለተኛው ትምህርት በተግባር የተደገፈነው፡፡ በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት የተሰሩ የሰብዐዊ መብት አያያዝ ሪፖርቶችን ማንበብ ከጀመርኩኝ ጥቂት አመታት አልፈዋል፡፡ሁሌም እንደተለመደው ኢትዮጵያ የዜጎቻቸውን ሰብዐዊ መብት ከሚጥሱ እና የማሰቃየት ተግባር የሚፈፅሙ በተለይም በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚጠራው የመንግስት ተቋም በዋነኝነትእንደሚጠቀስ ብዙዎቹ ሪፖርቶች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት እስካሁን ድረስ የማሰቃየት ተግባርን (Torture) እኔም ሆነ ጓደኞቼ የምንረዳው እንደማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁ ነበር፡፡በተለይ እኔ በበኩሌ የተለየ ትኩረት እንደማልሰጠው አልሸሽግም፡፡
አሁን እነዚያ የአለማወቅ ወራት አልፈዋል፡፡ በታሪክ መጽሃፍት ላይ በዘመነ ደርግ እንደሚፈጸሙ ያነበብናቸው አስከፊ ተግባራት አሁንም በሃገራችን እንደሚፈፀሙ ህያው ምስክሮች ሆነናል፡፡ ከስነ ልቦናዊ የማሰቃየት ተግባር አንስቶ የተለያዩ የማሰቃያ ቁሳቁስ በመጠቀም እስከሚፈፀሙ ዘግናኝ ተግባሮች በእኛና በሌሎች ላይ ሲፈፀም ተመልክተናል፡፡በከፍተኛ ድብደባ እግሮቹ የሚወላከፉ፣ መራመድ አቅቶት በሸክም ወደ ማረፊያ ቤት የሚመለስ፣ በግርፋት ብዛት ጀርባው ብዙ ሰንበርየተጋደመበት፣ ብልቱ ላይ ሁለት ሌትር ውሃ በመንጠልጠሉ ምክንያት ሽንቱን መሽናት የተቸገረ፣ ጆሮው በጥፊ ደንቁሮና አፍንጫው የሚደማሰው መመልከት የየዕለት ተግባራችን ሆነ፡፡ በኤሌክትሪክ ሾክ የተደረጉና ‹ወፌ ላላ› ተገልብጠው እንደተገረፉ የሚናገሩ ተጠርጣሪዎችም አጋጥመውኛል፡፡ ስድብ፣ ዛቻውና የማዋረዱ ተግባር አእምሮ ሊቆጣጠረው የሚችል አይደለም፡፡ የቀረውን የማሰቃየት ተግባር ሲፈፀም ያዩና በራሳቸው ላይ የተፈፃመባቸው ይናገሩት፡፡   
ይህ ተቋም ባለበት ከተማ ምንም ነገር እንዳልተፈጠሩ ቆጥሬ ስራዬን እየሰራሁ እየበላሁ እና እየጠጣሁ በቆየሁባቸው ዓመታት አፈርኩኝ፡፡ በአገሬ ኢ-ዲሞክራሲያዊነት እንዲታለፍ ዲሞክራሲያዊነት እንዲጀመር ከዜሮ ትንሽ ከፍ የሚል መፍጨርጨር በማድረጌ ግን ተፅናናሁኝ፡፡ የማሰቃየት ተግባርን በንድፈ ሀሳብ ደረጃ መረዳትና  መረጃዎችን በልብ ማኖር አንድ ነገር ነው፡፡ ዘግናኝ የማሰቃየት ተግባር የተፈፀመበት ተጠቂ ማግኘትና ማናገር ሌላ አንድ ነገር ነው፡፡ የማሰቃየት ተግባርን በራስ ሰውነት ማስተናገድ ግን ከሁሉም ይለያል፡፡ ባለቅኔው ሰው የሚማረው አንድም በሳር ‘ሀ’ ብሎ አንድም በአሳር ‘ ብሎ እንዳለ ከዚህ በላይ ትምህርት ከወዴት ይገኛል!?
የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ትልቅ ተቋም ነው፡፡ ምርመራ ደግሞ ሳይንስ፡፡ ሀገራችን የምር በሽብርና የሌሎች ወንጀሎች ስጋት ቢኖርባት ተጠርጣሪዎችን መርምሮ ለፍርድ የማቅረብ ዋና ሀላፊነት ያለበትይህ የፍትህ አካል ነው፡፡ በአግባቡ ከተከናወነ ሕጋዊነትን ባህል የሚያደርግ ነገር ግን ተጠርጣሪዎች ላይ የማሰቃየት ተግባር የሚፈፀምበት ከሆነ ደግሞ ሙሉ የፍትህ ስርዓቱን አቀጭጮ የሚያስቀር ነው፡፡ ይህንን የሰው ልጅ ማሰቃያ ስፍራ ለቀን ወደ ማረሚያ ቤት ስንወሰድ አበራ ጀምበሬ Agony in the grand palace ላይ ያሰፈረውን
Commit to the paper the suffering in that dark chamber
Announce to the world all the unbearable torture
የሚለውን ግጥም እያሰብኩኝ አንድ ተጨማሪ ህልም አለምኩኝ፡፡ ይህን ፖለቲካዊ የሀሳብ ልዩነትን መዳመጫና የህሊና እስረኞችን ደም ማፍሰሻ የሆነ ተቋም ወደ ሙዚየም ተቀይሮ ማየት ነው፡፡ ይህ የኔ ኢትየጵያዊ ህልም ነው፡፡
ትምህርት ሶሰት -የትውልድ እዳ
ሶስተኛው ትምህርት የሚገኘው መንግስት ወደ ጦማርያን እጁን እንዲሰድ ያደረገውን ተግባርና እስሩን ተከትሎ የታየውን ምላሽ በመገምገም ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ቮልቴር  If you wish to converse with me define your terms እንዳለው ከዚህ በኋላ ‹‹ትውልድ›› ወይም ‹‹የትውልድ ልሂቃን›› ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ብያኔ ሰጥቼ እቀጥለላሁ፡፡ የነገሩን ውል ለመጨበጥ ትንሽ ወደኋላ መንደርደር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ትውልድ ስንል ተቀራራቢ የእድሜ ክልል ውስጥየሚገኝ መሰረታዊ ለውጥ በሌለውና አንድ ሊባል በሚችል ስርዓተ ትምህርት ያለፈ የአንድ ስርዓት(Regime) ውጤት የሆነ እና የዘመኑን መንፈስ የተሸከመ ማለታችን ነው፡፡ የትውልድ ልሂቃን ስንል ደግሞ ሰፊውን የልህቅነት ትርጓሜ ሊገኝ ከሚችለው ነገር አብላጫውን ያገኙ(those who get the most of what there is to get)የሚለውን እንወስዳለን፡፡ ይህንን ብይን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ያገኘውን የትምህርትና የስራ እድል የገቢ መጠንና በማህበረሰቡ ያለውን ቦታ ከጠቅላላው የሀገሪቱ ዜጋ ጋር በማወዳደር የእርሱ ስፍራ የቱጋ እንደሆነ ይረዳል፡፡
አንድ ትውልድ ዘመኑ የሚጠይቀውን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ በዚያች ሀገር ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል ያለው እድል እየጠበበ ይመጣል፡፡ ሳንካ መፍትሄ ሳያገኝ በዘገየ መጠን የበለጠ እየከበደ እና እየተወሳሰበ ስለሚሄድ መፍትሔ ለመስጠት አዳጋችና ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ይሆናል፡፡ 
የሀገራችንን የቅርብ ጊዜ ታሪክ በዚህ አውድ ስናጤን ከጣሊያን ወረራ በኋላ ሀገሪቱን የተረከበው ልሂቅ የፊውዳል ስርዓቱ ዘመኑን እንደማይመጥን እና የሕዝቡን ችግር የመፍታት አላማ እንደሌለው ተገንዝቦ ለመሰረታዊ ለውጥና ማሻሻል ከመስራት ይልቅ ስርዓቱ የፈጠረለትንና የፈቀደለትን የትምህርትና የስራ እድል በመጠቀም ስርዓቱን ማገልገል ምርጫው አድርጓል፡፡ የነዚህ አዳዲስ ምሁራን ዘመኑን ያልዋጀ ጥረት የተመለከተው ማኅበረሰብም ‹‹ከእጅ አይሻል ዶማ›› ብሎ ይጠራቸው ነበር፡፡ በዘመኑ ከነበሩት ስመጥር ቴክኖክራቶች አንዱ የሆኑት የቀድሞውብሔራዊ ባንክ ገዢ  ተፈራ ደግፌ “Minutes of an Ethiopian Century” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እውነታ በሀዘኔታ ያስታውሱታል፡፡
‹‹The tragedy of our Post-war generationof Ethiopian elite was that we adapted an attitude of public silence and private passivity on this professional level walking away from society instead of confronting its problems››
ልሂቁ ከ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት በቀር ምንም ሊጠቀስ የሚችል እንቅስቃሴ ሳያደርግ ዝምታን መምረጡ ለሚቀጥለው ትውልድ ግዙፍ ያልተሰሩ የቤት ሥራዎችን እንዳስረከበው መረዳት አያዳግትም፡፡ በክፍሉ ታደሰ ስሌት መሰረት 1930ዎቹ፣ በ1940ዎቹ እና በ1950ዎቹ የመጀመሪያ አጋማሽ የተወለዱና በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ የነበረውን ልሂቅ ያቀፈው ‹‹ያ ትውልድ›› ከወታደራዊው መንግሥትና እርስ በእርሱ ብዙ ዋጋ ያስከፈለ ትግል አድርጓል፡፡እንደመሬት ላራሹ ያሉ ውጤቶች ቢገኙበትም ሕጋዊነትን ዲሞክራሲያዊነት እንዲጀመር መሰረት ባለመጣሉ በኋላ ለመጡት ሁለት አምባ ገነንሥርዓቶች መነሳት መንስዔ ሆኗል፡፡ 
ወታደራዊ መንግሥት ወድቆ የሽግግር መንግስት የተቋቋመ ሰሞን ስመ ጥሩ ኢኮኖሚስት እሸቱ ጮሌ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ማኅበረሰብ እንዲመሰረት የ1966ቱን አብዮት ለመራው ትውልድ የሰጠው እድል በወታደራዊው ኃይል መጨናገፉን በመጥቀስ ‹‹ታሪክ ሀገራችንን የምንታደግበት እና ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ጎትተን የምናወጣበት ተጨማሪ እድል ሰጥቶናል፡፡ ለአንድ ትውልድ የሚሰጥ ሁለት እድል እንዲሁ በዋዛ የሚገኝ አይደለም፡፡ ሁለቱንም በግዴለሽነትና በሞኝነት ማባከን በቀጣዩ ትውልድ ይቅር የማይባል ወንጀል ነው፡፡››ብለው ቢመክሩም ያ ትውልድ ከራሱ ታሪክ ሳይማር ቀርቶ ዳግም አገሪቱን ወደኋላ የሚጎትት ስህተት ሰርቷል፡፡ 
በስርዓቱ አምባገነንነት የተነሳ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በንቃትመሳተፍ የነበረበት አዲስ ትውልድ (በ1980ዎቹ እና በ1990ዎቹ) ምንም ሊጠቀስ የሚችል ነገር ሳይሰራ አልፏል፡፡ ስደተኛው ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ከምርጫ 97 ጋር ከተያያዙ እንቅስቃሴዎች በስተቀር ጉልህ ድርሻ ያልነበረውን ይህንን ትውልድ ‹‹የጠፋ ወይም የባከነ›› ብሎ ጠርቶታል፡፡ ምርጫ 97ትም በቅንጅትም ሆነ በሕወሀት ኢኅአዴግ በኩል የመሪነት ሚና የተጫወቱት የያ ትውልድ አባላት በመሆናቸው ለትውልዱ ሙሉ እውቅና ለመስጠት ይከብዳል፡፡
ከዚህ ተስፋ ሰጭ ሙከራ በኋላ ስርዓቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል ሚዲያውንና ሲቪል ማኅበረሰቡን አዳዲስ አፋኝ አዋጆች በማውጣት ፣ በማሰር እና በሌሎች እኩይ ተግባራት ማዳከሙ ሁላችንም የምናስታውሰው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ነው ዞን ዘጠኝ ኢ-መደበኛ የጦማርያን ቡድን  መንቀሳቀስ የጀመረው፡፡ የመጀመሪያዋ ጦማር ‹‹የሚያገባው ትውልድ ፍለጋ›› በሚል ርዕስ የወጣች ሲሆን ይህም ዞኑ ከዚያ በኋላ ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች በሙሉ የቃኘ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ከየትኛውም ብሔር ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያልወጣና አማራጭ ትርክት በማቅረብ ትውልዱ በሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ማነቃቃትን አላማው ያደረገ ነበር፡፡ አቅማችን በፈቀደ መጠን ከአለፉት ትውልዶች በተለይም ከያ ትውልድ ለመማር ሞክረናል፡፡ የሀገሪቱ ችግሮች ውስብስብ መሆናቸውን በመረዳት የትውልድ አቻዎቻችንን እኛም የምንማርበት መድረክ እንዲሆን ምኞታችን ነበር፡፡ ዝምታው ተሰብሮ በኃላፊነት ውይይት እንዲጀመር ተነሳሽነቱን ወሰድን፡፡ 
የውይይቱ መንፈስም ከጽንፈኝነት የፀዳ የሀሳብ ልዩነትን የሚያከብር እና ለአካዳሚያዊ ሀሳቦች ልዕልና የሚሰጥ ለማድረግም ሞክረናል፡፡( ህገ መንግስቱ ይከበር ሰንል የወያኔን ህገ መንግስት እውቅና ሰጡ ብለው ያጣጣሉን ድምጾች ቀላል አልነበሩም) ሀገራችን ያላት ደካማ የውይይት ባህልና ሥርዓቱ በየጊዜው የሚፈጥሯቸው ወደር የለሽ ብሶቶች ዋነኛ ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ እኛም የዚህ ማኅበረሰብ ባህልና ታሪክ ውጤቶች በመሆናችን መፈተናችን አልቀረም ፡፡ ነገር ግን ለጫና አልባው ውይይት (endless conversation) በተለይ እርስ በርሳችን በነበረን መስተጋብር ታማኞች ነበርን፡፡
ብዙዎች እንደቂልነት ሊወስዱት ቢችሉም የውይይቱ መድረክ አፍቃሪ ኢኅአዴግ የሆኑ ሰዎችና ራሱን ስርዓቱን የሚጨምርና የማያበሳጭ እንዲሆን በተቻለን መጠን ጥንቃቄ እናደርግ ነበር፡፡ ይህንን ጥረታችንን ብዙ ሰዎች  ትንሽ ሙከራችንን በለጋስነት እንዲወስዱት አደረጋቸው፡፡ ይህ ለጋስነት በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የሚገኙ የምናከብራቸው ሰዎችንና ተቋማትን ይጨምራል፡፡ እንደጠበቅነውም ብዙ ያልሆኑ ነገር ግን በቂ ሊባሉ የሚችሉ የትውልድ አቻ ወዳጆችን አፈራልን፡፡ ዞኑም የዘጠኝ ሰዎች ብቻ መሆኑ አከተመ፡፡ ‹‹ይህንን ብታስተካክሉት›› ‹‹ይህቺን ደግሞ እንዲህ ብታደርጓት›› እያሉ ድካማችንን እና ስንፍናችንን ማየት የማይፈልጉ ብዙ ሆኑ፡፡ 
በዚህ ሂደት እኛም ብዙ ተማርን፡፡ የተወሰኑ ኢ-መደበኛ የቡድኑ አባላትም የሕይወት ውሳኔዎችን በመወሰን ስራዎችን በመተው አራማጅነትን እና ጦማሪነት ጋር የተያያዙ ሙያዎች ውስጥ ገቡ፡፡ በፊት የምናከናውናቸውን ትንንሸ ስራዎች መስራት ለእኛ የማያረካ አክባሪዎቻችንንም መናቅ ሆኖ ተሰማን፡፡ ለበለጠ ስራ እራስን ወደ ማዘጋጀት ያሉብንን የአቅምና የቁርጠኝነት ችግሮች ለመፍታት ረዘም ያሉ እቅዶችን ያዝን፡፡ 
እኛ እንዲህ እና እንዲያ እያልን እናስባለን፡፡ መንግስት ደግሞ ስልካችንን ጠልፎ ከዋልንበት እየዋለ በብዙ ጆሮዎችና አይኖች እየሰለለን ወንጀል ሳይሆን ሰበብ ፈልጎ ሊያስረን አድፍጧል፡፡ በመጀመሪያ ‹‹ለራሳችን ትክክል ያልሆነ ትልቅ ግምት ስለሰጠን ነው እንጂ መንግሥት እኛን ምን ሰራችሁ? ምንአጠፋችሁ ብሎ ያስረናል?›› ብለን አጣጣልነው፡፡ የመታሰራችን ምልክቶች ሲገዝፉ ደግሞ ከብዙ ማሰላሰሎችእና ክርክሮች በኋላ እስከአሁን ያደረግነው ‹‹ወንጀል››  ከሆነ ካቴናው በእጃችን እንዲገባ ፈቅደን ጡመራውን እንደምንቀጥል በይፋ አውጀን ተመለስን፡፡ 
ጤናማ ሕዝባዊ ተዋስኦ (Public Discourse) እንዲዳብርና ኃላፊነትየሚሰማው ትውልድ እንዲፈጠር መድከም በእኛ የተጀመረ አይደለም፡፡ ብዙዎች በእስር፣ በግዞት (በስደት) እና በሞት ዋጋ የከፈሉበትነው፡፡ የኛን ትውልድ መንፈስ ለማረቅ ያደረጉት እያንዳንዱ ነገር በህሊናችን የገነነና በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ ነው፡፡ ማንም ሊቀይረው በማይችለው የተፈጥሮ ኡደት እኛም ባለተራ ሆነናል፡፡ አገር አገር የምንለው በግልብ ብሔረተኝነትና በአጉል አርበኝነት መንፈስ በመነሳት አይደለም፡፡ የሀገር አመሰራረት ንድፈ ሀሳብና የአለማችን ጂኦ-ፖለቲካዊ እውነታ በመገንዘብ ነው እንጂ፡፡ ሀገራችን ከታሪኳ፣ከራሷና ከአሁኗ ጋር እንድንታረቅ ዋና ፍላጎታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው የመናገር ነፃነት ሳይገደብ ሁሉም የሀገሪቱ ጉዳዮች የሰለጠነ ጫና አልባ ውይይት ሲደረግባቸው እንደሆነ እናምናለን፡፡
ከትውልድ ጥቂቶችን በማሰር፣ ከሀገር እንዲወጡ በማስገድዶ በማሰደድ እና በመግደል የትውልድ ጥያቄን መቀልበስ ይቻላል ብሎ የሚያስብ ቢኖር እንዳይስት ይጠንቀቅ፡፡ የ1953ቱን መፈንቅለ መንግሥት  መክሸፍን ተመልክቶ ንጉሱ የመፈንቅለ መንግሥቱን ጠንሳሾች በማሰርና በአደባባይ በመስቀል የትውልዱን የለውጥ ጥያቄ ያዳፈኑ መስሏቸው መሰረታዊ ማሻሻል ማድረጉን እንዳይዘነጉ ከመከሩ ሰዎች ውስጥ አንዱ ደራሲ ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ ናቸው፡፡ በዚህ ታሪካዊ ምክራቸውን ንጉሱ ከቁብ ባይቆጥሩትም‹‹ለማናቸውም ነገር መነሻ የሆነው ሥሩ እንደተደበቀ ተቀምጦ ከላይ እንደሚታየው ቅርንጫፉን ብቻ ቢጨፈጭፉትና ለጊዜውእንኳ የጠፋ ቢመስል የተመቸ ጊዜ ሲያገኝ የተደበቀው ስር ዳብሮ ተስፋፍቶ ለመጥፋትም እንደሚያስቸግር ሆኖ ይነሳል›› ብለው ተንብየው ነበር፡፡ የዚህ ዘመንም ነገር ጥቂት እድሜ የሰጠው ሰው ሲፈፀም የሚያየው ነው፡፡ 
እስር ሲታሰብ ብዙ ስጋቶች ወደ አዕምሮ ይመጣሉ፡፡ ከሁሉም የሚከብደው ግን ቤተሰብን ማንገላታትና በማረሚያ ቤት ተረስቶ መቅረት ነው፡፡ ቀበቶዬን አስረክቤ ወደማረሚያ ቤት ስወሰድ ይህንን እያወጣሁኝ እያወረድኩኝ ነበር፡፡ ያለፉት ሰባት ወራት የእስር ቆይታዬን ግን በመጠኑም ቢሆን መሳሳቴን ነግሮኛል፡፡ ማዕከላዊ ጨለማ ቤት በነበርኩኝ ጊዜ ጠያቂ ሰው ማግኘት የሚፈቀደው በሳምንት አንድ ቀን ለቤተሰብ አባላት ብቻ ነበር፡፡( እሱም ከሁለት ሳምንት “ምርመራ” በኋላ ከቤተሰብ ውጭ ጠያቂ ሲመጣ እኛን ማግኘት ስለማይፈቀድ የጠያቂው ስም በቁራጭ ወረቀት ላይ ተፅፎ ይመጣ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእኔ ብዙ ትርጉም ነበራቸው፡፡ በእስር ቤት አለመረሳቴን እና ስለእኔ እስር የሚጨነቁ ወዳጆች እንዳሉኝ እዚያ ጨለማ ቤት ያለሁት ለግልጉዳዬ ሳይሆን ማኅበረሰባዊ ጉዳይ(public cause) ይዤ መሆኑ እያስታወሰ መንፈሴ ሳይሰበር ያኖረኝ ነበር፡፡ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ከሩቅ የማያቸው ብዙ ፊቶች መንፈስን የሚያረጋጉና የሚያጽናኑ ናቸው፡፡ በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ያሉ የቅርብ ጓደኞቻችን በአካልነው እንጂ በመንፈስ ከእኛ ጋር አልታሰሩም ማለት ይከብዳል፡፡ ከከንፈር መጠጣ በዘለለ  እስሩ እንዳይከብደን እና በሕግ ፊት (ይፈተን ዘንድ ነው እንጂ የፍትሕ ስርዓቱ ብቻውን ተነጥሎ ጤናማ እንደማይሆን ለቀባሪው ማርዳት ነው) ንጽህናችንን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ከማድረግ አልቦዘኑም፡፡ 
ማንዴላ አንድ ሰው ወህኒ እስኪወርድ

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ዛሬ ጠዋት የተሰየመው 19ኛ ወንጀል ችሎት ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ቀድመው ቢገኙም ለሰአታት ያህል ችሎቱ ሳይጀመር ቆይቷል፡፡ የተወሰኑ ወዳጆች እና የቤተሰብ አባላት ችሎቱን ለመታደም እድል ያገኙ ሲሆን የተለመደው የቦታ ጥበትን ተከትሎ ብዙዎች ውጪ ቆመው ሲጠብቁ አንደነበርም ተስተውሏል፡፡ 

ባልተለመደ ሁኔታ ዘግይተው የተሰየሙት ዳኞች የጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያት ማቅረባቸውን ሰምተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ የጽሁፍ አስተያየታቸውን ማቅረባቸውን ነገር ግን አቃቤ ህግ ክሱን አለማሻሻሉን በቃል ክርክር ለማቅረብ ቢሞክሩም ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክር አስፈላጊ አንዳልሆነ እና መሻሻል አለመሻሻሉን አይቶ አንደሚወስን በማሳወቅ የጠበቆችን የቃል ክርክር ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት ጠበቃ አምሃ የጽሁፍ ምልልሱ የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው በመሆኑ በቃል ማስረዳትን አንደአማራጭ ለመጠቀም ፈልገው አንዳልተሳካ ገልጸዋል፡፡ 

ከሰአታት ጥበቃ በኋላ የተሰየመው የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የፍርድ ሂደቱን ለታህሳስ 27 በመቅጠር ተጠናቋል፡። በእለቱ የጦማሪ ዘላለም ክብረት የልደት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ብዙዎች ወዳጆቹ የመልካም ልደት ምኞታቸውን ገልጸውለታል፡። ጦማርያኑ ሲገቡ በጀርባ በር በኩል አንዲገቡ በመደረጋቸው ከሚጠብቃቸው ቤተሰብ እና ወዳጅ ጋር በደምብ ሰላምታ ለመለዋወጥ ባይችሉም በጠንካራ መንፈስ ጥንካሬ እና ፈገግታ ታይተዋል፡፡ 

የጠበቆቹ የተሻሻለው ክስ ፡፡#Ethiopia #FreeZonebloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

The bloggers and journalists outside at lideta court  
Edom Kassaye (journalist) and Mahilet Fantahun (bloggers) today outside court    
Birthday man, Zelalem Kibret with Zone9bloggers and Journalists

 

From Kilinto prison, Addis Ababa Ethiopia 
O! The mighty reminiscence! Of all the thoughts nothing is more haunting than reminiscence. When I read, walk; sleep — in all of my daily routines I recall yesterday. Yesterday as if it is painted by one of the renaissance realist painters. Those yesterdays are here facing me virtually, if Raphael and Titan meets for a team work and puts those yester times in a big canvas.
How you doing comrades? You might be confused by my word choice of comrade. I got you Yes, our (me and you) formal relationship was a ‘Master’ pupil, ‘teacher – Student’, ‘Boss – Subordinate ‘ relationship. I am not comfortable with such hierarchical dichotomy. Rather, we were friends. I think we are still friends but, from afar and I hope our friendship will blossom by tomorrow. Hence, our bond of relationship is the rationale behind my choice, comrade (with all its political connotations) instead of something else.
Comrades, since my departure from the scene that is common for both of us, I know some of you are done with your formal schooling and I know that some of you are still counting your orders in the main dish, please consider my humble wishes.  For those who are done with your time in school, I wish a good time of preparation for the sequel. For those who are still struggling in school, have a wonderful fight.
The ‘departed’
Friends, if you remember we used to have a term of relationship, which put us in a promise to get together in the classroom. Regrettably, I am the one who fails to fulfill my promise but, forgivably. I say, forgivably. Because it is not I rather tyranny that should take the blame. Dictatorship is the hurdle that set us apart. It is the state which is the sinner. I fail to keep my words of promise because of a force majeure called despotism.
A short summery of what happens to me may give you the excuses to forgive me for my incompliance with terms of our promise.
Hundreds of days back out of the blue I was arrested for a suspicion of felony, that eventually turned to be a crime of preparation and conspiracy to commit an act of terrorism. However, the charge was not a simple matter as I mentioned. Rather, I passed through a prolonged medieval-like ordeal or as ‘they’ called it ‘interrogation’. Finally I end up in a remand center which have thousands of ‘detainees -of – conscience’. Even if it is laughable but, the crime that I am accused of is neither bail able nor an easy thing to face. Since I face capital punishment if I fall in the ‘convicted’ basket. So, comrades ain’t my failure to fulfill our promise forgivable?
Addendum: let me know you something extra about the situation that I live, if it helps me to get your piety of forgiveness;
Since my departure from the chalk and talk I never saw the sunset. Because I am a detainee who should be roll-called before the sunset.
My privacy has gone with the wind of April, since I am a detainee who lives with hundred plus detainees in one cell.
Fellow friends, you have no idea about how a day in prison is vicious. The viciousness of the day is like dancing the same, with the same rhythm and in the same dance floor, day-in-day-out. I am a detainee who is dancing this ‘Sisyphusic’ dance in a minute base. Save my trail to dilute the viciousness of the day by the virtuous souls.
The depression that resulted from counting the plight of my love, my friends and my families is so immense. Because I am a detainee who have nothing to do for them. Again save my trial to console myself with a thought of how I am lucky to be expired to this prison environment and its population.
Comrades, the types of book that I have to read, the utensils that I have to use, even my hair-style and shoe-type must be ‘proper’, which fulfils the remand center’s regulation. Because I am a detainee.
Thus, comrades, in consideration of such ill facts of my life and how my life is digressed from its normal course, how could an inmate who lives in such a situation which limitation is a rule fulfills his promise of coming to the class room? How could a man who is in chain live to his terms of promise? I hope I got your forgiveness.
The Puzzled
The Roman jurist and philosopher, Cicero upon his Critic of the state says:
“The Republic is oppressed with arms and enfeebled by slavish fear. So it has no Power to innovate the free spirit”.
It seems present day Ethiopia is the incarnation of the republic that Cicero is critical of voices muzzled. Thinkers exiled and dissenters incarcerated. This is the situation that bewildered me. What is wrong with us comrades? Why the Free spirit is chained and cuffed? Why oppression exist in a continuum? Why fear reign, democracy manacled and the gun is the domineering player of the entire player? Why today looks like a Siamese twin of yesterday?…
Comrades, my list of whys about our nations illness is bottomless. I hope yours too. However, I feel that the answer/s for our quests is/are not bottomless; even it can be a single one. And the very question is what could be that panacea?
Out of those numerous thought wonderings, sometimes I stopped somewhere and start to feel that the problem of our nation lies on the ‘Clash of Generations’! I know it seems naive to think so. But, it is not something we have to ignore. My wandering result a question of is our country suffer because of the ‘Clash of Generations’ for ideas, for principles or for power?
Scott Fitzgerald in his ‘This Side Of Paradise’ puts the mission of ‘his’ generation eloquently as ‘our generation had grown up to find all gods deal, all wars fought and all faiths in mankind’ Yes every generation, perished or breathing have its own generational mission.
Ethiopia can’t be an anomaly in this regard. Each Ethiopian generation had its own generational mission some proved trans-generational and some other proved futile and abortive.
Upon the 1991 regime change in Ethiopia one of the prominent Ethiopia economists, Eshetu Chole puts the chance and hope of his generation as;
“History was giving us another chance to redeem two opportunities in less than a generation is a privilege seldom granted to a people; squandering both of them is a crime that will not be forgiven by posterity”
(Quoted in Tefera Degefe’s ‘minutes of an Ethiopian century’)
Poor Eshetu! We in the posterity are witnessing the second chance squandered flatly. But comrades, can’t we forgive the squanderers of the second chance in a generation? I hope we can. For a reason that we in the posterity should have something in excel than those who doomed the chance friends, might -have-been must leave its place for a by-gone is by-gone state of mind. I hope you are in my side.
A generation which misuse and abuse those two golden chances (As Eshetu mentioned) are still in the throne. And hunting the ‘Free spirit’ to death. Thus, we are not able to live our dreams and the spirit of our generation. But, by saying this I am not fool to dichotomize the problem in a ‘we’ and ‘then’ spectrum. Rather there are many ‘wes’ in them and the vice-verse.
When my generational clash thesis paled and blurred my puzzle reinvent itself and again forced me to ask if the problem is not a generational disparity, where its lies? Generation passed and Generation come but, those common denominators; turbines and trembling, the sound of the midnight knock, arbitrary arrest and summary execution, the feeling of the muzzle in the back, the sword in the nape, the cuff in the hand and that weird sound of ‘hands-in-the-air’ remains to live with us.
Comrades in those good-old class session side talks, we talk about a lot of things. But, I don’t remember about raising this grand issue of why we as a nation condemned to live in a state of terror? If we already talked about it take this note as a reminder, If not please think over it for the sake of our comradeship.
(By the way, when I am writing this, I am not about whether ‘they’ initiate a new criminal change against me for a ‘crime’ of inciting students to think. Because the state that we are living is a state that proclaims right as wrong, righteousness as wrong doing and the gun-bearer as the peace-lover.)
Sisters and brothers, to sum-up I am saying that our good nation is in a swamp of problems. To give answer for those problems first we have to identify the problems in a solvable manner. But my puzzle lies here, what are those problems? I mean the extent of the complexities makes the problem headless and tailless. Spotting the head and the tail of our problem is a mission that our generation shouldered. If we are done with that my state of bewilderment will be resolved.
The hopefull
Here the remand center of our cells have high windows that I developed a habit of staring to the darkness in the night time. Six months after my incarceration something beautiful happened via those windows. A full snow-white moon glares in those windows. Yes Jelaluddin  Rumi was right when he said ‘The moon won’t use the door, only the window’. A sight of the moon after a long wait was something new for me comrades. Because I am a prisoner. But that is what I called ‘Hope’, to wait and to see the moon. A lone awaited dream fulfilled.
Comrades, we are living in a state which employed a policy of ‘blood and iron’ in a form of ‘arrest and pardon’. In such a state freedom is omnipresent and dissent costs a lot of price, hope is the only shelter to hide.
After examining many failed human life projects, the sixth century Greek poet Theogins Megara concludes as ‘Hope is the only good god remains among mankind’, By now, I can’t say Megara was wrong.
I used to despise hope as a weapon of the weaklings. Even I was dare enough to say ‘is audacious about hope. Rather hope is overrated.’ I remember my feeling after reading Alber Camus’s double edged blow to hope and hopelessness as ‘Humans must learn to live beyond hope and hopelessness’ on his ‘the myth of Sisyphus’ which I endorsed.
Now I realize that it was one of my regrettable stances. Now I am re-reading Sisyphus’s story in a different state of mind I mean even Sisyphus, a poor creature who was condemned to do the something, forever, was hopeful for change in his life.
I know my present state of living is temporal. Thus, while Sisyphus who is condemned eternally was hopeful, why not me?
Friends, one of the ‘joy’ of prison is the plenty of time that you have to think, thanks to my detention, I got the time to audit the last ten thousand day that I live in flesh and blood. (By the way, funnily I was arrested in the week that I was celebrating the tenth thousand day of my life, if I am not mistaken). And my auditing should that there is nothing hopeless about the future.
In the state that I stand by now, even if I understand the situation of hopelessness. Rather again and after Patrick Henery’s brave state of questioning as. ‘If life so dear, or peace so sweet as to be purchased at the price of chains and slavery?’ is echoing in my ears, as if I were one of the attendants when Henery speaks.
Comrades, I am nostalgic of everything, the sessions, what we talk, even the greeting. My hope is that we will meet again. Upon my farewell Theognis  Megara is here again saying ‘As long as many lives and sees the light of the sun, let him … count on hope.’ Yes, as long as our comradery exist, let us count on hope.
O! Tyranny what a loser are you!? Whatever you are doing, for us there is hope and reminiscence!

Journalist Tesfalem Woldeyes

 #FreeZone9bloggers  #FreeEdom  #FreeTesfalem  #FreeAsemamaw  #Ethiopia

የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች “የተሻሻለ ክስ” ተሰማ ፡፡  ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በልደት በአሉ የደረሱትን የንኳን አደረሰህ መልእክቶች በፈገግታ ሲቀበል አርፍዷል፡፡

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ 10 ተከሳሾችን የፍርድ ሂደት የሚያየው  የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት ተሰይሞ ተሻሻለ የተባለውን የአቃቤ ህግ ክስ በቃል አዳምጧል፡፡ ክሱ አንዲሻሻል የታዘዘበትን ብይን ግልባጭ ማግኘት አልቻልንም ያሉት የተከሳሾች ጠበቆች ክሱ መቅረብ አንደማይገባው ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆች ክሱ ላይ አስተያየታቸውን አንዲሰጡ እድል አንደሚሰጥ በመጥቀስ ተሻሻለ የተባለው ክስ በንባብ ተሰምቷል፡፡

የተሻሻለው ክስ አንደቀደመው ሁሉ ዞን 9 የሚል ምንም አይነት ቃል ያልተጠቀመ ሲሆን በተለያየ ቦታ የተጠቀሰው የሽብር ቡድን ግንቦት ሰባት እንደሆነ እንድምታ ባለው ሁኔታ በተደጋጋሚ የግንቦት ሰባት ስም ተጠቅሷል፡፡ ተቀጣጣይ ቦንብ አጠቃቀምና የሽብር ተግባር ተከታታይ ስልጠናም ከግንቦት ሰባት አንደተሰጠ በደፈናው ጠቅሷል፡፡ በክሱ ውስጥ ስልጠናው በማን እና መቼ እነደተሰጠ የስልጠናው ዝርዝር ተሳትፎና ቦታ ያልተጠቀሰ ሲሆን ሊከናወን የነበረው የሽብር ተግባርም ምን አንደሆነ አሁንም አልታወቀም፡፡ ክሱ የግንቦት ሰባት ልሳን ለሆነው ኢሳት መረጃ ማቀበልንም የሰሩት የሽብር ተግባር ነው ሲል አካቶታል፡፡ 

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ተቀበለ የተባለው 48000 ብር አሁንም በድጋሚ የተጠቀሰ ሲሆን ብሩ ከማን አና ለምን ተግባር አንደተላከ በዝርዝር ያልተገለጸ ሲሆን በደፈናው ግን ለሽብር ተግባር ተብሎ በድጋሚ ተጠቅሷል፡፡ የተከሳሾችን የስራ ዝርዝር በግልጽ ለማቅረብ የሞከረው ክሱ ጦማሪት ሶልያና ሽመልስን የቡድኑ ዋና አስተባባሪ ጦማሪ በፍቀዱን ሃይሉን ጸሃፌ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን የአገር ውስጥ አስተባባሪ የሚል የሽብር ስራ ድርሻ የሰጣቸው ሲሆን ሌሎቹን ተከሰሾች መስራችና አባል ናቸው ሲል አስቀምጧል፡፡ ኦነግን ከክሱ ውስጥ ከማውጣት ውጪ መሰረታዊ ለውጥ ያላሳየው የተሻሻለው ክስ ፣ የስልጠናዎቸን ዝርዝር በማን እና የት አንደተሰጡ፣ ተቀበሉ የተባሉትን የሽብር ስትራቴጂ ፣ እነዲሁም ሊሰሩት የነበረውን ሽብር ተግባር ሳያስቀምጥ አልፏል፡፡
የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ አንዲሻሻል የታዘዘበትን ብይን ከፍርድ ቤቱ ተቀብለው ፣ አስተያየታቸውን ይዘው አንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዛሬው ቀጠሮ ጦማርያን እና ጋዜጠኞቹ  በጠንካራ መንፈስ እና ፈገግታ የታዩት ሲሆን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ልደት ቀኑን በማስመልከት የቀረበለትን የእንኳን አደረሰህ መልእክት በልባዊ አጸፋ ሲመልስ ታይቷል፡፡ የዞን9 ጦማርያንም ለጓደኛቸን ተስፋለም ወልደየስ መልካም ልደት ለመመኘት አንወዳለን፡፡

ማስታወሻ
ዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው አንደማያውቁና ክሱም ፓለቲካዊ አንደሆነ እያስታወስን ፍርድ ቤቱ የጀመረውን መንገድ በማጠናከር ለአገራቸው የሚያገባቸው ወጣት ጦማርያንን በነጻ በማሰናበት የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን ወገንተኛነት የመለወጥ እድሉን አንዲጠቀም ለማስታወስ አንወዳለን ፡፡

አሁንም ስለሚያገባን አንጦምራለን!
ዞን 9

Journalist Asmamaw, Blogger Atnaf and Natnael at Lideta Court Today


 ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች
 
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!
ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’ በሚል ርዕስ:
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡
ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት  ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡
እኛም የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች የዚህ ‘ልማታዊ ርምጃ’ ሰለባ የሆንን ግለሰቦች ነን፡፡ በርግጥ ከሁለት ዓመታት በፊት ‘ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስቱን’ ያስከብሩልን በማለት ጥያቄ ያቀረብንልዎት ግለሰቦች ‘ከ6ወራት በፊት ሕገ መንግስቱን ለመናድ  ሞክራችኋል’ በማለት መንግስትዎ ሲያስረን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር ጠይቀን ሕገ መንግስቱን ለመናድ በመሞከር ወንጀል ተጠርጥረን ስንታሰር እስሩ በጣም ግራ አጋብቶን ነበር፡፡ በዚህ ያልቆመው መንግስትዎ ክሱን ‘ሕብረተሰቡንና ሀገሪቱን ለማሸበር አቅዳችኋል ሞክራችኋል አሲራችኋል…’ በማለት ወደ ‘ሽብርተኝነት’ ያሳደገው ሲሆን እርስዎም ከዚህ ጋር በተያያዘ ሃሳብዎትን ሲሰጡ ስለተመለከትንዎ ትንሽ ቅሬታ ይዘን መጣን፡፡
በቅድሚያ አሁን ያለንበትን ሁኔታ በትንሹ ብናስረዳዎት ቅሬታችንን ለመረዳት ያስችልዎታልና አንዳንድ ጉዳዮችን እንንገርዎት፡፡
ይሄን ማስታወሻ በምንፅፍልዎት ወቅት ከታሰርን ከ 200 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ነገር ግን ጉዳያችን ገና በቅድመ ክስ (Pre Trial) የክርክር ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም መንግስትዎ እንኳን ለእኛ ለተከሳሾች ለከሳሽ አካልም ግልፅ ያልሆነ ክስ በማቅረቡ ነው፡፡ ይሄንንም ስንል ልትፈፅሙት ነበር የተባለው ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ ሳይጠቀስ ‘በቃ የሽብርተኝነት ድርጊት ልትፈፅሙ ነበር’ በማለት በጨበጣ ስለመጣብን ነው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዲህ የብዙ ድብደባ፣ ዛቻ እና ስድብ ሰለባዎች ከሆንን በኋላም የቀረበው ይሄ  ክስ ነው ከ6 ወራት በኋላም ተከሳሾች ከሳሾቻችንም ሳንረዳው በየቀጠሮው እየታሸ ነው የሚገኘው፡፡ ‘የተፋጠነ ፍትህ’ ሕገ መንግስትዊ መብት ነውና የተፋጠነ ፍትህ ይሰጠን፣ እርስዎም ይሄን ሕገ መንግስታዊ መብት ያክብሩ እያልንዎት አይደለም ‘ሕገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ ሕገ መንግስቱ ይከበር በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ’ በማለት ‘ጥፋት የሚያሳምን’ ( አንዱ የዚህ ደብዳቤ ጸሃፌ ጦማሪ ጥፋት ብሎ አንዲፈርም የተገደደው ህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ ህገመንግስቱ ይከበር ማለቴ ጥፋት ነው ብሎ መሆኑ መንግስትዎን መልክ ግልጽ አድርጎ ያሳያል) መንግስት አለዎትና ይህ ጥያቄ አንደሚበዛብዎት እናውቃለን፡፡
ይልቁንም ቀላልና ግልፅ ቅሬታን ነው ይዘን የመጣነው፡፡ ይሄውም የኢፌድሪ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 20/3/ ላይ
‘የተከሠሡ ሰዎች[…]  በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር […]መብት አላቸው::’
በማለት የደነገገ ሲሆን፣ ይሄንን ሕገ መንግስታዊ መብትም ማንኛውም የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እርስዎና መንግስትዎም በተደጋጋሚ ‘ሕገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ እናስከብራለን’ ይላሉና ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የምታውቁት ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ከታሰርን ወዲህ ስለእኛ የእስር ጉዳይ በተጠየቁባቸው ጊዜያት ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ ‘ፍርድዎትን’ በተደጋጋሚ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ እናስረዳዎ፡- ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣሚ መግለጫ ላይ ስለእኛ እስር ጉዳይ ለቀረበልዎት ጥያቄ ሲመልሱ፡-
‘ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት ውስጥ አንዴ ከገቡ በኋላ ብሎገር ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ማለት ዋጋ የለውም’
በማለት ብዙ ነገሮችን ተናገሩ፡፡ ይሔውልዎት ስህተትዎ፡-
  1.   የክሳችን ዋነኛ ጭብጥ በሃገር ውስጥ ‘የሽብርተኛ ድርጅት በማቋቋም ‘የሽብርተኝነት’ ተግባራትን ለመፈጸም አሲረዋል፡ አቅደዋል… የሚል እንጂ፣ እርስዎም እንደሚሉት ‘ሰንሰለት’ ምናምን አይደለም፣ 
  2.      እሺ አሸባሪዎችም ይበሉን፣ ነገር ግን ሕገ መንግስቱ እንደሚደነግገው በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኝነታችን’ እስሚረጋገጥ ቢጠብቁስ ምናለበት? ይህ የሚያመለክተው እርስዎም እነደማእከላዊ መርማሪዎች ነፃ ሆኖ የመገመት (presumption of innocence) መብታችንን እያከበሩልን እንዳይደለ ነው፡፡
ይሄ ነገር የሆነው በድንገት ሊሆን ይችላል ብለን ዝም ብንልም እርስዎ ግን በድጋሚ ጥቅምት 6/2007 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበልዎ ጥያቄ ሲመልሱ፡-
“የብሎገር ጭምብል አጥልቆና በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ተሸሽጎ ከተከሳሽነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሽብርተኝነትን መዋጋታችን ይቀጥላል…” እያሉ እርስዎ ያሉትን የብሎገር ጭምብል አውልቀውና ተሸሸጉበት ያሉትን የጋዜጠኝነት ሙያ መሸሸጊያ አፍርሰው ባንዴ ‘የአሸባሪነት’ ካባ ደረቡልን፡፡
ክቡር ጥቅላይ ሚኒስቴር፣ እያልን ያለነው የአንድ ሰው ‘አሸባሪነት/ወንጀለኝነት’ የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ደንግጎ እያለ፣ እርስዎ ግን ነፃ ሆኖ የመገመት መብታችን ወደ ጎን ብለው እንደ ከሳሽም እንደ ፈራጅም በመሆን ‘አሸባሪዎች’… እያሉን ይገኛሉ ነው፡፡
ምናልባት ‘ስራ አስፈጻሚው ከሳሽ ነውና እኔም የስራ አስፈጻሚው አካል መሪ ስለሆንኩ የፈለኩትን አስተያየት የመስጠት መብት አለኝ’ ብለው ከሆነ፣ ሕገ መንግስቱን የማክበር ጉዳይ ‘ርስዎን ጨምሮ ሁሉም ዜጎች ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ እርስዎ ‘L’e’tat, c’est moi’ ይሉት አይነት የራስ ግምት ውስጥዎ ከሌለ በስተቀር እንዲህ በግልፅ እየጠየቅንዎት ‘ሕገ መንግስትቱን  አላከብርም’ በማለት ገና ዋነኛ ክርክሩ እንኳን ያልተጀመረ ክስን (ዋነኛ ክርክር ካለው) መሠረት በማድረግ ከዚህ በኋላ እኛን ‘አሸባሪዎች’ አይሉንም ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህን ተመሳሳይ ምላሽ “በእርግጠኝነት አሸባሪ ናቸው” በሚል ቃና ለቢቢሲ ለኢንቢሲ ለመሳሰሉት አለም አቀፍ ሚዲያ  ተቋማትም መስጠትዎን ሰምተናል፡፡
ሌላው ልናስታውስዎ የምንፈልገው ጉዳይ እንደኛ አይነት የተራገበ( በሰፊው በታወቀ የአደባባይ) የፍርድ ጉዳይ ([un] popular case) ላይ የመንግስት አካላት አስተያየት (say) ያለውን ተፅእኖ እንዲያስቡት ነው፡፡ እርስዎ በምክር ቤት ቀርበው የአሸባሪነት ፍርድ ከበየኑብን (አሁን እያደረጉት እንዳሉት) ፍርድ ቤትም ሆነ ሌሎች የመንግስትዎ አካላት ምን ሊያስቡ እንደሚችሉ አስተውለውታልን?!
ይሄን ሁሉ ስንልዎ እንዲያው ሕጉን ያክብሩልን ለማለት ያክል ነው እንጅ፣ ከሽብርተኝነት ጋር የሚያገናኘን ቅንጣት ያክል እውነት /A segment of fact/ እንደሌለና የሰው ልጆች መልካምና ደስተኛ ሕይወት እንዲኖራቸው ከመመኘትና ለአገራችን ያገባናል ከማለት ያለፈ ሕይወትም ፍላጎትም እንደሌለን እኛም እናውቀዋለን እርስዎና መንግስትዎም ያውቁታል፡፡ ነገር ግን ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ጨዋታውን በግድ ካልተጫወታችሁ ተብለናልና እየተጫወትን ነው፡፡ የአሁኑ ጥያቄያችን ግን በጣም ቀላል ነው፣ ጨዋታው ገና በደንብ እንኳን ሳይጀመር ውጤቱን እይወስኑት ነው፡፡
እርስዎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የስልጣን ደረጃ በወጡ ሰሞን አብዛኞች የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች መጠነኛ ለውጥና ማሻሻዎች ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ሰንቀን “The First 100 Days” ወዘተ እያልን ብዙ ጠብቀንዎት ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በሚበልጥ ግዜ እንደተመለከትንዎ ግን ተስፋችን ፍሬ ሊያፈራልን አልቻለም፡፡ አሁንም አዲስ ተስፋ ሰንቀን ግን ፡- “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እባክዎትን ሕገ መንግስቱን ያክብሩ! የእኛንም መብት ያክብሩልን” እንላለን፡፡
‘’የብሎገር ካልሲ አድርጎ፣ የጋዜጠኝነት ጫማ ተጫምቶ የሽብረተኝነት ሰንሰለት ውስጥ ከገቡ በኋላ ሕገ መንግስቱን ያክብሩልኝ ማለት ዋጋ የለውም!’’ በማለት ተስፋችን ዋጋ እንደማያሳጡት ተስፋ አለን፡፡
ከአክብሮት ጋር
  ጦማርያን                    ጋዜጠኞች
 ዘላለም ክብረት                  ኤዶም ካሳዬ 
 ናትናኤል ፈለቀ                  ተስፋለው ወ/የስ
 በፍቃዱ ሃይሉ                   አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
 አጥናፍ ብርሃኔ                       
 አቤል ዋበላ
 ማህሌት ፋንታሁን
 

የዞን ፱ ጦማርያንና የጋዜጠኞችን የ200 ቀናት እስር አስመልክቶ በማኅሌት ሰለሞን የተዘጋጀ

                                     
                       


                                     
                       

#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Ethiopia 
ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ ይሰየማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ ችሎት ከወትሮው በተለየ ጥብቅ ጥበቃ ለአጭር ደቂቃዎች ተከናውኗል፡፡ 

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ተከሳሾች ( አንድ በሌለችበት) ዘጠኙ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ሲሆን በእለቱ ፍርድ ቤቱ የክሱ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ሀግን መልስ አይቶ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ 

ችሎቱ ከተለመደው አዳራሽ ይከናወናል በሚል እሳቤ ወዳጅና ቤተሰቦች ቢገኙም መጀመሪያ በደፈናው ወደ ችሎት አዳራሽ መግባትን በመከልከል በማስከተል ደግሞ የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ችሎት ውስጥ አንዲገቡ ተደርጎ ነበር፡፡ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ግን ችሎቱ ውስጥ ያለው የድምጽ ማጎያ ስለማይሰራ ይበልጥ አነስተኛ ወደሆነ ክፍል ችሎቱ አንዲዘዋወር ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የተከሳሽ ወዳጅና ቤተሰቡ ባልታደሙት አጭር ችሎት ሁለት የግራ እና የቀኝ ዳኞች አዲስ የተለመወጡ በመሆናቸውና ኬዙን ስላልመረመሩት ለህዳር ሶስት ( ኖቬምበር 12) ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ቀጠሮ በአጭሩ ተዘግቷል፡፡ 

እስር ላይ የሚገኙት ሴት ተከሳሾች ጉብኝት መብትን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቢሰየምም ለውጥ አለመኖሩን በመጥቀስ አቤቱታቸው ያሰሙ ሲሆን የማረሚያ ቤት ሃላፌው በሚቀጥለው ቀጠሮ መጥተው አንዲያስረዱ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ 

ዛሬ ከፍተኛ ግርግር እና የቦታ እጥረት አንዲሁም ወላጆች መንገላታት የታየ ሲሆን ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ እነደቀድሞው ችሎት ነጭ ልብስ በመልበስ በመልካም ሁኔታ ላይ አንደሚገኙ ታይቷል፡፡ 

በተያዘ ዜና የጦማርያኑን የዋስትና ጥያቄ አስመልክቶ ጠበቃቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የተባለ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነገ ጠዋት በሚሰየመው ችሎት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ( አጋርነታችሁን የምታሳዩ የዞን 9 ነዋሪያን ነገ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት በመገኘት አጋርነታችሁን እነድታሳዩ ጥሪ እናቀርባለን)

 #FreeZone9bloggers #Ethiopia

የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ውሎ

ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ በነሶልያና ሽመልስ የሽብር ወንጀል የክስ መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ቀጠሮ ችሎቱ ከ20 ቀን በኃላ እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቀቀ። 

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ። 

ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል። 

በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ። 

በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል። 

በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።

PDF
“ጋዜጠኝነትን እና የፖለቲካ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ የሀገሪቱንና የሕዝቦቿን ሰላም ለማደፍረስ ከሚያስቡና ከሚፈልጉ ‘ሀይላት’ ጋር ግንኙነት በማድረግ የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል።“ 
ይህ መግለጫ (መልስ) የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ከወጣበት ከነሀሴ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዜጠኞችና በሰላማዊ መንገድ ተመዝግበው የፖለቲካ ምህዳሩን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከታሰሩ በኋላ በመንግስት አካላት የሚሰጥ የተለመደ አባባል ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥም ከጋዜጠኛ እስከ ፖለቲከኛ (political personalities)፣ ከሀይማኖት መሪዎች እስከ ጦማሪያን፣ ከታጣቂ ወታደሮች እስከ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች… በዚሁ አዋጅ አማካኝነት ‘ሽብርተኝነታቸው ተረጋግጦላቸዋል’ ወይም ‘ይረጋገጥባቸው ዘንድ ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ።’ ለመሆኑ ይህ ከ14 ዓመት ህፃን[1]  እስከ 80 ዓመት አዛውንት[2]  በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የሚያስቀጣው፣ ይህ ከጉምቱ ምሁራን እስከ ገበሬዎች ድረስ የሚያስረው… ሕግ በተጨባጭ ስፋትና ጥበቱ ምን ያህል ይሆን? ለታሪካዊ ጥያቄዎች ያለው ምልከታስ?  በሀገሪቱ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታስ (The state of Democracy) ምን ይነግረናል? ስለ ጨቅላው የኢትዮጵያ ፌደራሊዝምስ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ተግባራዊነት አንፃር ምን ይታየናል? ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በመሬት ላይ ያሉ የሕጉ እውነታዎችን በመመርመር (Fact investigation) ምልከታዎቹን (Implications) በዚህ ፅሁፍ ለማየት ሞክረናል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ
ዓለማቀፉ የፀረ-ሽብር ውጊያ (The Global War on Terror) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቡሽ <We will not tire, we will not falter> ንግግር ከታወጀ ጀምሮ በተለያዩ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ሀገሮች በሽብርተኝነት ዙሪያ ያላቸውን የሕግ ማዕቀፍ ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ጀመሩ። ኢትዮጵያም የዓለማቀፉ የፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ አካል መሆን አለብኝ በማለት እንዲሁም ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ ላይ ግልፅ እና ድርስ አደጋ (clear and present danger) ደቅኗል በሚል መነሻ የፀረ-ሽብር ሕግ አርቅቃ ለፓርላማ አቀረበች።
ረቂቁ በቀረበበት ወቅት የተለያዩ  አካላት (የፓርላማ አባላት፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና የጋዜጠኛ ማኅበራት ወ.ዘ.ተ.) ረቂቅ ሕጉ ሰፊ የሽብርተኝነት ድርጊት ትርጉም ይዟል፣ ‘ማወቅ ሲገባው’፣ ‘አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት’ የመሳሰሉት የሚሉ ለትርጉም ክፍት የሆኑ የወንጀል አይነቶችን አካቷል፣ ለፖሊስና ለደህንነት አካላት እጅግ የተለጠጠ ስልጣን ይሰጣል፣ እንደ የዋስትና መብት ያሉ የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብቶች ይነፍጋል፣ የሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕጎችን በማቅለል ወንጀለኝነትን የማስረዳት ሸክምን ከዓቃቤ ሕግ ወደ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ያሸጋግራል (shifting burden of proof) ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ትችቶችን ቢያቀርቡም፤ ‘እነዚህን የሕጉን ክፍተቶች የተለያዩ  የመንግስት አካላት ላልተገባ ጉዳይ ሊያውሏቸው ይችላሉ’፣ ‘ተቃውሞን እና የመናገር ነፃነትን ወደ ወንጀልነት ያሸጋግራል’ የሚሉ ስጋቶችን በጊዜው ቢያነሱም ሕጉ በፓርላማ ከመፅደቅ ያገደው ነገር አልነበረም።
በሕጉ ዙሪያ የሚቀርቡ ብዙና የተለያዩ  ትችቶች ቢኖሩም ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የዚህ ፅሁፍ ዓላማ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ በተጨባጭ የትኞቹን የሕብረተሰብ ክፍሎች እያጠቃ ነው? ስለ አጠቃላይ የሀገሪቱ ሁኔታስ ምን ያመለክተናል? የሚሉትን ጉዳዮችን መዳሰስን ዓላማ ያደረገ ነው።
(ማስታወሻ: – በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የሚጠቀሱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊ ቀጠሮ ወይም ክስ ተመስርቶባቸው በመደበኛ ቀጠሮ ላይ ያሉ ናቸው።)
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አተገባበር
የፀረ- ሽብርተኝነት ሕጉ ከመውጣቱ በፊት እንዲሁም ከወጣ በኋላ የሚቀርቡበትን ትችቶች የመንግስት አካላት ምላሽ ሲሰጡበት: –
“ሕጉን ቃል በቃል የገለበጥነው ከAmerican Patriotic Act እንዲሁም ከእንግሊዙ የTerrorism Act ነው። እኛ ጋር ሲመጣ ለምን ትችት እንደሚቀርብበት ሊገባን አልቻለም።” የሚል ነው።  መንግስት እውን ቃል በቃል ገልብጦታልን? የሚለውን ጥያቄ ለመረዳት እንችል ዘንድ የአንዲት እንግሊዛዊት እና የአንድ አሜሪካዊ ታሪክን በማቅረብና በማነፃፀር ትግበራው ላይ ፍተሻ እናድርግ።
እንግሊዛዊቱ Kate Kaplan በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ Mathematicsን በMajorነት Computer Scienceን ደግሞ Minor በማድረግ ትምህርቷን የጨረሰች ስትሆን፤ በተለያዩ  መስሪያ ቤቶችም ከምረቃዋ በኋላ በስራ ዓለም ያሳለፈች ናት። በስራ ዓለምም በData Expertነት Specialize አድርጋለች። ከስራዋ ጎን ለጎን ደግሞ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም እንደርሷ ሁሉ ለሀገራቸው መሻሻል የሚተጉ ጓደኞችን ለማፍራት የቻለች ሲሆን፤ ከእነዚህ ወዳጆቿ ጋር በመሆንም በተለያዩ  ጉዳዮች ዙሪያ የምትጦምር ነች። ንባቧን እና ግንዛቤዋን ለማዳበር ይረዳት ዘንድም በተለያዩ  ርዕሶች ዙሪያ የተፃፉ ፅሁፎችን ከድረ-ገፆች ላይ በመገልበጥ ታነባለች። በIreland Republic ዙሪያ ጥያቄ ያለውን IRA የተባለ ፓርቲ ፕሮግራምም ለማንበብ Laptop ላይ ገልብጣ አስቀምጣለች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች የእንግሊዝ የፀጥታ አካላት እርሷንና የማኅበራዊ ሚዲያ ጓደኞቿን ሰብስቦ  ያሰራቸው ሲሆን ‘የሽብርተኝነት ተግባራትን ሊፈፅሙ ሲሉ ያዝኳቸው’ በማለት ክስ መስርቶባቸዋል። የክሱ ማስረጃ ሁነው ከቀረቡ ሰነዶችም አንዱ Kate ግንዛቤ ለማግኘት በማሰብ ከድረ-ገፅ የገለበጠችው እና ማንም ሰው በድረ-ገፁ አድራሻ ገብቶ ሊያነበው የሚችለው የIRA የፖለቲካ ፕሮግራም ነው። Kateና ጓደኞቿም ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ። የእንግሊዝ Terrorism Act ደግሞ የተወነጀሉበት አዋጅ ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ Andrew Martin በአሜሪካው New York University የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሲሆን ከስራው ጎን ለጎን ደግሞ የDemocratic Party የአመራር ክበብ ውስጥ ተሳትፎ አለው። ከፖለቲቻ ስራው ጋር በተያያዘም የተለያዩ  ሰነዶችን የሚያገላብጥ ሲሆን ከእነዚህ ሰነዶች አንዱ ደግሞ ስለ አሜሪካው Black Panters Party የሚገልፅ ሰነድ ነው። በስልጣን ላይ የነበረው የRepublican Party Andrewን ከሽብርተኛ ድርጅት ከሆነው Black Panters Party ጋር ግንኙነት አለው በማለት አሳስሮ የአምስት ዓመት ፍርድ ፈርዶበት በአሁን ሰዓት እስሩን እየገፋ ይገኛል። የRepublican መንግስት በአቶ Andrew ላይ ፍርድ የበየነበት የAmerican Patriotic Act አንቀፆችን በመጠቀም ነው።
እነዚህን ሁለት ጉዳዮች የጠቀስነው የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ቃል በቃል ገለበጥኩባቸው የሚላቸው ሀገሮች አሜሪካና እንግሊዝ የሽብርተኝነት ክሶች እስከምን ድረስ ይደርሳሉ? የሚለውን ጉዳይ ለማየት ሳይሆን ሕጉ ቃል በቃል ተገለበጠ በተባለባቸው ሀገሮች የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን እየተጠቀመበት ባለው አግባብ ቢጠቀሙ ምን ሊፈጠር እንደሚችል  ለማሳየት ሲባል፣ በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሳ በቃሊቲ የምትገኘውን ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን በKate Kaplan፣ እንዲሁም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ተከሶ አምስት ዓመት ተፈርዶበት እስሩን እየገፋ የሚገኘው መምህር በቀለ ገርባን በAndrew Martin በመተካት ማህሌት እና በቀለ ላይ እየሆነ ያለው ነገር የኢትዮጵያ መንግስት ‘ምዕራባውያንም ተመሳሳይ የህግ ማዕቀፍ ነው ያላቸው’ በማለት እያቀረበው ያለውን ማስተባበያ ምን ያህል በአተገባበሩ የተሳሳተ እንደሆነ በቀላሉ ያሳያል።
 ጦማርያን እና ሰላማዊ ፖለቲከኞችን በመፃፋቸው እና ለሀገራቸው መልካም ነገርን በማሰብ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ ግለሰቦችን የሚያስር – የሚከሰው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንጂ በሌላ ዓለም ማግኘት ከባድ ነው። Kateና Andrew ‘ሽብርተኛ’ የሚባሉት በኢትዮጵያ እንጂ በአሜሪካ ወይም በእንግሊዝ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊፈጠር አይችልም፡፡ ታዲያ ቃል በቃል ከምዕራቡ ዓለም የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጎች ‘የተገለበጠው’ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዴት ቢሰራ ነው ሁሉንም የሕይወት መስመሮች ‘በሽብርተኝነት’ ሊፈርጅ የቻለው?
“የሽብርተኛ ፍለጋና ምርመራው ሂደት “
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ በተግባር እንዴት ነው እየሰራ ያለው? የሚለውን ጥያቄ መመለሳችን ከላይ የጠየቅነውን ቀዳሚ ጥያቄ ይመልስልናል። እንዲህ በአጭር ምሳሌ እንመልከት:-
‘ሀሰን፣ ሀያት እና ከድር በፖሊስ (በደህንነት ኃይል) ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ ወንጀል ሊፈፅሙ ሲሉ ተያዙ’ ተብለው ታሰሩ። አሰራሩ እንዲህ ይቀጥላል:-
  1. በብሔራዊ የመረጃና የደህንነት ኃይል በቁጥጥር ስር ይውላሉ። በተለያዩ  የደህንነት ‘እስር ቤቶች’ ላልተወሰነ ጊዜ (ከ6 ወር በላይ በደህንነት ቢሮ የቆዩ ሰዎች አሉ) ከከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ጋር ይቆያሉ። በአብዛኛው ፍርድ ቤትም ሆነ ቤተሰብ ያሉበትን ሁኔታ አያውቅም።
  2. በደህንነት ‘እስር ቤቶች’ የነበራቸውን የፈተና (ordeal) ጊዜ ከጨረሱ በኋላ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው ይሰጣሉ። የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ‘ማረፊያ ቤት’ በማረፍም ‘የምርመራ’ ጊዜያቸውን ይጀምራሉ። የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ባለው ‘የፀረ-ሽብር ዲቪዚዮን’ አማካኝነት ባሉት ከ20 በላይ መርማሪዎችም ‘ምርመራው’ ይጀመራል። በዚህ የምርመራ ወቅትም እጅግ ኢሰብአዊ የሆኑ ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል። የተጠረጠሩበትን ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ እስኪያምኑ ድረስም መከራና ስቃያቸው ይቀጥላል። በዚህ ሁኔታ እስከ አራት ወራት ለሚቆይ ጊዜ ይቆያሉ (እስከ ስምንት ወራት በማዕከላዊ የቆዩ ሰዎች አሉ)።
  3. በአብዛኛው ‘የሽብርተኝነት ወንጀል ፋይሎች’ ላይ እንደሚታየው በነሀሰን፣ ሀያት እና ከድር ጉዳይ ላይም ፖሊሲ በቂ ማስረጃ ስለማይኖረው ‘ማስረጃ’ እዛው በወንጀል ምርመራ  ዘርፍ መርማሪዎች ይዘጋጃል። እንዴት?
ሀ. ድብደባና ስቃዩን በማጠናከር ከሶስቱ ተከሳሾች አንዱን (ለምሳሌ ከድርን) በጓደኞቹ በሀሰን እና በሀያት ላይ ምስክር እንዲሆን (Accomplice witness) በማስገደድ ፖሊስ የሰው ማስረጃ ይፈጥራል። ከድርም ከክሱ ይወጣል።
ለ. ፖሊስ የፈለገውን ቃል በመፃፉ ሀስን እና ሀያት እንዲፈርሙ ያስገድዳቸዋል። ቃላቸውንም ‘በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 27(2) መሰረት በነፃ የተሰጠ’ ይለያል።
ሐ. ምናልባትም ሀሰን እና ሀያት ‘ቃላችንን በድብደባ ያለፈቃዳችን ነው የሰጠነው’ በማለት በፍርድ ቤት በክሱ ሒደት ወቅት እንዳያስተባብሉት ፖሊስ ስጋት ካደረበት እዛው በወንጀል ምርመራ  ዘርፍ ማረፊያ ቤት (ማዕከላዊ) እያሉ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጉ አንቀፅ 35 መሰረት ‘አሸባሪነታቸውን’ አምነው ቃላቸውን እንዲሰጡ ያስደርጋል። በፍርድ ቤት የካዱ እንደሆነ ወደ ማረፊያ ቤት ሲመለሱ ሌሊቱን ሙሉ ከባድ ስቃይ ይጠብቃቸዋል።
መ. ካስፈለገም ‘የሀሰት ምስክሮችን ያሰለጥናል’፣ የወንጀል የሀሰት ሰነዶችን ያዘጋጃል። ወ.ዘ.ተ.
  1. ፖሊስ ‘ምርመራውን’ በዚህ መንገድ ካጠናቀቀ በኋላ ምርመራውን ለፍትህ ሚኒስትር ይልካል። የፍትህ ሚኒስትርም አስፈላጊውን ‘ፖለቲካዊ ግምገማ’ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ካደረገ በኋላ አራት አቃብያን ሕጎችን (አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ አቶ ዘውዱ በቀለንና አቶ ሰውበሰው አድማሱን) ላቀፈው የፀረ-ሽብርተኝነት case team ያስተላልፋል። አቃብያነ ሕጎቹም የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ ከተደነገጉት አስር (10) ወንጀሎች በአንዱ ወይም ከዛ በላይ ክስ ያቀርባሉ።
  2. በመጨረሻም የሀሰንና የሀያት ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል። አቃቤ ሕግ ከድርን የሰው ማስረጃ አድርጎ  ያቀርባል። የሀሰንና የሀያትን ለፖሊስ ወይም ለስር ፍርድቤት ተገደው የሰጡትን የተከሳሽነት ቃል በሰነድ ማስረጃነት ያቀርባል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ እና 19ኛ ወንጀል ችሎቶች ካሏቸው ዳኞች[4] ሶስቱ በጉዳዩ  ላይ ይሰየሙና ፍርድ ይሰጣሉ። ከድር ምስክር በመሆን ነፃ ይወጣል። ሀሰንና ሀያት ደግሞ ‘አሸባሪነታቸው’ ተረጋግጦባቸው ይፈረድባቸዋል። (በነገራችን ላይ አሁን ባለው አሰራር የፍርድ ሂደቱ ከሁለት ዓመት በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል)
ይህ ‘የሁሉም’ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ መሰረት የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ አካሄድ ነው። በዚህም መንገድ ዜጎች ከማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ገለል እንዲሉ ይደረጋሉ። ምክንያቱም እነሱ ‘ኢትዮጵያዊ አሸባሪዎች’ ናቸውና። የእነዚህን ኢትዮጵያውያን አሸባሪዎች ማንነት ማወቃችን የሽብርተኝነት ትግሉን ምንነት እና የሀገሪቱን ጉዞ በጉልህ ያሳየናልና እስኪ ፍተሻ እናድርግ።
‘መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ፌደራሊዝም’
 “ደርግ በወደቀበት ሰዓት በሀገሪቱ አስራ ሰባት (17) የሚሆኑ የታጠቁ ሀይላት ነበሩ። ይህም ዜጎች በደርግ ስርዓት የተከፉ ምን ያህል ወገኖች እንደነበሩ አመላካች ነው።” በማለት ኢህአዴግ ስልጣኑን ከደርግ በተረከበበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ በተደጋጋሚ ያስረዳል።
ኢህአዴግ አያይዞም የተለያዩ  ቡድኖችን መከፋትና ብሶት ለመቀነስና እስከ መጨረሻውም ለማስወገድ የፌደራል ስርዓት እንዲዘረጋ፤ ይህ የፌደራል ስርዓትም ‘ሀገሪቱን እንደ ዩጎዝላቪያ ከመሆን የታደጋት ፍቱን መድኃኒት’ እንደሆነ ይገልፃል።
ደርግም ከወደቀ ሩብ ምዕተ ዓመት እየሆነው ነው፤ የኢትዮጵያም የፌደራል ስርዓት ሀያኛ ዓመቱን ይዟል። እውን ከላይ የተጠቀሱት እውነታዎች ምን ያህል መሻሻል አሳይተዋል? የፌደራል ስርአቱስ ከቃላት ባለፈ ምን ያህል እውነተኛ ለውጥ አምጥቷል?  የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን እና ሕጉ ተግባራዊ የሆነባቸውን ቡድኖች ማንነት ማየቱ ለጥያቄዎቻችን መልስ ለመስጠት  ይሆናልና እስኪ እንመልከት።
በአሁኑ ወቅት ገዥውን ስርዓት ለመገዳደር በማሰብ ‘ፋኖነትን’ የመረጡ ቡድኖች የደርግ ጨካኝና አምባገነን ስርዓት ሲወድቅ ከነበሩት የታጠቁ ሀይሎች ቢበልጡ እንጂ አያንሱም። የአሁኖቹን ታጣቂዎች ከደርግ ወቅቶቹ የሚለያቸው፣ የአሁኖቹ ‘በአሸባሪነት’ የተፈረጁ መሆናቸውን ነው።
ይህ ፅሁፍ በተፃፈበት ወቅት ክስ ተመስርቶባቸው በቀጠሮ ላይ የሚገኙ አስር የተለያዩ  የክስ መዝገቦችን ብናይ መልሳችን ግልፅ ይሆንልናል።
“የጋምቤላ ክልል አሁን ባለው የፌደራል ስርዓት ምንም ዓይነት ጥቅም እያገኘ አይደለም። ለዚህም መፍትሄው ስርዓቱን በኃይል ማስወገድ ነው።” በሚል መነሻ አምስት (5) የተለያዩ  ቡድኖች መሳሪያ አንስተዋል። ከነዚህም አምስት (5) ፓርቲዎች መካከልም በአቶ ሙድ ጎይባሬ የሚመራው የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ጋር በተገናኘ 11 ሰዎች ማለትም
  1. ኡቺሚ አፐይ ኡቻላ
  2. ኡማን ኡድሉቻም
  3. ኡቻን ኡድላ ኦፒዮ
  4. ኡመድ ኡጁሉ ኡማን
  5. ኝበዲ ኡባንግ ኡጃቶ 
  6. ኦፒዮ ቹር ኡባንግ
  7. ኡመድ ኡቶ ኡማን
  8. ኡፐዶካ ኡቱን ኝግየው
  9. ታደሰ ኡዱጊ ቲፋ
  10. ኡማን ኡካይ ኡኩችና
  11. ኦኬሎ ኡበር ኡቻን
በፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 322/06 በቀን 18/07/06 በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 3 (1, 2 እና 3) መሰረት ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ጋህነንም የሽብርተኛ ድርጅት እንደሆነ በክሱ ተመልክቷል። ከጋምቤላ ሳንወጣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ እንደሚመራ በክሱ ከተመለከተው የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) አባላት ናችሁ ተብለው የተከሰሱ ሰባት ግለሰቦችን እናገኛለን። እነርሱም
  1. ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ
  2. ዴቪድ ኡጅሉ ኡባንግ
  3. ኡቻን ኦፒዮ ኡሞድ
  4. ኡማን ኝክየው ኡድሉ
  5. ኡጅሉ ቻሞ ኡኮይ
  6. ኦታካ ኡዋር ኡጋላና
  7. ኡባንግ ኡመድ አቦላ ናቸው።
በቀን 04/10/2006 ዓ.ም. በፌ/አ/ህ/መ/ቁ 508/06 በቀረበባቸው በዚህ ክስ ጋዴን የሽብርተኛ ድርጅት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ክሱም በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 4 ላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በመተላለፍ እንደሆነ ተገልጿል።
እስኪ ወደ ሌላ ክልል እንለፍ። በኮለኔል አለበል አማረ እንደሚመራ የሚነገርለትን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ህብረትን (አዴሀህ) እናገኛለን። የፌደራል አቃቢ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 071/06 በቀን 28/12/05 ባቀረበው ክስ ‘ግንቦት ሰባት ከተባለ አሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኦዴሀህ የተባለ ‘ሽብርተኛ ድርጅት’ ጋር አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ ያዝኳቸው’ ያላቸውን 10 ሰዎች በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) መሰረት ከሶ እናገኛለን። ግለሰቦቹም
  1. ማስረሻ ታፈረ ወ/ገብርኤል
  2. ሻለቃ አለምነው አየለ ነጋሽ
  3. ብርቁ አዲሱ ውቡ
  4. ታደሰ መንግስቱ በላይ
  5. የፀዳው ካሴ አሉላ
  6. አወቀ ደስታው ምህረቴ
  7. መሀመድ ግዛቸው ፋንታው
  8. ቴዎድሮስ ሀይሌ
  9. ታደሰ በለጠ
  10. ታደሰ ባዩ  ገበየሁ ናቸው።
ወደ ኦሮሚያ ክልል ተጉዘናል። ባለፉት 20 ዓመታት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ናችሁ በሚል እጅግ በጣም ብዙ ኦሮሞዎች ታስረዋል፣ ተሰደዋል ወይም ተገድለዋል። ይህ ሁኔታ አሁንም በሰፊው ቀጥሏል። የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ክሱ ‘ራሱን ኦነግ ብሎ ከሚጠራው ‘ፀረ-ሰላም’ ሀይል ውስጥ አባል በመሆን…’ ከሚለው የተለመደ የክስ ቃል  በተለየ መንገድ ‘ራሱን ኦነግ ብሎ ከሚጠራው ‘አሸባሪ’ ድርጅት ውስጥ አባል በመሆን…’ ወደሚል መቀየሩ ብቻ ነው። ምስጋና ለፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ይሁንና። ለዚህም ጥሩ ማሳያ ይሆኑን ዘንድ ሁለት የአቃቢ ሕግ መዝገቦችን እንጠቅሳለን።
በ22/07/2006 ዓ.ም. በፌ/ዓ/ሕግ/መ/ቁ 376/06 በመሰረተው ክስ
  1. ደልዴሳ ዋቆ ጃርሶ
  2. ገልገሎ ጉዮ ቦሩ
  3. ዋርዮ ጣጤሳ ጉዮ
የተባሉ ግለሰቦች የኦነግ አባል በመሆን ‘የሽብርተኝነት ድርጊቶችን’ ሲፈፅሙ ይዣቸዋለሁ’ በማለት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀፅ 3(1 እና 2) እንዲሁም አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ክስ መስርቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በቀን 11/2006 ባቀረበው ‘የሽብር ወንጀል’ ክስ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩት
  1. አብዲ ከማል የሱፍና
  2. ቶፊቅ ረሽድ ዩያ
‘የአሸባሪው’ ድርጅት የኦነግ አባላት በመሆን የሽብር ተግባራትን ልትፈፅሙ ስትሉ ተይዛችኋል’ ተብለው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) ተጠቅሶባቸው ክሳቸውን በማረፊያ ቤት ሆነው እየተከታተሉ ይገኛሉ። በ2006 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከተለያዩ  የክልሉ ዩኒቨርስቲዎች (ከሀሮማያ፣ ከጅማ፣ ከወለጋ… ዩኒቨርስቲዎች) የተያዙ ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ  የክልሉ አካባቢዎች (ከወለጋ፣ ከሞያሌ ወ.ዘ.ተ.)ተይዘው የታሰሩ ዜጎች በኦነግነት ተጠርጥረው በፌደራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) የሚገኙ ሲሆን ይህ ፅሁፍ እስከተፃፈበት ቀን ድረስም ክስ ሳይመሰረትባቸው ከአራት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በወንጀል ምርመራ ዘርፍ ‘ማረፊያ ቤት’ ውስጥ ይገኛሉ።
በድጋሚ ወደ ሀገሪቱ የምዕራብ ጫፍ እንጓዝ፤ ‘አሸባሪው’ ቤሕነንን እናገኛለን – የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ። በአቶ አብዱል ወሀብ መሀዲ  የሚመራው ቤሕነን “የክልሉ ነዋሪዎች ኢህአዴግ ከዘረጋው ስርዓት ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም። መፍትሔውም ስርዓትቱን በሀይል ማስወገድ ነው።” በሚል መነሻ ነፍጥ ያነገበ ፓርቲ ነው። በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ ከመባል ግን አልተረፈም። የፌደራል አቃቢ ሕግ በ19/12/2006 ዓ.ም. ባቀረበው ክስ
  1. አብዱልከሪም አብዱሰመድ አብዱልቃድር
  2. ሀዎጃ ሚነሳ አጉር
  3. ኢላቅ ኢብራሒም ዓሊ (ዕድሜ 17)
  4. አዴላ ጃባለ ንምር
  5. አብዲ ሀሚዝ ፈረንሳ
  6. ፋተልሙላ አጣሂር አከሶ
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ከላይ የተዘረዘሩትን ስድስት ግለሰቦች ‘የአሸባሪው የቤሕነን አባል ናችሁ በማለት ክስ አቅርቦባቸዋል።
ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፉ ላይ ነን። በስልጣን ላይ የሚገኘው ‘ኢህአዴግ’ ትግሉን የጀመረበት የትግራይ ክልል ውስጥ። ‘ገዢው ስርዓት ለትግራይ ሕዝብ አመጣልሃለሁ ያለውን ዴሞክራሲና ፍትህ ማምጣት አልቻለምና ስልጣን በቃው’ በማለት የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ሕዝቢ ምንቅሳቀስ ትግራይ (ዴሕምት) ደግሞ ከትግራይ ክልል የተገኘው ‘አሸባሪ’ ድርጅት ነው። የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በ
  1. ብሎፅ ገ/ፃድቃን
  2. ነጋሌ ብርሃኑ
  3. ሹማይ ተበጀ
ላይ ባቀረበው ክስ ‘የአሸባሪው’ ዴሕምት አባል በመሆን የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ሊፈፅሙ ሲሉ ይዣቸዋለሁ በማለት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ክስ መስርቶባቸዋል።
በዘጠኙም የፌደራል ክልሎች ‘አሸባሪ’ ድርጅቶችን መፈለጋችንን ቀጥለናል፤ ማረፊያችንም ኦጋዴንያ ሆኗል። የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 25 መሰረት በሽብርተኛ ድርጅትነት ከሰየማቸው 5 ድርጅቶች ውስጥ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ኦጋዴንን ነፃ ለማውጣት እየታገለ የሚገኘው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) አንዱ ሲሆን፤ የፌደራል አቃቢ ሕግም በየጊዜው ‘የአሸባሪው’ የኦብነግ አባላት ናችሁ በማለት እጅግ ብዙ ክሶችን በኦጋዴን ተወላጆች ላይ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ ክስ አቅርቦ ‘ፍርዳቸውን’ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
እስኪ በዓላማ ደረጃ ብሄር ተኮር ከሆ

ያ ትውልድ ያመነበትን ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ መስዋዕትነትን እንደከፈለው ሁሉ እህት በወንድም ላይ ጠቁማ ወደ ሞት የነዳችበትም አጋጣሚዎች ተፈጥረዋል ወንድም ከወንድም ጋር የሚያፋጅ ግዜ ላይም ነበሩ፤ ዛሬ ላይ እንደቀልድ ምንሰማው ለመፍረድም ቀላል የሚመስሉትአስቀያሚ የታሪኮቻችን አጋጣሚዎች ዛሬም ላይ ይከሰታሉ እኛም ስህተቶችን የምንደግም እንጂ ከስህተቶቻችን የምንማር ዓይነቶች አይደለንም፡፡
ከኢህአዴግ ወገን ላልሆነው ፖለቲካ የሚወደድ ሆኖባይሆንም በአገር ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ሰዎች የሚገናኙባቸው ቦታዎች የተለመዱ ናቸው እስር ቤት፣ ሰላማዊ ሰልፍ(እጥረት ቢኖርብንም)እንዲሁም ፌስቡክ የመጀመሪያውን ተርታ ይይዛሉ፡፡ እንደውም ማህበረሰብ ሚዲያው እርስ በርስ ለመግባባት ለመገማገምና  ለመተዋወቅ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ በኤዶም ካሳዬ እና በእኔ መካከልም ትውውቅምክንያት የሆነውና በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ለመሄድ ከተሰባሰቡት የዞን ዘጠኝ አባላት ጋር ተሰባስበን በነበረበት ወቅት ነበር ወዲያውም ኤዲ ጆማ ተባብለን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ሞቅ ወዳለው የፖለቲካ ጨዋታ ስንገባ አይተውን የተጠራጠሩት ጓደኞቻችን ከዛሬ በፊትም ሳትገናኙ አልቀራችሁም አይነት ትንኮሳ ጀምረው ነበር የምንታጨቅበት ታክሲ ሲመጣ ወሬያችን ቢቋረጥም፡፡
Journalist Edom Kassaye
ከቂሊንጦው እስር ቤት የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ጥየቃ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተን ተጨዋውተናል፣ እንደውም በአንድ ወቅት በጨዋታችን ውስጥ ደጋፊና ተቃዋሚ ጥግ እና ጥግ (አንዳንዴም ጽንፍ) የያዙ ፍረጃዎች ኑሮ ፈተና ለሆነባቸው የቤተሰብ ሃላፊዎች ስራቸው አስተማማኝ ይሆን ዘንድ አባልነት ግዴታ ሆኖባቸው አባል የሆኑትንና ያልሆኑት ግን ውሳኔዎችን ለማስቀየር ምንም ዓይነት አቅም እና ስልጣን የሌላቸው ነገር ግን በተቃውሞ ጎራ በካድሬነት የመፈረጅና የመዘለፍ አጋጣሚዎችን ያስተናገዱ ሰዎች ስለመኖራቸውና አንዳንዶች በብሔር ፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ ተቸንክረው ወደ መከላከልና ጽንፍ የያዙ ደጋፊ ሆነው ስለመገኘታቸው እንዲሁም በኑሮ ውድነት ምክንያት መቃወም እየፈለገ ቤተሰቡን ማስተዳደር ፈተና ሆኖበት ከቤት ኪራይና ከሌሎች ወጪዎች የሚናጡ ባልና ሚስቶች ብሶትን መሰረት አድርገን መሃከል ላይ ስለምንገናኝበት አልያም የእነኚህን ሰዎች ስሜት ሌሎች እንዲረዱ ለማድረግ አንድ ጽሁፍ በጋራ ለመጻፍ ሁሉ ተመካክረን ነበር፡፡

በጋዜጠኛነት በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችውስጥ ያሳለፈችው ኤዶም ከዞን ዘጠኞችና ከእነ አስማማውና ተስፋለም ጋር ስትከሰስ የግድ ዞን ዘጠኝ ነሽ እያሉ ነበር በሕግ የሚቀልዱትፖሊሶች የከሰሷት፡፡

ከዛ በፊት ግን ዞን ዘጠኝ ባትሆኚም ከእነሱ ጋርስለምትቀራረቢ መረጃ ስጪን እያሉ የገባችበት የሚገቡ በስልክ ፋታ የሚያሳጧት “ደህንነቶች” ነበሩ፤ ኤዲ በአንድ ወቅት የሆነ መስሪያ ቤት ስራ ለማመልከት ጎራ ብላ ስትወጣ አፍታም ሳይቆይ ይደወልላታል በዚህ ወቅት የደወለው ደህንነቱ ነበር የመስሪያ ቤቱን ባለቤትስም ጠርቶ “ ሥራ እንዳመለከትሽ ሰምቼያለሁ ከእኛ ጋር እኮ ብትተባበሪ የተሻለ ደረጃ በተሻለ ደሞዝ አስቀጥርሻለሁ” ብሏት ነበር፤በተደጋጋሚ ወቅትም “ዞን ዘጠኞች ለምን መጻፍ አቆሙ የተደበቀ ህቡህ ሥራ ስለጀመሩ ነውና መረጃ እንድትሰጪኝ እፈልጋለሁ አለበለዚያ ውጪ አገር ስብሰባ ላይ መንግስትን ለማሳጣት የተናገርሻቸውን ምክንያት አድርገን ልናስርሽ እንችላለን አንቺ ብቻ ተባበሪን እንጂ ወደ ውጪም መሄድ ከፈለግሽ አሜሪካም ሆነ አውሮፓ ምንም ችግር የለውም ትሄጃለሽ አንቺ ብቻ ተባበሪን “ የሚሉ ማስፈራሪያዎችና ማግባቢያዎች ይቀርቡላት ነበር ፡፡ ኤዶም በመልሷ “እኔ እስከማውቀው ልጆቹ ምንም እየሰሩ አይደለም ትልልቅ ሆቴል ውስጥ ኢንተርኔት ነጻ ስለሆነ እና ሰውም ስለማይበዛ ማኪያቶ  እየጠጡ የሚጨዋወቱናቸው መጻፍ ስላቆሙ ጓደኝታቸው ተቋረጠ ማለት ስላልሆነ ይገናኛሉ ከመንግስት ጫና ስላበዛችሁባቸው እንዲሁም በግል ምክንያቶቻቸውእንጂ ሌላ ነገር ስላሰቡ አይደለም” ብላ መልሳላቸው ነበር፡፡ የደህንነቶች ክትትል አሁንም የተባበሪና መረጃ አምጪ ትዕዛዝ ለረጅም ጊዜ ፋታ አልሰጣትም ነበር ፡፡በአንድ ወቅት ስብሰባ ላይ ሆና ስልክ ባለማንሳቷ የገባችበት እንደሚገባ እና እንደማታመልጣቸው ከዛቻ ጋር የጽሁፍ መልዕክት ተልኮላት እነደነበር ትዝ ይለኛል፡፡
ደህንነቱና አለቆቹ የሆነ ነገር እየተካሄደ ነው የሚል ስጋት መስከራቸው ምንም የሚያጠያይቅ አልነበረም፡፡ ( እኛም እነደ ቡድን አውነቱን ሲያውቁ ይተውታል የሚል የዋህነት ነበረብን) እናም ኤዶም የምታቀርበው እውነተኛ መረጃ ከሌለ በፈጠራም ቢሆን እንድትተባበራቸው ግፊት ሲደርጉባት የቆየ ቢሆንምለእንደዚህ አይነት ርካሽ ተግባር ተባባሪ ባለመሆኗ የጅምላ እስሩ ተቋዳሽ ሆናለች፡፡ የእኔም መትረፍ ያለኤዶም እና ናትናኤል ፈለቀ(ናቲ) የሚቻል አልነበረም፡፡ “freedom of expression ትሰራላችሁ ወንጀል አንደሆነ አታውቁም?” የሚሉ የእውቀት ደረጃቸው ለመግባባት አንኳን የሚያስቸግሩ ሰዎቸን እነ ኤዲ ለወራት ለማሳመን ሲጥሩ ከርመዋል፡፡
በታሰሩ ቀን ማግስት በነበረው ቅዳሜ ጠዋት ላይ በቅርቡ የልጅ አባት የሆኑትን ወዳጆቼንለመጠየቅ ከሰአት በኋላ ከዞን ዘጠኞች ጋር ቴስት ኦፍ አዲስ የምግብ ፌስቲቫልን ለመታደም ማታ ላይ የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመታደምአስቀድሜ አቅጄ የነበረ ቢሆንም ሰው ያስባል ኢህአዴግ ያስራል ሆነና የሕይወቴ አንዱ እና ትልቁ የምለው ብዙ ወንድሞቼንና እህቶቼን በእስር ያጣሁበት ማግስት ሆነ፡፡
#TimeStandStill pic edited by Mahilet Solomon
ጊዜው አምስት ወራት ተቆጥረዋል ቢልም ለብዙዎቻችን እንደቆመ ነው፣ ንጹህ ኅሊና ያላቸው ለትውልድ ምሳሌ የሚሆኑ ጓደኞቼን ህገ መንግስታዊ መብት ባልተከበረበት፣ የህግ የበላይነት እና የህግ ስርአት መመራት ቀልድ በሆነበት በስርአቱ አገልጋዩች መነካታቸው ያንገበግበኛል፣  ለኔ ጊዜው አሁንም እንደቆመ ነው ሻንጣዬ ውስጥ ያለውን እቃ አውጥቼ ቁምሳጥን ውስጥ ለመጨመር አዲስ ሕይወት ከጀመርኩ እነሱን የምረሳ እየመሰለኝ እንዳለ አለ ተመልሶ እነሱን እንደሚያገኝ ለጉዞ እነደተሰናዳ ሰው ልቤ እንደተሰቀለ እስካሁን አለሁ፡፡ ይህ እኔም ሆነ የተረፍነው ወዳጆቼ የምንጋራው ስሜት ነው፡፡
ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን የሚያኮራ መከራን ለመጋፈጥ የቆረጡ እውነተኛና ሃቀኛ ሰዎች ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል፤ እነሱንም የወለዱ እናትና አባቶች ሊኮሩ እንጂ ሊያዝኑ አይገባም፡፡
ኤዲ ያንቺ ጓደኛ ስለሆንኩ ኩራት ይሰማኛል፡፡

 #TimeStandStill #FreeZone9Bloggres #FreeEdom#FreeTesfalem #FreeAsmamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

Befekadu Hailu

There was a time in my life when I used to think a lot about revolution in Ethiopia. In fact, in 2011 during the so called ‘Arab Spring’ I wrote a rejoinder article when Ethiopian democracy activists (especially those who are based in diaspora) planned a ‘Day of Rage’ using Facebook and aimed at ending EPRDF’s two-decade authoritarian rule. Just after a year I wrote one more rejoinder titled “Revolution is Ephemeral ’. In this article I tried to highlight what Ethiopians truly lack to launch a genuine social revolution using social media. In these couple of articles it appeared that I went up against proponents of revolution but I was trying to explain the traceable causes and conditions of social revolution. In a nutshell, I was saying that the significant portion of the Ethiopian population, the opposition politicians, and the intellectuals and generally the elite and social ideals and social reality were not sufficiently prepared to kick-start an authentic and organic social change.
Yet again in 2012, I was inspired enough to write a series of articles under a general title ‘Concerning Change’ on our own blog Zone9. In the first of my series of articles titled “Will EPRDF hand over power by means of election?”  I tried to explain why EPRDF will keep on clinging to power. I argued that EPRDF is not yet ready for an electoral democracy. In a bid to demonstrate an alternative yet constitutional means of possible social change such as civil disobedience I wrote further articles as a follow up to my critique and highlighted different elements of social change across a spectrum of societal issues. As much as I can  I tried to kindle genuine public conversations in bringing these issues to the public’s attention through my articles such as ‘Fear and Social Change’ ‘Regime Change and Religion’, ‘The Role of Civil Society in 1974 Ethiopian Revolution’ and “Revolution or Sluggish Change”  It was during this time that I contemplated deeply about revolution. It was one phase of my life in which I have tried to articulate my comprehension of revolution into pieces of writings but it was also a stage of my life in which my belief on revolution was dropped off significantly.  But I have to confess here that my belief on revolution plummeted to its all-time low merely in 2013. Subsequently, I found myself turned into an activist of an organic social change through processes (not a transient revolution) from an avid reader and advocate of revolutionary ideas.  I have to put in plain words that what made me skeptic of transient revolutions; I have to explain at length that how I progressed (say it regress if you like) from being optimistic revolutionary to a proponent of an organic and authentic social change through processes, as the 1960s Ethiopian Marxist revolutionaries put it, what turned me from being ‘Revo’ (revolutionary) to ‘Sabo’ (Saboteur). Please note that I was only an enthusiastic reader of revolutionary ideas.  
  At some stage while I was grappling with the revolutionary ideals of intending to bring fundamental structural change in favor of the mass but unexpectedly might turn to be like unrestrained wildfire which could be destructive; Mohamed Morsi was ousted in Egypt’s second revolution just in two years. The second Egyptian rebellion (revolution) made me feel perplexed about revolutions. But I thought in his short-lived presidency Morsi operated against basic principles of democracy and hence I believed the second revolution was born in resistance to another form of dictatorship. Certainly the second revolution even made me assert “A Conscious public will not be a possession of a despot and Egyptians are a proof”. I genuinely took the idea seriously that Egyptians would thrive in protesting until they get their preferred form of government; just like the 18th century series of French Revolutions which profoundly affected modern history. However, I realized that this is not the case when I observe the Egyptian army suspended the constitution and took control the revolution. In a similar manner of the 1974 Ethiopian Revolution during which the Ethiopian army  hacked the revolution the Egyptian army did the same. After that I even went as far as asking “If Revolutions are inherently similar?” 
In the meantime the Ethiopian social media sphere and the private press spontaneously embarked on entertaining a sort of peculiar conversations. These conversations were prompted by Jawar Mohamed’s public comment on Al Jazeera’s English daily television program called The Stream. On the show when Jawar was pressed by the host of the show what he prefers, flanked by his ethnic and national identity; he declared his ethnicity comes first over his national identity and acknowledged himself as ‘Oromo First’. Many consider the public discussion which followed the Jawar incident as a pointless exercise of talking past each other but I think of this spectacle in a different way.  I consider this incident as one of fascinating things because it really helped many people to re-examine their understanding of Ethiopia’s historical and political phenomenon. For me that incident was an excellent opportunity and serves as an evidence that we need a ground for long-running debates and a continuous scholarship on Ethiopia’s historical and political phenomenon. The spectacle should be an eye opening and insightful opportunity especially for those of us who are a loosely-knit community of dissents, oppositions groups, writers and activists whose organizing purpose is only to triumph over EPRDF. It was an incident that tasked all of us to find a possible way and build a system that can maintain a consensus among opponents. Furthermore, the incident made it clearer than ever that most of us only know what we do not want but we do not clearly know what we really want. To conclude on this, the incident exposed that Ethiopians struggle for democracy is not principled but rather it is based on indignation and grudge.  
As difficult as this issue to contemplate I started to realize the fact that despotic leaders are generally results of broader and yet fundamental societal flaws. For me this was like the aha! moment. So when revolution is conceived in a society with a high degree of authoritarianism, the end result is usually more authoritarianism. I think it comes down to individual elite who appeared liberal and revolutionary from authoritarian society are either concealed  authoritarian themselves or the society is not yet ready to allow  them to exercise their liberty. This is like a classic causality dilemma, which one came first a chicken or the egg.  But I think one should change first and it should be the society. It is with this eureka effect that I tried to revisit the revolutions in the Arab world. Tunisia, Egypt, Libya, and Syria… and I tend to think that the revolutions in these countries have done more harm than good. They caused a great deal of human suffering. Removing a despot does not necessarily guarantee a change. In similar manner the 1974 Ethiopian Revolution which removed HaileSelassie’s rule and replaced with the Dergue, a Marxist military junta is just as bad (If not worse) than the revolutions of the Arab world. It is even worse if we consider the human suffering that was caused by the infighting and power struggle of the political parties of the time. I have watched when the storied Ukraine for its Orange revolution of 2004 back to revolution all over again in 2014. I even tweeted about it ‘to revolution then calmness and back’. The February 2014 Ukrainian revolution culminated (I am not sure if I can say it is culminated) in turning over its own State Crimea to pro-Russian forces even though it appeared the Russian involvement in Ukrainian affairs cited as one of the cause of the revolution. I also wrote a commentary on my personal blog asking Are revolutions meant to be betrayed? ››My point in this particular blog post was showing reasons why elite citizens who usually initiate revolutions would end up in brawl and infighting after they started revolutions. I used the old Amharic saying to illustrate my point ‘Thieves usually do not fight when they steal but they brawl when they divide what they robbed”.  I intentionally used the word ‘thieves’ to illustrate the context of Ethiopian political reality. I am referring to Ethiopian astroturf political originations (formal or informal) that are organized in the name of interest group to bring social change. Beyond their being astroturf in their nature they fight each other. We have numerous such groups and their sole propose is to get hold of political power and harvest the benefits from it not brining genuine revolution.
For this reason I truly believe we can bring change without going through an instantaneous revolution. We can take a good lesson from the history of English people. The English people have a lot of exemplary deeds. Rule of law, discussion and public engagement though grass root organizations can bring the desired form of government and we can also achieve social change peacefully.
An acquaintance of mine who knows my stance of instantaneous social change came to visit me in prison after I was unjustly accused of inciting revolution.  He looked at me and said ” Aha, what did I told you, there will never be a change without revolution’. But remarkably even in the injustices and sufferings me and my zone9 blogging collective colleagues have been through I still see the need for an authentic social change. Had the society have had the consciousness; they would have seen the impunity of the Ethiopian government (police) enjoy and the injustice we are suffering from. Apparently the Ethiopian government does not have the slightest concern for legitimate questions of Ethiopians but rather they are deeply bothered by the ‘noise of foreign powers’.   Suffering the consequence of using the right to freedom of expression has become a social reality because the society sits silently and watches all the injustice. Society should start to speak up against injustice but to do so we should embark on educative and liberating process through grassroots activism and peaceful disobedience which are yet not happened in Ethiopia. Once a society has become conscious of the benefits of liberating social change and developed a test for liberty there is no way back. I believe consciousness comes first then liberty follows. We have failed spectacularly because as a society we havethe cart before the horse in mostof our projects.  That is how explained for my acquaintance who visited me in prison as well. However, as Kiflu Tadesse put it on the first of two volumed books “That Generation” which dealt with the 1974 Ethiopian Revolution Haile Fida one of the iconic figures of the storied Ethiopian Socialist Movement never predicted Ethiopians would revolted just one year ahead of the 1974 Ethiopian Revolution. According to Kiflu, in 1973 Haile said for Ethiopians to start a revolution it would take them a minimum of twenty five years. Unless I blunder like Haile I don’t think there will be a revolution in Ethiopia in the foreseeable future. Finally like the Ethiopian satirist Abebe Tola usually say if I screw-up on this screw me over. 

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ
 

ርዕሱን  አላስታውሰውም ‘ንጂ እ.ኤ.አ በ2011 Arab Uprising በመባል የሚታወሰውን አብዮትተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን ፌስቡከኞችም (በተለይ ዲያስፖራ የሚገኙ) ግንቦት 20 ላይ (ልክ በኢሕአዴግ የ20ኛ አገዛዝ ዕድሜ)   “Anger day” በሚል በፌስቡክ አብዮትመጥራታቸውን ተቃውሜ አንዲት ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ በዓመቱ ደግሞ ‹‹ አብዮት ወረት ነው›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ አብዮት ለማስነሳት ፍላጎት ያላቸው በርካቶች እንዳሉ ገልጬ ነገር ግን ይጎድላቸዋል የሚባሉትንነገሮች ዘርዝሬ ጽፌ ነበር፡፡ በነዚህ ሁለት ጽሑፎች ላይ፣ ላዩን አብዮትን የተቃወምኩ ቢመስልም እውነታው ግን ጽሑፎቹ በተጻፉበትወቅት ሕዝቡም፣ ተቃዋሚ ልሂቃኑም፣ ሁኔታዎቹም ለአብዮት ዝግጁ አይደሉም የሚል ዝንባሌ ማሳየቱ ነበር፡፡
ከሌላ ዓመት በኋላደግሞ ‹‹ስለለውጥ›› በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎችን በ‹‹ዞን 9›› ላይ በግል ተነሳሽነት ማስፈር ጀምሬ ነበር፡፡ ጽሑፉን የጀመርኩት ‹‹ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በምርጫ ይለቃል?›› በሚል ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹አይለቅም›› የምልባቸውን ምክንያቶች ካስቀመጥኩ በኋላ የለውጥ አማራጭ የምላቸውን (አብዮት፣ሰላማዊ አለመታዘዝ /civil disobedience/ የመሳሰሉትን) በየዘርፉ እየቀነጫጨብኩ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ ከዚያም ‹‹የለውጥ ፍርሃት››፣ ‹‹የሥርዓት ለውጥ እና ሃይማኖት››፣ ‹‹የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት እና የማኅበራት ሚና›› የሚሉ ርዕሶችን በማንሳት በሐሳቦቹ ላይ በሐቀኝነት ለመከራከር ጥረት አድርጌያለሁ (ከዚህ በላይ አልገፋሁበትም እንጂ)፡፡ በበኩሌ ስለአብዮት በደንብ ያነበብኩትም፣ ያሰብኩትም፣ የጻፍኩትም፣ የተረዳሁትም ያኔ ነበር፡፡ ያኔ በአብዮት ላይ የነበረኝ እምነት ተሸርሽሮ ግማሽ ደርሶ ነበር፡፡ ተንጠፍጥፎ ያለቀው ግን አሁንም በዓመቱ (በ2006 አጋማሽ) ነው፡፡ አንባቢ ከአብዮት አድናቂነት ወደ ዝግመተ ለውጥ አራማጅነት (በ ‹‹ያ ትውልድ›› ሰዎች አጠራር ከRevo ወደ Sabo) የተሸጋገርኩበትን የሐሳብ ዳገት (ከፈለጋችሁ ቁልቁለት በሉት) ይረዳ ዘንድ በመጠኑ ዘርዘርአድርጌ ማስረዳት አለብኝ፡፡ (ታዲያ አብዮት አድናቆቱም ቢሆን ከወረቀት እንዳላለፈ ልብ በሉልኝ)፡፡
እነዚያን ተከታታይ ጽሑፎች በጻፍኩበት ሰሞን  ‹አብዮት ‹‹እቆጣጠረዋለሁ›› ብለው ያሰቡትንነገር ግን ድንገት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን የሚችል እሳትን መለኮስ› እንደሆነ እያሰብኩ ባለሁበት ሰሞን ግብጻውያን ሙርሲን ለመጣል ያምጹ ጀመር፡፡ የግብጹ ድጋሚ አመጽ (አብዮት) በጣም የተዘበራረቀ ስሜት ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ሙርሲ እኔ በግሌ ከማምንባቸውና ቋሚም ከሆኑ የዲሞክራሲ መርሆች እያፈነገጠ ነበር፡፡ ስለዚህ የግብጾች ማበይ ምክንያታዊ ነው ብዬ አምኛለሁ፤ እንዲያውም ሕዝብ አንዴ ‹ከነቃ አይሆንም ዕቃ› ብዬ ነበር፡፡ የግብጽ ሕዝብ የሚፈልገውን ዓይነት ሥርዓት እስከሚያገኝ እያበየ ይቀጥላል የሚል ግምት ነበረኝ- ልክ እንደ ፈረንሳዮቹ ተከታታይ አብዮቶች፡፡  ነገር ግን የግብጽ ሕዝብ እያበየ ቢቀጥልም እንኳን የፈለገውን ላያገኝ እንደሚችል የተረዳሁት ወታደራዊ ክንፍ ቀስ በቀስ አገሪቱን በአብዮቱ ተከልሎ ሲጠቀልላት ስመለከት ነበር ፡፡ ከአገራችን የደርግ አመጣጥ አልለይ ብሎኝ ‹አብዮቶች ሁሉ አንድ ናቸው እንዴ?› እስከሚያስብል ድረስ ተመሳስሎብኝም ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ እና ፕሬሶች በአንዳች ተዋስኦ ይናጡ ጀመር፡፡ ተዋስኦው የተጀመረው የጃዋር መሐመድን ‹ኦሮሞ ቅድሚያ›(Oromo First) የአልጄዚራ ምላሹን ተከትሎ ነበር፡፡ ብዙዎች ይሄን ወቅት የሚያስታውሱት እንደአላስፈላጊ የንትርክ ወቅት ቢሆንም፣በበኩሌ ብዙዎች ቆም ብለው አቋማቸውን እና የአቋማቸውን መሠረት እንዲፈትሹ፣ በታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ኩነቶች ላይ ንባባቸውን እንዲቀጥሉ ያስታወሰ መልካም አጋጣሚ ነው ባይ ነኝ፡፡ ይህ አጋጣሚ በስመ ተቃዋሚ (dissent) የአንድ ኢሕአዴግን ከሥልጣን መውረድ ብቻ እንደ ለውጥ ግብ አድርገን በጋራ ስንንቀሳቀስ የነበርን ተቃዋሚ ግለሰቦች እና ቡድኖች እርስ በርስ ያሉትን ልዩነቶች እና ልዩነቶቻችንን የምናቻችልባቸውን መንገዶች እንድናስተውል መንገድ ፈጥሯል፡፡ ብዙዎቻችን የማንፈልገውን እንጂ የምንፈልገው ምን እንደሆነ በቅጡ እንደማናውቅ፣ትግላችን ከመርሕ ይልቅ በእልሕ እንደሚመራ ያጋለጠ፣ ራሳችንን እንድንገመግም ያስገደደ አጋጣሚ ነበር፡፡

ከዚህ ድንጋጤ ውስጥነው ‹አምባገነን መሪዎቻችን ከሕዝብ ጉያ የወጡ› የአስተሳሰብ ችግር የወለዳቸው የመሆናቸው ሐቅ ዘልቆ የገባኝ (ወይም genuinely comprehend ማድረግ የተቻለኝ) ስለዚህ አብዮት ሲፀነስ ዓላማው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ የተለወጠ መሪ ማስቀመጥ ቢሆንም ሲወለድ ግን አንድም ያልተለወጠ ሕዝብ የተለወጠ መሪ መውለድ ስለማይችል፣ አንድም ደግሞ የተለወጠ መሪ እና ያልተለወጠ ሕዝብ  መዋሐድ ስለማይችሉ፣ አብዮቱ (ዓላማው) ይጨናገፋል፡፡
በዚሁ ጊዜ ነበር የቅርብጊዜ ምሳሌያችንን የአረብ አብዮትን መልሼ በወፍ በረር ለመገምገም የተገደድኩት፡፡ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ…. ከተሳካው የከሸፈው፣ከለማው የወደመው ይበዛል፡፡ የአምባገነን መገርሰስ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፤ ከነዚህኞቹ ለውጦች ይልቅ የእኛው ፊውዳሊዝምን ገርስሶ- ወታደራዊ አምባገነንነትን ያመጣው አብዮት የተሻለ ኪሳራ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡ (እዚህጋ በኢሕአፓ፣ መኢሶን እና ሌሎችም የደርግ ፓርቲዎች መካከል የተደረገው የድኅረ አብዮት የሥልጣን ሽኩቻ ሳቢያ የጠፋውን ሕይወት ሳንቆጥር መሆኑ ነው፡፡) ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ በብርቱካናማ አብዮቷ የምትደነቀው ዩክሬን አበየች፡፡(‹“የተውኩትን ነገር ተነግሬ፣ ተመክሬ ባገር ምን ጎትቶ አመጣብኝ፣ የአብዮትን ነገር?” Another revolution? ብዬ ትዊት አድርጌም› ነበር) አብዮቷ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የአካሏ ክፋይ የሆነችው ክሬሚያን በማሳጣት ይጀምራል፡፡ ምዕራብ ዩክሬናውያን ሲያብዩ ‹የአገራችን መንግሥት ከምዕብራባውያን ይልቅ ምስራቃውያን (ራሺያ….) አደላ› ብለው ቢሆንም በውጤቱ ግን ጭራሽ ራሺያ ክሬሚያን ጠቅልላ አረፈችው፡፡ልብ በሉ! አብዮቱ ከተነሳበት 360 ዲግሪ ዞሮ ተጠናቀቀ፡፡ ለነገሩ አልተጠናቀቀም፤ አሁን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ተሸጋግሯል፡፡
ይኼኔ ነበር በግል ጦማሬ ላይ ጥር 2006 ‹‹Are revolutions meant to be betrayed?›› ብዬ በመጠየቅ የጻፍኩት፡፡ ዜጎች አብዮትን ሲጀምሩት የማይታዩ ችግሮች ሲጨርሱት የሚስተዋለው ‹ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም› ነበር የጽሑፌ አንኳር ሐሳብ፡፡ ‹‹ሌባ›› ያልኳቸው  በሕዝባዊ አብዮት ስም የግል ሕልማቸውን የሚያሳኩ አጀንዳ ያላቸውን ቡድኖች (interest groups) ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ እውነታ ደግሞ እነዚህ ዓይነቶቹ interest groups ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በአብዮት ለውጥ አማጭነት ተስፋ ስቆርጥ የመጀመሪያ ጥያቄዬ ‹‹ሳያብዩ ለውጥ ማምጣት ይቻላል?›› የሚል ነበር፡፡ የመጀመሪያ መልሴ ‹‹እንግሊዝ›› ነበረች፡፡ የእንግሊዝ ሕዝብና መንግሥት በሕግ የበላይነት ላይ ለማንም ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ የዓለምን ግማሽ በገዙበት ጊዜም አሁንም አብየው አያውቁም- እንግሊዛውያን፡፡ ምክንያቱም ተወያይተው ችግራቸውን መፍታት ይችላሉ፡፡ ሕዝብና መንግሥት ሲለወጡ ሁሉም በሰላም ይካሄዳል፡፡
ይህንን የመጨረሻ አቋሜን ያውቅ የነበረ ወዳጄ፣ ‹‹እህ አሁንስ?›› አለኝ ‹አብዮት ልታስነሳ አሲረሃል› ተብዬ ተጠርጥሬ ከታሰርኩ በኋላ  ሊጎበኘኝ መጥቶ፡፡ ‹‹አየኸው አይደል፣ ያለአብዮት ለውጥ እንደማይመጣ?›› የሚገርመው፣ የኔና የጓደኞቼ በሕገ-ወጣዊ ማንአለብኝነት መታሰርና፣ የመንግሥት (ፖሊስ) ተጠያቂነት ማጣት ውስጥም ሕዝባዊ አለመለወጥ ነው የሚታየኝ፡፡ መንግሥት አሁንም ቢሆን የሚያስጨንቀው ‹‹የውጭ ኃይሎች ጫጫታ›› እንጂ የውስጥ ሰዎች ጥያቄ አይደለም፡፡ በእኛ ላይ የደረሰው (ሐሳብን በመግለጽ ጦስ መታሰር) በሌሎች ላይ ሲደርስ የነበረ፣ እየደረሰ ያለ ፣ ወደፊትም የሚደርስ መሆኑ ቢታወቀውም ሕዝባችን ግን ‹‹መብቴን ማስጠበቅ አለብኝ›› ከማለት ይልቅ ‹‹ዝም ብል ይሻለኛል›› (ጎመን በጤና) mode ውስጥ ነው፡፡ ሕዝብ ገና አልተለወጠም፤ የለውጥ ጣዕሙም የገባው አይመስልም፡፡ ሌሎች ሰላማዊ የትግል አማራጮችም ገና በኢትዮጵያ አልተሞከሩም፡፡ ሕዝቡ ጣዕሙን የማያውቀውን ለውጥ ከመስጠት በፊት ደግሞ የለውጡን ጣዕም አውቆ ለውጡን ራሱ ጠይቆ፣ ራሱ እንዲያመጣው ማንቃት ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ እንግሊዛውያኑ እንደሚሉት ‹ጋሪው ከፈረሱ ቀድሞ› አይሆንም! ለወዳጄም ይህንኑ ሃሳቤን ነበር የነገርኩት፡፡
ለነገሩ ይህንን ሁሉአልኩ እንጂ ክፍሉ ታደሰ በ‹‹ያ ትውልድ›› (ቅጽ 1) ላይ  ‹ኃይሌፊዳ በ1965 በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ አብዮት ይነሳል ብዬ አልገምትም ብሎ ነበር› እንዳለው ካልሆንኩ በቀር እኔም በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይነሳል የሚል ምንም ግምት የለኝም፤ በመጨረሻም በአቤ ቶክቻው ዋዘኛ አባባል ‹‹ካጠፋሁ፣ልጥፋ!››

ይህ አመት አንደተለመደው አይነት አመት ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የዞን9 ጦማርያን በጦማሪት ማህሌት አስተባባሪነት ፣ በአጥናፍ ብርሃኔ እና በጆማኔክስ ካሳዬ ትብብር የአመቱን ታላላቅ ክስተቶች አሰባስበው ከመታተሙ በፊት ለቡድኑ ክለሳ የሚያቀርቡበትና የተረሱ እና ለክስተትነት የማይበቁ የምንላቸውን ሁነቶች የምንለይበትና የአመቱን የጊዜ መስመር የምናወጣበት ወቅት ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ያንን ከማድረግ ይልቅ የዞን9 የጦማርያን ቡድን የጊዜ መስመርን በመስራት ያለፈው አንድ አመት አሁን በስደት እና በእስር የሚገኙት ወዳጆች አንዴት አሳለፉት የሚለውን ለመግለጽ ወደድን፡፡  ይህ የጊዜ መስመር የመጨረሻው የዞን9 ኢትዮጲያዊ ህልም ዘመቻ ከተካሄደ በሁዋላ ባለው የ2006 ዓ/ም በዞን9 ዙሪያ የነበሩ ነገር ግን ለአደባባይ ያልበቁ ክስተቶቸን ይዘግባል፡፡ አላማውም አመቱ አንደቀልድ አለማለፉን እና በአደባባይ ያልተባሉት ጉዳዪች ምን እነደነበሩ ለዞን9 ነዋሪያን ግንዛቤ ያህል ከብዙ በጥቂቱ የቀረበ ነው ፡፡
መስከረም 2006 –አራት የዞን9 ጦማርያን የተሳተፉበት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በኢትዮጲያ ምን ይመስላል የሚል ሪፓርት ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡ በሪፓርቱም ላይ ሃሳብን የነጸነት የመግለጽ መብት ምን ይመስላል የሚለውን ሪፓርት ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ በሚያዝያ ኢትዪጵያ መንግሰት ላይ ለሚያደርገው ዩንቨርሳል ፔሪዲክ ሪቪው (UPR)- የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ በሰባአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የሀገራት የእርስ በርስ መገማገሚያ ስነ ስርአት  የሚቀርብ  (ለሚዲያ የማይቀርብ ለተባበሩት መንግሰትት ብቻ የሚገባ) ሪፓርት ነበር፡፡
በሪፓርቱ ከተሰራ በሁዋላ ጦማርያን ጓደኞቻቸውን እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ጠንካራ አቋም አላቸው የሚሏቸውን የገዢውን ፓርቲ ደጋፌዎች በመጨመር የሪፓርቱን ውጤት አሳይተው ግብረ መልስ ተቀበሉ፡፡ በወሩ መጨረሻም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስረከቡ፡፡ (በዚህ ሂደት በሁዋላ ለደህንነት አካላት የወዳጆቸን እንቅስቃሴ በመንገር አየር መንገድ ላይ ሲወጡ አንዲጠየቁ ያደረገው የሪፓርተሩ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ የዚህ ሪፓርት ዝግጅትም ንቁ ተሳታፌ ነበር፡፡ )
 በዚሁ ወር የዞን9 ጦማርያን ወዳጅ የሆኑ የተለያዩ አጋር አካላት መንግሰት ጦማርያኑን ከግንቦት ሰባት ጋር በማያያዝ ስማቸውን እያነሳ ነው በሚል ለጦማርያኑ ጉዳዩን ግልጽ አንዲያደርጉላቸው ጠየቁ፡፡ በማስከተልም   የዞን9 ጦማሪ እንዳልካቸው ሃይለሚካኤልን ለትምህርት ከአገር መሄድ አስመልክቶ በተደረገ የምሳ ግብዣ ላይ የቡድን የደህንነት ጉዳይ የውይይት ርእስ ሆኖ ተነሳ ፡፡ በወቅቱ ብዙ የዞን9 ጦማርያን መንግስት አንደ አደጋ አይቆጥረንም የሰራነውም ወንጀል የለም፣ ያለን እንቅስቃሴም ኢንተርኔት ላይ የተገደበ በመሆኑ የደህንነት( እስርም ሆነ የስደት ) ስጋት የለብንም በሚል ተከራከሩ፡፡ በተቃራኒው ቢሆንም አንዲህ አይነት የመንግስት አረዳድ ላይ ችግር ካለ ለጊዜው ለሚቀጥሉት ወራት አንቅስቃሴያችንን በማቀዝቀዝ የመንግሰት ጥርጣሬ አግባብ አለመሆኑን ለማሳየት እንሞክር የሚል ሌላ ክርክር በመምጣቱ ሃሳቡ ተቀባይነት አግኝቶ ውሳኔ ላይ ተደረሰ፡፡ በመሆኑም የበይነ መረብ ዘመቻዎች ለተወሰነ ጊዜ አንዲቆሙ ፣ ወደአፍሪካ ኮሚሽንም ሆነ ወደተባበሩት መንግስታት አንዲሁም የኢንተርኔት አራማጅነትን አስመልክቶ ልምድ ለማካፈል የሚደረጉ ማንኛውም አይነት አለም አቀፍ ጉዞዎች ( በጣም አስፈላጊ እና ቀድመው የታቀዱ ካልሆኑ በስተቀር) አንዲተላለፉ ተወሰነ
በዚሁ ወር አጋማሽ ጦማሪ እነዳልካቸውለፒኤች ዲ ትምህርት ወደአሜሪካን አገር ኦሪጎን ዪንቨርሲቲ አቀና፡፡
በዚሁ ወር መጨረሻ ሁለት የዞን9 ወዳጆች እና አጋሮች ከአዲስ አበባ ኤርፓርት ለመውጣት ሲሞክሩ ኢሜግሬሽን ላይ ካገር አንዳይወጡ ለተወሰነ ሰአት ተይዘው የተለያዩ ጥያቄዎች ቀረበላቸው ፡፡ ሁለቱም ወዳጆች ላይ በተደረገው ድንገተኛ ምርመራ ከዞን9 ጦማርያን ጋር ያላቸውን ግንኙነት አንዲያስረዱ ተጠየቁ ፡፡
ጥቅምት/ ህዳር 2006 – ጦማርያኑ በዞን9 በኩል የሚጻፉ ጽሁፎችን አቀዝቅዘው በግል የማህበረሰብ ሚዲያው ላይ ወጣ ገባ ሲሉ ቆዩ፡። በዝምታው ቆይታ በጦማርያኑ የታየ ይህ ነው የሚባል የአደባባይ ስራ ቢኖር አሜሪካን አገር ለሚገኘው የኤንፒአር ኮጆ ሾው ኢትዮጲያ ውስጥ በትችት ድምጽ መጦመር ምን ይመስላል የሚለውና የሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በኢትዮጵያ የሚለው አርቲክል 19 በተባለው መንግስታዊ ያልሆነ የሰብአዊ መብት ድርጅት የተሰራው ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ተሳትፎ ማድረግ ብቻ ነበር፡፡
ታህሳስ 2006  – በዚህ ወር በተደረገ ስብሰባ የታየ በቂ ደህንነት ችግር ስለሌለ ስጋታችን የተጋነነ ነውና ወደተለመደው አንቅስቀሴያችን መመለስ አለብን የሚል ውይይት ተካሄደ፡፡ ወደ ሥራ ለመመለስ የጋራ እቅድ ለማውጣት እና የተለመዱ የዞን9 ስራዎችን ይዞ መመለስ ይገባል የሚል ሃሳብ ተነስቶ ለመመለስ የሚያስፈልጉ ዘመቻዎች እቅዶች እና አዳዲስ ጉዳዮቸን የማስተዋወቅ እቅድ አንዲወጣ የስራ ክፍፍል ተደረገ፡፡  ተያይዞም ኢንተርኔት ላይ የዞን9 ህጋዊ ምዝገባን ለማረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ ባለመኖሩ በተለያየ መልክ በመመዝገብ ይበልጥ ወደ ማህበረሰባዊ ስራ መጠጋትና ተቋማዊ ማድረግ ይገባል ተብሎ ተወሰነ፡፡ በ6 ወር ጊዜ ገደብ ውስጥም ወደሚዲያ/ሲቪል ሶሳይቲ ለማሳደግ ያሉትን እድሎች የማየት እቅድም አብሮ ተያዘ፡፡  በተመሳሳይ ወር አቶ አቤል አባተ አቀናባሪነት በመንግሰት ደህንነትና በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ድጋፍ የዞን9 ጦማርያን ላይ የተነጣጠረ የቀለም አብዩት የተሰኘው አሳፋሪ ሃሳብን የሚያቀርበው የቴሌቪዥን ዶክምንተሪ ታየ፡፡ (በወቅቱ በጦማርያኑ መካከል በተደረገ ውይይት ከዶክንተሪው በፌት ዞን9ን ይመለከታል የሚል ግምት መጀመሪያም አሳድሮ ነበር፡፡ )  
ጥር 2006 – ጦማሪ ናትናኤል ከአንድ ራሱን ከብሄራዊ ደህንነት አንደመጣ ባስተዋወቀ ሰው በመኖርያ ወረዳው አስተዳደር አማካኝነት ጥያቄ ቀረበለት፡፡ በወቅቱ ጥያቄው ስለጦማሪ ናትናኤል የፓለቲካ ተሳትፎ ስለዞን9 ምስረታ፣ አላማ ፣ እና አባላት የመሳሰሉት ሲሆኑ የደህንነት አባሉ የዞን9 አባላት 10፣000 ናቸው አላማችሁ ምንድነው? የአገር ደህንነትን የሚነካ ነገር እየሰራችሁ እንዳልሆነ በምን እናውቃለን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር፡፡ ናትናኤል የዞን9 አላማ እና የሚሰራቸውን ስራዎች በዝርዝር አስረድቶ አባላቱ 9 አንደሆኑ 10.000 የተባሉት የዞን9 የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደረጉት ናቸው በማለት አብራራለት፡፡ የደህንነት አባሉ የቡድን አደረጃጀት ምን ይመስላል? ድጋፍ ታገኛላችሁ ወይ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ናትናኤልን አብረኸን እንድትሰራ አንፈልጋለን የሚል ጥያቄ አቀረበለት፡፡ ናትናኤል በወቅቱ ከደህንነት ጋር የሚያሰራ ምንም ችሎታ አንደሌለው ሌላ ጊዜ ቢጠየቅም ተመሳሳይ መልስ አንደሚመልስለት[JK4]  በማሳወቁ ደህንነቱ ወደፌት እናወራለን በማለት ተለየው፡፡ በዚህም የተነሳ በዚሁ ወር የታቀደው ጽሁፎችን እና ዘመቻዎችን ይዞ የመመለስ ውሳኔ ጉዳይ በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡ በተመሳሳይ ወር ከታሳሪዎች አንዳቸው ከናትናኤል ጋር ተመሳሳይ የሆነ የደህንነት ጥየቃ አስተናገዱ ፡፡ በወቅቱ ከአሁን ታሳሪዎችን አንዱን ያናገረው ሌላ የደህንነት አባል  የሚሰሩትን ነገር ሪፓርት አድርጉልን እየተከታተላችሁ በመናገር አብራችሁን ስሩ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡
የካቲት 2006 – በዚሁ ወር መጨረሻ ጦማሪት ሶልያና ሽመልስ ሰብአዊ መብት አማካሪ ፌሎ በመሆን በቀጣዩ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ግምገማ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስራዎቸን ለመስራት ለመስራት ተጓዘች፡፡ በጦማሪያኑ በተደጋጋሚ የሚገናኙባቸው ቦታዎች ላይ በግልጽ እና በሚታይ መልኩ የደህንነት ሰዎች አዘውትረው መታየት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ  ወር ጦማሪ ሶልያና ቀድማ የምትሰራበት መስሪያ ቤቶች ሃላፌዎች ጋር የደህነት ሰዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀረቡ፡፡ በዚሁ ወር በተመሳሳይ ናትናኤል እና በሌላ አሁን ታሳሪ ላይ ላይ የሚደርሰው ወከባ (በአካልም በስልክም) በረታ ከሚጠየቁት ጥያቄዎችም መካከል አላማችሁ ምንድነው ? ከነማን ጋር ነው የምትሰሩት? በፓርላማ ከታገዱ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ ? ባለፉት ወራት ዝም ያላችሁት ለምንድነው ? እየሰራችሁ ያላችሁት ሌላ ስራ አለ ወይ? የሚሉ ነበሩ፡፡ በወቅቱ የተነሱት ጥያቄዎች አላማችሁ ምንድነው? አባላታችሁ አደጃጀት አላችሁ ወይ የሚሉ ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ሲሆኑ ጥያቄ ፣ የደህንነት አባላቶቹ ስለ ኢንተርኔትም ሆነ ስለማህበረሰብ ሚዲያ ያላቸው እውቀት በጣም አነስተኛ በመሆኑ ግማሹ ጊዜ መሰረታዊ የማህበረሰብ ሚዲያን አሰራር በማስረዳት የሚያልቅ ሲሆን በአንድ ወቅት አንዱ የደህንነት አባል ፍሪደም ኦፍ ኤክስፐረሽን ትሰራላችሁ የሚል ክስ በማቅረቡ በተመጣጣኝ ደረጃ መነጋገር አስቸጋሪ እየሆነ ነበር፡፡
መጋቢት 2006-  ከአሁን ታሳሪዎች አንዱ ላይ  አሁን ዝም ያሉት ለምንድነው?  የሚሰሩት ሌላ ነገር ስላለ ነው የሚሉ ጥያቄዎቸን በተደጋጋሚ አስተናገዱ፡፡ ፣ በዚሁ ወር ነገሮች መክፋታቸውን ተከትሎ ለዞን9 ጦማርን ለሌሎች ልምድ እንዲያካፍሉ በተጋበዙበት በታንዛንያ በተደረገው ስብሰባ ውጪ ያሉ የዞን9 ጦማርያን በስካይፕ የተሳተፉበት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄደ፡፡ በዚህ ውይይት ላይም የምንሰራው ወንጀል የለምና ምንም ሊያሰጋን የሚገባ ነገር የለም የሚለው ክርክር አንዳለ ቢሆንም እየበረታ ካለው የደህንነቶች ወከባ አንጻር ተረጋግተው አንዲመለሱ ማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውሳኔ ተሰጠ፡፡ ፡፡ በዚህም መሰረት ጦማሪ ናትናኤል ደህንነት አባሉ በሚያናግረው ወቅት ስራችንን አንዲያስረዳው (  ደህንንቱ ትዊተር ፌስ ቡክ አጠቃቀም አንዲያሳየው ፣ የተጠረዘውን የዞን9 ስራዎች ስብስብ አንዲሰጠው እና ክትትላቸውም አግባብ አንዳልሆነ እንዲገልጽለት) ተወሰነ፡፡ መንግሰት አዲሱ ስጋት ከ ለምን ተናገራችሁ? ወደ ለምን ዝም አላችሁ? የተቀየረ በመሆኑ ዝምታችን ማቆምና የመመለስ ዝግጅት ማድረግ አንደሚገባ፣ እንዲሁም በደህንነቶች በከፍተኛ ሁኔታ ስማቸው የሚነሳ የቡድኑ አባላት ከፍተኛ የደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አንዲመች የደህንነት ስጋት ቅደም ተከተል በማውጣት ጦማሪት ሶልያና እና ጦማሪ በፍቃዱ በአንደኛ ደረጃ በመንግሰት ደህንነቶች አይን በመታየት ጦማሪ አጥናፍ እና ናትናኤል (ናትናኤል በቀጥታ እያናገሩት በመሆኑ እና አጥናፍ ቀድሞ የሚሰራበት መስሪያ ቤት በመሄድም ጭምር የክትትል ሂደቱ ስለጠነከረበት ) በሁለተኛ ደረጃ  በከፍተኛ የደህንነት ግንኙነት መረብ ውስጥ በመሆን  እነዚህ ጦማርያን አስፈላጊውን ጥንቃቄ አንዲያደርጉ እና ወደፊትም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አንደሚያስፈልግ  ለጊዜው ግን ወደ ተለመደው ኢንተርኔት በመመለስ ምንም እየሰራን አንዳልሆነ ማሳየት አለብን የሚል ውሳኔ ተደረሰ፡፡ ( በወቅቱ ሌሎች ጦማርያን ላይ ያለው ስጋት ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ነው የሚል ድምዳሜ ነበር)
በዚሁ ወር መጨረሻ ጦማሪ አቤል ዋበላ ላይ ከምሽቱ 2 ሰአት 22 አካባቢ በፌዴራል ከሚጠበቅ የመንግስት መስሪያ ቤት አጠገብ ከፍተኛ የአካል ድብደባ ደረሰበት በድብደባው ራሱን የሳተ ሲሆን ሲነቃ ከላፕቶፑና ከስማርት ስልኩ ውጨ የተወሰደ ምንም ንብረት አለመኖሩም ሌላ ከፍተኛ ጥርጣሬን አስነሳ፡፡
በዚያው ወር መጨረሻ ጦማሪ ናትናኤል ለደህንነት አባሉ የዞን9 ስራዎችን የሚያሳይ ጥራዝ በመስጠት የአባላቱን የፌስ ቡክ እና የትዊተር አንቅስቃሴ አንዴት መከታተል አንደሚችል በተወሰነው መሰረት አስረዳው፡፡ ከሚታየው ውጪ የምንሰራው ነገር የለም የዝምታችን ምንጭም የደህንነቶች ወከባ መሆኑን ተናገረ ፡፡ በተደጋጋሚ ህጋዊ መታወቂያ ቢጠይቀውም የደህንነት አባሉ መታወቂያ ለማሳየት ፍቃደኛ አልነበረም፡፡ በዚሁ ወር ከቀድሞው በተጨማሪ ከአሁን ታሳሪዎች በአንደኛው ላይ ከደህንነቶች ጋር አብሮ የመስራት ጥያቄው ጠነከረ፡፡ አብሮ ካልሰራ የመታሰር አደጋ አንዳለውም ደጋግመው አስጠነቀቁት፡፡ ነገር ግን ማስፈራሪያውን ተከትሎ የሰሩትን ህገ ወጥ ስራ ስለማላውቅ ልተባበር አልችልም ብሎ በአቋም ጸና፡፡
ሚያዝያ 2006  -የቡድኑ የወቅቱ አስተባባሪ ናትናኤል ፈለቀ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቶች ጋዜጠኞች እና ጦማርያን የሚያደርጉበት አመታዊ የልምድ ልውውጥ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስዊድን ተጉዞ ተመለሰ፡፡ በዚሁ ወር መጀመሪያ ከዞን9 ጦማርያን ጋር ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ጋር ተያያዥ ስራዎችን በመስራት አጋር ድርጅት የሆነው የአርቲክል 19 ሰራተኛ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ለ36 ሰአታት ተይዞ ከአገር አንዲወጣ ተደረገ፡፡ በወቅቱም መንግሰት ድርጅቱ የሚሰራውን ስራ አንወደውም ከማለት ውጪ ለማባረሩ የሰጠው ሌላ ምክንያት አልነበረም (ይህ ድርጅት ከዚህ ቀደም አቶ ሽመልስ ከማልን ጨምሮ ለሌሎች ባለስልጣናት ስልጠና የሰጠ ሲሆን የሚዲያ ሕጉ በሚወጣበት ወቅት ከመንግስት ጋር አብሮ ይሰራ የነበረ መሆኑ ይታወሳል )
በዚሁ ወር በነበረው በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሚካሄደው የኢትዮጲያ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ በሰባአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የሀገራት የእርስ በርስ መገማገሚያ ስነ ስረአት ቅድመ ግምገማ (Pre UPR) ሊሳተፉ ተጋብዘው የነበሩ ሁለት ጦማርያን የመንግስትን ክትትል ለማረጋጋት በማሰብ ጉዞአቸውን ሰረዙ ፡፡
በመጀመሪያው ሳምንት በጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ፣ በጦማሪ አጥናፍ ላይ የነበረው ክትትል በመጨመሩ እና በጦማሪ አቤል ላይ የደረሰው ድብደባ አጠራጣሪነቱ ከመጨመሩም በተጨማሪ ሌሎች የዞን9 ወዳጆች ከደህንነቶች በተደረገ ተከታታይ የስልክ ጥሪ ጆማኔክስ እና ማሂፋንትሽ የሚባሉ ጦማርያንን አድራሻ አንደሚያውቁና አንዲናገሩ መጠየቃቸውን ተናገሩ፡፡  
በተመሳሳይ ቀን ከደህንነት ቢሮ ጦማሪ ናትናኤል ጋር ተደውሎ የዘጠኙንም አባላት ሙሉ ስም የስልክ አድራሻ እና የሚሰሩበትን መስሪያ ቤት አንዲገልጽ ተጠየቀ፡፡ ( ናትናኤል በወቅቱ ስራቸውን ለመስራት የተሻለ ስልት መጠቀም አንደሚገባቸው በማሳሰብ የማንንም አድራሻ ለመናገር ፍቃደኛ አንዳልሆነ መለሰ)
በእለቱ  ምሽት በጣም አስጊ የሆኑትን ጉዳዪች አስመልክቶ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰበት ውይይት ተካሄደ፡፡ በመሆኑም ዝም በማለት የመንግስት ደህንነቱን ለማረጋጋት የተደረገው ሙከራ አለመሳካቱ አንደውም ለምን ዝም አሉ ወደሚለው መንገድ ማምራቱን ተከትሎ መናገርም ዝም ማለትም ያልተፈቀደልን የቡድኑ አባላት የተለያዩ ምን ማድረግ ይገባል የሚሉ ተከታተይ ውይይቶችን በየቀኑ ማካሄድ ተጀመረ፡፡[በወቅቱ የስጋቱን ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ተከትሎ አውሮፓ ቪዛ ያለው ጦማሪ በፍቃዱ ለጊዜው ከአገር ወጥቶ ዞር አንዲል  የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው፡፡ ( በወቅቱ በነበረው መረዳት ከፍተኛ አደጋ ላይ አለ ተብሎ የታሰበው በፍቃዱ ነበር)
 ተከታታይ ውይይቶቹ ሲጠናቀቁ ሁለት ሃሳቦች ለውሳኔ ቀረቡ – አንደኛው እየተጠናከረ የመጣውን ጫና በይፋ በመግለጽ ዞን9ን በመበተን ቡድኑ በይፋ እንዲዘጋ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ ወደተለመደው የኢንተርኔት  እንቅስቃሴ በመመለስ እስካሁን ቡድኑ የጠፋበትን ምክንያት መግለጽና ተመሳሳይ የሆኑ ክትትሎችን በተከታታይ ለአአደባባይ ማዋል  በሚል ውይይት ተደረገ፡፡ በዚህ ቀናትን በፈጀ ውይይት ለመጀመሪያም ( ምናልባትም ለመጨረሻ ጊዜም) ውሳኔ ለመስጠት ድምጽ ብልጫ ይደረግ በተባለው መሰረት  በአንድ ተቃውሞ በሁለት አብላጫው በወሰነው እስማማለሁ እና በስድስት ድጋፍ ወደእንቅስቃሴ ለመመለስ ተወሰነ፡፡ ተያይዞም ከደህነት የሚመጡ ጥያቄዎቸን ከዚህ በሁዋላ ማስተናገድ አንደማይገባ ተወሰነ፡፡  
( በዚህ ውሳኔ ወቅት ሁሉም ጦማርያን መንግስት በፍጥነት የእስር እርምጃ ይወስዳል የሚል ግምት ያልነበረን ሲሆን ወደስራ ተመልሰን “ተጽእኖ” እስክንፈጥር ወይም የስራችንን ይዘት አይተው እርምጃ ይወስዳሉ በሚል ግምት ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ሊመጣ የሚችለውን ነገር አና መደረግ የሚገባቸውን ስራዎች ማዘጋጀት ላይ ከማቀድ ውጨ ያደረግነው ዝግጅት አልነበረም፡፡) 
ሚያዝያ 15 – የዞን9 አባላት ሁሉም በተለመደው ሁኔታ የኢንተርኔት እንቅስቃሴያቸን መመለሳቸውን የሚገልጽ መግለጫ ወጣ፡፡ በወቅቱም ለጊዜው የእስረኞች አያያዝን፣ እየተነቃቃ መጣውን የኦሮሞ ብሄርተኝነት ተከትሎ ታዋቂ የኦሮሞ ፓርቲዎች ፕሮግራምን ማስተዋወቅን( ልዩነቶቻቸው እና አንድነቶቻቸውን)  እና ለመጪው ምርጫ የሚሰሩ ዘመቻዎችን ማዘጋጀት ላይ ማተኮር የመመለሻ ስራዎች አቅጣጫ አንዲሆን ተወሰነ፡፡  ተወሰነ፡፡ በተጨማሪም በመጪው ሳምንት የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ በሰባአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የሀገራት የእርስ በርስ መገማገሚያ ስነ ስረአት አስመልክቶ መረጃዎችን መስጠት ላይ አንድናተኩር እና ቀድመው ታቅደው ነበሩ የዞን9 ስራዎችን መከለስ የመሳሰሉ የስራ ክፍፍሎች ተሰጡ፡፡ 
ሚያዝያ 17 – ሚያዝያ 17 ማምሻውን በተመሳሳይ ሰአት የዞን9 ጦማርን በያሉበት እየተያዙ እነደሆነ መረጃዎች ተሰሙ፡፡ያንን ተከትሎ  እስሩ እየተከናወነ ያለው በተመሳሳይ ሰአት  በመሆኑ መረጃዎች እነደተሰሙ ለሁሉም ጦማርያን ለማስተላለፍ የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀረ፡፡ በእለቱ 6 ጦማርያን መያዝ ሲረጋገጥ እስሩ እየተከናወነ እያለ ከመታሰሩ ቀድሞ መረጃ ማድረስ የተቻለው ለጦማሪ ጆማኔከስ በመሆኑ ማምሻውን በአስቸኳይ ነበረበትን ከተማ ቀየረ፡፡
ሚያዝያ 18 – ጦማሪ ጆማኔክስ ካሳየ በተጣደፈ በጣም አጭር የቡድን ውሳኔ ከአገር በፍጥነት ወጣ፡፡ ( ከአገር የወጣው የመጨረሻው ጦማሪ በመሆን ከመንግሰት የተቀናጀ አፈና የተረፈው ብቸኛው የዞኑ ጦማሪ በመሆን ስደትን ተቀላቀለ) በተጨማሪም የዞን 9 ወዳጅ የነበሩ ጋዜጠኞች በተመሳሳይ ክስ መአከላዊ ምርመራ ለእስር አንደተወሰዱ ተሰማ።
 ሚያዝያ 19 – የህግ አማካሪ እና ቤተሰብ ባልተገኘበት እሁድ ቀን አራዳ ፍርድ ቤት ጦማርያኑ ከእስረኛ ጋዜጠኞች ጋር ቀረቡ በወቅቱም ፓሊስ ራሱን የሰብአዊ መብት ተቋም በሚል ከሚጠራ ድርጅት ጋር በመተባበር ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ በማህበረሰብ ሚዲያ አመጽ የመቀስቀስ ዝግጅት በማድረግ ወንጀል መጠርጠራቸውን መግለጹን ከፍርድ ቤት ፋይሉ መረዳት ተቻለ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ክሱን ተከትሎ ከሰብአዊ መብት ተቋማት ጋር መስራትን ወንጀል ማድረግ አደገኛ እና ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎች ጋር የሚጋጭ መሆኑን በማሳወቅ አስቸኳይ መግለጫ አወጣ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመቶዎች የሚጠጉ የሰብአዊ መብት ተቋማት እስሩን የሚያወግዙ መግለጫዎችን አወጡ፡። በተመሳሳይ ወር ግሎባል ቮይስስ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ እስርን የሚቃወም ዘመቻ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በሺዎች  የሚቆጠሩ በመላው አለም ያሉ የሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተሟጋቾች አጋርነታቸውን አሳዩ፡፡ በማህበረሰብ ሚዲያዎችም አበረታች የአጋርነት ድጋፎች  ታዩ፡፡
ሚያዝያ 23 እና 24 – ጦማሪ ጆማኔክስ ካሳየ መኖሪያ እና የስራ ቦታ ከፍተኛ ወከባ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ለተለያዪ ሰዎች ቀረቡ፡፡ መንግሰት ደህንነት ሰዎች ባደረጉት በዚህ ከበባ የጦማሪውን አገር ውስጥ አለመኖር ተረዱ፡፡
ሚያዝያ 29 እና 30 – የዞን9 ጦማርን እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተሰብ አና በጓደኞቻቸው መታየት ቻሉ፡፡ ሁለት ጦማርያንም ድበደባ እና ኢሰብዓዊ  የሆነ እንግልት እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ በተመሳሳይ ወር በሁሉም እስረኞች ላይ ከድብደባ ከኢሰብአዊ አያያዝ  የአንቅልፍና የምግብ መክከል አንዲሁም ሌሎች ለአደባባይ የማይገለጹ መንገላታቶች ደረሱባቸው፡፡
 ግንቦት 2006 – በዚህ ወር በአራት የተለያዩ ቀናት በተለያዪ ቡድኖች ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡት ጦማርያን እና ጋዜጠኞቹ ክስ ከሰብአዊ መብት ተቋማት ጋር በመስራት አመጽ ማነሳሳት ከሚለው ወደ ሽብተኛነት ጥርጣሬ ተቀየረ፡፡ አዲስ ወንጀል ለመቀየሩ ማእከላዊ ምርመራ ያሳየው ምንም አይነት ማስረጃ ባይኖርም የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮን እንደፈለገ ማግኘት ቻለ፡፡ በዚሁ ወር በነበረው የመጀመሪያ ቀጠሮ ባለፈው አቤቱታ ካቀረቡት በተጨማሪ ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ በሌሊት እየተጠራ ምርመራ እንደሚደረግበት እና ድብደባ አንደተፈጸመበት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቀረበ፡፡
በዚሁ ወር ጦማርኑ ከታሰሩ ከአራት ሳምንት በሁዋላ “የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪ” በሆነችው በጦማሪ ሶልያና ሽመልስ ቤት በሌለችበት  በሁለት ዙር የተከፈለ ብርበራ ተካሄደ፡፡ በመጀመያው ዙር ምርመራውን ጨርሶ የሄደው ፓ

ይድረስ ለወዳጄ

ከ6ተኛ ተከሳሽ

ዘላለም ክብረት
የኔ ፅጌረዳ  ሰላም ላንቺ ይሁን! እንዴት ነሽልኝ? ባለፈው የፃፍኩልሽን ቧልታይ የበዛበት ደብዳቤ አነበብሽው ይሆን? ዛሬ ደግሞ ስለክሴ፣ ስለከሳሼና ስለአጠቃላይ ሁኔታዎች ልጽፍልሽ አሰብኩ፡፡ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ትንሽ ኮስተር ሳልል አልቀርምና ከወዲሁ ይቅርታን እለምናለሁ፡፡

ግርምቴ
ከታሰርኩበት ሚያዝያ 17/2006 ጀምሮ በጣም ሲገርመኝ የነበረው ነገር የፖሊስ/የመንግስትና የሕግ ታላቅ እኩያ ከተያዝኩበት ደቂቃ ጀምሮ አውቆ በሚመስል መልኩ የተለያዩ የፍትሕ አካላት እያንዳንዱን የሕግ አንቀፆች በተግባር ሊጥሷቸው ማየቴ ነበር፡፡
 ለሕጎቹና ለሕግ አካላቱ ቅርብ በመሆኔ ምክንያት የመንግስት አካላቱ ይወስዷቸው የነበሩትን የተለያዩ ርምጃዎች በሕጉ አይን በማየቴ ሊሆን ይችላል የሕግ ጥሰቱ እጅግ ጎልቶ የታየኝ፡፡

የፍተሻ ፈቃድ (Search Warrant) ከእስር ማዘዣ (Arrest Warrant) ጋር በአንድ ወረቀት ላይ ተደባልቆ በመምጣቱ ገና ከመታሰሬ ነው የሕጉ ነገር ያሳሰበኝ የጀመረው፡፡ ሕግ ስንማር የፍተሻ ፈቃድ ከእስር ማዘዣ ተለይቶ እንደሚመጣ፣ በፍተሻ ፈቃዱ ላይ ሊፈተሽ የተፈለገው ነገር በግልፅ ሊቀመጥ እንደሚገባ፣ ፍተሻ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መከናወን እንዳለበት …ብንማርም ‹ፖሊስ› በታሰርኩበት ወቅት አንዱንም የሕግ አንቀፅ ላለማክበር ያሰበ በሚመስል መልኩ የፍተሻ ፈቃድን ከእስር ፈቃድ ሳይለይ፣ ፍተሻውን ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ በመጀመር፣ በፍተሻው ምን ማግኘት እንደሚፈልግ የማይገልፅ የፍተሸ ፈቃድ በማሳየትና እኔ ስጠይቅም ለመናገር ፍቃደኛ ባለመሆን… ሕጉን‹ንዶ ንዶ› የኔን የግለሰቡን መብቶች በዜሮ በማባዛት ‹ወንጀልን የመከላከል እርምጃውን› ጀመረ፡፡ በፍተሻ ወቅት የሚፈለገው ነገር ምንነት አለመገለፁም ፖሊስ ‹ለጠረጠረኝ› ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል፣ በዛቻና በአድማ የመናድ ወንጀል እንደ ኤግዚቢት የያዛቸው ‹ማስረጃዎች› ምንነት ይገልጣቸዋል፡፡
በፍተሻ ወቅት ፖሊስ ከቤቴ በኤግዚቢትነት ከያዛቸው ‹እቃዎች› መካከል 90 በመቶው ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍት ሲሆኑ ከነዚሀም መካከል የPaulo Coelho “By the river paedra I set down and wept’ PV.I.Lenin ‘what is to be done’ የአፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል፣ የፍቅረስላሴ ወግደረስ ‹እኛና አብዮቱ›… ጨምሮ ሌሎች መፅሀፍት የሚገኝበት ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሲዲዎችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

(የሚገርመው ፍተሻው ሕገወጥ መሆኑን ‹ለፖሊስ› በተደጋጋሚ ብናገርም ‹ብርበራ ከጀመርን በኋላ ልናቋርጥ አንችልም›፣ የሚያስፈልገንን ነገር አንተ ልትነግረን አትችልም… የሚሉ መልሶች በመስጠት ‹አዲዮስ ሕግ› የሚል አሰራር ከመከተላቸውም በላይ በቤቴ የተገኘ እንደ ‹አዲስ ራእይ› አይነት መፅሄቶችን የብርበራው መሪ የሆኑ ግለሰብ ለበታች መርማሪዎች ‹ተዉት እሱ የኛ ነው› የሚል አመራር እየሰጡ ግርምቴን አብዝተውት ነበር፡፡ ጉዳዩን አስቂኝ የሚያደርገው ደግሞ በፍተሸው ወቅት ቤቴ ውስጥ ከተያዙት ‹ኤግዚቢቶች› መካከል አንዱም እንኳን ለክስ ማስረጃ ሁነው አለመቅረባቸው ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ለህግ ት/ቤት ‹search is not a fishing expedition in which the police grabs every thing › ተብለን የተማርነው፡፡)

የእስርና የምርመራ ጊዜ ደግሞ ፖሊስ ሕጉን ለመጣስ ሆን ብሎ የተጋ በሚያስመስለው መልኩ ሕጉ ግድ ሳየሰጠው የፈለገውን ሲያደርግ የከረመበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ነው ‹እኛ የሚያሳስበን የአንተ የአንድ ግለሰብ መብት ሳይሆን፣የሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ ደህንነት ነው› የተባልኩት (ውዴ! Ayn Rand እንኳንም ይሔን ሳትሰማ ሞተች አላልሽም?)፡፡ በዚህ ወቅት ነው ‹የሽብር ሕጉን ጥርስ አውልቃችሁ አምጡ የሚለን ከሆነ ጥርስ ከማውለቅ ወደኋላ አንልም› ብሎ ፖሊስ ሕገ-መንግስቱንና የዜጎች መብትን በአንድ ላይ ሲቀብራቸው የተመለከትኩት፡፡ (‹ሕገ -መንግስቱ የሀገሩ ህጎች በሙሉ የበላይ ሕግ ነው› የሚለው የህገ መንግስቱ አንቀፅ በምድረ በጋ የተደነገገ እንደሆነ ግንዛቤ ለመጨበጥ ችያለሁ)፡፡ በዚህ ወቅት ነው፡ የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲፈፀምልኝ ለጠየኩት ጥያቄ ‹ሂድ ከዚህ!የማነው?! ፍርድ ቤት ማነው እኛን የሚያዘው? ከፈለገች ዳኛዋ ራሷ ትፈፅምልህ…› የሚል መልስ ‹ከህግ አስከባሪ ፖሊስ› የተሰጠኝ፡፡
            ‹‹ምን አይነት ዘመን ነው ፣ የተገላቢጦሽ፤
            አህያ ወደ ቤት፣ ውሻ ወደግጦሽ፡፡
ይሏል እንዲህ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ነው፤ ምንም አይነት ሕጋዊ መብቶቼ ሳይነገሩኝ ‹ለምርመራ የተቀመጥኩበትና ብሎግ ላይ የተፃፉ ፅሁፎች የእኔ ‹የእምነት ክህደት ›ቃል እንደሆኑ ተደርገው መፃፍ እንዳለባቸው ትእዛዝ የተሰዘጠኝና በእምነት ክህደት ቃሌ ውስጥ ወይ ‹ጥፋተኛ ነኝ› ማለት አለያም ባዶውን መተው እንጂ ‹ጥፋተኛ አይደለሁም› የሚል ነገር መስፈር እንደማይችል የተረዳሁትና ‹ለምን?› ብዬ ስጠይቅም ‹ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ› እንደሆነ የተነገረኝ፡፡ (ማሬ፣ ዕድለኛ ባልሆን ኖሮ እንደ ‹አንድ› አባሪዬ ‹ህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ፣ ሕገ-መንግስቱ ይከበር ‹በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ› ብለህ ፈርም ተብዬ መከራዬን አይ ነበር፡፡)በዚህ ወቅት ነው፤ መንግስቴ በመጀመሪያ ‹በሽብር ወንጀል› ባይጠረጥረኝም የፀረ-ሽብር ሕጉ አንቀፅ 14 በሚያዘው መሰረት ስልኬን ከግንቦት 2005 ዓ.ም ጀምሮ በመጥለፍ ንግግሬን ሁሉ ሊያደምጥ እንደነበር የተረዳሁትና ‹‹እንዴ ‹የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም የማሴር ወንጀል› የተጠረጠርኩት ከታሰርኩ ከ23 ቀናት በኋላ ነው፤ ይሄም ፖሊስ እስከታሰርኩበት 23ኛ ቀን ድረስ በሽብር ጉዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ ያልነበረው ሲሆን ታዲያ ስልኬን አንድ አመት ለሚሆን ጊዜ እንዴት የፀረ ሽብር-ሕጉን ጠቅሶ ሊጠልፍ ቻለ?›› ብዬ ለጠየኩት ጥያቄ መልሱ ዝምታ እንደሆነ የተረዳሁት፡፡ (በነገራችን ላይ ስልኬ ለረጅም ጊዜ ቢጠለፍም ለማስረጃነት የቀረበብኝ ከአባሪዎቼ ጋር ‹ሻይ-ቡና እንበል እስኪ ብለን ያወራናቸው ወሬዎች ሲሆኑ፤ካንቺ ጋር ያውራናቸው ወሬዎች በማስረጃነት ባለመምጣታቸው ቅር መሰኘቴን በዚህ አጋጣሚ እገልፃለሁ፡፡)

  ግርምቴ ብዙ ቢሆንም እንዳይሰለችሽ በማሰብ አንድ የመጨረሻ ግርምቴን ልንገርሽና ሌላ ጉዳይ ላይ እናልፋለን፡፡ የእስር፣ የምርመራ፣ የብርበራ … ሁሉ ዓላማ ተጠርጥረው የተጠረጠረበትን ወንጀል የሚያረጋግጥ መረጃ ለማግኘት ቢሆንም ከሁለት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ፣ እጅግ የተራዘመ ምርመራ ተደርጎብኝ የቀረበብኝን ክስ ስመለከት ብዙ ነገሮች አስገረሙኝ፡፡ ቀዳሚው ጉዳይ የተከሰስኩበትን ‹የሽብር ተግባር ለመፈፀም የማሴር ወንጀል› በሚመለከት በምርመራ ወቅት አንድም ጥያቄ ያልቀረበልኝ ሲሆን፤ ይሄም ነገር ታዲያ የምርመራው አላማ ምን ነበር? እንድል አድርጎኛል፡፡ ሌላው ገራሚው ጉዳይ የሀገሪቱ ከፍተኛ የምርመራ ሂደት እንዲህ ቧልትና እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ከሕጉ ጋር በመላተም እንደሚያከናውን መገንዘቤ ነው፡፡ ታዲያ ‹ፖሊስ› ህግን ለመጣስ ካለው ትጋት የበለጠ ምን አስገራሚ ነገር አለ ውዴ?!

 The Fridgegate Scandal እና ሌሎችም …

እኔ አሁን ደግሞ ወደ ክሴ ልውሰድሽ እስኪ ክሴን ባጭሩ ለማስረዳት ያክል (ምንም እንኳን ክሱ ግልፅ ባይሆንም፣ እኔ እንደመሰለኝ)፤ ‹የሽብር ቡድን በማቋቋም (ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለማድረግ የሚልም ‹ይመስላል›)በሀገር ውስጥ የተለያዩ የሽብር ድርጅቶችን (ሰውን ለመግደል የሕብረተሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ ለማጋለጥ፣ እገታ ወይም ጠለፋ ለመፈፀም፣ ንብረት ለማውደም፣ በተፈጥሮ፣ በታሪካዊና በባሕላዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት ለማድረስ፣ የህዝብ አገልግሎቶችን ለአደጋ ለማጋለጥ ወይም በቁጥጥር ስር ለማዋልና ለማበላሸት) በመዘጋጀት፣ በማሴር፣ በማነሳሳትና በመሞከር የሚለው የመጀመሪያውና ዋነኛው ክሴ ሲሆን፤ሁለተኛው ክሴ ደግሞ ያች የፈረደባት ‹ሕገ-መንግስትንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የመናድ ወንጀል ነው፡፡
            ሁለቱም ክሶቼ የቅጣት ጣሪያቸው እስከ ሞት ድረስ መሆኑን መግለፄም አያስከፋሽም ብዬ አስባለሁ፡፡ (ዘጠኝ ሞት መጥቶ ከደጅ ቁሟል ቢለው፣ ስምንቱን ተውና አንዱን ግባ በለው› አለ የሞት ዳኛ፡፡ እንደዳኛው ‹አንዱን ሞት ግባ› ብዬ ከመጋበዜ በፊት ብዙ የማጫውትሽ ጉዳይ አለኝና አስኪ ተከተይኝ ውቤ)

ከሳሼ ‹የሽብር ተግባራትን› ልፈፅም እንደተዘጋሁና እንዳሴርኩ እንዲሁም ‹ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ› እንደሞከርኩ ለማስረዳት ያቀረቡልኝ የማስረጃ ዝርዝርን ስመለከት ግን የአሳሪዎችን ፍላጎት ‹ወዲህ› መሆኑን የተረዳሁት፡፡

በምርመራ ወቅት አንድም ጥያቄ ያልቀረበልኝ ‹የሽብር ድርጊት› ዋና ‹ወንጀሌ› ሁኖ ሲመጣ አሳሪዬ ጋር ያለው ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ የወንጀል እንዳልሆነ ያስረዳኝ ሲሆን፤ በሰነድ ማስረጃነት ከቀረቡብን ብዙ ገራሚና አስቂኝ ‹ማስረጃዎች› መካከል ‹የሽብር ተግባራትን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለመፈፀም እንዳሴርን› ያስረዳል ተብሎ የቀረበው ዋነኛና ብቸኛ ማስረጃም ከጓደኛዬና አባሪዬ አንደኛ ተከሳሽ፣ ሶልያና ሽመልስ (ክሷ In Abesntia) እየታየ ያለችና በአንድ ቀጠሯችን ፖሊስ ከ Interpol ጋር በመሆን ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የገለፁት በጥብቅ የምትፈለግ ‹አሸባሪ› ቤት በሌለችበት ፖሊስ ላደረገው ብርበራ ማቀዝቀዣ  Fridge ዙሪያ ‹አገኘሁት› ያለው ግንቦት ሰባት የተባለ ፓርቲ በታህሳስ 2005 የወጣ የአባላት የውስጥ Newsletterና ቀኑ በሰነዱ ላይ ያልተመለከተ ሌላ የዚሁ ፓርቲ ሰነድ ነው፡፡

ውዴ ለመረጃ አንች ከእኔ ትቀርቢያለሽና ከላይ ስለጠቀስኩት ‹ሰነድ› ጉዳይ ብዙ ሰምተሻል የሚል ግምት አለኝ፡፡ እኔ ያለኝን መረጃ እና የዚህ ሰነድ ስለክስ ሒደቱ ሊኖረው ስለሚችለው አመላካችነት አንዳንድ ወሬዎችን እያመጣን እንተክዝ እስኪ፡፡

መቼም አሜሪካ ግሩም ሀገር ነው፡፡ ብዙ ነገሮች እንደቅሌት (Scandal) እየሆኑ ሲወጡ የምናይበት የቅሌቶች ሁሉ ቅሌት ድሞ የRichard Nixon ነው   ‘The Watergatge scandal’ ይሉታል፤ ኒክሰን በ1972 ለተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መረጃ ለማግኘት በማሰብ በ Washington DC የሚገኘውን የዲሞክራቲክ ፓርቲ ICT ዋና መሥሪያ ቤት Watergate የተባለው ሕንፃ ውስጥ) እንዲበዘበዝ በማስደረጋቸውና ይሄም ድርጊታቸው በፕሬሱ ይፋ በመሆኑ ኒክሰን ከስልጠናቸው ተዋርደው እንዲለቁ ሆነ፡፡

የWatergate ብዝበዛን ተከትሎ ብዙ ሐረጎች ለብዙ ሁነቶች መግለጫ በመሆን ይቀርቡም ጀመር ለምሳሌ ‘The Watergate Burglars’ ‘The Saturday Night Massacre:- ‘United States Vs Nixon’…. (የእያንዳንዷን ዝርዝር Google እያደረግሽ እንደምታይው ተስፋ አለኝ አበባዬ)፡፡ ከዛም በኋላ የተለያዩ ቅሌቶችን ከWatergate ጋር እያያያዙ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ አሁንም ሌላ ምሳሌ  ‘The Monicagate’ የፕሬዚዳንት ክሊንተንን የወሲብ ቅሌት ለመግለጽ)፣( ‘The Nipplegate’ (በ2003 ዓ.ም ጃኒት ጃክሰን በLive የቴሌቪዥን የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ባልታሰበ ሁኔታ ያጋጠማትን የጡት ጫፍ (Nipple) መራቆትና በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ታሪክን የቀየረ ሁነት ለመግለፅ)፤

ይሔን ሁሉ ማለቴ ወዴት ለመሔድ አስቤ እንደሆነ ሳትረጂው አትቀሪም ፍቅር፡፡ ከላይ ወደጠቀስኩልሽ ግንቦት 7 የተባለ ፓርቲ ሰነድ ጓደኛችን ቤት ተገኝ ስለመባሉ ጉዳይ ላስረዳሽ አስቤ ነው፡፡ ተገኘ የተባለው ሰነድ ላይ ጓደኛችን ወክለው ቤቷን ሲያስፈትሹ የነበሩት እናቷ ‹ይህ ሰነድ ፖሊስ ከፋይሉ ጋር ይዞት የመጣው ሰነድ ነው፡፡ እዚህ ቤት የተገኘ አይደለምና እዚህ ቤት ተገኘ ብዬ ልፈርም አልችልም› ማለታቸው በሰነዱ ላይ በግልጽ የተመለከተ ሲሆን፤ ሰነዱ ተገኘ የተባለበት ቦታ ደግሞ የጉዳዩን አስገራሚነት ያንረዋል- ማቀዝቀዣ (Fridge)!  (በነገራችን ላይ ፖሊስ የወንጀል ‹ማስረጃ› ከውጪ ይዞ ቤት ውስጥ በመጣል ‘Eureka’ ‹ማስረጃ› አገኘሁ የሚልበት ልማድ አዲስ አይደለም፤ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጉዳይ የተከሰሱ ብዙ ሰዎች የዚህ ዓይነት ‹ፖሊስ አመጣሽ› ማስረጃዎች ሰለባ መሆናቸውን እያነበብን/እየሰማን ነው የጎለመስነው፡፡ ፖሊስን ወደቤታቸው ፈትሸው ከማስገባት ጀምሮ የተለያዩ ፖሊስን የመጠበቅ አስቂኝ ተግባራትን በቤት ብርበራ ወቅት እንደሚያከናውኑ ስንለውም ኖረናል፡፡ አስቢው እስኪ ውዴ፤ ሕዝብ ፖሊስን ሲጠብቀው የሚኖርበት ሀገር!)

ለማንኛውም ይህ ‹ Fridge ማስረጃ› ‹አገኘሁ› የሚለው የፖሊስ ተግባር ነው… ‘The Fridgegate Scandal’ እንድል ያደረገኝ፡፡ እስርም፣ ክስም፣ ‹ማስረጃም›…. ከአሳሪዬ በኩል መምጣቱ ‹ፍርድም› ከአሳሪዬ በኩል ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ቢከተኝም ተስፋ አልቆርጥም! ወዳጄ ‘The Fridgegate scandalን’ እንደ አንድ የክስ ሒደቱ ማሳያ ማቅረቤ ‘The Fridgegate Burgalrs’ ለፍትሕ ይቀርባሉ ብዬ በማሰብ አይደለም ወይም በባለስልጣኖቻችን መካከል ‘The Renaissance Massacre’ ተከስቶ ስልጣን ይለቃሉ የሚል ቅዠትም የለኝም፤ይልቁንም (በክርክሩ ሒደት የምናየው ቢሆንም) የቀረቡብን የሰነድ ማስረጃዎች አስቂኝነትና ምን እንደሚያስረዱ ካለመታወቃቸው አልፎ እንዲህ የአሳሪዎቻችን የቅሌት ተግባራት ውጤት መሆናቸውን ከ Alexander Hamilton የFederaliot Paper Number 78:

“The Judiciary is ‘beyond comparison the weakest of the three department of power”
ቃል ጋር አንድ ላይ ስመለከተው ‹ማስረጃ› ፈጣሪው› እና ጠንካራው አሳሪያችን ‹ደካማውን› ፍርድ ቤት እንዳይጫነው ብሰጋ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ሁሌም ተስፈኛ ነኝ፡፡ ማሬ በሕግ ቋንቋ (በልሳን) ትንሽ አውርተን ወደ ሌላ ጉዳያችን እንሂድ፡፡ ያን ረጅም የምርመራ ሂደት አልፈንና ሕግ-አስፈፃሚው ሂደቱን እንዲያስጠብቁ በሕግ-አውጭው የወጡትን የስነ-ስርዓትና መሰረታዊ የመብት መጠበቂያ (Procedual and substantive) ሕጎችን አንድ በአንድ እየሰባበረ ለሕግ ተርጓሚው አካል ያቀረባቸውን ‹የወንጀል ድርጊት ማሳያ ማስረጃዎችን› በሕግ ትምህርት ቤት ‘The Fruits of Poisonous free’ የተባሉት ሲሆኑ፤ ተስፋዬም ከሶስቱ የመንግሥት አካላት ደካማ የተባው ሕግ ተርጓሚው አካል የቀረበለት ነገር በትክክል ‹ፍሬ› እንዳልሆነ ይገነዘባል የሚል ሲሆን፤ ያ ካልሆነም ‹ፍሬው› ከተመረዘ ዛፉ ለሕግ ተርጓሚው አካል በግድ ካልገመጥ አይለውም አይባልም፤ ዛፉን ለመመረዝ አካል ፍሬውን ለማስገመጥ አይሰንፉምና፡፡ ፍቅር! ለማንኛውም ተስፋ ጥሩ ነው፡፡

መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝን (MHD) አየኋችሁ

የኔ እመቤት! እውነት እውነት እልሻለሁ እንደ መታሰር ያለ አስተውሎትን የሚያሳድግ ነገር የለም፡፡ ምክንያቴን ከነማስረጃዬ አቀርባለሁ፡፡ ያኔ በዞን ዘጠኝ እያለሁ (ከመታሰሬ በፊት) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን አጠር አድርገን ‘HMD’ በሚል አፅርሆት እንጠራቸው ነበር፡፡ መታሰሬ ግን ዓይኔን አበራልኝና የእስከዛሬው አጠራራችን የፊደል መፋለስ እንዳለበት ለመረዳት ችያለሁ፡፡ እንዴት?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሽብር፣ ስለእስርና ስለመንግስታቸው አቋም በቅርቡ ተጠይቀው የሰጡትን ምላሽ በኢቲቪ ተመለከትኩ፡፡ ‹‹እነዚህ አሸባሪዎች ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት አካላት ናቸው (በነገራችን ላይ በቅርቡ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከደቡብ ሱዳን ጁባ ተይዘው መምጣታቸውን ተከትሎ የሽብር ሰንሰለቱ ከአስመራ-ሞቃዲሾ-ጁባ ተለጥጦ ሶስት ማዕዘን መስራቱን መንግስት እየገለፀ ነው) ጋዜጠኛ ነኝ፣ ብሎገር ነኝ እያሉ የሽብር ዓላማን ማንገብ አይቻልም፡፡ እናንት ጋዜጠኞችም ተጠንቀቁ….›› አይነት ዱላ ቀረሽ ዛቻ ሲያሰሙ ተመልክቼ እንደሰውየው ‹ ኃይለማርያም አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ ማለቴ አልቀረም፡፡ ለዛም ነው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝን (MHD) የሚለውን ስያሜ አፌ ላይ አልጠፋ ያለው፡፡

እንደዱሮው ‹ይሄ በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ አስተያየት መስጠት አልፈልግም› ማለት ቀረና እንደዳኛ ግራና ቀኝ የተቀመጡትን ጋዜጠኞች እየገላመጡ ቢሯቸው ውስጥ ፍርድ ስጡኝ፡፡ ሌላው ሁሉ ይቅር በሕግ ፊት ነፃ ሆኖ የመገመት ሕገመንግስታዊ መብቴን ያክብሩ አላልኩም፡፡ ባይሆን የቀረበብኝን ‹ማስረጃ› ተመልክተው ፍርድዎችን ይስጡም አልልም፡፡ ግን ግን ‹ለባንዲራ ፕሮጀክታችን› (የሕዳሴው ግድብ) ማሰሪያ ይሆን ዘንድ የሁለት ወር ደመወዜን ለቦንድ መግዣ (ምንም እንኳን ለቦንድ ግዢ ጠቅላላ ክፍያ ሳልጨርስ ከስራ በመሰናበቴ ምክንያት ደመወዜ ቢቋረጥም) መስጠቴን እንደውለታ ቆጥረው በቤተ-መንግስት የዘረጉት ‹የፍርድ ችሎት› ላይ ምህረት ቢያደርጉልኝ ምን አለ? ‹ወርቅ ላበደረ ጠጠር፣ እህል ላበደረ አፈር› ይሰጡታልን?
ውቤ! ለማንኛውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተበየነብንን የሽብርተኝነት ካባ በፍርድ ቤት እንደማይፀናብን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

‹የነሲቡ ችሎት›

አፈ ንጉስ ነሲቡ መስቀሉ ከ1874 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 30 ዓመት ለሚሆን ጊዜ በዳኝነት የተለያዩ የኢትዮጵያን ነገስታት ያገለገሉ ሲሆን ፍርዳቸው እጅግ ከባድና ጠንካራ ስለነበር በዘመኑ ‹እባክህ ከነሲቡ ፊት አታቁመኝ› እየተባለ ይለመን እንደነበር መርስኤ ሀዘን ወልደቂርቆስ በዓይን ያዩትን፤ በጆሮ የሰሙትን፤ ከትበው ይነግሩናል፡፡ በተመሳሳይ ጉዳይ በንጉሱ ዘመን አርሲ፣ አሰላ ላይ እጅግ ጨካኝ ደኛ ተሹመው ፍርዳቸው ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ‹አቤት አቤት፤ የአሰላው ፍርድ ቤት› እስከመባል ደርሶ እንደነበር አሁንም ማስረጃችን ታሪክ ነው፡፡

ውዴ! ይሔን የምፅፍልሽ የእኛው ዘመንን ‹የነሲቡ ችሎት› አስመለክቶ ትንሽ ነገር ብዬሽ ደብዳቤዬን ልቋጭልሽ በማሰብ ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 652/2001 (የፀረ-ሽብር አዋጅ) ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሽብር ጉዳዮች ላይ ስልጣን (Juridiction) ያለው የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሆነ በመደንገጉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት የተለያዩ በፀረ-ሽብር ሕጉ የተከሰሱ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ጉዳይ እያየ የቆየ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ‹የፀረ-ሽብር ሕጉ ሰለባዎች› እየተበራከቱ በመሔዳቸው ምክንያት 4ተኛውን ወንጀል ችሎ ለማገዝ በማሰብ 19ኛ ወንጀል ችሎ የሽብር ጉዳዮችን በማዬት ላይ ይገኛል፡፡

በፀረ ሽብር ሕጉ ተከሰውኖ 4ተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነፃ የወጡ (Acquit) ሰዎች ብዛት ለጊዜው ለማወቅ ባልችልም እጅግ በጣም ትንሽ እንደሆኑ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህ የሆነው ችሎቱ ከሌሎች ችሎቶች የተለየ በመሆኑ እንዳልሆነም አስባለሁ፡፡ ይልቁንም ችሎቱ የሚይዛቸው ጉዳዮች በፀረ-ሽብር ሕጉ አግባብ ለማየት ስለሚገደድ ነው፡፡ መቼም የፀረ-ሽብር ሕጉን አሳፋሪነትና ጅምላ ጨራሽነት ላንች እንዳዲስ በመንገር ጊዜሽን አላባክንብሽም፡፡ ለዛም ነው በዚህ ዘመን ‹እባክህ ከ4ተኛ ወንጀል ችሎት ፊት አታቁመኝ› ወይም ‹አቤት አቤት፣ 4ተኛው ወንጀል ችሎት› ብንል ብዙም የማያስገርመው፡፡ የፀረ-ሽብር ሕጉ ከሚሰጠው ሰፊና ጠቅላይ የሆነ የወንጀል ትርጉም አንፃር ከልብ ወለዳዊው ‘Moratorium on the Brain’ አዋጅ ጋር በተነፃፃሪ መቆም የሚችል ከመሆኑም በላይ በሽብር ጉዳይ የተሰየወን ችሎትም እጅግ አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡

እንግዲህ የእኛም ጉዳይ የ4ተኛ ወንጀል ችሎት እህት ከሆነው 19ነኛ ወንጀል ችሎት እየታዬ የሚገኝ ሲሆን የፀረ-ሽብር ሕጉም ‹ሰለባ› ፍለጋ በችሎታችን ተገኝቷል፡፡ እንግዲህ አበባዬ ጉዳያችን በፀረ-ሽብር ሕጉ ከመታየቱ ጋር ተያይዞ ስራ አስፈፃሚው አካል ‹ማስረጃ› ፈጥሮ የከሰስን መሆኑ ነው ችሎቱን ‹የነሲቡ ችሎት› ያደረገው፡፡ ለማንኛውም ግን ይሄን ስታነቢ ታዲያ ‹ከአንበሳ መንጋጋ፣ ማን ያወጣል ስጋ› ብለሽ ተስፋ እንደማትቆርጪ አምናለሁ፡፡ እኔና አንች እኮ ተሸንፈን አናውቅም ውዴ፡፡ ሁሌም ማሸነፍ፣ ሁሌም ሌላ ተስፋ ማድረግ፣ ሁሌም ደስተኛ መሆን፣ ሁሌም መዋደድ የሕይወት ግባችን አይደለምን ? ታዲያ ይችን ክስ በድል እንዳንወጣት ማን ያግደናል? ምን አልባት አሳሪያችን፡፡ Hamilton በድጋሚ ጠቅሼልሽ ተስፋችንን አለምልመን እንለያይ፡

‘The Judiciary (…) has no influence over either the sword or the purse (…) It may truly be said to have neither force nor will, but merely judgement’

Amen!

                                                                                                                        ያንችው ዘላለም
                                                                                                                        ከብዙ ፍቅር ጋር!

ዘላለም ክብረት 

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት
እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን?  የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ? ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው)  ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ
አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››
(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

 ‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡

 ነገሩ ብዙም አልገረመኝም፡፡ ትንሽ ያበሳጨኝ አቶ ዘላለም ለጥያቄ ስለምንፈልጎት አዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ  ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡

1.    ተማሪዎቼን እንዳላበላሻቸው በማሰብ በቁጥጥር ስር ስላዋለኝ አመሰግናለሁ
ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ
‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››
            እኔ፡ አዎ
            ደህንነቱ  “ስንት ጠበቆች ዳኞች ማፍራት ሲጠበቅብህ አንተ ‹ልማቱን ካላደናቀፍኩ› ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ                  ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን                  በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.   አላማችሁ ምንድን ነው?
እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው? በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣
           መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?
           እኔ፡ ዓላማችን ግልፅ ነው፡፡ ማንም ብሎጋችንን የተመለከተ ሰው በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡ባጭሩ የተለያዩ ተረኮችን የሚያስተናግድ እና ሕብረተሰባዊ ተዋጾን የሚያሳድግ ፕሮፋይል ነው፡፡
           መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?
           እኔ፡ ከዚህ የተለየ አላማ የለንም!

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”
ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.   ከመርማሪዎች ጋር የነበረኝ ቆይታ
የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡
         መርማሪ ፖሊስከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?
         እኔ፡ ማንንም
         መርማሪ ፖሊስእኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡
         እኔእስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ         የማስታውሰው የለም፡፡
        መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም? አሜሪካ በ አፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው፡፡ ወጣት አመራሮች ምናምን             እያለች የምታሰለጥነው?
        እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት           ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም               መቼም?!››
        መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

            (‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.   ‹አሸባሪው› ገብረሕይወት ባይከዳኝና ሀገሪቱን በሀራጅ የመሸጥ ጉዳይ
ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡
መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡

 ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች›  “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው”  በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ  “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡
ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.   ናፍቆቴ ሆይ!
እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡

  •  በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን  (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡
  •  በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?
  • አንድ ቀኑንና ወሩን በማላስታውሰው ቀን አንድ ጎልማሳ የታሰርንበትን ክፍል አስከፍተው ገቡና እያንዳንዳችን መጠየቅ ጀመሩ፡

–   ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)
–   ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›
****
–   ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›
–   ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›
*****
–   ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)
–   ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹ሕዝቡን እርስ በ&

#Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

የልደታ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት የዞን9 ጦማርያኑን እና የጋዜጠኞቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ 

ስድስቱን የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ማኅሌት ታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና አጥናፍ ብርሃነ እንዲሁም በሌለችበት ክሷ እየታየ ያለው በሶልያና ሽመልስ እንዲሁም በጋዜጠኞቹ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው /ጊዮርጊስ በልደታ 19ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት የተሰየመ ሲሆን ከሙስሊም ኮሚቴ አመራሮች ጋር በአንድ ችሎት እንዲታደሙ በመደረጉ የታሳሪዎችን ቤተሰቦችም ሆነ ወዳጆችን ለማስተናገድ ቦታ የለም በሚል ለጋዜጠኞች ብቻ የፍርድ ሂደቱ እንዲታይ በፖሊስ ተፈቅዶ ነበር፡፡

በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ መጥሪያ በጋዜጣ መውጣቱን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የዋስትና መብትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት በአንቀጽ 3 የሽብር ተግባራት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድም ወይም ሁለትም ከዚያም በላይ ወንጀል የፈጸመ መሆኑ ወይም ለመፈጸም ያቀደ ለመሆኑ ተገልጾ ክስ ሲቀርብ ነው በተመሰረተባቸው ክስ ዋስትናን ሊያሳጣቸው የሚችለው ብለው ጠበቆቻቸው የተከራከሩ ሲሆን ደንበኞቻቸው በአዋጁ መሰረት የሰሩት የሽብር ተግባር ክስ አልቀረበባቸውም ስለዚህ በአዋጁ ተጠቀሰ ማለት በአዋጁ መሰረት ክስ ቀርቧል ማለት ስለማይቻል የዋስትናው ጥያቄ በመደበኛ ስርዓት እንጂ በጸረሽብር ሕጉ መሰረት ሊታይ አይገባም፤ በተጨማሪም አዋጁ ዋስትና ይከለክላል ተብሎ ቢተረጎምም ከሕገመንግስቱ ጋር ስለሚጋጭ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ አንቀጽ ተጠቅሶ መከሰሳቸውን እንጂ በዚህ መከሰስ ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም ብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ አይገደድም እንዲሁም የጸረሽብር አዋጁ ከሕገመንግስቱ ጋር አይጋጭም ብለዋል በዚሁም መሰረት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ተደርጎ ለጥቅምት 5 ቀን2007. ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ችሎት የተጠናቀቀ ሲሆን ጠበቆቻቸውም የዋስትና ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍረድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

ችሎት ውስጥ መግባት የቻሉት ጥቂት ጋዜጠኞች እና ጉዳዩን ለመታዘብ የተገኙ ዲፕሎማቶች ብቻ ናቸው፡፡

በቦታው በመገኘት አጋርነታችሁን ላሳያችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡


Is bad excuse better than none? Not exactly 
 By Befeqadu Hailu


  
“So what do you think is your offense?” my interrogator signed off with this intriguing question    after he made me recount my works as an activist and progressive blogger. Soon after, when my captors permitted me to be reunited with my blogger friends, who are now described as ‘associates’ in the lexicon of inmates we have realized that we were all asked this same question “So what do you think is your offense?” This question is intriguing because it has a comprehensive and totalizing power to describe the entire interrogation process. It is intriguing because it sheds light into our innocence or our into our refusal to acknowledge what our captors suspected us of violating. Yes, our captors probed us severely but they all ended with the same question   “So what do you think is your offense?”  The whole point of the investigation was not to proof or to disproof our offenses but it was to make us plead guilty. With that, our brief two years of operation as Zone9ers which was a perplexity for a lot of people has got answers. Observers perplexed why Ethiopian government tolerated Zone9ers for so long. Given the sensitive nature of Ethiopia’s government to freedom of expression the annoying perplexity of these people is understandable. As the curiosity of these perplexed people come to end; we got apprehended, investigated and blame is being laid up on us for committing acts of ‘crime’ by being a ‘member’ and ‘accepting missions’ of Ginbot7/May 15 and OLF as well.  Next in a row is ‘due processes’ in the prosecution, but I believe there are issues that necessitate this piece.How did our incarceration & investigation go?  Are we really a member of Ginbot7/May15?  If not why have they arrested us?  Will they release us soon?
No matter what, the bounds exist among people if they write about Ethiopia’s s political reality they will have to survive with a peril of incarceration as long as they live in the country. I believe that is why Prof. Mesfin poignantly described Ethiopians as those who have gone through imprisonment, those who are now in prison and those who await imprisonment.  In his book, Prof. Mesfincited these three layers of Ethiopian captives to his unidentified conversant, credit to him, but we believe everyone who has to survive with a dread to exercise their freedom of expression live in outer ring of the prison, the Nation Itself, that is why we call our blog Zone9.  Merely we were two weeks into our nascent blogging when they made our collective blog inaccessible in Ethiopia in 2012. We gave it a trial until the end but we knew that the fate of our blocked blogs could be our own. We know that we could end up being arrested. In the days and weeks leading up to our incarceration in April 2014, government security agents have been threatening us about our imminent arrest but it is only human to get shaken when it happened. The arrest besieged six obtainable members of the blogging collective and our three journalist allies. Here; I would like to point out that the incarceration of our three journalist allies was a bit of shock at least for us; but later it became noticeable that we were only used as a pretext and their arrest is part of a grand arrangement. The highly coordinated manner of our seizures on its own speaks volumes about government’s pre-calculated grand arrangement. With the exception of one of the journalist (Asmamaw) we were all arrested on Friday the 25th of April on or about 11:00 pm; from our respective locations.  Asmamaw was arrested the next morning. By the time we were seized and taken to the detention center the search ‘warrant’ that authorized the law enforcement personnel was well over its time limit at least according to Ethiopian law. In fact, the unlawful intrusion of our rights starts right here. Without delay, we become victims of various unlawful courses of actions.  
The very idea of setting a foot in the compound of the ill-famed Maekalawi detention center gives a cold shiver to anyone. But my sheer optimistic trust that the brutal and inhuman treatment of people as Ethiopia’s distant memory saved me from trembling while I was escorted into the compound.  So were my friends, I suppose. What is more; we had nothing to be scared of because; we are neither undercover agents nor members of armed forces; we are just writers. However, as soon as I arrived at Maekelawi detainees informed me that I am in one of the notorious section of the detention centre called ‘Siberia’. In just less than a week I felt I was living right in the middle of the account of Human Rights Watch report of the 2013 titled- They Want a Confession 

The Standard Maekalawi Interrogation
The standard Maekalawi interrogation methods are more of dominance and submission, rather than confidence and creativity. Instead of extracting information from ‘suspects’ the police officers usually fool around; they spend too much time in I know it all kind of game. If this does not succeed in extracting information, they force confessions by punching, beatings, extended physical exercise and flogging. I concluded that this is the standard interrogation routine in Maekalawi since I have endured it with five different police officers. Other detainees have informed me that they have gone through the same procedure. In fact I had an opportunity to converse with detainees who have passed through even wicked procedures that intrude detainees’ privacies. Some detainees got stripped off their clothes and asked to perform stand up-sit dawn. Particularly, I was able to meet with people who suffered from medieval type of torture in an anonymous detention centre before they were brought to their pre-trial detention centre at Maekalawi. These detainees suffer from diabolical barbarity such as forcible extraction of their nails from their fingers, flogging and hooding; among these are students from Haromaya University. What is nauseating is the extracted information from detainees in anonymous detention centre is usually brought to their pre-trial detention center for the purpose of verification. Detainees never know where they were taken for this brutal investigation; because they are hooded. The anonymous detention centers are like black holes. Ethiopian prisoners’ anguish which appeared to be so distant in memory is not that far after all.
Finally, we were made to plead guilty, we confessed under duress. We could not bear with the ceaseless brutal and psychologically degrading pressure. We could not carry on surviving the hellhole of Maekalawi. We end up recounting what our detectives would like better to listen. To the delight of our detectives we have added as many self-incriminating phrases as possible. But phrases such as ‘yes we wanted to incite violence’ never pleased them. Subsequently they have re-written our confessions so that it will fit their frame. Some of us tried to explain; others we had to endure beatings but at last we all succumbed to the pressure and signed the carefully scripted confession pages with the exception of Abel, he refused to sign the rewritten confession pages. He has survived the pain but even his confession pages are complete mendacities let alone ours.

Now we are a living witnesses that torture is part of Maekelawi’s ceremony that reveals the ‘truth’ of a crime. I thought police interrogations were so complex involving high end skills, knowledge   and psychological tactics to establish facts. Thanks to our time at Maeklawi I have realized that police interrogations in Maeklawi are not that complex. In fact they are simple. They are like machines that produce guilt in the detainees. In Maeklawi, the driving principle of police interrogations is ‘you are guilty unless proven otherwise’. Your pleas for innocence or explanation for that matter fell on deaf ears; detectives will cook a crime for you; I call this Maeklawi-sque interrogations.
My experience, especially our own case; convinced me stronger than ever that Maeklawi should go through a complete reform. One can simply observe that there is a significant economy of power invested in Maeklawi. The investigation is not principled; detectives ingratiate the power wielders. I think they are recruited based on their willingness to carry out the desires of the power wielders, not to uphold the rule of law. I think the staffing of employees should be merit based.  These kinds of law enforcement employees should be knowledgeable if they are not they might overlook insightful information when they deal with real criminals and this might jeopardized the safety & security of the country.

An Apple & Orange

The evident part of each of our confession pages which forced us plead guilty were our online campaigns , our plans, the articles we wrote, the trainings we partake, the training manuals, the skills we attempted to impart. I had to admit that we all expected that their plan was to indict us with agitating the public to strife. We thought the ceiling for our ‘crime’ is accusing us of violating article 257/8 criminal code of the Federal Democratic Republic of Ethiopia. But eureka, when they formally charge us we have realized that we are charged with Ethiopian terrorism law, particularly with violation of its Article 4 which can result in severe punishment of 15 years to life imprisonment. Honestly, speaking this makes my face beam with smile. 


The terrorism charge is smirking because the evidences brought to support the charge are merely our writings, the press releases we wrote during our online campaigns and different training manuals. Other than these documents, there are three ‘documents’ which purportedly proof our connections with Ginbot 7 and OLF. The first one is Ginbot7’s newsletter from September 2009. This newsletter was located in Natnael’s email. Here, it is important to note that Ethiopia’s anti-terror proclamation was not passed into law and Ginbot7 was not yet labeled as a terrorist organization when Natty received the newsletter. The second document was, the one located in the house of Soliyana’s mom during the search and seizures.  The alleged document is the guiding document to draft members of Ginbot7 popular force. Apparently, Soli’s mom refused to acknowledge this document insisting it was inserted by the security agents themselves in their house rather than located. In any way this should not be a big deal especially considering Soli’s stance on armed struggle. We all know that Soli does not support regime change by means of armed struggle. Before my detention last time I check her Twitter bio has an adage “no for war”   The third document is the political program of OLF which was located in the personal computer of Mahlet. In fact, Mahlet has had many political programs of other Oromo political parties but they were not presented as evidence. I don’t want to engage in ping pong kind of argument that yields nonentity. Apparently, for our loved ones if not our leaders it is clear that possessing these documents does confirm neither allegiance nor working relationship with both Ginbot7 & OLF. Our activities and the charges we received are like an apple & orange.  

The preposterous of all allegations is the one which blames us of receiving $2400 money using Natnael as our contact person. This money was a remittance transferred from Article 19 to encourage Reyoot, an imprisoned journalist and of course support her family. During our interrogation we have explained this fact in great detail to the police officers. Adjacent to our claim attached was the receipt to proof the transfer was made by Article 19. But in the charge sheet they tried to get us perceived wrongly and they have attempted to show that we have received the money from the ‘terrorist’ organizations. I imagine they know our innocence; but I think either they maliciously want us suffer or they want to take their time until we prove our innocence.

  

Is bad excuse better than none? Not exactly
Some conundrums are simply explained in old adages like bad excuse is better than none but I think our story can be best explained in an Ethiopian folk story of a hyena and a donkey. The story goes like this. Once upon a time a donkey and a hyena were drinking from the same stream of water. The belligerent hyena whined to the donkey that she is making his water filthy despite he is drinking up in the stream; but the donkey told to the hyena to stop looking for a reason to prey on her. People say a bad excuse is better than none but not in our case! Our story is much more analogous to the story of the hyena and the donkey than to the old adage.
They arrested us without knowing anything other than our names. We genuinely believed that if they know what we have been doing they might understand us. With that sprit we have even passed some of our writings to them through one of their undercover agent who has been following us before our detention but I don’t think they have read the anthology of our writings. Indeed our detectives were craving to plead us guilty in a very desperate manner. But why would they do that? They might want us to stay away from Ethiopian social media sphere until the upcoming Ethiopian national election in May 2015.  Hitherto, we have the first hand experience of favoritism and partiality towards the ruling party. What is left is to try out to defend ourselves using the judicial system. For now let me ponder about our future; will they ‘release’ us? I will not dwell on the legal possibilities of our‘acquitance’ but I will only look into our hypothetical chances. Even though the Ethiopian Federal Police which is an apparatus of the government arrested us without having probable cause; they still thought they would find some sort of transgression. As a matter of fact they could not find anything that would get us accused even in the wildest interpretation of the already broad anti-terrorism proclamation. However; this has not prevented them from using it. The verbosity and trivialities of the charges on its own is an apparent suggestion for the sham nature of their accusations. But I do not think we will get ‘exonerated’ any time soon. Why because;
  
1.      EPRDF is bullheaded. They are stubborn in annoying way. If they think the detainees have generated a lot of support and are critical of their governance. They don’t want to release their captives without dehumanizing them. EPRDF is foolishly childish. Note; I am not saying the global support we received is not helping us. Your support is our daily bread. It is warming us like sunshine. I am sure the day shall come on which we say thank you for your support.
2.      They don’t want take a risk. Even though they have seen our innocence regarding their fear of inciting violence after the upcoming election; they did not want to take a risk. In weeks leading up to our arrest they have been accusing us of planning color revolution following the national election using their media.
3.      They want us suffer. They want us spend our time jail because we are strong critics of their policies.
4.      They do not have any sense of decency that prevent them to hand dawn judgment on innocent people

 

#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsmamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

“Dear Hyena no need for excuses, just eat me” – Ethiopian Proverb 
By BefeQadu Hailu

“So what do you think is your crime?” I was asked by one of my interrogators while I was telling him about what I did as a blogger, an advocate and an activist. Later on, after I was allowed to meet with my “collaborators” according to my prisoners and asked each other, we found out we were all asked this same question “what do you think is your crime”? This describes the overall outcome of our interrogation. Since they couldn’t figure out what our supposed crime was or what law we were suspected of violating, we were asked “So what do you think is your crime?”. The interrogation was not to ultimately find out whether we are innocent or not but to find anything that could be a crime. Some have asked why the Government has tolerated Zone 9 for 2 years, because tolerance isn’t in its nature. Ethiopia’s Freedom of expression, as I have imagined, has easily gotten us arrested, interrogated, alleged with being a member of Ginbot 7 (OLF as well) and is prosecuting us. The rest will be left for the court to deal with in time.
Many people who have known Zone 9 in the past could be confused and would demand an explanation to figure out why we’re being prosecuted. This is what has forced me to respond in this short piece. How did we get here? What is our imprisonment like? How was the interrogation? Are we really members of Ginbot 7? If not then why were we arrested? Will we be released soon?
Whether a scholar or a layman, anyone who writes about Ethiopian politics will always have a fear of being imprisoned. That is why, I think, Professor Mesfin wrote on one of his books that the people of Ethiopia are of three categories, the imprisoned, the imprisoned and released, and the one that is waiting to be imprisoned. In fact everyone that has refrained from expressing ones views in fear of persecution is technically imprisoned and can easily put all the categories into one, the imprisoned. Two weeks after we officially started blogging as Zone9ers, we had to set up a second blog after our first one was blocked in Ethiopia. We knew one day that it will be us who will be locked up behind bars. We were under surveillance, have been receiving threats and signals that indirectly revealed what is to come. Though our arrest caught us by surprise, it was not unexpected.   
Following the surveillance, the arrest targeted six members of Zone9 and three journalist who are our close friends. The arrest of the three journalists has been a complete surprise at least to us. Later we were able to understand their arrest in relation to their friendship and closeness to us was well orchestrated as a sweep up operation. All of us except Asmamaw were arrested on Friday April 25th at 5:00pm from different locations at the same time. Asmamaw was arrested the next day on Saturday. They were also conducting the search warrant in our houses after it expired at 6:00pm.The brutal and unjust treatment started immediately after our arrest.

The picture shows the six bloggers and three journalists

For anyone who knows about the notorious Maekelawi, finding oneself in its compound sends shocks to the heart. In the contrary I was a bit optimistic and knew my friends have felt the same the minute they stepped in because one we are bloggers not soldiers or spies and two I had a foolish impression that there is better human treatment than the bygone era of the past.  On the first day an inmate conveyed to me that I am in the worst part of Maeklawi called Siberia. Later it took me less than a week to admit what was written in the report “They want a Confession”  by HRW was all true.
Interrogation Maekelawi Style
Interrogation in Maekelawi is more brutal than technical. The interrogators spend more time trying to show their skill than actually interrogating and attempting to find out more. If that doesn’t work they will slap, kick and make the prisoner perform tough physical exercise. These are among the few things that I went through in the hands of the five interrogators and also what I heard from other inmates. Some are made to stand naked and do sit ups. Other inmates told me that they have gone through even more brutal punishments like hanging upside down and removing nails but that was before they were moved to Maekelawi. Among them were students from Haromaya University  Intriguingly the confession the prisoners give after such punishment was brought to Maekelawi as an evidence to their alleged crime. Similarly these prisoners had their eyes covered so that they would not know where they were. This reminds me of DERGs Bermuda – another notorious place of interrogation. 
Hence we gave our confession after being humiliated, insulted and brutally treated under the roof of the horrific Maekelawi. Our confession was 100% untrue. When the brutal force used against us became unbearable we admitted to crimes of “Conspiring to instigate violence”. While taking notes they were making sure every word we spitted out was twisted as “self-incriminating” to help with our prosecution. We argued to the best of our physical and mental abilities and when it became impossible we signed the documents, they beat us to sign these documents. The only person who managed to withstand the beating was Abel, who refused to sign by saying “I will not sign anything other than my own confession”.
The important thing that we understood was that Maekelawi’s interrogators are experienced in brutality than fundamental intelligence. I always had an impression that the police will acquire all the relevant evidence and then interrogate the prisoner how and why they carried out the crime. Thanks to Maekelawi now I understand that interrogation starts with “What is the crime you committed? Tell us!” Maekelawi style. “I am innocent” will always fall on deaf ears. Once you are arrested, you must admit to a crime or else they will bake one for you.
When I think about it now, Maekelawi investigation center needs a fundamental restructuring due to two important reasons.
1.     The interrogation technique (as I have understood from our case) is more about carrying out an order, meaning it is not strategized or determined on case by case basis.  
2.     The interrogation is not knowledge or intelligence based. And this will endanger the security of the country as such approach will certainly fail to gather, capture or control real threat. This problem occurs because police investigators are recruited more based on loyalty and a willingness to take orders than carrying out skillful investigation.  
The Goat is here but the herder rod is there, afar
In the interrogation process what we were forced to sign was an admittance to inciting violence through the articles we have written, the campaigns we conducts, the trainings we took or the trainings some of us gave hence our expectation was to be charged with crime under the criminal code 238 and 257.  Unfortunately we were charged with Terrorism, a crime that could get us 15 year to life sentence. This actually made me laugh. 
The evidence that were brought against us were the articles we wrote, the campaigns we conducted, the press releases and training manuals. In addition to these were documents of Ginbot 7 and OLF which they claimed they found under our possession. First evidence was Ginbot 7’s newsletter that was sent to Natnail Feleke in September 2009 that is way before the Anti-Terrorism Proclamation was set in motion and way before Ginbot 7 was convicted as a Terrorist organization. The second was a Ginbot 7 recruitment document claimed to be found in Soliyana’s home in which her mother refused to sign accepting the document was found in the house. What I remember, before my arrest was Soliyana’s twitter bio read “No for war”. The third evidence was OLF’s program that was found on Mahlet’s computer. Apparently there were other Oromo Party programs found as well but were not presented as evidence. Neither was she asked why OLF’s or other Oromo party programs were found in her computer while she’s being prosecuted for possessing only one? Needless to say, having these documents does not and does not mean working with them or agreeing with what they do. This wasn’t clear to our interrogators but I am sure our compatriots and friends will definitely understand.
The other laughable charge was that states “they have accepted and distributed among themselves 48 thousand Birr(Eth) that was sent through Natnail Feleke”. Though the charge is written so as to create an impression that the money was sent from the so called “Terrorist Organizations, the bank receipt shows that the money was sent from Article 19. We explained to the interrogators that the money was sent to an imprisoned journalist and her family. They still made it part of the charge not because they believed we are criminals but rather due to their evil intention of getting us punished or use it to buy time during the series of court appearances.
Stop looking for excuses!
A donkey and a hyena were drinking at the river. The donkey was drinking downstream and the hyena was drinking upstream. The hyena looked at the donkey and said, “You dirty fellow, you’re dirtying the water.”
The donkey said, “That’s impossible. I’m drinking from downstream.” The hyena said, “But you are.”
The donkey said, “Look, if you want to attack me, stop looking for excuses.” Such is our story!
The police arrested us with no evidence. They did not even know more than our names. By the time they arrested us, they had not even read a collection of our writings that we sent them through one of their security agents. And I believe that ninety percent of the “document” evidence the police presented against us now are our own writings which we gave them in good faith. In our interrogator’s statements, we have seen their desperate interest to make us criminals. As we guessed it, maybe they do not want our presence on social media, at least until the upcoming 2015 election. May be they have not found other options. 
So far, we have witnessed how the investigators are biased towards the ruling party. What follows is for us to publicly test the justice system. For now, however, could we be free soon? I will say we’ve theoretical, not legal options. 
When EPRDF (or the police that EPRDF orders) arrested us, they did not have a “beyond reasonable doubt” evidence, as the lawyers would say. They only hoped to find a mistake, any mistake. However, they have found nothing that could stick and make us criminals within the anti-terrorism law which is already criticized for being  a potent tool for suppressing political opposition and independent criticism of government policy to mean stretched to its limit.
However, the fact that they were not able to find evidence did not prevent them from their objective of charging us. The fact that they did not even write a coherent statement by the time they appeared in court to charge us is an evidence that they do not have a valid suspicion or evidence. Yet, I do not believe that they will release us soon. Why?
1st Unless it is in a humiliating way, one of the things EPRDF does not do is release individuals it detains, especially those who have many supporters. By this I mean EPRDF is as stubborn as a child. (I am not saying I do not like the cries against our unjust detention. Our spirit would not have healed without such a support. We will, one day, publicly say thank you)
 2nd. Their initial paranoia and the paranoia that they found was wrong: meaning, even if they know that we have no plan (following the election) to instigate violence, may be they do not want to miscalculate and take a risk. (one recalls the intentions of the documentary “Colour revolution” to begin with)
3rd. Even though they believe that we have no intention or the capacity to instigate violence, they know that we are strong critics of the ruling party and they do not like it. For this reason, they want us to suffer the bitter reality of detention. At least serving time and following our case in court. It’s as if being released after finishing our sentence.
4th EPRDF is not afraid of judging


Translated by Mahilet Solomon

‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ  ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን (ወይም ‹‹ባለመናገራችን››) ታዲያ ጥፋትህ ምንድን ነው? ተባልን፡፡ ምርመራው የኛን ነፃ መሆን አለመሆን ለማጣራት ሳይሆን ጥፋት ለማግኘት ነበር፡፡ ብዙዎች ‹መንግሥት ዞን ዘጠኝን ለምን ሁለት ዓመት እንደታገሠው› ግራ በመጋባት ይጠይቃሉ፤ ባሕሪው አይደለምና፡፡ የኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምኅዳር በቀላሉ እንደገመቱት ተይዘን፣ ተመርምረንና ‹‹ተገኘባችሁ›› የተባልነው ‹‹ የግንቦት 7 [እና ኦነግም ጭምር] አባልነት [ብሎም ግብ አስፈጻሚነት] ›› በሽታ ለተከሳሽነት አብቅቶናል፡፡ ቀጣዩ የክርክር ሂደት ነው፡፡
ከዚያ በፊት ግን ዞን ዘጠኝን በሩቅም በቅርብም የሚያውቁ በግራ መጋባት መልስ እንደሚሹ በማሰብ ይቺን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የእስራችን ሂደት ምን ይመስላል? የምርመራችንስ? እውን የግንቦት ሰባት አባል ነን? [ታዲያ] ለምን ታሰርን? በቅርቡ እንፈታ ይሆን? 
ደቂቅም ይሁን ሊቅ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታ የሚጽፍ ማንኛውም ሰው [ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ] አንድ ቀን እታሰር ይሆን እያለ መስጋቱ አይቀርም ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ሰው ነገረኝ ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብን በሦስት የመደቡት፡- የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታ እና ወደፊት የሚታሰር በማለት፡፡ እርግጥ ዞን ዘጠኝ ‹‹ሐሳቡን መግለጽ ፈርቶ ዝም ያለ ሁሉ እስረኛ ነው›› ብሎ መደምደም ሦስቱም ምድብ አንደኛው ውስጥ ያጠቃልለዋል ‹‹የታሰረ›› በሚል፡፡ ዞን ዘጠኞች ጦማራችንን በከፈተን በሁለት ሳምንት ሲታገድብን እና ሌላ ስንከፍት ግና መጨረሻ ላይ ታጋቾቹ እኛ እንደምንሆን እናውቅ ነበር፡፡ ያንን የሚያረጋግጥ ተደጋጋሚ የደህንነቶች ክትትል እና ምልክቶች ስለደረሱን መታሰራችን ማስደንገጡ ባይቀርም ያልተጠበቀ ግን አልነበረም፡፡
እስሩ በክትትሉ የተገኘነውን ስድስት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሦስት ጋዜጠኛ ጓደኞቻችንን መሆኑን በተለይ የጋዜጠኞቹ [ቢያንስ ለእኛ] ያልተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኋላ ኋላ ስንመለከተው ግን በእኛ አስታኮ እነሱንም ማሰሩ የታሰበበት ዘመቻ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እኛን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሒደትም ቢሆን በቅጡ የታሰበበት ነበር ሁላችንም (ከአስማማው በቀር) ከቀኑ በ11፡00 ገደማ በያለንበት ስንያዝ አስማማው በማግሥቱ ታስሯል፡፡  ሌሎቻችን ቤታችን በሚፈተሸበት ሰዓት ሕጉ የሚፈቅድበት ሰዓት(12፡00) አልፎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ካዋሉን በኋላ የሕገ-ወጥ አያያዝ ሰለባ የመሆናችን ሂደት የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡
ማዕከላዊን በክፉ ስሙ ቀድሞ ለሚያውቀው ሰው ግቢውን መርገጥ በራሱ ልብን ያርዳል፡፡ ሆኖም በልቤ /ጓደኞቼም እንደእኔ ሳይሰማቸው አይቀርም/ አንደኛ እኛ ጸሐፊ እንጂ ወታደር ወይም ሰላይ ባለመሆናች፣ ሁለተኛ መቼም ከበፊቱ የተሻለ ሰብዓዊ አያያዝ ሳይኖርም አይቀርም የሚል የዋህ ተስፋ በማሳደሬ ብዙም አልተሸበርኩም ነበር፡፡ የገባሁ እለት ከታሳሪዎች በተሰጠኝ ማብራሪያ ‹‹ሳይቤሪያ›› መግባቴን አወቅኩ፡፡ ከዚያ የ HRW-They want confession የተሰኘ ሪፖርት ላይ የተፃፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል መሆናቸውን ለመረዳት የፈጀብኝ ከአንድ ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነበር፡፡
ምርመራ ማዕከላዊ ስታይል
ምርመራ በማዕከላዊ ከብልጠት ይልቅ ጉልበት ይበዛበታል፡፡ መርማሪዎቹ የምርመራ ችሎታቸው ተጠርጣሪውን የተጠረጠረበትን ጉዳይ ከማውጣጣት ይልቅ የምርመራ ችሎታ እንዳላቸው ለማሳመን የሚጥሩበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ይህም አልሰራ ሲል ጥፊ፣ ካልቾ፣ ከአቅም በላይ ስፖርት ማሰራት እና ግርፋት ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ ላይ ከተፈራረቁብኝ አምስት መርማሪዎች እና ሌሎችም አብሮ ታሳሪዎቼ ከነገሩኝ የተረዳሁት ነው፡፡ እርግጥ ሌሎች ‹‹እርቃንን ቁጭ ብድግ›› የሰሩ ተጠርጣሪዎችም ገጥመውኛል፡፡ ከባባድ ቅጣት (ወፌ ላላ ግርፋት፣ ጥፍር መንቀል) የደረሰባቸው ሌሎች ታሳሪዎች አብረውኝ የታሰሩ ቢሆንም ይህ የተፈፀመባቸው ግን ወደማዕከላዊ ከመምጣታቸው በፊት  ነው፡፡ ከነዚህ መካከል የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡ የሚገርመው በዚህ ዓይነቱ ምርመራ የሰጡት ቃል ለማመሳከርያ ማዕከላዊ መምጣቱ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ወደማዕከላዊ ከመዛወራቸው በፊት ከባድ ቅጣት የተቀጡበትን ቦታ የት እንደሆነ እንዳያውቁ አይናቸው ተሸፍኖ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እሥረኞችም መኖራቸው ነው – የደርግን ‹‹ቤርሙዳ›› ያስታውሳል!
እናም በሚያዋርድ እና ክብርን በሚነካ ስድብ በሚያስፈራ የቤቱ (የማዕከላዊ) ጥላ እና ኃይል በተቀላቀለበት የምርመራ ሂደት የተከሳሽ ቃላችንን ሰጠን፡፡ ቃላችን መቶ በመቶ እውነት አልነበረም፡፡ ጫናው በበረታ ቁጥር መስማት የሚፈልጉትን ‹‹ዓመፅ ለመቀስቀስ ፈልገን›› የመሳሰሉ በራስ ላይ ፈራጅ (Self-incriminating) ሐረጎችን እየተናገርን ነበር፡፡ ያም ግን ለመርማሪዎቻችን በቂ አልነበረም፡፡ ስለዚህ በሚጽፉበት ሰዓት እያንዳንዷን ‹‹ሠራን›› ያልነውን ሁሉ ሊያስከስሰን በሚችልበት ሁኔታ እየገለበጡ እና እየበጠበጡ ፃፉት፡፡ አንዳንዶቻችን እየተከራከርን ሲያቅተን ፍርድ ቤት ይፍታው ብለን ፈረምን፣ቀሪዎቻችን የቻልነውን ያህል ተደብድበንበት ፈረምን፡፡ ‹‹ከተናገርኩት ቃል ውጪ አንድም ቃል አልፈርምም›› በሚል እስከመጨረሻው ታግሎ የተሳካለት አቤል ብቻ ነበር፡፡
በምርመራው ሂደት የተረዳነው ነገር ቢኖር የማዕከላዊ መርማሪዎች ብቃት (Intelligence) አርጩሜ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ምርመራ ሲባል ይመስለኝ የነበረው ፖሊሶች ተጠርጣሪዎችን ፈፀሙ ስለሚባለው ነገር በቂ መረጃ ይዘው ግፋ ቢል ለምንና እንዴት እንደፈፀሙት ማውጣጣት ነበር፡፡ ‹‹ዕድሜ ለማዕከላዊ›› የተረዳሁት ነገር ቢኖር ምርመራ ማለት ለካስ ‹‹የሠራኸው ወንጀል ምንድን ነው?አውጣት!›› ማለት ኖሯል- ማዕከላዊ ስታይል፡፡ ‹‹ነጻ ነኝ›› ቢሉ ሰሚ የለም፡፡ አንዴ ታስረሃል ወንጀል ሊገኝብህ የግድ ነው፤ ካልሆነ ይጋገርብሃል፡፡
አሁን ሳስበው ማዕከላዊ ፈርሶ በሥር-ነቀል ለውጥ እንደገና መቋቋም ያለበት ተቋም ነው፤ ቢያንስ በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ የምርመራው ሂደት (በራሳችን ጉዳይ እንደተረዳሁት) ትዕዛዝ አስፈፃሚነት ይስተዋልበታል፡፡ ማለትም በመርህ የሚመራ አይደለም፡፡ ሁለተኛ ምርመራው እውቀት መር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የአገሪቱን ደህንት አደጋ ውስጥ የሚጥል ጉዳይ በምርመራው ድክመት ሳይታወቅ ሊታለፍ ይችላል፡፡ ይህ ችግር የተከሰተው ደግሞ መርማሪ ፖሊሶቹ ከብቃት ይልቅ ለታዛዥነት የተመቹ ታማኞች ሆነው በመመልመላቸው ነው፡፡
‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ››
በምርመራው ሂደት የተጨቀጨቅነውም ሆነ ተገድደን የፈረምነው ጽሑፎቻችንን የበይነ መረብ ዘመቻዎቻችንን፣ የወሰድናቸው ስልጠናዎችም ሆኑ አንዳንዶቻችን የሰጠናቸው ስልጠናዎች አመፅ ለማስነሳት መሆኑን ‹‹እመኑ›› በሚል ስለነበር የጠበቅነው ግፋ ቢል በወንጀለኛ መቅጫው አንቀጽ 238 ወይም 257 ሊከሱን አስበው ነው ብለን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክስ መዝገቡ ሲመጣ ‹‹ሽብር›› ያውም ከአስራ አምሰት ዓመት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አንቀጽ 4 መሆኑን ሳውቅ በበኩሌ ሳቄ ነበር የመጣው፡፡
ማስረጃ ተብለው ከክስ መዝገቡ ጋር የተያያዙት በአብዛኛው ጽሑፎቻችን፣ የዘመቻዎቻችን፣ የጋዜጣ መግለጫዎች እና በተለያዩ ሥልጠናዎች ወቅት የተዘጋጁ የሥልጠና መመሪያዎች (Manuals) ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ከግንቦት 7 እና ከኦነግ ጋር ያገናኛችኋል የተባልነው በሦስት ‹‹ሰነዶች›› ነው፡፡ አንደኛው ናትናኤል ኢሜይል ውስጥ በጥቅምት 2001 ተልኮለት የተገኘ የግንቦት 7 የዜና መጽሔት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ገና የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አዋጁ ሳይወጣ፤ ግንቦት ሰባትም አሸባሪ ከመባሉ በፊት መሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛ ሶልያና ቤት ተገኘ ተብሎ እናቷ ‹‹ቤቴ ውስጥ አልተገኘም፣አልፈርምበትም›› ያሉት እና ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ሰራዊት ምልመላ መመዘኛ ሰነድ ነው፡፡ ይህ የሶሊ የዘለቀ አቋም ለሚያውቅ ሙግት አያስፈልገውም፡፡ እኔ እንደውም ትዝ ያለኝ ከመታሰሬ በፊት የትዊተር ፕሮፋይሏ ውስጥ የነበረው ‹‹no for war›› የሚል መፈክር ነው፡፡ ሦስትኛው ደግሞ ማሕሌት ኮምፒውተር ውስጥ የተገኘው የኦነግ ፕሮግራም ነው፡፡ በርግጥ አብረው የተገኙት የሌሎች የኦሮሞ ፓርቲዎች ፕሮግራሞች ማስረጃ ተብለው አለመቅረባቸው መረዳት ብቻ – እሷም ለምን ፕሮግራሙን እንደያዘችው፤ እነሱም ለምን የኦነግን እንደመረጡ ያጋልጣልና የእመኑኝ ሙግት አያስፈልገንም፡፡ በመሰረቱ ሦስቱንም ‹‹ሰነዶች›› መያዝ ከቡድኞቹ ጋር ግንኙነት መመሥረት የሚሰሩትንም መውደድ ማለት አየደለም፡፡ ይህም ለመሪዎቻችን ባይታያቸውም እንኳ ለወገኖቻችን የጠፋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡
ሌላውና በአስቂኝለቱ ተወዳዳሪነት የሌለው ውንጀላ ‹‹48 ሺሕ ብር በናትናኤል በኩል ተቀብለው ተከፋፍለዋል›› የሚለው ነው፡፡ ይህ ብር ፤‹‹አሸባሪ›› ከተባሉት ቡድኖች የተወሰደ እንዲመስል በሚያደናግር አገላለጽ የተጻፈ ቢሆንም የክስ መዝገቡ ውስጥ የተያያዘውና ገንዘቡ የመጣበት ደረሰኝ እንደሚያረጋግጠው የተላከው ከARTICLE 19 ነው፡፡ ይህንን ጨምሮ በእስር ላይ ለምትገኝ ጋዜጠኛ ቤተሰቦች መደገፊያ /ለእስረኛይቱም ማበረታቻ/ የተላከ መሆኑን ለመርማሪዎቹ በዝርዝር አስረድተናቸዋል፡፡ ይህንን እያወቁ ውንጀላውን ማኖራቸው እውነትም እኒህ ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው ብለው አምነው ሳይሆን ‹‹ከቻልን አደናግረን እናስቀጣቸዋለን (የማይችሉበት ሁኔታ አይታየኝም)፣ካልቻልን ደግሞ በቀጠሮ ጊዜ እንገዛበታለን፣ ነጻ እስኪወጡም ቢሆን በእስር እናቆያቸዋለን›› የሚል ክፉ ምኞት ነው፡፡
… ሳታመኻኝ ብላኝ!
አህዩት ከታች አያ ጅቦ ከላይ ሆነው ወራጅ ውሀ እየጠጡ ነበር አሉ፡፡ ነገር ያማረው አህዩትን ‹‹አታደፍርሽብኝ›› ሲላት ነገሩ የገባት አህይትም ‹‹ሳታመኸኝ ብላኝ›› አለችው ይባላል፡፡ የኛም ነገር እንደዚያው ነው፡፡
ፖሊስ ሲይዘን እኛ ላይ ይህ ነው የሚባል የመክሰሻ መረጃ አልነበረውም፤ እንዲያውም ከስማችን በቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከደህንነቶታቸው በአንዱ ልከንላቸው የነበረውን የጽሑፋችንን ስብስብ እንኳን ሳያነቡት ነበር የያዙን፡፡
አሁንም ማስረጃ ብለው ከክስ መዝገባችን ጋር ያያያዙት ቢያንስ በእኔ ግምት ዘጠና በመቶ የሚሆነው ‹‹ሰነድ›› እኛው ነፃ ያወጣናል ብለን የሰጠናቸው ጽሑፎቻችን ናቸው፡፡ በመርማሪዎቻችን ንግግር ውስጥ እኛ ላይ ወንጀል የማግኘት Desperate ፍላጎት አይተናል፡፡ ምናልባትም እንደገመትነው ቢያንስ እስከ 2007ቱ ምርጫ ድረስ ከማኅበራዊ ሚዲያ ገለል እንድንልላቸው ፈልገዋል፡፡ ከዚህ የተሻለም አማራጭ አልታያቸውም ይሆናል፡፡
በእስካሁኑ ሂደት የማዕከላዊን ለገዢው ፓርቲ ወገንተኝነት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል፡፡ ቀጣዩ ደግሞ የፍትሕ ሥርዓቱን በአደባባይ መፈተሽ ይቀረናል፡፡ ለአሁኑ ግን በቅርቡ እንፈታ ይሆን… የሚል ጥያቄ ‹ሕጋዊ› ሳይሆን መላ ምታዊ አማራጮችን እገምታለሁ፡፡
ኢህአዴግ ወይም የኢህአዴግ መንግሥት የሚያዘው ፖሊስ እኛን በቁጥጥር ሥር ሲያውለን ስለወንጀላችን ማረጋገጫ (ጠበቆች Beyond reasonable doubt) እንደሚሉት ዓይነት ባይኖረውም መቼም የሆነች ስህተት ሳላገኝባቸው አልቀርም በሚል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወትሮም የተንቦረቀቀ የሚባለው የፀረ-ሸብርተኝነቱ አዋጅ ውስጥ የሚጥለን ነገር በቀላሉ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አለመቻላቸው ግን የተነሱበትን እኛን የመክሰስ ዓላማ አላጠፋውም፡፡  የክስ መዝገቡን ሲያዘጋጁ አንድም የረባ ዐረፍተ ነገር ሳይጽፉ ይዘውን ፍርድ ቤት መቅረባቸው በራሱ አንድም የረባ ጥርጣሬና ማረጋገጫ እንደሌላቸው አመላካች ነው፡፡ ቢሆንም በቅርቡ ይለቁናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ለምን;
1ኛ. ኢህአዴግ በጣም የሚናደድባቸው እና ታሳሪውን በሚያዋርድ መልኩ ካልሆነ በቀር ከማያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ- አንዴ ያሰረውን ተቺውን ፤ ያውም ብዙ ደጋፊ ያለውን መፍታት ነው፡፡ ኢህአዴግ እንደልጅ እልህ ይጋባል ማለቴ ነው፡፡ (ይህንን ስል የእስራችንን ኢፍትሀዊነት የተመለከቱትን ጩኸቶች መጥላቴ አይደለም፤ ያለ እነርሱ መንፈሳችን አይጠገንም ነበር፡በአደባባይ የምናመሰግንበት ቀን ይመጣል)
2ኛ. መጀመሪያ የተጠራጠሩበት እና ኋላ የዋጧት ጥርጣሬያቸው፤ ማለትም (ምርጫውን ተከትሎ) አመፅ ማስነሳት በሚሉት ጉዳይ ላይ እቅድ እንደሌለን ቢያምኑም እንኳን ምናልባት እምነታቸው ከተሳሳተ Risk መውሰድ አይፈልጉም፡፡ ( መጀመሪያም የቀለም አብዩት ዶክመንተሪ አዝማሚያ ያስታውሷል)
3ኛ. ምንም እንኳን ዓመፅም፤ሽብርም  የማስነሳት ፍላጎትም አቅምም፤  እንደሌለን ቢያምኑም የገዥው ፓርቲ ጠንካራ ተቺዎች መሆናችንን ስለሚያውቁ እና ስላልወደዱልን ፍርድ ቤት በምንመላለስበት ረዘም ያለ ጊዜ ባለው እስር ወቅት ቢያንስ የእስርን ምሬት እንድንቀምሳት ይፈልጋሉ፡፡ ቅጣትን ጨርሶ በነፃ መለቀቅ እንደማለት፡፡
4ኛ. ኢህአዴግ መፍረድ አይፈራም፡፡
Befekadu Hailu

የጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ የክስ መቃወሚያ ቀጠሮ ተላለፈ
የዞን ዘጠኝ ስድስት ጦማርያንና ሶሰት ጋዜጠኞች በወንጀለኛ መቅጫ ህግና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም አቅደዋል፣ ተዘጋጅተዋል፣ አሲረዋል፣ አነሳስተዋል እንዲሁም ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሁከትና በአመፅ ለመለወጥ አስበዋል ተብለው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በህገ መንግሥትና በህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በሚደረግ የሙከራ ወንጀል ተከሰው ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡ 
ከሦስት ወራት የምርመራ ጊዜ በኃላ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች በፅሑፍ የቀረበላቸውን ክስ ካደመጡ በኃላ በአቃቢ ህግና በጠበቆቻቸው መካከል በተደረገ የዋስትና ጥያቄ ክርክር ብይን ለመስጠትና የክስ መቃወሚያ ለማዳመጥ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በዛሬው ቀጠሮ ዘጠኙም ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በዋስትና መብት ጉዳይ በጠበቃና በአቃቢ ሕግ መካከል የተደረገው ክርክር የህግ ትርጓሜ እንደሚያስፈልገው ጠበቃዎች በጠየቁት መሰረት ከመቅረጸ ድምጹ ላይ ተገልብጦ ለህግ አስተርጓሚ እንዲላክ እንዲሁም በሌለችበት ክስ የተመሰረተባት 1ኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላት የተሰጠው ትዕዛዝ ባለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። 
ባለፈው ቀጠሮ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ከፍርድ ቤቱ ብይን ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በዛሬው ቀጠሮ የሰጣቸው ትዕዛዞች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው ለብይን ያስቸግረናል በሚል የክስ መቃወሚያቸውን ሳያደምጥ ቀርቷል፡፡ 
ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት አስተያየት በመጀመሪያው የፍርድ ቤት ውሎ ለዛሬ ቀጠሮ የክስ መቃወሚያ እንዲቀርብ ብይን የተሰጠ መሆኑን አስታውሰው ፍርድ ቤቱም ሆነ አቃቢ ህጉ የክስ መቃመወሚውን ለማየት በቂ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ እንድናቀርብ ይፈቀድልን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ችሎቱም የጠበቆችን ጥያቄ በመቀበሉ የክስ መቃወሚያው ለአቃቢ ህግና ለፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ቀርቦ በቀጣዩ ቀጠሮ በንባብ እንዲሰማ አዟል።
በ1ኛ ክስ ላይ ለተዘረዘሩ የወንጀል ድርጊቶች 5 መቃወሚያ እንዲሁም በ2ኛ ክስ ለቀረቡት የወንጀል ድርጊቶች 4 መቃወሚያ ነጥቦች የተዘረዘረበት ሰነድ “የቀረበው ክስ ከተጠቀሰው የህግ አነጋገር ጋር የሚቀራረብ አለመሆኑን፣ ተከሳሾች ፈጽመዋቸዋል የተባሉት በክስ ዝርዝሩ የተመለከቱ ተግባራት በህግ የተፈቀዱና ሕገ መንግስታዊ ጥበቃም የተደረገባቸው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መሆናቸውን፣ የቀረበው ክስ ግልፅ አለመሆኑን፣ ወስደዋል የተባሉት ሥልጠናዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ያስተላለፉት መረጃ ወንጀል አለመሆኑን የተመለከቱ መቃወሚያዎችን የያዘ ነው፡፡
በ2ኛ ክስ የቀረበው የክስ መቃወሚያ ደግሞ ጠበቃው ማሰብ የማያስከስስና የማያስቀጣ መሆኑን፣ መደራጀት፣ የሥራ ክፍፍል መፍጠር እና የተለያዩ ሥልጠናዎችን መውሰድ ወንጀል አለመሆኑን፣ በአንድ ድርጊት ሁለት ክስ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑ፣ የቀረበው የማስረጃ ሰነድ አለመሟላትን በተመለከተ ከወንጀለኛ መቅጫ እና ከጸረሽብር አዋጁ አንቀጽ ጠቅሰው ተቃውሞዎቻቸውን በጽሑፍ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ 
የዕለቱን ችሎት የሚመሩት ዳኛ ባስተላለፉት ውሳኔ የዋስትና መብት ጥያቄ ክርክር ከመቅረጸ ድምጽ ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ ለህግ አውጪ አካል እንዲልክ እንዲሁም ለ1ኛ ተከሳሽ በፕሬስ ጥሪ እንዲደረግና የክስ መቃወሚያ በንባብ እንዲደመጥ ትዕዛዝ አስተላልፈው ለነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡


አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነው መቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽ ሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል

ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባት የምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰት እድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁን ግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸው ክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡

  ክሱ በአጭሩ

በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን (የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238) የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብር ተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ

1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል

2. ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
3. Security in a boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
4. አመጽ ቡድኖችን ማደራጀትና አመጽ ማነሳሳት  የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
ከዚህ በፊትም እነደተናገርነው  ማንኛቸውም የዞን9 ጦማርያን በፓርላማ በሽብር ከተፈረጁ ወገኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡  ብዙ  የዞን9 ነዋሪያንንም አንደሚረዱት አብዛኛዎቹ የዞን9 ጦማርያን እነዚህ አካላት ላይ በሚያደርጉት ከፍተኛ ትችት እየታወቁ ጉዳዩን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ መሞከር ፣መንግስት የፈረጃቸውን ድርጅቶች እነደፈለገ ማንንም ሰው ለመክሰስ አንደሚጠቀምበት ከማሳየት ባለፈ ትርጉም የማይኖረው ነው፡፡ ለማጠቃለል ያህል ማንኛቸውም የዞን9 አባላት አገር ውስጥም ሆነ ውጪ አገር ያለ የፓለቲካ ደርጅት አባላት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያሳይ መረጃም መንግሰት ለማቅረብ አንደማይችልም አናውቃለን፡፡ ( የማስረጃ ዝርዝር ላይ ወደታች የምንመለስበት ይሆናል)
ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
በክሱ ላይ ስሙ ያልተጠቀሰ የህቡእ ሽብር ድርጅት በመመስረት ተከሰናል፡፡ በመሰረቱ መንግስት ዞን9 የሚለውን ስም አንድም ቦታ በክሱ ላይ ለመጠቀም ያልፈለገው የጦማርያኑን ቡድን ይበልጥ ታዋቂ እነዳይሆን ለማድረግ አንደሆነ አንገምታለን፡፡ ይህ አስቂኝ ክስ አንድም ቦታ ላይ የዞን9 ስም ባያነሳም በደፈናው በህቡዕ መደራጀት ብሎ ከሶናል፡፡ በመሰረቱ መንግሰት እኛን ለማግኘት ምንም አይነት የደህንነት ስራ እነዳላስፈለገው አናውቃለን፣. ምክንያቱም ሁሉም የዞን ፱ ጦማርያን ስማቸውና ፎቶአቸውን ማስቀመጣቸው ቋሚ የምንስማማበት እሴት ስለነበር ነው፡፡ የምንጽፈው ነገር በተናጠል ሃላፊነትን አንድንወስድ አንዲሁም ሌሎችን ሃሳብ መግለጽን ለማበረታታት በማሰብ በአደባባይ  እነዲታይ የወሰነውን የጦማርያንን ስብስብ ‹‹ህቡዕ›› ብሎ መጥራት ማንን ለማሞኘት አንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ዞን፱ ድብቅ እነዳልሆነ እያንዳንዱ ጽሁፍም በተናጠል ሃላፊነቱን የሚወስድ ጸሃፊ የቡድን ጽሁፎች ሲሆኑ ደሞ የቡድን ሃላፌነት አንደምወስድ ማንም የጦማራችን አንባቢ ያውቀዋል፡፡ መንግስት የዞን፱ አይነት ጦማሮችንም ሆኑ የአንተርኔት አንቅስቃሴዎቸን የሚመዘግብበት አሰራር አለመኖሩ ደሞ የእኛ ጥፋት ተብሎ ሊቆጠር አይችልም፡፡ተሰብስቦ መጦመርን የሚከለክል ምንም አይነት የህግ ክልከላም የለም፡፡ በመሆኑም ተሰብስበን መጻፋችን  ራሳችንን ገልጸን ሃሳባችንን መግለጻችን የጣስነው ምንም ሕግ የለም፡፡ፓሊስም ሆነ መንግሰት ሶስት ወር በፈጀ ምርመራው ህቡዕን ትርጉም ትርጉም በሚገባ አለማወቁም ጉዳዩን አስተዛዛቢ ባስ ሲልም መሳለቂያ ያደርገዋል፡።  
Security in a boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ

Security in a box ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የኢንተርኔት አንቅስቃሴን በጥንቃቄ ለማድረግ የሚረዳ ኦፕን ሶርስ የስልጠና ማንዋል ሲሆን ይህንን ስልጠና መውሰድ በምንም መልኩ ወንጀል ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የስልጠና ማንዋል ለማንኛውም የሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያሳስባቸው ሰዎች አንዲያገኙት ሆኖ የተዘጋጅ  ፍሮንት ላየን ዲፌንደርስ እና ታክቲካል ቴክ የተባሉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ያዘጋጁት ስልጠና ነው፡፡ በመሰረቱ ይህንን ስልጠና ወንጀል አድርጎ ከማቅረብ በፊት ጎግል ላይ አስገብቶ መፈለግና ውጤቱን ማየት ከአንደዚህ አይነት አሳፋሪ ክስ ያድን ነበር፡፡ ይህ በበጎ መልኩ አንረዳው ካልን የፍትህ አካላቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ከፍተኛ ርቀት የሚያሳይና መንግሰትም በሰፊውና በቅንጅት ሊሰራበት የሚገባ ክፍተት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ካየነው ደሞ መንግሰት እሱ የማያውቀውን ማንኛውንም ነገር ያለምንም የህግ ክልከላ  ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ያለውን ጉጉት ያሳያል ያ በራሱ ደሞ መንግስትን ራሱን ህገ ወጥ እነደሚያደርገው ያለምንም የህግ እውቀት ማሰብ ብቻ ለሚችል ሰው የሚገለጥ ሀቅ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ወንጀል ተብለው የተለያዩ ስልጠናዎች በሚል የተጠቀሱት የኮምኒኬሽን ስልጠና የስትራቴጂክ ስልጠና የአድቮኬሲ ስልጠና የመሳሰሉት መሆናቸውን ለመጥቀስ አንወዳለን፡፡ በመሰረቱ በተለያዩ ድርጅቶች ግብዣ ስልጠና መውሰድና የሰብአዊ መብት ፎረሞች ላይ መገኘትን ወንጀል የሚያደርግ ህግ አለመኖሩን መንቀሳቀስም የዜጎች ሰብአዊ መብት መሆኑን ለአቃቢ ህግ ህግና ፓሊስ ካላወቁ ማን ሊያውቅ ነው ??

የተደራጁት የአመጽ ቡድኖችን ማደራጀት  እና 48 ሺህ ብር ለአመጽ ማከፋፈል
መንግሰት የአመጽ ቡድኖችን ማደራጀት በሚል ያቀረበውን ክስ ለመመለስ ያህል አንድ ጥያቄ ብቻ አንጠይቃለን? የታሉ የተደራጁት ቡድኖች?  ምንም የተደራጀ ቡድን በሌለበት ይህንን ክስ ማቅረብ በፍትህ ስርአቱ ማፌዝ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምን ይባላል? በ48 ሺህ ብር የአመጽ ማነሳሳት ክሱን ከብሩ ማነስ በላይ ይበልጥ አስቂኝ የሚያደርገው የማስረጃው ዝርዝር ላይ ያለው ማስረጃ እና ክሱ የተለያዩ መሆናቸው ነው፡፡ ክሱ 48,000 ብር ከውጪ በመቀበል በማለት በደፈናው ላኪውን ሳይጠቅስ ያለፈው እና ለሽብር ተግባር የተባለው አርቲክል 19 ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ለታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች የሚደረግ ድጋፍ ሲሆን በወቅቱ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ባንክ ስለሚሰራ ተቀብሎ ለጋዜጠኛ ርዩት አለሙ ቤተሰቦች እስር ቤት መመላለሻ ተብሎ የተሰጠ ድጋፍ ነው፡፡
የተያያዘው የባንክ ደረሰኝም ያንን የሚያሳይ ሲሆን ክሱ ላይ በይፋ መጥቀስ ያልተፈለገው ለምን ይሆን? (ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹን መታሰር ተከትሎ መንግስት ፋይል የከፈተበትን ከሰብአዊ መብት ተቋማት ነን ከሚሉ ድርጅቶች የሃሳብና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም አመጽ ማነሳሳት የሚለውን ክስ ተከትሎ የተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት ወንጀል ሊሆን አይገባም በሚል ርእስ እስሩን የሚያወግዝ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል)

ማስረጃው ሲገመገም
እስካሁን በእጃችን የደረሰውን የማስረጃ ዝርዝር በሶሰት ከፍለን ማየት አንችላለን ፡፡ ከማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ አብዛኛውን ቦታ የሚይዘው በተለያየ ወቅት የተጻፉ የጦማርያኑ ጽሁፎች ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ላይ ደሞ ጭራሽ የመረጃ ዝርዝር ለማቅረብም አልተቻለም፡፡(አቃቤ ህግ የሁሉንም የበይነ መረብ ዘመቻዎች መግለጫ እና እቅድ እንደማስረጃ አቅርቧል)  በሁለተኛ ደረጃ የቀረቡት የተለያዩ የጉዞ ትኬቶች አለም አቀፍ ስብሰባ ማስታወሻዎች አንዲሁም ፕረዘንቴሽኖች  ሲሆኑ ሁሉም ጦማርያኑ ያደረጓቸው አለም አቀፍ ጉዞዎችን የሚያሳዩ የተሳተፉባቸው ሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የተመለከቱ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተደረጉ ጉዞዎችን ናቸው፡፡

በማስረጃ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት የሽብር ተግባር የተደረጉ ጉዞዎች ተብለው መሆኑ ይበልጥ ክሱን አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ መንግሰት ጉዞዎቹ የተደረጉትም ሆነ የስልጠና ግብዣዎቹ የመጡት ከአለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አንደሆነ እያወቀና እና ማስረጃው ላይም በግልጽ እየታየ የሽብር ቡድኞች ብሎ ግንቦት ሰባትና ኦነግን ጣልቃ ማስገባቱ አስገራሚ ነው፡፡ (የፍርድ ሂደቱ ላይ እነዚህ ተቋማት ጋር የተደረጉ ግንኙነቶቸን አንዴት ብለው በፓርላማ ከተፈረጁ የሽብር ተቋማት ጋር እነደሚያገናኛቸው አብረን የምናየው ይሆናል)  በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የተደረጉ የስልክ ልውውጦች ሲሆኑ በፍርድ ቤት ሂደቱ ውስጥ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡  በመጨረሻም ተከሳሽ ቤት ተገኘ የተባለውና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት ከግንቦት ሰባት ጋር የተገናኙ ዶክመንቶች እና የአባላት መጽሄት ሲሆን በፍተሻው ወቅት ፓሊሶች ራሳቸው ፍሪጅ በስተጀርባ አገኘን ብለው በፍተሻ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ የራሳቸውን ምስክሮች ብቻ አስፈርመው መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድ ቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተት ወስነናል፡፡

እንደማጠቃለያ

የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅት አንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይ ሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩ አለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህ ስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋ ጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራት በፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡

የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!  

ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል

ዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎች

  1. ነጻነትና ዳቦ – በናትናኤል ፈለቀ
  2. ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል – በናትናኤል ፈለቀ
  3. ስደትና ፍቅር – በሰለሞን አብርሃም(ከአውሮጳ)
  4. ዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….? – በበፍቃዱ ሃይሉ
  5. ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት? – በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤል
  6. እኛና ሶማልያ – በናትናኤል ፈለቀ
  7. ድምፃችን ይሰማ – በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤልና እና በፍቃዱ ሃይሉ
  8. እንዴት እንደመጥ – በማህሌት ፋንታሁን
  9. የመለስ ውርስ እና ራዕይ – በሶሊያና ሽመልስ
  10. የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራ – በማህሌት ፋንታሁን
  11. ትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ? -በበፍቃዱ ሃይሉ
  12. ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ በዘላለም ክብረት

ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ

  1. ከ21 አመት በኋላ ዴሞክራሲ ሲሰላ
  2. ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መመሪያ በማክበር መሥራት ይቻላል?
  3. አብዮት ወረት ነው
  4. የእህአዴግ ‹‹ትርፍ›› እና ኪሳራ
  5. የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች
  6. ከእከሌን አሰሩት እስከ እከሌን አገዱት
  7. ሰማኒያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
  8. “ድር ቢያብር” ለአምባገነኖች ምናቸው ነው ?
ከሌሎች ብዙ ዝርዝሮች በጥቂቱ

  1. “ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ ትግሬያዊ ማንነት የለም” – (በአብርሃ ደስታ ጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  2. “መንግስት የለም ወይ ?” የምንና ምን አይነት መንግስት(የመስፍን ነጋሽ ጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  3. የሁለተኛው ዘመቻ ዕቅድ ( ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  4. የ2ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  5. ዳዊት ሰለሞን ስለአዲሱ የጋዜጠኞች ፎረም ፕሬዚዳንት ፌስቡክ  ላይ የፃፈው እና አጥናፍ ለበፍቄ ኢሜል የደረገለት ጽሑፍ
  6.  “ፍርሃታችን የት ያደርሰናል ?” በሚል በኤልያስ ገብሩ ተጽፎ በፍቄ ላፕቶፕ ውስጥ የተገኘ(ለዕንቁ መጽሄት ተዘጋጅቶ ያልታተመ ጽሑፍ)
  7. የ3ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ( ዴሞክራሲን በተግባር እናውል የሰላማዊ ሰልፍ መብታቸን ይመለስ)
  8. “ሰልፍና ሰይፍ ” በሚል በበፍቄ ተጽፎ ነገር ግን ያልታተመ ጽሁፍ ከላፕቶፑ
  9. የ1ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ(draft ሕገ መንግሰቱ ይከበር)
  10. የ4ኛው ዘመቻ ዕቅድ( ኑ ኢትዪጲያዊ ህልም አብረን እናልም)
  11. ጋዜጠኛ አስማማው ለድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ያዘጋጀቸው ጥያቄዎች ከኢሜሉ (ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት)
  12. ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.org ላይ የታተሙ ጽሑፎች
  13. በናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19 የተላከ 48,170.25(ብር) የዌስተርን ዩኒየን ኮፒ
  14.  “የተቃውሞ ሰልፉ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች” በሚል አዲስ ጉዳይ ላይ የታተመ ጽሁፍ (draft)
  15. ማሒ ስለ ርዕዮት ዓለሙ እና ስለ አዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት ” በቀልድ የጻፈችው ጽሑፍ፡፡
  16. የዞን 9 ወደፌት ለመስራት የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክት ፕሮፓዛሎች ( ምርጫ 2007 ሪፓርት የማድረግ ስራ፣ የኢትዮጲያ የነጻነት ኢንዴክስ ማዘጋጃት ስራ ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጲያ ላይ ለመስራት የታሰበ ዶክመንተሪ እቅድ)
  17. እና ሌሎችም ትርኪሚርኪዎች (ለምሳሌ የዳንኤል ብርሃነ ጽሑፍ፣ የናቲ የ10ኛ ክፍል ግጥም)

#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsmamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

    #Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

    የኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለዞን9 ጦማርያን ሽልማት አበረከተ 

    በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በእስር ለሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ያልተዘመረላቸው ጀግኖች በሚል በአራተኛው አመታዊ ክብረ በአል ላይ ሽልማትን አበርክቶላቸዋል፡ 

     
    በየአመቱ በሚደረገው በዚህ ክብረ በአል መዝጊያ ስነስርአት ላይ የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበበ የዞን9 ጦማርያን ከፍተኛ መስዋእትነትን የሚከፈልበትን ሃሳብን አገር ውስጥ ሆኖ እውነትን የመናገርን ሃላፌነት ወስደው እየከፈሉት ላሉት መስዋእትነት እውቅና መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።


    ይህ ያልተነገረላቸው ጀግኖች በሚለው ምድብ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከዚያ በተጨማሪ ሁለት ተሸላሚዎች ከአገረ አሜሪካን ሽልማት ወስደዋል፡፡

    የዞን9 ጦማርያን በታሰሩ ጦማሪ ጓደኞቻችን እና ጋዜጠኞችን ስም ለተሰጠው እውቅና ሽልማት ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡


    #Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

    ትላንትና ያለምንም ክስ ድፍን 80 ቀን የሞላቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ጓደኞቻቸን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ ያካሄደውን ምርመራ መጨረሱን ፓሊስ በጓሮ በኩል ፍርድ ቤትበመቅረብ አሳውቋል፡፡ ቅዳሜ እለት 28 ቀናት የምርመራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደፍርድ ቤትከመሄዳቸው ከቀናት አስቀድሞ ከነበሩበት የጨለማ ክፍል እስር በተለምዶው ሸራተን ወደሚባለው ቦታ የተዘዋወሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላለፉት ጥቂት ቀናት በወዳጅ እና ጓደኛም ጭምር መታየት ችለዋል፡፡ 

    ቅዳሜ በመቶዎች ተሰብስበው የሚጠበቁበት ችሎት ላይ ፓሊስ ብቻውን በመገኘት እና ጠበቃውን ባላካተተ ከዳኛ ጋር የተደረገ ንግግር የፓሊስ የምርመራ ፋይሉን በማጠናቀቁ ወደ አቃቤ ህግ ማስተላለፉን እና ክሱም በከፍተኛውፍርድ ቤትአንደሚታይ በማመልከት የጊዜ ቀጠሮ ፋይሉ አንዲዘጋ ጠይቋል፡፡ ታሳሪዎችም ሆነ የህግ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ፍርድ ቤቱ የፓሊስን ጥያቄ ተከትሎ ፋይሉ የተዘጋ ሲሆን ከሰአታት ጥበቃ በኋላ በመዝገብ ቤት በኩል ጠበቃቸውና ወዳጆች ፋይሉ መዘጋቱን ለማወቅ ችለዋል፡፡ 

    በተመሳሳይ ሁኔታ ትላንት ሰኞ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት ሌሎች ሶስት የዞን 9 ጦማርያንም ፓሊስም ሳይቀርቡ ፓሊስ በጻፈው የሶስት መስመር ደብዳቤ ምርመራ መጨረሱን አና ለአቃቤ ህግ ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡ በመሆኑም የጓደኞቻችን ሆኑ ፓሊስ ባልተገኙበት የትላንትናው ሂደትን አስከትሎ የጓደኞቻቸን ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን ክሱን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ለደንበኞቻቸው አንደሚሰጥ እነደሚጠብቁና እሳቸው ባሉበት መከናወን እነዳለበት ገልጸዋል፡፡ የፓሊስን አሰራር የወንጀል ስነስርአት ህግን ያልጠበቀ ድብብቆሽ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

    ጓደኞቻችን ቀድሞ የነበሩት የእስር ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ 15 ደቂቃ ወደውጪ ለመናፈስ ከመውጣት ባሻገር ምንም ከውጪው አለም ጋር የመገናኘት እድል ሳይኖራቸው ከሁለት ወራት ከግማሽ በላይ ካሳለፉበት ጊዜ በመገላገል ሊጠየቁ ወደሚችሉበት ቦታ መዘዋወራቸውን ተከትሎ በጠንካራ ሞራል አና አካላዊ ደህንነት ላይ አንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል፡፡ በቦታው ለጎበኙዋቸው ወዳጆች አንደተናገሩትም ሁሉም ራሳቸው ላይ ጥፋተኝነትን የሚመሰክር ቃል ላይ የፈረሙ ሲሆን ጦማሪ አቤል ዋበላ ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆኑ እስካሁን ሌሎች ሊጎበኘት የማይችሉት ቦታ ላይ አንደቆየ ታውቋል፡፡ 

    የተከሰሱት አና ምርመራ እየተካሄደባቸው ያለው በጻፏቸው ጽሁፎች አይደለም የሚል ክርክር ሲያቀርብ የነበረው ፓሊስም ጽሁፎቻቸውን ማስረጃ አድርጎ እነዳስፈረማቸው ገልጸውልናል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የሪፓርተር ጋዜጣ ሁለት ዜናዎችን በማጋራቱ ብቻ መስረጃ ተብሎበት አንዲፈርም የተገደደ ሲሆን ዜናው የመከላከያ የብሄር ተዋእጾን አና አዲሱን የይቅርታ አዋጅን የሚመለከት ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ስለለውጥ የሚለው በዞን9 ላይ የተጻፉ ተከታታይ ጽሁፎቹ እነዲሁም ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህግ መንገድ ወይስ ምርኩዝ እና ሳንሱር ድሮና ዘንድሮ የሚሉት ጽሁፎች ይገኙበታል ፡፡ 

    የዞን 9 ጦማርያን በጠንካራ አካላዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን አላአግባብ እስሩን ተከትሎ በተለያየ መልኩ አጋርነታችሁን ላሳያችሁ የዞን 9 ነዋሪያን እና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ የተፈጸመባቸው የመብት ጥሰትም ሃሳባቸውን መግለጻቸው ትክክል መሆኑን ያረጋገጠላቸው መሆኑን አስታውሰው መጪውን የህግ ሂደት ለመከታተል እና ለታሪክ ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

    ዞን 9 ጦማርያን ስብስብ በምንም ድብቅ ህገ ወጥ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈን አንደማናውቅ እና ጦማሪ ጓደኞቻችን አንዲፈቱ መጠየቃችንን እንደማናቆም እያስታወስን መጪውን የህግ ሂደት በሚገባ ለመዘገብ እና የፍትህ ስርአቱን ለመፈተሽ ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ አንገልጻለን፡፡ 
    የጦማሪ በፍቃዱና ዘላለም ጽሁፎች ሊንክ ከስር ይገኛል፡፡

    — ኢህአዴግ ሰልጣኑን በምርጫ ይለቃል?

    —ለውጥን መቋቋም እና ለውጥን መፍራት

    —የሥርዐት-ለውጥ-እና-ሃይማኖቶች
     

    — -የ66 ቱ አብዪቶች እና የነጻ ማህበራት ፋይዳ  

    —-ሳንሱር አና ህግ ትላንትና እና ዛሬ
     

    — ሕግ ምርኩዝ ነው ዱላ ? 

    — አብዩት ወይስ አዝጋሚ ለውጥ 



    በዳዊት ሰለሞን


    (በቴክኒክ ብልሽት የዘገየ ኢንተርቪው)

    ከጦማርያኑና ከጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ አምሐ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

    ‹‹ከቅዳሜ አራት ሰዓት ጀምሮ ደምበኞቼ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው መታወቅ አለበት ››

    ‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን››


    የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ የሚመላለስ ጥያቄም ነበር፡፡ከዘጠኙ ታሳሪዎች መካከል ስምንቱን በፍርድ ቤት ሲወክሉ የቆዩት ጠበቃ አምሀም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቀደም ብለው ቅጥር ግቢው ተገኝተዋል፡፡

    አራት ሰዓት እንደሚጀመር የተገመተው ችሉቱ እስከ አምስት ከሩብ ድረስ በሌሎች ጉዳዩች ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነፍጥ ባነገቱ ወታደሮች ታጅበው መምጣት የነበረባቸው ኪቦርድ አንጋቾች እስራት ያልበገረውን ተስፋቸውን እየዘሩ ሊመጡ አልቻሉም፡፡ሁኔታው አግራሞት የፈጠረባቸው የተወሰኑ ጋዜጠኞች ወደ መዝገብ ቤት በማምራት መረጃ ጠየቁ፡፡የተሰማው በግቢው ውስጥ የነበሩትን ጠበቃ አምሀን ጨምሮ ያስገረመ፣ ያሳዘነና ያሳፈረ ነበር፡፡ከጠበቃው ጋር ያደረግኩት አጠር ያለ ቃለ ምልልስ እንደወረደ እነሆ፡፡

    ጥያቄ—ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመጡ በአእምሮዎ ያመላልሱት የነበረው ነገር ምንድን ነው?

    ጠበቃ አምሀ—ምናልባት ምርመራ ባለመጨረሳችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ይላሉ እያልኩ ነበር፡፡ይህንን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በምን አይነት መንገድ እንደሚመልስ ለማወቅም ፈልጌ ነበር፡፡የሆነው ግን በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ያመሩ ጋዜጠኞች ‹‹የልጆቹ መርማሪ ነኝ ያለ ሰው ምርመራዬን በመጨረሴ ለአቃቤ ህግ አስተላልፊያለሁ›› በማለቱ መዝገቡ እንደተዘጋ እንደተነገራቸው እንደነገሩኝ እውነት መሆኑን አጣርቻለሁ፡፡

    ጥያቄ — ሁኔታውን እንደሰሙ ምን አደረጉ?

    ጠበቃ አምሀ — እኛ ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብለን ግቢው ውስጥ ተገኝተን መርማሪው እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያቀርብ መስማት ነበረብን፡፡ በፍጹም እንዲህ አይነት መደረግ እንደሌለበት ቅሬታ እንደተሰማንና የተፈጸመው ነገር ህገ ወጥ መሆኑን ለዳኛው ተናግረናል፡፡

    ጥያቄ — ህገ ወጥ የሆነው ምንድን ነው?

    ጠበቃ አምሀ –ለፖሊስ ልጆቹን ለተጨማሪ 28 ቀናት እንዲያስር ፈቅዶለት የነበረው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡እስካሁን ድረስ ደምበኞቼ የታሰሩት በፍርድ ቤት እውቅና ነው፡፡ከዛሬ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ደምበኞቼ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ እስራታቸው ህገ ወጥ ነው፡፡ፖሊስ ልጆቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ምርመራውን መጨረሱን ማስረዳትና ክስ የሚመሰርት ከሆነም ማሳወቅ ይገባው ነበር፡፡የሚመሰርተው ክስ ዋስትና የሚያስከለክልና የማያስከለክል መሆኑን መወሰን የነበረበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ይህ ሳይደረግ መዝገቡ ተዘግቷል መባሉ ህገ ወጥ ነው፡፡

    ጥያቄ — ከአሁን በኋላ ለደምበኞችዎ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ምንድን ነው?

    ጠበቃ አምሀ — ሰኞ ወይም ማክሰኞ የደምበኞቼ የአካል ነጻነት እንዲከበር ክስ እመሰርታለሁ፡፡ሰኞን የምንጠብቀው እንደተናገሩት ክስ የሚመሰርቱ ከሆነና የት እንደሚመሰርቱ ለማጣራት ነው፡፡

    ጥያቄ –በ‹‹ሃፒየስ ኮርፐስ›› ደምበኞችዎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ክስ የምትመሰርቱት በየትኛው ፍርድ ቤት ነው?

    ጠበቃ አምሀ –ክሱን የምንመሰርተው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው፡፡

    ጥያቄ –ደምበኞችዎን በማዕከላዊ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ነገር ግን እስካሁን ድረስ አቤል ዋበላን ሰዎች ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርጋችኋል?

    ጠበቃ አምሀ — ከዚህ በፊት ልጆቹን በሳምንት አንድ ቀን እንዳናግራቸው ይፈቀድልኝ ነበር፡፡በዚሁ ቀን ስምንቱንም ልጆች የማናገር ዕድል ነበረኝ፡፡ አሁን ግን በአንድ ቀን ማናገር የምትችለው አንዱን ደምበኛህን ብቻ ነው ብለውኛል፡፡እንግዲህ ስምንቱን ደምበኞቼን ለማግኘት አራት ሳምንት ያስፈልገኛል ማለት ነው፡፡ ይህም ፍጹም ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡ደምበኞቼ ከጠበቃቸው ጋር የመገናኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡
    አቤልን በተመለከተ በተወሰነ ደረጃ ከመርማሪዎቹ ጋር ያልተስማማበት ነገር እንዳለ ሰምቼያለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ከእርሱ አንደበት ለመስማት እርሱን መጀመሪያ ማግኘት ይኖርብኛል፡፡

    ጥያቄ –ደምበኞችዎ በምርመራ ወቅት የማያምኑትን ወይም ያልተሳተፉበትን ጉዳይ እንደተሳተፉበት አድርገው ቃላቸውን በሃይል እንዲሰጡ ስለመደረጋቸው ይነገራል፡፡በሀይል የሰጡት ቃል በፍርድ ቤት የሚኖረው ተቀባይነት ምን ያህል ነው? በተለይ በጸረ ሽብር አዋጁ?

    ጠበቃ አምሀ — ለፖሊስ የሚሰጥን ቃል በተመለከተ የወንጀልና የሥነ-ስርዓት ህጉ በዝርዝር ይናገራሉ፡፡ለፖሊስ በሀይል እንደተሰጠ የተነገረበት የተጠርጣሪ ቃል ያን ያህል ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሰዎችም በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ ሊገደዱ አይገባም፡፡

    ጥያቄ — ቀሪዎቹ ደምበኞችዎ የፊታችን ሰኞ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተይዞባቸው ነበር፡፡ ከዛሬው በመነሳት ሰኞ የሚቀርቡ ይመስልዎታል?

    ጠበቃ አምሀ —- አይመስለኝም፡፡ እኛ ግን ቀጠሯችንን አክብረን በቦታው እንገኛለን፡፡ 

    ————– ታላቅ ምስጋና ለጠበቃ አምሀ ————-


    በትላንትናው ዕለት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኞች ከታሰሩ 60ኛ ቀናቸውን (ሁለተኛ ወራቸውን) አስቆጥረዋል እስካሁን ማስረጃ ያልቀረበባቸውና በሕገ-መንግስቱ ሊከበርላቸው የሚገቡ መብቶች ሁሉ ተንደው በማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ እተሰቃዩ ይገኛሉ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኛ ጓደኞቻቸው በምንም አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ያልተሳተፉ ሕገ-ወጥነትን የሚጠየፉና መንግስት ሕገ-መንግስቱን አክብሮ እንዲሰራ የሚወተውቱ ሃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ናቸው፡፡

    Poster Credit Mahilet Solomon

    ያለአግባብ የታሰሩት ጓደኞቻችን ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ዛሬም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
    #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeAsmamaw #Ethiopia

     በእዩብ መሳፍንት 

    ጦማርያንን እና ጋዜጠኞችን ጉዳይ ለማየት የተሰየመው ችሎት ለ4ኛ ግዜ የተቀጠረው ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፤ ያልተያዙ ግብራበሮቻቸው አሉ፤ እንዲሁም ማስረጃዬን አጠናቅሬ አልጨረስኩም በማለቱ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ሁሉም ቀጠሮዎች ፖሊስ ለተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ በምክኒያትነት ያቀረበው እነዚሁኑ ምክኒያቶች ነበር፡፡

    ከሶስተኛው ቀጠሮ ጀምሮ ክሱ ወደ “ሽብርተኝነት” የዞረ በመሆኑ ጉዳያቸውና የቀጠሮ አሰጣጡ በዚሁ ህግ መሰረት መካሄድ አለበት፡፡ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 20/3/ መሰረት ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የ28ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጠው እንደሚችልና ይህ ግዜም በድምሩ ከ4 ወር ሊበልጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ የዚህ አንቀፅ ዋናው አላማውም ለፖሊስ በቂ የምርመራ ጊዜ መስጠትና ተጠርጣሪውም እንዳይጎዳ የፖሊስን የምርመራ ጊዜ መገደብ ነው፡፡
    ፖሊስ የጠረጠረው ወንጀል ምንም ያህል ውስብስብ ቢሆን ከ4 ወር በላይ ሊፈቀድለት አይችልም፡፡ እስከዛሬ ቀን ድረስ ጓደኞቻችን ለ52 ቀናት የታሰሩ ሲሆን ፖሊስ ግን በነዚህ ቀናት ይህን ሰርቻለሁ ያለው አንድም ነገር የለም፡፡ አንድ አይነት ምክኒያት በመስጠት ብቻ ይጠይቃል ፍ/ቤቱም ይፈቅዳል፡፡ ባሁኑ ችሎት ለየት የሚለው ነገር ዳኛዋ ለፖሊስ ቀጠሮውን የሰጡት ከከባድ ማስጠንቀቅያ ጋር መሆኑ ነው፡፡ (ግዴላችሁም ሴት ዳኞች ሳይሻሉን አይቀሩም)


     

    ፖሊስ የሽብር ህጉን አላማ በማሳት የምርመራ ጊዜውን በአግባቡ እየተጠቀመበት አለመሆኑን ከዚህ በላይ ማሳያ አያስፈልግም፡፡ በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች አንድ አይነት የማይረባ ምክኒያት በማቅረብ ቀጠሮ ማራዘምን መጠቀም የክሱን ፓለቲካዊነት ያጎላዋል፡፡ ለዚህ ነው የፍትህ አካላት ፖሊስን ጨምሮ ከገዢው ፓርቲ ተፅኖ ነፃ አይደሉም የምንለው፡፡ የገዢዎችን ፊት እያየ የሚሰራ የፍትህ አካል መቼም ገለልተኛ ስራ መስራት አይችልም፡፡ ኢህአዲግም ከሀገር አንድነት በመቀጠል በእምብርክክ ያስኬደው እና ለፓለቲካዊ ጥቅሙ እየተጠቀመበት ያለው የፍትህ ስርአቱን ነው፡፡

    የሆነው ሆኖ ፖሊስ በማይረባ ምክኒያትም ቢሆን ባቀረበው ጥያቄ ሌላ የ28 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ የሰው ክብር እና ሉአላዊነት (autonomy) በረከሰበት ሀገር የ28 ቀናት ተጨማሪ እስር ምንም ላይመስል ይችላል፡፡ ምክኒያቱም እውነተኛውን ነፃነት በተመለከተ እኔና የዞን ዘጠኙ አጥናፍ ሁለታችንም ታሳሪዎች ነን፡፡ የእስር ቤቱ ስፋት እና ያለንበት ዞን ቢለያይም፡፡
    ከምሬቱ ወደ ህግ አስተያየቱ ስመለስ ፍ/ቤቱ የዛሬ 28ቀንም በዚሁ ሰንካላ ምክኒያት ተጨማሪ የግዜ ቀጠሮ አይሰጥም የሚል እምነት የለኝም፡፡ እኔም ገራም የሆነውን የጠበቃ አምሀን ቃል ልዋስና ሂደቱን በሚመለከት

    “ብሩህ ነገር ይታየኛል ለማለት ባለመቻሌ አዝናለሁ”


    ከአምባገነን ስርአት ፍትህን መጠበቅ ሞኝነት ነውና፡፡ ኢህአዴግ ማሰር እንጂ መፍታት የሚያስችል የሞራል የበላይነት የለውም፡፡ ተፈጥሮውም አይፈቅድለትም፡፡
    ብዙ ወገኖች ጥሩ ዜና ጠብቀው ፍ/ቤት መገኘታቸውን ሳይ አዝኛለሁ ለእኔ የዋህነት እና የስርአቱን ባህሪይ ጠንቅቆ አለማወቀ ነው፡፡ በሚቀጥለውም ከዚህ የተሻለ ነገር ይጠበቃል ብየ አላስብም፡፡ የዚህን የአምባገነን ስርአት ባህሪ የታሰሩ ጦማሪያኑም በሚገባ ያውቁ ነበር፡፡ እኔ ጀግኖች ናቸው የምላቸው የሚደርስባቸውን እያወቁ ይህንን መንገድ በመምረጣቸው ነው፡፡
    ውጤ ቱ ምንም ይሁን ምን አሁንም ቢሆን ጩኀታችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ ዝም የሚያስብል ህሊና የለንምና፡፡ 

    ማስታወሻ
    በመጨረሻም ፅሁፉ በብስጭት፤ በቁጭት፤ በንዴትና እና በአቅም ማጣት የተፃፈ ስለሆነ ከህጉ ይልቅ በፖለቲካ ላይ ካተኮርኩ አትዘኑብኝ፡፡ (ለነገሩ ጉዳዩን ቀድሞ የቀላቀለው ራሱ ኢህአዴግ ነው) 

    #FreerZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Ethiopia

    የዞንዘጠኝ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ! 

    ዛሬ አራዳ “ፍርድ ቤት” አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት
    ናትናኤል ፈለቀ
    አጥናፍ ብርሃኔ
    ዘላለም ክብረት
    እንዲሁም
    ጋዜጠኞቹ
    ኤዶም ካሳየ
    ተስፋዓለም ወልደየስ
    አስማማው ሀይለጊዮርጊስ ላይ ተጨማሪ 28 “የምርመራ ቀናት” ሲፈቀድ ፣ ፍርድ ቤቱ የፍትህ ስርአቱ መፋጠን እንዳለበት እና ከዚህ በሁዋላ የፓሊስን ምክንያቶች እንደማይቀበል አስጠንቅቋልም ተብሏል። ሁሉም ታሳሪዎች በጥሩ መንፈስ ላይ እንደሆኑ በቦታው የነበሩ ወዳጆቻችን አስተውለዋል።

    ማስታወሻ
    የጦማርያኖቹ እና የጋዜጠኞች እስር ፓለቲካዊ መሆኑን እና ምንም ወንጀል አለመስራታቸውን እያስታወስን ዛሬ ፍርድ ቤት ለተገኙ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የዞን ዘጠኝ ወዳጆች ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። 

    #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Ethiopia


    ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፊት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ 7 ሰዓታት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡
    በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።
    የጦማሪዋን ወላጅ እናት እነዲፈርሙ ያግባቡ ቢሆንም ወላጅ እናትዋ ከክፍሏ እና ሌላም ቦታ በመፈተሽ ስታገኙ ያየሁት ወረቀት ላይ ፈርሜያለሁ ይህ ግን ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ያልነበረ እና እዚህ ያልተገኘ ሌላ ወረቀት ነው ሲገኝም አላየሁም በማለት አልፈርምም ብለዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ፈታሾች ተጨማሪ የሰው ሃይል ደውለው በማስጠራት ለማግባባት ቢሞክሩም ስላልተሳካላቸው ይዘዋቸው የመጡትን የራሳቸውን ሁለት ምስክሮች ብቻ አስፈርመው ባለቤትዋ ለመፈረም ፍቃደኛ አይደሉም ብለው ቤቱን ለቀው ሄደዋል፡፡ ከፓሊስ ጋር የመጡት ምስክሮች አንደኛው አድራሻቸው በብርበራ ምስክርነት ዶክመንቱ ላይ ያልተጻፈ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል ፡፡
    በብርበራው ወቅት በነበራቸው 7 ሰአት ቆይታ የጦማሪዋን መጸሃፍት የጉዞ ትኬቶች የስልጠና ማንዋል እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ወረቀቶች የወሰዱ ሲሆን ማብሰያ ክፍል ከፍሪጅ ጀርባ አገኘነው ካሉት ወረቀት ግን ቤት ውስጥ ያልነበረና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት በመሆኑ እናትዋ ተናግረዋል፡፡
    የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አባላት ከየትኛውም በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑና ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እነዲሁም አነዚህ ድርጅቶች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ትችቶቻቸውን ሲያቀርቡና ሲቃወሙ የሚታወቁ ቢሆንም ሲሆን በተያዙት አባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስገድዶ ለሃሰተኛ መረጃ እንዲፈርሙ የማድረግ ተግባር ሳያንስ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ ማስረጃን እንደተገኘ አድርጎ የማቅረቡ ተግባር መንግሰት ይታማበት የነበረውን የፓለቲካ ውንጀላን በሽብር የመቀየር ክስ በተግባር እንድናይ ያስቻለን ነው ፡።
    በመሆኑም አሁንም ቢሆነ ጦማሪ ጓደኞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጻቸው ውጪ ምንም አይነት የወንጀልም ሆነ ሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው እያስታወስን መንግስት ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አንዲፈታ አሁንም አንጠይቃለን፡፡