እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች […]

– ሕወሓት አልሸባብን ሽፋን አድርጎ ፍንዳታ ለመፈጸም እንዳቀደ መረጃዎች ያሳያሉ። – አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ላለማጣት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራች ነው። – አልሸባብ ላይ ማሳበብ ለምን አስፈለገ ? በምስራቅ አፍሪካ ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት የአሸባሪ ቡድኖች ስሙ በዋነኛነት የሚጠቀሰው አልሸባብ በቡድን ደረጃ የታጠቀ ሲሆ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የሕወሓት ቡድንም ሌላኛው ነው። እንዲሁም ሻእቢያ በግርግር መሃል ለመሹለክለክ […]

“ልዩነት የግድ ጥላቻን ወይም ድብድብን ማስከተል አለበት ብለው የሚያምን እና የሚያስብ በድርጊቱም የሚገፉ ካለ ከባድ ስዕተት ነው፡፡ ፣ልዩነትን በአንድ ጊዜና ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በሰለጠነና በሰከነ አካሄድ በውይይትና በሀሳብ ልውውጥ ማጥበብ ይቻላል፡፡” ለዚህም ይመስላል አንድነት ፓርቲ ውስጣዊ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ባይባልም መሠረታዊ ችግሩን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቻለው፡፡ የዚህም ጥሩ ማመላከቻ የሚሆነው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ […]

ይህ በአቶ ነሲቡ ስብሃት የተፃፈ መጽሓፍ በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ በነበረው አረመኔያዊ ሥርዓትና ሥርዓቱን ሲታገል በነበረው ኢሕአፓ የተመራው ቆራጥ ትውልድ መካከል የተካሄደው መራራ ትንቅንቅን በዝርዝር መረጃዎች አስደግፎ ያቀርባል። ስለሆነም፤ በዛን ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ማለት፣ በአንድ በኩል ላገርቷ አንድነት፣ ለህዝቧ ነፃነት፣ ፍትሕና እኩልነት ለመታገል ቆርጦ የተነሣ ትውልድ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝቡን ትግል አጨናግፎ የራሱ ፍላጎት በህዝቡ […]

የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ። በጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል። ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ […]

አንድነት አዲስ ወጣት አመራር ይዞ ብቅ ብሏል። አቶ በላይ ፍቃዱ። ከዚህ በፊት በተከበሩ ዶር ነጋሶ ጊዳዳና እና የተከበሩ ኢንጂነር ግዛቸው አመራር ወቅት የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በማጠናከር፣ በአዲስ አሰራና በአዲስ የትግል ግለት አዲስ ጉዞ ተጀምሯል። የአንድነት ፓርቲ በአገሪቷ አራቱም ማእዘናት መረቡን የዘረጋ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ከተደረገ ኢሕአዴግን ማሸነፍ የሚችል፣ ብዙ አመራር አባላቱ እየታሰሩበትና ከፍተኛ ጫና እየደረሰበትም፣ […]

የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እስራኤላዊውን ነቢዩ ኤርምያስን ‹‹አልቃሻው ነቢይ›› በሚል ሰቆቃና ምሬት፣ ዕንባና ኀዘን ዕጣ ፈንታው የሆነበት የመከራ ሰው ሲሉ በዚህ ቅፅል ስም ይጠሩታል፡፡ ለነገሩ ራሱ ነቢዩም ቢሆን ስለ እስራኤል፣ ስለ እናት ምድሩ የታሪክ ስብራት አሊያም ፕሮፍ እንደሚሉት ‹‹የታሪክ መክሸፍ››፣ ስለ ሕዝቦቹ ስደት፣ መከራና ውርደት አነባ ዘንድ ምናለ ዓይኖቼ ሳያቋርጥ እንደሚፈልቅ የምንጭ ውኃ በሆኑልኝ ሲል የለመነና […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አቶ በላይ ፍቃደን የድርጅቱ ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል። ከሰባት ወራት በፊት ድርጅቱን እንዲመሩ የተመረጡት ኢንጂነር ግዛቸው ፣ “ወጣቶችን ወደ አመራር አመጣለሁ፣ ወጣቶችን ባካችሁ አቅማችሁን አጎልብቱና ተኩኝ” በማለት ለወጣት አመራሮች ሃላፊነታቸውን ለማስረክብ ፍላጎት እንደነበራቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ቃላቸውን በመጠበቅ አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት መምጣታቸው ትግሉን ይረዳል የሚል እምነት ስላደረባቸው ኢንጂነር ግዛቸው፣ […]

ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ […]

ጥቂት የሕወሓት የዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ሠራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ በሚሰጣቸው የስኮላርሺፕ ገንዘብ የደለቡ የስርዓቱ ደጋፊዎች በሰለሞን ተካልኝ መሪነት በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ ዛሬ ሰልፍ ወጡ። በተመሳሳይም የአሜሪካ መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት ኢምባሲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰውን የስርዓቱን ተላላኪ ከሃገሩ በማባረሩ ለዚህም ምስጋና ለማቅረብ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመንት ተመሳሳይ ሰልፍ አድርገዋል። ሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን […]

የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና ጽፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም በመድረክ የስ/አስፈጻሚና የፋይናንስ ተግባር ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ አየለ ሥዩም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከመድረክ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡ አቶ አየለ ስዩም ከ 1986 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ከደቡብ ህብረት እየታገሉ የነበሩና በ1997 ዓ.ም በተወለዱበት አካባቢ ሃዲያ ለፓርላማ […]

ዶ/ር ጳውሎስ አለፈ፤ የቀብር ስነ ስርዓቱ የፊታችን ቅዳሜ በቦስተን የሚፈጸም መሆኑ ታውቋል!! የቀብሩን ዝርዝር መረጃ እናዳገኘን እናስታውቃለን። ደግነትን፣ ለአገርና ወገን ተቆርቋሪነትን፣ በሙያው ለሚሳቃዩ ወገኖች ነፃ የህክምና እርዳታ መስጠትን፣ አክብሮት የተሞላበት ትህትናና የሰዎችን ሃሳብ በዝምታና ትእግስት የማዳመጥን፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በበሳል ሁኔታ የማስረዳትና የመተንተንን፣ ለኢትዮጵያና ለዜጐቿ ዘወትር በማሰብ ከተገፉና በጭቆና ስር ለሚማቅቁ ወገኖች በገንዘብና በሙያው ፍፁም […]

ያለፈው የ2006 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ከዘጠና ሰባት አመት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ፣ ለሕዝቡ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ፣ ከፍተኛ አገር አቀፍና ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል። በባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በጊዶሌ፣ በጂንካ, በአርባ ምንጭ ፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በወላይታ ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍቼ በመሳስሉ ከተሞች የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ንቅናቄ ፣ ብዙዎችን ለትግሉ ለማነሳሳት የቻለ ሲሆን፣ የፓርቲው ተቀባይነት […]

ለሰሚም ግራ ሆነ አማርኛ ይመስላል-አይደል…ነገሩ ግን ወዲህ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በ2006 ሚያዚያ 5 በቶኩማ ሆቴል ከአዳማ ዩኒቨርሲቴ ተማሪዎችና ከከተማው ደጋፊዎቹ ጋር ውይይትና በእለቱም አዲሳባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን በመጋበዝ በፖለተካዊ ፍልስፍና ላይ በጥያቄና መልስየዳበረ ፓናል ተካሂዶ ነበር፡፡በፕሮግራሙ ላይ ከዋናው ቢሮ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እናተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ያፓርቲው ሕ/ግ […]

በኦሮሚያ ክልል መቱ ዞን የአንድነት ፓርቲ የድ/ጉ/ኃላፊ የሆኑት አቶ ታመነ መንገሻ ጳጉሜ 4 ቀን ታስረው እንደነበረና ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በዋስ እንደተለቀቁ በመለቃቸውም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ካድሬዎች ለምን ተለቀቁ መታሰር አለባቸው በማለታቸው በድጋሚ መታሰራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ አይዘነጋም፡፡ አቶ ታመነ መንገሻ የታሰሩት አማራ ይውጣ ብለሃል በሚል ሰበብ እንደሆነ ይህን ተናገሩ በተባለበት ወቅትም ታመው አልጋ […]

ትክክለኛውን የቀጠሮ ቀን ለማወቅ አልተቻለም (ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 22 ነው ሲሉ፤ ፖሊስ ጥቅምት 20 ነው ብሏል) ዘሬ መስከረም 22/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ኃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ የአረና ም/ የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ […]

በፋሽሽቱ ወያኔ ከጋምቤላ ክልል በግፍ የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የተረፉት አማሮች ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መጥተዋል፡፡ በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ አቶ በለጠ ጌታቸው ጎጃም ቢቸና አካባቢ የመጡ የግራ እጃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀበሌ ከወሎ መካነሰላም ቦረና አካባቢ የመጡ አቶ ገበየሁ ኮስትር በጀርባቸው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ በጥይት ከተመቱ በኋላ ጥይቱ በሰውነታቸው ውስጥ […]

መስከረም 25 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ምክር ቤት ወጣቶች፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር የእውቅና ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወቃል። አስተዳደሩ ደብዳቤው በደረሰው በ48 ሰዓት መልስ ሳይሰጥ ዛሬ መስከረም 22 ቀን፣ በቂ ቅስቀሳ ሳይደረግ፣ «ነገ መጥታችሁ፣ የእውቅና ደብዳቤ አስገቡና ሰልፍ ማድረግ ትችላላችሁ» የሚል መልስ እንደሰጠ ለማረጋገጥ ችለናል። የአዲስ አበባ አንድነት ምክር ቤት […]

ነገ መስከረም 22 ቀን በ”ሽብርተኛ” ክስ የተከሰሱት አራቱ ወጣት ፖለቲከኞች፣ ሃብታሙ አያለዉና ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነት፣ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ እና አብርሃ ደስታ ከአረና ፣ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ወጣቶቹ ምንም አይነት ክስ እሰከአሁን ያልተመሰረተባቸው ሲሆን፣ ከሐምሌ አንድ ቀን ጀመሮ በማእከላዊ እሥር ቤት ነው የሚገኙት። እስረኞቹ ለምን እንደታሰሩ አያውቁም። ክስ ሳይመሰረትባቸው ነው ለ86 ቀናት የታሰሩት። ፖሊስ መረጃ ገና […]

ኢትዮጵያዉያኖች በኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረጉት የተቃዉሞ ሰልፍ፣ ኮከብ ያለበትን የአገዛዙ ባንዲራ አንስተው፣ የጠራዉን የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ መትከላቸው ይታወቃል። መሳሪያ ያልታጠቁ፣ ወረቀትና ባንዲራ ብቻ በእጃችቸው የያዙ ሰላማዊ ዜጎች “ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንፈልጋለን፣ ወንጀለኞች አይደለንም” በሚሉበት ጊዜ፣ አንዱ የኤምባሲ ጠባቂ፣ ጥይት መደቀኑና ሶስት ጊዜ መተኮሱ፣ በኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሜዲያዎች ሁሉ በስፋት እየተዘገበ ነው። […]

መምህር ብርሃነመስቀል ንጉሤ ዘውዴ በአክሱም ዩኒቨርስቲ መምህር ሲሆን በአዳማ የአንድነት ፓርቲ አባል ነው የመጀመሪያ ዲግሪውን በ2001 ዓ.ም ከአዳማ ዩኒቨርስቲ በፔዳጎጂካል ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪውን በ2004 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሂዩማን ሪሶርስ ኤንድ ኦርጋናይዜሽናል ዴቨሎፐመንት ኢን ኢዱኬሽን አግኝቷል፡፡ አስከፊውን የኢህአዴግ ሥርዓት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተቀላቀልኩት የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ነው:: በ1997 ዓ.ም በምስራቅ ሸዋ ናዝሬት የመኢአድ አባል […]

“ በሽብር” ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የፓርቲ አመራሮች ነሐሴ 27 እና ነሐሴ 29 ቀን አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለ3ኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሐብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ኃላፊ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት ም/ሰብሳቢ እና አብርሃ ደስታ የአረና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ሐሙስ […]

በትግራይ ክልል በተለያዩ ከተማዎችና ወረዳዎች የተደረገው ስልጠና በተሳታፊዎች ተቃዎሞ የገጠመውና ሰልጣኞችን ያስተባበረና ለአሰልጣኞቹ ፈተና የሆነ እንደነበር ከስፍራው ዜናውን ያደረሱን የዜና ምንጫችን ገልጸዋል፡፡ ገበሬዎችን እያታለላችሁ እኛን ለማታለል መጣችሁ አንድ ፓፓያ ቀርጻችሁ ልማት አለ ባገሩ በማለት 50 ጊዜ በቴሌቪዥን እያሳያችሁ፣ ዲሞክራሲ በሌለበት መልካም አስተዳደር በሌለበት ምን ልትነግሩን ምን ልትሰብኩን ነው የመጣችሁት በማለት የመድረክ መሪዎችን በጥያቄ ያስጨነቀ እንደነበር […]

በትግራይ ኣፅቢ 5 ጣልያናውያንና 2 ኢትዮዽያውያን በሕወሓት ፖሊሶች ለሰዓታት ታገቱ። የህወሓት ፖሊሶች ጋዘጠኞቹን ኣግቶ፣ ፈትሾ፣ ኣንገላትቶ ለቋቸዋል። ትናንት ሰኞ 19/ 01 / 2007 ዓ/ ም ለስራ ጉዳይ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በኣንድ ጣልያን የሚገኝ ቴሌቭዥን ጣብያ የሚሰሩ 4 ጣልያናውያን ጋዜጠኞችና ኣንድ ሌላ ኣገር ጎብኚ ጣልያናዊ ከሁለት ኣብሯቸው የሚሰሩ ኢትዮዽያውያን ጋራ ወደ ተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች የጎበኙ ሲሆኑ […]

”መሣርያውን ወደሚከራከሩት ሰዎች ደገነ እና ተኮሰ” ”He points the weapon at others who argue with him and fires” ሮይተርስ ከዋሽግተን ዲሲ ዛሬ የዘገበው። ዛሬ መስከረም 19፣2007 ዓም ዋሽግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተቃዋሚ ኢትዮጵያውያን ቁጥጥር ስር ውሎ ባለ ኮከቡ ሰንደቅ ዓላማ በነፃው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተቀይሯል። ተቃውሞውን አስመልክቶ ኢሳት ዘግይቶ በለቀቀው ተጨማሪ ዘገባ ተቃዋሚዎቹ በኢምባሲው […]

ባለፈው ዓመት ሃገራችንንም በሚመለከት አስደሳችም፣ አስከፊም፣ አስደናቂም፣ አናዳጅም ተግባሮች ተፈፅመዋል። አሮጌው ዓመት ለአዲሱ ዓመት ቦታውን ሲለቅ ፈጣሪ አምላክ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የመግባቢያና ችግሮቻችንን ሁሉ የምንፈታበት ዓመት ይሁን ማለታችን አልቀረም። ግን የዚህ ምኞታችን ፍፃሜ ከቅርብነቱ ሩቅነቱ በክፍፍላችን ምክንያት የጎላ ነው። አንዳንዶቹ ቅራኔዎቻችንን መፍትሔ ለማግኘት ስናጠናቸው የችግሩን መንስዔ ለማግኘት እንኳን የተጠላለፉ በመሆናቸው በጣም የሚያስቸግሩ መሆናቸውን እንረዳለን። […]

አገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ፣ በረእቡ መስከረም 7 እትሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከቱርክ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ አናዶሉ ጋር በቅርቡ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ለአንባቢያኑ አቅርቧልል። ከቃለ መጠይቁ፣ በተለይም በምርጫውና በፖለቲካ እስረኞች ረገድ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የመለሱትን ቀንጭቤ ለማቅረብ እወዳለሁ። “ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ዓመት በአገር አቀፍ ምርጫ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ምርጫውን የሥርዓቱ አካላት በሕግና በደንብ እንዲሠሩ […]

በስታቲስቲክስ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ዘገባ ማቅረብ ባልችልም፤ ባካባቢዬ ያለውን ሀቅ ተከታትዬ የሚኖረኝ ግንዛቤ፤ መንገዱኝ ይከፍትልኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሰብስቤ፤ ይሄ ነው ብዬ የማቀርበው የጥናት ዘገባ የለኝም። ውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ስለሚፈልጉት ወይንም ስለሚያደርጉት ተጨባጭ ማስረጃ ያጠራቀምኩት ዝርዝር የለኝም። ነገር ግን፤ በመጀመሪያ እኔ ራሴ የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን አካል በመሆኔ፤ በዙሪያዬ ከምገናኛቸው እንደኔው የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለሀገራችን ሁኔታ እወያያለሁ። ለጥቆም […]

ቦስተን መስከረም 17/2007 (ሴፕቴምበር 27፣ 2014 ዓ.ም) የደመራ በዓል በካምብሪድጅ ከተማ 808 Memorial Dr. አጠገብ በሚገኘው ፓርክ በቦስተን እና አካባቢዋ ነዋሪ በሆኑ የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕምናን ዘንድ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተከበረ። በበዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ […]

የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ከትላንት መስከረም 15 ቀን ጀመሮ መሰወራቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። « ዳግም፣ ድህንነቶች መኖሪያ ቤቱድረስ (ኦሎምፒያ) ሰሞኑን በዲኤክስ መኪና መጥተው ያነጋሩትንና ያስፈራሩትን አውግቶን ነበር፡፡ ይህንን ሲያወጋን ግን በራስ መታማመኑ እና ድፍረቱ ከራሱ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ለዛሬጥዋት ፖሊስ ጋር ተጠርቶ ቀጠሮ ቢኖርበትም እሱ ግን ይበልጥ ትኩረት […]

በአንድነት ፓርቲ ወጣቶች አነሳሽነት፣ በአዲሱ የ2007 ዓ.ም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ወጣቶች ኮሚቴ እየተንቀሳቀሰ ነው። እንደለመዱትና እንደከዚህ በፊቱም ሕወአት/ኢሕአዴጎች የዜጎችን ነጻ የመስብሰብ መብት እየረገጡ ፣ ሕገ መንግስቱን እየሻሩ ፣ እነርሱ ከሚፈልጉት ስብሰባ በቀር ምንም አይነት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ጫና እያሳደሩ ነው። የፓርቲው ብሄራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቢሮ ዉስጥ በሚደረጉ ስራዎች ተጠምዶ፣ […]

“ምንም አይነት ደብዳቤ አልደረሰንም” አቶ ማርቆስ ብዙነህ የአ.አ.ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ አንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የህሊና እስረኞችን ለማሰብ በመስከረም 3 እና መስከረም 11 ቀን 2007 ዓ.ም ለማድረግ ያሰብኩት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ሊሳካልኝ ባይችልም፣ በመጪው መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም ግን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅጃለሁ ሲል አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር […]

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሟቹ የመለስ ዜናዊ ሰላባ ከሆኑት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አንዱ ነበሩ። ከ19 ዘጠኝ አመታት በፊት፣ በኩወቤክ ካናዳ የቀድሞ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆን ክሬቲየን፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ በስክቶላንድ የአሁኑ የእንግሊዘ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሮን ፣ የአገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ፣ ክዌቤክና ስኮትላንድ እንዳይገነጠሉ ብዙ የደከሙ፣ የድካማቸውን ፍሬ ያዩ አገራቸዉን እና ህዝባቸውን የሚወዱ መሪዎች መሆናቸውን ያስመሰከሩ […]

ከሁለት ሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የፈጀው ባህርዳር ላይ የተደረገው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ ትናንት መስከረም 14/2007 ዓ.ም በአቶ በረከት ስምኦን ማስጠንቀቂያ መጠናቀቁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ስብሰባውን የዘጉት አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ፖሊስ፣ አቀቤ ህግና ዳኛ ከአስፈጻሚው (ከካቢኔው) ጋር ተስማምቶና እጅና ጓንት ሆኖ መስራ አለበት፡፡ ይህ ነው ልማታዊ የፍትህ ስርዓት፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ […]

ከመስከረም 10/2007 ዓ.ም እስከ መስከረም 12/2007 ዓ.ም በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የማጥመቅ ስልጠና በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኢህአዴግ እንዲመረጥ እንዲሰሩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውና እቅዱን ካላሳኩ ሸዳቸውን መስሪያ ቦታውን እንደሚያጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰልጣኞቹ ‹‹ግብር በዝቶብናል፣ ደንብ አስከባሪዎች በየጊዜው እየመጡ ገንዘብ ይወስዱብናል፣ በየወረዳው የመልካም አስተዳደር ችግር መፍትሄ ልናኝ አልቻልንም፣ ስለዚህ […]

የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች። ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው። በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት […]

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 98 በመቶ የሚሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ፣ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል […]

የፊታችን ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ነገሮች ሳይበላሹና ሳይቆላለፉ ከወዲሁ እንዲታሰብበት ይችን አጭር ጽሁፍ ላቅርብ:: ምርጫ ማለት ከቀረቡ በርካታ አማራጮች መካከል አንዱን መምረጥ ማለት ነው። ሬስቶራንት ስንሄድ አስተናጋጆች ይመጣሉ። ሜኒዩ ይሰጡናል። የምግብ አይነቶች ተዘርዝረው እናነባለን።። ክትፎ፣ ጥብስ፣ ምጥን ሽሮ ..እያለ ብዙ አማራጮች ተደርድረዋል። አንዱን እንመርጣለን። ምርጫ ማለት ይሄ ነው። አማራጮች ካልቀረቡ፣ የተሰጠንን ተመገብን […]