የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ አየለ ሥዩም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና ጽፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም በመድረክ የስ/አስፈጻሚና የፋይናንስ ተግባር ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ አየለ ሥዩም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከመድረክ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡
አቶ አየለ ስዩም ከ 1986 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ከደቡብ ህብረት እየታገሉ የነበሩና በ1997 ዓ.ም በተወለዱበት አካባቢ ሃዲያ ለፓርላማ ተወዳድረው በማሸንፍ ለ 5 ዓመታት 2002 ዓ.ም ህብረትን በመወከል የተወካዮች ም/ቤት አባል የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል።
ዓርብ መስከረም 23 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ 10፡00 ሰዓት በስራ ላይ የነበሩ ሲሆን ወደቤታቸው ከገቡ በኋላ ማታ በድንገት በመታመማቸው ጎተራ አካባቢ የሚገኘው ኢንተርናሽናል የልብ ህሙማን ሆስፒታል ተወስደው ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል፡፡ እሁድ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት አስኮ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዘመድ ወዳጆቻቸው እና የትግል አጋሮቻቸው በተገኙበት የቀብራቸው ስነ-ስርዓት ተፈጽሟል፡፡