ዛሬ ግንቦት ሰባትን አስመልክቶ አንዳንድ የተለቃቀሙ ጨዋታዎችን ለማቅረብ ዕቅድ ነበረኝ ነገር ግን በ”ሙድ” እጦት ጨዋታው ሳያልቅልኝ ቀኑ አለቀብኝ። ስለዚህ ለዛሬ ቢያንስ እንኳን አደረሳችሁ እንባባል። እና ለነገ በሀገርቤቱም በዲያስፖራውም ብሎጋችን “ሙድ ያፈራውን” የግንቦት ሰባት ወሬ እንቃመሳለን። (ማስታወቂያ መሆኑ ነው እንግዲህ) ኢቲቪም “በነገው ዕለት”  አያለ የፕሮግራም ማስታወቂያ ይሰራ የለ እንዴ…? ማን ከማን ያንሳል! በነገራችን ላይ ለኢትዮጵያ ብለን […]

ሰሞኑን ሰለሞን ተካ “ፅናት” በተባለ የሬድዮ ጣቢያው ላይ ጮክ ብሎ ሙስሊም ወንድሞቻችንን በሚመለከት አንድ መግለጫ ሰጥቷል። ሰለሞን የቱ…? ብሎ የጠየቀ ካለ ሰለሞን ዜሮ ዞሮው በሚል አብራራለሁ። መጨመር ካስፈለገም ምን ነካው? የማይባለው ሰለሞን ተካ! ብንለውም ይሆናል። የሚገርመኝ ነገር 1 ይሄ “ፅናት” የተባለው ራዲዮ ጣቢያ አዘጋጁ ራሱ ሰለሞን ተካ ነው። ስጠረጥር ባለቤቱም እርሱ ይመስለኛል። ታድያ እዚህ ላይ […]

ቅዳሜን አባቴ “ሰንበተ ጢኖ” ሲል ይጠራው ነበር። ነገም ዋናው የእረፍት ቀን ነው በነዚህ የእረፍት ቀናት ደግሞ “ክቡር…” ምናምን እያልኩ ከማካብድብዎ ዝም ብዬ መለስ ብልዎትስ ስል አሰብኩልዎ…! አዎና በነዚህ የእረፍት ቀናት እርስዎም ቢሆኑ ዘወትር የማይለይዎትን የክብር ከረባትዎንም ሆነ ያቺ “ማን እንደሰፋት የማያወቁት” ሱፍዎን ወለቅ አድርገው የሆነበት አስቀምጠው እና ቱታዎን ለብሰው ለሃያ አመታት በምቾት እና በድልዎት የተቀመጡባት […]

ጋሽ ግዛው በድፍን ሽሮሜዳ ታዋቂ የነበሩ ሞቅታን እንደገንዘብ እየቆጠቡ የሚጠቀሙ ሰው ነበሩ። እርሳቸውን ሳይሰክሩ ያያቸው ሰው ካለ እርሱ አብሯቸው ያደረ መሆን አለበት፤ በቀረ ግን ሁሌም ሞቅታ ውስጥ ናቸው። ጋሽ ግዝሽ ሁልግዜም ወደቤታቸው የሚገቡት እምቢኝ እያሉም ቢሆን፤ በሰዎች ተደጋግፈው ነው። አንዳንዴም በወሳንሳ! አለበለዛ ሲወድቁ ሲነሱ የሚያዩት አበሳ አይወሳ…! ጋሽ ግዛው በሞቅታቸው ተዓምር ካመጡት ልዩ ልዩ ጠባይ […]

ይቺ ጨዋታ ዛሬ ቀን ላይ ለኢትዮጵያ ተዘጋጅቶ የነበረው ብሎጋችን ላይ ለጥፈናት ነበር። በዋናው ቤትስ ለምን ይቅርባት ተብላ እነሆ እዚህም መጣች! ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ሁልግዜም እከታተለዋለሁ። ወደኔ የሚመጣውን ካላቋረጡት በቀር… ወደፊትም  በትጋት ማየቴን እቀጥላለሁ። ታድያ ሁልግዜም እንዳስደነቀኝ ሁልግዜም እንዳስገረመኝ ነው። እንደውም አሁን አሁን “ከሪሞት” ላይ ወደ ኢቲቪ የሚወስደውን ቁጥር ስጫን በለሆሳስ  “ታምረ ኢቲቪን ልከታተል” እያልኩ ነው። እኔ […]

እኔ ዘወትር ስለመንግስቴ የምጨነቀው፤ እኔ ሁሌም የፀሐዩ መንግስቴ ነገር የሚያቃጥለኝ፣ እኔ ከታማሚ ካድሬዎች ይልቅ ለድርጅታችን ታማኝ የሆንኩት… ሰሞኑን ስለመንግስቴ አብዝቼ ስጨነቅ እና ስጠበብ ቆይቻለሁ። ባለፈው ግዜ በመርካቶው አንዋር መስጂድ ውስጥ ሁለት የመካከለኛው ምስራቅ ወጣቶች “በቁጥጥር ስር” ውለው በኢቲቪ ዜና አይተናቸዋል። ወጣቶቹ “ከኤርፖርት በቀጥታ መርካቶ ሄደው ወረቀት ሲበትኑ እንደነበር” ተነግሮናል። እዚች ላይ አንዳንድ አስተያየቶችን ሰጥቼ ዘወር […]

ባለፈው ግዜ ቼልሲ ከባርሴሎና ጋር ሲጫወት በሩን ጥርቅም አድርጎ በፓስዋርድ ነበር የዘጋው። ለምን ዘጋ ያልን እንደሆነ በርካታ ምክንያቶችን መደርደር እንችላለን። ከእኛ ይልቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ኤርሚያስ የሆነ ነገር ብሎ እንደሆነ እንፈልግ እና እንመልከት። ምንም ካላለም ከቀጣዩ የዋንጫ ጨዋታ ጋር አያይዞ ዘርዘር ያለ አጥጋቢ ምክንያቶች እንደሚነግረን ተስፋ እናድርግ። ትላንት አንድ ፈረንጅ ወዳጃችን፤ “ብሎጌ በተደጋጋሚ ተዘጋ […]

ባለፈው ግዜ መንግስት ቅድመ ምርመራ ወይም የሳንሱርን ትንሳኤ ሊያመጣው እንደሆነ ፍንጭ አግኝተናል ብለን አንዳንድ ጩኸቶችን ጮኸን ነበር። በጩኸታችን ማግስት የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በመላው አለም ተከበረ። ከመላው አለም አክባሪዎች ውስጥ “ወጉ ለምን ይቀራል” ብላ ኢትዮጵያም አንዷ ሆና ነበር። በክብረ በዓሉ ላይ አቶ ሽመልስ ከማል ካልታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር አንድ መድረክ ላይ ተገናኝተው ነበር አሉ። ታድያ አንድ […]

ባለፈው ግዜ መንግስት ቅድመ ምርመራ ወይም የሳንሱርን ትንሳኤ ሊያመጣው እንደሆነ ፍንጭ አግኝተናል ብለን አንዳንድ ጩኸቶችን ጮኸን ነበር። በጩኸታችን ማግስት የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በመላው አለም ተከበረ። ከመላው አለም አክባሪዎች ውስጥ “ወጉ ለምን ይቀራል” ብላ ኢትዮጵያም አንዷ ሆና ነበር። በክብረ በዓሉ ላይ አቶ ሽመልስ ከማል ካልታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር አንድ መድረክ ላይ ተገናኝተው ነበር አሉ። ታድያ አንድ […]

ከዛሬ ስድስት ወር በፊት ወፍራሙ መንግስታችን ተጭኗት “ህልፈተ ህይወት አደረገች” ብለን አዝነን ለቅሶ ተቀምጠንላት የነበረችው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ “እጅ መስጠት የለም ብላ” (ትንሽ እናጋነው ካልድ ደግሞ መቃብሯን ፈንቅላ) በዌብ ሳይት በኩል መምጣቷን ትላት ይፋ አደረገች። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “መንግስታችን እኔ ብቻ ላውራ እናንት ዝም በሉ” በሚል እንድተዘጋ ያደረጋት፤ ተወዳጇ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ ሰማይ […]

[email protected] ውድ የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆቼ እንዴት አላችሁልኝ? “እኔስ አለሁ አለሁ አለሁ እንደምንም እግዜር ያመጣውን ሰው አልችል አይልም” የሚል ዘፈን የሚዘፍንልን ሁነኛ ሞዛቂ አጣን አይደል…? ለማንኛወም አንተ እንዴት ነህ ብለው የጠየቁኝ እንደሆነ እኔው ራሴ አዜማታለሁ! ይህ ደብዳቤ ለቀዳማዊት አዜብ መስፍን በታላቅ ትህትና እና አክብሮት የተፃፈ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ለቤተመንስግስቱ ቤተሰቦች ያነኝን የላቀ ፍቅር እና […]

[email protected] ውድ የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆቼ እንዴት አላችሁልኝ? “እኔስ አለሁ አለሁ አለሁ እንደምንም እግዜር ያመጣውን ሰው አልችል አይልም” የሚል ዘፈን የሚዘፍንልን ሁነኛ ሞዛቂ አጣን አይደል…? ለማንኛወም አንተ እንዴት ነህ ብለው የጠየቁኝ እንደሆነ እኔው ራሴ አዜማታለሁ! ይህ ደብዳቤ ለቀዳማዊት አዜብ መስፍን በታላቅ ትህትና እና አክብሮት የተፃፈ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ለቤተመንስግስቱ ቤተሰቦች ያነኝን የላቀ ፍቅር እና […]

በፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ሆና በምትሰራበት ወቅት “አሸበርሽ” ተብላ የታሰረችው ርዮት አለሙ “ኢንተርናሽናል ውመን ሚዲያ ፋውንዴሽን” የተባለ ድርጅት የሚዲያ ጀግና ሲል ለሽልማት መረጣት። ሽልማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ራስን ለአደጋ አጋልጦ በጋዜጠኝነታቸው ለተጉ ሴቶች የሚሰጥ ሲሆን፤ ከርዮት አለሙ ጋር አንዲት የፓልስቲን እና አንዲት የአዠርባዣን ጋዜጠኞች ለሽልማቱ ተመርጠዋል። እንደሚታወቀው ርዮት አለሙ በአሁኑ ግዜ የገንዘብና የእስር ቅጣት ተወስኖባት በቃሊቲ […]

ከዚህ በፊት ሳይገባኝ “ሪፖርተር” የሚል ማዕረግ ሰጥታኝ የነበረ አንድ ጋዜጣ ነበረች። “ሆመር” ትባላለች። እንዴት በፍቅር ምንወዳት ጋዜጣ ነበረች መሰላችሁ። በአሁኑ ወቅት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ጋዜጣ ወግ ደርሷት “ነብስ ይማር” ለመባል በቅታለች። በዚሁ አጋጣሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የፕሬስ ቀን እየተከበረ ነው አሉ ስላቅ በየፈርጁ ማለት ይሄኔ ነው! ግን እንኳን አደረሰን ማለት ይገባል። በዛች ጋዜጣ ላይ የሚወጣ “ዶሮዋ […]

ከዚህ በፊት ሳይገባኝ “ሪፖርተር” የሚል ማዕረግ ሰጥታኝ የነበረ አንድ ጋዜጣ ነበረች። “ሆመር” ትባላለች። እንዴት በፍቅር ምንወዳት ጋዜጣ ነበረች መሰላችሁ። በአሁኑ ወቅት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ጋዜጣ ወግ ደርሷት “ነብስ ይማር” ለመባል በቅታለች። በዚሁ አጋጣሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የፕሬስ ቀን እየተከበረ ነው አሉ ስላቅ በየፈርጁ ማለት ይሄኔ ነው! ግን እንኳን አደረሰን ማለት ይገባል። በዛች ጋዜጣ ላይ የሚወጣ “ዶሮዋ […]

ይህንን ጨዋታ ስፅፍ ፋሲል ደሞዜ የተባለ አቀንቃኝ “አለ ነገር…” እያለ የሚያንጎራጉረውን ሙዚቃ እየሰማሁ ነው! ልብ አድርጉልኝ ይህ ስጋት ነው እንጂ ቅስቀሳ አይደለም! ምክር ነው እንጂ ቁጣም አይደለም! አክብራቹሁ ብሎጋችንን የምትዘጉ ሰዎች ምክራችንንም ስሙ…! አስቲ ሰሞኑን የሰማኋቸውን አጫጭር ዜናዎች ልንገራችሁ። አንድ በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን” ያሉ ሙስሊሞች ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ […]

ይህንን ጨዋታ ስፅፍ ፋሲል ደሞዜ የተባለ አቀንቃኝ “አለ ነገር…” እያለ የሚያንጎራጉረውን ሙዚቃ እየሰማሁ ነው! ልብ አድርጉልኝ ይህ ስጋት ነው እንጂ ቅስቀሳ አይደለም! ምክር ነው እንጂ ቁጣም አይደለም! አክብራቹሁ ብሎጋችንን የምትዘጉ ሰዎች ምክራችንንም ስሙ…! አስቲ ሰሞኑን የሰማኋቸውን አጫጭር ዜናዎች ልንገራችሁ። አንድ በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን” ያሉ ሙስሊሞች ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ […]

እኔ የምለው ወዳጄ ሳሱር ነብሴ ድጋሚ መጣች አይደል እንዴ!? እሰይ! እልል በሉ እንጂ። ድግስ አትደግሱም እንዴ!? ጠላው ይጠመቅ፣ ድፎው ይደፋ፣ ቡናውም ይፈላ፣ ፈንዲሻው ይፈንደሽ፣ እጣን ሰንደሉ ተጫጭሶ ቄጤማውም ይጎዝጎዝ። በዓሉ የትንሳኤ በዓል ነውና ሁሉም ሰው ይደሰት። አዎ አሁን ወቅቱ የትንሳኤ ነው። ሞቱ ተቀበሩ ያልናቸው ችግሮቻችን በሙሉ በስንተኛው ቀን እየተነሱ ዳግም ህያው እየሆኑ ነው። ይህ እንዲሆን […]

እኔ የምለው ወዳጄ ሳሱር ነብሴ ድጋሚ መጣች አይደል እንዴ!? እሰይ! እልል በሉ እንጂ። ድግስ አትደግሱም እንዴ!? ጠላው ይጠመቅ፣ ድፎው ይደፋ፣ ቡናውም ይፈላ፣ ፈንዲሻው ይፈንደሽ፣ እጣን ሰንደሉ ተጫጭሶ ቄጤማውም ይጎዝጎዝ። በዓሉ የትንሳኤ በዓል ነውና ሁሉም ሰው ይደሰት። አዎ አሁን ወቅቱ የትንሳኤ ነው። ሞቱ ተቀበሩ ያልናቸው ችግሮቻችን በሙሉ በስንተኛው ቀን እየተነሱ ዳግም ህያው እየሆኑ ነው። ይህ እንዲሆን […]

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመሰገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በምታወጣቸው ፅሁፎች በፍርድ ሂደቱ ላይ ጣልቃ ገብተሃል  ተብሎ ተከሶ እንደነበር ይታወሳል። ተመስገን “የተከሰሱኩት አለ አግባበብ ነው ነው” በሚል ተከራክሮ ፅሁፉ ተከሳሾች የሰጡት መሆኑን አስረድቶ ነበር። ይህንንም ለማረጋገጥ አቃቤ ህግ አበበ ቀስቶ (ክንፈሚካኤል ደበበን) ለምስክርነት ጠርቶት የነበረ ሲሆን መስካሪውም “በፅሁፉ መጠየቅ ካለብኝ የምጠየቀው እኔ ነኝ። ሃሳቤን በፍርድ ቤት […]

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመሰገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በምታወጣቸው ፅሁፎች በፍርድ ሂደቱ ላይ ጣልቃ ገብተሃል  ተብሎ ተከሶ እንደነበር ይታወሳል። ተመስገን “የተከሰሱኩት አለ አግባበብ ነው ነው” በሚል ተከራክሮ ፅሁፉ ተከሳሾች የሰጡት መሆኑን አስረድቶ ነበር። ይህንንም ለማረጋገጥ አቃቤ ህግ አበበ ቀስቶ (ክንፈሚካኤል ደበበን) ለምስክርነት ጠርቶት የነበረ ሲሆን መስካሪውም “በፅሁፉ መጠየቅ ካለብኝ የምጠየቀው እኔ ነኝ። ሃሳቤን በፍርድ ቤት […]

በአንድ ቤተሰብ ውጥ የሚኖሩ ሰዎች ነበሩ። የቤተሰቡ ሃላፊ የሆኑት አባወራ ሲያገኙ በድፍረት ሲያጡም በሌላ ድፍረት ጠጥተው ሞቅ ብሏቸው ነው የሚገቡት። ስጠረጥር የዘንድሮ ኑሮ እንደምንም ብለው ሞቅታ ውስጥ ካልተደበቁ በስተቀር እንደማይቻል ገብቷቸዋል። አሁንም ስጠረጥር አባወራው በዱቤም ይሁን፣ በብድርም ይሁን፣ በቅልውጥ መጠጥ ቤት ካላመሹ በቀር በጊዜ ቤታቸው ቢገቡ የቤተሰቡ አባላት የሚጠይቋቸውን ጥያቄ መመለስ እንደማይችሉ  ስለሚረዱትም ይመስለኛል። ታድያልዎ […]

ሰሞኑን ከተሰሙ አስደንጋጭ ዜናዎች ውስጥ የሚከተለው ይገኛል… “በዛሬዉ እለት በአርሲ አሳሳ ከተማ የጁምአ ሰላት ከተሰገደ በኋላ ሼህ ሱዑድ በአንድ መስጂድ ዳዕዎ አድርገዉ ሲወጡ በፓሊስ በመያዛቸዉ፤ የአካባቢዉ ሙስሊም ህብረተሰብ “ሼሁ ለምን ይታሰራሉ ምንም ጥፋት አልፈፀሙም” በሚል ለማስለቀቅ ሲሞክሩ ከፓሊሶች ጋር በተፈጠረዉ አለመግባባት ፓሊስ በከፈተዉ ተኩስ እስካሁን ባለዉ መረጃ መሠረት አምስት(5) ሰዎች መገደላቸዉና ብዙ ሰዎች መቁሰላቸዉን የአካባቢዉ […]

ዛሬ ሰንበት ነው። እንዴት አደራችሁ!  ነገ ጠዋት በሰፊው እስክንገናኝ  ለሰንበት ታኽል ግን የሆነች ነገር መሰንዘር ግድ ይላል ብዬ አሰብኩ። አስቤስ …? ትላንት የበሀይሉ ገ/ኢግዚአብሔር አዲስ መፅሐፍ “ኑሮ እና ፖለቲካ” እጄ ገባ። እንዴት እንዴት አይነት ጨዋታዎችን ይዟል መሰለችሁ!? በእውነቱ  ዛሬ በማውጊያችን አንድ ለሰንበት ጣል ባደርግ ደስ እንደሚላችሁ ርግጠኛ ሆንኩ… ሆኜም እነሆ አልኩ፤ የቢል ነገር እንደ ትናንት […]

አንጋፋው ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር ነብሱን ይማረው እያልን ማውራት ከጀመርን ሰማንያ ቀን እንደሚሞላው በቅርቡ አንድ ወዳጃችን በለጠፈው ማስታወሻ አስታውሰናል። እንደውም ዛሬ ሳይሆን አይቀርም… የሆነ ሆኖ ከዚህ ቀጥሎ ጋሽ ስብሀት ፅፎት በሳቅ ፍርስ ካደረገኝ ጨዋታ መካከል የሚከተለውን እንድናወጋ ወደድኩ…  እንደሚከተለው አስታውሳለሁ! በቀድሞ ግዜ ከነበሩ “ዋና ሰዎች” መካከል አሉ የሚባሉ አንድ ባለስልጠን ቀኟዝማች ይሁኑ ግራ አዝማች ወይም […]

ትላንት ለሊቱን በሙሉ ማውጊያ ብሎጋችን ኢትዮጵያ ውስጥ የማይዘጋበትን መላ ሳንሰላስል ነበር። ታድያ አንዳች ዘዴ መጣልኝ። ልማታዊ ጨዋታዎችን  መጨዋወት ጥሩ ዘዴ እንደሚሆን አስብኩ። ታድያ ልማታዊ ዜና ከየት ይመጣል…? ብዬ ሳስብ፣ ሳስብ፣ ሳስብ… አንድ ወዳጃችን በዚህ ሳምንት ውስጥ በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ የለጠፈው አሪፍ ልማታዊ ዜና ትዝ አለኝ። ወዳጄ ስሙ ጠፋኝ… (ምን የስደተኛ ነገር እንኳን የሰው ስም […]

ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዮት አለሙ “አሸብረሽናል” ተብላ አስራ አራት አመት እስር እና ሰላሳ አምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባት (መቼም የዛሬ ፈራጅ ከየት ይመጣል ብሎ አያስብም…) ብቻ በአሁኑ ሰዓት በቃሊት እስር ቤት ትገኛለች። ርዕዮት ከፍርዱ በፊት “ኤልያስ ክፍሌ አሸባሪ ነው” ስትይ መስክሪ እና ትፈቻለሽ ተብላ፤ በማስፈራራትም በማባበልም ብትጠየቅ አሻፈረኝ “እኔ የማውቀው ኤልያስ ጋዜጠኛ እንደሆነ ነው። …

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎችን ቃል በጋዜጣህ ላይ አትመሃል ይህም በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት ነው ተብሎ ተከሶ እንደነበር ይታወቃል። (ካልታወቀም አሁን ይታወቅ… ልል ነበር በዜና ላይ አይቀለድም ለካ…) ተሜ የተከሰሰበት ጣልቃ መግባት ክስ የአንዷለም አራጌን፣ የእስክንድር ነጋ፣ የናትናኤልን እና የአበበ ቀስቶን ፅሁፍ በጋዜጣህ ላይ በማተምህ የሚል ሲሆን፤ …

ሰንደቅ ጋዜጣ በዛሬ እትሟ “አዲስ ራዕይ” የተሰኘውን የኢህአዴግ “ቅዱስ” መፅሀፍ ጠቅሳ እንደዘገበችው ከሆነ፤ ገዢው ፓርቲ ምንም እንኳ ላለፉት ሃያ አመታት ሲገዛ እና ሲሸጠን የቆየ ቢሆንም የተሳካለት ግን ግማሹን ያኸል ብቻ መሆኑን እንዳመነ አውስታለች። ይህንን የሰሙ ሽሙጠኞችም ኢህአዴግ አስሩን አመቱ በኪሳራ ሲገዛን፤ እንዲሁም ሌላውን አስር አመት በትርፍ ሲሸጠን ከርሟል ማለት ነው ሲሉ በሪፖርቱ ተሳልቀዋል። የምር ግን …

በዛ ሰሞን ዳውሮ ወረዳ ተርጫ ውስጥ የኔ ሰው ገብሬ የተባለ መመህር ራሱን አቃጠለ። ሞተም። መንግስትም አለ አይምሮው የተቃወሰ ሰው ነው። አይምሮ ያላቸውም ጠየቁ “አዕምሮውን ማን አቃወሰው?” መንግስትም መልስ አልነበረውምና ዝም አለ…! “ራሳቸው እያስለቀሱ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ያቋቁማሉ” የለው ማን ነበር? ከየኔሰው ገብሬ በኋላም ሆነ በፊት በርካታ መምህራን በመንግስት የተጠናገረ አስተዳደር የተነሳ ሲቃጠሉ ውለው ሲቃጠሉ እንደሚያድሩ …

በወዳጃችን ዳንኤል ተፈራ የተሰናዳው “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” የተሰኘው መፅሀፍ ላይ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በአንድ ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ እነ ስዬን አጓጉል ሲዘልፏቸው ይሰማሉ። (ምን እያሉ…? ይበሉ እንጂ…) ምን የማይሉት አለ ብዬ እቀጥላለሁ፤  “አፈንጋጮቹን ጃኬታቸውን አስወልቀን ሸኝተናቸዋል።” በማለት ይናገሩ ነበር። ይሄኔ ዶክተር ነጋሶ ሆዬ መንጌ በአንድ ወቅት ጀነራሎቹን “ማዕረጋቸውን አስወልቀን ቂጣቸውን በሳንጃ ወግተናቸዋል” ያለው ትዝ …

ሰሞኑን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከነ አንዷለም አራጌ ጋር በተያያዘ ባወጣው ዘገባ ምክንያት አቃቤ ህግ “በፍርድ ሂደቱ ላያ ጣልቃ ገብተሀል” በሚል ፍርድ ቤት እንዳቀረበው ይታወሳል። (በቅርቡ አይደል እንዴ… እንዴት ይረሳል…? ብለው ይከተሉኝ) ያንን ወሬ ባቀበልኩዎ ግዜ ከዚህ በፊት ኢቲቪ አካልዳማ የተባለውን “ፊልም” ሲያቀርብ  አቶ አንዷለም አራጌ “ኢቲቪ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ ገብቷል” ብለው ቢከሱ …

ይህ ፅሑፍ “አርብ አርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም” በተባለበት በዕለተ ጁምአ ለምትታተመው ፍትህ ጋዜጣ የተሰናዳ  ነው። ከጋዜጣዋ ርቃችሁ ለምትገኙ ወዳጆች ደግም እነሆ በዚህ መልኩ… የፍቅር ደብዳቤውን ያሰናዳው ታታሪ ካድሬ ከዚህ በፊት ቁጥር አንዱን በአውራምባ መፅሔት፣ እንዲሁም ቁጥር ሁለቱን ደግሞ በአውራምባ ጋዜጣ ላይ ታትመውለታል። የዛሬውም የነዛ ተከታይ መሆኑ ነው። እሱም ይበርታ ይበርታ እና ይፃፍ ፤ እርስዎም ይበርቱና ያንብቡለት! ይድረስ …

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ “በአንዷለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ እና ናትናኤል መኮንን ላይ ያቀረብከው ፅሁፍ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት ነው” ሲል አቃቤ ህግ በከሰሰው መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ። ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ምድብ ችሎት ዛሬ ጠዋት የተከሰሰበትን እንዲያስረዳ ቀርቦ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን በችሎቱ በተገኘበት ወቅት ከተጠበቀው በላይ ሰው በመምጣቱ ችሎቱ …

ያው እንደሚታወቀው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፍቅር ከወደቅሁኝ ቆይቻለሁ። ስለዚህ ነጋ ጠባ ኢቲቪን ብጠቅስብዎ አየሰልቹ። ዛሬም “ቸር ያሳደርከኝ ቸር አውለኝ፣ ከተናግሮ አናጋሪ አገናኘኝ” ብዬ ፀሎት ካደረስኩ በኋላ መጀመሪያ ያገኘሁትት የኢቲቪ ዜና አንባቢን ነበር። ባትሰማኝም “ደህና አደርሽ እግዚአብሄር ይመስገን” ብዬ ተቀበልኳት። እርሷም ዜናዋን ቀጠለች። “የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ሊከበር መሆኑ ተገለጠ…” አለችኝ። እውነትሽን ነው? ፍትህ …ፍትህ… ፍትህ የቱ…? ብላት …

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ብቸኛው የተቀናቃኝ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተውላቸው ነበር። ከጥያቄዎቹ መካከልም ስለ ፖለቲካ ምህዳሩ፤ ፓርቲያቸው በይፋ ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ኢቲቪ የቀረፀውን ዋቢ በማድረግ “በህቡዕ በማሴር” ተብለው አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ተከሰውበት እስር ቤት ይገኛሉ፣ ስብሰባ ለማድረግ አዳራሽ አከራዮች …

Tweet ከአቤ ቶኪቻው ቆይ ቆይ አይደናገጡ! መጀመሪያ የቱ ግድብ? ብለው ይጠይቁ እንጂ፤ “ወይኔ ቦንዴ? ወይኔ ደሞዜ” ብለው ሀዘን አይግባዎ! መንግስታችን አባይን ለመገደብ ከማሰቡም በፊት በትጋት ሲገድብ የነበረው ድረ ገፆችን፣ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ጣቢያዎችን እንደነበረ የታወቀ ነው። እንደውም አንዳንድ አሽሟጠጮች እንደሚሉት ከሆነ መንግስት ያለ ምንም ዕቅድ አባይን ልገድብ ብሎ የተነሳው፤ ድረ ገፅ እና ራዲዮ ጣቢያ በመገደብ […]

ቴዲ አፍሮ ሰሞኑን “ጥቁር ሰው” የሚል የሙዚቃ አልበም ይለቃል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነበር። እንደሚታወቀው የቴዲ አፈሮ ሙዚቃ መልቀቅ ከኢህአዴግ ስልጣን መልቀቅ እኩል በጉጉት የሚጠብቁት ብዙዎች ናቸው። እኔም… አንዱ ሳልሆን አልቀርም። ታድያ ቴዲ ሙዚቃውን ከመልቀቁ ከጥቂት ቀናት አስቀድሞ በርካቶች በራሱ በቴዲ ላይ ነጠላ ዜና ሲለቁ ሰምተናል። (በዚህ አረፍተ ነገር አግባብ “ዜና” ማለት ወሬ ማለት ነው። ለነገሩ …

ትላንት ፀሎተ ሀሙስ ነበር። ቀኑን የጀመርኩት ግን በፀሎት አይደለም በሀዘን ነው። ይሄኔ ምን ሆነክ ይላል ብልህ ሰው፤ አዎ እንደርሱ ነው የሚባለው። በፌስ ቡክ መልዕክት ሳጥኔ ፤ “አንድ ኢትዮጵያዊ ኩዌት ውስጥ በድንገት ሞቶ ተገኘ ልጁ ወደ ኩዌት ከመጣ ገና ሶስት ወር እንኳ አልሞላውም” ሲል ከወዳጆቼ አንዱ መርዶ አስቀምጦልኛል። መልዕክቱን አንብቤ እንደጨርስኩ ድብርት እና ሀዘን በላዬ ላይ …

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የትንሳኤ በዓል ሊመጣ ሳምንት የማይሞላ ግዜ ቀርቶታል። እስቲ በሰላም ያምጣውና ሌላው ቢቀር እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል ያብቃን። አሁን ህማማት ላይ እንገኛለን። በሀይማኖቱ የበቁ ወዳጆቻችን እንደሚነግሩን በዚህ ሰሞነ ህማማት ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ቀናት ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ የደረሰበት ስቃይ የሚታሰብባቸው ናቸው። በተለይም ኢየሱስ በአደባባይ ቆሞ ባስተማረ እና በተናገረ ግዜ የደረሰበት …

Tweet አቤ ቶኪቻው መጀመሪያ ቆይ ርዕሱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንቱ ያላልኩት በትህትና ጉድለት ሳይሆን ርዕሴ ቤት እንዲመታልኝ ፈልጌ ነው። ዛሬ እና ትላንት ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ ሀሳቤን ላካፍላችሁ ሙከራ አድርጌያለሁ። እውነቱን ለመናገር እየተፈጠረ ያለው ነገር በጣም የሚያስጨንቅ ነው። ለዚህም ነው ደጋግሜ ነገሩን ማንሳቴ ወደፊትም ደግሜ አነሳዋለሁ። ታድያ በእናት ድርጅታችን ኢህአዴግ ውስጥ “የብሎግ እና ፌስ […]

ይህው እንግዲህ ፆም ሊፈታ ነው። ተስፋዬ ካሳ በአንድ ቀልዱ ላይ ሁለት ችግር ያላቸው…! (“ር”ን ረዘም ያድርጉልኝ) እናም ሁለት ችግርርርር … ያላቸው ባልና ሚስቶች ብላችሁ አንብቡልኝ፤ ስለ ፆም ፍቺ ያወሩትን እንዲህ ነግሮን ነበር፤ ሚስት “እንግዲህ አሁን ፆሙ ሊፈታ ነው። ምን ይሻለናል?” ብላ ትጠይቀዋለች። ባል ታድያ ምን አላት፤ “አይዞሽ ሌላ ፆም እንይዛለን” ብሎ “አፅናናታ” ተስፋዬን ደግሞም ደግሞም …

Tweet (አቤ ቶኪቻው) ሰሞኑን መነጋገሪያ ከነበሩት ጉዳዮች መካከል አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተባሉ የኢህአዴግ ባለሰይጣን (ታይፕ አልገደፍኩም ዝም ብለው ይከተሉኝ ወዳጄ) ባለስይጣኑ በሚያስተዳድሩት ክልል ሲኖሩ የነበሩ ከሰባ ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን “ወደ ሀገራችሁ ሂዱ” ብለው አባረዋቸዋል። ይህንን አስመልክቶ ዛሬ በኢሜል የደረሰኝ የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በርዕሰ አንቀፁ ባስቀመጠው ካርቱን ስዕል፤ ሰውየው አቶ ሽፈራው […]

ይሄ ወግ ትላንት አርብ አዲሳባ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የወጣ ነው። ታድያ ለዲያስፖራ አንባቢዎቼ አዲሳባ በተዘጋችው በዝችኛዋ ብሎግ አቅርቤያለሁ። ኢትዮጵያ አላችሁ ወዳጆቼ ፍትህ ላይ ታነቡታላችሁ በሚል እሳቤ ነው  በዛችኛዋ መስኮት ያለጠፍኩላችሁ። ወዳጄ እንዴት አሉልኝ ? እኔ ከእርሰዎ ሃሳብ እና ከፒያሳ ናፍቆት በሰተቀረ በጣም ደህና ነኝ። በዝች በምንወዳት እና በምትወደን፤ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ባለፈው ሳምንት እከሰታለሁ ብዬ …

Tweetአቤ ቶኪቻው ባለፈው ሳምንት ውስጥ ተዓምረኛው ኢቲቪ ለማርች ስምንት የሴቶች ቀን መታሰቢያ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶናል። ቐሽ ገብሩ ስለተባለች የህውሃት ህፃን ታጋይ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም። (ፊልሙ ልብ ብለው ሲከታተሉት ዘጋቢ ብቻ ሳይሆን አወዛጋቢም ነው… እንዴት…? የሚለውን የታገሰ ያነባል (ሳቅ)) በመጀመሪያ አበሻ እንደመሆኔ መጠን ጭቆናን “እምቢ” ብለው ፋኖን ለዘመሩ ታጋዮች ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ያለ ሽሙጥ እገልፃለሁ። […]

ባለፈው ሳምንት ውስጥ ተዓምረኛው ኢቲቪ ለማርች ስምንት የሴቶች ቀን መታሰቢያ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶናል። ቐሽ ገብሩ ስለተባለች የህውሃት ህፃን ታጋይ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም። (ፊልሙ ልብ ብለው ሲከታተሉት ዘጋቢ ብቻ ሳይሆን አወዛጋቢም ነው… እንዴት…? የሚለውን የታገሰ ያነባል (ሳቅ)) በመጀመሪያ አበሻ እንደመሆኔ መጠን ጭቆናን “እምቢ” ብለው ፋኖን ለዘመሩ ታጋዮች ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ያለ ሽሙጥ እገልፃለሁ። ተስፋዬ ገብረ …

ዛሬ ለቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን አንድ መልዕክት ለመስደድ አስቤያለሁ። እስከ ዛሬ ድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትራችን የተለያዩ መልዕክቶችን ስንልክላቸው ነበር። እርሳቸው ግን አይተው እንዳላየ፣ ሰምተው እንዳልሰማ ዝም ብለውናል። በርግጥ መልዕክቶቻችንን እንደሚያነቡ ባለፈው ግዜ ጠቁመውናል። “እያንዳንዳችሁ በየጋዜጣው የምትፅፉትን እናያለን የጋዜጠኝነት ሀሁ ያልገባችሁ ጋጥ ወጦች ናችሁ” ብለው እስከ ዶቃ ማሰሪያችን በተናገሩበት “ዲስኩር” ቢያንስ መልዕክቶቻችንን እያዩ እንደሆነ ተረድተናል። እኛም “ጠቅላይ …

ይህ ጨዋታ በተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ ላይ አርብ የካቲት 23 የታተመ ነው። እግረ መንገዴን እንኳን ለአድዋ በዓል አደረሳችሁ ብዬ ልጀምር… ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው ለዛሬ ጨዋታችን በዋነኛነት ይዤ የመጣሁት ጉዳይ መሪዎቻችን እንማን እንደሆኑ የሚጠይቅ ነው። ያው እንደተለመደው ሌሎች ጨዋታዎችም ይኖሩናል። አውራ ርዕሱ ግን “መሪዎቻችን እነማን ናቸው… አርቲስቶቹ ወይስ ታጋዮቹ?” የሚለው ይሆናል። “ለፓርቲ አውራ እንዳለው ሁሉ ለጨዋታም አውራ …