ምን ነካው? የማይባለው ሰለሞን ተካ!

ሰሞኑን ሰለሞን ተካ “ፅናት” በተባለ የሬድዮ ጣቢያው ላይ ጮክ ብሎ ሙስሊም ወንድሞቻችንን በሚመለከት አንድ መግለጫ ሰጥቷል። ሰለሞን የቱ…? ብሎ የጠየቀ ካለ ሰለሞን ዜሮ ዞሮው በሚል አብራራለሁ። መጨመር ካስፈለገም ምን ነካው? የማይባለው ሰለሞን ተካ! ብንለውም ይሆናል።

የሚገርመኝ ነገር 1

ይሄ “ፅናት” የተባለው ራዲዮ ጣቢያ አዘጋጁ ራሱ ሰለሞን ተካ ነው። ስጠረጥር ባለቤቱም እርሱ ይመስለኛል። ታድያ እዚህ ላይ ግርም ያለኝ ነገር፤ ሰለሞን እንዴት ይሄንን ስም ተሸክሞ ቆሞ መሄድ እንደቻለ ነው። በእውነቱ ይሄ ተዓምር ነው። ሰለሞን ተካ ዜሮ ዜሮ፤ ፅናት የሚል ስም በላዩ ላይ ተጭኖት በአደባባይ ሲንከላወስ ማየት አይጥ አንበሳ አዝላ ስትዞር ከማየት ጋር እኩል ያስደንቃል።

የሚገርመኝ ነገር 2

እኔ የምለው ሰለሞን ተካ እንዴት ነው ነገሩ አነጋገረህ እኮ እንደ መንግስት ነው። መቼ ነው የነገስከው የኔ ጌታ። አለግባኝም “ጨለፍ” አደረግህ እንዴ? እውነቴን ነው የምለው ከቤተሰብ እና ዘመድ ጋር ተቆራርጠሃል ማለት ነው? እንጂማ በአደባባይ እንደዚህ ስትናገር በቀጥታ የአዕምሮ ህክምና ቦታ ወይም ደግሞ ፀበል… ወይም ዱዓ ለሚያደርግ ቃልቻ ወስዶ መስጠት ይገባ ነበር።

የሚገርመኝ ነገር 3

የኢህአዴግ ሰዎች እንዴት ዝም አሉ? የምሬን ነው። በዚህ አነጋገሩ እና በዚህ ለዛው ስለሞን ተካን ኢህአዴግን የሚወክል ጋዜጠኛ ማድረግ የሚያመለክተው ትልቅ የሆነ የሰው ሃይል ችግር መኖሩን ነው። እውነቴን ነው የምላችሁ ውድ የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች ሆይ ሰለሞን ተካ እንኳንስ በጋዜጠኝነት እና በዘፈኑም ቢሆን ለሚያደርገው “አስተዋፅኦ” ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ባለፈው ግዜ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን “ቅንድቡ ያማረው” ብሎ ዘፍኖላቸው ስንቱ ነው በሌላ የጠረጠራቸው? እሱ የራሱ ጉዳይ እርሳቸው ግን በምን እዳቸው እንዲህ አይነት ጥርጣሬ ውስጥ ይወድቃሉ። ምንም ቢሆን ባለትዳር ናቸውኮ!

እውነቱን ለመናገር ሰለሞን ተካ ለኢህአዴግ በጋዜጠኝነት እሰራለሁ ማለቱን ማንኛውም ለድርጅቱ አሳቢ የሆነ ግለሰብ ሊያስቆመው ይገባል። የምሬን ነው የምለው ድርጅቱ ስንት የሚተችበት ጉዳዮች እያሉት በማንም ሰርጎ ገብ የሚብጠለጠልበት ምክንያት አለ ብዬ አላስብም።

ቀጥሎ ያለው አንቀፅ ለኢህአዴግ ከልብ በመቆርቆር የተሰነዘረ ነው።

እንደኔ እምነት ሰለሞን ተካ በቅፅል ስሙ “ብሪቱ” እልም ካለው የተቃውሞ ጎራ ወደ ኢህአዴግ ደጃፍ መምጣቱ ለኢህአዴግ ጥሩ ነው። ነገር ግን “ደርሶ ከኔ በላይ ኢህአዴግ ላሳር” ማለቱ እና በየአደባባዩ ድርጅቱን የሚወክል ወሬ ማውራቱ ለኢህአዴግም መልካም ገፅታ አይበጅም። አረ በድንብ ስሙት ጎበዝ ሰውየው እኮ እሳት ይቀረዋል። ስለ እውነት እላችኋለሁ አልበሰለም። ታድያ በሳል ሰው ከየት እናምጣ? ካላችሁ ድርጅቱ ራሱ ተሀድሶ ያስፈልገዋል ማለት ነው። አለበለዛ ግን “ሃይ” ባይ ሰው ያስፈልጋል። ልክ ተቃዋሚዎች “መለስ በቃ” እንደሚሉት አይነት የኢህአዴግ ሰዎች ይበልጡኑም ለድርጅቱ አሳቢ የሆኑቱ “ሰለሞን በቃ” ብለው ሊያስቆሙት ይገባል። ከልቤ ነው የምላችሁ። (ከፈለጋችሁ ንግግሬ ላብራቶሪ “ቼክ” ይደረግ)

ለማንኛውም ሰለሞን ተካ ሰሞኑን ራሱን መንግስት አድርጎ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም “መጅሊስ ይውረድ መንግስት በእምነታችን ጣልቃ አይግባ” ሲሉ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ ሙስሊም ወዳጆቻችንን “የአልቃኢዳ ቅጥረኞች” ብሏቸዋል። ሰለሞን ይህንን ነገር ከየት አመጣው ያልን እንደሆነ ባለፈው ግዜ ጠቅላይ ሚንስትራችን “በአርሲ እና ጅማ አካባቢ የአልቃይዳ ሴል ተገኝቷል” በማለት የተናገሩትን ለመኮረጅ ሞክሮ ነው። ሰሌ በእብደቱ ተዓምር በየ ጁምዓው ተቃውሞ የሚያሰሙ ሙስሊሞችን በሙሉ “የአልቃይዳ ቅጥረኛ” ብሏቸዋል። አላህ ምህረቱን ያውርድልህ እንጂ ይሄ የጤና አይደለም። “ፍሬንዴ” የአልቃይዳ ቅጥረኛ ቢሆኑማ በአንድ ቦንብ “እምጷ” ያደርጉህ ነበር።

በመጨረሻም

አንድ ጥያቄ

እኔ የምልህ ሰለሞን ተካ ባለፈው ግዜ እኮ “ከዚህ ቀጥሎ ቤተሰቤን ይዤ መጥቼ አዲሳባ መኖር እጀምራለሁ” ብለህ የአዲሳባ ህዝብ በጉጉት እየጠበቀህ ነው። እኔ የምልህ ያንግዜ ካዛንቺስ አካባቢ የጎሻሸሙህ ነገር አናትህን ነክቶት ይሆን እንዴ!? ያልከውንም አስረሱህ የምትናገረውንም አቀዣበሩብህ እኮ!

ሌላ ደግሞ ራስህን “አርቲስት” እያልክ ስተጠራ ሰምቼ ለዚህ ጨዋታ የሚሆን ፎቶ ፍለጋ “ጎግል ኢሜጅ” ውስጥ ገባሁልህና “አርቲስት ሰለሞን ተካን” አፋልገኝ ብለው ብሰራው አንዴ አበበ ተካን ሲያመጣልኝ፤ አንዴ ሰለሞን ቦጋለን ሲያመጣልኝ ስሰማ ተሳስቼ ይሆናል ብዬ ደመደምኩ። ይቅርታ ትደግምልኛለህ…  ምን “…ቲስት”  ነኝ ያልከው?

15 Comments on “ምን ነካው? የማይባለው ሰለሞን ተካ!”

  1. አህያ ፈሳ ተብሎ አፍንጫ አይያዝም ነው ነገሩ እኮ!!! አቤ እንጂ ስንት ማለት በተቻለ ነበር::

  2. ጎሽ ያሄንን ጎተራ ልክ ልኩን ነገርክልኝ ከገባው ደደብ የወያኔ አሽከር አንደ አሱ አይንት አስማ ጽናት የት ያውቃታል በሁሉ ቦታ አየገባ ይዝባርቃል

  3. Tell him Abe,for this bastard hodam aleklaki he may understand some thing from your article if he knows how to read.

  4. አቢየ በሳቅ ገደልክን| the guy is animal who eat grass. as you said how woyyane kept quite unless they are not better of him. are they might proud of him?

  5. አቤ እውነት ለመናገር ይህ ጽሁፍ ያንተ መሆኑን እጠራጠራለሁ ይህን ስልህ ስለ ሰውየው ለመከራከር ፈልጌ አይደለም በማንኛውም መመዘኛ የተጠቀምካቸውን እነዚህን ቃላት ካንተ አልጠብቃቸውም ለካ አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ ትሆናለህ ::

  6. ባንዳና አህያ ፈጹም አንድ ናቸው
    ጅራትና ጋማ ነው የሚለያቸው……ታዴዎስ ታንቱ….ፍትህ ጋዜጣ

  7. diro high school temari eyalen አንድ sewye gibi keguadegnoche gar gebten min alen meselachihu yewilachihu lijoch yihe(duba wodemimesil atikilt beju eyetekome) duba new biye biteklew siyadig kil hone alen yeduba firena yekil fire temesaslewbet. engidih kezih nigigir solomonin wud ethiopians endefelegachihu tergumut.

  8. I am wondering why you guys still call this garbage,”solomon”.I rather call him, “Salvage”,used, second hand,thrown into the garbage(woyane).

  9. ጎበዝ ሰለሞን የኢህኣዴግ ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚ አይደለም፡፡ ዝም ብሎ ሆዳም ነው፡፡ ይሄንን የምለው በእውነት ስሙን ለማኮስስ ወይም ለመሳደብ አይደለም፡፡ እውነት ስለሆነና በአካል ስለማውቀው ነው፡፡ አንድ ምግብ ስለማይበቃው አቤት የዚህ ቤት ሚጥሚጣ እያለ ደረቅ እንጀራ የሚጎሰጉስ ሆዳም ስለነበር ነው እንጂ፡፡ ውሸት ነው ካለ ሰሜን ሆቴል አጠገብ ዘንባባ ሆቴል በሉልኝ፡፡ አይክድም፡፡

  10. He is just a pig! I swear he is a pig. He is good for nothing! Abe and Elias I know you are journalists and you can write whatever you felt to share but Solomon doesn’t deserve such attention.

  11. ሰለሞን ውሻ በበላበት ይጮሀል ሆነና መለሰ ባስነጠሰ ቁጥር ጩኸቱን ይቀጥላል በጣም የሚያስቀው እኮ እኛም ስናስነጥስ መጮኹ ነው

  12. Abe and Elias! Why do you give him half page cover for this human like pig, He must have a mental issue. Please forget this BIG PIG. And focus on your wonderful job

  13. ፃድቅ ሆይ ወዴት ነህ…
    ፃድቁ ተኝቷል
    ላይነቃ አንቀላፍቷል
    መለስ ብየ ባየው ፣ ወንበር ላይ ተጋድሟል
    መሰሎቹን ሆኗል
    ሆዱን እያለመ ህሌናውን ሽጧል
    ስጋውን አድልቦ ነፍሱን አዘርፏል
    ተነስ ብትሉትም
    እርሱ እንደሆነ የለም፤
    ልቡ ስላልባባ
    ንስሃ አይገባ ፤
    መንፈሱን ለንቁጦ
    ግለ ሂሱን ውጦ
    ግብዙ አፍጥጦ
    በቅቤ ለጥልጦ
    በግድ ተፈናጦ
    ላይመለስ ሄደ፣ጋለበ ሸምጥጦ፤
    ዕለት ዕለት ሞቷል
    ወንበር ስር ተቀብሯል
    መንበረ ሱስ ሆኗል
    በስልጣን ጎልቷል ( ወፉ Pico-Rampu, may25, 2011)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*