መንግስት እንደ ቼልሲ ዘግቶ መጫወትን ለምን መረጠ!?
ባለፈው ግዜ ቼልሲ ከባርሴሎና ጋር ሲጫወት በሩን ጥርቅም አድርጎ በፓስዋርድ ነበር የዘጋው። ለምን ዘጋ ያልን እንደሆነ በርካታ ምክንያቶችን መደርደር እንችላለን። ከእኛ ይልቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ኤርሚያስ የሆነ ነገር ብሎ እንደሆነ እንፈልግ እና እንመልከት። ምንም ካላለም ከቀጣዩ የዋንጫ ጨዋታ ጋር አያይዞ ዘርዘር ያለ አጥጋቢ ምክንያቶች እንደሚነግረን ተስፋ እናድርግ።
ትላንት አንድ ፈረንጅ ወዳጃችን፤ “ብሎጌ በተደጋጋሚ ተዘጋ ብዬ ዋይ ዋይ” ማለቴን ወሬ ሰምቶ ደውሎልኝ ነበር። እኔም ስለሁኔታው አስረዳሁት። “ብታምነም ባታምንም አስራ አንድ ግዜ ብሎጌ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተዘግቷል፤ ከዛም አልፎ ተርፎ አንዳንድ አክቲቭ የሆኑ ልጆች ፌስ ቡክ አካውንት ሁሉ እየተዘጋባቸው ድጋሚ እየከፈቱ ነው።” ብዬ ማቃጠር፤ ከዛልዎ ፈረንጁ ወዳጃችን በእንግሊዘኛ ተገርሞ ተገርሞ ተገርሞ ሲያበቃ ለመሆኑ “መንግስት ለምንድነው በዚህ ግዜ እንዲህ የሚያደርገው? ምርጫ እንኳ ቢኖር ድምፅ እንዳያሳጡኝ ብሎ ነው ይባላል? አሁን ግን ምን ሆኖ ነው…?” አለኝ። ለዚህ መልስ የለኝም። ስለዚህ እኔ ራሴ ይህንን ጥያቄ ልጠይቅ… መንግስት እንደ ቼልሲ ዘግቶ መጫወት ለምን ፈለገ?
ወሬዬን ልቀጥል ነበር ሳስበው ሁልግዜ እኔ ብቻ ሳወራ “ያንተ ወሬ ብቻ አላልቅ አለ!” እንዳይሉኝ ሰጋሁና ለምን መድረኩን ለአንባቢ ወዳጆቻችን አልተወውም አልኩ “እርስዎም ይሞክሩት” ብንለውም ይሆናል። እንደሚያውቁት ወይም ደግሞ ማወቅ እንደሚገባዎ መንግስታችን የተለያዩ ዌብ ሳይቶችን ጥርቅም አድርጎ ዘግቷል። ለምን…? እባክዎን ወዳጄ ይሳተፉ… መንግስት ዘግቶ መጫወትን ለምን መረጠ…? እንደ “ሙዳችን” ፈቃድ መልስዎን ከፌስቡኩም ከብሎጉም ሰብሰብ አድርጌ ሌላ ጨዋታ ይወጣው ይሆናል።
ፈራ ቀዘነ አሁንማ ጥላውንም አላመነ
ፈሪ ስለሆነ ነዉ
ቶኪቻው,ችልሲ ዘግቶ ቢቻውት ለድል ነው መለስ ቢዘጋ ፈርቶ ነው የፈሪ በር ምን ጊዘም ዝግ ነው ትሩ ነገር ስለማይስሩ ሁልግዘ ፍርሃት አለ ትርታሬ አለ ስላም የላችውም ህዝብ ሆ ብሎ ተነስቶ ይበላናል ብለው ስለሚፈሩ በራችው ሁል ጊዘ ዝግ ነው አይዞህ በርታ አቤ ሁሉም ያልፋል በሃገራችን አንድ ተረት አለ
ያገነም ያታና ያታም ያገንና
ያስትዛዝበናል ይሀ ቀን ያልፍና እትዮፕያ ለዘላለም ተከብራና ተፈርትታ ትኑር;
ቦቅባቃ ስለሀነ ነው!
It is the so called the public secrete.The bullies of woyanie afraids the oppresed people of ethio.come on habesha heros,lets burried woyanie at the dessert of dedebit.
ደስ የሚል ጥያቄ …
ቼልሲ በሩ ዘግቶ የተጫወተው … አለን የሚሉት ተገናቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ጉድ ሲሰራቸውና ራሳቸውን ከተቀናቃኝ ሃይላቸው ጋር ሲመዛዝኑ አቅመ ቢስነት ስለተሰማቸው, ይህን ሃይል ፊት ለፊት ተጋፍጠን ጉድ ከምንሰራ ሰው ያለውን ይበል የቀርችውን የጨዋታ ሰአት በረችን ዘግተን አንፋለም ብለው ነው:: የጨዋታው ሰአትም አለቀ, ሰውም ያለውን አለ, እነርሱ ግን ድል አደረጉ::
መንግስትስ? አለኝ የሚለው ሰው ሸሸው? ከተቀናቃኝቹ ጋር እራሱን ስያነጻጽር አቅመቢስነት ተሰማው? የጨዋታ ዘመኔ እያለቀ ነው ብሎ አሰበ? … ምናልባት ምናልባት! ምናልባት! ትንተና የሚያስፈልገው ርእስ ነው::