በረሃብ ጠኔ ኣደጋ የሟቾች ቁጥር አየጨመረ ነው፥ በሁመራ ሰዎች አየሞቱ ነው።
ረሃብ የወለደው መርዶ
*************
ዛሬ እሮብ 15 / 03 / 2008 ዓ/ም ከቀኑ ኣምስት ሰዓት ኣከባቢ ከሑመራ ኣደባይ ቀበሌ የደረሰኝ የስልክ ጥሪ እጅግ የሚያሳዝን ረሃብ የፈጠረው መርዶ ነበር።
ዛሬ ረፋድ የኣደባይ ከተማ ህዝብ ኣንዲት በረሃብ የሞቱት እናት ቀብር መዋሉን ከቦታው ተደውሎ ተነገረኝ።
የሞቱት እናት ስማቸው በመግለፅ ከነገረኝ በኋላ ሰሞኑን በረሃብ የሞቱት ሌሎች ተጨማሪ የሁለት ሰዎች ስም ዝርዝርም ሰጠኝ።
ኣስከትሎም በኣሁኑ ሰዓት በረሃብ ጠኔ ተይዘው እግራቸው ያበጠና በሞት ኣፋፍ የሚገኙ በርካታ ኑዋሪዎች ዝርዝር ስም ሊሰጠኝ እንደሚችል ከነገረኝ በኋላ ቤቶቻቸው ዘግተው ለስደት ከሄዱትና ሱዳን ድንበር ከደረሱ በኋላ ወሬያቸው የታጣ 63 ቤተ ሰቦች ህልውና እንዳጡ ገልፀውልኛል።
ህዝቡ ከመንግስት ምንም እርዳታ እንዳልቀረበለት፣ ተስፋ ቆርጦ ወደ ስደት እግሩ ኣምርቶ ኣለማቀፍ ገባሬ ሰናይ ድርጅቶች እርዳታ እንዲያደርጉለትና የስደተኞች ካምፕ እንዲያዘጋጁለት እንደሚጠብቅና እንደሚፈልግ ገልፀውልኛል።
በምዕራባዊ ዞን ሰቲት ሑመራ ከተማ ጨምሮ 7 ቀበሌዎች በከባድ ድርቅ መመታታቸው ይታወቃል።
በተለይ በማይካድራ ቀበሌ በመስከረም ወር 3 ኑዋሪዎች በረሃብ ሙተው እንደተገኙ ተገልፆ ነበር።
የትግራይ ክልል መንግስት ረሃቡ በመደበቅና ህዝቡ እንዳይሰደድ በማገድ በርካታ ሰዎች ቤታቸው ዘግተው በረሃብ እያለቁ እያደረገ ነው።
እርዳታ ማከፋፈል በተጀመረባቸው ኣከባቢዎችም የመዳበርያ፣ የጋዜጣ፣ የማሕበራት ዕዳ ወዘተ እየተባለ እርዳታው እየተቆረጠ ተመልሶ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ እየተደረገ ይገኛል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO………! Amdom Gebreslassie

min yihalal qedmiya lerabu acawunt
የኢትዮጵያ ድርቀና የረሃብ አደጋውን የተፈጠረው በሰው በአስተዳደራዊ ግድፈት፣በዜጎች፣በሙስና፣በሌብነት፣በስርቆት፣በምቀኝት፣በጎሰኝነት ሲሆን፡
መፍትሔው
1- ሕዝብን ማስተባበር
2- መተሳሰብ
3- መወያየት
4- ግድብ መገደብ
5- ወንዞችን መጥለፍ
6- ውሃ ማቆርስራን መስራት
7- በሌቦች የተሰረቀውን ገንዘብ አስመልሶ ለረሃቡ ማዋል
8- ስግብግቦችን በአይነ ቁራኛ መከታተል
9- በተለይ የምሁራን ስግብግብነት ዘመቻ ማካሄድ
10- አሁን ያሉትን ግድቦች ለመስኖ፣በግጦሽ ቦታ (ለምሳሌ ከሰምን፣ተንዳሆን፣አልዎሮን፣ጊቤን፣ፊንጫን) ሸንኮራውን ትተን ለወቅቱ ግችር መፍቻ ማዋል ከውረደት ያድናል! ርዳታ ሃገርን ሕዝብ ያዋረዳል! ይቁም! ጠባብነት ውረደት ነው! ድህነት ነው! ሌብነት ነው!
ሳተናው አሊ
መጡልህ/መጠልን/ የኢትዮጵያ ጡትነካሾች
ሊበትሁን
ሊያዋርዱን
ሲያስረቡን
ሊያጠሙን
ሊያሳርዙን
ሊያንቋሽሹን
አፍነው ሊገድሉን
ሊያሰድቱን
ሊያዘረፉን ወዘተ.. ወዘተ
ስሜ፡ አከርካሪው የተመታው አማራ ነኝ
ውድ ወገኖች ሁሉ እንደሰው ለሚያስቡ ጤናይስጥልኝ ሰላም ናችሁ
እኛ መቼም ቢሆን ያለንበትን ሁኔታ ከባድ ነው
ጥያቄ አለኝ
1- በ22/03/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን በሆስፒታልና ከተጎጅ ቤተሰቦች እየተነገር ነው ስለዚህ እባከችሁ ወገኖች ሬድዩ ሆስፒታሎችንና ትምህርት ሚኒስትር ጠይቃችሁ ለወደፊቱ ለሚደረገው ጥንቃቄ እንድንወስድ ብትረዱን?
2- በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ድርቅና ርሃብ ምክንያት የሚመጣው የበሽታ አይንት ምን እንደሚሆን ወርርሽ፣ተስቦ፣ኮሌራ ወዘተ ሕዝብ ቢያውቀውና ብናውቀው መልካም አይመስላችሁም ?
3- ሌላው ጥያቄዩ በአዲስ አበባ ውስጥ ለህክምና ለካርድ ብቻ 1000 (አንድ ሽህ ብር) የሚጠየቀው በምን ምክንያት ይሆን? እሱም ሎሪት የማነብርሃን ክሊኒክ ሲሆን እውነት ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያዊነትን ያውም ብዙ ድሃ ሕዝብ ባለት ሃገር ውስጥ ለካርድ 1000 ብር ለካርድ 1000 ብር ተው ዶ/ር በዛ እጅግ በዛ ከዚህ ሕዝብ ነው የተፈጠራችሁት ያስተማራችሁ ተው እባከችሁ እንደ ሰው አስቡ?
ሳተናው አሊ