በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተነሱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለዋል::የፖለቲካ ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ:: ‪

Minilik Salsawi's photo.

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተነሱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለዋል::የፖለቲካ ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ ካለማቋረጥ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የመልካም አስተዳደር የፍትህ እና የለውጥ ጥያቄዎችን አካቶ በስፋት የቀጠለ ሲሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችም ሕዝቡ በዛሬው እለት ድምጹን ማሰማቱን ቀጥሏል:: እንዲሁም በቡራዩ ከተማ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ተከትሉ ሁለት የኦሮሚኛ ዘፋኞች ቢሊሱማ ድንቁ እና ጂረና ሺፈራው በሕወሓት ፖሊስ መታፈናቸው ሲታወቅ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች አቶ በቀለ ገርባ እና የኦሮሞ ገበሬዎችን ቃለመጠይቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተባረዋል::

በዛሬው እለት ለሶስተኛ ጊዜ በሃሮማያ በወለጋ ላሎቃሌ በደንቢ ዶሎ በመንዲ በአየራ ወለጋ በአርሲ አሰላ ፕሪፓራቶሪ ት/ቤት አሰላ ሜዲካል ኮሌጅ ሸዋ መቲ ከተማ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆ በሌሎች ቀሪ ከተሞችን ሕዝቡ አድባባይ ለመውጣት እና ድምጹን ለማሰማት እየተዘጋጀ ይገኛል የወያኔ ወታደሮች በየአከባቢው የኦሮሞ ነጋዴዎችን የሃገር ሽማግሌዎችን እና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች እየነጠሉ በጥይት መምታት መጀመራቸውን አንዳንድ ዘገባዎች ይጠቁማሉ::እንዲሁም በኦሮሚያ ዙሪያ በየአከባቢው የተመደቡ ባለስልጣናት እና ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን በተመደበላቸው ላንድ ክሩዘር ይዘው ወደ አዲስ አበባ በመሸሽ ላይ ይገኛሉ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

15 Comments on “በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተነሱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለዋል::የፖለቲካ ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ:: ‪”

  1. መቶ በመቶ ያሸነፈው ወያኔ ሕዝብ እጨረሰ ነው ከተመረጠ ታድያ ለምን እመራዋለሁ የሚለው ሕዝብ በርሃብ፣በጥይት ይቆላል? አይደንቅም ጉድ ነው ነገሩ!
    በአማራና በኦሮሞ መካከል ያስነሳውስ ግጭት መቼ ይብዳል ትላላችሁ? አቅጣጫ ለማስለወጥ ጎሳን ከጎሳ ማጋደል፣መግደል ስራው የሆነው ወያኔ ጋር ያሉ ምሁር ተብየዎች እባከችሁ ሳይማር ራቁቱን እየሄደ ያስተማራችሁን ወገናችሁን አታጥፋ/አትጉዲት/!ጥፋት ይቁም
    ተው እንደሰው አስቡ?

  2. ‘አዋቂው ፓርቲ ‘….ሁሉን ካስተማረህ ህዝብ ዝቅ ብለህ ተማር… አጉል ተንታኝ ነኝ እያልክ አትፈላሰፍ… የ40 ዓመት ጉልበት አለኝ ብለህ ህዝብ አትጨፍጭፍ… ሽንፈትህን ጉድፍህን ሲያሳዩህ አትጨፍን እይ… በቃ አልፈልግም ብሎዋል መሬቱን ለባለሃብቱ ሳይሆን ለባለንብረቱ መልስ እሱ ላመነበት አላማ ያውለው…. ይህ ነው ዴምክራሲ የራስን ዕድል በራስ መወሰን ከዚህ ያለፈው እኔ አውቅልሃለው ነው… የዚህን ውጤት ምልክት እያየኸው ነው… ከዚህ ተምረህ ምክንያት መደርደርህንና ጥፋትን ሌሎች ለይ ለመለጠፍ መሞከር ትርፋ መጋጋጥ ይመስለኛል… አውቃለሁ ትዕቢትህ ብዙ ጆሮህ ትንሽ መሆኗን …ብትሰማ ስማ ካልሰማህ ………….

  3. በምዕራብ ሸዋ ዞን ሆሎንኮሜ ከተማ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ሶስት ሰዎች በመንግስት ሀይሎች የተገደሉ ሲሆን በተመሳሳይ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ በተደረገ ሰልፍም ሁለት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል ።
    በዚህ የተነሳም ነዋሪዎቹ አንድ የአስተዳደር ቢሮ መኪና አንድ የፌደራል መኪና ያቃጠሉ ሲሆን አንድ የፌደራል ፓሊስ አባልንም በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንና ከሀረር ወደ ድሬዳዋ የሚወስደውን መንገድ ሙሉ ለሙሉ መዝጋታቸው ታውቋል ።

  4. የተከበራችሁት እድምተኞ የወያኔው ኢንሣ አሁን በደረሠን መረጃ መሠረት mereja.com/amharic ብሎክ መደረጉን በ አ.አ ያሉ ተከታታዬቻችን ነግረውናል እናም ነፃ የVPN አገልግሎት ዳውን ሎድ አድርጋችሁ እንድትጠቀሙ ሞያዊ እገዛዬን ለግሣለሁ።

    ወያኔ የመረጃ ፍሠቱን ይህዝብ ነውጡን ማቆም አይችልም!!!

    ሞት ለወያኔ !!!

  5. የህን የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው የወያኔው አግአዚ ጦር መሆኑን በቂ መረጃ አለን ቆርጦ ድባቅ መምታት ይኖርብናል።

  6. ኤጆሌ ኦሮሚያ ብራቮ ! ! ! ! አደራ የምላችሁ ግን ልክ የሙባረክ መንግስት ሲወድቅ እስላሞቹ የአለክሳንደርያን ክርስቲያኖች ዘብ ሆነው ከእስላም አክራሪ ጥቃት እንደተከላከሉ ሁሉ እናንተም እናንተም በክልላችሁ የሚኖሩትን ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች አንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦችም ሆነ ቡድን እንዳይጠቁ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባችኁዋል።በተለይም ከወያኔ መሰሪ ጥቃት።

  7. Non Oromos brothers and sisters who lives in Oromia has the right to live free with Oromo brothers and sisters as long as he/she respect our rights.Their rights should be respected too. Our problem is not religion. If anyone wants to use religion to kill people we don’t tolerate. We are seeking freedom not only free our self but also others.

  8. የኦሮሞ ኢትዬጵያን ወንድሞቻችን ኢትዬጵያዊነትን ለማስጠላትና ለማጥፋት የተነሱትን የባንዳ ልጆች ወያኔዎችን ከስራቸው ለመንቀል የምታደርጉት ትግል ለሁሉም ብሄሮች ትልቅ አርዓያ ነውና በርቱ እንቀላቀላችኧለን። ጠንካራ ክንድና አላማ ያሸንፋል ፤ የኢትዬጵያ ህዝብ ጥያቄ ብዙ ነው

  9. የብሄር እና ሃይማኖት ችግር በምን አይነት አይፈጠርም።የህዝቡ አንድነት በጣም ያስፈልጋል፣እንበርታ….!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*