የጋራ ጠላታችን ወያኔ ስለሆነ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የጋራ ጠላታችን ወያኔ ስለሆነ  ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው::
‪Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችሁ ሆነዋል:: በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል::ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል::የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው::

ይህንን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ይኖርባቸዋል::የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ይሁን በውጪው አለም ያሉ የለውጥ ሃይሎች ለሕዝብ ነጻነት እና መብት እንታገላለን እስካሉ ድረስ እርስ በእርስ መናከስ አቁመው በመደማመጥ እና በመወያየት በመመካከር እና በመቻቻል በመግባባት እና በመፋቃር ለሃገራዊ አጀንዳ በጋራ መቆም ችላ የማይባልበት ወቅት ላይ ተደርሷል::የሕዝብን ታማኝነት ለማግኘት የለውጥ ሃይሎች እርስ በርሳቸው እየተባሉ እንዴት እኛን ነጻ ያወጣሉ የሚለውን ቅብብሎሽ ለመቁረጥ እና በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ፈጥሮ ትልቅ የለውጥ ስራ በመስራት አገዛዙን ማስወገድ ይቻላል::በሰላማዊ ትግል ይሁን በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ሃይሎች ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመምራት የሁሉንም የጋራ ልብ ለመግዛት የሚችሉት በአንድነት ቆመው የህዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመደምሰስ የፖለቲካ ቆራጥነት እና የትግል ጽናት ሲኖር ነው::ተበታትኖ ትግል አንድም ለወያኔ ክፍተት መፍጠር ሲሆን በሌላውም በር የህዝብን ዝምተኝነት ማበርታት ይሆናል::መሰራት ያለባቸው የለውጥ ስራዎች ሁሉ በመደጋገፍ እና በመቻቻል መሆን ይገባዋል::

በዚህ ግፎች እየበረቱ በሄዱበት ወቅት ላይ የሕዝቡ የለውጥ ፍላጎት አብሮ እየጨመረ ይመጣል::ሕዝቡ ዝምታው ለምንድነው? እኛ ጋር ምን ችግር አለ? መቻቻል እና መተባበር የምንችለው እንዴት ነው? ለስልጣን የሚቋምጠው እና ልለውጥ የመሰራው እንዴት ይለይ?የሃሳብ ልዩነቶችን ማግባባት እና ማቻቻል የምንችለው እንዼት ነው? የሕዝቡን ዝምታ እንዴት መስበር ይቻላል?ሕዝባዊ ታማኝነትን በጋራ ሃገራዊ አጀንዳ እንዴት መፍጠር እንችላለን? የያዝነው ስትራቴጄ አዋጭነቱ ምን ያህል ነው..ተጠባባቂ ስትራቴጂ አለን ወይ? ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በአንድነት ማቆም የሚቻለው የትኛው ግድፈት ቢቀረፍ ነው? ሰላም እና ዲሞክራሲን ለመተግበር ተነሳሽነት ምን ያህል ነው? ባለፉ 20 አመታት የተበታተነው ትግል እና የተበታተኑ ድርጅቶች ምን ፈጠሩ ? ካለፈው የትግል ተሞክሮ ምን እንማራለን ?…ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ የለውጥ ሃይሎች ግዴታ ነው::ዋናው ነጥብ ግን በአንድነት መቆም ነው::ሃገራዊ አጀንዳ ይዞ የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በማጥፋት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

10 Comments on “የጋራ ጠላታችን ወያኔ ስለሆነ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው::(ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. ©
    “የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ይሁን በውጪው አለም ያሉ የለውጥ ሃይሎች ለሕዝብ ነጻነት እና መብት እንታገላለን እስካሉ ድረስ እርስ በእርስ መናከስ አቁመው በመደማመጥ እና በመወያየት በመመካከር እና በመቻቻልበመግባባት እና በመፋቃር ለሃገራዊ አጀንዳ በጋራ መቆም ችላ የማይባልበት ወቅትላይ ተደርሷል::”

    ሞት ለውያኔ

  2. Do not believe the picture it is a fake
    one . Its a copy and paste from the recent
    BURKINFASO PRTEST . ITS THE GIMATAM 7
    SLAVES WHO ARE POSTING THIS FALSE PICTURE .

  3. Minilik Salsawi, you are helping the crumbling regime unintentionally by keep saying “people in xyz are on demonstration opposing the ADDIS MASTER plan” in every article you are posting as if the master plan is the only and main reasoning for the uprising. the demonstration is simply beyond the master plan issue since that is only 1 tiny element for the people’s anger. People are sick and tiered of the oppressive, treacherous and Banda system entirely. People in Tunisia went out first day demonstration for the poor guy who burned himself to death, that was a first reason. But after, people uprise saying enough is enough and removed the dictatorial regime entirely. Therefore don’t serve the Banda regime unintentionally as if the master plan is the only reason for the people in every corner of our country. My advise, it is ok to mention the master plan issue but not as a core and main reason for the uprise of the general population, but it is as a result of a failed system and 25 adictatorial years.

  4. Btw: Minilike Salsawi, I admire this and all writings and articles. My advise above was simply for the other postings and thank you for your service.

    Freedom and democracy now!!

  5. የችጋር ዘበኛና፣ብጣሻም ወያኔ ሆይ ከዘረኛዉ ፓለቲካቹ ጋር በፈጣሪ ስም አትላንቲክ ግቡ! ሞረሽ ወያኔ ቻዉ..ቻዉ

  6. weygud hwehat ena Oneg yegara telatachn yalutma yeamhara sreat ethiopiyanoch endeager tesebasbew yekomubetn ye ortodoks haymanotn new ye ethiopiya hzb yeabesha nguse negest mengst beshewa beakakamubet wekt bezer tesebasbew zari zer eyatefachu be 21Naw kfle zemen ager lementek yasebachubet sistem alneberem ye ethiopiya bhireseboch debubum msrakum merabunm seminunm be ortodoks haymanot eyawahadu ager akumew enditenakeru ager yetemeseretebet enji maferaresha sreat alneberem bezer amhara stesebasbo oromon alchefechefem yekll atr alneberem bzu eyawreachu new edmi leweyani blachu beterefe ethiopiya beabesha nguse negest sreat ende ager bealem yemttawek ager neberech ahunm ttawekalech yemejemeriya muslim sdeteNochn yetekebele yeabesha krstiyan ngus ethiopiya endehonech alem ymesekral slezih yh ye ethiopiyameseret slehone mechim bemnm teamr ltanekankut atchlum yezer lhikanoch alneberum awo ye ethiopiya yemejemeriya telat graN mahmed yhn zari yeamhara sreat yemtlutn yeshewa nguse negest sreat yeabeshan ngus katefahu ethiopiya ye eslam ager adergalew bemalet le graNmehamed wetader bemehon ye shewa amharanm hone bedebub bemerab bemsrak wedesemin eyale krstiyanun ena abyate bitekrstiyanun eyefeje bezemenu lemetekem ager lemewrer endtchlu yaderegachu krstiyan nefteNoch amharam belut yetekerut endezariw agerachewn ena mannetachewn lemasmeles lemejemeriya gzi neft anstew graN mahmesdn dl argew ethiopiyan wedeneberechbet eyemelesu begraN yewedemewn ager bemakakam yeneberechwn ethiopiya bememelesachew zari enate lk ager tekemtachu ende tewererachu ena mililik ethiopiyawi endthonu krstnan endtkebelu aderegn bemalet beri welede tarik aeamhara sreat chanebn melese stlu atafrum wey tadiya ager bezer kemekefafel gar mn agenaNew ? oromo sisefr amhara alneberem wey? lilaw mahbereseb? slezih ethiopiya mannetan lezelalem astebka yenorech ager ahunm mannetan astebka tnoralech ye ethiopiya telatoch yezemenu bezer ena behaymanot kefaflew ager lemekemat mannetn lemasatat yekomu yezer lhikanoch ena weyaniwoch nachew

  7. የተከበራችሁት እድምተኞ የወያኔው ኢንሣ አሁን በደረሠን መረጃ መሠረት mereja.com/amharic ብሎክ መደረጉን በ አ.አ ያሉ ተከታታዬቻችን ነግረውናል እናም ነፃ የVPN አገልግሎት ዳውን ሎድ አድርጋችሁ እንድትጠቀሙ ሞያዊ እገዛዬን ለግሣለሁ።

    ወያኔ የመረጃ ፍሠቱን ይህዝብ ነውጡን ማቆም አይችልም!!!

    ሞት ለወያኔ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*