በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ እስሩ እና በዋስትና ስም ዘረፋው ቀጥሏል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)'s photo.

በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ እስሩ እና በዋስትና ስም ዘረፋው ቀጥሏል::በአዳማ ከተማ የግራፊቲ ፅሁፍ ፅፋቹሃል በሚል ምክንያት የታሰሩት ስድስቱ ታዳጊ ሙስሊሞች ባጠቃላይ በ90ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ::በዛሬው ዕለትም እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች አዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን እያንዳንዳቸው በ10ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ እንደወሰነላቸው ታውቋል፡፡ከታዳጊዎቹ መካከል አብዱልሃኪም ቃሲም የተባለው ወጣት ላይ ተጨማሪ ክስ የቀረበበት በመሆኑ ለሁለተኛው ክስ 30ሺህ ብር ዋስ ባጠቃላይ 40ሺህ ብር በሁለቱም ክሶቹ እንዲያሲዝ እንደተጠየቀ ታውቋል፡፡

1 Comment on “በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ እስሩ እና በዋስትና ስም ዘረፋው ቀጥሏል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)”

  1. የወያኔ የዝርፊያ ጥበብ አጃኢብ ነው።

    “ሠዶ ማሣደድ ካሠብክ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ”

    ይቅርታ ምኒሊክ ይህን ምሣሌ በማንሣቴ ተባረክ ልጃችን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*